Wednesday, October 30, 2019

ጉድ ስማ ሙሽሮቹ ከነ አጃቢና ሚዜወቻቸው ታስረዋል (Ethio Semay)`


· 
· 
ጉድ ስማ ሙሽሮቹ ከነ አጃቢና ሚዜወቻቸው ታስረዋል
Posted on Sofanit Love Asamnew facebook (source Zemedkun Bekele)
Ethio Semay

የፋሺስቱ የአፓርታይድ አብይ አሕመድ  የኦሮሞ መንግሥት  ዱርየ (ጌስታፖ )ወታደሮች  ዜጎች በሠርጋቸው ዕለት ሓዘን እንዲለብሱ አድርጎአቸዋል። ናዚው አብይ በጊዜው ካለስቆምነው ሌላ ጉድ ያሳየናል! ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ
ሌሎች ዘግናኝ የግድያ ታሪኮች ሳሰናድ ስላመሸሁ የነገ ሰው ይበለን። በግድ ስላሰለሟቸው ክርስቲያኖች፣ ሀገር ለቀው ስላስወጧቸው ዐማሮች፣ በገጀራ ስለከተፉት ህጻን፣ የገደሏቸውን ዜጎች ዕጣ ተጣጥለው ስለወሰዷቸው ቤቶች እሱን ሳወራ ነው ያመሸሁት። በመሃል ይሄ መጣ። በሉ እያነበባችሁ ስለ ራሳችሁ አስቡ። ጮሆ መሳቅ ሊያሳስር ይችላል። አዳሜ ይሄን እወቅ ።
ፎቶው ሙሽራውና ሙሽሪት ዘብጥያ ገብተው የተነሳ ፎቶ ነው።
•••
ሰርጋቸው ከትናንት ወዲያ እሁድ ዕለት ነበር። ዛሬ ማክሰኞ ደግሞ ያው እንደተለመደው በሀገሩ ወግና በባህሉ መሰረት የሙሽሪት ቤተ ሰቦች መልስ የሚጠሩበት ዕለት ነው። ይህ ቀን በሙሽሪት ቤተሰቦች ዘንድ ታላቅ የደስታ ቀን መሆኑ ይታወቃል።
•••
ቦታው አዲስ አበባ ጀሞ ቁጥር 3 ነው። ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መጥተዋል። ወዳጅ ዘመድ ቦታ ቦታውን ይዟል። መጠጡም፣ ምግቡም በየዓይነቱ በመልክ በመልኩ መዘጋጀቱም ተነግሯል።
•••
የሚጠበቁት ሙሽሮች መጡ። አቧራው ጨሰ ተዘፈነ። እልልታ፣ ጭፈራም ሆነ። ከበሮው ተመታ፣ እልልታው ጭፈራው ደራ። በመሃል የሙሽሪትና የሙሽራውን ደስታ ልዩና የሚታወስ ለማድረግ ሲባል የመልስ ጥሪው ላይ ርችት ተተኮሰ። ድብልቅልቅ ያለ ደስታም ሆነ። አበቃ።
•••
ቆይቶ ፎሊስ ነፍሴ ከተፍ አለ። ዓይናቸው ደም ለብሶ አራስ ነብር መስለው ነው የመጡት አሉ። ይቆጣሉ። ማነው ሙሽራው? ማነው ሙሽሪት? ጠየቁ። ተነገራቸው። አንዴ ይፈለጋሉ ያናግሩን አሉ። ሰው ግራ ተጋባ። ለምን ብለው ቢጠይቋቸውም አሻፈረን አሉ። ሙሽሪትና ሙሽራው ጉዳዩ ተነግሯቸው ከአዳራሹ ወጥተው ፖሊሶቹን አናገሯቸው።
•••
ወደ ፎሊስ ጣቢያ ቀጥሉ አሏቸው ፎሊስ ነፍሴ። ደነገጡ ሙሽሮች። ለምን? ጠየቁ ሙሽሮች። ቀጥሉ ቀጥሉ። ተቆጡ ፖሊሶቹ። ሁሉም ደነገጡ። ቢባል ቢሠሩ ትእዛዝ ትእዛዝ ነው ቀጥሉ ተባሉ። ግራ የገባው ነገር። ሚዜዎቹም ጠየቁ ለምን ይሄዳሉ? ፎሊስ ነፍሴ እናንተም ቀጥሉ።
•••
እልህ ቁጣቸው ሲታይ ነገሩ ወደ ሌላ የከፋ ነገር ሊሄድ ስለሆነ ሽማግሌዎች መሃል ገብተው፣ ስለ ሙሽራ ክብር፣ ቢያስረዱም ኧረ እነሱ እቴ ቀጥሉ ብቻ ነው። ሙሽሮቹ ከነ ሚዜዎቹ ወደ ጣቢያ ሄዱ። ሰርጉ በአንዴ ሀዘን ቤት ሆነ።
•••
የክሳቸው ምክንያት ወንጀላቸው ተነገራቸው። ወንጀሉም ርችት ተኩሳቹሃል አሏቸው። ታዲያ እኛ ምን አገባን። እኛ እንግዶች ነን፣ መልስ ተጠርተን ነው የመጣነው ቢሉ ማን ሰምቷቸው። በዚህ ተልካሻ ሰበብ ምክንያት በህይወታቸው አንድ ጊዜ ብቻ የሚገጥማቸውን የደስታ ምሽት ተረኞቹ ነጠቋቸው።
•••
ሙሽሮቹ ከምሽቱ 2 : 00 ጀምሮ ታስረዋል። 2 እህታማቾች ሙሽራውና 2 ሴት ሚዜዎች ከአጃቢዎች ጋር ታስረዋል። ደጋሹ አቶ ፍጹምም ታስረዋል። ለሽምግልና ጣቢያ የሄዱትንም በሙሉ አስረዋቸዋል። የጣቢያው ኃላፊ ከበላይ በመጣ ትእዛዝ ስለሆነ እዚሁ ነው የምታድሩት መባላቸውን የታሳሪዎቹ ቤተ ሰቦች ይናገራሉ። ነገርየው ደስ አይልም ነው የሚሉኝ የሰርጉ ተጋባዥ የመረጃ ምንጮቼ።
••• ይንጋና ደግሞ ጠዋት የሚሆነውን አብሮ ማየት ነው።
••• አፓርታይድ ኢዝ ካሚንግ አለ ማንዴላ ነፍሱን ይማረውና !!
ሻሎም ! ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ጥቅምት 19/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።






Tuesday, October 29, 2019

የጃዋር ኑሮና ተግባሩ ነፃነት ዘለቀ Posted on Ethio Semay)


የጃዋር ኑሮና ተግባሩ
ነፃነት ዘለቀ (netsanetz28@gmail.com)
Posted on Ethio Semay)
ሰው በወደደው ይቆርባልና በጃዋር ፍቅር ያበዱ ቄሮዎችና ድጋፍ ሰጪ ፖለቲከኞች  እነሱ ብቻ  በሚያውቁት እኛ ግን ከግምት ባለፈ ብዙም በማንረዳው ምክንያት በዚህ የሰይጣን ቁራጭ ጫማ ሥር ተንበርክከው ከርሱ ተርፎ  የሚጣልላቸውን ፍርፋሪ እየለቀሙ ለርሱ ቅን ታዛዥ መሆንን መርጠዋል፤ ነገንና ከነገ ወዲያንም ከነመፈጠራቸው ረስተዋል፡፡ ይህ ጉዞ እስከየት እንደሚወስዳቸው ከአንድዬ በስተቀር እኛም እነሱም አናውቅም፡፡ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ጃዋር እያዘዛቸው እነሱ እየታዘዙ በተለይ ኦርቶዶክስንና ኢትዮጵያን ከያሉበት ድምጥማጣቸውን ማጥፋታቸውን ካለአንዳች መሰልቸት ተያይዘውታል፡፡ እየሸሸ ያለ ዐውሬ ወደኋላው ሲመለስ ሊከሰት የሚችለውን ትዕይንትም የዘነጉ ይመስላሉ፡፡ የፈሪ ዱላ አይጣል ነው ወገኖቼ፡፡ እንደፈሪ ደግሞ  ባለም ላይ ጨካኝ የለም፡፡

1.     የቄሮዎችንና የጃዋርን የግል ኑሮ ስመለከት ልዩነቱ የሰማይና የምድርን ለማለት እንኳን ይከብደኛል፡፡ እንደሰማሁትና ከአንደበቱም “እኔም አቢይም በቪ 8 እንሄዳለን...” እያለ ራሱን በጠ/ሚኒስትር ደረጃ ከተቀመጠ ሰው ጋር ሲያወዳድር እንደሰማሁት ኑሮው እጅግ ቅንጡና ያሉት መኪኖችም ጥይት የማይበሳቸው፣ በ20 ሚሊዮኖች የሚገመቱና ሁሉም ነገር የተሟላላቸው ናቸው፡፡ ይህን ሁሉ ገንዘብ አንዳችም ነገር ሳይሠራ ከየት ሊያገኝ እንደሚችል ማናችንም ከግምት ባለፈ እንረዳለን፡፡ ሌሎች አክቲቪስቶች ደህና ጫማ እንኳን ሳይኖራቸው በነተበ ሸሚዝና ባረጀ ኮት በእግራቸው ሲንከራተቱ ይህ ለኑሮውም ሆነ ለሚያራምደው የሩዋንዳው ሚለ ኮሊንስ ዓይነት ሚዲያ አንድም ዕርዳታ ከማንም ሳይጠይቅ ይህን ሁሉ ገንዘብ ለጥፋት ሲያፈስ የሚጠይቀው የመንግሥት አካልም ሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት አለመኖሩ የጃዋርን ተልእኮ ዕንቆቅልሽ በእጅጉ ያጦዘዋል፡፡ እርሱ በቀጥታና በጀሌዎቹ አማካይነት እያዘዛቸው ሕዝብንና ሀገርን በደቦ እያረዱ ያሉ ምሥኪን ዜጎች ግን ከጭፍን ታዛዥነትና ከድንቁርና በስተቀር ምንም ሀብት የሌላቸው በመጨረሻ ለከፍተኛ ጉዳት የሚዳረጉ ዜጎች ናቸው፡፡ የርሱን ኑሮና የነሱን ድህነት ሳስተያይ የታዘዘብን መቅሰፍት ከሰው ሳይሆን ከላይ ከፈጣሪ መሆኑ ይሰማኛል፡፡ እንጸልይ!

2.    አያቶላ ጃዋር መሀመድ በቅርብ ከአሜሪካ መልስ በ60 ሚሊዮን ብር ቦሌ ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ የግል መኖሪያ ቤት ገዝቷል፡፡ ይህም የከተማው ወሬ ከሆነ ሰነበተ፡፡ ይታያችሁ - የትኛው አክቲቪስት ነው በዚህ መልክ እየተንቀባረረ በዚያ ላይ ንጹሓን ዜጎችን በማስገደል በዜጎች መሪር ሀዘንና በሀገር መፍረስ ከጌቶቹና ከጌቶቹ ጭፍሮች እየተሸለመ የሚኖር?

3.    ጃዋር በዚህን ሁሉ ዐረመኔያዊ ተግባሩ መያዝና ለፍርድ መቅረብ ሲገባው በመንግሥትና በክልል መንግሥት ጥበቃ ሥር ሆኖ የግፍ ግፍ የሕዝብንና የሀገርን ጥሪት እየተቀራመተ ነው - ላኪዎቹ የበጀቱለት በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠረው ዶላር አንሶት መሆኑ ነው፡፡ ለሚያደርሰው ጭፍጨፋ ድጋፍ የሚያደርጉለት በጥላቻ ፖለቲካ የተመረዙ የሱ ቢጤ ደናቁርት “ወንድማችን ጃዋር በመንግሥት ጥበቃ እየተደረገለት ስለሆነ አይዟችሁ፤ ማንም ዝምቡን እንኳን እሽ አይለውም...” በማለት ይህን   ቀንዱ ሀገር ውስጥ ጭራው ግን ውጪ ሀገር ያለ ታላቅ ክፍለ ዘመናዊ ሀገርን የማውደም ዘመቻ በማጧጧፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

4.    ጃዋር ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው ተሰሚነቱም ሆነ ሀገርን በመሸጥ ያካበተው ገንዘብ ወደር አይገኝለትም፡፡ ነገር ግን ለተንኮል ሥራው ከሚያውለው ገንዘብ ውጪ ለልማትና ለበጎ አድራጎት ጉዳይ አንዲትም ሣንቲም - ለማስመሰል እንኳን - ሲያወጣ አይታይም - ለነገሩ ሰይጣንን በበጎ ሥራ ተሠማርቶ ለማየት መከጀል ከእባብ ዕንቁላል የዕርግብ ጫጩት እንደመጠበቅ ያለ ጅልነት ነው - ከመነሻው፡፡ እነቢኒያምን - የመቄዶንያውን መሥራች - ተመልከቱ፡፡ የክብር ዶ/ር አበበች ጎበናን ተመልከቱ፡፡ እነሙዳይን ተመልከቱ፡፡ ... መንገዶች በመኪናና በሰው ተሞልተው ተዘጋግተውና ተጨናንቀው ሳይ፣ ድሆች የሚቀምሱትና የሚጠለሉበት አጥተው በየመንገዱ ወድቀው ሳይ፣ የድሆች ሠፈሮች ሽንት ቤት አጥተው ቆሽሸውና ተበለሻሽተው ሳይ፣ ሕጻናት የሚያስተምራቸው አጥተው ከትምህርት ገበታ ተለይተው በየመንገዱ ሲያድሩና ሲንገላወዱ ሳይ፣ አእሩግ በየመንገዱ ሲለምኑ ሳይ፣ ሕዝባችን በርሀብና በውኃ ጥም፣ በድንቁርናና በርዛት ሲሰቃይ ሳይ፣ ... ብዙ መልካም ያልሆኑ የድህነት ገጽታዎቻችንን ስታዘብ ትዝ ከሚሉኝ አንዱ ጃዋር መሀመድ ነው፡፡ የጃዋር በጎ አድራጎት ባፍንጫችን ይውጣ፡፡ ግን “በዚህ ሁሉ ተደራራቢ ችግራችን ላይ እግዜሩስ እንዴት ቢጠላን ይሆን ይህን ጭራቅ ያዘዘብን?” ብዬ እርሱንም አማርራለሁ፤ እርግጥ ነው ከሌላው ዓለም ስለመለየታችን አላውቅም እንጂ ፈጣሪን የሚያስቀይም ብዙ ዕኩይ ተግባር እንዳለብንም አስባለሁ፡፡ ቅጣታችን ግን ከሌሎችም ዕጥፍ ድርብ እንደሚሆን እገምታለሁ፡፡ እንደኛ የተቀጣና የሚቀጣ አለ ብዬ አላምንም፡፡

5.    ጃዋር የኦሮሞ ደም እንደሌለበት በቅርቡ መረጃ ወጥቷል፡፡ እንደጊዜው ፖለቲካ ወደታች ዘቅጠን በደም መክሊት እናስብ ብንል ጃዋር በቋንቋው ብቻ ከሚገናኘው ኦሮሞ ይልቅ በእናቱ በኩል እንደሚገናኝ ለሚነገርለት ለአማራው ይጠጋል፡፡ የዝርያ ቆጠራ ደግሞ በሀገራችን ይበልጡኑ በአባት ስለሚሄድ ይህ ሰው ከኢትዮጵያ ይልቅ ለየመን ይቀርባል፡፡ ስለሆነም የመንን ያፈራረሰ ደም ኢትዮጵያንም ለማፈራረስ ሁኔታዎች ከውጭም ከውስጥም እየተመቻቹለት ነው ማለት ነው፡፡ ዕንቆቅልሽ፡፡

6.   በጥቅሉ ሲታይ ይህን መሰሉ ሰው ከየትም የዘር ሐረግ ቢመጣ ለማስመሰል ካልሆነ በስተቀር ሃይማኖትም ሆነ ባህል፣ ወግና ሥርዓትም ሆነ የሞራል ዕሤቶች ... የሉትም፡፡ የሚታዘዘው ለኅሊናው ሳይሆን ቁሣዊ ድህነትን ከማሸነፍ ረገድ ከየትም ለሚገኝ ገንዘብ ነው፡፡ ተልእኮው የእናቱን ወይም የልጆቹን አንገት ማስቀላት ቢሆንም እንኳን ከመታዘዝ ወደኋላ አይልም፡፡ የሚያናድደውና እጅጉን የሚደንቀው ግን ለዚህ ዓይነቱ የወረደ ስብዕና የሚታዘዝ ሰው መገኘቱ ነው - ሊያውም ዕልፍ አእላፍ ሠራዊተ መንጋ፡፡ (Posted on Ethio Semay)

Sunday, October 27, 2019

ለጠ/ሚኒስትሩ አድርሱልኝ... ግርማ በላይ (Ethio Semay) 10/27/2019


ለጠ/ሚኒስትሩ አድርሱልኝ...
ግርማ በላይ (Ethio Semay) 10/27/2019
Abiy Ahmed the thuggish Hutu look a like leader of the Oromo in Ethiopia. He is a treacherous thug and a clear danger to Ethiopia.

         ለየትኛው ጠ/ሚኒስትር እንደማልባል ተስፋ አለኝ - ለዶ/ር አቢይ አህመድ ማለቴ ነው፡፡ ሀገራችንን እየመራ ያለው የአጋንንት መንጋ ተቆጥሮ ስለማይዘለቅ ለማን እንደጻፍኩ ግልጥ ይሆን ዘንድ ነው ይህንን ማለቴ፡፡

ዶ/ር አቢይን በአካል ባገኘው ብዙ የምጠይቀው ጥያቄ ነበረኝ፡፡ የተወሰኑትን እዚህ ልጠይቅ፤ የሚሰማኝንም ልንገረው፡፡

-      ወደ ውጭ ሀገር በተጓዘ ቁጥር ሀገር ውስጥ ችግር የሚፈጠረው ለምንድን ነው? ይህ ነገር በዕቅድና በተሰናሰለ ጥናት ይደረግ ይሆን? እዚህ እያለ ለምን አይሆንም - መሆን ካለበት፡፡

-      የፖለቲካ ዱላው ከዘር መርጦ አማራን፣
-       ከሃይማኖት መርጦ ኦርቶዶክስን፣
-      ከዕድሜ መርጦ ትልልቆችን፣
-       ከባህል መርጦ የጋራ ዕሤቶችን፣
-       ከዓርማ መርጦ አረንጓዴ ቢጫና ቀይን....
-      በተለዬ ሁኔታ የሚያጠቃው ለምንድን ነው?
-       
-      ይህንንስ አካሄድ አቢይ አያውቅም ወይ? ካወቀስ ዝምታውና “ትግስቱ” ገደብ ያጣው ለምን ይሆን? የብዙ ስብዕናዎች ባለቤት የሆነው ዶ/ር አቢይ ከገባበት የተዘበራረቀ ሁኔታ በአፋጣኝ ካልወጣ ተያይዘን እንጠፋለን - ትንሣኤያችን ባይቀርም ብዙ ሊያለፋን ይችላል፡፡
-       
-       
-      ጠ/ሚኒስትሩ ጃዋር ምን እየሠራና እያሠራ እንደሆነ ጠንቅቆ የሚያውቅ ይመስለኛል፡፡ እርሱ በአደባባይ እንዲህ አገር ምድር እያነደደ ምንም ሳይሆንና እንዲያውም ጥበቃ እየተደረገለት ሳለ የአማራን መብት ለማስከበር በሚል የሚንቀሳቀሱ ደካማና አቅመ ቢስ አክቲቪስቶችንና በወፌ ቆመች ደረጃ የሚገኙ ፖለቲከኞችን በሻማና በኩራዝ እየፈለገ ወደ ዘብጥያ ማውረድ ምን ዓይነት ካርማዊ ጽላሎት በራሱ ላይ ሊያከማችና መጨረሻውን ሊያበላሽ እንደሚችል አቢይ አያውቅምን? በሀገር ደረጃ ህግና ፍትህ ርትዕ ቢኖሩ ኖሮ ክርስቲያን ታደለ “የአማራ ወጣት መደራጀትና መብቱን ማስከበር አለበት” በማለቱ ብቻ በሀሰት በተቀነባበረ የክስ መዝገብ ለእሥር ከተዳረገ “ጠ/ሚኒትስሩ ካላነጋገረን ሀገርን ድምጥማጧን እናጠፋለን፡፡ በአካባቢያችን ክርስቲያን አንገቱን ቀና ቢያደርግ በሜጫ እንቆርጠዋለን፤ ሽማግሌ ልከንም ቢሆን የኢትዮጵያ ገዳዮች ጋር ታርቀን ይህን ለውጥ እንቀለብሳለን፣....”” የሚል አፄ በጉልበቱ መሀል አዲስ አበባ ላይ በመንግሥት በጀት ሲፏልል ቢገኝ ምን ይደርስበት ነበር? (የዚህን ታሪካዊ ዕንቆቅልሽና ምፀት አጸፋ ለመቀበል አቢይና ቡድኑ ዝግጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ምንም ዕዳ ሳይከፈል አይቀርምና! ከምላሤ ፀጉር ይነቀል በቅርብ ይከፈላሉ፡፡ ደምና ዕንባ በዝቷላ! ፈጣሪ ደግሞ ፍጡራኑን መቼም ቢሆን አይረሳም፡፡)

-      ጠ/ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን ከሚያጠፉ የውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነት እንዳለው ወይም እንደሌለው እንደምን ማመን ይቻላል? በሌሎች ላይ በግልጽ እንደምናየው በርሱም ላይ የግብፅና የዐረቦች ጥላ እንዳጠላ ወይ እንዳላጠላ እንዴት እንወቅ? (ለነገሩ ብናውቅ ባናውቅስ ምን ማድረግ እንችላለን! እርግማኑ ካልከሸፈ ዐይናቸውን እንዳልገለጡ ቡችሎች ነን፡፡)

-       
-      በናዝሬትና በደብረ ዘይት ዜጎች በዘራቸውና በእምነታቸው ምክንያት ሲገደሉ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ገዳዮቻቸውን ሊያባርሩ ሲነሱ መንግሥትና የፀጥታ ተቋሙ ተባብሮ ከቄሮዎች ጋር በመቆም ንጹሑን ዜጋ ለምን  ያጠቃል? ይህንን የግፍ ግፍ አቢይ አያውቅም ወይ? ካወቀ እንዴት አስቻለው? የታሪክ ተወቃሽነትን እንዴት ሊችለው ነው?  ይህ ዓይነቱ ፍርደ ገምድልነት እርሱን ከመሰለ የዕውቀት ጌታ ይጠበቃል ወይ?
-       
-       
-      አቢይ የሚሾማቸው ሁሉ በግድ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መሆን አለባቸው ወይ? ይህች አገር የሁሉም አይደለችምን? እንኳንስ ባለሃይማኖቱ ሃይማኖት የለሹስ የዚህች ሀገር ዕጣ ፋንታ ይመለከተው የለምን? ዘርና ሃይማኖት ተመርኩዞ የሰው ግርድና አመሳሶ ማውጣት የኋላ ኋላ አጥፊ ነው፡፡ ትምህርትንና ችሎታን ወደ ጎን ትቶ በሌላ ሌላ ማዳላት ትርፉ ኪሣራ ነው፡፡
            

በመጨረሻ አንድ መሠረታዊ ነገር ልጠቁም፡፡ በሌሎች ሀገራት እንደምንታዘበው በሀገር ውስጥ አንድ ችግር ሲፈጠር ለሥራ ወደ ውጭ የሚሄድ መሪ ጉዞውን ይሰርዛል ወይም ለሌላ ጊዜ ያዛውራል፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ ጉዞውን ጀምሮ ከሆነም አቋርጦ ወዳገሩ ይመለሳል እንጂ በመጣ ይምጣና በትዕቢት ወይም “‹ለሥልጣኑ ፈርቶ ነው የተመለሰው› ይሉኛል” በሚል የአሉቧልተኞች አቃቂር ተሸንፎ በዚያው ቀልጦ አይቀርም፡፡ ቤቱ እየተቃጠለ ሽርሽር የሚያምረው አባውራ ካለ አባውራነቱ ባፍንጫ ይውጣ፤ ትልቅ ነውር ነው፡፡ የድሆች ነፍስ ከሀብታሞች ቁጥር የማይገልጸው ዶላር የበለጠ ይመዝናል - ይህን እውነት ብዙ ነገር እንደሚያውቅ ለምገምተው አቢይ መንገር አይገባኝም ነበር፡፡ ስለሆነም በሰሞኑ የዜጎች ግድያና የንብረት ውድመት ጠ/ሚኒስትሩ በዚያው ሸፍቶ ከርቀት መከታተልን መምረጡ የሚጠቁመው ብዙ ነገር ቢሆንም ለተራ ታዛቢ ግን ወሰን አልባ ግዴለሽነቱን ነው - አቢይ ደግሞ ለሰዎች ሕይወት ግዴለሽ ነው ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ይመስለኛል - ይህ ጠባዩ ዕንቆቅልሽ ነው የሆነብኝ - ሌላው ቀርቶ ባለበት ሀገርም ሆኖ (የሀዘን) መግለጫ አልሰጠም - ሰጥቶም ከሆነ ይቅርታ፡፡ የራስ መተማመን ገደቡን ሲያልፍ ለከፍተኛ ትዝብት እንደሚዳርግ ጠ/ሚኒስትሩ ሊገነዘብ ይገባል፡፡ “ማንን ይዞ ጉዞ” ይባላል፡፡

በተረፈ የጃዋር ጉዳይ በፈጣሪም እጅ የተያዘ ስለሆነ ወደዚያ ገብቼ አልዳክርም፡፡ ሀገራችንን ይቅናት፡፡ ከተደገሰላት ዕልቂትም በፍጥነት ይታደጋት፡፡

Saturday, October 26, 2019

የመደመር መጽሐፍ ምረቃ - የዘገምተኞችና አድር ባዮች ጭብጨባ በሚሌኒየም አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ) Ethio Semay


የመደመር መጽሐፍ ምረቃ - የዘገምተኞችና አድር ባዮች ጭብጨባ በሚሌኒየም
አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ) Ethio Semay
በዛሬዋ ዕለት - ጥቅምት 8 ቀን 2012ዓ.ም - የዶ/ር ዐቢይ መጽሐፍ ተመርቋል፡፡ እኔም ከዚያ በተያያዘ ራሴን ታምሜ ዋልኩ - አሁን ድረስ፡፡ የነበረኝ የEmotional Quotient አንጻራዊ የተሻለ ደረጃ ወርዶብኝ ራሴው ስቸገርና ሰዎችንም ሳስቸግር አመሸሁ፡፡ የሚገነዘብህ ሰው ሲጠፋ ራስህን ያምሃል፤ ሲያምህ ሁሉም ነገር ያስጠላሃል፡፡

“እውነት እንደፀሐይ ናት፤ ፊት ለፊት በባዶ ዐይኖች አትታይም” ይላል ናማያራ የተባለ ህንዳዊ ደራሲ በአንዲት አጭር ልቦለድ ትረካው፡፡ በጣም እውነት ነው፡፡ የኔ ነው የምትለውን እውነት ይዘህ ግትር ከላክና የሚቃወምህ እንጂ የሚደግፍህ ካጣህ በርግጥም በቃላት ልትገልጸው የሚቸግርህ ህመም ጭንቅላትህን ሰንጎ ይይዝህና ትሰቃያለህ፡፡

ባመሸሁበት ሥፍራ ከማንም ሳልስማማ ተጣልቼ ወጣሁ - በሰው ቁስል እንጨት የሚሰደው ጭፍን ዜጋ እየበዛ ነው፡፡ አያቶላ ጃዋር እየቀጠቀጠ የሚገዛትን አገር ከቤተ መንግሥት ውጪ ተሰሚነት የሌለው ወይም በማወቅም ይሁን በሆነ ነገር ተገዶ አክራሪ ኦሮሞዎች እንዳሻቸው እንዲምነሸነሹበት ወዶና ፈቅዶ ሥልጣኑን ያስረከበው ዐቢይ እንደሚያስዳድራት የሚያምነው ነሆለል ዜጋ ብዙ ነው - በሰውዬው የቅፈላ ንግግር የሚማረከው የጣፋጭ ቃላት ምርኮኛ የትዬለሌ ሆነና ከአሳባጁ ሸርና ተንኮል ይልቅ የጣዖት አምላኪው ጅልነት ይበልጥ እያሳረረን ተቸግረናል፡፡ የታምራት ገለታንና የእሥራኤል ዳንሳን ተሞክሮና የአብዶ አጋንንታዊ ጥበብ ለዓመታት ቀስሞ የመጣው ዶ/ር ዐቢይ ለጊዜው አልተቻለም - በለስ ቀንቶት በምትሃታዊ ቱማታው ታላላቆችን ሳይቀር በእግሩ ሥር አውሏል -   ለነገሩ ትንቢትም ይደግፈዋል፡፡ ለማንኛውም የኔ መጣላት ትንሽ መጮህና ዝም ማለት ነው፡፡ ዝም ስል ጓደኞቼ መናደዴን ያውቃሉ - በሚነሱ ነገሮች አለመስማማቴን ጭምር፡፡ የአሁኒቷን ኢትዮጵያ እርግፍ አድርገው ካልተው አደጋ አለው!

በሚሊየኒየም አዳራሽ ዐቢይ “እኔ ዴሞክራት መሪ ስለሆንኩ ብቻየን የምወስነው ነገር የለም” ሲልና ጭብጨባው ሲቀልጥ የተሰብሳቢዎቹ ማንነት ገባኝ፡፡ በዚህ ንግግሩም ከንቱነቱን ከመግለጥ በስተቀር ሰውዬው እውነትን እንዳልተናገረ እረዳለሁና ፖለቲካ ምን ያህል ውሸታምና ከሃዲ እንደሚያደርግ ታወሰኝ፡፡ የሚገርመው ግን የርሱ ሀሰተኝነት ሳይሆን እዚያ የተኮለኮለው አጨብጫቢ የአእምሮ ዘገምተኛና አድር ባይ ነው፡፡ ዶ/ር ምሕረት ደበበን የመሰለ በጣም የማደንቀው ሰው ሳይቀር በዚያ የጨረባ ተዝካር፣ በዚያ የስብዕና ግንባታ የአምልኮት ሥነ ሥርዓት ላይ እንደሌሎች ዘገምተኞች የዚያ በተግባር የሚቀንስ በቲዎሪ ግን የሚደምር አርቲ ቡርቲ መጽሐፍ ዋና አድናቂ ሆኖ ሲገኝ በሰዎች ተፈጥሮ ተገረምኩ፡፡ በሀገራችን በተጨባጭ ምን እየተከናወነ እንዳለ የሚገባው ሰው በዚያ የቁጭ በሉ የሚሌኒየም ትርዒት ተገኝቶ ለነገ ሀፍረትና የኅሊና ትዝብት አይዳረግም - ኅሊና ላለው፡፡ እዚያ ለተገኙ ዜጎች በነሱ ምትክ እኔ አፈርኩ፡፡ አንዳች እርኩስ መንፈስ ቢያስገድዳቸው እንጂ በውዴታቸው እንደዚያ እጃቸው እስኪግል እንደማያጨበጭቡም ገመትኩ፡፡ ልብን ከሚሰብር ሀዘን ባለፈ ዶ/ር ዐቢይ በተለይ በዚህን ወቅት ምን የሚያስጨበጭብ ነገር አለውና! “ዐይን አይቶ ልብ ይፈርዳል” ይባላል፡፡ በፈርንጆች የሤራ ፖለቲካ የተገኘ ባዶ የኖቤል ሽልማትም ኃጢኣተኛ ሰው ንስሃውን ሳያወርድ በጉልበቱ ወስዶት ሣለ ነገር ግን በረሃ ላይ እያጣጣረ ለወደቀና የክርስቶስን ሥጋና ደም መቀበል እንዳይችል ከቤተ መቅደስ ለራቀ ሰው ከማይገባው በሥውር ተነጥቆ ለሚገባው እንደሚደርሰው ሥጋ ወደሙ የሚመሰል ነው፡፡ ስንቶች እየተገባቸው ሳያገኙ ዐረቦችን በተለይም ግብጽን ለማስደሰት ሲባል በኛ ይጫወታሉ፡፡

አፄ ኃይለ ሥላሤም ሆኑ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም የዚህን ሰውዬ ያህል አላጭበረበሩም፤ አጭበርብረውም በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ያህል አልተመለኩም፡፡ ሚሌኒየም አዳራሽ ውስጥ የተገኙና ሰውዬውን ሰማየ ሰማያት በመስቀል የሚለው ነገር ገና ሳይገባቸው ዐረፍተ ነገሩን በቅጡ ሳይጨርስ በቃላትና በሐረጋት ሳይቀር ያጨበጨቡ ኢትዮጵያውያን የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ የማያውቁ ደናቁርት ከመሆናቸውም በተጨማሪ የአእምሮ ችግር እንዳለባቸው ለመገንዘብ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡ ይህን እውነት በገሃድ የምመሰክረው የዛሬ ታሪካችን ተመዝገቦ የሚቀመጥ እንደመሆኑ በነፃነታችን ማግሥት - አንድዬ ለዚያ ካበቃኝ - አሁን እየሆኑ ያሉትን ፍጹም ተቃራኒ ኹነቶች በማነጻጸር ይሆናል፡፡ ከዚህ ዓይነቱ አምልኮ ካልወጣን ደግሞ መቼም ሰው አንሆንም፡፡

በርግጥ ሰውዬውም ጭብጨባ ይወዳል፡፡ እውነትም እንደሚባለው የናርሲዝም ተጠቂ ሳይሆን አይቀርም - ራስን ከልክ በላይ የማፍቀርና በሌሎች የመመለክ መጥፎ ልክፍት፡፡ ይህ ዓይነቱ በሽታ በነሂትለርና ሙሶሊኒም ታይቷል፡፡ ዐቢይ አያምንበትም እንጂ ቢያምንበት ኖሮ ወደ ዘብር ገብርኤል ሄዶ አንድ ሦስት ያህል ሰባቶችን ቢጠመቅ ከዚህ ሰይጣናዊ የእዩኝ እዩኝ የፎቶና ቪዲዮ ካሜራ ፍቅር ይፈወስ ነበር፡፡ ባናውቀው እንጂ መጥፎ በሽታ ነው፡፡

ምንም ቁም ነገር እንዳልተናገርኩ ይገባኛል፡፡ ቢሆንም ለምን ከዚህ በላይ ያልኩትን እንዳልኩ ሁሉንም በዝርዝር  ስለምታውቁት ማብራራት አይጠበቅብኝም፡፡ የሰውን አድርባይነትና አጨብጫቢነት እንዲሁም ለዚህ ያበቃውን የአእምሮ ዘገምተኝነት ከገለጥኩ በቂ ነው፡፡የኢትዮጵያን የወቅቱን ሁኔታ የሚረዳ በዚያ ልጭና ጎፈሬ ወይም ቂጥ  ከፍቶ ክንንብ ዓይነት ከእውነት የሚጣረስ ዝግጅት መናደዱ አይቀርም፡፡

ቢሆንም…. ቢሆንም… በጃዋርና በበቀለ ገርባ፣ በዶ/ር ገመቹና በሕዝቅኤል ጋቢሣ የሚመለመልና በኦህዲድ ሠልጥኖ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት አንድ ሐሙስ የቀረው አክራሪ ኦሮሞ በገነነባትና ከላይ እስከታች ሀገሪቱን በወረረበት ወቅት፤ አየር መንገድን፣ ባንክን፣ ትምህርት ሚኒስቴርን፣ ሌሎች የሚኒስቴርና የኮሚሽን መ/ቤቶችን፤ ማዘጋጃን፣ ክፍለ ከተማን፣ ወረዳን፣ ቀበሌን፣ ንግዱን፣ ፖለቲካውን፣ ሃይማኖቱን፣ መሬቱን፣ ኮንዶምንየሙን፣ኮንዶሙን፣… ሁሉንም ኦሮሞና የኦሮሞ የማድረጉ ኦነጋዊ ተግባር በተገባደደበት ወቅት ይህን መሰል የተጨፈኑ ላሞኛችሁ የመደመር ፖለቲካ የሰም ለበስ ቅኔ ሲመረቅ ማየት ደግ ነው - የሚገርመው ወያኔዎች በፈራ ተባ 27 ዓመታት የፈጀባቸውን ሁሉንም ወይም ቸርነትን በተላበሰ አገላለጽ አብዛኛውን ሥልጣንና የጥቅም ምንጭ በገዢው ጎሣና በሆድ አደር ተላላኪዎች የመጠቅለል አባዜ እነዚህኞቹ ንክሮች ገና ሁለት ዓመትም ሳይሞላቸው አጠናቀቁት - የኖቤል ሽልማቱ በዚህ ርዕስ ቢሆን ይልቁንስ አሣማኝ በሆነ - ይህን ዓይነት ርዕስ ካላቸው ሸላሚዎቹ፡፡ “ራሴን መትተው እግሬን ቢያኩኝ” አይገባኝም አለ ትግሬ - ዘርን መሠረት ባደረገ መልክ ምሥኪን ዜጎች ላይ የሚሠራው ግፍና በደል ሌላ - የሚመረቀው መጽሐፍ ሌላ፤ በሀፍረተቢስነትና ይሉኝታቢስነት ወያኔን የሚበልጥ እንደማይኖር ቀደም ሲል የወሰድኩት አቋም ፈተና የገጠመው ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ነው፡፡ “ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ” አሉ? አንዱ ፈላስፋ “ተማሪ ከአስተማሪው ካልበለጠ ምኑን አስተማረ?” ይል ነበር፡፡ የሕወሓት ተማሪዎች ኦህዲድና ኦነግ ፈጣሪያቸውንና መምህራቸውን በልበ-ሥውርነት አስከንድተውት ዐረፉ፡፡ “ወያኔ ማረኝ!” እንዳንል እፈራለሁ፡፡ አሸናፊው ጎልቶ እስኪወጣ ሀገራዊ የነጻነት ትግሉ በሦስት ቃላት ሊገለጽ በሚችል መልኩ የሚቀጥል ይመስለኛል፡- ብልጥነት፣ ሞኝነትና ብልኅነት፡፡

ላጨብጫቢዎቹም ለአስጨብጫቢዎቹም መልካም የጣዖት አምልኮት ዘመን ያድርግላቸው - ሲፈልጉ ከቢዮንሴ ቀጥለው 46ኛ ጽላት ያስቀርጹለትና ለሁለትም ለሦስትም ጌቶች የሚገዙ ዲያቆናትና ቀሣውስት ከሣሎናቸው ስለማያጡ ሠርክ ተስቀድሱለት፡፡ አንድዬ ይህን ሁሉ አፍዝ አደንግዝ እያዬ ግና ዝም አይልምና ሁሉም በቅርብ ዋጋውን እንደሚያገኝ አንጠራጠር፡፡ ቀልድ በዚህኛው እንጂ በዚያኛው የለም፡፡ ችግሩ ሞት ሲዘገይ የቀረ መምሰሉ፡፡ እንጂ ሌላውን ሁሉ ትተነው ምሥራቅ አፍሪቃን በፍርሀት ያምጰረጰረው መንጌ ዛሬ እርጅና ቤቱን ሠርቶበት የዝምብ መጫወቻ ሆኖ የለ? …. Ethio semay

Thursday, October 24, 2019

ይድረስ ግልጽ የቅሬታ ደብዳቤየ ለምወዳችሁ የልጅነት ጓዶቼ ሆይ ከጌታቸው ረዳ (Ethio seamy ኢትዮ ሰማይ)


ይድረስ ግልጽ የቅሬታ ደብዳቤየ ለምወዳችሁ የልጅነት ጓዶቼ ሆይ
ከጌታቸው ረዳ (Ethio seamy ኢትዮ ሰማይ)
Photo Getachew Reda (Ethio Semay)
ይህ የቅሬታ ደብዳቤ ይፋ እንድጽፍላችሁ ያስገደደኝ ሁኔታ አሁን ላለው እጅግ ጸረ ሕዝብ የሆነ ከፋፋይ፤ ፋሺስታዊ ፤ስርዓተ አልባዊ ወንጀለኛና የተንኮታኮተ መንግሥት (ፌይልድ ስቴት/A wrecked State) አብይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሞ የገዳ ሥርዓት (መደመር) አጭብጫቢዎች ሆናችሁ በሚያሳፍር ሁኔታ ስታሽቃብጡ ማየቴ ልቤ ስለሰበረው፤ ከናንተ ጋር ያለኝን ወንድማዊ እና አብሮ አደጋዊ ግንኙነቴ ከማቋረጤ በፊት ወደ ልባችሁ ተመልሳችሁ በዚህ ሥርዓት እየተጎዱ ያሉ ማሕበረሰቦች እና ግለሰቦች እምባ እንዲቆም የድረሱልን ጩኸታቸውን አብራችሁ ከኔው ጋር እንድታስተጋቢ ከሚል ነው።


ለ18 ወራት ያላቋረጠ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የመጣው የዜጎች ሞት፤ስጋት እያያችሁ ዛሬም ያንኑ የዜጎች እምባ ከምንም ባለመቁጠር የአንድ ግለሰብ ልዕልና ማሞገስና ማስበለጥ ከቀጠላችሁ ላንዴ እና ለመጨረሻ ወንድማዊ ግንኙነቴን የማቆም መሆኔን እንድታውቁልኝ ቅር እያለኝ ልግልጽላችሁ ተገድጃለሁ።  
  

እንደምታውቁት አገሬን ጥየ ለበርካታ አመታት ስደት ላይ በመኖር ወላጆቼን ሳልቀብር፤ ወንደም እህቶቼን  ዓይን ናፍቆት እያንገበገበኝ እና እነሱም ሌት ተቀን እያለቀሱ በናፍቆት ሳንተያይ አኔም ላለመመለስ የመቀጠሌ ምክንያት ባንዴም ሆነ በሌላ መልኩ በገንዘብ፤ ተዋጊነትና በፕሮፓጋንዳ  ያገለገላችሗቸው የወያነ ትግራይ መሪዎች፤ ዛሬ ደግሞ በምትካቸው ሌሎችን በማስገበር በጭካኔ የሚጓዝ በገዳ (መደመር) ሥርዓት ለማስፈን እየተሯሯጠ ያለው ሥልጣን የጨበጠው የኦሮሞዎች ስርዓት የፕሮፓጋንዳቸው አቀንቃኞች ሆናችሁ ለምታገለግሉት ሥርዓት ‘ከድጡ ወደ ማጡ’ ሆኖ ስላገኘሁት ወደ አገሬ መመለስ አልቻልኩም።


 አገሬ ሄጀ እንድጎበኝ እና አገሬ ሰላማዊ ዕንቅልፏን የምትተኛበት ሌሊትና ቀን ለማየት ስጓጓ ባልጠረጠርኳችሁ ሁኔታ “ዛሬም የዜጎች ደህንነት በባሰ መልኩ ወደ ስራ ሄደው የማይመለሱበት አስፈሪ የቀውስ ሰዓት” ሆኖ እያያችሁ፡ በወንጀል ለተጨማለቀው ለኦሕዴድ (አፒዲኦ) ድርጅት መሪው ለአብይ አሕመድ ድጋፍ በመስጠታችሁ ፤አገሬ እንዳትረጋጋና እኔም አገሬ እንዳላይ ተጨማሪ ብትር በመሆናችሁ ከዚህ አሳፋሪ ታሪክ እንድትታቀቡ ይህ ደብዳቤ ጽፌላችለሁ። በተለይም ለኔ ብላችሁ ሳይሆን ደም ለሚያለቅሰው ማሕበረሰባችን ብላችሁ ከዕብደታችሁ እንድትመለሱ ወንድማዊ ተግሳጽና ልመና አቀርብላችለሁ።


እንደምታውቁት አብረውኝ ያደጉ ብዙዎቹ ጓዶቼ (የራሴ ወንም እና ዘመዶቼም ጭምር) በተለያዩ ምክንያቶቻቸው አረመኔ ለሆነው ለፋሺስቱ ድርጅት “ለትሕነግ” (ለህዝባዊ ወየነ ሓርነት ትግራይ) አባል ሆነው ህይታቸው መስዋእት ያደረጉ አሉ (ወንድሜ ቆስሎ በህይወት ቢተርፍም) ። አንዳንዶቹም የታገሉለትን አራዊታዊው ‘የትግሬዎች ሥርዓት’ ሳያስተካክሉ “መከረኛውን ሕዝብ እንዲጋፈጠው ጥለውት ወደ ውጭ አገር መጥተው” “ጨቋኝ ድርጅት ነው ብለው የጣሉሉት ድርጅት ተመልሰው የድርጅቱ አጨብጫቢዎች እና የልብ አገልጋዮች ሆነው አይተናቸዋል”። ይህ ልብ ይሰብራል። በጣም ጥቂቶችም ዕድለኞች ሆነው ከተዋጊነት ወጥተው ግማሽ በግማሽ ወየኔን በመኮነንና በማሞገስ (በተለይ አረመኔውን መለስን በማሞገስ ረገድ) እስከመጨረሻ ድረስ ዘልቀው ሲጓዙ ቆይተው ዛሬ ደግሞ  በመጨረሻዋ ሰዓት (በ11ኛዋ  ሰዓት) የሥልጣን ጥመኛው ኦሮሞው ለኦፒዲኦ መሪ ለአብይ አሕመድ “ድምጽ ማጉያ” ሆነው፤ ሕዝብ ሲበደል ከመጤፍ ሳይቆጥሩ ዝምታቸውን እያስተጋቡ ነው። እንዲህ ያሉ ሰዎች  በታሪክ ታይተዋል። ስለሆነም ነው ታላቁ የጥቁር አፍሪካን አሜሪካን መሪው “ማርትን ሉተር” In the end we will remember not the words of our enemies but the silence of our friends (Martin Luther King Jr)
 የተፈጸመብን ጭካኔ ሳይሆን የምናስታውሰው የጓደኞቻችን ዝምታን እናስታውሳለን” (ማርቲን ሉተር ኪንግ ጆር) ሲል ታሪካዊ ትዝብቱን የዘገበው።

አብሮ አደጎቼ የሆናችሁ ወዳጆቼ ሆይ!

ለአገሬ ሕዝብና ፍቅር እንዴት እንደምንገበገብ ከልጅነቴ ጀምሮ የምታውቁኝ ጉዳይ ነው። ዛሬ ያንን ልተው አይቻለኝም። የኔን ቅሬታ ተገንዝባችሁ አብይ አሕመድ ለተባለው አገሪቷ ከድጡ ወደ ማጡ እየከተታት ያለው የሚሊዮኖች ህይወት ተጠያቂ ለሆነው ‘ጸረ አማራ በሆነ ተዋጊ ድርጅት ታጋይ ሆኖ ያደገ’፤ እንደጃዋር መሓመድ የናቱን ዘመዶች የሚያብጠለጥል “ጸረ አማራ” የሆነ ‘ወንጀለኛ ሰው’ ድጋፋችሁን እና አገልግሎታችሁ ላለመንፈግ ብላችሁ “ከዚህ ደብዳቤ በላ በወንጀል ለተጨማለቀው መሪያችሁ ለማጎብደድ ከወሰናችሁ የኔን አብሮ አደግነትና ወንድምነት ያለኝን ሰብኣዊ ጥብቅና “ስላጣጣላችሁት” እጅግ ሐዘን ተሰምቶኛል፡፡


ስለሆነም ቤተ እምነቶችን ዜገችን እና አገርን በገዛ ጓዶቹ የኦሮሞ አሸባሪዎች እየተናወጠች እያየ ‘ጀሮ ለማይሰጥ አልሰማሁ አላየሁ ለሚል” ፤ የደገፈውን ሕዝብ “የሚክድ” አሸባሪዎችን እና የጥላቻ መሪዎችን በዙሪያው እያስከተለ “ጥበቃ የሚያደርግላቸው” ይህ ከሓዲ የሆነ  “ይሁዳ” ስትደግፉ “የመደገፍ መብታችሁ ማክበር እንደሌለብኝ እያወቃችሁ” በጣም መበሳጨቴን እወቁልኝ።
አዎ እናንተ የቅርብ አብሮ አደጎቼም ሕዝባችን ሲያለቅስ ለአንድ “ግለሰብ የስብእና ቀረጻ/የግል አምልኮ” ስትሉ ሰምታችሁ አይታችሁ እንዳላያችሁ እልቂትን እያሳነሳችሁ፤ሞትን እስርን ስቃይን፤ዘረኝንትን እንዲሁም ሥርዓተ አልባነት እንዲቀጥል ተዋናዮች ሆናችል። ፌስ ቡክ ድረገጻችሁ ወደ ኢቲ ቪ እና ፋና ብሮድካስቲንግነት ተለውጣል።  የዘር ጭፍጨፋ /ጀነሳይድ/ በሚካሄድባት አገር “ኦርቶዶከስ ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰንደቃላማን” መሪዬ!!” ብምተሉት በራሱ በመሪያችሁ በአብይ አሕመድ “ወታደሮች ትዕዛዝ” በደል ሲደርስ አይታችሁ ዝም በማለታችሁ ማርትን ሉተር አሁንም  “አደገኛ ነገሮች ሲከናወኑ ላለመቃወም ዝም በምንልበት ቀን የህይወታችን ማለቂያ የመጀመሪያዋ ጉዞ ነች።(ማርቲን ሉተር ኪንግ) Our lives begin to end the day we become silent about things that matter,” ያለውን በናንተው አይተነዋል።

በመጨረሻም ስለቀበጣችሁለት የአብይ ኖብል ሽልማት ጉዳይ አንድ ልበል እና ልደምድም፡

ለአብይ ድጋፋችሁ የጦፈው በቅርቡ ኖብል ሽልማት በመሸለሙ ፍቅራችሁ ግሏል። ማወቅ ያለባችሁ፡ በብዙ መንገዶች ፣ የኖቤል ሽልማትን ለማግኘት ከመሪዎቹ አንዱ ለመሆን ፣ የአገሩን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ ግብዝ ሰው ቅድምያ ትኩረት ይደረግለታል። ሽልማቱ እንዲሰጠው ከእርሱ የሚፈለጉትን በሺዎች የሚቆጠሩ ነገሮችን መቀበል አለበት፡፡አንድ መሪ ግብረሰዶም የሚቃወም ከሆነ ለሽልማት አያበቃውም። አብይ የዚህ ኮድ አክባሪ ነው (ራሱ የመረጣት የከፍተኛ የአገራችን ዳኛም ብትሆን የዚህ ኮድ አክባሪ ነች) ፡ ይህ ከባድ “አገራዊ ጣጣ” በሕሊና ሚዛን ሲመዘን ማንም ብልህ ሰው አይቀበላቸውም፡፡ የሁኔታ መመዘኛዎች ቁልፎች/ ኮድን መቀበል ማሟላት አለበት። ተሸላሚው ‘በስልጣን ላይ ላሉት ወይም ገንዘብ ላላቸው ብቻ አሻንጉሊት ለመሆን ዝግጁነቱን ማሳየት ዝግጁ መሆን አለበት፡፡


አዎ ከዓለም ወንጀለኞች ጋር የጋራ ሴራ መጣጣም አለበት፡፡ እነሱ የኖብል ሽልማትን ወይም የተከበረ የክብር ዶክቶሬት ይሰጡታል ፣ ታዲያ እቅዶቻቸውን ፣ በአገሩና እና በአጎራባች ሀገሮች ውስጥ የሚያደርጉትን ማንኛውንም ግድ የለሽ ተግባር በመደገፍ (ሉዓላዊ ክብር ለማያገናዝብ ትብብር)‘ምላሽ በመስጠቱ’  በዓለም ታዋቂ ያደርገዋል፡፡ ለዚህም ነው አብሮ አደግ ጓዶቼም ለዚህ ፕሮፓጋንዳ ‘ታዋቂነት’ ተገዢ ሆናችሁ የኖብል ሽልማት ተሸላሚውን አብይን ከሚገባው በላይ “obssessed” ሆናችሁ “በተሰፈጠ የህዋሳት ስሜት” ገብታችሁ ለግለሰብ ልዕለና አምልኮት ተጋልጧችል (የሰከረ ሰው ስካሩ አያውቀውምና ለናንተ አይሰማችሁም)። የሚቀጥለው ተቀረው ጫዋታ በናንተ አድማቂነት ይወድቃል። መሪያችሁ የተከበረ ሽልማት ተቀባይ ነው ተብሎ በተነገረ ማግስት በተራው ሕዝብ መመረጥ ቀላል ይሆንለታል። የሽልማቱ ዋና ማጠንጠኛውም እዚህ ላይ ነው። ቀስቱ በናንተ ላይ ያነጣጠረ ነበር፤ በሚገርም ሁኔታ ዒላማው መትቷል። የማኪያቬሊው ተማሪ “አብይ አሕመድ” ከህጻንነቱ ጀምሮ የቋመጠለትን ንግሥና አገርም ሽጦም ቢሆን፡ በሬውን ሳሩን እያሳየ ወደ ገደል ከትቶትም ይሁን “የቃዠለትን ንግሥናውን” በናንተው እውን እየሆነለት ነው። አሳዛኙ የዘመናችን ትዕይንት! (ትራጀዲ) ይህ ነው። በስልክ ደውላችሁ እንድንነጋግርበት ጥሪ አቅርቤላችሁ አሁንም ምላሽ አልሰጣችሁም። ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ። ካልሆነ መልካም ዕድል ለናንተም ለመሪያቸሁም። እኛ ግን ከየእናት አገራችን ዕምባና እሮሮ ማድመጥ አንቦዝንም።ስለ እስዋ “ዝም አንልም”! ያለችን አንድ እናት፤ አንድ አገር፤ አንድ ሰንደቅ ነች! ስለ ክብርዋ እንቆማለን!
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay


Wednesday, October 23, 2019

የሸዋ ሕዝብ ድርጅት (ሸሕድ) Shoan People Organization (SPO) 23/10/19 (10/23/2019) (posted on Ethio semay)


የሸዋ  ሕዝብ  ድርጅት (ሸሕድ)
Shoan  People Organization (SPO)
23/10/19 (10/23/2019) (posted on Ethio semay)
Evidence of the Fascistic Oromo Cruelty in Ethiopia 2018 ፎቶ የአብይ አሕመድ ኦፒዲኦ እና የኦነግ የ27 አመት የጋራ የጥላቻ ቅስቀሳ ውጤት
ፎቶ የአብይ አሕመድ ኦፒዲኦ እና የኦነግ የ27 አመት የጋራ የጥላቻ ቅስቀሳ ውጤት
በኢትዩጵያ ባንቱስታን አፓርታይድ የጎሣ ፌደራሊዝም ክልል ተብዬ በረቶች ዉስጥ ከደቡብ እስከ ሰሜን፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ባሉት ሁሉም አካባቢ በአለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ እንኩዋ ከፍተኛ ቁጥረ ያለዉ ሕይወት ጠፍቷል፣ ንብረት ወድሟል። ሰላማዊ ኑሮ ታዉኮዋል፣ የሕግ የበላይነት ሞቶ ተቀብሯል። አዉራ ጎዳናዎች ተዘግተዉ ወደ አዲስ አበባና ከአዲስ አበባ የሚደረገዉ የሕዝብ ማመላለሽ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ተገቶ ተሳፋሪዎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል። የተረኛዉ የኮለኔል አቢይ አሕመድ ኦዴፓ/ኦነግ ጠቅላይ ሚኒስቴር መንግሥት ለፍፁም አርመኔ ቄሮ መንጋ ጀሌዎቹ ወግኖ እንበለ ሕግና ሥርዓት በአእዋሚ (ፓጋን) ወይም አሕዛብ ኢሬቻ በዓል ሽፋን የአዲስ አበባን ስምንት ሚሊዎን ነዋሪ ለሦስት ቀናት ያህል ሲያሸብሩ፣ ሲዘርፉ፣ ሴቶችንና አዛዉንቶችን ሲያጉላሉ አልፈው ተርፈዉም የኦዴፓ/ኦነግ የጋላ ብሔረተኞች ባንድነት ተባብረዉ የፈጠራ ዝባዝንኪ "ለመቶ ሃምሳ ዓመታት ተቇርጦ የነበረዉ ኢሬቻ ፊንፊኔ፣ ነፍጠኞች በሰበሩን በዚህ ቦታ ሰብረናቸዋል፣ ኦሮሞ ደስ ይበልህ" በማለት ጉጀሌዉ አባ ዱላ ሽመልስ ሲፎልል ተሰምቷል።


ሰላምና የሕግ የበላይነት በሌለበት፣ የጎሳ፣ የዘር ማጥፋትና ማጥዳት ከሩብ ምዕተ ዓመታት በላይ በሰፈነባት፣ ከሦስት ሚሊዎን በላይ ሕዝብ ተፈናቃይ በሆነባት፣ በሰዉ ሥራሽ ፖለቲካዊ አሻጥርና በቅጥረኛ ጥቂት ልሂቃን ዋና ምክንያት የዓለም የመጨረሽዋ አገር ለሆነችዉና የባንቱስታን አፓርታይድ የጎሣ ፖለቲካ ቀዳሚ ተዋናይ ለአቢይ አሕመድ አሊ የሰላም ኖብል ሽልማት መስጠት የጸረ ኢትዮጵያ ኃይላት የተቀነባበረ ሴራ ለመሆኑ አያጠራጥርም።


የኦዴፓ/ኦነግ መሪ አቢይ አሕመድ "ፊንፊኔ ኬኛ" ባይና የኦሮሚያ ልዩ ጥቅምን በአዲስ አበባ ላይ አስክብራለሁ ባይ ነዉ በባላደራዉ ምክር ቤት በነ እስክንድር ነጋ ላይ ጦርነት እግጥማለሁ ብሎ ያወጀዉና አባለቱን እነ ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩን፣ መርከብ ኃይሌን ወዘተረፈ እንበለ ሕግ ወህኒ ያወረዳቸዉ። የምዕራቡ ምንደኛ የሰላም ተሸላሚዉ ኮለኔል አበይ አሕመድ ነዉ በባሕርዳር ተገኝቶ ልዩ ቅልብ ጦሩን አዝምቶ እነ ጀነራል አሳመነዉ ጽጌንና ከአራት ሽህ በላይ ዐማሮችን ያስጨፈጨው። የሥልጣን ጥመኛዉና በከይሲዉ አቢይ አሕመድ የሚመራው ኦዴፓ/ኦነግ አይደለም እንዴ በመፈንቅለ መንግሥት የፈጠራ ድራማ ዐማሮችን በዘር ለይቶ ከጅማ፣ ከአዲስ አበባ ከናዝሬት፣ ከአምቦ፣ ከደብረ ዘይት፣ ከአሰላ፣ ከፍቼ፣ ወዘተረፈ በገፍ አፍሶ ያስራቸዉ?


ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ፣ ስብሰባ፣ የኢትዩጵያን ብሐራዊ ሰንድቅ ዓላማ አረንጏዴ፣ ብጫ ቀይ በመስቀል አደባባይ መያዝ በአቢይ አሕመድ መንግሥት ክልክል ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ ጋላ ቄሮዎች በፖሊስ ድጋፍ እየተደረግላቸው የባላደረዉን ስብስባ፣ ጋዜጣዊ መግልጫን ለማደናቀፍ ችለዋል።


አረመኔዉ አቢይ አሕመድ ከግብረ አበሩ የትሕነግ እና የኦዴፓ/ኦነግ መጋዣ አጋሰስ አዴፓ ተብዬው ጸረ ዐማራ ጋራ በመሆን የሚፈፅሙት ኢሰባዊ ድርጊት ተዘርዝሮ አያልቅም። የጀነራል አሳመነዉ ጽጌን ነፍሰጡር ባለቤት ወይዘሮ ደስታ አስፋዉን እንበለ ሕግ ወህኒ ቤት አስገብተዉ ስለአስቃዩዋት አስወርዳላች። ምዕራባዉያኑ ለአቢይ አሕመድ የሰላም ኖብል ሽልማት የሰጡት ለዚህ ዓይነት አረመኔያዊ ተግባሩና ኢትዩጵያን እንደ ዩጎዝላቢያ በቅርብ ጊዜ ከዓለም ካርታ እንድትጠፋና "ኦሮሚያ የገዳ ሪፑብሊክ" ምሥረታን ለማሳካት የታቀደ ሴራ ነዉ። መክሸፉ ግን አይቀርም።


በመሆኑም  ሸሕድ ወቅታዊዉን  ተጨባጭ ሁኔታ  አስመልክቶ  የሚከተለዉን  ያቁዋም  መግለጫ  አዉጥቷል።

1/ ሁሉም የሕሊና እስረኞች በአስቸኯይ ይፈቱ ።

2/ አዴፓ ተብይዉ ጉጀሌ ከምድረ ሸዋና አዲስ አበባ በፍጥነት ይባረር። አዴፓ ነዉ የሸዋን ግዛትና አዲስ አበባ ከተማን ለወራሪ መጤ ጋሎችና ለወያኔ ትግሬ አስረክቦ በዘዉትር አሽከርነት ባሕር ዳር ተወሽቆ ያማራን ሕዝብ ለሕልዉና አደጋ ያጋለጠው።

3/ አዴፓና ያማራ ብሔረተኛ ነንባይ አወናባጆችኛ እና ተሞዳሟጅ ሁሉ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በምሥራቅና ምዕራብ ኢትዩጵያ ክፍለ ሀገራት ዉስጥ የሚኖረዉን ነባር ዐማራ ሕዝብ  ለዘቀጠ ፓለቲካቸዉ ማካካሻ ብለው "ያማራ ክልል ተወላጅ" እያሉ የሚያድክሩትን በአጽናኦት እንኮንናለን። የሐረርጌ ድሬዳዋ ከተማ ዐማራ ነባር ነዋሪ ነዉ፣ የሐረር ከተማም እንዲሁ ያማራ ክልል ተወላጅ ብሎ ማወናበድ ዐማራዉን ከቤት ንብረቱና ከትዉልድ ቀበሌዉ በጎሣ ማፅዳት ዘመቻ ለማጥፋት የሚደረግ ሴራ ነዉ። የድሬ ዳዋ፣ የሐረር፣ የጅጅጋ፣ የአሩሲ፣ የባሌ፣ የአዋሳ፣ የሲዳሞ፣ የከፋ፣ የጅማ፣ የአማሮ፣ የጋሞ፣ የጋምቤላ ወዘተረፈ ዐማሮች ሁሉ የራሳችሁን አካባቢ በራሳችሁ ለማስተዳደር መደረጀት አለባችሁ እንጂ ከአባይ ማዶ ባሕርዳር ያለዉ ቅጥረኛ ባንዳ ስብስብ አዴፓ በዐማራነት ጨንበል ሊያታልላችሁ ፈፅሞ አይገባም።


4/ ሼዌ በመላዉ በመራ ቤቴ ደራ፣ በኤፌሶን/አጣዬ፣ በፈንታሌ፣ በቅምብቢትና በየረር፣ በዟይ፣ በሰላሌ፣ በግንደበረት፣ በመናገሻ፣ በጉራጌ ሰዶ፣  በከምባታና ሃድያ ወዘተረፈ ለሚደረገው ፍልሚያ ተዘጋጂ!

5/ በሰሜን በጌምድር ክፍለ ሀገር ባንዳዉ አዴፓ ጅግናዉን ሻለቃ አስቻለዉ ደሴን አስገድሏል። ፋኖዎችን በያለበት ትጥቅ ለማስፈታትና ለመግደል በዘመቻ ላይ ይገኛል። አዴፓ ያማራን ሕዝብ ለጠላቶቹ ዳርጎ ለሕልዉናዉ የሚያደርገዉን ትግል ለማክሽፍ አስቦ ነዉ ከነ አቢይ አሕመድ ጋራ እየተሞዳሞደ የአስቸኩያ ጊዜ አዋጅ አድርጎ ያማራን ሕዝብ ትጥቅ አስፈትቶ የጌኛ መፈንጭ ሊያደርጉት ያሰቡት።

6/ በአፋር ኢትዩጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመዉን ወረራ ሸሕድ በአጽናኦት ያውግዛል።  በማንኛዉም ጊዜና ስፍራ ከጎናቸዉ ይቆማል።

7/ የአዴፓ ቅጥረኛ ባንዳ በዐማራ ክልል ተብዬዉ ዉስጥ ሰላምና ጸጥታ እድገትና ልማት ማምጣት ያልቻለ ተላላኪ በመሆኑ በአስቸኩዋይ ከሥልጣን ወርዶ ለፍርድ ይቅረብ።
 የመከክላካያ ሠራዊት የሚባላዉ የነአቢይ ኦዴፓ/ኦነግና ትሕነግ ጥርቃሞ ጸረ  ዐማራ ስብስብ ከዐማራ ክልል  በአስቸኩዋይ  ይዉጣ።


ጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓም
ሸሕድ
(Posted  on Ethio Semay)