Friday, May 22, 2026

አበቤች አደኔ አብይና ዝናሽ ሆይ እንደ ዛጉዌው መስራች እንደ ንጉሥ መራ እልፎችን እቤታችሁ ለማኖርና ለመቀለብ ፈቃደኞች ናችሁ? ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 5/22/26

 

አበቤች አደኔ አብይና ዝናሽ ሆይ እንደ ዛጉዌው መስራች እንደ ንጉሥ መራ እልፎችን እቤታችሁ ለማኖርና ለመቀለብ  ፈቃደኞች ናችሁ?

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

5/22/26

ዛሬ የምንመለክተው ጉዳይ “መጽዋች እና ተመጽዋች” በሕግ አውጥቶ ድሆችን እንደ ቆሻሻ እያየ ከጎዳና እየለቀመ እስር የሚያስገባ (social cleansing) አብይ አሕመድ እና የሱ ታማኝ የሆነቺው በሰው ሰራሽ ውበት የምትዋብ እና የሞዴል  ልዕቶች የማይለብሱዋሸው በውድ ልብሶችና ሽቶዎች የምትሽቀረቀረው የአዲስ አበባ ውቢትዋ አበቤች አደኔ ለድሃ ማሕበረሰብ ያላቸው ጥላቻን እንመለከታለን።

ምንም እንኳ አብይ አሕመድ ለመለመን ይተፈቀደለት ፥ ለማኝ እና ልመናም እንደሚሳካለት የልመና ባለሞያ መሆኑን ሳይሸማቀቅ ቢነግረንም ፤ በሚገርም ነገር ‘ልመና ለአብይ ሲፈቀድ  “አዱንያ አልሆን ብላቻቸው” የዕለት ጉርሻ አጥተው ለሚለምኑ እና ለሚመጸውቱ መጽዋቾች ግን አብረው እንደሚቀጡ አዲስ አዋጅ ተግባር ላይ እየዋለ እንደሆነ በዚህ በተለጠፈው የቪዲዮ እና የድምጽ ማስረጃ ማረጋገጥ ይቻላል ።

 ሳምንቱን አበቤች አደኔ በድሆች ሕይወት ስታሾፍ ሰምተናታል። በዚህ ቪዲዮም ታደምጠዋታላችሁ። በዚህ Ethio forum ዘገባ የሥርዓቱ ጨኻኝነተ እና ንቅዘት ባስገራሚ ማስረጃ ዘግቦ አሳይቶናል (ምስጋና ይግባው!) 

 የሃገራችን ሕዝብ እስላምም ክርስትያንም ይሁን ታዋቂ ሃይማኖቶችን የማይከተል በየዋህ ባሕሪ በመነሳሳት ይሁን የሃይማኖቱን ሕግጋቶች ተከተለው ለታረዙ ድሆች “ልብስ” ለተራቡ “ምግብ” የሚመጸውቱ መጽዋቾች እና ተመጽዋቾች ፣ (የኦነጉ መሪ ሌንጮ ለታ «የኦሮሞዎች መንግሥት) እያለ የሚጠራው «አብይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሞዎች መንግሥት» በሕግ ይቀጣል። መጽዋቾች እና ተመጽዋቾችን ለመቅጣት ሰላዮችን መድቦ እየተከታተለ ፤ ከገንዘብ ቅጣት ጀምሮ ንግድ ቤቶችን እሰከማሸግ/ እሰከመዝጋት/ የሚደርስ ሕግ አጽድቆ እየቀጣቸው ይገኛል።

ይህም የነገረችን ለሥርዓቱ ከሚሸቅሉ ሎሌዎች አንድዋ ከላይ ከነ አበቤች አደኔ ፎቶ ጋር የምታይዋት «አለምፀሃይ ጳውሎስ” የተባለች “barbaric” የአዋጁ ምሕረት-የለሽነትና ጭካኔ  ታሪክ ይታዘበኛል ሳትል ፣ሳትሸማቀቅ “ጀርመኖች በ1933 ለድሆች እና ለቤት-አልባዎች ሲያደርጉት የነበረው ዓይነት እስራት፤ቅጣትና ንቀት በኩራት ነግራናለች።

የኦሮሙማው ቡድን  ወደ ሥልጣን ከመጣበት የመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ ውሸት እና መቀደድ የማንነቱ መገለጫ ባሕሪ እንደነበር በሂደት አይተናል። ልምድ አደረጉትና ቅጥ ያጡ ዋሾች እና ከራባት ያጠለቁ ጤናማ የሚመስሉ የአእመሮ በሽተኞችን ከየቦታው ለቃቅሞ እየሾመ ሲዋሹለት ምቾት ሰጣቸዋል። እንዲህ ያሉ ሰዎች የስነ ልቦና ሊቃውንት Mythomania ይሏቸዋል።

ዛሬ የምንመለከተው የአብይ አሕመድ የወንጀል ተጋሪዋ  አበቤች አደኔን ነው።የሕከምና ባለሞያ ዶክተሮች በኑሮ ውድነት በደሞዝ ማነስ የተመጣጠነ ምግብ ቀርቶ በቀን አንድ ቀን ብቻ እየበላን በርሃብ ተሰቃይተናል እያሉ ሲጮሁ አበቤች አደኔ ደግሞ ድሆችን ወደ መመገቢያ ማእክላት ሂዳችሁ “እጃችሁን ታጥባችሁ” የተመጣጠነ ምግብ ተመገቡ እያለች የምትቀልደውን ቀልድዋን አይተን ፣ አብይን ዳብሰን ከዚያም ወደ 12ኛው ክ/ዘመን ንጉሥ እና የድሆች አያያዝን እንመለከታለን።

አበቤች አደኔ ለድሆች ያላት ግሃዳዊ ጥላቻ ከማሳይተዋ በፊት ጥላቻና ውሸት የጀመራት ገና ሥልጣን ላይ ከመውጣትዋ በፊት ቢሆንም ሥልጣን ስትይዝ ግን ድብቅ ጥላቻዋ በግሃድ የወጣው የግምሩክ ሐላፊ ሆና ስትሾም የአማራ ነገድ ሰራተኞች እያባረረች በምትኩ ኦሮሞዎችን ስትቀጥር ከዚያም ጥላቻዋ ወደ ትግሬዎች ዞሮ “ትግርኛ ተናጋሪዎች እንዲጨፈጨፉና እንዲለቀሙ (ቱ ቢ ሃንትድ) ሆን ብላ በማቀድ ‘’ሓጫሉን የገደሉት ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው” ማለትዋ ሳይበቃ ‘’ ፥ (ፍንፍኔ ውስጥ) ትግሬዎችን ፈቅደንና ወድደን ብናኖራቸው ጠገቡ’’ የምትለን የኦሮሙማው ኢንትርሃሙዌ ቡድን አባል አበበች አደኔ ፡ ሰሞኑን አዲሰ አበባ ውስጥ ሰላሉ ርሃብተኞች እንዲህ ስትል ተናግራለች፡

«አዲስ አበባ ላይ ጎዳና ላይ ወጥቶ ምግብ የሚያስለምን ምንም ምክንያት የለም። አዲሰ አበባ ውስጥ እንደው እውነቱን ለመናገር አዲሰ አበባ ላይ ጎዳና ላይ የሚያስወጣ ምክንያት በአሁኑ ሰዓት  የለም ወደ ምገባ ማእከላት ውስጥ ጎራ ብሎ ትኩስ ፥ ንጹህ እና የተመጣጠነ ምግብ  መመገብ የሚቻልበት ከተማ ሆኗል።ማረፊያ የሌላቸው ደግሞ ቤታቸው ነው፡ ማረፊያቸው ነው። ርቧቸው ምግብ በልተው አረፍ ብለው እርስ-በርሳቸው ተወያይተው የሚሄዱበት ቤታቸው ነው። ስለዚህ በየጎዳና ላይ የዕለት ጉርሻቸው የሚለምኑ ወገኖቻችን ሁሉ መልእክት ለማስተላለፍ እወዳለሁ። “በከተማ ውስጥ የተገነቡ የምገብ ማዕከላትን በመሄድ እጃችሁን ታጥባችሁ በንጽሕና መጥታችሁ መመገብ ትችላላችሁ። የሚያስፈልገው ሰው ከየት እንድየት መጣህ የሚለው ማንም ሰው የለም።” ተላለች ስትቀደድ፡

የሚገርመው፤ ጉልበታቸው ለደከመ አረጋዊያን ፤ ዕርጉዞች፤ ህጻናት እና አካለ ስንኩላን አድራሻ ወዳልተገለጸላቸው የመመገቢያ ጣቢያዎች «ማጓጓዣ አዘጋጅታ የሚያመላልሳቸው አብቶቡስ እና ታከሲ ያዘጋጀችላቸው ይመስል እየሄዳችሁ ተመገቡ ትላለች”።

አንድ መንግስት የድህነትን መዋቅራዊ መንስኤዎችን ከማንሳት ይልቅ የበጎ አድራጎት ገጽታ በመፍጠር ድሆችን ሕጋዊ እና ኢ-ሕጋዊ ድሆች” በሚል ደረጃ በመሰየም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ በዚህ ዓለም ተሰምቶ የማያውቅ የድሆች ዓይነት ስም እያወጣ በዘር መድለዎ እና በቤት ግንባታ ሽፋን ድሆችን ከተጠለሉበት መኖርያቸው እያፈረሰ ፥ ከሥራቸው እያፈናቀለ፤ መናፈሻ ፓርክ ሰራሁላችሁ እያለ ሲያሟርት ወደ ጎዳና እንዲወጡ ያደረጋቸው ተፈናቃዮችና  ድሆች ፣ የሚያስለምን ምክንያት ምን እንደሆነ አላውቅም ትላለች (እያወቀች)።

አለቃዋም እንዲሁ«ከብት የሚግጠው የጓሮ ቅጠል እጁ ላይ ይዞ እያሳየ)» ሃገራችን  ችግር ውስጥ ሰላለች በርሃብ ከመሞት ይህንን ቀጠል ሸምጥጣችሁ ጨው ጨምራችሁ ፥ ካስፈለገም ትንሽ ዘይት ጨምራችሁበት ለ7 ሰው መመገብ ትችላላችሁ፡ እያለ “በሕዝብ ሕይወት” ቀልድ ይሰራል።

እንደመታውቁት ተምረው የመቅጠርያ ባጀት ስለታጣ  መንግሥት ባጀት የለኝም ሰላላቸው ፤ ሥራ ያጡ 1500 ሃኪሞችና በርካታ ነርሶች ስራ የላቸውም ሲል አዲስ ዘመን እንደዘገበ እናስታሳለን።

ስራ ላይ ያሉ የሕክምና ባለሞያዎችም ደማዛችን  ለኪራይ ፥ ለምግብና ለመጓጓዣ ሰለማይበቃን ቁርስ በልተን ምሳ ሳንበላ ውለን በመከራ እየስራን ነው ፤ በማለት ሥራ ያጡ እና የተራቡ ሃኪሞች በሚል የጻፍኩትን አስታውሱ።በወቅቱ የኢትዮጵያ ጠ/ምኒስተር ነኝ የሚለን የኦነግ ሸኔው ሰው አብይ አሕመድ እሮሮአቸው ሲያቀርቡለት ምን እንዳላቸው ላስታውሳችሁ።

የብዙ ሰው ልብ በሐዘን የነካቺው አንዲት የልብ ቀዶ ጥገና ስፕሻሊስት፡

«እባካችሁ አትግፉን (don't push us) ሀገራችንን ማገልገል እንፈልጋለን»  ስትል፣

አብይ አሕመድ ደጎሞ እኔም የ IT ባለሙያ ነኝ ወደ ውጪ መውጣት አቅቶኝ አይደለም ሀገሬን ላገልግል ብዬ ነው። እኔም ለሃገሬ እያገለገልኩ ነው አሞኝ እንኳ አሞኛል ሳልል እሰራለሁ፡ የሕክምና ሙያ ከምንም አይበልጥም» አላቸው።

ሃቁ ግን አብይ ከድሮ ጀምሮ ወደ ሥልጣን ሳይመጣ ከኋላ የራስ ቅል  (ጭንቅላቱ) ላይ እባጭ (ዒጥ) ስለነበረው ፤ ያችን ሥልጣኑን ተጥቅሞ ወደ ውጭ አገር በመሄድ ቀዶ ጥገና አድርጎ ታክሞ እንደመጣ እሱ ቢክድም ፎቶውን ከማየት ነው። እንዲያውም አዲሰ አበባ ውስጥም “ለአምላክ ምስጋና እና ፍቅር” በሚል ታክሞ መምጣቱን ሕዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ አድርጎ  ትርጉሙን ሳያውቅ ሕዝቡን ሸውዶታል።

ከተማችንን አዲስ አበባን ለማስዋብ ስንል ባለሃብቶችን ኑ ግቡና አግዙን እያልን ስንት በጀት እያፈሰስን ባለንበት ሰዓት እናንተ ሐኪሞች "ብር" "ብር" አትበሉ ሕክምናን ብር ማግኛ አርጋችው አትስሩ ፡ስትመረቁ በገባችሁት ቃል መሠረት አርፋችሁ ሥሩ! አላቸው።

«ብርን አስባችሁ ከመጣችሁ አታስቡት ፡ ኢትዮጽያ በአሁኑ ወቅት ተመንዝሮ የማያልቅ ተስፋ እንጂ ብር የላትም፡ ምናልባት ለዘይትና ሽንኩርት 500ብር  እንጨምርላቹ ይሆናል።» ሲል ቀለደባቸው።

በሬ እየታረሰበት ሥጋውም እየተበላ ቆዳውም  ለጅማት ክር እየዋለ ይሄ ሁሉ ሲደረግበት ምንም ነገር አይናገርም… ሐኪምም እንደዚ በሬ ነዉ መሆን ያለበት...!"

እያለ በሕኪሞች ላይ ከቀለደ በኋላ አንድ ሓኪም በጻፈው መጣጥፍ ላይ እንዲህ ያለውን ላስነብባችሁ እና ወደ ጉዳያችን እናምራ፤

አብይ ለሐኪሞች እንዲህ አላቸው

ሰሞኑን ሐኪሞች ስላኮረፋችሁ ለኩርፊያችሁ የሚሆን ምሳ ብሉና ቤተ-መንግስቱን ጎብኝታችሁ ወደ ሥራ ሂዱ” አለን። ይላል አንድ ሐኪም። በማስቀጠልም

...ብቻ ብዙ ብዙ ነገር ተብለናል ፣ መሪያችን ባደባባይ ባሪያ መሆናችንን በድጋሚ ሲያበስረን እጅጉኑ አመመኝ።ሲል በቁጭት ለሕዝብ አስረዳ።

ሓኪሞች ሳይቀሩ ለሽንኩርት መግዣ በማጣት በሚሰቃዩባት አገር የባንቱስታዋ ከንቲባ አበቤች አደኔ ደግሞ ወደ ጎዳና ያስወጣቻቸው ድሆች “ኑ የተመጣጠነ ምግብ ተመግቡ” እያለች ታሾፋለች።

በ11 እና 12ኛው ክ/ዘመን የነበሩት መንግስታቶቻችን ስለ ድሆች አያያዝ እና የምግብ ማዕከላት ጉዳይ እንመልከት

የዛጉውዌ ሥርወ መንግሥት የንጉሥ መራ ተከለኃይማኖት የድሆች አያያዝ እና አመጋገብ ከመመልከታችን በፊት የሚክተሉት እንግዳ ቃላቶች ትርጉማቸውን እንመልከት

መጀምርያ የዘመኑ ቃላቶች እና ትርጉማቸውን እነሆ፡

 እልፍ(እልፍ ማለት የግዕዙ “ቁጥር ማለት ሳይሆን- ችግረኛ ሰው፤ ጧሪ እና ደጋፊ የሌላቸው ማለት ነው

 እልፍ አውል- እልፍ አውል ማለት ብዙ ሕዝብ የሚያውል፤ የሚረዳ የሚመግብ ማለት ነው።

እልፍ አስከባሪ--  እልፍ አስከባሪው እናት እና አባታቸው የማይጦሩትን ሰዎች እየተዘዋወረ እየመዘገበ ለቅጣት የሚያቀርብ ክፍል ነው።

ሐሰሴ ፍትሕ - ፍርድ አስፈጻሚ- ፍትሕ ሚኒስተር /ፍርድ አሳሽ /ፈታሽ/ መርማሪ/አጣሪ ማለት ነው

አበጋዝ - በመራ ተ/ሃይማኖት ዘመን  የተቋቋመ “በሐሰሴ ፍትሕ ሠራዊት” ስር የነበረ - ዋና ሥራው የሕዝብ መብት ሲደፈር ፥ገዢዎች ያለ አግባብ  በደል ሲፈጽሙ፤ክፉ ቀን ሲመጣ፤ድርቅ፤አንበጣ በአገሪቱ ላይ ችግር ሲደርስ ፤ ሕዝቡ ሳይጎዳና ርሃብ ሥር ሳይሰድ በአጭር የሚቀጭበትን መንገድ የሚያደርግ።

 ዶሚና የተባለ ደግሞ’ “የሰላም ዘበኛ’’ የመንግሥት ግብር በየወረዳው ሲሰበስብ ሕዝቡን ያለአግባብ እንዳይበደል መቆጣጠር ነው።  “አበጋዝ ከቱርክ የተገኘ ስም ነው” ብለው ቀ/ዳማዊ ኃለስላሴ “ሕይወቴ እና የኢትዮጵያ እርምጃ” በሚለው መጽሐፋቸው  በምዕራፍ 15 ላይ ‘’ቃሉ የተገኘው ቱርክ ሐረር ሲገባ ያመጣው ቃል ነው ቢሉም ፡ ንጉሡ ወይንም አማካሪዎቻቸው ተሳስተዋል። ይህ ቃል በ12ኛ ከ/ዘመን የነበረ በዘመኑ የተጻፉ የግዕዝ መጽሕፎቶች እንደተገኙ (አሁን እኔ ለዚህ መጣጥፍ የተጠቀምኩት መጽሐፍ ደራሲ ይገልጻሉ)። ደራሲውም ከታች አስቀምጣለሁ።

ጉሮጉሮኒንደር- በመራ ተክለሃያምኖት ዘመን ሐሰሴ ፍትሕ (ፍርድ አስፈጻሚ) የፍትሕ  ሚኒስተር የነበረ የከፋ አውራጃ (የአናርያ) ተወላጅ በቆዳ ቀለሙ “ጥቁር ሰው ነበር። በመራ ተክለሃያምኖት ለካም እና ለኩሽ ሰዎች (በቆዳ ቀለም) እየለየ ሥልጣን በመስጠቱ ከጠያይም ኢትዮጰያዊያን የካም እና የኩሽ (የአናረያ እና የመረዌ) ዘሮች ካልሆኑ ሲማዊያን ነን የሚሉ ወደ ጥንት ቦታቸው እንዲመለሱ እና የዓረብ ዘር ሆነው እስልምና የሚከተሉ ዓረቦችም አገራቸው እንዲገቡ፤ ሲማዊያን  ነን የሚሉትም  ከሥልጣን ተገልለው ኢትዮጵያዊያን ሆነው እሰላምና እመነት የሚከተሉ ካሉ ከሃያምኖት ወገኖቻቸው ጋር አብረው እንዲሄዱ ፥ ይህንን አንፈጽምም ካሉ ተጠምቀው ኢትዮጵያ አገራቸው  ሰለሆነች አርሰው የርስት ተካፋይ ሆነው  እንዲኖሩ በመደረጉ፤ በዚህ ላይ ከዮዲት ዘመን ጀመሮ በሃይማኖት ግጭት ሰለተፈጠረ ሰላም ደፍርሶ በመታየቱ።

ጉሮጉሮኒንደር ይህንን በማየት የቀለም እና የሃይማኖት ልዩነት ማድረግ ለሃገሪቱ ሰላም እና ባሕል መረጋጋት ጠንቅ ሰለሆነ ይህንን ማስቀረት አለብን ብሎ እሱ ሲሾም፤ጥቁሮችን ከየቦታው (ከመርዌ -ሱዳን) ሳይቀር በማስመጣት ከቀያዮች እና ጠያይም ኢትዮጵያዊያን ጋር ቀላቅሎ ሠራዊት የመሰረተ በንጉሡ እና በሕዝብ የተወደደ ሰው ነበር። (ስለ ጉሮጉሮኒንደር አስገራሚ የፍትሕ ሰው መሆን ሌላ ቀን እመለስበታለሁ) ዘመኑ ከመላው ኢትዮጵያ የመጡ ሰዎች የገነቡት አስተዋጽኦ መሆኑን ላሰምርበት እሻለሁ። ሥራውና ግንባታው የአገው ብቻ ፥ የአማራ ብቻ የትግሬ ብቻ.... ወዘተ... የሚሉ ደናቁርት ትንሽ መቆጠብ ያስፈልጋል።

አሁን ወደ ድሆች እንግባ፡

ንጉሥ መራ ተክለሃይማኖት ላስታ ውስጥ የተወለደ ነው። መራ በመጀመሪያ የአክሱማዊው የንጉሥ ድል ናኦድ (ጸረ ዮዲት ጉዲት ወገኖች ላይ ከባድ እርምጃ የወሰደ ንጉሥ) የጦር መሪ (በዘመኑ አጠራር “መሪ ፈረሰኛ የሰላም ዘበኛ” ነበር። ከዚያም የድል ናኦድ ልጅ መሶበ ወርቅን አገባ። ቆይቶም አማቹን ገልብጦ የዛግዌ ሥርወ መንግሥት መስርቶ የሰለሞንን ቤት ገለበጠ።

 ይሀ ንጉሥ ጧሪ እና ደጋፊ የሌላቸው “እልፎችን” ድሆችን እንዴት ይረዱ እንደነበር ያዋቀረው ልዩ የሆነ አስገራሚ አያያዝን እንመልከት።

ከላይ እንደተመለከትነው “እልፍ” ማለት ቁጥር ሳይሆን ችግረኛ ሰው/ሰዎች ማለት ነው። እነዚህ እልፎች «እልፍ አስከባር» በሚባል የችግረኞች እንባ ጠባቂ ድርጀት ችግራቸው እየታየ ዕርዳታ እንዲያገኙ ያደረጋል። ዕርዳታ የሚያገኙበት ቦታ ደግሞ “እልፍ አውል” በሚባል የመመገቢያ እና የዕርዳታ ቦታ ነው። እልፍ አስከባሪም ይሁን እልፍ አውል፤ ሁለቱም “በሐሰሴ ፍትሕ” (በፍትሕ ሚኒስቲር) ቁጥጥር ሥር የሚካሄዱ የዕርዳታ ዘርፎች ናቸው።

የእልፍ አውል ዋና ተግባር ወይንም የሥራ ድርሻ፤ ልጅ የሌላቸው መካኖች በበሽታ ወይንም እርጅና ምክንያት መሥራት ያልቻሉ ችግረኞችን መጦር፤ ከሥራ የተገለሉ በሽተኞች ፥ ጧሪ ከሌላቸው መደገፍ፤ ወላጆቻቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩና ዘመድ የሌላቸው ሕፃናትን መደገፍ ነው።

ጎረሞሶች ሆነው ሥራ ጠል ከሆኑ ይመረመሩና ወደ ፀጥታ አስከባሪነት ተመልመለው ይገባሉ። ጎረምሶች ሆነው ሥራ በማጣት ሲነከራተቱ የሚበሉት ካጡ ማቆያ ስፍራ ይሰጣቸውና  እና እንደ እየ የስራ ችሎታቸው እየታየ ህንጻ ሥራ ወይንም እርሻ እና ንግድ ከሆነም አጋሰሶች እየተሰጣቸው እንዲሰማሩ ይደረጋል።

ጧሪ እና ደጋፊ የሌላቸው አረጋዊያን እና ልጅ እግሮች ከሆኑ ግን እልፍ አስከባሪው ችግረኞችን እየተዘዋወረ በመሰብሰብ በተሠሪነት  እየገቡ እንዲቀለቡ ያደርጋል። ችግረኞችን የሚቀበለው ሰው ምግባቸውን፤ልብሳቸውንና ንጽህናቸውን የማሟላት ግዴታ አለበት። ተሠሪ የሚቀበለው ድሀው ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ እሰክ ተራው ወታደር ያለውም ነው።

 ንጉሠ ነገሥቱ ሁለት ድርሻ አለው። አንዱ ከሕዝቡ የበለጠ ድርሻ ተሰጥቶት ተነቃናቂ ያልሆኑ እሰከ 300 የሚሆኑ ችግረኞችን ይቀልባል፥ ያለብሳል። በራሥ እና ደጃዝማች ማዕረግ ያሉት ደግሞ በቋሚነት አሥር ሰው በየቤታቸው ይዘው ሲቀልቡ፣ ከዚህ በተጨማሪ በተራ ሲደርሳቸው አንድ እልፍ (አድ ችግረኛ ሰው) ለወር ይቀልብ እና ለተረኛ ያዛውራሉ።

ከፊታውራሪ እሰክ ባላምባራስ ማዕረግ ያላቸው በነዋሪነት ሦስት ሰው ይይዙና በተረኛነት አንድ እልፍ ሰው ለስደስት ቀን ቀልበው ለተረኛ ያስተላለፋሉ።-

እልፍ አስከባሪው ቤተመንግሥት ያሉትን ሳይቀር በመልካም አያያዝ ወይንም በችግር ላይ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በየጊዜው ቁጥጥር  ያደርጋል። በቋሚነት የተቀመጡትም ሆነ በወር ተራ የሚዞሩት ደህንነታቸው፥ ንጽሕናቸው፥ ልብሳቸው ፥ ምግባቸው እንደምን እንደሚሰራላቸው በመመርመር ጉድለት ያገኙበት ሰው ካዩ  ጉድለቱ ሰለሚያስጠይቅ በመልካም ሁኔታ የተረከቡትን ሰው ተነከባክበው ይይዙት እንደነበር በግዕዝ የተጻፉ የመዛግብት መረጃዎችን ያመላክታሉ።

እልፍ አስከባሪው እናት እና አባታቸው የማይጦሩትን ሰዎች እየተዘዋወረ በማጣራት ከአጽመ እርስት እንዲነቀሉ ያደርጋል። ከእርስቱ የተነቀለው ለጌታ ብያድርም ተቀባይነት የለውም። እናትና አባቱ ያልጦረ ሰው ፤ አሽከርነት አስገብቶ የተገኘ ማንኛውም ሰው ንብረቱ ተወርሶ ለመንግሥት ገቢ ይደረግበታል።የተወረሰው ንብረትም ድሆች እንዲረዱበት ይደረጋል።

ከዚህ የሥራ ከፍል ሌላ በሐሰሴ ፍትሕ ስር የሚተዳደሩ ብዙ የሕዝብ መብት አስከባሪ ቅርንጫፎች እንደነበሩ በታሪክ ስፍሯል።

አበጋዝ ፦ይህ ሹም በመራ ተክለሃይማኖት ዘመነ መንግሥት የተቋቋመና በሐሰሴ ፍትሕ ሠራዊት ስር የነበረ ነው። የሥራ ድርሻው የሕዝብ መብት ሲደፈር ፥ ገዢዎች  ያለአግባብ በደል ሲፈጽሙ ፥ርሃብን እና ድሕነተን ይሚያመጣ ከፉ ቀን ሲመጣ ፥ድርቅ አንበጣ በአገሪቱ ላይ ችግር ሲደርስ ሕዝቡ ሳይጎዳና ርሃቡ ስር ሳይሰድ በአጭሩ የሚቀጭበትን መንገድ መሻት ነው።

ሌላው በአበጋዝ ሥር የሚታዘዝ የሥራ ክፍል «ዶሚና» የሚባለው የሰላም ዘበኛ ነው። ሃላፊነቱም በወረዳ ውስጥ ያለውን ሕዝብ ግብር በወቅቱ እንዲገብር ማድርግ፥ መልከኛው ሕዝብም “”በግብርም ሆነ በሌላ የተንኮል ዘዴ እንዳይበደለውና ጎዳና ወጥቶ ደህይቶ እንዳይለምን የበላይ ሆኖ መቆጣጠር ነው።

 አበጋዙ ዶሚና የሚሰራውን እና የሰጠውን ጥናት ከዶሚና እየተቀበለ በሕዝብ ላይ የሚደረሰውን ከፈተኛም ይሁን ዝቅተኛ በደል ለአውራጃው አበጋዝ ያቀርባል። አውራጃውም ለበላይ አበጋዝ ያቀርብና እና ለሐሰሴ ፍትሕ ያቀርባል።”

ከዶሚና በታች ደግሞ «ገራዳ» የተባለው አካል አለ። ገራዳ ከዶሚና በታች ሆኖ የሕዝቡን ምሬት ይሁን አቤቱታ እና በደል ለዶሚና ያቀርባል።እነዚህ ክፍሎች በዘመነ መራ ተክለኃይማኖት  የነበሩ አሰራሮች እና ስሞች እንደነበሩ  በልዩ ልዩ የግዕዝ መጻሕፍት ውስጥ ሰፍሮ  ይገኛል።

ሕ ማጣት ለድህነት ምክንያት ከሆኑት አንዱ በመሆኑ በዚህ ንጉሥ ዘመን ከላይ የጠቀስኩት  «ጉሮጉሮኒንደር» የተባለው የናራ (ዛሬ አርሲ) ተወላጅ የነበረ የሰላም ጠባቂ የፍትሕ ሰው የድህነት መክንያት ፍትሕ ማጣት እንደሆነ ሰለገባው ፍትሕ እንዲሰፍን ከመኳንንቱ ጋር በመጋጨት ንጉሡ ሕጎቹን እና አሰራሩን እንዲለውጥ ያሳምነው ነበር።

ምንጭ፤

ጥንታዊ የኢትዮጰያ የሰላም ጥበቃ ታሪክ ከቅራት - እስከ ዘምናዊ ፖሊስ (ከአእምሮ ንጉሤ) ደራሲውም በመላ የኢትዮጰያ ገዳማት በመሄድ ያገኙዋቸውን ሦስት የግዕዝ መጻሕፍትን እንደ ምንጭ ይጠቅሳሉ።

እንግዲህ ከላይ እንዳያችሁት በ12ኛው ዘመን እልፎችን (ድሆችን) ከንጉሡ ጀምሮ ከተራ ሕዝብ ድረስ የተቸገሩትን በወረፋ እና በቋሚነት እንዲመግብ ይደረግ እንደነበር እና ወላጆቻቸውን አንጦርም ብለው ወላጆች ለልመና የዳርጉ ልጆች ንብረታቸው ይወረስ እንደነበር አይተናል።

   «በርሃብ ልናልቅ ነው ደሞዝ ጨምሩልን»ብለው ለጮሁ የኢትዮጵያ ሓኪሞች «ሰሞኑን ሐኪሞች ስላኮረፋችሁ ለኩርፊያችሁ የሚሆን ምሳ ብሉና ቤተ-መንግስቱን ጎብኝታችሁ ወደ ስራ ሂዱ እያለ ለተሳለቀባቸው አብይ አሕመድም ይሁን “የሰጠናችሁ ዳቦ ብቻ እየገመጣችሁ ፖለቲካ ሳታወሩ ተኙ” የምትለን ለሚስቱ “ለፓስተር ዝናሽ ታያቸው እና ለአበቤች አደኔ” የማቀርብላቸው ጥያቄ “እንደ ዛጉዌው መስራች እንደ ንጉሥ መራ እልፎችን እቤታችሁ ለማኖርና ለመቀለብ  ፈቃደኞች ናችሁ?

‘‘የለማኝ ልጅ’’ ከንቲባዋና ሚኒስትሯ|ETHIO FORUM

https://youtu.be/HEMMglhpdmQ?si=TXU1-bO9_7EBzCCJ


ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

 

 

 

 

Saturday, May 16, 2026

ገራፊዎች የሚመሩት የፋኖ ጎጠኛ ትርኪምርኪዎች እና እጅ የሚቆርጡ ብልት ቆርጠው ጠብሰው ተቃዋሚያቸውን ለማጉረስ በሚዝቱ የፋኖ ደጋፊዎች የሚመጣ የአማራ ሕዝብ ነፃነት ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 5/16/2026

 

ገራፊዎች የሚመሩት የፋኖ ጎጠኛ ትርኪምርኪዎች እና እጅ የሚቆርጡ ብልት ቆርጠው ጠብሰው ተቃዋሚያቸውን ለማጉረስ በሚዝቱ የፋኖ ደጋፊዎች የሚመጣ የአማራ ሕዝብ ነፃነት

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

5/16/2026

በአገራችን የብሔርተኞች ሽምቅ ተዋጊ ቡድኖች ታሪክ እንደሚያሳየው ታጣቂዎተነሱበት መፈክር (ዓላማ) ትተው በጫካ ሕግ እየተመሩ ከሳሽም ፈራጅም ፈጻሚም እነሱ ብቻ ሆነው የሚንቀሳቀሱበት በረሃ እና ሕዝብ “ናሺናላይዝ” በማድረግ በማን አህለኝነት ተነስተው ከመፈክራቸው እና ከሚያከብሩዋቸው በዓላትም ይሁኑ ስብሰባዎች ጋር የማይስማማ ቡደን/ሕዝብ/ግለሰብ  ከመግ እስከ መረሸን ድረስ ሲፈጽሙ እንደነበር ማህደራቸው ያሳያል።  ሰሞኑን እየሰማን ያለነው አስገራሚ ዜና ልክ ወያኔን ሲመሩት እንደነበሩት የዓድዋ ልጆችፋኖ ተበሎ የሚጠራው በዘመነ ካሴ ፥ በአስረሰ እና ዝናቡ በተባሉ የጎጃም ልጆች የሚመራ ታጣቂ ቡድንም የራሳቸው የጎጃም ተወላጅ የሆነውን «በሃሰት ሰማይ እና ምድር በማጣበቅ” የሚታወቀው አንድ ታዋቂ ጸሐፊ |*አር-ሸት* ብለው የሚጠሩት ዋሾው “ማርሸት ጸሃዩን* አስረው ጭንቅላቱን ቁልቁል ዘቅዝቀው ወፌ-ላላ ቀጥቅጠው የገረፉትን “የእግር ባቱን” የሚያሳይ ‘ፎቶ’ በሚዲያ እየተዘዋወረ እንደሆነ ሰምተናል።  

ይህ እንደ አስደንጋጭ ዜና እየተዘገበ ያለው የጎጃም ፋኖ መሪዎች ሰውን ማፈን፤ ማሳደድ፤ መረሽን፤ ሴቶችን መድፈር፤ ባንክ መዝረፍ የመሳሰሉ በታጋዮቻቸው እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ ይፈጽሙ እንደነበር ስንዘገበው የነበረ ምግባራቸው ነው። አሁን አዲሰ ዜና ሆኖ አስደንጋጭ የሆነበት ምክንያት በገዛ የአመራር አባላቸው ላይ በሕዝብና በተራ ታጣቂዎቻቸው ላይ ሲፈጽሙት የነበረው የግርፋት ስራ «የገዛ ጓዳቸውን ልከ እንደ ጅብ ሲነክሱት» መስማት ነው ሕዝቡን ያሰገረመ ድርጊት።

 ዝቡ የሚፈጽሙትን ጭካኔ ውሎ አድሮ  በአባሎቻቸው እና በአመራሮቹ ላይ ይፈጸም እንደነበር ከፋኖ በፊት የነበሩት በሻዕቢያ፥ በኦነግ እና በትህነግ/ወያነ/ የግድያ፤ የዘረፋ፤ የግርፋት እና የፖለለቲካ ዝሙትነት ይፈጽሙ እንደነበር የገመና ማሕደር ታሪካቸው አሳይቶናል።

አመራሩ በውጫዊ (በሕዝቡ ላይ) የሚፈጽማቸው የጭካኔ እርምጃዎች ውሎ አድሮ ወደ ውስጥ (ከሕዝብ ወደ ድርጅቱ) የሚዞርበት ምክንያት ቀደም ብሎ እደተገለጸው አመራሮቹ በበሕሪያቸው ጨካኝ (አንስቲንክት)  ገለሰቦች ከሆኑ “በሞራል ኮምፓስ” ስለማይመሩና “የራሳቸው ጥላ ሳይቀር የሚያባንናቸው ተጠራጣሪዎች” ሰለሚሆኑ የሰሩት ወንጀልና ምስጢር ካለም በዙርያቸው ያሉትን ሰዎች ውሎ አድሮ ያጋልጡኛል በሚላቸው አባላቶቹ ላይ “በትግሉ ስም” ለትግሉ አዛኝ በመመሰል  ልክ እንደ ጅብ “በውስጣዊ ፓራኖያ” ቅጽበታዊ እርምጃ እንዲወስዱ ሰለሚያስገድዳቸው  ቀለበት ውስጥ ያስገቧቸው አመራሮቹ” ከጠላት ጋር ሲገናኙ ይዣቸዋለሁ በሚል ወደ “ማጽዳት ዕርምጃ ውስጥ ይገባሉ።

ይህ በሚሆንበት ወቅት ድርጀቱ የሞራል ውደቅት ውስጥ እየገባ መሆኑ አመላካች ምልክት እየሰጠ ቢሆንም፤ አባላቶቹ /ካልቶቹ/ (ለምሳሌ የፋኖ ደጋፊ የሆነው የ Wamera media አዘጋጅ የሆነ ከነ ዘመነ ጋር እገናኛለሁ የሚል ግርማ ካሳ የተባለ Sycophant: (“Someone who acts subserviently toward a powerful, tyrannical abuser, dangerous,  or disreputable leader”)  የተበለ አስገራሚ “ውትፍ ነቃይ”  (አሳማሪ) የሆነ ይህ ሰው “ድበረ-ኤልያስ ውስጥ ከዕድሜ በታች የሆኑ 3 ልጃገረዶች ከነሱ ውስጥ አንድዋ ጀሮዋ የማይሰማ (አካለ ጎዶሎ) ጨምሮ ሰላዮች ናቸው በሚል  ውንጀላ ያስረሸናቸው አስረስ ማረ ይተባለ ይህ የሰው ደም ጥማት ያለው “የፋኖ አምራረ አሸባሪ ሰው” እነዚህን ልጃገረዶች በማስረሸኑ “አስረስ ማረን” በጦር ወንጀል (war crime)  ሲከሰው እና በጠቅላላ የድርጀቱ ሦስቱን መሪዎች (ዘመነ፥አስረስ እና ዝናቡ) ሰዎችን በመረሸንና በመግረፍ ብቻ ሳይወሰኑ የራሳችወ ታጋይ የነበረች “አስካለ ደምሌ” የተባለች በመርማሪዎች መደፍርዋና የት እንዳለች እንደማይታወቅ ወዘተ.. ወዘተ..ወዘተ የፋኖ አመራር ወንጀሎች እየዘረዘረ ያምን እና እነዚህ ወንጀሎች የጦር ወንጀሎች ሕግ የጣሱ ወንጅሎች መሆናቸው “ለስሙልኝ” ይናገርና ትንሽ ሳይቆይ ወዲያውኑ እንዲህ ሲል ሕዝቡ እነዚህ ውንጀለኞች እንዲንከባከባቸው ይማጸናል፡

« በማርሸት ብቻ እኮ አይደለም ይህንን የተፈጸመው ፥ ጎጃም ውስጥ እኮ እንዲህ ያለ (ወንጀልና ግርፋት ማለቱ ነው) ፓተርን (pattern) የተደጋገመ ክስተት ነው። ግን ወገኖቼ “3 አመት ሙሉ ሕይወታቸውን ሰጥተው እንደው አንዴ  ሁለቴ ተሳሳቱ ብለን እንደ ትልቅ ወንጀል ይመስል ልንፈጠፍጣቸው አይገባም ......”

“እነዚህ የሕዝብ ዕንቆች ናቸው፡ አንድ ሁለት ሦስት ስሕተት ሰሩ ብሎ መፈጥፈጥ አያስፈልግም።.....”

“ዝናቡም ዘመነም አስርስም” በተለይ አስረስ ኤለኩዋንት በሆነ (ማራኪ ንግግር) እየተናገረ እኮ ነው ስሕተትም ቢሰራ ብዙ ሥራ የሰሩ ናቸው እኮ ወገኖቼ።..... “የተፈጠረው ነገረ ደግሞ ማይነር ነው። እንደ ትልቅ ወንጀል ይመስል........”

እያለ የሰላማዊ ሰዎች ንብረትን መዝረፍ፤ ማሸበር ፥  የተማረኩ ሙርከኞች ርሸና እና የግርፋት ወንጀልን በተለይ “War crim እና torture በGeneva Conventions ሕግ ተነድፎባቸው የተጠቀሱ ከባድ ወንጀሎችን ነው ግርማ ካሳ የተባለ የፋኖ አምራር ጫማ የሚልስ Bootlicker በነዚህ ወንጀለኞች የተፈጸሙ ወንበጀሎችን  “ማይነር ነው” “እንደ ትልቅ ወንጀል ይመስል አትንጫጩ“እነዚህ የሕዝብ ዕንቆች እንደው አንዴ  ሁለቴ ተሳሳቱ ብለን እንደ ትልቅ ወንጀል ይመስል መፈጥፈጥ አይኖርብንም” እያለ ይህ ድርጊቱን የተቃወሙ አባሎችን ሲስብክ መስማት አስፈሪው የአገራችን ትልቁ ችግር ወንጀል ሲፈጸም እንደተፈጸ ማምን ግን የድርጅቱን ችግር እንዳይጋለጥ አሳነሶ በማየት ፥ ውርደትን ለመሸፈን ወዲያ ወዲህ በማመንታት  ፥ አእምሮም በሚጋጩ ሁለት ሃሳቦች ተወጥሮ  ምቾትን የማጣት ክስተት ቁልጭ ብሎ በግርማ ካሳ ያየንበት አጋጣሚ ቢሆንም፤ የግርማ ካሳ ክስተት በብዙ የአገራችን የፖለቲካ ካልቶች (አምላኪዎች) ያየነው ምፍትሄ ያልተገኘበት ከባድ የአገራችን psychological discomfort ችግር ነው።

አስገራሚው የግርማ ካሳ Cognitive dissonance  ክስተት ድርጀቱ የፈጸመው ከባድ ወንጀልን አሳንሶ በማየት ብቻ  ሳይገደብ ፤ ድርጅቱ እግርዋ እንደተሰበረች ኤሊ  3 አመት ሙሉ መላወስ አቅቶት በአሳፋሪ ሁኔታ እርስበርስ እየተጋደለ ሲንፏቀቅ እያየ እና አሁን ደገሞ ያ “ፓተርን” በሎ እራሱ የሚጠራው የወንጀል ድግግሞሽ ባሕሪ እየቀጠለ መሆኑን እያመነም “ድረጀቱ ብጥሩ ቁመና ነው ያለው፤ ስጋት አይግባችሁ” እያለ ሲስብክም አድምጨዋለሁ። የሞራል ኮማፓስ የተሰበረበት ድረጅት በዛው “ፓተርን” እንዲቀጥል መስበክ ለብዙ አመታት ድርጅቶች የሚፈጽሙት ወንጀል እንዲቀጥሉበት ከሚያደርገው ካብዱ ችግር እንዲህ ያሉ ቅሰቀሳዎች ናቸው።

እንዲህ ያለ የመግረፍ እና የመረሸን ወንጀሎችን አሳንሶ ማየት እና ድርጀቱ በዛው የድግምግሞሽ (ፓተርን) መንገድ እንዳይቀጥል ስናወግዝ በነበርን ሰዎች ላይ በፋኖ አባሎች ዛቻ ደርሶብናል።

ለምሳሌ የጎጃም ፋኖ መሪዎች ብራሳችወ ታጋዮም ሆነ በሕዝብ ላይ እና በምርኮኞች ላይ የሚፈጽሙት ወንጅል መወገዝ እንዳለብተ እና አመራሮቹ ከመሪንተ እንዲነሱ ተደጋጋሚ ትችትና ምክር ስለግስ በነበረኩባችወ ወቅቶች የጎጃም ፋኖ የዲያስፖራ ደጋፊዎቻቸው ብዙ ዛቻ ካደረሱብኝ ሰዎች አንዱን ልጠቀስላችሁ፡

Yonas Andulem Abawa የተባለ የጎጃም ፋኖ ተከታይ እና የጎጃም ተወላጅ  ምን ሲሉ እንደ ዛተብኝ ይህንን አንብቡ፤ 

«Yonas Andulem Abawa

አቶ ጌታቸው ብታርፍ መልካም ነው።በተደጋጋሚ ጊዜ በጎጃም ላይ የአለህ ጥላቻና ንቀት ከልክ የአለፈ ነው ።ተው! አንተና መሰሎችህ ስለዚህ ትግል ተንትኖ ማስረዳት አንደኛ አይጠበቅብንም ሲቀጥል አይገባችሁም።

ሌላው አንተን ቀኝ ጅህን በሚገባ ቆርጦ ማስቀመጥ ይቻላል መፍቴው ቀላል ነው።ዝርዝር አያስፈልገውም አንተም ታቀው አለህ ።ደርሰህ መሪአችንን አትዝለፍ እረፍ ።አልያ ግን ከላይ እንደነገርሁህ ነው!» ሲል


የምትከተለዋ ሌላዋ አሸባሪት ደግሞ ለተቃወማት አንድ ሰው ምን እንዳለቺው ተመለከቱ። 

ቤተልሄም ዳኛቸው ትባላለች፡ የጎጃም ተወላጅ ነች። አውሮፓ ውስጥ ትኖራለች። የጎጃም ፋኖ ደጋፊ ብቻ ሳትሆን  ልክ እንደ እነ ዘመድኩን በቀለ ፥ እንደ ግርማ ካሳ እዋም “ከእነ ዘመነ ካሴ እና አስረስ ማረ” ጋር ቀጥታዊ ግንኙነት ያላት የውጭ ፋኖ “ዲያስፖራ ካድሬ” ነች። ይህች ልጅ ባንድ ወቅት “ዘፋኝ” እንደነበረች እራሰዋ ስትናገር ሰምቻታለሁ (ዩ ቱብ ላይም አልበምዋ ይገኛል)። ታዲያ የዘመኑ ጭካኔ ካፈራቸው ዩቱብ እና የቲክ ቶክ ዕብዶች  አንደዋ ይህች  ፡ ሕሊናዋ በሽብር  የሞላ፥ የሚቃወሙዋትን ሰዎች ብልት ቆርጣ ጠብሳ እንደምታጎርስ እና ይህንንም “የምታወቅበት ስብዕናየ ነው” ስትል በሚዲያ ቀርባ በኩራት ላንድ ተከራካሪዋ ሰው እንዲህ ስትል

 ዝታበታለች፡

«እኔ ቤተልሄም ዳኛቸው እንዳንተው ዓይነቱ ቆሻሻ ፣ ሽንታም፤ ስድብ ብቻ አይደለም እንዳንተው ዓይነቱ ሽንታም ባገኝህ ብልትህን ጠብሸ” ነው የማጎርስህ በዚህ ልክ ነው የኔ ስብዕና» በማለት ተከራካሪዋን አሸብረዋለች።

እንደ ቤተልሄም ዳኛቸው እና Yonas Andulem Abawa የመሳሰሉ እጅ እና ብልት ቆራጭ የፋኖ  ግብረ-አሸባሪ (terrorist) ደጋፊዎች ሰላሉዋቸው ነው የጎጃም ፋኖ አመራሮች ለጃገርዶችን የሚረሽኑ፤ ቀሳውስትን አረጋዊያንን መመሕራንን የሚረሽኑ እና ሴቶችን የሚደፍሩ እጅ ቆርጠው የሚያሳዩ፤ አሁን ደግሞ የራሳቸው አመራረ አባልን ጭንቅላቱን ዘቅዘቀው ቁልቁል ሰቅለው  የእግር መዳፉን ገርፈው ደም በደም አድርገውት እርስበርስ ወደ መታኮስ ተቃርበው እያየንበት ያለንው ምክንያት የፋኖ እንቀሰቃሴና አደረጃጀት የሽብር ባሕሪ  በተጠናወታቸው አመራሮች እና  ደጋፊዎች ስለሚመራ ነው።

ለዚህ ነው አስቀድሜ ትግሉ በማይረቡ ኩታራዎች ተጠልፎ የጫካ “በጋሚዶዎች” (አጉራ ዘለሎች) እየተመራ እና የወረበላዎች ማፈንጫ የጎጠኞች ታጣቂዎች መፎካከሪያ ሆኗል ስንል “እጅህን እንቆርጣለን” ሲሉ እንዳንዱም ብልታችሁን ቆርጨ ጠብሸ አጎርሳችሃለሁ የሚሉ  ይህንን የሽብር ስነ-ትካት (እንሲቲንክት የሚታወቁበት ስብዕና መሆኑን ነው ከአመራሩ ጋር ጥበቅ ግንኙነት ያላቸው የፋኖ ደጋፎች በኩራት ሲናገሩ መስማት የድረጀቱ አመራሮችም ስብዕና ማንነትም አብሮ የነግረናል

ፋኖ የተባለው ታጣቂ ስበዕና የጎደለው ፤ አርቀው የሚያስቡ የተማሩ ሰዎች የጎደሉበት የሞራል ኮምፓሳቸው በተበላሹ መሪዎችና Sycophant በሆኑ ደጋፊዎች ሰለተበከለ ሌላ አመራር እና ስልት ቀይሱ እያልን ስንጮህ ሰሚ አጥተን እነሆ የገዛ ወንጀል ተባባሪያቸው እና የፋኖ አመራረ አባላቸው ማርሸት ጸሐዩን ዝቅዝቅ ሰቅለው ገርፍውት ዕርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ፍጥጫ ውስጥ ገበተዋል። ቅጣዩስ ማን ይሆን?

ሰላም እንሰንብት!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay