ይድረስ ግልጽ የቅሬታ ደብዳቤየ
ለምወዳችሁ የልጅነት ጓዶቼ ሆይ
ከጌታቸው ረዳ (Ethio
seamy ኢትዮ ሰማይ)
Photo Getachew Reda
(Ethio Semay)
ይህ የቅሬታ ደብዳቤ ይፋ እንድጽፍላችሁ
ያስገደደኝ ሁኔታ አሁን ላለው እጅግ ጸረ ሕዝብ የሆነ ከፋፋይ፤ ፋሺስታዊ ፤ስርዓተ አልባዊ ወንጀለኛና የተንኮታኮተ መንግሥት (ፌይልድ
ስቴት/A wrecked State) አብይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሞ
የገዳ ሥርዓት (መደመር) አጭብጫቢዎች ሆናችሁ በሚያሳፍር ሁኔታ ስታሽቃብጡ ማየቴ ልቤ ስለሰበረው፤ ከናንተ ጋር ያለኝን
ወንድማዊ እና አብሮ አደጋዊ ግንኙነቴ ከማቋረጤ በፊት ወደ ልባችሁ ተመልሳችሁ በዚህ ሥርዓት እየተጎዱ ያሉ ማሕበረሰቦች እና ግለሰቦች
እምባ እንዲቆም የድረሱልን ጩኸታቸውን አብራችሁ ከኔው ጋር እንድታስተጋቢ ከሚል ነው።
ለ18 ወራት ያላቋረጠ ከቀን ወደ
ቀን እየተባባሰ የመጣው የዜጎች ሞት፤ስጋት እያያችሁ ዛሬም ያንኑ የዜጎች እምባ ከምንም ባለመቁጠር የአንድ ግለሰብ ልዕልና ማሞገስና
ማስበለጥ ከቀጠላችሁ ላንዴ እና ለመጨረሻ ወንድማዊ ግንኙነቴን የማቆም መሆኔን እንድታውቁልኝ ቅር እያለኝ ልግልጽላችሁ ተገድጃለሁ።
እንደምታውቁት አገሬን ጥየ ለበርካታ
አመታት ስደት ላይ በመኖር ወላጆቼን ሳልቀብር፤ ወንደም እህቶቼን
ዓይን ናፍቆት እያንገበገበኝ እና እነሱም ሌት ተቀን እያለቀሱ በናፍቆት ሳንተያይ አኔም ላለመመለስ የመቀጠሌ ምክንያት
ባንዴም ሆነ በሌላ መልኩ በገንዘብ፤ ተዋጊነትና በፕሮፓጋንዳ ያገለገላችሗቸው
የወያነ ትግራይ መሪዎች፤ ዛሬ ደግሞ በምትካቸው ሌሎችን በማስገበር በጭካኔ የሚጓዝ በገዳ (መደመር) ሥርዓት ለማስፈን እየተሯሯጠ
ያለው ሥልጣን የጨበጠው የኦሮሞዎች ስርዓት የፕሮፓጋንዳቸው አቀንቃኞች ሆናችሁ ለምታገለግሉት ሥርዓት ‘ከድጡ ወደ ማጡ’ ሆኖ ስላገኘሁት
ወደ አገሬ መመለስ አልቻልኩም።
አገሬ ሄጀ እንድጎበኝ እና አገሬ ሰላማዊ ዕንቅልፏን የምትተኛበት ሌሊትና ቀን
ለማየት ስጓጓ ባልጠረጠርኳችሁ ሁኔታ “ዛሬም የዜጎች ደህንነት በባሰ መልኩ ወደ ስራ ሄደው የማይመለሱበት አስፈሪ የቀውስ ሰዓት”
ሆኖ እያያችሁ፡ በወንጀል ለተጨማለቀው ለኦሕዴድ (አፒዲኦ)
ድርጅት መሪው ለአብይ አሕመድ ድጋፍ በመስጠታችሁ ፤አገሬ እንዳትረጋጋና እኔም አገሬ እንዳላይ ተጨማሪ ብትር በመሆናችሁ ከዚህ አሳፋሪ
ታሪክ እንድትታቀቡ ይህ ደብዳቤ ጽፌላችኋለሁ። በተለይም ለኔ ብላችሁ ሳይሆን ደም ለሚያለቅሰው ማሕበረሰባችን
ብላችሁ ከዕብደታችሁ እንድትመለሱ ወንድማዊ ተግሳጽና ልመና አቀርብላችኋለሁ።
እንደምታውቁት አብረውኝ ያደጉ ብዙዎቹ
ጓዶቼ (የራሴ ወንም እና ዘመዶቼም ጭምር) በተለያዩ ምክንያቶቻቸው አረመኔ ለሆነው ለፋሺስቱ ድርጅት “ለትሕነግ” (ለህዝባዊ ወየነ
ሓርነት ትግራይ) አባል ሆነው ህይታቸው መስዋእት ያደረጉ አሉ (ወንድሜ ቆስሎ በህይወት ቢተርፍም) ። አንዳንዶቹም የታገሉለትን
አራዊታዊው ‘የትግሬዎች ሥርዓት’ ሳያስተካክሉ “መከረኛውን ሕዝብ እንዲጋፈጠው ጥለውት ወደ ውጭ አገር መጥተው” “ጨቋኝ ድርጅት
ነው ብለው የጣሉሉት ድርጅት ተመልሰው የድርጅቱ አጨብጫቢዎች እና የልብ አገልጋዮች ሆነው አይተናቸዋል”። ይህ ልብ ይሰብራል። በጣም
ጥቂቶችም ዕድለኞች ሆነው ከተዋጊነት ወጥተው ግማሽ በግማሽ ወየኔን በመኮነንና በማሞገስ (በተለይ አረመኔውን መለስን በማሞገስ ረገድ)
እስከመጨረሻ ድረስ ዘልቀው ሲጓዙ ቆይተው ዛሬ ደግሞ በመጨረሻዋ ሰዓት
(በ11ኛዋ ሰዓት) የሥልጣን ጥመኛው ኦሮሞው ለኦፒዲኦ መሪ ለአብይ
አሕመድ “ድምጽ ማጉያ” ሆነው፤ ሕዝብ ሲበደል ከመጤፍ ሳይቆጥሩ ዝምታቸውን እያስተጋቡ ነው። እንዲህ ያሉ ሰዎች በታሪክ ታይተዋል። ስለሆነም ነው ታላቁ የጥቁር አፍሪካን አሜሪካን መሪው
“ማርትን ሉተር” In the end we will remember not the words of our enemies but the
silence of our friends (Martin Luther King Jr)
የተፈጸመብን ጭካኔ ሳይሆን የምናስታውሰው የጓደኞቻችን ዝምታን እናስታውሳለን”
(ማርቲን ሉተር ኪንግ ጆር) ሲል ታሪካዊ ትዝብቱን የዘገበው።
አብሮ አደጎቼ የሆናችሁ ወዳጆቼ
ሆይ!
ለአገሬ ሕዝብና ፍቅር እንዴት እንደምንገበገብ
ከልጅነቴ ጀምሮ የምታውቁኝ ጉዳይ ነው። ዛሬ ያንን ልተው አይቻለኝም። የኔን ቅሬታ ተገንዝባችሁ አብይ አሕመድ ለተባለው አገሪቷ
ከድጡ ወደ ማጡ እየከተታት ያለው የሚሊዮኖች ህይወት ተጠያቂ ለሆነው ‘ጸረ አማራ በሆነ ተዋጊ ድርጅት ታጋይ ሆኖ ያደገ’፤ እንደጃዋር
መሓመድ የናቱን ዘመዶች የሚያብጠለጥል “ጸረ አማራ” የሆነ ‘ወንጀለኛ ሰው’ ድጋፋችሁን እና አገልግሎታችሁ ላለመንፈግ ብላችሁ
“ከዚህ ደብዳቤ በኋላ በወንጀል ለተጨማለቀው መሪያችሁ ለማጎብደድ ከወሰናችሁ የኔን አብሮ
አደግነትና ወንድምነት ያለኝን ሰብኣዊ ጥብቅና “ስላጣጣላችሁት” እጅግ ሐዘን ተሰምቶኛል፡፡
ስለሆነም ቤተ እምነቶችን ዜገችን
እና አገርን በገዛ ጓዶቹ የኦሮሞ አሸባሪዎች እየተናወጠች እያየ ‘ጀሮ ለማይሰጥ አልሰማሁ አላየሁ ለሚል” ፤ የደገፈውን ሕዝብ “የሚክድ”
አሸባሪዎችን እና የጥላቻ መሪዎችን በዙሪያው እያስከተለ “ጥበቃ የሚያደርግላቸው” ይህ ከሓዲ የሆነ “ይሁዳ” ስትደግፉ “የመደገፍ መብታችሁ ማክበር እንደሌለብኝ እያወቃችሁ” በጣም
መበሳጨቴን እወቁልኝ።
አዎ እናንተ የቅርብ አብሮ አደጎቼም
ሕዝባችን ሲያለቅስ ለአንድ “ግለሰብ የስብእና ቀረጻ/የግል አምልኮ” ስትሉ ሰምታችሁ አይታችሁ እንዳላያችሁ እልቂትን እያሳነሳችሁ፤ሞትን
እስርን ስቃይን፤ዘረኝንትን እንዲሁም ሥርዓተ አልባነት እንዲቀጥል ተዋናዮች ሆናችኋል።
ፌስ ቡክ ድረገጻችሁ ወደ ኢቲ ቪ እና ፋና ብሮድካስቲንግነት ተለውጣል። የዘር ጭፍጨፋ /ጀነሳይድ/ በሚካሄድባት አገር “ኦርቶዶከስ ኢትዮጵያውያንን
እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰንደቃላማን” መሪዬ!!” ብምተሉት በራሱ በመሪያችሁ በአብይ አሕመድ “ወታደሮች ትዕዛዝ” በደል ሲደርስ አይታችሁ
ዝም በማለታችሁ ማርትን ሉተር አሁንም “አደገኛ ነገሮች ሲከናወኑ
ላለመቃወም ዝም በምንልበት ቀን የህይወታችን ማለቂያ የመጀመሪያዋ ጉዞ ነች።(ማርቲን ሉተር ኪንግ) Our lives begin
to end the day we become silent about things that matter,” ያለውን በናንተው አይተነዋል።
በመጨረሻም ስለቀበጣችሁለት የአብይ ኖብል ሽልማት ጉዳይ አንድ ልበል እና
ልደምድም፡
ለአብይ ድጋፋችሁ የጦፈው በቅርቡ
ኖብል ሽልማት በመሸለሙ ፍቅራችሁ ግሏል። ማወቅ ያለባችሁ፡ በብዙ መንገዶች ፣ የኖቤል ሽልማትን ለማግኘት ከመሪዎቹ አንዱ ለመሆን
፣ የአገሩን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ ግብዝ ሰው ቅድምያ ትኩረት ይደረግለታል። ሽልማቱ እንዲሰጠው ከእርሱ የሚፈለጉትን በሺዎች የሚቆጠሩ
ነገሮችን መቀበል አለበት፡፡አንድ መሪ ግብረሰዶም የሚቃወም ከሆነ ለሽልማት አያበቃውም። አብይ የዚህ ኮድ አክባሪ ነው (ራሱ የመረጣት
የከፍተኛ የአገራችን ዳኛም ብትሆን የዚህ ኮድ አክባሪ ነች) ፡ ይህ ከባድ “አገራዊ ጣጣ” በሕሊና ሚዛን ሲመዘን ማንም ብልህ ሰው
አይቀበላቸውም፡፡ የሁኔታ መመዘኛዎች ቁልፎች/ ኮድን መቀበል ማሟላት አለበት። ተሸላሚው ‘በስልጣን ላይ ላሉት ወይም ገንዘብ ላላቸው
ብቻ አሻንጉሊት ለመሆን ዝግጁነቱን ማሳየት ዝግጁ መሆን አለበት፡፡
አዎ ከዓለም ወንጀለኞች ጋር የጋራ ሴራ መጣጣም አለበት፡፡ እነሱ የኖብል ሽልማትን ወይም
የተከበረ የክብር ዶክቶሬት ይሰጡታል ፣ ታዲያ እቅዶቻቸውን ፣ በአገሩና እና በአጎራባች ሀገሮች ውስጥ የሚያደርጉትን ማንኛውንም
ግድ የለሽ ተግባር በመደገፍ (ሉዓላዊ ክብር ለማያገናዝብ ትብብር)‘ምላሽ በመስጠቱ’ በዓለም ታዋቂ ያደርገዋል፡፡ ለዚህም ነው አብሮ አደግ ጓዶቼም ለዚህ ፕሮፓጋንዳ
‘ታዋቂነት’ ተገዢ ሆናችሁ የኖብል ሽልማት ተሸላሚውን አብይን ከሚገባው በላይ “obssessed” ሆናችሁ “በተሰፈጠ የህዋሳት ስሜት”
ገብታችሁ ለግለሰብ ልዕለና አምልኮት ተጋልጧችኋል (የሰከረ ሰው ስካሩ አያውቀውምና
ለናንተ አይሰማችሁም)። የሚቀጥለው ተቀረው ጫዋታ በናንተ አድማቂነት ይወድቃል። መሪያችሁ የተከበረ ሽልማት ተቀባይ ነው ተብሎ በተነገረ
ማግስት በተራው ሕዝብ መመረጥ ቀላል ይሆንለታል። የሽልማቱ ዋና ማጠንጠኛውም እዚህ ላይ ነው። ቀስቱ በናንተ ላይ ያነጣጠረ ነበር፤
በሚገርም ሁኔታ ዒላማው መትቷል። የማኪያቬሊው ተማሪ “አብይ አሕመድ” ከህጻንነቱ ጀምሮ የቋመጠለትን ንግሥና አገርም ሽጦም ቢሆን፡
በሬውን ሳሩን እያሳየ ወደ ገደል ከትቶትም ይሁን “የቃዠለትን ንግሥናውን” በናንተው እውን እየሆነለት ነው። አሳዛኙ የዘመናችን
ትዕይንት! (ትራጀዲ) ይህ ነው። በስልክ ደውላችሁ እንድንነጋግርበት ጥሪ አቅርቤላችሁ አሁንም ምላሽ አልሰጣችሁም። ለመነጋገር ዝግጁ
ነኝ። ካልሆነ መልካም ዕድል ለናንተም ለመሪያቸሁም። እኛ ግን ከየእናት አገራችን ዕምባና እሮሮ ማድመጥ አንቦዝንም።ስለ እስዋ “ዝም
አንልም”! ያለችን አንድ እናት፤ አንድ አገር፤ አንድ ሰንደቅ ነች! ስለ ክብርዋ እንቆማለን!
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay
No comments:
Post a Comment