Monday, February 11, 2019

በተለይ ለኦሮሞ ልሂቃን የምጋብዘው ጽሑፍ /ነፃነት ዘለቀ (netsanetz28@gmail.com) Ethio Semay


በተለይ ለኦሮሞ ልሂቃን የምጋብዘው ጽሑፍ
                                            ነፃነት ዘለቀ (netsanetz28@gmail.com)

ይህችን ማስታወሻ ጽፌ የላክኋት ትናንት እሁድ የካቲት 3 ቀን 2011ዓ.ም ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ስንቅሪጦችን (insertions) ማስገባት እንዳለብኝ ዛሬ ተረዳሁና አስተካክዬ እንደገና ላክኋት፡፡ ባለፈው ሰሞን ስለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አይሆኑ እየሆነ መምጣት መክተቤም ይታወሳል፡፡ ዛሬ ሌሊት በሣተናው ድረገጽ ላይ ሳነብ ደግሞ ያንን መረጃ የሚያጠናክር አዲስ ነገር አየሁ (https://www.satenaw.com/amharic/archives/63435) - ሁኔታዎች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ናቸው፤ ያስጨንቃል፡፡ ይህን በሚመለከትም ጉዳዩ የሚመለከታችሁ በተለይም የኦሮሞ አክቲቪስቶችና ምሁራን ሁኔታው በአፋጣኝ እንዲስተካከል የበኩላችሁን ጥረት ታደርጉ ዘንድ የዜግነት ጥሪየን በዚህ አጋጣሚ አቀርባለሁ፡፡ የኔን ጽሑፍ ማንበብ የሚፈልግ “በዘረኝነት ጦስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ባፍጢሙ ሊደፋ ነው!” በሚል ርዕስ ገብቶ ከሁነኛ ድረገፆች ማንበብ ይቻላል፡፡ ማንኛቸው እንደተናገሩት ማስታወስ አልችልም እንጂ ከወያኔዎች አንዱ - ቀደም ሲል - “እኛ ይህችን አገር ማስተዳደር ካልቻልን ለኦሮሞ አሳልፈን እንሰጥና እርስ በርሳቸው (አማራና ኦሮሞን ማለት ነው) አባልተናቸው ወደ ትግራይ እንሄዳለን” ማለቱ ተዘግቧል፡፡ ያ ጊዜ አሁን በትክክል እንደመጣ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል፡፡ ዋናው መፍትሔ በታቀደልን መሠረት እንባላ ወይንስ ቆም ብለን በማሰብ ለሁላችን የሚሆን የጋራ ምቹ ሁኔታን እንፍጠር የሚለው ነው፡፡ በቀላሉ አትዩት፡፡ እነሱ ባቀዱት መንገድ ወደ ትግራይ መሄድ አለመሄዳቸውን አንድዬ የሚያውቀው ሆኖ ባሰቡትም ሆነ ባላሰቡት መንገድ ትንቢታቸው እየተፈጸመ ይመስላል፡፡ ስለዚህ ይህ አዲሱ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ችላ ባይባል መልካም ነው - ለሁላችንም ደኅንነት ሲባል፡፡ የልደት ቀን እንዳለ የሞትም አለ፤ የመደሰት ቀን እንዳለ የማዘንም አለ፤ “የጨው ተራራ ሲናድ ብልኅ ያለቅስ ፣ ሞኝ ይስቅ” እንዲሉ በምናየው ወንዝ የማያሻር አልባሌ ነገር ሁሉ ጥቂት የማንባል ዜጎች ውስጣችን እየደማ እንገኛለን፡፡ ….

የቀደመውን ጽሑፌን ለማየት የሚፈልግ በርዕሱ አጋዥነት እነዚህን ድረገፆች መጎብኘት ይችላል - satenaw.com, welkait.com, ethiolion.com, ethioexplorer.com, ethioreference.com, ethioforum.com.

ይህን ዘመን ዝም ካሉት ሁላችንም በአንድ ወይ በሌላ ምክንያት ተቆራርጠን መቅረታችን ነው፡፡ ለደቂቃዎች ብንጠፋፋ ዓመት የተለያየን የምንመስል የነበርነው የዘሀበሻው ሄኖክ ዓለማየሁና እኔ እንኳን ይሄውና በቁርጥ “ከተጣላን” ድፍን አምስት ወር ተኩል ሊሆነን ምንም አልቀረንም፡፡ ይሄ ዘር የሚሉት የሰይጣን ትክል ለካንስ ይህን ያህል ወራዳና ብስብስ ኖሯል! እደግመዋለሁ - ወራዳና ብስብስ ያለ ብስብስ ነው! ወያኔን ምሥጋን ይንሳውና እንኳንስ በአካል የማንተዋወቅን የአንዲት ሀገር ዜጎች ይቅርና ይህ ዘመን እኮ አባትንና ልጅን፣ እናትንና ልጅን እኮ በዘር ምክንያት አባልቷል፤ አለያይቷል - አሁን እዚህ ማስታወሱ ተገቢና ገምቢ አይደለም እንጂ - ወያኔ በገባ ሰሞን - በዘረኝነት የወረት ፍቅር ያበደች አንዲት ትግሬ ከአንድ ወሎዬ አማራ የወለደችውን ሕጻን ሽንት ቤት ውስጥ ጨምራ ገድላለች - (ቀድሞ ነገር ማን ከርሱ ጋር ተኝ አላት በል)፡፡ ዘረኝነት ማለት ዐይንንም፣ ኅሊናንም፣ አእምሮንም፣ በጥቅሉ ሁለመናን የሚያሣውር መጥፎ በሽታ ነው -  በኔ ግምትና የእስካሁን ግንዛቤ ይህ በሽታ መድኃኒቱ ሞት ወይም በአንዳንዶች ላይ እንዳስተዋልኩት በእርጅና ዘመን አካባቢ ሊመጣ የሚችል ጸጸት ብቻ ነው - የጸጸት ዋጋ ደግሞ ትንሽ ነው ወይም ከናካቴው ምንም ዋጋ ላይኖረውም ይችላል፡፡ “ባልገጨሁት ባልሞተ” ብትል መግጨትህንም ገጭተህ መግደልህንም ስለማያስቀረው ጸጸትህ ከንቱ ነው፡፡ … ፍቅር በበዛበት ጠብም ትበዛለች … ወንድሜ ሄኖክ ወያኔ ትግሬዎችን ጥምብ እርኩሳቸውን ሳወጣ፣ የክት ስድቤንና ትችቴን ከየኮረጆየ ያለአንዳች ስስት እየመዠረጥኩ በነገር ጦር እንዳይሸጡ እንዳይለወጡ አድርጌ ስወርፍ ከአፌ እየነጠቀ በድረገጹ ይለጥፍ እንዳልነበር ዛሬ የነካውን እንጃ እንደ አብርሃ በላይና እንደነስም አይጠሬ አንዳንድ ሞገደኛ “የዴሞክራሲ ጠበቃ ሚዲያዎች” አሽቀንጥሮ ጣለኝ - ስጠረጥር ግን ይህ አዝማሚያ የተከሰተው ከነዚህ አሥርና ዘጠኝ ወራት ወዲህ በመጣብን አዲስ የዘረኝነት ልምሻ መሆን አለበት - ይቺ “ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ ትወጋ” የሚሏት ነገር ኢትዮጵያ ላይ ድንኳኗን ደኩና እየተጫወተችብን ናት - ትናንት በውስጥ ተደብቆ የነበረ dormant volcano of racism ዛሬ active volcano ይሆንና በብርቱ ያስቸግረን ይዟል፡፡ በዚህች ደዌ እየተለከፈ ስንቱ ትልቅ ሰው ትንሽ ሆነ መሰላችሁ! የምትገርም ማግኔት ናት ወንድሞቼ፡፡ እኔን ቀልበቢስ ሞነጫጫሪውን ብቻ ሳይሆን ግርማ ካሣንና መስከረም አበራን የመሰሉ ግሩም ጸሐፊዎችን ሁሉ ጥርቅም አድርጎ በ15 ነጥብ 9 ቁጥር ምስማር ዘግቷቸዋል፡፡ እስካሁን ያወጣልን የነበረው እርሱ የሚፈልገው ሀገራዊ ምስል እስኪከሰት እንደመናጆ ቆጥሮን ነበር ማለት ነው፡፡ ይሁን፡፡ ይህም ተራውን ጠብቆ ያልፋል፡፡ “ያልፋል” ብለን ያላለፈ ባለመኖሩ በዚህ አቋምም አናፍርም፡፡ ደግሞም ሰው ነውና አይፈረድበትም፡፡ በወዳጅነታችን የምንቀጥልበት ሌላ አዲስ ዘመን መምጣቱ ስለማይቀር ልፋቱን ሁሉ በነዚህ አሥር ወሮች ምክንያት አንሰርዝም፡፡ የሆነውንና እየሆነ ያለውን መናገር ግን አስፈላጊና ተገቢም ነው፡፡ መተፋፈር የለም፡፡ ለምኑ ተብሎ?

በነገራችን ላይ የአዲሱ የዘረኝነት ቅኝት ጓደኛሞችን ሳይቀር እያናቆረ ነው፡፡ ዛሬ ጧት የሰማሁትን ሹክ ልበላችሁ፡፡ አንድ ሠርግ ላይ ነው፡፡ ትናንትና ማታ፡፡ እሁድ የካቲት 3 ቀን 2011 ዓ.ም፡፡ ልጆቻቸው በአንድ የሚማሩና የሚያጠኑ፣ እነሱም ልጆቻቸውም እንደአህያ ጡት የማይነጣጠሉ አንድ ኦሮሞና አንድ ራያ በሠርጉ ታድመዋል፡፡ ሞቅታ እየጨመረ ሲሄድ ኦሮሞው በራያው ላይ ዘረኝነትን የተንተራሰ የነገር ዶፍ ያወርድበት ገባ፡፡ መብሰልና ማስተዋል ደግ ነውና ያ ራያ በአዲስ የጎሠኝነት ወረት የሚያጓራውን ጓደኛውን ችላ በማለት ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ ብዙ ችግር ሊደርስ ሲል ሰዎች ጣልቃ ገብተው ለማብረድ ሞከሩ፡፡ የተነጋሩትን እዚህ መናገር ስላልፈለግሁ ትቸዋለሁ፡፡

እናም እባካችሁን ወገኖቼ ጊዜያችሁ “የመጣ”ም፣ ጊዜያችሁ “ያለፈ”ም፣ ገና ጊዜ ይመጣልናል ብላችሁ በተስፋና በጉጉት የምትጠባበቁም ሁለ ነገራችሁን በአግባቡ ያዙት - ብትችሉ ሰው ሁኑ፤ እንደሰውም ለማሰብ ሞክሩ - በጊዜና በሁኔታ የሚንሸራተት ስብዕና አይኑራችሁ፡፡ ሁሉም ቀሪ ነው፡፡ ይህች ምድር የስደት ሥፍራ እንጂ በአንድ ወይ በሌላ ጠፊ ነገር ልንኮራባትና ልንኮፈስባት የምንችልባት አይደለችም፡፡ ሥልጣን አላፊ ነው፤ መልክና ውበት ረጋፊ ነው፤ ሀብትን የኪሣራና የዕዳ ብል ይበላዋል፡፡ ዕድሜም ያረጃል፤ ሞትንም ተሸክመነው የምንዞረው ወንድማችን ነው፡፡ ለዚህች እንደጤዛ ለምትረግፍና እንደጉም ለምትበን ምድር ብለን ታዲያ በወገናችን ላይ ለምን እንጨክናለን? በጊዜ አመጣሽ ነገሮች ቀላልነታችንን እያወጣን አንዋረድ፡፡ ጥጋብንና ዕብሪትን በቅጡ ያልያዘ ሰው ብዙ ርቀት አይጓዝም፡፡ እንደጎማ ይተነፍሳል፡፡ ይዋረዳል፡፡ ይቀላል፡፡ በቅጡ ያልተያዘ ማግኘትና ማጣት ሰውን ትዝብት ውስጥ ይከታል - በትንሹ ሊያውም፡፡ አለበለዚያ ለጥጋበኛ ጥጋበኛን መላክ የማይሳነው ፈጣሪ ይዋል ይደር እንጂ እርሱንም የሚያንቆራጥጥ ሌላ ጥጋበኛ ወይም ፍርድ አስተካካይ ይልክበታል፡፡ ከምናየው ካልተማርን በውነቱ ሞኞች ነን፡፡ ከዚህ ነጥብ አኳያ አስተዋይነት የጎደላቸው ብዙ ጥጋበኛ ባለጊዜዎችን እየታዘብን ነውና ለራሳችሁና ለቀሪ ቤተሰባችሁ ስትሉ ጥጋባችሁን በልክ እንድትይዙት አደራ እንላለን፡፡ ሻል ያለ አስተሳሰብ ያላችሁ የየጎሣው ወገኖችም ምከሯቸው - በፍጹም አያዋጣም፡፡ መለስ እንደዚያ በቁሙ ተፈረካክሶ የሞተው በጥጋቡና በዕብሪቱ ሳቢያ መሆኑን አንርሳ፡፡ የበረከት ስምዖን ጥጋብና ዕብሪት ባህር ዳር ላይ “ኢንተርኔት እንዲናፍቀው” አድርጎታል፡፡ ገና ምን ታየና ደግሞስ!

ከፍ ሲል ወደጀመርኩት ተመለስኩ፡፡ እንደአጠቃላይ አውነት ከሆነ ጆሮዋችን መስማት የሚፈልገውን ብቻ እንዲሰማ ካደረግን፣ ዐይናችን ማየት የሚፈልገውን ብቻ እንዲያይ ከፈቀድን፣ አንጎላችን ማሰብ የምንፈልገውን ብቻ እንዲያስብ ካስገደድንና መሬት ላይ የፈጠጠውን እውነት ከካድን የሁለት ጌቶች ባርያ ሆን፡፡ እንደፈረንጆቹም በ double standard አራማጅነት ታወቅን፡፡ ለሆዳችን አደርን፡፡ እውነትን ጠላን፡፡ ለሚጠፋ ነገር ሰገድን፡፡ ስብዕናችንን አጣብቂኝ ውስጥ ከተትን፡፡….

በነገራችን ላይ ዘረኝነትና የፍየል ሥጋ አንድ ናቸው፡፡

የፍየል ሥጋ ሁሉም ሰው እኩል አይመገበውም፡፡ በሽተኞች ይጠነቀቃሉ፡፡ ምክንያቱም የፍየል ሥጋ የሚበላ ሰው የውስጥ ህመሙን ሁሉ ይበረብረውና ገሃድ ያወጣበታል - ፍየል የማትበላው ነገር ስለሌላት - ይገርማችኋል እባብን ጭምር - ይህ ነገር ከዚያ ይመነጫል የሚሉ አሉ - በሌላም በኩል ፍየልን ከሰይጣን ጋር ስለሚያመሳስሏት ከዚያም አኳያ የሚያያይዙት ወገኖች አሉ - ብቻ የፍየል ሥጋ የተደበቀን በሽታ ሳይቀር ይቀሰቅሳል፡፡፡ ስለዚህም የፍየልን ሥጋ የሚበላ ሰው የሠራ አካላቱ ጤና መሆኑን መፈተሸ አለበት፡፡ አለበለዚያ ጠቅሞ ላይጠቅመው ነገረኛ ሥጋ በልቶ ለበሽታ ሊዳረግ ይችላል - እንደኔ አነሳስ ለትዝትብም፡፡ ፖለቲካችንም የፍየል ሥጋ ሆና! ሆ!

አዎ፣ “የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ” ነው ነገሩ፡፡ አዎ፣ “ያንተ ልጅ የኔን ልጅ መትቶት ከሆነ ምች ይምታው፤ የኔ ልጅ ያንተን ልጅ መትቶት ከሆነ ግን መቼም…” እንዲሉ እየሆነ ነው ነገሩ፡፡ አዎ፣ “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነው” አካሄዳችን ሁሉ፡፡ አዎ፣ “የኔ ባል ካንቺ ባል ይበልጣልና ሽሮ አበድሪኝ” እንዲሉ ነው እማዎች፡፡ በርግጥ ምን ዓይነት የዘመን ሙጣጭ ውስጥ ገባን? እንዲህ ፍርክስክሳችን የወጣው የዱሮ አባት እናቶቻችን እንዴት አድርገው ፈጣሪን ቢያስቀይሙት ይሆን?...

አብርሃ በላይ ስለትግሬ በጨረፍታም ቢሆን ከነካህ ጽሑፍህን የጎሪጥ ያይብሃል  - መለጠፉ ይቅርና፡፡ ግንቦት ሰባትንና የወቅቱን ፖለቲካ ከነቀፍክ ወይም እየሆነ ያለውን ከተነፈስክ ኢካድፍ ከንፈሩን ይነክስብሃል - መለጠፉን ተወውና፡፡ ኦሮሞንና በፊንፊኔ ፍቅር ያበዱትን እነታከለ ኡማን መንካት አይደለም አሉታዊ በሆነ መንገድ በተዛዋሪም ቢሆን ጠቀስ ካደረግህ ዘሀበሻ ጀርባውን ይሰጥሃል፡፡ አማራን ከነካህ የአማራነት ፍቅር ከኢትዮጵያዊነትና ከሰውነት ደረጃ የሚበልጥባቸው አዲስ ግልብጦች ይፎክሩብሃል (ስላልተነሳሁበት እንጂ አማራን ሊነገር የሚሰቀጥጥ መስዋዕትነት ከከፈለበት ኢትዮጵያዊነት ለመለየት የሚደረገውን ጥረት በአዲስ ወያኔነት እንደምፈርጀው በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እወዳለሁ፤ አያዋጣም፤ አማራን የጎሣ ከረጢት ውስጥ መክተት የማይቻል መሆኑን ብረዳም ሙከራው ግን ጥቂቶችንም ቢሆን ማሳቱና ማሳሳቱ አይቀርምና በዚህ ረገድ ጥንቃቄ ይደረግ)፡፡ ሕወሓትን ከነካህ - ያው አንዴውኑ ተነክቶና ተነካክቶ መዘረሩ ወይም የተዘረረ መምሰሉ በጄ እንጂ - ምድረ ወያኔ በየአይጋፎረሙና በየትግራይኦንላይኑ ይንጫጫብሃል፡፡ ሁሉንም በአንዴ ማስደሰት ዶሞ አትችልም፡፡ ጨለማንና ብርሃንን ለማቀላቀል የሞከረችው ብቸኛዋ ፃዲቅ ሴት ክርስቶስ ሠምራ ናት፡፡ ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ላስታርቅ ብላ ስትነሳ - እርሱም ሀሰት ይሁን እውነት አላውቅም፡፡ በኛ ሁኔታ ግን አንዱን ስታወደስ ሌላው ያበሻቅጥሃል፤ አንዱን ድርጅት ስትሄስ ነፈዝ ደጋፊው በስድብ ያጥረገርግሃል፡፡ ተቸገርነ፡፡ No politics of any nation on this bloody planet is more polarized than that of ours now. በለበጣ የሚያስቀውና እጅጉን የሚገርመው ደ’ሞ ሁሉም እየተነሣ “ዴሞክራሲ፣ ዴሞክራሲ” እያለ በዴሞክራሲ ስም ሲቀልድ ቅንጣት አያፍርም፡፡ ቃሊቱን የቃቃ መጫወቻ አደረጓት፡፡ ዴሞክራሲ ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ እንዳልሆነ የምዕራቡንና የአውሮፓን ዴሞክራሲ በማየት መረዳት ይቻላል፡፡

ለነገሩ ዴሞክራሲ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ አይችልም፡፡ ምን ቅብጥ አድርጎት? ዱሮም ዱሮ ነን - አሁንማ አንድ ሁለት ቃል ከመነጋገራችን “አሃ! ከምዚ ዝብለኒ ዘሎ ትግራዋይ ስለዝሆንኩ እምበር…?”፣ “አሃ፣ እንዲህ የሚለኝ አማራ ስለሆንኩ አይዶል እንዴ…?”፣ “አካሲሚቲ! ሲላ ኦሮሞ ታኤቲ …?” እየተባባልን ከእንስሳትም ባሕርይ በወረደና እጅግ ባፈነገጠ ሁኔታ እየተመነቃቀርን እንገኛለን፡፡ መልካምን ነገር በባዶ መሬት ቢመኙት ጠብ የሚል ነገር የለም፡፡ አታሟርትብን የሚለኝ ካለ እርሱ ማኅበረሰብኣዊ እውነቱን እንዳያይ ሌሎች ሰዎች ጋርደውበት ወይም ቁሣዊ ሕይወቱ በቦሌና በባሌ ተመቻችቶለት በተመሳስሎ የድሎት ግርዶሽ ዐይኑ የተሸፈነበት ግልብ ወገን ነው፡፡ እንጂ ሀገራችን በአሁኑ ቅጽበት ቤንዚን ተርከፍክፎበት ክብሪት የተጫረበት ደን መሆኗን ለመረዳት ሌላው ቀርቶ የታከለ ኡማ መንግሥት በአሁኑ ወቅት የሚሠራቸውን አዲስ አበባን በአዲሱ ቋንቋ oromize የማድረግ የ24/7 አጣዳፊ ተግባር መታዘብ ከበቂ በላይ ነው፡፡ ደግነቱ ግን ይህም ልክ እንደወያኔዎቹ ሁሉ ብዙ አይዘልቅም፡፡ የነዚህም ዕኩይ ተግባር ወረት በአጭር ጊዜ ይቀጫል፡፡ ኢትዮጵያን እየጠበቃት ያለውን ኃይል ያለመረዳት ችግር ነው ሰዎችን ወደዚህ ዓይነት ብልጥነትን ማዕከል ያደረገ ጅልነት እየከተታቸው የሚገኘው - ከወያኔ የማይማር መቼም የመጨረሻው ደንቆሮ መሆን አለበት፡፡ እንጂ መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ከዓለም አቀፉ የሤረኞች ኅቡዕ ኃይል ጋር ተባብረው ማጥፋት ያልቻሏትን ሀገር ዛሬ ጃዋርና ታከለ ያጠፏታል ብሎ ማሰብ በትንሹ የዋህነት ነው - ብዙ ቡልሃ አለ - ኢትዮጵያን ከደራጎኑ የወያኔ ፈርዖናዊ አገዛዝ ነፃ ያወጣው ቄሮና አቢይ ወይም እነጃዋር ናቸው ብሎ የሚያምን ብዙ ጅል አለ - ይገርመኛል፡፡ እነዚህ ከማን አንሼዎች የሚከናቱት ክፍተት ያገኙ መስሏቸው ነው፡፡ ወያኔም እኮ ይህን መሰል ክፍተት ነው የተጠቀመችው፡፡ ከላይ የተላከው በአካል እስኪከሰት እንዲህ ያለ የሽግግር ሁከት የሚጠበቅና ያለም ነው፡፡

እርግጥ ነው - እንዲህ ያለው አካሄድ የተወሰነ ጉዳት ላልተወሰነ ጊዜ ማስከተሉ አይቀርም፡፡ ሰዎች መፈናቀላቸውና ሀብትና ንብረት ማጣታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ በሀገረ አሜሪካ - ሰለጠነ በሚባለው ዓለም ውስጥ አምስት ዓመት ተኑሮ ስንትና ስንት ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረት ማፍራትና ከፕሬዝደንትነት ቦታ ውጪ - እርሱም እዚያው መወለድን ስለሚጠይቅ እንጂ በቀለምና በዘር አይደለም - ከዚህ የኃላፊነት ሥፍራ ውጪ ባሉ የሥልጣን ቦታዎች ተመርጦ ወይ ተመድቦ ማገልገል በሚቻልበት ሁኔታ እኔ 40 ዓመት በኖርኩባት ከተማ መጤ ከተባልኩ በጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ መመዝገብና ለወደፊቷ ዓለማችን መሣቂያነት መብቃት አለበት - አሁንማ መሣቂያ መች ጠፋና - ሞልቶ! … ዶሮ መሬት ስትጭር ብዙ ነገር ታወጣለች - ስለዚህ ብዙ መጫር ላይኖርባት ነው፤ “በቀላሉ ጭራ መኖር ስትችል ለምንስ ብዙ መጫር አስፈለጋት?” ብሎ መጠየቅም ሞኝነት አይደለም፡፡ ለማንኛውም ግን ይቺ የወያኔ አካሄድ ለማንም አትጠቅምም፡፡

“ፍቅር ያዘኝ ብለህ አትበል ደምበር ገተር፤
እኛም አንድ ሰሞን እንዲህ አ’ርጎን ነበር”   ብላ አቀንቅናለች ‹አብረኸት ባራኺ› ነፍሷን ይማረውና፡፡ (ሞታለች እንዴ ግን?)


ዴሞክራሲና ሃሳብን በነፃነት መግለጽ እንግዲህ እንደዚህ ነው፡፡ ለራስህ ሲሆን እስከፑንት - ለሌሎች ሲሆን አንድያውን ጥርቅም! ወይም በመለኪያና በመቁነን - እንደገዳም ሬሽን፡፡ አየ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን! ከስደትና በስደት እንኳን ምንም የማንማር ግትሮች፡፡

እኔ ደግሞ እላለሁ - አንድ ሰው የሚናገረው እውነት እስከሆነ ድረስ - እውነት ባይሆን እንኳን በተሳሳተ መረጃ ምክንያት የመሰለውን ግን ለጦርነትና ለዐመፅ የማይጋብዝ ሃሳብ እስከተናገረ ወይ እስከጻፈ ድረስ ሃሳብን በሃሳብ መሞገት እንጂ ማፈን ወይም ባልተመጣጠነ መሣሪያ ወግቶ በሚገኝ ድል መቦረቅ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ባደጉ ሀገሮች መሪዎቻቸውን በጦጣና በዝንጀሮ፣ ሲፈልጉ በውሻና በጉማሬ እየመሰሉ ቢያወጡ ማንም ዝምባቸውን እሽ የሚላቸው የለም (እኛ ጋ እኮ ወዲያውኑ ማምለክ ወይም በሰይጣንነት ፈርጆ ማውገዝ እንጂ ማስተዋል ብሎ ነገር አልፈጠረብንም፤ አሁን አቢይን በትችት መልክ ተስቶህ ወይም አምነህበት ትንሽ ብትነካ … ኧሯሯ… ይወርዱብሃልኝ፡፡) ባደጉ ሀገሮች ሰዎች እላፊ ቢናገሩ እንኳን አበዱ ተብለው በአንባቢዎች ይተቻሉ እንጂ እነሱን እየተከተለ ጊዜውን የሚያጠፋ መንግሥታዊም ሆነ ግላዊ አካል ያለ አይመስለኝም፡፡ የኛ ሀገር እኮ የተለዬ ነው፡፡ ሁሉም ስላንተ እርሱ ነው የሚያውቅልህ፡፡ ሁሉም ምርጫህን እርሱ ነው የሚወስንልህ፡፡ የቤቢሲተሩ (babysitter) ብዛት ከቁጥር በላይ ነው፡፡ መንግሥት  ቤቢሲተር ነው፤ ተቃዋሚዎች ቤቢሲተር(ስ?) ናቸው፤ ጋዜጠኞች ቤቢሲተር ናቸው፤ ባለድረገፆች ቤቢሲተር ናቸው፤ ሁሉም እንዳልል ጥቂቶች ስለሚጨፈለቁብኝ ፈርቼ እንጂ አብዛኛው የግልም ሆነ የመንግሥት ሚዲያ ቤቢሲተር ነው፤ ታዋቂ ግለሰቦች ቤቢሲተር ናቸው፤ ነጋዴው ቤቢሰተር ነው፤ ሀኪሙ ቤቢሲተር ነው (ራስህን አሞህ እግርህን ሊያክምህ የሚጎነበስ እኮ አለ - ብትነግረውም በትዕቢት ተወጥሮ የማይሰማህ)፤ … እኛ እንግዲህ የት እንግባ? የዚህ ሁኔታ ምንጭ ሕዝብን መናቅ ነው፤ ሕዝብን ምርጫ እንደሌለው ባዶ ጭንቅላት (ነጮቹ ታቡላ ራዛ የሚሉት) እንደሆነ አድርጎ የመቁጠርና ራስን ሰማየ ሰማያት የመስቀል ልክፍት ነው፡፡ የሚገርም ሀገራዊ ቋሚ ልክፍት፡፡ ሕዝብ አያውቅም ካልን እንዲያውቅ መንገዶችን ማመቻቸት ነው፤ ትምህርትን በጥራት መስጠት ነው፤ የንቃተ ኅሊና ማሳደጊያ ማዕከላትን ማቋቋምና በሁሉም ረገድ መደገፍ ነው፡፡ ሕዝብን የማብቃት ሥራ መሥራት ነው፡፡ ራስንም ከሙስናና ከዘረኝነት ማጽዳት፣ በዕውቀትና ችሎታም ማነጽ ነው፡፡ …. በዚህ መልክ መቀጠሉ ግን ወደ ገደል መጓዝ ነው፡፡

እንግዲህ ስለኛ የሚገርም ጉዳይ ይችን ታህል ከተነፈስኩ በቃኝ፡፡ ግን ከጀርባቸውም ሆነ ከፊት ለፊታቸው ምንም ዓይነት ቁስል የሌለባቸው (የሚመስሉኝ - ቢያንስ)፣ ከፊትም ሆነ ከኋላ ገራፊና ተቆጣጣሪ ያልተመደበባቸው፣ ለእንጀራ ሲሉ የዴሞክራሲን ባህል እንደሸቀጥ ዋጋ የማያወጡና የማያወርዱ፣ በዘር ልክፍትም የማይሰቃዩ፣ ሙያን በእንጀራ የማይለውጡ፣ ዴሞክራሲን ለመተሻሻነትና ለመሞዳሞጃነት ወይም ለመመሳሰል ሲሉ የቃሉን ፍቺ በመዘንጋት ራሳቸውን ለትዝብት የማይዳርጉ እነ እንትናን የመሰሉ ግለሰቦችና ድረገፆች እንዳሉ በዚህ አጋጣሚ መናገር ተገቢ ነው - ማስታወቂያ እንዳይመስልብኝ ለጊዜው ስማቸውን መናገር አልፈለግም፡፡ እንጂ ወላድ በድባብ ትሂድ አሉ፡፡ በነገው ቀን የማያሳፍሩን ለፈይሣ የማይሉ፣ ለአምባቸው የማይሉ፣ ለፍትዊ የማይሉ፣ ዘበርጋ ሲነሳ ወከክ የማይሉ፣ ግምብወግሽ ስትጠራ ፊታቸውን ኮሶ የማያስመሰሉ፣ …. ጥቂትም ቢሆኑ ለኅሊናቸው ያደሩ አሉን - በምድረ በዳው ጉዟችን ጉልበታችን እንዳይዝል የሚያበረታቱንና ተስፋ የሚሆኑን፤ በበረሃማው ጠመዝማዛ መንገዳችን ምንጭ ሆነው የውኃ ጥማታችንን የሚያስታግሱልን - በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የብርሃን መቅረዝ የሚሆኑን እጅግ ጥቂት ሻማዎች አሉን - እግዚአብሔር እነሱን ያብዛልን፤ ከሀሰተኛና አስመሳይ ነቢያት፣ ጊዜ እየጠበቁ በዚህ ወይ በዚያ ሰበብ-አስባብ ከሚከዱን ግን ይጠብቀን፡፡ የዛሬው ማፈሪያ ታሪካችን በነገው ዕለት ሲለወጥ - የድል አጥቢያ አርበኛው ቢበዛና በዚያም ሥርዓት እንደእስስት ዐመልን ቀይሮ ማስቸገሩን ቢቀጥልም - ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ተገቢ ክብራቸውን ያገኛሉ፡፡ ዛሬ የተጎሳቆሉ፣ ኑሮና ሕይወታቸውን ለማሻሻል ሲሉ ሕዝባዊውን የሀገር ትንሣኤ ዓላማና ትግል እንደኢሣው በጭብጥ ምሥር ያልለወጡ ወገኖቻችን ይህችን ሀገር ከፈጣሪ እጅ ተረክበው እንደገና የዓለም ቁንጮ ያደርጓታል፡፡ ከሥር የነበረ ቁንጮ ቢሆን ያስደስታል የፈጣሪን ፍርድ ትክክለኝነትም ያሳያል  እንጂ አያስከፋም፤ ትዕቢተኛና ትምክህተኛም አያስብልም - የቀኝ ኋላ ዙር አንዱ ትርጉምም ይሄው ነውና! መጽሐፉስ “ፊተኞች ኋለኞች፤ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ” ይል የለምን?
Posted at Ethio Semay

Wednesday, February 6, 2019

የችግሩ ፈጣሪዎች የመፍትሔው አካል መሆን እንዴት ይችላሉ? በነዚህ ሰዎችስ ዕውነተኛ የአገሪቱ ችግሮች መፍትሔ ያገኛል ወይ? Ethio Semay

ከኢትዮ ሰማይ ዝግጅት ክፍል ማስታወሻ፦
ለአብይ አህመድ ተከታዮች፦
መሪያችሁ የአብይ አህመድ፤ የኦነግ እና የወያኔ ጥምር ሴራ ዛሬ “እነ ሌንጮን እና እነ ነጋሶ ጊዳዳን የመሳሰሉ የሰሩትን ወንጀል ሰይጠየቁበት” በድጋሚ ሌላ ሴራ ለመስራት ተፈቅዶላቸዋል። ቀደም ብየ ከሦት አራት አመታት በፊት በግልጽ እንደጻፍኩት “የኦሮሞ ፋሺታዊ ስርወ-መንግሥት ሦሰተኛውን የመሬት እና የሥልጣን ሽሚያቸው ይፋ ለማድርግ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀውታል” በማለት ስለ ኦሮሞና ትግሬዎች ጥምር ፋሺስታዊ ስርወ-መንግስት ሰፊ ሐተታ ደጋግሜ መጻፌ ይታወሳል። ዛሬም ኦሮሞዎች ከትግሬ ፋሺሰቶች ጋር በጣምራ ያቀዱት ‘የመሬትና የሥልጣን ወረራ’ ፤ ኦሮሞዎች በይዞታቸው ስር ያደረጉትን የመላ የኢትዮጵያ ዜጎች 3/4ኛውን የመሬት ወረራቸውን ለማስጠበቅ በአብይ እና በለማ አማራር ለማስጠበቅ በርትተው እየሰሩ ነው። ከአራት አመት በፊት (ከዚያም ከ10 አመት በፊት) የተነበይኩትን “ኦሮሞዊ አጀንዳቸው” እውን ለማድረግ እንዲመቻቸው የናንተንም  የወደፊት ዕጣ ፈንታችሁን መንግዱን ለመቀየስ ከላይ የተጠቀሱ ሰዎች በናንተ ስም “የአብይ አህመድ እርካብ” ፈቅዶላቸዋል።
 እጃቸው በሰው ልጆች ደም የተጨማለቁ ሰዎች እና አልፈውም የትግሬዎች የፋሺሰት አፓርታይድ ሥርዓትን በፕረዚዳንትት ያገለገሉ ሐፈት ምን እንደሆነ የማይሰማቸው ማፈሪያዎች ዛሬም በድጋሜ ወደ መድረክ ብቅ ብለው በሕዝብ እርካብ ላይ ተንጠላጥለው ማየት እጅግ ያማል። ለማንኛውም ከታች የቀረበው ሰነድ አንብቡና የኦሮሞዊው አብይ አህመድ “ኢትዮጵያዊነት ዲስኩር” ጣፋጭነት ስካራችሁ ሲለቃችሁ ይህንን ሰነድ አንብቡ።

ኢትዮ- ሰማይ

                                                                                      
ጥር 28 ቀን 2011 ዓም
የችግሩ ፈጣሪዎች የመፍትሔው አካል መሆን  እንዴት ይችላሉ? በነዚህ ሰዎችስ ዕውነተኛ የአገሪቱ ችግሮች መፍትሔ ያገኛል ወይ?
      ይድረስ ለዐማራ ሕዝብ፣
      ይድረስ በዐማራ ስም ለተደራጃችሁ የፖለቲካና ሲቪክ ድርጅቶች፣
      ይድረስ ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣
      ይድረስ ለዶር ዐቢይ አሕመድ ``የኢፌዴሪ`` ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢሕአዴግ ሊቀመንበር፣
ጉዳዩ፦ የማንነትና የወሰን ጉዳዮችን እንዲያጠና የተቋቋመውን ኮሚሽን አባላት ማንነት ይመለከታል
 የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት፣የኦሮሞ ነፃ አውጭ ድርጅትና የኤርትራ ነፃ አውጭ ድርጅት የአገሪቱን ማዕከላዊ መንግሥት እና የአንድነት ኃይሉን እንዴት በታትነው፣ የጋራ ጠላታችን ነው  ያሉትን ዐማራ ከተቻላቸው ለማጥፋት፣ ካልሆነም ለማዳከም የሚያስችል የጋራ ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል። ይህ ስምምነታቸውም`` የተሰኔ ማንፌስቶ`` በመባል ይታወቃል። በዚህ ስምነት መሠረት ባካሄዱት የእርዳ ተራዳ የጥፋት ዘመቻ፣ ማዕከላዊ መንግሥትን አዳክመው ፣የአንድነት ኃይሉን በታትነው በ1983 ላይ ሻዕቢያ አሥመራን፣ ወያኔና አጋሮቹ ፀረ-ዐማራና ኢትዮጵያ የሆኑት ቡድኖች አዲስ አበባን መቆጣጠራቸው ግልጽ ነው።
እነዚህ ፀረ-ዐማራና ኢትዮጵያ የሆኑ ቡድኖች ለጥፋት ዘመናቸው መራዘም  የሚበጅ የሽግግር መንግሥት  የሚያዋቅርና መንግሥቱ የሚመራበት ቻርተር  የሚያጸድቅ፣ አብዛኛዎቹ በዚህ የማንነትና የወሰን ኮሚሽን በተባለው የተካተቱበት ሰዎች የተካፈሉበት ጉባዔ ሰኔ 24 ቀን 1983 በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ  ተሰየመ። ይህ ጉባዔ በመለስ ዜናዊ ተመርቶ፣ ቀደም ሲል በሦስቱ ፀረ-ዐማራና ኢትዮጵያ ቡድኖች የተስማሙበትን የተሰኔው ማንፌስቶ የተባለውን ለሥልጣን አወጣጥ፣ አጠባበቅና አያያዝ  እንዲሁም ኢትዮጵያንኢትዮጵያ ያሰኙት የወል ዕሴቶች ደረጃ በደረጃ ሊያከስም  በሚችል መልኩ በሕወሓት ተቃኝቶ የቀረበውን ሰነድ አንድም ማሻሻያ ሳይደረግበት የኢትዮጵያ ሕዝብ መገዣ እንዲሆን አጽቆ መነሳቱ አይዘነጋም። ይህን አገር ከፋፋይ፣ ፀረ-ዐማራና ኢትዮጵያ የሆነ ሰነድ ያዘጋጀው አቶ ሌንጮ ለታ መሆኑም ይታወቃል። ራሱ ሳያፍር በአደባባይ ያዘጋጀው እንደሆነ ነግሮናል።
የሽግግር ቻርተር የተባለው መገዣ፣ መረገጫና የዐማራና የኢትዮጵያ መጥፊያ መሣሪያ፣ ዳብሮ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊት ረፐብሊክ ሕገመንግሥት ሆኖ እስካሁን በማገልገል ላይ እንዳለ ከማንም የተሰወረ አይደለም። በሕወሓት ሁለተናዊ አመራር፣ በኦነግ ያልተቆጠብ የባለድርሻነት  ሁሉ አቀፍ ትብብር የተዘጋጁት የሽግግር ቻርተርና ሕገመንግሥት ተብየዎች፣ ይህም በሕዝቡ ላይ ባስከተለው የማንነት ረገጣ፣ የመሬት ነጠቃ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀሎች፣ የተፈጸሙ ኢሰባዊ ድርጊቶች፣ በአገሪቱና በሕዝቡ ኢኮኖሚ ላይ የተካሄደው ድርጅታዊ ምዝበራ፣ የፓርሪና የመንግሥት ፍፁም ውኅደት የወለደው ሌብነት ያስነሳው የቄሮ፣ የፋኖ እና የዘርማ እንዲሁም በውስጥና በውጭ የተጋጋመው የለውጥ ማዕበል፣ ከኢሕአዴግ ማዕቀፍ ውስጥ ዶር ዐቢይ አሕመድና ቡድናቸው ወደ አገሪቱ ፖለቲካ ቁንጮ እንዲዘልቁ  እንዳስቻላቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።
ዶ/ር ዐቢይና ቡድናቸው የኢሕአዴግ አባላትና አመራር ሰጭዎች በመሆን በአገሪቱ እና በሕዝቡ ላይ ለተፈጸመው ግፍና በደል ከሚጠየቁት  መካከ  እንደሆኑ በማመን፣ ሕዝቡ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው በይፋ በመጠየቅ፣ ላለፉት 27 ዓመታት ሆን ተብሎ እንዲጠፉ የተደረጉትን የኢትዮጵያዊነት አያያዥ ዕሴችን በማንሳት ፣አንድነት፣ ሃይማኖት፣ ዕኩልነት፣ መቻቻል፤ ይቅርታ፣ አብሮነት፣ ወዘተ የተባሉትን በመደመር ``ፍልስፍናቸው`` ሕዝቡ የሚሻውንና መሆን የሚፈልገውን በመናገሩ፣ የታሰሩትን በመፍታታቸው፣ የተሰደዱትን በመመለሳቸው፣ የመናገርና የመደራጀት ነፃነትን በመፍቀዳቸው፣ ለሀሳብ ልዕልና በመቆማቸው፣ የተበደለው ሕዝብ፣ ``እንባ ጠራጊ አገኘን``፣ ``ተነፈስን``፣ ``አንድ ሊያደርገን ነው``፣ ``ከፈርኦን ቤት ያደገ ሙሴ ነው``፣`` ከአምላክ የተሰጠን ፀጋ ነው`` በማለት ምላተ ሕዝቡና ተቃዋሚ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሞገሥና ክብርን እንዲያገኙ ከማድረጉም በላይ፣ ሁሉም መሪያችን ነው ብሎ መቀበሉን በቃል፣ በጽሑፍ እና በሰላማዊ ሰልፍ አረጋግጧል። ይህ ለዶር ዐቢይ እና ለቡድኑ ከሕዝብ የተሰጠ በረከት ከጊዜአዊነት ወደ ዘላቂነት እንዲሸጋገር፣ አመራሩ ከሀሳብ አፈላለቅ እስከ አፈጻጸም ድረስ የሕዝቡን ቀጥተኛ እና ኢቀጥተኛ ተሳትፎ ማሳደግ ተገቢ ብቻ ሳይሆን፣ የዲሞክራሲ ዋልታ ነው። ይህ ካልሆን ዶ/ር ዐቢይ `` እርካብና መንበር`` በሚለው መጽሐፋቸው፣ ``ሕዝብን ፍላጎቱን ተከትልህ ገደል ልትከተው ትችላለህ፤ አያ በሬ ሆይ፣ ሳሩና አየህን ገደሉን ሳታይ`` ሲሉ ያስፈሩት ሀሳብ፣ በዚህ የማንነትና የወሰን ኮሚሽን አባላት አመራረጥ ላይ በግልጽ የወጣ ይመስላል።
ማንም እንደሚገነዘበው፣የኢትዮጵያ ችግር የብሔረሰብም ሆነ የመደብ ጭቆና አይደለም። የአገሪቱ ችግር የመልካም አስተዳደር ችግር ነው። የአገሪቱና የሕዝቡ ተከታታይነት  የሌለው፣ የወል ዕሴቶች፣  ኢኮኖሚ፣ አስተዳደር፣ የአገዛዝ ፍልስፍና፣ የሕዝብ አደረጃጀት ወዘተ ነው። የዛሬው የኢትዮጵያ ችግር ቋጠሮም የመነጨው፣ ከተከታታይነት የወጣው የመንግሥት አደረጃጀትና በቋንቋላይ የተመሠረተው ፌደራላዊ አወቃቀር፣ አብሮነትን፣ አንድነትንና ኢትዮጵያዊ ማንነትን  በአውራ ጠላትነት ፈርጆ የተራመደው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የዓለም አመለካከት፣ ያስከተለው የማንነት ጥያቄና የመሬት ቅርምት መሆኑ ግልጽ ነው። የዚህ ሁሉ ምንጭ ደግሞ ሕገመንግሥቱ ነው።

ችግሩ ሕዝባዊ ማዕበልን አስነስቶ ለውጥን ወልዷል። ለውጡን  የሚመሩትን ደግሞ ሕዝቡ ከልቡ ወዷል። ተቀብሏል። ይህ ዕውነት ነው። ይህን ዕውነት ሥር እንዳይሰድ፣ ቅርጫፍ እንዳያወጣ፤ ግንዱ እንዳይደነድን የሚያደርጉ የራሱ የለውጡ ተፈጥሮአዊ ባሕሪይ ከፖለቲካውና ኢኮኖሚው የበላይነት ያሳጣቸውና ጥቅማቸውን የሚነካባቸው ቡድኖችና ግለሰቦች ከሚፈጥሩት መሰናክል ውጪ፣ በራሱ በለውጥ አመራር ውስጥ ፣ለውጥ አደናቃፊ የሆኑ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ጥብቅ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠይቃል።

ለዚህ አባባል መነሻ የሆነን፣ ለማንነትና ወሰን ኮሚሽ አባልነት የተመረጡት ሰዎች የአመራረጥ ሁኔታ  ሕዝቡ እንዲያውቅ አልተደረገም። የተመረጡበት መመዘኛ ምን እንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም። የሰዎቹ ያለፈ የፖለቲካ ታሪክ በበጎም ሆነ  መጥፎው ተመዝኖ ለዚህ ተግባር ብቁ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ የለም። በሕዝቡ ዘንድ ያላቸው ታማኒነትና ቅቡልነት እስከምን እንደሆነ አይታወቅም። እንዳውም አብዛኞቹ የችግሩ ፈጣሪዎች እንደሆኑ ሕዝቡ ያውቃል። እነርሱም አይክዱ። ሕዝቡ ዛሬ መሆን የሚሻውን ትክክለኛ የአንድነትና የአብሮነት ስሜት ዕውን እንዲሆን የማድረግ ቁርጠኝነታቸው እስከምን ሊሆን እንደሚችል ማረጋገጫ የለም። በተቃራኒው ሕዝቡ፣ በተለይም የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል የተፈጸመበት ዐማራ ``በጡት ቆራጭነት፣ በትምክህተኝነት፣ በመጤነት፣ በአድኃሪነትና በዝባዥነት`` ፈርጀው ዕልቂት የፈጸሙበትና ያስፈጽሙበትን ግለሰቦች በዚህ ኮሚሽን ውስጥ መካተት``ትናንት ጦምክን ያደርክ ዛሬም ድገም ብለውሃል`` ዓይነት እንደሚሆንበት መጠራጠር አይቻልም።  በማንነታቸው ከፍተኛ በደል የተፈጸመባቸው የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ሠቲት፣ ራያ፣ ደራ; መተከልና መሰል አውራጃና ወረዳዎች ሕዝብ ዕውነተኛ ጥያቄ ተገቢ መልስ ለማስገኘት ከሆነ የኮሚሽኑ መቋቋም ፋይዳ፣አረጋዊ በርሄ፣ ሌንጮ ለታ፣ ነጋሶ ጊዳዳ፣ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ሙላቱ ተሾመ፣ገብሩ ታረቀኝ፣ዘገየ አስፋው ቦታቸው ወይም አገልግሎታቸው ጠቃሚ የሚሆነው በዚህ ኮሚሽን ውስጥ ነው ብለን አናምንም። ለፍርድ ይቅረቡ እንኳን ባንል፣ ሊፈርዱብን ግን አይገባም። ችግሩን የፈጠሩት ሰዎች ለችግሩ መፍትሔ ያመጣሉ ብለንም አናምንም! ከእነዚህ ሰዎች አዕምሮ፣ በዐማራው ላይ የዘር ዕልቂት እንዲፈጸም ሀሳብ ያፈለቁ፣ ያቀዱ፣ የመሩና ተግባራዊ እንዲሆን ያደረጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች አመራር አባሎች፣ የሕዝቡን ቁስል የሚያጠግግ የመፍትሔ ሀሳብ ያመነጫሉ ብሎ ይቀበላቸዋል ማለት ``ሸንበቆ ያፈራል፣ ገለባ ያብባል`` ከማለት የተለየ አይሆንም፣

በሌላ በኩል የአገሪቱ ፖለቲካ የሚያጠነጥለው በማንነት እና በነገዶች ዙሪያ ነው። ይህ ባለበት ሁኔታ የማንነትና የወሰን አጥኝ ኮሚሽን አባላት መመረጥ ወይም መሰየም የነበረባቸው፦

 አንደኛ፦ አጣሪ ኮሚቴ ተሰይሞ በሕዝባችን በአብዛኛው በመልካም ሥነ-ምግባራቸው፣ በዕውቀታቸው፣ በችሎታቸው፣ከፖለቲካ ገለልተኛነታቸው፣የሚታወቁ ምሑራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እና የአገር ሽማግሌዎች መካከል በዕጩ ተወዳዳሪነት ቀርበው ምርጫው በግልጽ ወይም በሚስጢር በተወካዮች ምክር ቤት ቢመረጡ:

ሁለተኛ፦ አጠቃላይ የኮሚሽኑ አባላት ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ዘርዝሮ፣በአገሪቱ የጎሣ/ቋንቋ አስተዳደር ያሉት ምክር ቤቶች በወከሉት ሕዝብ መጠን ተሰልቶ ዘጠኙ ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች መርጠው ቢያሳቁና ምክር ቤቱ ተወያይቶ ቢያጸድቀው፣

ሦስተኛ፦በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት የፖቲካ፣ የሃይማኖት፣ የሲቪክና መሰል ድርጅቶች ለኮሚሽኑ ይጠቅማሉ ያሏቸውን አባሎች ለምክር ቤቱ አቅርበው ምክር ቤቱ ተወያይቶ ቢያጸድቃቸው የተሻለ ታማኒነት ከማትረፉም በላይ፣ ዘለቄታን ያሳይ ነበር። የዲሞክራሲ አንዱ መርሕ የሆነውንም የተሳትፎ ሁኔታ በተጨባጫ ማሳየት ያስችል ነበር።

በሌላ በኩል የማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛዎች እንደሚሉት ከሆነ ከኮሚሽኑ አባላት ውስጥ 20ው ኦሮሞች፣13 ትግሬዎች እንደሆኑና የቀሩት ከሌሎች ነገዶች እንደሆኑ ያስረዳሉ። ይህ ከሆነ የኮሚሽኑ የጥናት ውጤት የኦነግ  እና የሕወሓት ፍላጎት የበላይነቱን ይዞ እንደሚወጣ መናገር ነቢይ መሆንን አይጠይቅም። ምክንያቱም  የችግሩን ጉድጓድ አጥልቀው የቆፈሩት ሁለቱ ድርጅቶች በመሆናቸው ለዘመናት የታገሉለት የማንነት ፖለቲካ እና የቋንቋ  ፌደራሊዝም በሌላ እንዲተካ ይሻሉ ለማለት አይቻልም። ይህም ግልጽ አቋማቸው፣ ዶር መረራ ጉዲና፣ ዶር ብርሃኑ ነጋ፣ ዶር አረጋዊ በርሄ እና ዶር ዐቢይ አሕመድ `` ውይይት ስለኢትዮጵያ`` (Dialogue on Ethiopia) በሚል ርዕስ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ላንድ ቀን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቭል እና መሠል ድርጅቶች አመራሮች ጋር ባቀረቡት ጥናት ባብዛኛው አካዳሚካዊ ቢሆንም፣ ሕገመንግሥቱና የመንግሥቱ አደረጃጀት ችግር የለበትም፣ ችግሩ አመራሩ ዲሞክራሲያዊ አለመሆኑ ነው በማለት አቋማቸውን ገልጸዋል። ይህ ስብሰባ በተካሄደ ማግሥት የማንነትና የደንበር ኮሚሽ አባላት ይፋ መሆንና ፣ ኮሚሽኑ ለግባት የሚሆነው መረጃ ቀድሞ እየተሰጠውና የጥናቱ ውጤት ምን መሆን እንዳለበት ማመላከቻ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።
      በጥቅሉ ወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት፣ሠቲትና ራያ ወደ ትግራይ እንዲጠቃለል ካርታ የሠራው ፣ሕወሓትን ከመሠረቱት አንዱ የሆነውና ለረጅም ጊዜ የመራው  ዶር አረጋዊ በርሄ፣
      የሽግግር መንግሥቱን ቻርተር ካፀደቁት፣ ሕገመንግሥቱን ካረቀቁትና ካጸደቁት ፣በኋላም ፕሬዚዳንት ሆነው ተግባራዊ ያደረጉት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣
      የሽግግር መንግሥቱን ቻርተር ያዘጋጀና ያጸደቀ፣ በሕገመንግሥቱ ዝግጅትና ጽድቀት ወሳኝ ሚና የተጫዎተው  አቶ ሌንጮ ለታ፤
      ፀረ-ዐማራ የሆኑት  አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ዶር መራራ ጉዲና፣ አቶ ዘገየ አስፋው፣ ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀኝ
      የአገሪቱ ፕሬዚንዳንት ሆነው ለሕገመንግሥቱ ተፈጻሚነት ብዙ የደከሙት ዶር  ሙላቱ ተሾመ በዚህ የማንነትና የወሰን ኮሚሽን አባልነት መካተት፣ በዐማራው የኅልውና ጥያቄ ላይ፣ በወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ሰቲት፤ ደራ:  መተከል እና ራያ ሕዝብ የማንነት  ጥያቄ ላይ ተገቢ መልስ እንዳይገኝ ከወዲሁ ሠፊ እና ጥልቅ መሰናክል የተዘጋጀ መሆኑን አመላካች ነው። ይህም አገራችን እና ሕዝባችን ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉበት የለውጥ ሂደት እንዳለፉት የለውጥ ጅማሮች ወደ ማይፈለግ አቅጣጫ ሊያመራ እንደሚችል መጠራጠር አይቻልም።
ስለሆነም፣ ትግሉ ሰላማዊና ሕዝባዊ እንዲሆን በማድረግ፣ የዐማራ ፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክና የሙያ ማኅበራት፣ ወጣትና አዛውንቱ፣ ከተሜውና ገጠሬው፣ እነዚህ ሰዎች ቢቻል ራሳቸውን ከኮሚሽኑ እንዲያገሉ፣ ካልተቻለ የለውጥ አራማጁ ቡድን ከኮሚሽኑ አባልነታቸው እንዲገለሉ  ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጫና ለማድረግ ተግተን ልንቀሳቀስ ይገባል። በዚህ ረገድ፣ በፌስ ቡክ፣ በቲዊተር፣ በኢሜል፣ በስልክ፣ በቴክስት፣ እና ባሉን የብዙኃን መገናኛዎች ሰላማዊ ተቃውሞአችን ማጋጋል ይገባል። ``ቁጭ ብሎ የሰቀሉት ቁሞ ለማውረድ ያስቸግራል``ና፣ በኋላ በነዚህ ሰዎች የሚቀርበው ጥናት ዐማራውን የዘላለም ተጠቂ ያደርገዋልና ፣``ሳይቃጠል በቅጠል`` ልንል ይገባል።
የዐማራ ኅልውና መጠበቅ፣ ለኢትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ዋስትና ነው!
ዐማራው የአባቶቹን ማንነትና ክብር በትግሉ ያስጠብቃል!
 Posted at Ethio Semay
Saturday, February 2, 2019

በትግራይ ኦንላይን ላይ የወጣው የኢትዮጵያን ምጣኔ ሓብት ለማቃወስ ለትግሬዎች የተላለፈ መልዕክት! ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጎመው ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)


በትግራይ ኦንላይን ላይ የወጣው የኢትዮጵያን ምጣኔ ሓብት ለማቃወስ ለትግሬዎች የተላለፈ መልዕክት!
ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጎመው ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)

ትግራይ ኦንላይን (Tigrai online)  የተባለ የወያኔዎች አቀንቃኝ የሆነ ጸረ ኢትዮጵያ እና በተለይም በጸረ አማራነቱ የታወቀው ድረገጽ Short advice to Tigraians in Ethiopia, important!.  http://www.tigraionline.com/short-advice-to-tegaru.pdf በሚል ከድረገጹ ማውጪያ ላይ በተጠቀሰው እንግሊዝኛ ርዕስ በመስጠት፤ አንባቢ ርዕሱን ሲጨቁን “ሓፀርቲ ምኽርታት ንተጋሩ ኣሓትን ንአሕዋትን፤ከምኡ እውን ንሓለፍቲ መንግስቲ ክልል ትግራይ፡” በሚል ርዕስ በትግርኛ የዘገበው ወደ አማርኛ ሲተረጎም “አጫጭር ምክሮች ለትግሬ እህቶች እና ወንድሞች እንዲሁም ለትግራይ ክልላዊ መንግስት ሐላፊዎች” የሚል 13 ዝርዝር ነጥቦችን በትግርኛ የተጻፈ “ማኒ ላውንደሪ” “ሕገ ወጥ” የገንዘብና የንግድ አሰራር በመስራት የኢትዮጵያን ምጣኔ ሐብት እንዲቃወስ የትግራይ ሕብረተሰብ ሊሳተፋቸው የሚገቡ ሕገወጥ ተግባሮች በዝርዝር በማስቀመጥ ለትግራይ ማሕበረሰብ ሕገወጥ መልእክት በድረገጹ ላይ ለጥፎታል። ከዚህ በተጨማሪ “እግራችሁ አጣጥፋችሁ የምትጠብቁ ካላችሁ እናንተን እና ልጆቻችሁ ገድለው ያፈራችሁትን ሃብት ሊወርሱት ነው በማለት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ተጋሩ ባለሃብቶች “እነ ልጆቻቸው ተጨፍጭፈው ንብረታቸው እንደሚዘረፍ” ያስተላለፈው ፍርሃት የሚለቅ ቅስቀሳ በማሰራጨት የትግራይ ባለሃብቶች ከነቤተሰቦቻቸው ለግድያ እንደታጩ በሃሰት ቅስቀሳ ለትግራይ ባለሃብቶች አስተላልፏል።

ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጎምኩት ትርጉም ከዚህ በታች የተገለጸ ቢሆንም፤ የአብይ አስተዳዳር በትግራይ ኦን ላይን (Tigrai online) ላይ ሕጋዊ እርምጃ ካልወሰደ ኢትዮጵያውያኖች ለአብይ ያለው ድጋፍ እንዲያቆሙ በዚህ አጋጣሚ አሳስባለሁ።

በዚህ ሰነድ ትርጉም አማርኛው አስቀድሜ ከዚያም ዋናው የትግርኛ ዝርዝር ነጥቦቹ ከድረገጹ ቀጥተኛ ቅጅ ከታች አያይዤ አቅርቤዋለሁ።

Short advice to Tigraians in Ethiopia, important!
 አጫጭር ምክሮች ለትግሬ እህቶች እና ወንሞች እንዲሁም ለትግራይ ክልላዊ መንግስት ሐላፊዎች”
   ትርጉም ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

    ተቀማጭ ገንዘብ ካላችሁ ትግራይ ውስጥ በሚገኙ ማይክሮፋይናንስ ድርጅቶች (ደደቢት፤ፋና፤ አደዳይ) ብቻ እንዲቀመጥላችሁ አድርጉ። በተለይም በንግድ ዘርፍ ላይ ገንዘብ እንዳይኖራችሁ አድርጉ፤ አደራ።
   
     ከቻላችሁ ገንዘባችሁ በብር ሳይሆን በወርቅ መልክ እና በውጭ አገሮች ገንዘብ (ዶላር፣ ዩሮ፣ ዲርሃም ወ.ዘ.ተ) የምታስቀምጡበት መንገድ ፈልጉ።
    
    • በተለይም ኣዲስ አበባ ከተማ የምትኖሩ ገንዘብ ያላችሁ ወገኖች- እከተማዋ ውስጥ የሚገኝ ወርቅ ሁሉ ገዝታችሁ በማከማቸት ወደ ትግራይ እንዲሸሽ አድርጉ።

• ከትግራይ ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባ ወርቅ ኣይኑራችሁ።

• ውጫዊ የንግድ እና ሳፋየር በአንድ ትልቅ ድርጅት መልክ ሳይሆን በርከት ባሉ በትናንሽ (small scale) ዘርፎችና ማሕበራት እንዲካሄድ ይሁን። ዘርፎቹ የሚያስገኙት ገቢ (ሮያሊቲ ታክስ፣ ትርፍ ታክስ) ወደ ትግራይ እንዲገባ ይደረግ።

  በአንድ ትልቅ ድርጅት (large scale mining) የሚፈጸም ሆኖ ከተመዘገበ ገቢው ወደ ፌደራል
  መንግሥት ስለሚገባ እንዳይገባ ይህንን ዘዴ መጠቀም ያሻል። ይህም በሕገ-መንግሥቱ በግልጽ የሰፈረ ሕግ ነው (አንቀጽ 96፣ 97 ፌደራል ሕገ-መንግስትን ተመልከት)

• ትዳር አድርጉ፣ ውለዱ፣ ብዙ ተባዙ፤ ሆኖም ለሰርግ ተብሎ ከሚገባ በላይ መምነሽነሽ ይቁም። ተስካር ግን በሕግ መታገድ አለበት። ያለንን ሀብት እንቆጥብ።

• የሕክምና ድርጅቶች እንደሌሎቹ ድርጅቶች ገንዘብ የላቸውም። "ገንዘብ የለም" ብለን ስራዎቻቸው እንዲያቆሙ ማድረግ ስለማይገባ ያለ መንግሥታዊ በጀት ቆመው የሚሄዱበት መንገድ ለማድረግ ካሁኑ ጀምሮ ጥናት ይካሄድ። በተለይም እንደ  ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ፣እና ኣክሱም ሆስፒታል የመሳሰሉትን ይመለከታል። ሌሎችም እራሳቸው የሚችሉበት መንገድ ማፈላለግ አለባቸው።

• ተጋሩ ባለሃብቶች እመሃል አገር የሚገኝ ሃብታችሁና ድርጅቶቻችሁ፣ ህንጻዎቻችሁ ጫና መፍጠር ለሚችሉ አገሮች (ሃያላን መንግሥታት አገሮች) በከፊል ሽርክና ለነሱ ሽጣችሁ ንግዶቻችሁ በዛው መልክ እንዲካሄድ አድርጉ።

• ማታ ማታ የዊስኪ ጠርሙስ እያጋጫችሁ ዊስኪ በመጨለጥ ገንዘባችሁ የምታባክኑ የትግራይ ባለሃብቶች የምንሰጠው ምክር አለ። ይኸውም በሺሕ የሚቆጠር የትግራይ ሰው እየጠፈናቀለ ባለበት ባሁኑ ወቅት እናንተ በደቂቃ ብዙ ሺሕ ብር ለዊስኩ ማውጣታችሁ እንዲቆረቁራችሁ ይሁን። ነገ የናንተ ህንጻ ቢቃጠል እንዴት ብሎ ነው የናንተን ሃብትና ህንጻ የሚከላከልላችሁ። ድሃ ወገናችሁ ካልረዳችሁ ትግራዋይነታችሁ የት ላይ ነው? ስለዚህ ልብ አድርጉ ትግራይ ወገናችሁን እርዱት።

• ተጋሩ ትግራይ ውስጥ ብሕብረት/በሽርክና… በአምራች ኩባንያዎች፤ ማኑፋክቹሪንግ ኢንቨስትመንቶች ተሳተፉ፤ የትግራይ እምባሳደሮች ሆናችሁ የውጭ ‘ኢንሸስተሮችን’ ወደ ትግራይ እንዲሳቡ አድርጉ።

• ቆፍጠን ብላችሁ (ደፈር ብላችሁ) ደህና ገንዘብ መድባችሁ፣ ላይና ታች ብላችሁ በማስተዋል ጥናት አድርጋችሁ ለነዚያ ጸረ ትግሬ ለሆኑ መርዝ የሚረጩ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጀነሳየድ የሚያውጁ፤በትግራይ ሕዝብ ላይ የጥፋት ሴራ የሚጎነጉኑ ‘ተለቅ፤ተለቅ’ ያሉትን የሚደረግ አድርጉአቸው”።መርዝ ከሚረጩበት ሜዳቸው እንዲወገዱ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
ካሁን ወዲያ በትግራይ ሕዝብ ላይ ሞት እና ጥፋት ማወጅ ዋጋ የሚያስከፍል እንደሆነ እንድያውቁት ማድረግ ይገባችኋል።

በተለይ ትግሬዎች የሆናችሁ ባለሃብቶች፤ ሃብታችሁ ለትግራይ ህልውና እና ለትግራይ ሕዝብ መከበር አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅባችኋል። “ይህ አሁን የመጣ ሃይለኛ አውሎ ነፋስ እኛን ሳይነካ ያልፍ ይሆን?!” ብላችሁ እጅና እግራችሁ አጣጥፋችሁ የምትጠብቁ ካላችሁ ‘እነሱ” እናንተን እና ልጆቻችሁ ገድለው ያፈራችሁትን ሃብት ሊወርሱት ነው (ኢድኩምን እግርኹምን ዓፃፂፍኩም ንሳቶም ንዓኹምን ንደቅኹምን ቐቲሎም ኩሉ ሃብትኹም ክወርሱዎ እዮም)። ይህንን ለማድረግም ይህ ትምቢታቸው እውን ለማድረግ የሚችሉበትን ዕድል ለመፍጠር ሌት ተቀን እየሰሩ ነው። እውነታውም እየሰፋ እየሄደ ነው። ይህ ከመሆኑ እና ይህ ከመሆኑ በፊት (ንብረታችሁ ተወርሶ እናንተ እና ልጆቻችሁ ከመጨፍጨፋቸው በፊት) ካለችሁ ንብረት/ሃብት/ የህዝባቸሁን ደህንነት /ህልውና/ በሚውል ተግባር በመርዳትና የናንተን ጥፋት በሚመኙት ላይ ለማስቆም በሚረዳ ተግባር እንዲውል ንብረታችሁ በከፊል ለዚህ ስራ እንዲውል ለግሱ።

• የፕሮፖጋንዳ ሃያልነት እንደምታዩት ሃያል ነው። ጠንካራ የተጋሩ መልዕክቶች የሚተላለፉባቸው ሚዲያዎች በገንዘብ እና በሃሳብ በመርዳት በውጭ እና በአገር ውስጥ እንዲደመጥ ተነሳሽነት እንዲኖሮው መልዕክቱ ለሁሉም ትግሬ እንዲዳረስ አድርጉ!
                   ትርጉም ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
Short advice to Tigraians in Ethiopia, important!
ሓፀርቲ ምኽርታት ንተጋሩ ኣሓትን ንኣሕዋትን፤ ከምኡ እውን ንሓለፍቲ መንግስቲ ክልል ትግራይ፣

  • ዝቕመጥ ገንዝብ እንተሃሊዩኩም ኣብ ትግራይ ኣብ ዘለዋ ማይክሮፋይናንሳት (ደደቢት፣ ፋና፣ ኣደዳይ) ጥራሕ ዕቖሩ፤ ብፍላይ ኣብ ንግዲ ዝቕመጥ ገንዘብ ከይህልወኩም ሓደራ፤

  • እንተኽኢልኩም ግን ገንዘብኩም ብብር ዘይኮነስ ብመልክዕ ወርቂ፣ ናይ ወፅኢ ሃገራት ገንዘብ (ዶላር፣ ዩሮ፣ ዲርሃም ወ.ዘ.ተ) እትዓቑሩሉ መንገዲ ድልዩ፣

  • ብፍላይ ኣብ ኣዲስ አበባ እትነብሩ ገንዘብ ዘለኩም ወገናት- ኣብታ ኸተማ ዘሎ ወርቂ ኹሉ ገዚእኹም ኣክቡዎ፣ ኣብ
ትግራይ ክቕመጥ ድማ ግበሩ፤

        • ካብ ትግራይ ናብ ብሄራዊ ባንኪ ዝኣቱ ወርቂ ኣይሃሉ፣

        • ምውፃእን ንግዲን ሳፋየር ብሓደ ገዚፍ ትካል ዘይኮነስ ብርክት ብዝበሉ ኣናእሽቱ (small scale) ትካላት ፣
ማሕበራት ክካይድ ይኹን። እዚ እቲ ዘፈር ዘእትዎ ኣታዊ (ሮያሊቲ ታክስ፣ ናይ ትርፊ ታክስ) ናብ ትግራይ ክኣቱ
ይገብሮ፤ ብሓደ ገዚፍ ትካል (large scale mining) ዝፍፀም ኮይኑ እንንተተመዝጊቡ እዞም እቶታት ናብ ፌደራል
መንግስቲ እዮም።እዚ ኣብቲ ሕገ-መንግስቲ እውን ብግልፂ ሰፊሩ ኣሎ (ዓንቀፃት 96፣ 97 ሐገ-መንግስቲ ፌዴሪኢ
ተወከስ)፡፡

        • ሓዳር ግበሩ፣ ውለዱ፣ ብዝሑ፤ ኮይኑ ግን ንመርዓ ኢልካ ፍሰስ ተፋሰስ ይትረፍ፤ ናይ ተስካር እንግዲት ግን ብስሩ
ብሕጊ ክእገድ እውን እዩ ዘለዎ። ዘለና ሃፍቲ ንዕቖር።

       • ትካላት ሕክምናና ከምቲ ካልእ ዓውዲ "ገንዘብ የለን" ኢለን ስራሕ ከቋርፃ ስለዘይግባእ ብዘይ ናይ መንግስቲ በጀት
ደው ኢለን ክኸዳ ዝኽእላሉ መንገዲ ካብ ብሐዚኡ እናሰርሓሉ ይፅናሓ። እዚ ብፍላይ ንሪፈራል ሆስፒታል ዓይደር ፣
ንሪፈራልሆስፒታል ኣኽሱም ዝምልከት እዩ። እተን ኻልኦት እውን ብፋይናንስ ዓርሰን ዝኽእላሉ መንገዲ እናኣለሻ
ይኺዳ።

       • ተጋሩ ሰብሳቢ ሃፍቲ እንተኽኢልኩም ኣብ ማእኸል ዓዲ ዘለዉ ትካላትኩም፣ ህንፃታትኩም ብኽፋል ንናይ ወፃኢ
ዓዲ (እሞ ድማ ናይ ግዝፍ ዝበላ ፅዕንቶ ፈጠርቲ ዓድታት) ሰብ ሃፍቲ ሸይጥኩም ብሽርክና ክካየዱ ግበሩ፤

        • ኣቱም ዊስኪታት ሚፅ እናበልኩም ትሓድሩ ዘለኹም ሰባት፣ ግደፉ ዘለናሉ እዋን ኣስተውዑሉ፣ ክንደይ ትግራዋይ
ተፈናቒሉ ኣብ መንገዲ ወዲቑስ ብደቓይቕ ኣሽሓት ፊፍ ኢልኩም ክትኣትዉ ንእሽቶይ'ባ ይሰቆርኩም። ኣበይ ድኣ እዩ
ዘሎትግራዋይነት? ሎሚ ቆላሕ ኢልካ ዘይረኣኻዮ ወድ ድኻ ፅባሕ ናትካ ህንፃ ከይቃፀል ከመይ ይቃለስልካ? "ንመን
ኢል እየ ዝመውት?" ዝብል ሰብ ከይበዝሕ ግበሩ፤ እዚ ድማ ብኻልእ ዘይኮነስ ወገናውነትካ ብምርኣይ፣ ዘለካ
ብምክፋል፣ ኣብ ቅድሚዝበልዖ ዝሰኣነ ወገንካ ብገንዘብ ዘይምፅዋት እዩ።

        • ኣብ ትግራይ ብሕብረት/ብሽርክና ኣብ ዓውደ መፍረይቲ ማኑፋክቹሪንግ ኢንቨስትመንታት ተሳተፉ፤ ናይ ዓድኹም
እምባሳደራት ኪይንኩም ናይ ወፃኢ ኢንሸስተራት ስሓቡ፤

        • ሓደ ሓደ እዋን ድፍር ኢልኩም፣ ደሓን ገንዘብ መዲብኩም፣ ላዕልን ታሕትን ኣስተንቲንኩምን ኣፅኒዕኹምን ነቶም
ዝኽፍኡ ፀረ ተጋሩ መርዚ ዝነዝሑ፣ ኣብ ልዕሊ ህዝቢ ትግራይ ጄኖሳይድ ዝእውጁ፣ ኣብ ልዕሊ ትግራይ ናይ ጥፍኣት
ተንኮል ዝፍሕሱፍርይ ፍርይ ዝበሉ ዝግበር ገይርኩም ካብቲ መርዚ ዝዝርአሉ ሜድኦም ክእለዩ ምግባር የድሊ።
ድሕሪ ሀዚ ኣብ ልዕሊ ትግራይን ተጋሩን ሞትን ዕንወትን ምእዋጅ ዋጋ ዘኽፍል ክኸውን ክትሰርሑ ይግባእ።

        • ብፍላይ ተጋሩ ዓበይቲ ሰብ ሃፍቲ ናትኩም ሃፍቲ ኣብ ህልውናን ኽብሪን ትግራይን ተጋሩን ኣወንታዊ ኣበርክቶ
ዝፃወት ክኸውን ኣለዎ። እዞም ሰባት ንስኹም "እዚ ህቦብላ ንፋስ ከይነኽአ ክገድፈና ዶ ይኸውን!" ብዝብል ተስፋ
ኢድኩምንእግርኹምን ዓፃፂፍኩም ንሳቶም ንዓኹምን ንደቅኹምን ቐቲሎም ኩሉ ሃብትኹም ክወርሱዎ እዮም
ዝሰርሑ ዘለዉ፣ ካብ ዕለት ናብ ዕለት ድማ እዚ ትምኒቶም ናብ ምድሪ ዘውርዱሉ ዕድል እናስፍሑ ይኸዱ ኣለዉ።
እዚ ቅድሚ ምዃኑ ካብቲ ዘለኩምሃፍቲ ዝተወሰነ ሰሊዕኹም ድሕንነትን ህልውናን ህዝብኹም ኣብ ምሕላው፣
ንወገንኩም ኣብ ምሕጋዝ፣ ጥፍኣትኩም ንዝምነ ኣብ ምቕዳም ኣውዕሉዎ።

         • ሓይሊ ፕሮፖጋንዳ ከምቲ እትሪኡዎ እዩ፤ ሓያላት ናይ ተጋሩ ድምፂ፣ ተረኽ ዝስምዐለን ሚድያታት ኣብ ውሽጢ
ዓድን ኣብ ወፃእን ክፍጠራ ብፋይናንስን ብሓሳብን ሓግዙ ወይ ባዕልኹም ተበግሶ ወሲድኩም መስርቱ።
እቲ ሓበሬታ ናብ ኩሉ ትግራዋይ ክባፃሕ ግበሩ!