Tuesday, June 30, 2026

ሲንጋፖር እና ማሌዥያ ትግራይ እና ኢትዮጵያ ጌታቸው ረዳ 6/30/26

 

ሲንጋፖር እና ማሌዥያ ትግራይ እና ኢትዮጵያ

ጌታቸው ረዳ

6/30/26

Ethiopian Semay

ከዚህ በታች የምተቻቸው እና የምንዳስሳቸው የትግራይ ምሑራን እና የድርጅታቸው የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ «ሉጋም የበጠሰ» (Balky/Nappy) ባሕሪ ዋናው ተጠያቂው ሥልጣን ላይ ያለው አብይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሞዎች ሥርዓት ነው። ይህ ለምን እንዲያ ሊሆን እንደቻለ በጦነቱ ወቅት እና ጦነቱ ከመነሳቱ በፊት  አብይ አሕመድ የሰጠኋቸው ትችቶች እና ማስጥንቀቂያዎች አንባቢዎች ማስታወስ ይኖርባችኋል። ያንን አሁን አልገባበትም። አሁን የምናየው የትግራይ መሑራን በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት ገና ትግሉ ከ1967 ዓ.ም “ተጋድሎ ሓርነት ትግራይ” (ተ.ሓ.ህ.ት) ብሎ ራሱን በመሰየም የተመሰርተው የትግራይ ፋሺስት ፓርቲ ሲጀመር ጀምሮ እሰካሁን ድረስ «በትግራይ exceptionalism» እየዳከሩ ባልጠፋባቸው ማንነት “በራስ ፍለጋ ዑደት” ሲጋጋጡ ብዙ ሕዝብ አስፈጅተዋል (ኢትዮጵያዊያኖችንም ሕዝባችን የሚሉት የትግራይ ሕዝብንም ጭምር)።

 በዚህ የፋሺስቶች ውልደትና ዕድገት ግስጋሴ ዋና ተዋናዮች ሆነው የተገኙ የትግራይ ምሑራን ናቸው። የነዚህ መሁራን ቅስቀሳና ድጋፍ  ምክንያት ቀስ በቀስ ከምስረታው ጀምሮ ፣ ድርጅቱ ጉልበት እያገኘ፤ ሕዝቡን ከማስፍራራት እሰክ ማሰር ፥ በእሳት እየለበለቡ ማሰቃይትና መግረፍ ፥ ነሱ የሸሸውም  ንብረቱን በመውረስ ፤ ጠንክሮ የተዋጋቸውም በመግደል እና በማሳደድ በዙሃኑን የግራይ ሕዝብ በማሰለፍ 17 አመት የጫካኔ ጦርነት አካሂደው ደርግን ቦርቡረው በመጣል ሲመኙት የነበረው የበላይ የመሆን ሥልጣንን አገኙና 27 አመት ሕዝቡን ረግጠው አለያይተው አበጣብጠው አጣልተው ቅጥቅጥ አርገው ገዙት።

የትግራይ ተወላጆችም “ከደቂቅ እሰ ሊቅ” ሕሊናው በበላይነትና ማን አሕሎኝነት ሰክሮ “ዞር ብሎ ያያቸው ሁሉ” እንደጠላት እያዩ  ”ምን አባህ ታየኛለህ!” እያሉ ሲያንጓጥጡት 27 አመት ከገዙ በኋላ ወዳጄ “ጉዱ ካሳ” ጠብ ያላለቺው ትንቢቱ ልክ እንዳለው  ውስጥ ለውስጥ ሲፍም የነበረው እሳት በጥቂት ወራት ልዩነት ወያነ ፈነዳ፦ 

(በነገራችን ላይ ሚነሶታ ላይ ቁጭ ብሎ ሲያሻው አስመራ እየተሽሞነሞነ ከአንዳርጋቸው እና ብርሃኑ ነጋ ጀምሮ እሰክ ምሁራን የዎች ወያነ በ3 ወር ውስጥ ያልቅለታል አዲሰ አበባ እንገባለን ሲሉን ከነበሩት እና አሁን ደግሞ ፋኖዎች በጥቂት ወራት አዲስ እበባን እንጭብጣታለን ከማለት አልፈው ለሚመጣው አመት አስተላለፈውት ሰምቻለሁ፤ ከነዚህ ሁሉ ትንባዊ ሽምቅ ተዋጊዎች ትንቢቱን በትክክል መትቶ ያየሁት የወዳጅ ዳግማዊ ጉዱ ካሣ ትንቢት ብቻ ነው)።

 ታሪክ ነውና እሰኪ ላስታውሳችሁ

እንዲህ ይላል ስለ ወያኔዎች አወዳደቅ፡

«.........አዲስ አበባ ማቀጣጠያ ካምሱሯ የተለኮሰ ፈንጅ ሆናለች። መቼ እንደምትፈነዳ ትክክለኛ ሰዓቱን አንድዬ ብቻ የሚያውቀው ሆኖ በቅርብ መፈንዳቷ የማይቀር ስለመሆኑ ግን የማንም ተራ ግንዛቤ ሊሆን ይገባል። በቃኝ። ስለነሱ አፈነዳድ ትንሽ ልናገር ነበር ይቅርብኝ። እንዴትም ይፈንዱ ዋናው መፈንዳታቸው ነው፤ እናም እንዳፈነዱን አይቀሩም እነሱም አሁን በቅርቡ ይፈነዳሉ!!»  ምንጭ “አዲስ አበባ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ትፈነዳለች! (በኤፕሪል 2, 2018 ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)::

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ የትግሬዎቹ የአዲስ አበባ የልብ እብጠት (እነሱ “ፍናን” ይሉታል) ሲያስታውስ እንዲህ ይላል፤

<<….ሌት ከቀን የሚዝናናው፣ በመኪናው ውስጥ በሚከፍተው የሙዚቃ ድለቃ ሕዝብን እንቅልፍ የሚነሳው፣ በየቡና ቤቱ እየዞረ ትግርኛ ካልተከፈተልኝ በማለት ሌላውን ዘፈን በነፍጠኛነት የሚፈርጀውና የሚያስፈራራው ጠግቦ እየዘለለ የሚገኘው ትግሬ ወያኔና አሽከሮቹ ናቸው፡የሚገርመው ጠጪዉና ተዝናኙ ትግሬ ብቻ ነው ተብሎ በአዋጅ የተነገረ ይመስል በየመዝናኛውና በየምሽት ክበቡ የሚከፈተው ዘፈን ከሞላ ጎደል ትግርኛ ብቻ ነው።  ትግርኛ ካልከፈታችሁ ቡና ቤታችሁ ይዘጋል የተባለ ይመስል አዳሜ ከገዢው ወገን ጋር የተዛመደ እየመሰለው የሚከፍተው ሙዚቃ ትግርኛ ብቻ የሚሆንት አጋጣሚ ሞልቷል>> ይላል ዳግማዊ ጉዱ ካሣ።

ዘልሎ ፥ ዘልሎ ሕዝብን ሲያሰለቹት በሚያደርሱበት ስቃይና ግፍ በመጨረሻ ሕዝቡም ቋቊ ሲለው ከነጭራሹ ሙዚቃቸውን ሁሉ ሳይቀር መስማት አስጠላው።

 ይህንን ትዕይንት በማስረጃ ላስታውሳችሁ፦

ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ ይባላል፤ ድሮ የኢሕአፓ ታጋይ የነበረ አሁን ግን “ሃገረ ትግራይ ይመስረት” ከሚሉት እና የሽዋ ሕዝብ ቤተ ክርስትያን ከመሳለሙ በፊት ‘’ጠንቋይ  ቤት” የሚሳለም ሕዝብ ነው፡” ሲል የነበረ ኤርትራ ውስጥ ተወልዶ ያደገ የዓጋመ አውራጃ ተወላጅ የሆነ ከትግራይ ፋሺስት መሁራኖች አንዱ ነው።

ከትግርኛ መጽሄት ወደ አማርኛ የተረጎምኩትን ላስነብባችሁ፡

 እንዲህ ይላል

«አንዳንድ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የተዘጋጁ ለሕዝብ ሚቀርቡ መዝናኛዎች አያለሁ። አንድ ቀን “ሰይፉ ሸው” መዝናኛ እመለከት ነበር። የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰይፉ አንዲት የትግራይ ተወላጅ የሆነች ድምጻዊት ቃለ መጠይቅ ያደርግላት ነበር። ለተመቾቹ ዘፍን እንድትዘፍንላቸው ጠይቋት፤ እሷም እሺ ብላ በጣም ቢመገርም ድምጽ የትግርኛ ዘፈንዋን አቀረበች። አዳራሹ ውስጥ የነበሩት ተመልካቾች ግን አያንጨበጭቡ፤ እስክስታ አይመቱ፤ እጆቻቸውን አጣምረው “ዝም ፥ ዝም ፥ ብቻ” ዝም ብለው ይመለከትዋታል።እኔ ያኔ በጣም ገረመኝ። በጃንሆይ ጊዜ እኮ ትግርኛ ሲዘፈን ጉራጌው፤አማራው፤ኦሮሞው ከኛ ጋር አብሮ ነበር አስከስታውና ደስታው ሲያስኬደው የነበረ። እስከዚህ ድረስ ትግርኛ ሙዚቃ እንኳ እስከመጥላት የሚደርስ ሁኔታ እየተከሰተ ነው። እኛ ብቻ ካልገዛን የሚለው አስተሳሰብ መወገድ አለበት።>> ይላል ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ “ውራይና” በሚባለው ትግርኛ መጽሄት (ሕታም ቁ31 2010)

 «አዳራሹ ውስጥ የነበሩት ተመልካቾች ግን አያንጨበጭቡ፤ እስክስታ አይመቱ፤ እጆቻቸውን አጣምረው “ዝም ፥ ዝም ፥ ብቻ” ዝም ብለው ይመለከትዋታል።እኔ ያኔ በጣም ገረመኝ” ሲል ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ ተመልካቹ ለምን እንዳላንጨብጨብላት ሰፊ ሐተታ ካሁን በፊት በሰፊው ስለገለጽኩት ፤ባጭር አገላለጽ የወዳጄን የይነጋል በላቸው አባባል ላስቀምጥና ሕዝቡ ወደ ጸጥታ ስሜት የገባበት ምክንያት ስለበረው ነው፡ ይህም የሚከትለው ግፍ ሲፈጸም እዋ እና መሰል ትግሬዎች ይጨፍሩ ነበር (ጎንደር ሲጮህ ትግራይ ላይ ጠጅ ሲንቆረቆር” የሚለውን ጽሑፌን አስታውሱ)።

ይነጋል እንዲህ ይላል፤

«አብዛኛው ትግሬ ተጠቀመም አልተጠቀመም በፕሮፓጋንዳው ተሸንፎ ወያኔ ሆኗል ወይም መስሎ ነበርአምባሻ ሻጯ፣ ቁራሌው፣ መጥረጊያ አዟሪው፣ ወዘተ. እየተራበና እየተጠማም ቢሆን ህወሓትን ከልቡ ይወድና ግፉ የግፍ ነበር“ዘር ከልጓም ይስባል” ወይም “ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ ትወጋ” የሚባለውም በትግባር ሰላየው..”

 ሕዝቡ ጸጥታን መርጦ “ዝም ፤ዝም አለ።

የሚክተለው ግፍ በዓይኑ አይልና።ለመሰል ትግሬዎች ሲደግፉት የነበረው መንግሥት

“...ዐማራውና ሌላውን የሚያቆራኘውን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አውድሜ ድራሹን አጥፍቻለሁ ብሏል፡፡ ታዋቂና ተሰሚ የዐማራ ምሁራንንና የሀገር ሽማግሌዎችን ገድዬ ጨርሻለሁ ብሏል፡፡ የኢትዮጵያዊነት ምልክቶችን ሁሉ አንድባንድ ደምስሻለሁ ብሏል፡፡ በተቃውሞው ጎራ የሚገኙ ዐማሮችን ለቃቅሜ አይቀጡ ቅጣት በመስጠት – በስድብ፣ በግርፋት፣ በወፌላላ፣ በግብረ ሶዶም፣ በወሲብ ጥቃት፣ በጥፍር ንቅላትና በፈላ ዘይት ጥብሳት … ስብዕናቸውን በማዋረድ መቼም እንዳያንሠራሩ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡ የዐማሮችን ቅስም ሰባብሬ ዳግመኛ ወደ ሥልጣን ዝር እንዳይሉ በአካልም በመንፈስም ኮድኩጃቸዋለሁ ብሏል፡፡ በአዲሲቷ ሕወሓት ሠራሽ ኢትዮጵያ ዐማራ ምንም ዓይነት ቦታ እንዳይኖረው በማድረግ ብዙ ግፍ ፈጽሟል..” ታዲያ ሕዝቡ ይትግርኛ ዘፋኝ እና ዘፍን ሲይጣድመጥ አብሮ 27 አመት ሲጨፍርበት የነብረብረበትን ሙዚቃ ደንገት ለምን “ቋቍ” አለው?

ወቅታቸው ነበርና ወዳጅ ዳግማዊ ጉዱ ብ1983 ሥልጣን ሲይዙ ያስታወሰውን የትግሬዎቹ ንግግር እንዲህ ያስታውሰናል፤

 አስታውሳለሁበ83 ዓ.ም ወያኔ አዲስ አበባ እንደገባ በወያኔ ሬዲዮ የትግርኛ ፕሮግራም ስለትግራይ ሕዝብ በወያኔ ሥልጣን መያዝ ተጠቃሚነት የተጠየቀ አንድ ትግሬ ባለሥልጣን “የመጀመሪያው ጠቀሜታ ሥነ ልቦናዊ ነው፡፡ ‹የኔ ሰው ሥልጣን ያዘልኝ› ብሎ ማሰቡ በራሱ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ሁለተኛ ….” እያለ በኩራት ይደሰኩር ነበር፡፡ እየተናገረኩት ያለሁት ጉዳይ እነሱ በተግባር ሲፈጽሙትየሚኮሩበትን፣ እኛ ግን ስንናገረው እንኳን በሀፍረት የምንሸማቀቅበትን የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡

አንድ የወዳጄ ወዳጅ የላክለት አዲስ አበብ አደርሶ ከመጣ አንድ ሰው የታዘበውን በመጽሐፌ የጠቀስኩትን ላስታውሳችሁ፡ የሰማዩን ምድሩን መሰሶ የሚያነቃንቅ ጥጋባቸው ምን ይመስል እንደነበር አዲስ አበባ ደርሶ ከመጣ ወዳጅ የተላከልኝን ላስነብባችሁ፦

<<…….እግዚአብሔር ይስጥልኝ ወንድሜ። ወደ ኢትዮጵያ ሄጄ ነበር የተወሰነ ወር ቆይቼ ነው የመጣሁት። የሰውን ፊት አይተው ይለያሉ ሊቃወመን ይችላል ብለው የሚያስቡትን ኤርፓርት ኢሚግሬሽን ቡት ውስጥ ከሚቀመጡት ዘረኛ ትግሬዎች ጀምሮ። በተለይ ቦሌ መድሐኒአለም ፊት ለፊት በኤድና ሞል ዝቅ ብሎ ብዙ ዘመናዊ ባለ 5 ኮከብ ሆቴሎች ተከፍተዋል ሁሉም የትግሬ ናቸውነጮቹ ‘ሆቴል ዲስትሪክት’ ይሉታል። የኛ ህዝብ መቀሌ እና አፓርታይድ ይለዋል ሰፈሩን። በተለይ “ቬኒሺያን” የሚባለው የትግሬ ሆቴል ገብተን 10 ዲቂቃ እንደተቀመጥን ካውንተሩ ላይ የሚቀመጠው እጅግ በጣም የጠገበ ሲራመድ መሬት የሚነቀንቅ ትግሬ የተቀመጥንበት ድረስ መጥቶ ያፈጣል። አስተያየቱ ሀሉ በጣም ነው የሚከብድው። ህዝቡ ኪሱ ውስጥ ያለውን ብር ቶሎ አራግፎ እንዲወጣ ነው የሚፈልጉትጥላቻቸው በግልፅ የሚታይ ነውበዘረኝነት እና በጥላቻ ከተመረዘ ህዝብ ጋር መኖር በጣም ነው የሚከብደው ህዝባችን በገዛ አገሩ ላይ እንዲሸማቀቅ እየተደረገ ነው። ባካባቢው ባሉት ሌሎች የትግሬ ሆቴሎች ውስጥም ተመሳሳይ ዘረኝነት ነው ያየሁት። “> ይላል፡  ለዚህ ደራሲ  የተላከለት ደብዳቤ (ምንጭ-የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ክመን የመነጨ ነው? ገጽ 176)። ይህንን ወታደሮች ያልሆኑ የወያነ ወጣት ትግሬዎች በየቡና ቤቱ የሚያሳዩት ጥጋብ አዲስ አበባ ውስጥ  ሽጉጥ ታጥቀው፤ ምድሪቱን እንዴት አንደሚነቀንቋትና የአማራን ሕዝብ እልቂት መሪ የነበርረውና የባሕር በራችንን ለጠላቶቻችን ያስረከበብንን ታላቁ መሪያቸው መለስ ዜናዊን ለምን ተቻችሁ እያሉ እንዴት ይዝቱ እንደነበር ይህንን ጥጋብ  በቪዲዮ ይመልከቱ፤

ይነጋል እንዳለውም ፈነዱና

በየመጠጥ ቤቱ እናንት አህዮች “የትግርኛ ሙዚቃ“ ካልክፈታችሁ እያለ ቡና ቤቶችን ሲያስፈራራ “ወዲ ትግራይ” እያለ ሲፎክር የነበረው  እና “ይህን አህያ ንዳው” ሲል ቆይቶ በመጨረሻ ግፉ ሲያበዛ በባለተራው የኦሮሞ ሥርዓት ተገፍትሮ ሲገለል፤ ምሁራን ተብየዎቹና መሪዎቻቸው በልባቸው ውስጥ ይዘዋት የነብሩዋትን ሃገረ ትግራይ ለመመስረት ወደ ትግራይ አፈገፈጉ።ይህ ድንገት ያለሙት ሳይሆን በማኒፍስቷቸው ይሁን በንግግሮቻቸው ሲነግሩን ይነበረው ነው። የወያነ አባት ‘’የስብሓት ነጋን’ “ሥልጣናችን ከተቀማን በየምንደራችን እንከፍጋፈላለን” ንግግር አስታውሱ።

ያንን ጥጋብ እና የሃገረ ትግራይ ምስረታ ዓላማ እውን ለማድረግ በወሰዱት የተሳሳተ የልብ ዕብጠትና ጉራ ሕዝብ አሳልቀው ራሳቸውም ተዋርደው ግማሹ ተማርከው፤ ግማሾቹ ተግድለው አሁን ወዳሉበት የጭለማ መሰላለ ተንጠልጥለው አንዱ እግር ሰማይ አንዱ እግር ምድር የፖለቲካ ዥዋዥዎ እየሰሩ “እግር ተወርች ታስረው ፥ ምሁራኖቻቸውም የሚይዙትና የሚጨብጡት አጥተው ሃገረ ትግራይን ለመመስረት “እሰኪሳካልን ድረስ ኢትዮጵያዊያኖችን መስለን ኢትዮጵያን እየበዘበዝን እና እየቦረቦርን በስልት እንራመድ በሚል በየወቅቱ እይተሰበሰቡ እየተነጋገሩ ነው።

ብዙዎቹ ምሁራኖቻቸው በሁለት የቆመ ፍላጎት ቆመዋል።ጠላቶቻችን የሚጓጓዋት ሃገር እንመሰርታለን የሚሉ አንደኛው ጎራ ነው።  ሌላኛው በሁለት “ባላ” ላይ የቆመ ፍላጎት (Ambivalent) ኢትዮጵያ ሃገራችን ነች” ይልና እንደገና የትግራይ ናሺናሊዝም ጎራ “ሲብረታ” ወደ ሃገረ ትግራይ ቡድን የሚያዘነብል ወላዋዩ ሁለተኛው ጎራ ነው።

በሁለት ባላ የቆመ ፍላጎት በሚመለክት (ሃገረ ትግራይ እመሰርታለሁ ከሚለው አንዱ (ገ/መድህን ሮምሃ በጥሩ አግላለጽ ያቀረበውን ላቅርብ ፤ እንዲህ ይላል፡

«ባለሁለት ገጽታ ፍላጎት’ ያልኩበት ምክንያት፤ ምሁሩ በአንድ በኩል ስለኢትዮጵያዊነት ይሰብካሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ብሔረ ሰቦች እርስ በእርሳቸው የሚያጋጭና የሚለያይ መርዙ ይረጫሉ፤ ባለሁለት ገጽታ ፍላጎት፡፡ የመጽሐፉን አሉታዊ ጎኑን ለግዜው እናቆየውና፤ ሞቲ ቢያ (2009) ‘የኦሮሞ ጥያቄና ፈተናዎቹ’ በተሰኘ መጽሐፉ፤ የዚህ ዓይነት ባህርይ ‘የአንድነት ስም እየጠሩ ለበላይነት ለቅሶ’ በማለት ገልጾታል፡፡» (ገ/መድህን ሮምሃ (ዶ/ር)

ይህ እውነተኛ አገላለጽ ስንመለከት አንድ የፖለቲካ ድርጅት ስለ አንድ አገር አንድነት እተሰበከ ወደ  ሥልጣን ሲወጡ ግን  ከ8 አመት በፊት የነበረው ወያነ እና አሁን ያለው ኦሮሙማው ስርዓት ስትመከቱዋቸው አንድነትን ይሚቀበሉት እነሱ የበላይ ሲሆኑ ብቻ ነው። የሁለቱ ችግሮች በገልጽ አይተነዋል።

የትግራይ ምሑራን ስንመለከት የምናየው ወዳጄ ዳግማዊ ጉዱ ካሳ እንዳለው ፣ ከአላውኃ ምላሽ (ወንዝ) ጎጥ-ሰቀል አድማስ ያልዘለለ የአእምሮ ስንኩላን አስተሳሰባቸውን ስናስተውል ምን እንደገጠማቸው ለማወቅ አዲስ ጥናት መደረግ ይኖርበታል ባይ ነኝ፡፡

«ዕይታቸው ከአላውኃ ወንዝ ጎጥ-ሰቀል አድማስ ያልዘለለ የአእምሮ ስንኩላን የሆኑ የትግራይ ኤሊቶች ይህን በዘረኝነት ደዌ የተመታና ሀገርን የሚያወድም ወያኔ መደገፋቸውን ስናይ ከዕውቀትና ከጥበብ ለሚመነጭ አስተዋይነት መገዛታቸውን ሣይሆን እንደውሻ ደምና አጥንት እያነፈነፉ ወደ እሚከረፋው የሆድ ውስጥ ዕቃ ወደ ጨጓራና ጅብ አይበላሽ መውረዳቸውን እንገነዘባለን።» ይላል።

በሁለተኛው ጎራ የተሰገሰገው ወላዋይ የትግራይ ምሑር የሚክተለው ስልት የሚክተለው ይመስላል፦

ለምሳሌ መዘክር ዘሞ (የወያኔ አምራረ አባል የአባዲ ዘሞ ልጅ) መዘክር ዘሞ እንዲህ ይላል በትግርኛ (ወደ አማርኛ ልተርጉመው)

ሃገረ ትግራይ ዝብሃል ሃገር ክርእዮ ይደልይ እየ- (ሃገረ ትግራይ የሚባል ሃገር ለማየት እፈልጋለሁ) በሚል ረዕስ መዘክር ዘሞ እንዲህ ይላል፤-

«....መሬት ላይ ያለውን እውነት እንረዳ። ትግራይ አሁን ያለችበትን ሁኔታ እንወቅ። ትግራይ ውጥንቅጥ ውስጥ ነች። ችግሩን ለመፍታት በጋራ ከመስራት ይልቅ በትንንሽ ጉዳዮች እንዳንገመት መጣር አለብን። ኦሮሞዎች (ሥልጣን ላይ ሆነው) በስልት ለሃገረ ኦሮሚያ ምስረታ ለምን እንደሚሠሩ ግልጽ ነው። አገር ለመመስረት ነው የሚንቀሳቀሱት ፣ ግን እንደኛ ጮክ ብለው “ለሃገረ ኦሮሚያ” ምስረታ ነው ውጥናችን እና ግባችን  ብለው ሲናገሩ አትሰሙዋቸውም። ተጨባጭ ትግል ሲኖር ነው የሃገር ምስረታ ሞራል የሚዳብረው፤ የትኛው ትግል መስርተን ነው ለትግራይ ምስረታ የምንጮሆው?  በመጀመሪያ ኢኮኖሚያዊ ጥቅማ ጥቅሞችን መገንባታችን ማረጋገጥ አለብን። ከግጭት የወጣች ሀገር ( መዘክር - ትግራይን ነው “ሀገር” እያላት ያለው) በተከበብንበት እና መውጫ በር በተቆለፈብን ወቅት ትግራይ ምን እንደምትመስል አይተናል:: ታጥሮ መከበብና የመቆለፍ ከስተት ሳይዘጋጁ ለሃገር ምስረታ መሮጥ “ጥሩ ምሳሌዎች” ናቸው። እንዲያ ባለ ሁኔታ ሃገር መመስረት ትንፋሽ ማጣት ነው። ማስተንፈሻና መውጫ በር የሌለው ሀገር መሆን ከንቱ መሆኑን በቅርቡ አይተናል።ሰለዚህ ምኞቶቻችንን ለማሳካት አስቀድመን ኢኮኖሚያዊ ዝግጅቶችን ማድረግ አለብን።ከጠላቶች የተሻለ መሆን አለብን።ከዛሬው ጦርነት ልንማር ከምንችላቸው በጣም አስፈላጊ ነገሮች አንዱ ሁሉም ሰው አንጻራችን ተሰልፎ ሊገለበጥብን እንደሚችል ነው ያየነው።ግባችን ላይ እስክንደርስ ድረስ ግን ግንኙነታችንን ስትራቴጂ አስይዘነው እስከምስረታው ድረስ “ኢትዮጵያዊያን ነን” እያልን በብልሃት እይተራመድን ግባችን ላይ መድረስ ይገባል።» (መዘክር ዘሞ (አዲሰ አበባ)

እንግዲህ የሃገር ምስረታቸው በስልት እንዴት እየተንቀሳሱ እንዳሉ እና ሃገር ላምውደም የሚከተሉት ስልት አይተናል (ያውም አዲሰ አበባ እምብርተዋ ውስጥ እየኖሩ) አይዝዋችሁ የሚል ፤ እኛም ወደ ዚያው ግብ እያመራን ነው የሚል መንግሥት መኒሊክ ቤተመንግሥት ስላለ፤ ስልታቸው ቨዝግታና በደፈጣ የድንጋይ መሰረት እየጣሉ እያደመጥናቸው ነው። አስገራሚ ይሚያድረገው ደግሞ ለሀገረ ትግራይ ምስረታ በፕሮግራማቸው አጽደቀው “በተወዳዳሪ ፓርቲ” በሕግ ጸድቆላቸው እውቅና አግኝተው አብይ አሕመድ ፈቅዶላቸው የሚንቀሳቀሱ ሰብ ሕድሪ ፥ ባይቶና፤ ሳልሳየ ወያነ፥ ሰብዓ እንደርታ ወዘተ....ወዘተ.. ፡ አዲሰ አበባና ትግራይ እየተመላለሱ መሪ ያጣች አገር “ኢትዮጵያን ማውደም” መብታችሁ ነው ተብለው ያለ ስጋት እየተንቀሳቀሱ ነው። ዞምቢው ኢትዮጵያዊ ምሁር ግን ሰለዚህ ምንም አይተነፍስም።

ይህንን የሃገረ ትግራይ ምስረታ የሚተጉ በዘረኛነት ደዌ  የተመቱ  ፋሺስቶች “አማራ እና አማርኛን” “ኢትዮጵያን እና ሰንደቃላማዋን” እንዴት እንደሚያዩት ከአንድ የትግራይ ምሑር ተብየው ለዩኒቨርሲቲ ተማሪች ምረቃ ዕለት የጻፈውን ልጥቀስ ።

እንዲህ ይላል፡

Always remember that we have to keep fighting until we make sure the social and political contract that sustained and enabled the genocidal empire (Ethiopia) is dismantled. It is not something new. The Irish people have done it against the greatest empire to ever exist—the British Empire—and we will do it so.

For instance, during your graduation, you could have claimed that you feel so traumatized to listen to any Amharic speech delivered in front of you on your special day, and that you prefer it to be in English.

And also, no University—specially those in Tigray are mandated to use the genocidal flag to the gold medalists.»

እንዲሕ ያሉ አገር እና መሪ ለይተው ማየት ያቃታቸው ደናቁርት የትግራይ መሑራን “ትግራይ ታስራለች” የሚልዋት ትግራይ እራሳቸው በድንቁርናቸው እንዳሰርዋት አላወቁትም ውይንም እያውቁም ሊያምኑ አይፈልጉም። ለዚህ ሁሉ ውድመት ሲከተሉት የነበረው የፋሺስት ድርጅት እንደሆነ ግን ጨርሰው አይቀበሉትም። በውያኔነቱ የልብ ኩራት የሚሰማው ሲሳይ ሕሸ ይተባለ ሙዚቀኛ እና ካናዳ ቶሮንቶ ውስጥ የስደተኞች የሕግ ጠበቃ -በመለስ ዜናዊ ሞት” የገጠመው የትግርኛ ግጥም ምሑራኖቻቸው ለፋሺዝም ያላቸው ፍቅር ምን ያህል ጥልቀት ውስጥ እንደገቡ ማሳያ ነው።

እንደ ጥጋበኛ ፈረስ ሉጋማቸው (Balky/Nappy) ከበጠሱ ለሃገር ትግራይ መስረታ ከሚረጉት የትግራይ ፋሺስቶች አንዱ ኢንጅኔር ታደሰ የማነ ነው፤-

እንዲህ ይላል

«ትግራይ ታስራለች ብየ አምናለሁ። ስለዚህ «ኣን ሎክ ትግራይ/Therfore, unlock Tigray/» በሚል መመሪያ መጀመር አለብን። ለምሳሌ በቅርቡ በተደርገው «መኸተ» (የመክት ጦርነትና ዘምቻ) «ተአምር» የሰራ ሕዝብ ነው። ትግራይ እግር ከወርች መታሰርዋ እውን ነው። 90% ሕዝባችን ርሃብ ላይ ነው። ለማኝ ሕዝብ ደግሞ አክብሮት አያገኝም። ለማኞች ሆነን ዓለም ጀሮው አይሰጠንም። የተጋሩ ምኞትና ጉጉት ምንድነው? የኔ አስተሳሰብ ልስጣችሁ። ፍላጎታችን ዋስትና ያለው ሰላም እና ያልተገደበ ዕድገት ናቸው። እነዚህ ሁለት ጉጉቶች ማሳካት ይኖርብናል። ቢያንስ ቢያንስ የአፍሪካ ሮል ሞዴል የሆነች የሰው ልጆች የሚመኝዋት ትግራይ ማነጽ ነው  ይህንን እውን ለማድረግ የሲንጋፖር ትይዩነት እና ልምድ ከኛ ጋር ለዩነት ቢኖርም ፣ እጀግ እጅግ በጣም የሚመሳሰል ነገር ሰላለን ያንን ጠቃሚ ልምድ እንመልከት።

ሲንጋፖር በ1965 (በፈረንጅ አቆጣጠር) ወደ ማሌዥያ ፈደረሽን ስትጠቃለል፤ማሌዥያኖቹ “አንፈልጋችሁም ፤እሳት ልትጭሩብን ነው ስለዚህ ራሳችሁን ቻሉ ሂዱ አንፈልፍጋችሁም” ብለው ማሌዥያኖች ገፈተርዋቸው። የሆነው እንዴት ነው፤ የማሌዥያ ፓርላማ 126 ለ 0 ድምጽ አንፈልጋችሁም ብለው ድምፅ በመስጠት ፈደረሺኑን አንቀበላችሁም አሉዋቸ። በወቅቱ ሲጋፖርያዊያኑ የወሰዱት ውሳኔ «አንቀበላችሁም ካሉን  ማሌዥያዊያን የሚጓጉዋት ሲንጋፖር እናንጻለን/እንመሰርታለን!!” ያ ነበረ የወሰኑት ቃል። እኛም ጠላቶቻችን የሚጓጉዋትን ትግራይ እንመሰርታለን። ሲንጋፖራዊያን ማሌዥያዊያኖች ጂ ዲ ፒ (GDP) ሲነጻጸር፣ ሲንጋፖራዊያን ማሌዥያዊያኖች በ6 ዕጥፍ ጂ ዲ ፒ ይበልጥዋቸዋል። አንዳንድ አንባቢዎች  (ጂ ዲ ፒ) ምን ማለት እንደሆነ ያልገባችሁ ሰለምትኖሩ  GDP (Gross Domestic Product) ማለት ትርጉሙ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት በአንድ የተወሰነ ጊዜ ውስጥ የሚመረቱ ሁሉም የመጨረሻ እቃዎች እና አገልግሎቶች አጠቃላይ የገንዘብ ዋጋ ሲሆን ይህም የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ቁልፍ መለኪያ ሆኖ የሚያገለግል መለኪያ ነው።

እንግዲህ ሲንጋፖራዊያን ማሌዥያዊያኖችን በምጣኔ ሀብት ስለሚበልጥዋቸው  ማሌዥያዊያኖች  “የጉጉት ልሃጭ ማንጠባጥባቸው ብቻ ሳይሆን ማሌዥያዊያኖች ወደ ሲንጋፖር እየሄዱ ይሸቅላሉ።” ይላል።

ተናጋሪው ባያብራራውም፤ አንባቢዎች ግራ እንዳይገባችሁ ትግራይ እና ሲንጋፖር በጣም በጣም ይመሳሰላሉ የሚለው የተናጋሪው ንግግር ስሕትተ መሆኑ ልንገራችሁ። ሲንጋፖር ልክ እንደ ኤርትራ (ጣሊያን) በእንግሊዝ ቅኝ  ስትገዛ የነበረች ትንሽየ አገር ነች። የሲንጋፖርን በማሌዥያ ሕብረት ውስጥ መካተቱን በማሌዥያ ብሔርተኞች ተቃውሞ የደረሰበት ምከንያት ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም ዋናው ምክንያት፣ ሲንጋፖር ውስጥ ቻይናዎች አብላጫውን የህዝብ ቁጥር ሰለሆኑ ፣ ማሌዥያ ብሔርተኞች የቻናዎቹ በሲንጋፖር ሕዝብ ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸው ለማሌዥያዊያን የወደፊት ስጋት ሰለሚሆኑብን አንፈልጋቸውም .. በነበሩብት ይሂዱ ፣ የማለታቸው ምክንያት ዋነኛው ይህ ነው። 

በመቀጠል ተናጋሪው ለትግራይ መፍትኄ ሲያስቀምጥ (መፍትኄ ዝርዝሩ ለማስቀመጥ እዚግ ቦታ አይበቃም) ከየአሕጉራቱ ወደ መቀሌ መጠው ይተሰበስቡትን ታላላቅ አካዳሚክ የትግራይ ምሑራን እና የሃያምኖት የፕሮተስታንት የእስላም እና ካቶሊክ እንዲሁም ለኦርቶዶክስ ተጠሪ መሪዎችና ተናጋሪዎች ባጨሩ በትግርኛ እንዲህ ይቀጥላል፤

«...ስለዚህ እኛ ምን ማድረግ አለብን። የኛ ነገር እንደምታውቁት 90 በመቶ የተራበ ሕዝብ ነው ያለን፤ አገራዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታ ለመገመት ሚያስቸግር ህነታ ነው እየኖርንብት ያለው አካባቢ፡ድሆች ንነ፤ ባጀት ትሁት ነው፤ ትግራይ በመአከላዊ መንግሥት አትታወቅም (እውቅና የላትም) ፤ እልቂት ደርሶብናል ወዘተ ወዘተ....... ስለዚህ  ምን ይደርግ። መደረግ ያለበት የጫዋታው ቀያሪ ( Game Changer) ቁልፎች በትክክል ለይቶ ማውቅ ነው። ትግራይ እራስዋን ደፍታ እንደትኖር ትከሻዋ አጎምብሳ እንድትኖር የሚፈልግ ኃይል ትናንትም ነበረ ዛሬም አዲስ ኃይል አለ። አሁን እያሰብን ያለነው ልክ 4 ኪሎ ተቀምጥነ እንደነበርነው ነው እያስብን ያለነው (ይህ ስሕተት ነው)።

በዚህ አገር “የሃርድ ካረንሲ” (ጠንካራ የሆኑ የውጭ ገንዝቦች) ችግር አለ። ይህ የሃርድ ካርንሲ ወደ ትግራይ የሚያሸጋግርበት ስልት ቀይሶ ለትግራይ ፍጆታ ብቻ እንዴት መዋል እንዳለበት የትግራይ ኢንቭስተሮች ማሰብ አለባቸው።.....በማለት

( ሰውየ እያለ ያለው የሃገሪቱ ብር እንዲወደቅና እንደወደቀም በመገንዘብ “ሃርድ ካረንሲ” ወደ ትግራይ በማስገባትና በማከማቸት ሃገሪትዋ መውድቅዋ ስለማይቀር ግን “ገና ያ ከመሆኑ በፊት ለመጪዋ ሃገረ ትይራይ ግናባታ እንዴት እንደሚውል ነው እየነገራቸው ያለው።) ይህ ስልት ካሁን በፊት ትግራይ ኦን-ላይን በተባለ አፍቃሬ ወያኔዎች ሚዲያ “የኢትዮጵያ ብር ያላችሁ ወርቅ በመግዛት እና ወደ ውጭ አገር ገንዘብ (ሃርድ ካረንሲ) በመለወጥ ለትግራይ ግናባታ ክምች እንዲያደርጉ እና አገሪቱ እንድትወድቅ እንዴት እንደታቀደ ካህን በፊት እንድ መጣጥፍ እንደጻፍኩ ታስታውሳላችሁ ብየ እገምታለሁ።

ኢንጅኔር ታደሰ የማነ ንግግሩን በመቀጠል አጋሮቹን እንዲህ  ይመክራል፤-የተከማቹ mega projects (ትልልቅ ኩባንያዎች..... ወዘተ) (ባለፈው ጦርነትና በድንገተኛው ይመንግሥት ለውጥ እንዳይነው) ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው። ሰለዚህ በምትካቸው ምን እንተካ? ማድረግ ያለበን ኢትዮጵያ ውሥጥ የማይረጋ እና መቸውንም የማይድን ከባድ የምጣኔ ቀውስ አለ። በዚህ ምክንያት ሃገሪቱ የምግብ አቅርቦት ችግር ይገጥማታል፡ ይበልጥኑ የባሰ ሊገጥማት ነው።  So, we have to unlock Tigray at house hold level (የእያንዳንዱ አባወራ ቤት በምጣኔው ውስጥ ፤በፖለቲካው ውስጥ ፤በማሕበራዊ፤ በሃያምኖት፤ በኢኮኖሚ ወዘተ...ሚና እንዲኖሮው ማድረግ አለብን ማልት ነው።፡እነዚህ የተዘጉ ቁልፎች እንዲፈቱ የምንላቸው ምንድናቸው? መጀምሪያ ፖለቲካው መፈታት አለበት፤ እየተከተልነው ያለው ፖለቲካ የትግራይ ችግር የሚፈታ አይደለም (ሁሉም የትግራይ ተወላጅ እኩል የመናገርና ሃሳብ የምስጠት መብት መፍቀድ አለብን)። የኛ ብልጫ (በነፊት) ሆሞጂኒቲ  ነው። ሆሞጂኒይቲ ማለት አንድ መሆን ማለት ነው። በታሪክ በጎሳ፤ በሃይማኖት በታሪክ ሆሚጂኒቲ አለን። ይህ ግን ወጥ (አንድ) መሆን እንጂ አንድነት አያመጣም። ችግራችን ቁጥራችን በጣም ንኡሳን ነን ፤ ችሎታችንም ዝቅተኛ ነው። ስለዚህ ይልና 3 መፍትኄዎች ብሎ ካስቀምጣቸው ሰፊ ዝርዝሮች ውስጥ

 How to unlock Tigray (ትግራይ ከታሰረቺበት እንዴት እንፍታት) ለሚለው ፣ እንዲህ ያስቀምጣል፤

1ኛ equal political level (ሁሉም የትግራይ  ተወላጅ ያለ ምንም ቅደም ሁኔታ ድምፁ መሰማይት አለበት። ላልሆነ አንደ ትናነቱ ሳይሆን ወደ በጥበተ እና እርስበርስ ለነባላ ነው።) 2ኛ- elite of the elite in every sector (|ሊቀ ሊቃውንትን መፍጠር” የምስለኛል ወደ አማርኛ ስተረጉመው) ቁጥራችን ከብዙሃን ከሚባሉት ጋር እኩል ላምድረግ  quality (ጥራት) መኖር አለብን። ይህ ማለት ልሂቅ ምሑር፤ ሊሂቅ ገበሬ ፥ በየትኛውም “ሰክተር” የሙያ እና የንግድ ዘርፎች ሊሂቅ መፈጥር አለብን። 3ኛ- ገበያ፦ ሻጮች (አቅራቢዎች) እንጂ ገበያ ሸማቾም መሆን የለብንም። ሸማች ሆኖ “ፖሊሲ” ሊያዋቅር ሊያወጣ አይችልም። እሰራኤል ፥ ሲንጋፖር ፥ ቻያና “ሸማቾች ስላልሆኑ” አቅራቢዎች /አምራቾች/ ስለሆኑ ፖሊሲ አላቸው። ሰለዚህ ትግራይ ሸማች ሆና ፖሊሲ ማውጣት አትችልም ፤ አምራች አቅራቢ መሆን አለባት። ቁጥራችን ትንሽ ስለሆነ በየዘርፉ elite of the elite ለመፍጥር ከፈለግን ንኡስነታችንን በጥራት መቀየር እና በጥራት በልጠን መገኘት አለብን። እያለ ኢትዮጵያ የትግራይ፡ ሸቃይ እና ገብያተኛ (ሸማች) ትግራይ ደግሞ ለኢትዮጵያና ላካባቢዋ አቅራቢ ፥ አምራች እና ቀጣሪ የምትሆንበትን የሃገረ ትግራይ ምስረታ ስልት በሰፊው ይዘረዝራል።   

በመጨረሻ

ለዚህ ሁሉ ቅዠትና መከራ የዳረጋቸው ምንድ ነው? በሚል ልደምድምና ልሰናበታችሁ፡

የተቃወማቸውን ወደ “አገር እንዳይገባ አገር የነሱ ብቻ አድረገዋት”፡ ግማሾቻችንም ገድለው ከምድረ ገጽ እንደንጠፋ አድርገው፣ በመላው አፍርቃ እና በዱባይ እንዲሁም በሱዳን ፥ አሜሪካ እና በመላ ሃገሪቱ እንደ ዱባ ሐረግ የተንሰራፉት ከባድ ከባድ ኩባንያዎች፤ ትላልቅ ሕንጻ ቤቶች ፥ እርሻዎች ፥ ንግዶች አዛዥና አምራች ሆነው “ጠቅላላ የምዝበራውና ይበላይነቱ ጥጋብ” አላስችል አላቸውና ጦርነት ከፍተው “እኛ ትግሬዎች እናስልቀሳለን እንጂ አናለቅስም! ብላ ማይምዋ “አጀብነሽ” እንዳለቺው አልሆነላቸውምና መጨረሻው የአጀብነሽ ለቅሶና ሐፍረት ተከናንበው እነ ስብሓትና እነ ፥ እነ..... ውስጣቸው ረጥበው የቁም ሬሳ ሆነው ግብአተ-መሬታቸው አየን።

በህይወት ያሉትም “ከዚያ ዕብሪት ሳይማሩ አሁንም ወደ ሃገረ ትግራይ ቀዥት ገብተው ይቃዣሉ”፡ ግማሹም ወደ ተፉት ትፋታቸው ተመልሰው ትፋታቸውን ለመላስ ወደ አሥመራ ሄዱ፤ ግማሹም ጀነሳይድ ፈጸመብን ወደ አሉት አዲሰ አበባ ገስግሰው የአብይ አሕመድ ጫማ ላሽ ሆኑ። ለራስ ከፍ ያለ ግምት በመስጠት አጉል የሚኮፈሰው የትግራይ በሔረተኞች ዕብሪት ፣ ቀስ ብሎ እየተጋባበት የምናየው የአማራ ወጣትም ከዚህ እንደሚማር ተሰፋ አደርጋለሁ እያልኩ፡ የትግራይ ምሑራን ቅዠት ‘’ኢትዮጵያ የትግራይ ሸቃይ ፥ ተቀጣሪ እና ገብያተኛ (ሸማች) ፥ ትግራይ ግን ሸቀጥ አቅራቢ አምራችና ቀጣሪ የምትሆንበትን “ሲንጋፖር እና ማሌዥያ ትግራይ እና ኢትዮጵያ” የሚለው ከኤርትራ የተጋባቸው ቅዠት የት እንደሚደርስ ታዛቢዎች ሆነን እየጠብቅን ነው።

ሰላም እንሰንብት

ጌታቸው ረዳ

 

Tuesday, June 16, 2026

የገዳዮችን ስም እና መለያ መለውጥ ለአብይ እና ለኦነጎች አዲስ ታክቲክ አይደለም ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 6/16/2026

 

የገዳዮችን ስም እና መለያ መለውጥ ለአብይ እና ለኦነጎች አዲስ ታክቲክ አይደለም

ታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

 6/16/2026

በውስጥ መስመር ለጠየቃችሁኝ አንባቢዎች መልስ እነሆ

የተለጠፈው የኦሮሞ “ኢንተርሃሙዌ ቄሮ” የእጅ ጽሑፍ  ለማንበብ ሰላስቸገረን ምን እንደሚል ንገረን ላላችሁኝ፤ “ክርስትያን እና እሰላም አማራዎች” አንገታቸው የተቀሉበት ሜንጫ የያዘው የኦሮሞ  “ኢንተርሃሙዌ ቄሮ” ስር የሚነበበው ጽሑፍ የሚለው እንዲህ ነው፡

«ያለ ኦሮሞ ፈቃድ እንኳን ሽግ ዕጣን ማጨስ አይቻልም! ፍንፍኔ ውስጥ! ቄሮ...» 

ፍንፍኔ ውስጥ የሚሉት አዲሰ አበባን ነው

ሰሞኑንን አርሲ ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ አድራጊዎቹ አይ ሲስ እና የሶማሊያው አልሸባብ ነው እያሉ ዜና ሲያሰራጩ እየስማን ነው (እነሱ የሚፈጽሙት ጥቃት ቢኖርም ፤ ዋና ተዋናዮች አይደሉም፡ ተዋናዩ የኦሮሞዎች መንግሥትሰለፊው እና ኦነግ  ናቸው)። አብይ ከመጣ 8 አመት ውስጥ ወያኔ ከነበረበት 27 አመት የጭለማ ጊዜ ለአማራው፤ ላጋሞው ለጉራጌውና ለኦርቶዶክስ ክርስትያኖች እጅግ የከፋ የዘር ጭፍጫፋ የተፈጸመበት ወቅት ነው አብይን ከዚህ ነጻ ለማውጣት ከአብይ ጎን ተሰልፈው እኛኑን ሲሞግቱን እና ሲከላከሉለት ከርመው አሁን ተቃዋሚው የሆኑት ከፉዎቹ እነሱ ነበሩ። ላደረጉለት ድጋፍ ይቅርታም አይጠይቁም (ሐፍረት የሚባል የለም) በይፋ በሚዲያ ይቅርታ የጠየቀ አንድ ሰው ብቻ ነው የማውቀው እሱም ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ ብቻ ነው (ምስጋና ይገባዋል)።

አንድ ወንጀል በተፈጸመ ቁጥር “ዝም ማለት” ወይንም “የገዳዮችን ስም እና መለያ መለውጥ”  አማራን እና አምርኛን ፥ ኦርቶዶክስን እና ስንደቅ አላማን በጥርሱም በጥፍሩም እየቦጫጨቃቸው ያለው አፓርታይዳዊው የኦሮሞዎቹ ሥርዓት የተካነበት ተንኮል ነው።

ከ1983 ጀመሮ ሥርዓቱ የተዋቀረው አማራን ያገለለ ነበር፡ አሁንም ሶበታል አማራን ቅድሚያ በጠላትነት የፈረጀ ነው ስንል በማስረጃ ነው አንድ  ሥር ነቀል መፍትሄ እሰካለተደረገ ስርዓቱና የሥርዓቱ መሪዎች ሥልጣን ላይ እስካሉ ድረስ አማራ እና ኦርቶዶክስ በዘሩ እልቂትን መፈናቀል እየተደረገበት መቀጠሉ ነው። አማራን በማፈናቀልና በመፍጀት የተዋቀረውን ሥርዓት በስንት ደምና በትግላችን የመጣ ስለሆነ በደማችን እናስቀጥለዋለን፡ ይህንን ሕገመንግሥት የማይቀበል ከምርጫ ውጭ መሆን አለበትብሎ አብይ አሕመድ በማያወላዳ ግልጽ ንግግር መናገሩን እኮ ታሪክ የተዘገበው ንግግሩ ነው። ሥርዓቱ አምሐራን ነጥሎ ግምባር ቀደም ተጠቂ ያደረገ አፓርታይድ ስለሆነ አንቀበለውም የሚል አምሓራ አብይ እንደተናገረው ለጀነሳይድ የተጋለጠ፡ነው። የሩዋንዳው ሁቱው ፕረዚዳንት ሃቢአሪማናም ልክ እንደ አብይ አሕመድ ቃል በቃል ደግሞት ነበር

አማራው በረሰብ ምሬቱን እየገለጸ ያለውይህ ሥርዓት ማንነታችን እየለየ እየገደለን ነው እና ሥርዓቱ ይወገድልንሲሉ አብይ ደግሞ14 አመቴ ወደ ጫካ ሄጄ በደሜና በላቤ ታግየ የገነባሁት ሥርዓት ስለሆነ አስቀጥለዋለሁ እናንተም መጨፍጨፋችሁ ይቀጥላል ነውየመልእክቱ ቀጥተኛ አቋሙ።ያ ትክክለኛ ንግግሩ ደግሞ ከሥር ቃል በቃል አቀርባለሁ።

ስለዚህ አማራን እያስገደለ ያለው ሥርዓት በመሪነት የተኮፈሰው አብይ አሕመድ እና ከየጫካው እና ከአወሮጳ እና አሜሪካ ሰብሰቦ ባለሥለጣኖች ያደረጋቸው የኦነግ መሪዎች እና አባሎች ተባብሶ ለቀጠለው ለዘር ጭፍጨፋው ወንጀል ተጠያቂዎች ናቸው

 ክርስትያን አማራ እና እሰላም አማራ  በየቀኑ እየተባረረ፤ መጨፍጨፉ ጨፍጫፊዎችም እነማን እንደሆኑ በተለያየ መልካቸው ሰለፊ (አክራሪው ውሃቢያ) ፤ አይሲስ ወዘተ ይባል እንጂ ያው ከላይ በተጠቀሰው ድርጅትና አመራሮች ማኒፌስቶ (አይዲኦሎጂ) የታጠቡ ከፍሎች ናቸው። ኦርቶኦክስን ላምጥፋተ እና የጀግኖች ሃውልቶችን በማፍረስ አማራን በመጥላትና አማራን በማስጨፍጨፍም ይሁን አማርኛ ቋንቋን ለማጥፋት ስኬታማ ናቸው ብሎ የሹመት እውቅና ሰጥቶ፤ ግድያና ጥላቻ የሚያስፈጽሙበት ዕድሎች ፣ (መኪኖች፥ መሳሪያዎች፥ የባንክ ዘረፋ..) መርቆ በሩን የከፈተላቸውና ወደ አገር እንዲገቡ የፈቀደላቸው ነብሰ ገዳዮች እና ወንጀለኞች አብይ አሕመድ ነው። 3000 አመት እንገዛችሗለን ብሎ አዲስ አባባ ውስጥ በቴ/ቪዥን ቀርቦ የተናገረው ሌንጮ ባቲ የአብይ ከፈተኛ ታማኝ ሰው ነው አደለም እንዴ?

እነ ታየ ደንዳኣ አማራው ቡራዩ ላይ ምን ይሰራል በጭነት መኪና ተጭኖ ወደ ጎጃም ይሂድብሎ የተናገረው አሁን የታሰረው ታየ ደንዳአ ነው፣ አደለም እንዴ? ከረሳችሁት ሙሉውን ንግግሩን እነሆ፡

«በአዲስ አበባ ዙርያ ጎጃሜ አምጥተው ካስፈሩ በኋላ “ሕገ ወጥ ቤቶች እንዳይፈርሱ ሲከላከሉ የነበሩ ነፍጠኞች ማንነታቸው በውል ስለታወቀ የነፍጠኛ ባለቤት መሆናቸው ሰልታወቀ ከዚህ  በኋላ ሂሳብ እናወራረዳለን”።

(ታየ ደንዳአ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ኦደፓ OPDO አመራር)

 የኦሮሞ ቄሮ ኢንተርሃሙዌው ካድሬ «ሽመልስ አብዲሳ “ነፍጠኛን በቀበረን ቀብረነዋል፤አማራን ሸውደንም ሆነ አሳምነን በቁጥጥራችን አድርገን መቸም ቢሆን እንደማይነሳ አድርገን ቋንቋውን አጥፍተነዋል፡ ላሚትዋንም ወተትዋንም እጃችን ውስጥ ገብታለች…..”

እያለ ኢንተርሃሙዌው ቡድን በግልጽ አዋጁን ለተከታዮቹ ያበሰረው ሽመልስ አብዲሳ ማን ነው የሾ? እሰካሁንስ ለምን ሥልጣኑ ላይ ቆየ? ይህ ሁሉ ፍጅት የዘር ጥቃት አዋጅ ነው ተብሎ አቤቱታ ሲቀርብለትም አብይ አሕመድ ለምን በንግግሩ አልተከፋም? ምክንያቱም ፍላጎቱ እየፈጸሙለት ስለሆነ ነው። ለዚህ ነው አልሸባብ ምንትስ እየተባለ ድብብቆሽ እይተደረገ ያለው።

የባሌ ሮቢ የጀነሳይድ አዋጅ እስኪ ላስታውሳችሁ።

የባሌ ሮቤ ቅድመ ጭፍጫፋ ከጀርመን EHRC ጽ/ቤት ለኦነጋዊው የአብይ አሕመድ መንግሥት ያስጠነቀቀው ደብዳቤ መጀመሪያ ለስነብባችሁና ከዚያም ወደ የኦሮሞ ኢነትርሃሙዌው ቡድን እንመለከታለን።

ስለ ባሌ ሮቤ ዘርና ሃይማኖት ተኮር ቅድመ ጭፍጨፋ ማስጠንቀቂያ EHRC (Ethiopian Human Rights Committee) ከጀርመን 

<<አስቸኳይ መግለጫ

 27 October 2019

አስቀድሞ ማስጠንቀቅ የዜጎችን ህይወት ለመታደግ” EHRC (Ethiopian Human Rights Committee)

በባሌ ሮቤ ባለፈው አርብ ዕለት በግልጽ በጥቃት አድራሾቹ ማስጠንቀቂያ የተሰጠበት ከሰኞ ጀምሮ ሊያካሂዱት ያስታወቁት የጅምላ ጭፍጨፋ እንዳይፈጸም መንግሥት የዜጎችን ህይወት የመጠበቅ ሃለፊነት አለበት።

በዛሬው ቀን ዕሁድ ጭምር ዜጎች ከሃይማኖት እና ዘር ተኮር መሰረት ያደረገን በህይወት ላይ ያነጣጠረን ጥቃት በመፍራት በቤተክርስትያን ተጠልለው ይገኛሉ።

የተቀሩት ቤታቸውን ቆልፈው በጭንቀት እያሳለፉ ነው። ስልካቸውን ለድረሱልን የስልክ ግንኙነት ለማድረግ ለመደወል ስለካቸው ካርድ መሙላት አልቻለም። ሱቆች ዝግ ናቸው።

ይልና በዚያ ባለፈው ሳምንት ዘርና ሃይማኖት ላይ ያነጣጣረ ጭፍጨፋ እንደተካሄደ እንደገና ያ መሰል ጭፍጨፋ እንዳይደገም በድጋሚ መንግሥትን ሲያስጠነቅቅ እንዲህ ይላል፤

“በአካባቢው የገባው የጥቃት ሃይል በቁጥር ከጥቃት አድራሾቹ በትጥቅም በቁጥርም በጣም ስለሚያንስ ስጋት ጨምሯል። ይህንን በባሌ ሮቢ በጥቃት አድራሾች አርብ ዕለት ማስጠንቀቂያ የተሰጠበትን የ“ሰኞ እንመለሳለንማስጠንቀቂያ ቀጣይ ዘር እና ሃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ እንዳይካሄድ የዜጎች ህይወት እንዳይጠፋ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ተቀብሎ ከግምት በማስገባት የዘጎችን ህይወት ለመታደግ እርምጃ እንዲወስድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ ይጠይቃል፤

(ስዩም ሀብተማርያም ጀርመን) >>

ድምቀትና ሰረዝ የተጨመረ።

አሁን ደግሞ ወደ ኦሮሞው ኢንተር ሃሙዌው ጨፍጫፊው ቡድን አዋጅ እነሆ!

በባሌ /ሃገር (ክልል) በሮቤ ከተማ ደግሞ የከተማው ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ በመሃል ሜዳ ቆሞ በብዙ ሺሕ ሰው ፊት

 

ከባሌ አባ ገዳዎች፤ከሃይማኖት አባቶች፤ከአገር ሽማግሌዎች እና ከቄሮዎች የአቋም መግለጫ ከተንጣለለው የገበያ አደባባይ በቪዲዮና በድምጽ የተቀረጻ አዋጅ ከድምጽ ወደ ጽሑፍ የገለበጥኩትን ላስነብባችሁ እንዲህ ይላል፦

 

ዶርዜና ነፍጠኛ ከሚባል ማንም ሰው ግንኙነት አድርጎ የተገኘ ሰው ፈጣሪ መአት እንዲያወርበት በሼኮች የተረገመ ሲሆን ይህንን ትዕዛዝ ተላልፎ የተገኘ ከነፍጠኛ እና ከጠላት ለይተን አናየውም። ይህን በተመለከተ

1) ከዛሬ ቀን ከዚች ሰዓት ጀምሮ ከነፍጠኛ እና ከዶርዜ ንግድ አንገዛም አንሸጥም።

2) ከዛሬ ጀምሮ መግብ መጠጥ ልብስ ሲገበያይ የተገኘ ሰው የተረገመ ይሁን።

3) ከነፍጠኛ እና ከዶርዜ በልተህ ብትገኝ ፈጣሪ በሽታ ያድርግብህ፤

4) ይህ ድርጊት ፈጽሞ በሃይማኖት በሸኮች የተወገዘ ነው።

5) የኪራይ ቤት ወይንም ሱቅ በረንዳ ይህንን የመሳሰሉትን ከዛሬ ጀምራችሁ ካሁንኑ ሰዓት አከራይታችሗቸው ከሆነ እንድትነጥቁዋቸው።ያላከራያችሗቸው ከሆነም እንዳታከራይዋቸው። እንጠይቃችሗለን፡

6) መሬት እና ቤት እንዳትሸጡላቸው። አሁንም ለመውጣት ተዘጋጅተው ለመሸጥ ከፈለጉም እንዳትገዝዋቸው። መሬቱ የናንተ ነው፤ቤቱም የናንተ ነው።

7) የእህል ወፍጮ ቤት የንግድ ተቋማትም እንዲሁ የመኪና አገልግሎት የመሳሰሉትን አገልግሎቶች ለነዚህ ሰዎች አትፍቀዱ፤ እናንተም እንዳትጠቀሙ። ይህንን አድርጎ የተገኘ ነፍጠኛ ነው ማለት ነው።

8) ዛሬ ሰልፍ የወጣነው ጀግናችን የቄሮ አባት የሆነውኦቦ ጃዋር መሓመድላይ ጠላት ለመግደል ሙከራ ስላደረገበት ድምጽ ሆነንለት ነው። ጃዋርን የሚቃወም መቼም ቢሆን የባሌ ሕዝብ ጠላት ነው።

9) የልጆቻችን ህይወት ያጠፉ የመንግሥት አካል የሆኑ፤ ደሞዝ የሚከፈላቸው መስተዳደሮች፤ ትናንት ልጆቻችንን የገደሉ፤ለፍረድ ይቅረቡልን።

 ይላል።

እንግዲህ ይህንን የዘር ማጥፋት ጥሪ ከተላለፈ በኋላ የኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት ድርጅት /ቤት የዘር ማጥፋት አዋጁ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት አደጋውን ለማስቆም ለአብይ አሕመድ ያስተላለፈው አስቸኳይ ጥሪአስቀድሞ ማስጠንቀቅ የዜጎችን ህይወት መታደግየሚል የባሌ ሮቤ አክራሪዎቹ እና አባ ገዳዎቹ እንዲሁም ሼኮች እና ቄሮዎች ከሰኞ ጀምሮ ሊወስዱት የተዘጋጀውየዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ አዋጅ/ጀነሳይድመግለጫ በጽሑፍ አስታውቆታል።

 የተፈራው እልቂትም ደረሰ። በዛው ርብ ዕለት አዋጅ ታውጆ ለሰኞ እንመለሳለን ያሉ ታጣቂዎች ዓርብ ጥቂት ቀናት በፊት በአማራ ብቻ ሳይሆን በጋሞ ነገዶች ላይም ጥቃት ፈጽመው ነበር መንግሥት ይህንን ያውቃል። የጋሞ ነገዶችም አርባ ምንጭ ውስጥ ለዜጎቻቸው ስጋትና ደህንነት ሲሉ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። ሰሚ አልነበረም 

ይሁንና እነዚህ በሃይማኖታቸው እና በነገዳቸው ተነጥለው ለግድያ የታጩ በሺዎች የሚቆጠሩ ዶርዜዎች እና ክርስትያን አማራ እና እሰላም አማራዎች እንዲሁም በቤተክርስትያን ተጠልለው በፍርሃት ቆፈን እየተንቀጠቀጡ፤ የአብይ አሕመድ መንግሥት እንዲያድናቸው የመንግሥት ያለህ /የአብይ ያለህያሉ ሲማጸኑ ነበር። ይህ ደግሞ በደምብ መረጃውም ጥሪውም ደርሶታል።

 ጋሞዎች ምን የሚል መልእክት ለአብይ አስተላለፈው ነበር? እንዲህ ይላል

መንግሥት ሕግን ማስከበር የሚችል ከሆነ ያስከብር የማይችል ከሆነም እራስችንን ለመከላከል የምንጠብቅበት መንገድ ሁሉ ለመጠበቅ እንገደዳለን”።ብለው ነበር፡ 

ሆኖም አብይ ይህንን አቤቱታ እና ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውምግድያው ይቀጥላል፤ ከዚያ ይሰክናልእያለ ነበር። በዚያው አዋጅ መአት ጋሞዎችና አማራዎች በሚያሳዝን አገዳደል ተጨፈጨፉ ይህ የሆነው ጥቅምት በፈረንጅ ኦክተበር መጨረሻ ገደማ 2019 ነው።

ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊውን አርዶ በላው ሲባልእርዱ ይቀጥላል፤ እስኪሰክን ግን ዝም በሉ፤ እኛ ከሠልጣን ከወረድን በመቶ ሺዎቹ ይታረዳሉስለዚም እርዳን አትበሉ ይልቅኑስ አመስግኑኝ! ሲል እርዱ ሕጋዊ አድርጎታል እኮ አብይ አሕመድ

አማራ እየተገደልን ነን ብለው አቤቱታ ሲያመለክቱም አብይ ለሚታረዱ እና ለተፈናቀሉ አማራዎች /ክርስትያነ እና እሰላም አማራዎች/ አልቃሾች ሲል ሰድቧቸዋል።

ቃል በቃሉ ልጥቀስላችሁ፡_

 እንዲህ ሲል፤

አንድም ሰው እሚያመሰግን የለም። ከእስላም አፍአልሓምዱላህንተነጥቋል። ክርስትያናትም ማመስገን የለምማልቀስ ብቻነው። አልቃሽ ሕዝብ ደግሞ አይሻገርም። ችግር ብቻ ነው የምሰማው።እናንተን እያረጋጋሁ ስራየን ልሰራ አልቻልኩም ሕዝቡ ሰላሙን ካልጠበቀ ይህ አሁን የሰማችሁት ልቅሶ ትናንትናም ብዙ ልቅሶ ነበር፤ አሁንም እናንተንም ሸኝቼ አዲስ አልቃሽ ይመጣል፤ የኔ ሥራ እምባ መጥረጊያሶፍት ይዞ መቅረብ ብቻ ሆኖ ቀረ። ሁላችንም እየተጋፋፋን እንዴት እንዲህ ሊሆን ይችላል? አደራችሁን በሚቀጥለው አመትም እንደዚሁመሃረምይዛችሁ ኑ፤ እንዳትረሱ። ወንድሙን ወንድሙን መንገድ የሚዘጋ ከሆነእኔ ምን አድርጌ እፈታዋለሁ?’ ሃይማኖታችሁ እንኳ የማይገዛችሁ ከሆነ? ምን አደርጋችሗለሁ እኔ! በልቅሶ ብዛት አገር አይገነባም እና ትንሽ እንኳን ብትሆን እያመሰገንን እንኑር።

ሲል ባለቤትዋ አንገ በካራ የታረደባት ሚስት ህጻናት በካራ የታረዱባ እናት፤ ሰውን ሰው በልቷል ብሎ ‘አቤቱ ሆይ! አድነን ፤ወታደር ላክልን፤ በክልልህ የሾምካቸው መሪዎች እየገደሉን ነው፤ እነሱን አስወግደህ ጤነኛ መሪዎችን አምጣልን አብያተ ጸሎታችን ተቃጠለብን፤ ብለው አቤት ለሚሉ የሃይማኖት መሪዎች እና ምእመናንእኔ ምን አድርጌ እፈታዋለሁ?’ለምን አታመሰግኑኝም ማልቀስ ብቻአልቃሾችእያለ ጉልበት የሌላቸው እናቶች እና ደከማ ተጠቂውን የሚሳደብ፤ ለሚቀጥለው ዙርም 'መሃረም አትርሱ' የኔ ስራሶፍት ይዞ አልቃሹን እንምባ ማበስ ሆኖ ቀረእያለ እራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ነብሰጡሮች እና አረጋዊያን እና እናቶች ከመኖርያ ቤቶቻቸው እየተጎተቱ ወደ በረንዳና ጫካ ሲጣሉ፤ አብይ ደግሞ አቤት ስላሉ «ማመስገን የለም “ማልቀስ ብቻ” ነውአልቃሾች እና ምስጋና ቢሶችእያለ ያሾፍባቸዋል

ሰሞኑን ደግሞ አርሲ ውስጥ ከርስትያኖችን ያረደ ቡድን አይ ሲ ስ እና አልሸባብ ነው ማለት ጀምረዋል ። አይ ሲ ስ እና አልሸባብ ከሆኑ ድረሱልን ብለው አቤቱታ ስላቀረቡ ቀሳውስቱን ወደ ጣቢያ ውሰዶ ያሰራቸው  “አልሸባብ” ነው? ታዲያ አርሲ ውስጥ አልሸባብ የራሱ ፖሊሶች እና እስርቤቶች ካለው አብይ ምን እያደረገ ነው?

16ኛው ክ/ዘመን የተደረገው አንዳንድ ጎሳዎች ከዚህ ዓለም የመደምሰስና የመዋጥ ወንጀል፥ የጾታ መደፈር ፥የንበረት ዝርፊያ ፥ ነባር ሕዝቦችን ባርያ (ገባሮ) የማድረግ ፥ የቋንቋዎች መጥፋትና መከለስ  ፥ የከተሞችና የገጠሮች የትራሮችና ውነዞች ሥም መለወጥ ፥ የቅርስ እና የታሪክ ዘረፋ እና እልቂት ሲደረግ “ብዙዎቹ የኦሮሞ ሊሂቃን” በዛው ዘመን ተፈጸመውን ግልጽ የሆነ የራሳቸው ታሪክ ጸሐፍት ድርጊቱን ሳያዛቡ የዘገቡት የሕዝብ ዕልቂት እና ወረራ  ጥያቄ ስንመለከት፤ የዛሬ ኦሮሞ ምሑራን  ጋ” ላ የሚል ቃል ‘ኦሮሞ’ በሚል መለወጥ አለበት በማለት ሥልጣን ከያዙ በኋላ ለውጠውታል። ይህ የታሪካ መበረዝ ሆን ተብሎ ላንድ ምስጢር የተደረገ ተልዕኮ ነው። የኦነግ መሪዎች ፍላጎት ግልጽ ነው (አንድም ወረራውን አያምኑበትም፤  ሌላው ደግሞ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀልና ወረራ በዛኛው  በሚታወቁበት ስም ስለነበር ያንን ስም ማስቀጠል ወንጀሉን ይፋ ማድረግ ሆኖ ስለተሰማቸው አዲስ የስም ለውጥ ያደረገላቸው “ዮሀን ከራፍት  የተባለ ጀርመናዊ ፓስተር” ተለዋጭ ስም በመቀበል  ያንን የማመለጫ እና መደበቂያ ስልት ተጠቅመውበታል።

  እውነትን መጣስ ነውር ነውና ነገሩን ማድበስበስ እስከ መቸ?  ታሪክ የዘገበው እውነታ በኢትዮጵያ የሶስት መቶ አመት ጥፋት የፈፀሙ ጋ” ላ  ይባላሉ እንጂ ኦሮሞ አይደሉም። የኢትዮጵያ ታሪክ ነውና የሞቱትን፣ የተዘረፉትን ሀብቶቻችንን፣ የተቃጠሉትን ቅርሶቻችንን መታሰቢያ ማቆየት የእኛ ኃላፊነት ነው። ከአክሱም መጥፋትና ውድቀት ጋር የተፈጠረውን ባዶነት ማስረዳት ባለመቻላችን የፈጠረውን ክፍተት እንዴት እንደምንገልጸው የምታውቁት ታሪክ ነው።

ያለፈውን ታሪክ ለመርሳት ሰዎች ራሳቸውን በሌላ ስም እንዲሸሽጉ መፍቀድ አይገባም። በተለይ ደግሞ ኦነግ በፈለሰፈው  "ኦሮሞ" የሚል የነገድ ስም "ኦሮሚያ" በሚባል ያለነበረ አዲስ አካባቢና ስም ሊጨፈጨፉን የጀመሩ እና ወደፊትም ሊጨፈጭፉን ቃል የገቡ ሰዎች ገና ከጅምሩ ጭፍጨፋን ሀ ብለው ሲጀምሩ ሀረር ውስጥ አማራዎችን ወደ ገደል ወርውረው ጨፍጭፈዋል፣ እንደ አርሲ አርባ ጉጉ አካባቢዎች “ሰው አቃጥለው” ፈጅተዋል።

በግልጽ እና በይፋ አማራን ብቻ ሳይሆን የተቀረው ኢትዮጵያዊያኖችን ከማስፈራራት በጭራሽ ቦዝነው አያውቁም። የኦነግን የፖለቲካ ፕሮግራም አንብቡ። አቢይ እና ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም በውስጥም ሆነ በዲያስፖራ የሚኖሩ የኦነግ ተከታዮች በሙሉ (እንደ ፀጋዬ አራርሳ - እጅግ በጣም የበታችነት ስሜት የተላበሱ ግለሰቦች) አማራን (ነፍጠኛን) እና ኢትዮጵያን ለማንም የማትሆን ብትንትን ያለች ሀገር እንድትሆን ይዝታሉ፥ የጀግኖችና የሀገር ስም ሲያጠፉና ሲሳደቡ ሰምተናል።

የ"ኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ" ታሪካችንን የነፍጠኛ ታሪክ ብሎ ሲናገር እና ሁላችንንም ከጫማው በታች እንደሚረግጠንና ሃገሪቱ አማርኛ አጥፍታ ኦሮምኛ እንድትናገር እንድሚያደርጉ ነግሮናል።

አስገራሚው ነገር ሊሂቃኖቹ እራሳቸው ሲጠሩበት የነበረ ስም እና  የኦነግ ራዲዮ ከሶማሊያ ምድር «ይህ የጋ’’ላ ነፃ አውጪ ራዲዮ ጣቢያ ነው” እያሉ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በጆሮየ ሰስማችወ የነበርውን ወቅት አስታውሳለሁ። ለምን ይዋሻሉ? እራሳቸውን ጋ;ላ ብለው ይጠሩ ነበር። እስከ ዛሬ ድረስ በኬንያ እና በሶማሊያ ጋ;ላ የሚል የጎሳ መጠሪያ አለ (አምስረጃውን ካሁን በፊት ለጥፌዋለሁ)።  ብታሪክ መጽሐፍት እሰከዚቺው ደቂቃ ድረስ “ኦሮሞ” የሚል የተጻፈ የኢትዮጵያ ምንጭ የለም – ዜና መዋዕል ወይም ጂኦግራፊያዊ ምንጮች፣ ወይንም በወቅቱ የነበሩት ሊቅ “አባ ባሕሪ” መጽሐፍቶችም ይሁን  የውጭ ምንጮች  ጋ፤ላዎች ሰለተባሉ የተለያዩ ጎሳዎች እንጂ “ኦሮሞ”  የሚል ስም የጠቀሱት የለም። እያወራን ያለነው እውነተኛ ታሪክ እንጂ የፈጠራ ስም አይደለም።ያለፈውን ታሪክ ለመርሳት ሰዎች ራሳቸውን በሌላ ስም ሊሸሽጉ ቢምክሩም ታሪክ አይፈቅድላቸውም። ቢሞከርም እየሾለከ ይወጣል። ታሪክን አፍነዋለሁ፤ ለጨብጠው ነው ማለት  ሜሪኩሪን ለመጨበጥ መሞክር ነው

አሁን ሰሞኑ እየሆነ ያለው ያንን ሽሸጋ ነው። አርሲ የተፈጸምው ጭፍጨፋ የሶማሊያ አልሸባብ እና አይ ሲስ በተባሉ የውጭ ሃይሎች እንጂ በሀገር ውስጥ ገዳዮች አልተፈጸመም ይሚል በስፋት እይተሰራጨ ነው። ያለፈውም ይሁን አሁን እይተፈጸመ ያለው ወንጀል ላለመርሳት ሰዎች ራሳቸውን በሌላ ስም እንዲሸሽጉ መፍቀድ አይገባም።የገዳዮችን ስም እና መለያ መለውጥ ለአብይ እና ለኦነጎች አዲስ ታክቲክ አይደለም

Ethiopian Semay