ዐቢይ አሕመድ ባድመ ላይ የሰቀለው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ !!! (አቻምየለህ ታምሩ)
October
1, 2019 Ethio Semay
ዐቢይ አሕመድ
ባድመ ላይ
የሰቀለው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ !!!
አቻምየለህ ታምሩ
ዐቢይ አሕመድ ስለ ባድመው ጦርነት አውርቶ አይጠግብም። ሻዕብያን ካሸነፉ በኋላ በሳሞራ ትዕዛዝ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሰቀለው እሱ እንደሆነ ነግሮናል። ዛሬ ታዲያ ተረኛ ሲሆን ሕገ ወጥ ያድረገውና ከሰሞኑ ደግሞ ባገሩ ከፍ ብሎ በመውለብለቡ ሕገ መንግሥታቸውን እንደሚጥስ የነገረን ባድመ ላይ እሱ ራሱ በ1991 ዓ.ም. የሰቀለውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ነው። እንግዲህ! ዐቢይ አሕመድ አሕመድ ሕገ ወጥ ሊያደርገው የሞከረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የመንፈስ አባቶቹ ተላላኪ በነበረበት ወቅት ጌቶቹ ጥጋብ ንፍት አድርጓቸው ሱሪ ካስታጠቃቸው ከሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ወይንም ከሻዕብያ ጋር በተቆራቆሱበት ወቅት ጦርነቱን አሸነፍን ብለው በ1991 ዓ.ም. ከታች በሚታየው መልኩ በባድመ ምድር ከፍ አድርጎ የሰቀለውንና የ “ሌተናት ኮሎኔልነት” ማዕረግ ያስገኘበትን ሰንደቅ ዓላማ ነው። ልብ በሉ! ወያኔዎችና ኦነጋውያን ሕገ መንግሥታችን የሚሉትን የሕወሓትና የኦነግ ፕሮግራም በኦፊሴል በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫኑት በሕዳር 1987 ዓ.ም. ነው። ከታች በተንቀሳቃሹ ምስሉ ላይ የሚታየውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት በባድመ የተካሄደው ግን በ1991 ዓ.ም. ነው። ይህ ማለት በ1987 ዓ.ም. የጫኑብንን ሕገ መንግሥታቸውን ዐቢይ አሕመድ ራሱ በ1991 ዓ.ም. ልሙጡን ሰንደቅ ዓላማ ባድመ ላይ ሲሰቅለው ጥሶታል ማለት ነው። ዐቢይ አሕመድ አክብሩልኝ የሚለው ሕገ መንግሥት እንግዲህ እሱ ራሱ ባፍጢሙ የደፋውን ደንብ ነው። (posted on Ethio Semay)
No comments:
Post a Comment