Sunday, June 30, 2019

ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎቹ እና ደም ተፊው የ666ቶቹ ተቀጣሪው ጋኔል (ክፍል4) ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎቹ እና ደም ተፊው የ666ቶቹ ተቀጣሪው ጋኔል (ክፍል4)
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

ትችቴን ከመጀመሬ በፊት በሚከተለው ንግግር ጥቅስ ልጀምር፡

“አማራን ለማፍረስ ያልተሰራ ሴራ የለም። ይሄ ምድር ላይ የተቀበረ ሳይሆን ምድር ላይ ወጥቶ እያየነው ያለው ነው።” (ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ)

“በፍቅር ከመጡ አማራዎች ስለሆነን ልብሳቸውንም ቢሆን አጥበን ንቀበላቸዋለን። በጠብ ከመጡ ግን ልብሳቸው ላይ እናሸናቸዋለን። ለዚህ መዘጋጀት አለባቸው!” (ዘመነ ካሴ ለደብረማርቆስ ወጣቶች ካደረገው የድምፅ ንግግር ወደ ጽሑፍ ከለወጥኩት ጥቅስ)

አገሪቷን በደም እየበከለ ተመናምናም ቢሆን አገር ተብላ ስትጠራ የነበረቺው አገር “ወደ መቃብር” ልትጠጋ “አንድ አርብ” ብቻ ያስቀራት አብይ በሚል ስም የሚጠራው ትልቅነቱን ያዋረደ “የአናርኮ ፋሺሰቶቹ መሪ አብይ አሕመድ” በሚያስደነግጥ ሂደት “በ12 ወራት” አገራችን ከድጡ ወደ ማጡ አስገብቶ እናቶች፤አባቶች እና ህጻናት የደም እምባ እንዲያነቡ አድርጓል። ይህ ደም የጠማው ግለሰብ መጽሐፍ ቅዱስ የጠቀሳቸው የ666ቶቹ ተቀጣሪ አባልነቱን ተጠቅሞ ጸረ ኢትዮጵያ ሃይላት ከጀርባው አስቁሞ በሕዝባችን ደም ተጨማልቋል። ለ27 አመትም ሆነ የስለላው እርካብ ረግጦ መንግሥታዊ መንበሩን ከተቆጣጠረ በ12 ወራት ውስጥ በሕዝባችን ላይ የደረሰው አሳዛኝ ጥቃት ተጠያቂ ነው።

 የመጀመሪያው ጠላቱ አማራ መሆኑን ገና ከመነሻው የመጀመሪያው የትግራይ ጉብኝት አድርጎ ወደ ባሕር ዳር ሄዶ አማሃራዊ ችግሮች በሚመለከት ለቀረበለት ቅሬታና ጥያቄ  የመለሳቸው  ‘ጸረ አማራ መልሶች’ ሲመልስ ለማን እንደቆመ ግልጽ ካደረገበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ በአማራ ሕዝብ ላይ ጥቃቱ ተጠናክሮ አሁን ላልንበት የነጀኔራል አሳምነው ጽጌ አሳዛኝ ሕልፈት እንድናይ የአብይ አሕመድ ጸረ አማራዊ የሴራ ውጤት ነው።

 ይህ አገር የማፍረስ ሴራው እንዲሳካም ‘ባንክ የሚዘርፉ፤ ቤተ ጸሎት የሚያቃጥሉ፤ሴቶች የሚደፍሩ፤ አረጋውይንን የሚደበድዱ የየኦሮሞ ዋልጌዎችን  መንግሥታዊ ከለላ እና ተሳትፎ እየተደረገላቸው ቸል ብሎ በማየት፤ የፈለጉትን ስራ እንዲሰሩ ፈቅዶ በሚሊዮን ዜጎች እያፈናቀለ ቤቶቻቸውን በማፍረስ እናቶችንና ህጻናትን ለዋይታ ጩኸት የዳረጋቸው ዋና ተጠያቂ የ66ቶቹ ተቀጣሪው “እርካብና መንበር” መጽሐፍ ደራሲው አብይ አሕመድ መሆኑን የሕግ እና የታሪክ ባለሞያዎች ሊዘገቡት ይገባል።

የዓለም የዜና መስመሮች አጣብቦ እያነጋገረ ያለው ሰሞኑን ጎጃም ውስጥ ባሕርዳር ከተማ የታየው የመገዳዳል አሳዛኝ ክስተት ከምን የተከሰተ ውጤት ሳይሆን አብይ አሕመድ የትግሬ የበላይነትን ከኦሮሞ ጋር አቀናጅቶ “ባንዳ አማራ ባለሥልጣኖችን” በማቀፍ ‘ዋልጌ የኦሮሞ ባለሥልጣኖችንና ሥርዓተ አልባ የሆኑ የኦሮሞ “ቄሮ” ነፍጥ አንጋቾች “ጉልበት አግኝተው” ሰላማዊ አማራ ገበሬዎች በሚኖሩበት ቦታ ሰርገው እየገቡ ሽብር እየነዙ፤ አማራዊ ስነ ሉቦና እና አማራዊ ታጋዮችን ለይቶ በማጥቃት ‘አዳክሞ ላንዴና ለመጨረሻ ተከብቦ በስርዓተ አልባ ቄሮዎች ጫማ ስር እንዲወድቅ እየተደረገ መሆኑን” የተመለከቱ “የአማራ አገራውያን ታጋዮች” የሰነዘሩት የጸረ-ከበባ ክስተት እንደሆነ መጠራጠር የለባችሁም

ይህንን ከበባ ተሎ ብሎ የገባቸው ‘ሃገራውያን የአማራ ታጋዮች’ “ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ፤ አርበኛ መሳፍንት ተስፋው፤ ወጣት ዘመነ ካሴ…ወዘተ” እየመጣ ያለው ከበባ በንግግሮቻቸው ግልጽ አድርገዋል። ስጋታቸው አደባባይ ላይ ሳያመነቱ ሊገልጹት የተገደዱበት ምክንያትም እየጎለበተ የመጣው “ኦሮሞዊ ጡንጫ” ስጋቱ ለነሱ ብቻ ሳይሆን ለአገሪቱም ስጋት እየሆነ መምጣቱ “የኦሮሞ ቄሮችና ሚሊሺያዎች እንዲሁም የኦሮሞ ባለሥልጣኖች በዜጎች ላይ ያደረጉዋቸው ማፈናቀሎች፤ግድያዎች፤ አመጾች፤ ዝርፍያዎች፤ ማስፈረራቶች፤ ነጠቃዎች፤ “ይህም የኔ ፤ ያም የኔ” የኦሮሞዎቹ “የኬኛ” ስግብግብ “ሁሉንም የማግበስበስ ባሕሪ” ያስከተለው ጥቃት ‘ከአማራ ህዳጣን ቤተሰቦች ጥቃት’ አልፎ በተቀሩት ዜጎች ላይም ያነጣጠረ “መፈናቀልና ግድያ” እያስተዋሉ ሲመጡ ስጋታቸው አደባባይ ላይ ሊያወጡት በመገደዳቸው መርሳት የለብንም።

ለምሳሌ ከጠቀስኳቸው ሦስት ሰዎች ከተናገርዋቸው ንግግሮችና ስጋቶቻቸው አንዳንዶቹን ልጠቅስ ነው። ጀኔራል አሳምነው ‘አፓርታይዱ አብይ አሕመድ’ በሕዝብ እሮሮ እና ተጋድሎ ወደ መንበረ ስልጣን ሲመጣ ከሞት ይፍታሕ እስር ብየና 9 አመት ታስረው ከእስር ተፈትተው የአማራ “ክልል” የጸጥታ ሹም ሆነው ሲያገለግሉ በነበሩበት ወቅት በአማራ ላይ ለ28 አመት የተሰነዘረው የዘር ማጥፋት ጥቃት እየተጠናከረ መምጣቱ ያሳሰባቸው እህ ጄኔራል ‘በወያኔ ትግራይ’ ታጣቂ ሃይሎች እና በታጠቁ ኦሮሞዎች” ከበባ ስር መውደቁ የአማራ ሕልውና ለመጨረሻ ጊዜ የሚፈታተን ችግር ስለሆነ ሕዝቡ ራሱን አስታጥቆ ራሱን መከላከል አዳይችል “በመንግሥት ደረጃ” ተጽእኖ ሲደረግ በማየታቸው፤  ውርደቱን ላለመቀበል ቆራጥ ውሳኔ በማድረግ “ ጥቃቱ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መቆም እንዳለበት” በመወሰን ያካባቢው ወጣት እያስታጠቁ እራሱን እና ሕዝቡን ከጥቃት እንዲከላከል ሲሞክሩ የኦሮሞዎቹ አፓርታይድ መሪ አብይ አሕመድ እርምጃው ስላልወደደለት ታፍኖ እንዲታሰር ወይንም ሴራ ጎንጉኖ እንዲገደል አብይ አሕመድ የቀየሰው መንገድ ሲታገሉ ከመሰዋታቸው በፊት ከተናገሩዋቸው ታሪካዊ ጥቅሶች አመላካች ንግሮቻቸውን እንመልከት::

የጀኔራል አሳምነው ጽጌ ስጋት፤
“አማራው መደራጀት አለበት። ሌሎቹ ወንድሞቻችን በዘር ተደራጅተው እኛ ዝም ማለት የለብንም። በአሁኑ ሰዓት አባቶቻችን የሄዱበት መንገድ ጊዜው ያለፈበት ነው! አያወጣም! በዘረኞች ምክንያት ተገፍተን ማንነታችን እንድንፈልግ ስለተጫኑን አማራው መደራጀት ግድ ይለዋል። ጠንካራ አማራ ከተደራጀ ጠንካራ ኢትዮጵያ መፍጠር ይቻላል፡፡”(ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ)

“ ሰሞኑን ሰፊ ስራ ጀምረናል። አሁን ያለው ሁኔታ እንዳለው አይቀጥልም፤ ሰሞኑን እንደሰማችሁት ችግራችን ከዚያ በላይ ነው፤ ሕዝቡ ራሱን ማደራጀት አለበት፡ ባካባቢው ሚሊሺያ፤ባካባቢው የጸጥታ ሃይል በጣም በተደራጀ ሃይል (ያንዣበበብንን ስጋት) ራሳችን ልንፈታው እንችላለን። ሕዝቡ ራሱን ማደራጀት አለበት፤ ራሱን ከዚያ በላይ ማዘጋጀት አለበት! ምክንያቱም አማራን ለማፍረስ ያልተሰራ ስራ የለም። ይሄ ምድር ላይ የተቀበረ ሳይሆን ምድር ላይ ወጥቶ እያየነው ያለው ነው።” (ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ)

 አባቶቻችን አንዳንድ ጊዜ የምትናገርዋቸው ንግግሮች አስተውላለሁ። አባቶቻችን ካሁን ባበሐዐበሐ ኋላ ፍትሕ ሲጓደል የሽምግልና፤የድርድር ንግግር አታድርጉ መሬት ላይ  ያለው እውነታ ለመናገር ሞክሩ፤ ከቻላችሁ ደግሞ እንደ “አቡነ ጴጥሮስ” መስዋእት ሁኑ” (ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ)

“በሦስት ቀጠና የተደራጀ የፌደራል የምርመራ ቡድን ክልልቻን ላይ መጥቷል። ይህ ሃይል ማኣከላዊ መንግሥት የላከው ይመስላል፤በፀጥታ ቢሮኣችን አውቅና የለውም፤ይህንን መዝግቡት፤ አስምሩበት።(ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ)

አሁን ያለንበት ዘመን ከሌሎቹ ዘመኖች እና ጊዜ የተለየ ጊዜ ነው።ለኛ ለአማራዎች በእጅጉ ከባድ ነው። በታሪክ ባላንጣዎቻችን አማራ ተወቃሽ ሆኖ ‘ያለ ሃጥያቱ’ እንዲሸከም ተደርጓል። በርእዮተ ዓለም ልንለያይ እንችላለን በአገር ህልውና ላይ ግን ድርድር የለም! አዴፓም፤አብንም፤ወጣቶችም ሽማግሌዎችም ሌላውም፤ ሌላውም አንድ መሆን አለብን። የሌሎችን አጀንዳ አስፈጻሚ መሆን የለብንም። የትግራይ ሕዝብ ወንድም ሕዝብ ነው፤እህት ሕዝብ ነው።ቲ ፒ ኤል ኤፍ እና የትግራይ ሕዝብ ይለያያሉ። ፓርቲዎች/ ድርጅቶች ከሳሚዎች/አላፊዎች ናቸው ሕዝብ ግን አያልፍም።”(ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ)

“አሁን እያየነው ያለው አጀንዳ ከሕግ በለይ ነው። አማራን የማፍረስ አጀንዳ ነው።”(ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ)

እኛ አረንጓዴ ብጫ ቀይ ሰንደቃላማችንን አዲስ አበባ ላይ ሰቀልነው፡ ኦሮምያ መሬት ላይ ደግሞ አወረዱት፤ ሌላ ቦታም አወረዱት!”(ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ)

“መጥፎ ሰዎች ሁሉ በሂደት ይጎዳሉ። ፈለግን አልፈለግንም ለሕግ ይቀርባሉ።ማንም በማንም ደም ተጠምቆ እዚህ ወምበር ላይ የሚቀመጥበት አይደለም። ከቻለ በራሱ መንገድ መንገዱን ይፈልገዋል። ፍለጎትን ለማስጠበቅ ከሆነ ደግሞ፤ ያ ዛሬ ብዙ መንገድ አያስኬድም፡ …ይስተካከላሉ።”(ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ)

የሌላ ሃይል ተላላኪ የሆኑት ሰዎች ተቁዋሙ እንዲያስተካክል ተነጋግረናል፤ካልተስተካከለ ደግሞ እኛ እናስተካክለዋለን።”(ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ)

እነ ዘመነ ካሴን በሚመለከት ያነሳችሁት ጥያቄ የክልሉ የፀጥታ ክፍል ሳያውቀው በማንም የበላይ ሃይል ትዕዛዝ፤በየትኛውም የስልጣን እርከን ያለ ባለስልጣን የፈለገው ንግግር ያድርግ ማንም ሰው ከዚህ ምድር ውስጥ ተወስዶ ወደ ሌላ አይሄድም።” (ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ)

በዕድሜ ጠገቡ ከጫካ የተመለሰ  አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ከተናገራቸው ጥቅሶች ውስጥ

ሕዝቡ የታጠቀውን ትጥቅ እንኳ ሕጋዊ አድርጎ ሊያስመዘግብ ሲፈልግ በአማራ መስተዳድሮች ተኮርኩዶ ተይዟል። አሁን ግን የሚፈቅድ ከተገኘ ዝግጁ ነን።” (አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ለጎንደር ወጣቶች ካደረጉት ንግግር)

አማራና ቅማንት እያሉ የሚያጣሉን የወያኔ ባንዳዎች እንጂ የትግራይ ሕብ እማ እህት እና ወንዳማማቾች ነን። ግን የትግራይ ሕዝብ በወያኔ በልቶ ጠጥቶ ካልጠገበ ልክ እንደኛው ትንሽ አቧራ በወያኔ መሪዎች ላይ እንዲያስነሳ እንጠይቀዋለን።” ((አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ለጎንደር ወጣቶች ካደረጉት ንግግር)

ከወጣት ዘመነ ካዜ ታሪካዊ ንግግር ያገኘሁት ጥቅስ
ትናንት ከሰሜን አቅታጫ ስንባረር ፤ ትናንት ከምስራቅ አቅጣጫ ሲያሳድዱን፤በኢትዮጵያዊነት ስም ስንለምን “አማራ ናችሁ” ሲሉን ነበር። መፈናቀሉ መገፋቱ፤መገደሉ፤ መሽቀንጠሩ መርሮን “ካላችሁ እማ እሺ ‘አማራ ነን’ ስንል “የለም ኢትዮጵያውያን ናችሁ ማለት ጀምረዋል። ትናንት በአርባ ጉጉ፤አሶሳ ወተር፤በበደኖ በማንኛውም የኢትዮጵያ “ማኣዝናት’ ሁሉ ‘ኣይሆኑ ስንሆን’  “አረ በሕግ አምላክ” ባቀናነው አገር እኩል እንኑር ብለን ስንለምን ፤ኢትዮጵያውያን ነን ስንል “አማራዎች ናችሁ” ብለው ያባረሩን ከንፈር እንኳ ያልመጠጡልን ሰዎች “አማራ መሆናችንን ስንነግራቸው”  ኢትዮጵያዊ መሆናችን ሊነግሩን ዓባይን ተሻግረው ጠላዋ እንዳማረላት ሴት ይወጣሉ ይገባሉ!”

ማን ነው የነ እምየ ምኒሊክ የነ በላይ ዘለቀ የንጉሥ ሚካኤልን ልጆች ደፍሮ ስለ ኢትዮጵያዊነት ላመስተማር ደፍሮ የመስበክ ሞራል ያለው?!”

አሁን ስለፖለቲካ የምናወራበት የቅንጦት ውቀት ስላልሆነ “አብን ነን ሳንል፤አዴፓ ነን ሳንል፤ ይህ ነኝ፤ ያ ነኝ፤ “ሳንል” ከገባንበት የሕልውና ፈተና ሰብረን እንድንወጣ በጋራ እንስራ ብለን ስንጀምር፤ “በመካካላችን የነበረው ስንጥቅ ሊደፈን ሲመስላቸው” አብይ አሕመድ “ብርሃኑ ነጋን በፍጥነት ወደ ባህር ዳር ላከው”። አልተሳካም!!”

የአማራ ልጆች ለሕልውናቸው ባንድ ቆመው ሊታገሉ ነው ብለው ሲያስቡ ከበባው ሰብረው ሊወጡ ነው ብለው ሲያስቡ፤እነ አብይ እና እነ ለማ “አዲስ አበባ ላይ የጀመሩትን ፕሮጀክት” በፍጥነት ለማጠናቀቅ ሲፈልጉ “እኔን ዘመነ ካሴን ኢትዮጵያዊነትን ሊያስተምሩኝ ብርሃኑ ነጋን ወደ ባሕር ዳር ላይ ላኩልኝ ነው የምላችሁ!!”

አዲስ አበባ ላይ በፍጥነት ምን እየተሰራ እንዳለ ብትሰሙ ጨርቃችሁን ትጥላላችሁ። ለውጡ ገና አልተጀመረም! በአራት አቅጣጫ ከበባ ውስጥ ነን!!”

“እኔ ስለ ኢትዮጵያ ለማወቅ የአባቴን ቀረርቶ እየሳመሁ ያደግኩት ይበቃል፤ ምንም ሰባካ አያስፈልገኝም። እኛ ኢትዮጵያውያን ነን!” ምነው ይህ ግፍ ይፈጸምብናል። እኛ እንደ አይሁዶች እንጠቃ እንዴ? ኦሮሞው፤ ሓድያው ሶማሌው…. ወንድማችን እህታችን ናቸው ብለን ተጋብተን ወልደን ተዋልደን ባሕላችን ሰጥተን፤ የነሱንም ተቀብለን፤ ብምኖርባት የወላጆቻችን አገር “አማራዎች ናችሁ” እያሉ ያሳድዱናል!” ታዲያ ዛሬ ምን ቆርቸው ነው “እሺ አማራዎች ነን” ስንላቸው “ኢትዮጵያውያን ናችሁ” ማለት የጀመሩት?”

“እኔ ዘመነ ካሴ ጨዋ ፤የዋህ፤ሳቅ እና ቀልድ ተጫዋች ወጣት ነኝ። ሰላዊ ሰው ነኝ፤ ባራት መዓዝን ከብበውናል። ጦርነት እየጎሰምኩ ግን አይደለም። የመለማመጥ ፖለቲካ አልወድም፤ ሰላም እወዳለሁ፤ሰላማዊ ሰው ነኝ። ግን ሲነኩኝ አልወድም፡ ምክንያቱም አማራ ነኝ!”

“በየትም ሕብረተሰብ፤ በዚች ምድር ውስጥ “መብቱን” በልመና ለምኖ አግኝቶ አያውቅም! ስትደራጅ ጉልበት ሲኖርህ ትፈራለህ “የሰላም እንቅልፍ ተኝተህ ታድራለህ!”

“አማራዎች ነን ሰው እንወዳለን፤ ግን እንደ አንድ ወጣት በራችን ሲንኳኳ እየሳመሁ ነው።”

“በፍቅር ከመጡ አማራዎች ስለሆነን ልብሳቸውንም ቢሆን አጥበን እንቀበላቸዋለን። በጠብ ከመጡ ግን ልብሳቸው ላይ እናሸናቸዋለን። ለዚህ መዘጋጀት አለባቸው!” (ዘመነ ካሴ ለደብረማርቆስ ወጣቶች ካደረገው የድምፅ ንግግር ወደ ጽሑፍ ከለወጥኩት ጥቅስ)
  
እንዳነበባችሁት እነኚህ በአማራነታችን ውርደት አንቀበልም፤በቃን! ብለው የአገር በቀል ፋሺሰቶችና የውጭ አገር ሴረኞች በአማራው ላይ ያነጣጠሩት የዘር ጥቃት ያስመረራቸው እነኚህ ዜጎቻችን የተናገሩትን ምሬት ተመልክተናል።

የሚቀጠለው ደግሞ ለአብይ አሕመድ ያደሩ ‘ነጭ ባንዴራ አውለብላቢ ባንዳ አማራዎች’ ስለ ሁኔታው አስመልክተው የሰነዘሩት ባንዳዊ ንግግሮችን እንመለከታለን።

ለዛሬ የምንመለከተው በመጀመሪያ በወያኔ እስር ቤት ውስጥ እያለ በራሱና በቤተሰቡ ላይ የግብረሰዶም ጥቃት ማስፋራሪያ ደርሶበት ነበር ተብሎ የሚታማው “የሓፍረት ትርጉም የማያውቀው” አንጋፋ ተዋናዩ የደበበ እሸቱ መልእክት እንቃኝ።

ደበበ እሸቱ እኔ ከምገልጠው በላይ መግለጽ የሚችለው ብርቅየ የታሪክና የፖለቲካ ስነ ፍልጠት ተሟጋች የሆነው ወዳጄ ወጣት አቻምየለህ ታምሩ ስለ ደበበ እሸቱ ማንነት የገለጸበት ትችት ልጥቀስ።

“መመከር ያለበት ማነው?” ለአርቲስት ደበበ እሸቱ «ምክር» የተሰጠ መልስ (አቻምየለህ ታምሩ) በሚል ርዕስ እንዲህ ይላል።

“አርቲስት ደበበ እሸቱ በትናንትናው እለት ‘አገዛዝ በተለዋወጠ ቁጥር’ አሰላለፋቸውን የሚያስተካክሉ ሆድ አደር ሰራዊቶችን ሰብስቦ በ1997 ዓ.ም. ይቃወመው የነበረውን የወያኔ አምባሻ ያረፈበት ባንዲራ በኋላው ሰቅሎ አማራውን ሰማዕት ጀኔራል አሳምነው ጽጌን በነውረኛ ቃላት እያወገዘ ለዐቢይ አሕመድ ያለውን ታማኝነት ለማስመስከር ሲኳትን ውሏል።

ደበበ እሸቱ ሰማዕቱን ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ከኮነነባቸው ዘግናኝ አገላለጾች መካከል «ሕሊና ቢስ»፤ «በአውሬያዊ ባሕሪ የተለከፈ» ፤ «ከእስር ሰንሰለት ነጻ ባወጣው ላይ የመሳሪያ ምላጭ የሳበ የሞት መልዕክተኛ» የሚሉ ልብ ሰባሪ ቃላት ይገኙበታል። ደበበ እሸቱ እንዲህ ያለ ለመስማት የሚቀፍ ውግዘትና ኩነኔ በጀኔራል አሳምነው ላይ ያወረደው የሰማዕቱ ጀኔራል ዐይን እንኳ ሳይፈርጥ ነው።

ደበበ በጀኔራል አሳምነው ላይ ይህን ያህል ውግዘት ያወረደው ጀኔራል አሳምነው አጠፋ የተባለውን ነገር አጣርቶ አውቆ አይደለም።ጀኔራል አሳምነው አጠፋ የተባለውን እንኳን በቦታው ያልነበረው ደበበ እሸቱ ይቅርና ነበርን ያሉትን የብአዴን መኳንንት እንኳ ስለ ሁኔታው የሚነግሩን ትርክት ርስበርሱ የሚጣረስ ነው። የደበበ ውግዘት መነሻ ስለሆነው ነገር ያለው እውቀት ሳይሆን ዐቢይ አሕመድ የአገር ውስጥ መረጃውን አፍኖ በአለማቀፉ ሜዲያዎች ዘንድ እንዲናኝ የተደረገው «አማራ መንግሥቴን ሊገለብጥ ተነስቷል» የሚለው ከመጠን በላይ የጮኸ በአማራ ላይ የተሸረበ ሴራ ነው።
ደበበ እሸቱ ራሱ የሴራ ሰለባና በፋሽስት ወያኔ የፈጠራ ክስ በሽብር ተወንጅሎ ዘብጥያ የወረደ ሰው ነበር። የሴራ ሰለባ የነበረው ደበበ ግን የሴራውን ሰለባ ሰማዕቱን አሳምነውን በሚዘገንን ቃላት ሲያወግዘው ሰማን።

ደበበ እሸቱ በ1999 ዓ.ም. ከተፈታ በኋላ እንደገና ዘብጥያ የወረደው ከግንቦት ሰባቱ መሪ ከብርሀኑ ነጋ ጋር በስልክ ግንኙነት ሲያደርግ በወቅቱ የኢንሳው የጃሚንግና ስልክ መጥለፍ ኃላፊ የነበረው ዐቢይ አሕመድ ንግግሩን ቀድቶ ለፋሽስት ወያኔ በመሰጠቱ ነበር።…” እያለ አቻም ስለ ደበበ እሸቱ ሰፋ ባለ ትችት ተችቶታል።

 አዎ አቻም አውነቱ ነው፡ በአሸባሪነት ከተፈረጀው ከብርሀኑ ነጋ ጋር ማውራቱን እየኮነነ ደበበ ራሱ መናገሩን በድብቅ ተቀድቶ የተለቀቀውን የቪዲዮ ምስል ያተመለከትን ሰዎች እናስታውሳለን።በዚያ ቪዲዮ ደበበ ምን ብሎ ነበር እዚህ ላስታውሳችሁ፡
ደበበ በቪዲዮ ሲታይ የነበረበትን ምስሉ ይህ ፎቶግራፍ ነበር፤
 “መንግሥት እኮ በግልጽ አስቅምጧል” ይላል ደበበ ዕንባ እየተናነቀው። “ግንቦት ሰባት አሸባሪ ድርጅት ነው ብሎ አስቀምጧል። እዚህ አገር ሁኜ፣ በየዕለቱ የሚሰጠውን መረጃ እያየሁ፣ አሸባሪ ነው ተብሎ ከተፈረጀ ድርጅት ጋር ለምንድነው በምንም መልኩ ይኹን ግንኙነት ያደረግኩት! ይኸ ነው የሚያስጸጽተኝ!”

እያለ ተዋናዩ ደበበ እሸቱ  በራሱ ላይ በመፍረድ አገር ጉድ ያስሰኘ ኑዛዜው አስተላልፎ እንደነበር እናስታውሳለን።ያንን አስመልክቶ ለምን እንዲህ ያለ አስገራሚ ድንጋጤና መምጰርጰር እንዳሳየ ተንታኞች ሲገልጹ እንዲህ ሲሉ ዘግበውት ነበር።

Woyanne threatened to sodomize Debebe Eshetu’s family (December 1, 2011, Updated on January 10, 2013 by Elias Kifle)

በሚል ርዕስ “የኢትዮጵያን ረቪው ኦን ላይን ድረገጽ አዘጋጅ ኤልያስ ክፍሌ’ ስለ ሁኔታው አስመልክቶ በጻፈው ለደበበ መልስ እንዲህ ብሎ ነበር፦

The star witness of Bereket’s fictitious docudrama is popular actor and member of the opposition UDJ Party. The video shows Artiste Debebe talking about various plots and the discussions he had with me and Dr Berhanu Nega. I cannot speak for Dr Berhanu, but none of what Debebe said about me is true. It’s a total fabrication. After hearing what Debebe had to say, I was convinced that he must have been tortured or something real bad had happened to him to say all the things he said, because no such conversation had taken place.

Yesterday, members of the Ethiopian Review Intelligence Unity in Addis Ababa sent me a report confirming what I had suspected. According to the report, Meles Zenawi’s deputy head of security, Esayas Woldegiorgis, gave a script to Debebe Eshetu to study and repeat in front of cameras every thing in the script in a convincing way or else his grand children and other members of his family will be sodomized with a bottle. This information is according to a close member of Debebe Eshetu’s family.

Sodomizing opponents, which is foreign to Ethiopian culture, is a method that Meles brought from his country Yemen. Victims of sodomy are extremely traumatized and that they are too ashamed to tell even those closest to them. In recent past, at least two prominent opposition politicians I know of who had been subjected to sodomy. I will not mention their names to keep their privacy. But in time, they themselves may be willing to talk about it in public so that the perpetrators face justice.”….. እያለ ስለሁኔታው ኤልያስ ክፍሌ ዘግቦ ነበር።

እንግዲህ ደበበ እሸቱ አልያስ እንደዘገበው በቤተሰቡ ወይንም “something real bad had happened to him to say all the things he said, (እንዲያ ሆኖ ያ ሁሉ ፈጠራ ለመናገር ያበቃው ለኛ ግልጽ ያልሆነ አንድ ነገር ተፈጽሞበት ኖሮ እንጂ ) በሚል ኤልያስ ክፍሌ ተዋናዩ ያሳየው አስደንጋጭ የመጰርጰር ባህሪ (December 1, 2011, Updated on January 10, 2013 by Elias Kifle) ለታሪክ ዘግቦታል።

ታዲያ አቻም የለህ አንዳለው “በውሸት ተወንጅሎ በሽብር ተከሶ የታሰረው ደበበ ያኔ የስልክ ንግግሩን የጠለፈው ዐቢይ አሕመድ በጀኔራል አሳምነው ጽጌ ላይ ያቀረበውን ተመሳሳይ ውንጀላ ተቀብሎ ለማውገዝ መነሳቱ ከምን የተነሳ ነው? ለሚለው ጥያቄ “ደበበ እሸቱ ንግግሩን ቀድቶ ዘብጥያ እንዲወርድ ላደረገው ለዐቢይ አሕመድ ያለው ፍቅር እጅግ ከመጠን ያለፈ እንዲሆን የሆነው አቻም እንደገለጸው “ተዋናዩ ደበበ እሸቱ ለቀድሞው አጋቹ ለዐቢይ አሕመድ እያሳየው ያለው ፍቅር ፈረንጆቹ Stockholm Syndrome ከሚሉት የአጋችና ታጋች ፍቅር በላይ እንደሆነ ያስቀምጠዋል።

ያ ሁሉ የቅንጅቱ የእስርቤቱ አስደንጋጭ ሁኔታ ኤልያስ ባስቀመጠው ሁኔታ ያለውን ሊለው “ስለተገደደ” እንዲያ ያለ መንቀጥቀጥ እና ለወያኔ የሽብር ሕግ ተገዢነት ማሳየቱ ሁላችንም በሚገባን የተገደደበት ምክንያት ሆነ ብለን እንለፈው። ዛሬ ነጻ በታባለበት እስር ባልገባበት ሁኔታ አብይ አሕመድን ያክል እጅግ አደገኛ ሰው “መጠን እና ቅጣ በሌለው አገላለጽ” በማምለክ ‘የቢሲ አማርኛ ጋዜጠኛ  ደበብን “ወደ መንግሥት እየተጠጋ ነው ብለው የሚተቹህ ሰዎች ገጥመውኛል” በማለት ጥያቄ ላቀረበለት ጥየቄ ሲመልስ

“ደግ አደረኩ! ነፃነቴን የሰጠኝ ዐቢይ ነው። ዶ/ር ዐቢይ ነው ቤተ መንግሥት ያስገባኝ። ዶ/ር ዐቢይ ነው ፕሮግራም ምራልኝ ያለኝ። ከመሸማቀቅና ማን አየኝ ከሚል መሳቀቅና መገላመጥ ያወጣኝ ዶ/ር ዐቢይ ነው። ስለዚህ ያደላሁት ወደ መንግሥት ሳይሆን ወደ ዶ/ር ዐቢይ ነው። ለእሱ ደግሞ መልሴ ደግ አደረኩ ነው።” የሚል ነበር።

የደበበ እሸቱ አሳዛኝና አስደንጋጭ ባሕሪው መንግሥትም ሆነ መሪም ይሁን ለቡድን ማሽቃበጡ ዛሬ አልጀመረውም። የጸሃፊው ስም ማግኘት ያልቻልኩኝ ‘በፌስ ቡክ’ የተለቀቀ አንድ አጭር ትችት የደበበ አሽቃባጭ ባሕሪ እንዲህ በእንዲህ ይገልጸዋል፡-

“ደበበ እሸቱ ማለት የደርጉ ቡድን ግርማዊነታቸውን ከቤተመንግሥታቸው እንዲወጡ ተደርጎ በቮልስዋገን ሲወሰዱ የመጨረሻውን  መርዶ ከደርጎች ጋር ሆኖ ያነበበ ታሪካዊ አድርባይ ሰው ነው። በኛ ትውልድ “አሳምነውን” እንደዚያ እያዋረደ የአብይን መልዕክት ሲያስተላልፍ በጣም ደም ያፈላል። ሲጀመርም እነ ቴዲ አፍሮን የሚያክሉ በዓለም የሙዚቃ ደረጃ ሰንጠረዥ (ቢልቦርድ) ስራቸው በአንደኛነት ለመቀመጥ የቻሉ አርቲስቶን ባፈራች አገር፤ ይህ “የአዜማ እና የአብይ ተላላኪ” እንደዚያ “አፉን ሲከፍት” ምን ያህል እንደተናቅን መገመት አይከብድም። ያ ሁሉ 
“አርቲስት ነኝ ባይ ሆዳም” አማራነትን ማዋረዱ አይነጋ መስሏቸው ያስብላል።”

ሲል ስለ ደበበ እሸቱ አድርባይነት አዲስ ባሕሪ ሳይሆን ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ የተከተለበት ተከታታይ ባሕሪው እንደነበረ ታዛቢዎች ገልጸዋል።

አብይ አሕመድ እነዚህ እና እነዚህ የመሳሰሉ አጎብጋቢ ግለሰቦችን ወደ ጎኑ በማስጠጋት የአማራን ማሕበረሰብና የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ግፍ ቀጣይነት እንዲኖሮው አስተዋጽኦ በማድረግ በአርበኞች እና አገር ወዳድ ዜጎች ላይ ይቅር የማይባል የተባባሪነትና ውግዘት በማስተላለፋቸው ታሪክ ይጠይቃአቸዋል።ጊዜ ሲለወጥ በስራቸው ይሸማቀቃሉ።የንጹሃን እና የግፉኣን አምባ ሃቀኛ ፍትሕ ሲሰፍን እምባቸው ይታበሳል። ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎቹ እና ደም ተፊው የ666ቶቹ ተቀጣሪው ጋኔል በቅርቡ በእግዚአብሐር ሰይፍ ቅጣቱን ያገኛል። (ይህ የኔ ትንቢት በማርች 2019 የጻፍኩትን ተመልከቱ አሁንም በአብይ እና በመሰሎቹ ይቀጥላል) ልብ ካላላችሁት የጻፍኩትን ላስታውሳችሁ፦

"የኦሮሞ ንጉሠ ነገሥቶቹ የአብይ አሕመድ እና የለማ መገርሳ አሽከሮች!  TUESDAY, MARCH 12, 2019(Getachew Reda ኢትዮ ሰማይ) በሚል ርዕስ እንዲህ ብየ ነበር፦

"ኢትዮጵያ አጆችዋን ወደ ፈጣሪዋ ዘርግታ የፋሺስቶቹ መሪ ‘መለስ ዜናዊን’ ከፊታችን እንዳስወገደው ፤ አሁንም ኢትዮጵያ እጆችዋን በገለጣፎ የእናቶች እና የህጻናት እምባ በኩል እጆቿን ዘርግታለች እና እናንተም በተራችሁ እንምባችሁ ሲፈስ በቅርቡ እናያለን!! ባጭሩ መጥሪያችሁ ተዘጋጅቷል እና ወደ ሃያሉ ፈጣሪ ትጠራላችሁ ማለት ነው!! ይህ ትንበያ ከሃቅ የራቀ እንዳይመስላችሁ። ካሁን በፊት በመለስ ዜናዊ አድርገናል (አልጄሪስ ስምምነት በተመለከተ ካናዳ ሓዋሪያ ጋዜጣ የጻፍኩትን ትንበያ ተመለክቱ) ፤ያ ትንበያ ዛሬም በናንተ ይደገማል!” ብየ ነበር። 

ይህ ባልኩኝ በሦስተኛው ወር ሰሞኑን  ባሕርዳር ውስጥ የተከሰተው የእግዚሔር ቁጣ አይታችኋል። ("የኦሮሞ ንጉሠ ነገሥቶቹ የአብይ አሕመድ እና የለማ መገርሳ አሽከሮች! ጌታቸው ረዳ ኢትዩ ሰማይ MARCH 12, 2019) ከሚል የጻፍኩት ትንቢታዊ ጥቅስ።

 ለተሰውት ሙታኖች ቤተሰብ ጽናቱን ይስጣችሁ።

ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay አዘጋጅ) 





Sunday, June 23, 2019

ብጄኔራል አሳምነው ጽጌ! የዘመናችን ታናሹ በላይ ዘለቀ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio semay)


ብጄኔራል አምነው ጽጌ! የዘመናችን ታናሹ በላይ ዘለቀ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio semay)
ቅዳሜ ከከተማየ ወጣ ብየ ነበር። አንድ ወዳጄ ደውሎ አዲስ ዜና አለ አለኝ። ስንጓዝበት የነበረው ድልድይ ረዥም እና  ስልክ ለማስተላለፍ ስለማያመች “በደምብ ማድመጥ ስላልቻልኩ ዘጋሁት”። ትኩስ የተባለውን ዜና ለማድመጥ ቸኩዬ ሲመሻሽ እቤት ስገባ ላንድ የቅርብ ወዳጄ ስልክ ደውየ፤ ምን ተፈጠረ? አልኩት። የሆነውን ሁሉ ነገረኝ። በስፋት ለማወቅ ድረገጾች ላይ ስፈትሽ ወዳጄ ከነገረኝ ጋር ተመሳሳይ ነው። ዜናው ባሕርዳር ከተማ በብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ መሪነት ‘መፈንቅለ መንግሥት’ እንደተካሄደ እና የተወሰኑ የ “ብኣዴን” (የቅርብ ስያሜው ‘ኣዴፓ’) ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አደመጥኩ።

መፈንቅለ መንግሥት የሚለው ስያሜ ምን ማለት እንደሆነ ባይገባኝም፤ የተከሰተው የመገዳደል ትዕይንት ዞሮ ዞሮ በፋሺሰት ግልገሎችና “አንጀታቸው በበገነ አገራውያን” መካከል የተከሰተ የዓላማ አለመጣጣም ውጤት ነው።  ግብግቡ ቅጽበታዊ ሳይሆን “በአገራውያን እና በፋሺሰት ግልገሎች መሃል” ለብዙ ጊዜ ሲብላላ ሲቋሰል የቆየ ውስጣዊ  ፍጥጫ ነው። አሳምነው ጽጌ ግጭቱን እንደመራው ይወራል። መያዙንም ተነግሯል። እውነትነት ካለው ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ ፋሺሰቶችን ለሁለተኛ ጊዜ አልገዛም ብሎ ማርበድበዱ ስሙ በልዩ ጀግኖች ማሕደር ውስጥ ያስመዘገበዋል።

ተንታኞች የተለያዩ እያታዎች ሊተነትኑት ይችላሉ። ሆኖም የአሳምነው “አንጀት እየበገነ መምጣቱ” በቅርብ ሳምንታትና ወራት ከተናገራቸው ንግግሮቹ ስንገምግመው፤ ጀኔራል አሳምነው ‘አናርኪሰቱን ስርዓት’ አገሪቱን ከድጡ ወደማጡ እየከተታት መሆኑን ስለገባው (በተለይም አማራው የተጋረጠበት ከበባ) ትዕግሰቱን ለመጨረሻ ጊዜ የተፈታተነው ስለሆነ ግለልጽ ብስጭት እንደገባ ያሳያል።

ከወር በፊት የክልሉ የጸጥታ ሓላፊ ሳያውቀው ከማንኛውም የአማራ ክልል ዜጎች ታፍነው ወደ ፌደራል እንደማይወሰዱ “ጥብቅ ማስጠንቀቂያ” ማሳለፉን ታስታውሳላችሁ። ጀኔራሉ ወታደር እንደመሆኑ መጠን ‘ሽኩቻው እየከረረ አንጀቱም እየበገነ መምጣቱ” እና ግልገል ፋሺሰቶቹ “እሱን በሚያምኑ ጓዶቹ እና በራሱ ላይም እየሸረቡበት” መኖሩን የሚያሳይ ምልክት እንደነበር ግልጽ ነው። እነ መኮንን ደመቀ እና ንጉሡ “አሳፋሪ እና አማራዊ ያልሆነ ባሕሪ” እያሉ “ቢለቀልቁም አሳፋሪዎቹ ግን እነሱ መሆናቸው መታወቅ አለበት። የአማራ ብሕል እና አማራነታቸውን አውልቀው ለ28 አመት አማራውን ምን ሲያደርጉት እንደነበር ዘንግተውት አሁን ስለ አማራ ባሕሪ እተመጻደቁ አሳምነውን ለማውገዝ ምላሳቸው ማሾል እንደ እባብ በጓዳቸው ማሾል ጀምረዋል።

ስለዚህም ጀኔራሉ በአዲስ አበባው የአናርኮ ፋሺሰት የኦሕዴዱ ቡድንም ሆነ ድሮ “አማራዊ ቆዳ፤የትግራዋይ ጭምብል”  ከአንድ አመት ወዲህ ደግሞ “አማራዊ ቆዳ፤ኦሮሞዊ ጭምብል” በለበሱ ወለዋይ የፋሺሰቶቹ ‘ግልገሎች’ ላይ የመጨረሻ አቋም መውሰዱ “በላይ ዘለቀ” በባንዳዎች ላይ የወሰደው አንጸባራቂ ርችት የሚያስታውስነን ክስተት ነው። ስለሆነም አሳምነው ለሁለተኛ ጊዜ በስርዓቱ ላይ ማመጹ አሳምነው የዘመናችን “ታናሹ በላይ ዘለቀ” ሆኗል።

የሚገርመኝ ደግሞ ‘ምሁራን ተብየዎች እና አሳፋሪ ተቃዋሚ ተብየው’ “ዛሬም” በየክልሉ እና በየከተማ ገጠሩ ሕዝባችንን ቁም ስቅሉን እያሳዩት ያሉት “ፋሺሰቶች” መሆናቸውን በመካድ ከታች  ያሉት ሹማምነቶች እንጂ “አብይ ብቻውን ምን ያድርግ ነው የምትሉት? ምንስ ያድረግ ሰው ነው መልኣካዊ ክንፍ የለውም” እያሉ የደርግ ጊዜ አለቅላቂዎች የሚመስሉ ሻለቃ ዳዊት በልዩ ደብዳቤአቸው ለመንግሥቱ በጻፉት ላይ “እረስዎ ብቻ ለአገርዎ ሲቆረቆሩ ከሥርዎ ግን አላሰራም የሚሉ በአድሃሪያን ሹማንቶች መከበብዎን ስመለከት አዝንለዎታለሁ..” ያሉትን ዓይነት ዛሬም በተቃዋሚ እና በምሁራን ተብየዎች አሳፋሪ ታሪክ እየተደገመ እያደመጥናቸው ነው። ስለዚህ ፋሺሰቶችን እና ግልገሎቻቸውን ለማስወገድ ሁሉንም መንገድ መደርገ አለበት!

 ይህንን ክስተት አስታክከው ‘የአብይ ነጭ ባንዲራ አውለብላቢ ሁላ’ “የአማራን ሰቆቃ” ሳይሰማው ለዘመናት አፉን ዘግቶ ከርሞ ‘ዛሬ ለፋሺት መንግሥት ያልተምበረከከው ጀግናው አሳምነው ጽጌን በመኮነን” ባንተ ላይ ያደረገው ጥቃት ነውና እናወግዘዋለን ብሎ “ለአማራ ሕዝብ” መልዕክት እያሉ ቢያስተላልፉም፡ የጸረ ፋሺሰት ታጋዮች ክንድ ማስቆም አያቻላቸውም! ፋሺሰቶቹና አለቅላቂ ግልገሎቻቸው አሁንም በአማራ ሕዝብ ላይ የተደረገ ጥቃት ነው የሚሉት “ለ28 አመት እስካሁን ድረስ የአማራ ሕዝብ ሲጠቃ የት ነበሩ?

የተለያዩ ዜናዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ፤ ጭቅጭቁ የተፈጠረው አጣየ እና በመሳሰሉ አካባቢዎች ‘ኦነጋዊ የኦሕዴድ ፋሺቶች’ ያደረሱት ጥፋት ተጠያቂዎችን ለይተው በማስቀመጣቸው በአሳምነው እና በአምባቸው ላይ የተሸረበ ሴራ ነው የሚሉ ትንተናዎች እየወጡ ነው። ከነዚህም ጥቂቶቹ እንዲህ ይላሉ፤-

“ምድረገኝ ሲባል የነበረው የጋላ (ኦሮሞ) ዘመን ወራሪዎች ‘ከምሴ’፤ እንዲሁም አጣዬና ማጀቴ’ በተባሉት አማራ ‘ክልል’ ስፍራዎች የደረሰው ጭፍጨፋ በ’ኦነጋዊ ኦሆዴዶች’ እንደሆነ እና በመንግሥት ውስጥ የተሰገሰጉ ኦሕዴዶች እንደሆኑ አምባቸው መኮንን፤ አሳምነው ጽጌ፤ ሰዓረ መኮንን፤ምግባሩ ከበደ፤አዘዝ ዋሴ ተፈራ ማሞ እና የድሮ የግንቦት 7 እና የኢሳት ባልደረባ የነበረው ዛሬ አገር ውስጥ የገባው ‘መቶአለቃ አበረ አዳሙ’ አጣሪ ሆነው ባገኙት አጠቃላይ ምርመራ ያለተደሰቱ ኦሕዴዶች እና ኦነጋዊ የውስጥ አርበኛ ባለሥልጣኖች የሸረቡት ሴራ ነው,፣’ ሲሉ አሰተያየታቸውን ይገልጻሉ። ለዚህም ያናርኮ ፋሺሱ አብይ ቅጽበታዊ ወታደራዊ ልብስ ለብሶ (ውቃቢው ርቆ፤ማዕረጉ በመቀስ ተበጥሶበት ለፍርድ የቀረበ ሞኮንን ቢመስልም) በቲ/ቪ መግለጫ መስጠቱና የእርሱ አለቅላቂ (አፈቀላጤ) የሆነው የጃዋር አድናቂ “ንጉሡ” የተባለው “ብኣዴናዊው አባል” ክስተቱን በሚመለከት በቅጽበት ወደ ሕዝብ መግለጫ ማድረጋቸው ነገሩ ከጀርባ የተሸረበ ነው የሚሉ ጥርጣሬዎችም አሉ። ያውም የተደጋገመ የአብይ አሕመድ የውሸት ባሕሪ ግምት ውስጥ ሲገባ።

ያም ሆነ ይህ አሳምነው ጽጌ ባለፉት ጥቂት ወራቶች በሥርዓቱ ላይ ግልጽ ብስጭት ይንጸባረቅበት እንደነበር ግልጽ ነው። 

በቅርቡ ከንግግሮቹ ውስጥ..;

 የአማራ ሕዝብ ከዚህም ከዚያም የመከበብ አደጋ ተጋርጦበታል!በተለይ ከ500 ዐመት በፊት አጋጥሞት የነበረ አሁን ካጋጠመው ጋር የሚመሳሰል ችግር አጋጥሞት ነበር። ያንን ፈተና አባቶቻችን ተጋፍጠው አልፈውታል። አሁን የገጠመንን  ፈተና በተለይም በዘራችን የመጠቃትና ራሳችንን የመከላከል ሓላፊነት ግን የዚህ ትውልድ ሓላፊነት ስለሆነ ራሳችንን መከላከል ይገባናል!” (ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ባሕር ዳር ፖሊስ ኮማንዶዎች ሰልጠንው ሲመረቁ ያደረገው ንግግር)።

ከዚህ እና ከመሳሰሉ ክስተቶች ስንመለከት አሳምነው ከግልገል ፋሺሰቶች ጋር እና ከሥርዓቱ መሪዎች ጋር ያለመጣጣም እንደነበረው ጥርጥር የለኝም።

እኔ በግሌ ዜናውን ስሰማ “ከነጭ ባንዴራ አውለብላቢ ‘ተቃዋሚ ተብየዎቹ” በየይቱብ ላይ ሕዝቡ ከመንግሥቱ ጋር እንዲቆም የተማጽኖት እና ጀኔራሉን የማውገዝ መልዕክት ያስተላለፉትን ሳደምጥ ይበልጥ ነገሩ አበሳጨኝ። የነኚህ የነጭ ባንዴራ አውለብላቢ ቡድኖች “ውግዘት” ሳደምጥ፦

“ጨቋኙን አውርዱ ማውረዱ ይበጃል
ይዋል ይደር ማለት ጠላት ይደራጃል!

የሚለው የየካቲቱ 66 ገጣሚ የግጥም ትዝታዎች ጭንቅላቴ ላይ አቃጨለ። የነጭ ባንዴራ አውለብቢዎቹ ጉደኞች ስርዓቱን እየመራ ያለው “ዛሬም የፋሺሰቶቹ ቡድን” መሆኑን ‘አሌ’ እያሉ ‘የፋሺሰት ግልገሎች በተነኩ ቁጥር’ “ውግዘትና ሙሾ ማውረድ” ለምደውታል። ያውም አንዳንዶቹ እማ “የጦር አበጋዞች” ይመስል እውጭ አገር ሆነው ጎጃምወሎ/ሸዋ እና በመላው አገሪቱ ያለው አማራ ልዩ መልዕክት አስተላልፈዋል። አማራው በየጥሻው በፋሺሰት ተገንጣይ ኦሮሞዎች እና በፋሺሰት ተገንጣይ ትግሬዎች እንዲሁም በአብይ አሕመድ ድርጅት “በኦሕዴድ” ሲፈናቀል እና ግፍ ሲፈጸምበት “የከፋ እንዳይመጣባችሁ እየተፈናቀላችሁ እየተገደላችሁም ቢሆን ዝም በሉ” እያሉ የሕዝቡን እሮሮ ለማዳከም የተቻላቸውን ያህል ፕሮፓጋንዳ በመስራት ላይ ናቸው። ሰለዚህም አገራውያን ትግላቸውን በማንኛውም መንገድ መቀጠል አለባቸው።የጊዜ ጉዳይ እንጂ ፋሺሰቶች በጥቂት የቁርጥ ቀን አገራውያን ቆራጥ ትግል ይወገዳሉ!

የቁርጥ ቀን ልጅ የብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ቁጭትና አገራዊነትን የሚያጠለሹ ሁሉ የነጭ ባንዴረ አውለብላቢ ቡድኖች ናቸው! ስለሆነም ታቀቡ እንላለን።የጸረ ፋሺሰት ታጋዮች ትግል በግልገል ፋሺሰት አቀንቃኞች አይታጠፍም!

አመሰግናለሁ:
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ Ethio Semay) getachre@aol.com




Thursday, June 20, 2019

ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች (ክፍል 3) ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ)



ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች (ክፍል 3)
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ)
ፎቶ አስቴር በዳኔ

እንደምን ሰነበታችሁ? እኛ ሰንብተናል፤ በኣናርኮ ፋሺስቱ የኦሆዴድ መሪው ኣብይ አሕመድ “ስርዓተ-አልባ” አመራር ምክንያት ላልሰነበቱ ወገኖቻችን በጥልቅ ስሜት እናስታውሳቸዋለን።

“በነጭ ባንዴራ አውለብላቢ ተሰላፊ ቡድኖች” ውስጥ ለዛሬ ልተነትን ተዘጋጅቼ ነበር ዛሬም እንዳለፈው ሳምንት ሊሆን አልቻለም። ሆኖም በዚህ ነጭ ባንዴራ ተሰላፊዎች ስር ሊካተቱ የሚችሉ ክስተቶች እና ግለሰቦች ቀልቤን ስላሰቡኝ በምትካቸው ለዛሬ የሳምንቱ ትኩስ መነጋጋርያ ሆኖ እስካሁን ድረስ እያነጋጋረ ያለው የግንቦት 7 ንብረት የሻዕቢያ ድምፅ ማጉያ እና የብርሃኑ ነጋ ጉሮሮ ማስተጋቢያ የነበረው ‘ኢሳት’ የተባለው አስገራሚ እና ሻጥረኛ የዜና ማሰራጫ ብትንትኑ መውጣቱን ያስገረማቸው ሰዎች በርካታ ስለሆኑ ‘ቀዳሚ ዜና’ ሆኖኛል። ኢሳት የግንቦት 7 የብርሃኑ ነጋ የፕሮፓጋንዳ ማስተጋቢያ ስለነበር በየአመቱ የዘመን መለወጫ መስከረም 1 ‘ቅዱስ ዮሃንስ’  በመጣ ቁጥር የብርሃኑ ነጋ ድምፅ ማስተጋቢያ እና የብርሃኑ ‘ተክለሰውነት’ መቅረጫ መኖሩን እናስታውሳለን።

በሚዲያው ቀርበው የታሪክ ትንተና ባካሄዱ የታሪክ ምሁራን እንደ እነ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ የመሳሰሉ የኦነግን ፖለቲካዊ ርካሽነት ስላጋለጡና በጥንታዊ ስሙ ‘የጋላ ማሕበረሰብ’ ሲኖርበት የነበረ አኗኗር “በከብት እረኛነት/ፓስቶራሊሰት” ሲተዳዳር ነበር በማለታቸው “ኢሳት በኦነግ ስም” ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦን “ይቅርታ እንዲጠይቁ” ሲጎተጉት ኢሳት ያለ ኣግባብ በስማቸው ኦነግን ይቅርታ ለመጠየቅ ሲቀላውጥ እንደነበር የቅርብ ትዝታ ነው። ይግረም ብሎ በአደገኛው ሰውየ በሓጂ ነጂብ አማካይነት “የዝግ ስብሰባ ተደርጎ ”ጃዋር” ፕላኑን ሲናገር  እኛ በምንኖርበት አካባቢ (አርሲ) አብዛኛው ሙስሊም ማሕበረሰብ ስለሆነ አንድ ክርስቲያን አንገቱን ቀና ካደረገ አንገቱን በሜጫ ነው የምንለው ብሎ ለተከታዩ ሲናገር ተከታዩ በታላቅ ጭብጨባ ሃሳቡን ሲያጸድቅ  “እንዳንተ አይነቱን ያብዛልን!” የሚሉትን የመናዊ እና ኢትዮጵያዊ ትውልድ ናቸው የሚባሉት እንደ እነ ሓጂ ነጂብ እና ጃዋር  ‘ኢሳት ሚዲያ’ ነፃ ቃለ መጠይቅ እየሰጠ ሲቀልድብን ነበር። “በነ ጃዋር ስብከት ተከትሎ ክርስቲያኑ እና አብያት ክርስቲያናት ላይ ከፍተኛ ጥቃት ደርሷል ንብረት ወድሟል ዜጋ ተገድሏል። (ሰመረ  ዓለሙ)
(https://www.youtube.com/watch?v=RMLLmAMWdG8)

ያንን በተነገረ ዕለት “የኢሳቱ ታማኝ በየነም” ተጨማሪ ዱላ በማቀል “አዎ እኛ ልጆች ሆነን ለኛ ለክርስትያኖች እንዲህ ሲደረግልን ለናንተ ሕዝበ ሙስሊሙ እንዲህ አልተደረገላችሁም ነበር! እያለ ነገር ሲያቀጣጥል እነ ሓጂ ነጂብና ከእነ ጃዋር ደስታቸው ቀልጦ ነበር። ኢሳቶች እየደጋጋሙ ‘የቃለ መጠይቅ’ ዕድል ከመስጠት ጀምሮ “አብረው” በእየ አገሩ ሲዞሩ የነበረውን ትዝታችን ዛሬም አልረሳነውም። 

ኢሳት ውስጥ የተሰባሰቡ አንዳንዶቹ የግንቦት 7 አባሎች የሚገርሙ ካድሬዎች ነበሩ።  “የግ7 አማራር” ጸረ አማራ የበዛበት ቡድን ነው ሲባሉ “በውሸት ይከንፉ ነበር”፡ የድርጅቱ ልሳን የሚጽፈው ዘረኛ ርዕሰ አንቀፅ እያነበቡትም ቢሆን ፤ (አስመራ ላይ ‘ከድምህት’ ጋር እፍ እፍ ፍቅር ይዞት ስለነበር ወልድያ ውስጥ ጥምቀት ቀን ስለደረሰው ክስተት የግንቦት 7 መሪዎች ምን እንዳሉ የምታስታውሱት ነው)። የገዛ ተጋዮቹን ለሻዕቢያ “ገራፊዎች” እያሳልፈ በመስጠት አስደብድቧል፤ አስረሽኗል፤ ብለው እያለቀሱ ላጋለጡት “ግንቦት 7 ለቀው ከኤርትራ የሸሹት ታጋዮችን” ሳይቀር  “ኢሳቶች የጋዜጠኛነት ሙያቸውን ጥለው” የግ7 ካድሬዎች በመሆን “ቅሬታ ላቀረቡ ታጋዮችን “የወያኔ ሰላዮች ናቸው” እያሉ እነ ሲሳይ እና መሳይ መኮንን ከግርፊያና ሞት ያመለጡ ታጋዮች “ስም ሲያጠለሹ ነበር።”
 
 “ታጋዮቹም” ገርሞኣቸው ፤ የግንቦት አመራር ከነበሩት ከብርሃኑ እና ከአንዳርጋቸው ጋር ሁለታችንን ግምባር ለግምባር ጋብዛችሁ ሕዝቡ ሚዛን ወስዶ እንዲያደምጠን “ጋብዙን” ብለው ደብዳቤ ሁለት ሦስቴ የጻፉትን ጥያቄ “ሳይቀበል” ደምጻቸውን ያፈነ ድርጅት መሆኑን ብዙ ጊዜ መጻፌን ታስታውሳላችሁ። ስለዚህ ኢሳት መፈረካከሱ የተጠናወታቸው ‘ካድሬኣዊ ባሕሪ’ ዛሬም “ለአብይ አሕመድ” በማጎንበሳቸው ‘ለኢሳት መፍረስ ምክንያት መሆኑን’ ባሕሪያቸው ለተከታልናቸው ብዙም አልገረመንም። ጠርቶ መውጣቱ ግን ጥሩ ነው!

ከብርሃኑ ጋር ያበረው የኢዜማው አባ ቄሱ “አንድአለም አራጌ” የተናገረው ስምታችሗል? እንዲህ ይላል፦

“ማሰር ማፈን እና ግድያ ስለቀረ “መንግሥት እንደሌለ አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች አሉ፡ ታሪካችን ከግድያ እና ከአፈና ስለሚየያዝ ነው መንግሥት እንደሌለ የሚመሰላቸው።” ሲል አሳፋሪ መጎንበሱን አስደምጦናል። ለመሆኑ መንግሥት የሚባል በዚህ አገር አለ ወይ? ብለው እየጠየቁ ያሉት እኮ የአንዱአለም አራጌ መንግሥት “መንግሥት አልባው” አብይ አሕመድ የሚመራው “ቤት አፍራሽ እስላም ሴት አረመኔ ከንቲባዎች (ጉዲቶች)” ቤቶቻቸው የፈረሰባቸው እናቶች እና አረጋዊያን እያለቀሱ የሚጠይቁት ጥያቄ ነው፤ ለመሆኑ “ለኛስ ለመሆኑ መንግሥት አለን ወይ?!! እያሉ “አረንጓዴ፤ቢጫ ቀይ ቀለም እንባ እያቀረሩና እያለቀሱ (አዛውንት አባቶችና እናቶች!) “መንግሥት የለም እንዴ?!” እያለ ያውም ወንድ ልጅ ስያለቅስ? “አንዱአለም” ይህንን አሳዛኝ እምባ እና ጥያቄ እንዴት ማየት ተሳነው?

“ማሰር መግደል ማፈን” ቀርቷልና “መንግሥት መኖሩን እንድናውቅለህ” ያንን አፈና ቀጥልበት” ብለን ስንጮህና ስንተች ሰምተሃል አቶ አንድአለም አራጌ? ነብሰገዳይ ሽብርተኛ እና የባንክ ዘራፊው ሌቦቹ ተበራክቷል፤ አረመኔኣዊ ግድያ ቀጥሏል፡ ዘር አጥፊና ቤቶች እያፈረሱ ህጻናትና እርጉዞች ከመኖርያ  ቤቶቻቻው ወደ ጎዳና የሚጥሉ የአፓርታይዱ የስርዓት ስራ አስፈጻዎችን “ስርዓት ማስያዝ የማይችል “ስርዓተ አልባ” መንግሥት እንጂ “መንግሥት የሚባል የለም” ነው ያልነው። መንግሥት ነኝ ባዩ የኦሮሞዎቹ ‘አፓርታይድ’ ስርዓት በካድሬዎቹ፤በፖሊሶቹ እና በከንቲባዎቹ በኩል አድርጎ “ጋዜጠኞችን እያሰረ፤ እያስደበደበ ነው፤ አገሪቷ ወደ ዘመነ መሳፍንት ተለውጣለች፤ አቤት ለሚሉ ዜጎች ‘ጦርነት እከፍትባችለሁ” እያለ የሚዝት “መንግሥት አልባ” (አናርኪነትን ያስፋፋ) ነው አልን እንጂ “ግድያና አፋና ቀርቷል እና “መንግስት መኖሩን እንድናውቅ “ያንን አፈናና ግድያ አምጣ” ስንል ሰምተህ ታውቃለህ? ማስረጃ አለህ?

ነጭ ባንዴራ አውለብላቢው አንዱአለም አራጌ እያደረ የሚገርም ንግግር መናገር ጀምሯል፡ እንዲህ ይላል፦

 “አብይ አሕመድ እንደኛ ሰው ነው “በሆነ አጋጣሚ ወደ ሥልጣን የወጣ እንደ ማንኛውም ፍጡር ሰው የሆነ እንጂ የተለየ ክንፍ የለውምና እባክችሁ ታገሱት” ሲል እንደ ፖለቲከኛ ሳይሆን ሕዝብን በቄስነት ባሕሪው ተማጽኗል። ያውም ቤቶቻቸው በቡልዶዘር ለፈረሰባቸው እርጉዞች፤ እናቶች፤ ቤቶቻቻው ስለፈረሰባቸው ‘ትምህርታቸው የተጓጎለባቸው ህጻናትን” እና እምባ ለሚያቀርሩ አዛውንቶችን!! ነው ታገሱት እያለ የሚማጸናቸው። በዚህ ሰውየ ብዙ የምለው ነገር አለኝ! እሱን ለሌላ ቀን ላሳልፈው።

ስለ የብርሃኑ ነጋ የለመድናቸው አለቅላቂዎች ጉዳይ!

 “ኤዜማ” የተባለው የብርሃኑ ነጋ “ጋሪ” (ትሮጃን ሆርስ) ወደ ምድረ አሜሪካ ለመተዋወቅ ብቅ ብሏል። ጋሪውን ለማስተዋወቅ ብርሃኑ ነጋ ሎስ አንጀለስ ውስጥ በሕዝብ ስብሰባ ተገኝቶ “ሰብለወንጌል” የተባለች ጋዜጠኛ አዳራሹ ውስጥ የደረሰባትን ወከባ በዩቱብ ቪዲዮ ላይ በለቀቀቺው ዜና መሰረት ብዙ ሰው ዜናውን ሰምቶ ተገርሟል። “እንደ ዜጋ ምን እንደተባለ ለማድመጥ ሄዳ “ንግግሮቹን ለመቅዳት በሞከረቺበት ወቅት የስብሰባ ንግግሮች መቅዳት አይፈቀድም” ብለው ግራና ቀኝ ‘ብዙ እንዳዋከብዋት’ ገልጻለች። የብርሃኑ ነጋ የግንቦት 7 የቆዩ ሞገደኞች አባሎቹ (በዚህ ስራ የምናውቃቸው ‘ከሻዕቢያ ጋር ወግነው’ የሻዕቢያ ባንዴራ እያውለበለቡ ሰው ሲዘልፉ የነበሩ እጅግ ሲበዛ ሰውን የሚገላምጡና የሚያስፈራሩ ተከታዮች እንደነበሩት ዛሬም ወደ “ነጭ ባንዴራ አውለብላቢው ድርጅት” እንደተዛወሩ የሚያሳይ ፍንጭ ነው።)

ዛሬም በሰብለወንጌል ላይ አሜሪካ አገር እየኖሩ የፖለቲከኞችን የስብሰባ ንግግር በዘመናዊ መሳሪያ ለመቅዳት በሚሞክሩ ላይ “አትቀዱም” እያሉ ዜናን የማስተላለፍ ‘መብት’ ሲጥሱ “ኢዜማ’ የተባለው የብርሃኑ ነጋ “አዲሱ ጋሪ” በብርሃኑ ነጋ ባሕሪና በግንቦት 7 ተከታዮቹ ለወደፊቱ “እንከን ገጥሞት እንደሚኮላሽ” ታልሞ ሳይፈታ የተነበይነው ነገር ነበር። ይኼው ገና “እግር ሳይተክል” በሰብለ ላይ ደገሙት!

ዋሺንገቶን ‘ዲሲ’ ውስጥም ባደረገው ሕዝባዊ የኢዜማ ስብሰባ ከወለሉ (Floor-men) አስተናጋጆቹ አንዱ ‘ካንድ አመት በፊት’ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱን “ሲዘልፉና ሲያስፈራሩ” (ለተወሰኑ ደቂቃዎች “ሃይጃክ” አድርገው ከተቀመጠበት እንዳይንቀሳቀስ ሲያስጨንቁት ከነበሩት “የማስጨነቁ ዜና ሪፖርታጅ አቅራቢ” ዩቱብ ላይ ሲያጓራ የነበረ አንድ ሞገደኛው የዲሲ ግብረሃል አባል ነኝ የሚል ዛሬም “የኢዜማ ወለል አስተናጋጅ” ሆኖ በቪዲዮው ስመለከት ብርሃኑ በለፈለፈ ቁጥር ያደነቆረንን የሙሶሎኒ እና የሶቭየት መነሸቪኮች “ፉጨትና የጭብጨባ ሞዴል” አዳራሹ ውስጥ ሲስተጋባ “ምንጩ” ከየትኛው ቡድን እንደነበር ቀጥታ ገባኝ። ዲሲ ውስጥ በግብረሃይሉ የተለመደ ባሕሪ “ብርሃኑን በጥያቄና በተቃውሞ ያፋጠጡትን እንግዶች” ጉሮራቸው ያለመታነቃቸውና ያለመዘለፋቸው ግን እድለኞች ናቸው። ሌላ ቀርቶ እነኚህ የዲሲ ግበረሃይል ናቸው የሚባሉት ጎረምሶች አምና “ቴክሳስ እስፖርት በዓል” ላይ “የፌስ ቡኩ ዮኒ ማኛን” በቡድን ሊደበድቡት ሞክረው ‘ተደባድበው’ እንደነበር ዮኒ ማኛ ነግሮናል። የ“ኢ-ዜማ” ሊቀመንበር ብርሃኑ ነጋ!  እውነትም ኢ-ዜማ!

በመጨረሻም ለኔ ባይገርመኝም ‘ለብዙዎቹ’ ያስገረመው ዜና “ኢሳት የኔ የግ7 ንብረት ነው” ብሎ ብርሃኑ ይፋ የማድረጉ ዜና የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች እርስ በርሳቸው እያነታረካቸው ነው። ኢሳት ‘የኢሳያስ እና የብርሃኑ ነጋ ተክለሰውነት መቅረጫ’ የግ7 ሮፓጋንዳ ቱለቱላ ክፍል ስለነበር ‘እነ ኤርሚያስ፤ ሃብታሙ፤ ቶቦርነ፤ ርዕዮት ዓለሙ፤ ምናላቸው፤ እየሩ እና ….ወዘተ… ከግ7 እና ከአብይ ካድሬዎች መለየታቸው ጥሩ ነው።

 ማሳሰቢያ፦
ኢትዮ 360 በገንዘብ ልረዳችሁ ነኝ ብየ ፌስ ቡካቸው ብጽፍም መልስ አላገኘሁም። በዚህ አጋጣሚ ብታገኙኝ ደስ ይለኛል። “ጎ ፋንድ ሚ” የሚባለው ከኔ ካረድ ጋር አልሄድ ስላለኝ ሌላ መንገድ ጠቁሙኝ) getachre@aol.com  

ቀጥሎ አብይ የደሴ አኩራፊነቱን እና ውሸቱን እንመለከታለን፡


 እንደተለመደው ውሸቱን ቀጥሎበታል፡ ማስፈራራቱንም እንደዚሁ። መለስ ዜናዊ ያስተማረው “አሉ! ብሎ መክዳት” ወይንም በውሸት መመለስ” አብይም ጭምር “ቁርጥ! የድሮ አለቃው መንትያ መስሏል። ሕዝብ ፊት ‘በመዋሸት’ “የመለስ ዜናዊ” ሞዴል ተከትሏል። ኦሮሞ ባንተ ዘመን ያላግባብ በብዛት ወደ ሥልጣን መጥቷል፡ ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ “ኦሮሞ የተለየ ጥቅም አላገኘም ስላላገኘ ነው ይህ ሁሉ ዘመን የታገለው” ሲል ይዋሻል። 3/4ኛ ሰፊ ኢትዮጵያውያን መሬት በብቸኛ ባለቤትነት ይዞ እንዴት አልተጠቀም እንደሚል እንናንተው ፍረዱ። የተቀረቺዋን አገሪቷ ‘ሚጢጢ መሬት’ እና ‘አዲስ አበባም’ ጭምር ቀርታቻቸው ያችንም ለማጠቃለል ሕዝብ እያፈናቀሉ ባይናችን እያየን ‘አብይ ደግሞ’ “የኦሮሞ ጥቅም ለማስጠበቅ ሁላችን እናግዝ” እያለ ሲያሾፍ፤ አረመኔ ከንቲባዎች “ሕዝብ ሲያፈናቅሉ ደግሞ”፤ “አላየሁም አልሰማሁም ውሸታችሁ ነው” “ዓይናችሁ ላፈር” ይላል። ከሰማም በላ ምንም የማስቆም እርምጃ አልወሰደም። ምክንያቱም የራሱ ፓርቲ አጀንዳ ነውና!!
ሲአስፈራራን ደግሞ ‘በእኔው በኦሆዴድ አስተዳዳር ዘመን” ኦሮሞ ተጠቅሞ ከሆነ “ነገ ከሥልጣን እውርዳለሁ” ሲል ያሾፋል።


እኔ ደግሞ “ትግሬው እገነጠላለሁ እያለ ካስፈራራ ይኼው ዘመን” አልፎታል። እኔ ደግሞ እባክህ አታስፈረራን ክፉኛ አሳክኮሃል እና ‘ተሎ አድርገው’ “ሂድ ተገንጠል እና ቆፈኑን ቅመሰው” እያልኩኝ ስማጸናቸው አመት ሆኖኝ “ትግሬዎች” ቢገነጠሉ ምን እንደሚከተላቸው ስለሚያውቁ አላደረጉትም (ጉራቸው ግን ጣራ ነክቶ ቀጥሏል)። አብይም እውርዳለሁ እያለ ሲዝት ሲያስፈራራ “እኔ ደግሞ እባክህ አድርገው!” ካልኩት ‘አመት’ ሆኖኛል። አሁንም ሊያደርገው አልፈለገም። አሽከሮቹና ነጭ ባንዴራ አውለብላቢው ቡድኖቹም አብይ ከለቀቀ ማንን እንተካለን?” እያሉ በዜጎች የአዋቂ መሪ አፍላቂነት እና በፈጣሪ ታምር አውራጂነት ላይ ሲያጣጥሉና ሲያስፈራሩ ይኼው አሉ።፡ሁሉም እኛ ካልገዛናችሁ እያሉ ወዮላችሁ! እያሉ ያስፈራሩናል። ይህ ሰው በነጭ ባንዲራ አውለብላቢ ቡድነኖች ፕሮፓጋንዳ “ብቸኛ ፍጡር” ተደርጎ በማየት ወደ አምላክነት ለውጠውታል።እሱ ከሌለ “የኢትዮጵያ መጨረሻ ይሆናል ይሉናል!”

ደሴ ውስጥ “እንደዛሬ ግድያና መፈናቀል አልበዛም” ብለው ለጠየቁ ዜጎች፤ “ለምን አስተዳደሬን ወቀሳችሁት” ብሎ ለደቡብ ሕዝብ ለገዴኦ-ተፈናቃዮች የሰጠው የተለመደው “አኩራፊው” መልሱ፤ ዛሬም ደሴ ላይ ደግሞታል። ያንን እንመለከታለን።


አብይ አሕመድ “ወሎ ድረስ ለመጎብኘት” ሄዶ ከሕዝቡ የሰማው ቅሬታ አልጣመውም። “እስላም እና ክርስትያን እንደ ዱሮው አልሆነም፤ እናንተ እንደምታወሩት “አንድ አይደለም”  ወሎ ምድር ውስጥ “መስጊድ ቤተክርስትያን” እኔ ልስራ እኔ ልስራ “ፉክክር” ገብተዋል፡ የቤተክርስትያን አባቶች ተጨንቀዋል፤ ቤተክርስትያን እተቃጠለ ነው፡ የደሴ ሕዝብ የነበረው ባሕላዊ መከባባር የጫት ሱስ አንድነቱን አፍርሶታል፤በየዩኒቨርሲቲው ደጃፍ ጫት መቃም ጣራ ነክቷል፡ ከ6 ሰዓት በላ ወጣቱ ጫት እየቃመ ቅዱስ ወንጌልንም ሆነ ቅዱስ ቁርኣን የሚማር ወጣት የለም፡ ግብረ ገብ የለውም፡ ለጫቱ ሱስ ማስቆሚያ መፍትሄ አምጡልን! አጣየ ውስጥ “የወታደር ልብስ የለበሰ “አሸባሪ” ማን አለበሰው?” ደረጃው የጠበቀ የወታደር መኪና እየነዳ መጥቶ ሕዝብን የሚጨፈጭፍ አሸባሪ መኪናውን ከየትኛው ሰማይ ተላከለት?” ፤ የህጻናት ዝውውር እየታየ ነው (ምን አይነት ወሬ እና ትዕይንት ነው እየታየ ያለው?!) በማለት አንድ መነኩሴ አምርረው ጠይቀዋል። 

ሌለው አባት ደግሞ  “ባቡር ተዘርግቶ ‘ደሴ ከተማ እንዳይነካው’ ተብሎ ጫካ ለጫካ አልፎ ሰው በማይደርስበት አካባቢ ዞሮ ለኪደርስ ወደ ታቀደት ቦታ ተዘርግቶ (ወደ ትግራይ) እኛን ወሎን ከላዋ ረግጦ ወደ መዳረሻው ተዘርግቷል፡ ይህ ሴራ ትርጉሙ ምንድ ነው? ሲሉ አንድ አባት ቄስ  ይህ የትግራይ ፋሺሰቶች ዘረኛ የሴራ ፖለቲካ እንቆቁሉሹ “ትርጉሙ ምን እንደሆነ” እንዲፈታላቸው አብይን ጠይቀዋል።

በማከታተልም አንዲት “ዓይነ ብርሃንዋ የተሰወረባት” እጅግ ብልህ የሆነች ወጣት “ዜጎች የሚኖሩባቸው ቤቶች በላያቸው ላይ በቡልዶዘር እየፈረሰባቸው ነው፤አማራው ዛሬም በየቦታው እየተጨፈጨፈ ነው፤ያማራ ልጆች በሚገደሉበት፤የአማራ ሕዝብ በሚፈናቀልበት እያየን ሳያመን ቀርቶ አይደለም (ክቡር ጠ/ሚኒሰቴር) ባንድ አመት ውስጥ ጤፍ ከየት ተነስቶ ወዴት ደረስ? እንዴት እንኑር!? ዛሬም አገሪቱ በባሰ መልኩ ከድጡ ወደ ማጡ ዓይን ባወጣ በዘር ተበክላለች፤ እኛ ደሴዎች ኢትዮጵያን ብንዘምርም ውስጣችን ግን እያመመን ነው ያለነው፤አሮሞ መንበረ መንግሥቱን ተቆጣጥሮታል ……ወዘተ..ወዘተ.. ብላ አምርራ ለጠየቀቺው “የስርዓተ አልባው መንግስት መሪው አብይ አሕመድ በለመደው ሞላጫ ችሎታው እንዲህ ሲል ሁለት መልስ ሰጥቷል፡-

“አንድ አባት ቄስ ከምን ጊዜም ታይቶ በማይታውቅ ግድያ አሁን ተፈጽሟል’ ብለዋል።” ይህንን ስለታነገሩት ጉዳይ ልምልስ።…” በማለት የተለመደው አጭበርባሪ ፊቱን እንደ ኩራትም፤ ጠያቂውን እንደማናናቅም እያሰኘው “ተዋናይ የፊቱ ገጽታ እየለዋወጠ” እንዲህ ይላል፦

 “የሃይማኖት አባቶች ከናንተ በላይ የጥፋትን ጉልበት የሚያውቅ የለም። አባቴ! የበሩን ሜዳ ታሪክ የሚገልጸው እሱን አይደለም! (ይህንን ሲናገር የአብይ ቡቹላዎች አዳራሹን በጭብጫባ አጅበውታል! በደፈናው አንጨብቻቢዎቹ እና በማፏጨት ያጀቡት አጃቢዎቹ እነ ማን እንደሆኑ ለመረዳት የሚያቅታችሁ ኣይመስለኝም። ለምን ጭብጫባ እንዳስፈለገ “ምንጩ” ቢገባኝም ግን አልገባኝም።)…….. ‘ኢትዮጵያ ውስጥ ባስተሳሰባቸው በሃይማኖታቸው ሲጮቆኑ ሲገረፉ ሲሰደዱ ነበር፤ አዲስ ታሪክ አይደለም። እኔ ደግሞ “ጅማ” ስለሆንኩ፤ ቡዙ የቦሩ ሜዳ ሰዎች ወደ ጅማ ተሰድደው እኛ ጋር ሰለኖሩ አውቀዋለሁ ታሪኩን (አሁንም ፉጮትና ጭብጫባ ተለግሶለታል፡ትርጉሙ እና እነማን መሆናቸውን ይገባችሗል ብየ እገምታለሁ)። “በእርግጥ የትናንት የዘሬን ያክል አይሰማም። እንደዛሬ “የፌስ ቡክ” ሚዲያ ስላልነበረ እንደዛሬ አይሰማም!” ….  በማለት ለተነገረው እውነታ መልስ ሲያጣ “ከጥላቻ ብዛት የተነሳ ‘ገድሎ የሰው ስጋ’ የሚበላበት የትግሬና የኦሮሞ አስተዳዳር ያስከተለው “ፋሺስቶች አረመኔ ዘመን” ያውም ‘የሰው ልጅ መሃል ከተማ በቀትር ጠራራ ‘ፓሎ ላይ ተዘቅዝቆ የሚጨፈርበት” የመለስ/ተሓህት/ እና የአብይ/ኦሆዴድ/ የእልቂት ዘመን” ከ ከቦሩ ሜዳ ፍርደገምድል ጋር አነጻጽሮ መልስ ነው ብሎ መልሶላቸዋል። ያውም “ኦሮሞ ከማይናገር ኢትዮጵያዊ ጋር ጋብቻ እንዳትጋቡ፤ንግድ እንዳትገበያዩ” እያሉ እነ በቀለ ገርባ ያለ ምንም ስጋት የዘር ጥላቻ ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ቸል ብሎ ልቅ ሲለቃቸው ፤ “ዘረኞች” ልባችሁ ነፍታችሁ የፈለጋችሁን የጥላቻ ንግግር አሰራጩ ተብለው በሚፎልሉበት አገር፤ ከቦሩ ሜዳ ጋር እያነጻጻረ መልስ ሲሰጥ ስቅጥጥ አላለውም።

በእውነት አሁን ይህ ከአንድ መሪ የሚጠበቅ መልስ ነው? የካራማራ ጀግናው የወለጋ ኦሮሞው ተወላጅ “አሊ በርኬ” ኢትዮጵያ ፤ ኢትዮጵያ ስለሚል ከእርሱ ጋር አብረን ግብዣ አንበላም” የሚሉ “የሰው እንሰሳዎች” የሚያሽሞነሙናቸው አናርኪስቱ አብይ አሕመድ ኦሮሞዎች ተገቢውን ነፃነትና ሥልጣን አልያዙም ይለናል።   

((በነገራችን ላይ እባካችሁ “የአሊ በርኬ” ስልኩ ካላችሁ ስጡኝ፡ አንድ ነገር ልልከለት አፈልጋለሁ፡ታማኝ ካነበብከኝ ብትልክልኝ ደስ ይለኛል። ከኔ ጋር ‘ፖለቲካዊ ጸብ’ ቢኖርህም ለዚህ አርበኛ ስትል የግል ስልኩን ላክልኝ!!)
 
አውነት ሲነገረው ‘የሚያኮርፍ’ አብይ አሕመድ ከወራት በፊት ወደ ደቡብ ክፍላችን በመሄድ በጠባብ ኦሮሞ ወረቦሎች የተፈናቀሉት በሺዎቹ የሚቆጠሩ ዜጎች ለማነጋገር ሄዶ “አንተ ስትመጣ ሞት በረከተ ፤ ስደት በረከተ፤ መፈናቀልና መከራ በዛብን..” ብለው አምርረው ቅሬታቸው ለተናገሩ ተፈናቃዮች “እኔ ከስልጣን ስወርድ ይቆማል’ ብሎ “ለምን የኔን ስልጣን ነቀፋችሁ፤ለምንስ አመረራችሁ” ብሎ ያለውን ይህ አስቀያሚ ንግግሩ በስደተኞች ላይ ማሾፉንና ቅሬታቸውን ማጣጣሉን ‘ክፉኛ እንደተተቸ’ የሚታወስ ነው።

ያ እንዳይበቃ፤ ዛሬ ደግሞ “ለምን አስተዳደሬን ተነቀፋችሁ” በሚል ቁጭት ተነሳስቶ “ሰለጠነ በተባለበት ዘመን ፤ ዲሞክራሲ አለ በተባለለት ዘመን” ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ በመንግስት የታገዘ መፈናቀል እና ግድያ ፤ በመንግሥት የታገዘ ትዕዛዝ የአዛውንት እና ነብሰ ጡሮች መኖርያ ቤቶች ሲፈርሱ “አላያሁ አልሰማሁ” እያለ የግፉ አስፈጻሚ መሆኑን ለመደበቅ ሲል  ፤ የዜጎችን ሰቆቃ ምንም ሳያሳስበው ‘ስንት እና ስንት አመት ያለፈበትን ዘመን’ ወደ ላ ሄዶ  በአፄ ዮሐንስ ትዕዛዝ ምላሳቸው የተቆረጡ ቱምቧሆ እየቃሙ ለተገኙ አፍንጫቸው ለተፎነኑ ጥቂት የወሎ ኗሪዎች (እስላሞች) እና ክርስትያኖች “ለጅማው ልጅ” ለአብይ አሕመድ፤ “የቦሩ ሜዳን” ኢፍትሃዊ  የነበረው “ንጉሳዊው” ፍርደገምድል ‘በዲሞክራሲ ያልታነጹትን ከነገሥታት’ እርምጃ ጋር እያነጻጸረ እዚህ ግባ የማይባለውን “የቦሩ” ፍርደገምድል ማወዳደሩን ሳደምጥ ይህ ሰው “ታሪክ የማያውቅ” (ልክ ባሮ ቱምሳ ኦነግ ገድሎት መንግስት ነው የገደለው ብሎ ያለውን ድንቁርናውን ያክል) የሚገርም “ደካማ” ሰው ነው።

 አብይ መስማት የሚፈልገው ነገር ካለ “አትውቀሱኝ” ፤ “ሰላም ነን በሉኝ” “አብይ! አብይ” በሉኝ” የሚል ሱስ ይዞት ናላው የሙገሳ ስካር ‘ፍላጎቱ’ ሕሊናው በጥብጦታል። አጨብጫቢዎች ጫማው ስር እየወደቁ አስክረውታል፤ ሱስ አስይዘውታል! በቃ! ወቀሳ የማይወድ ልክ “ሁለተኛ መለስ ዜናዊ” የሆነ አሳፋሪ መሪ እየሆነ መጥቷል? ቁርጥ መሪውን መለስ ዜናዊ የተካ!

ይህ ሰውየ ስለ አማራ እልቂት፤ ስለ ኦርቶዶክስ ሰቆቃ ተነስቶ ለሚጠይቅ መልሱ ሁሌም ማጣጣል ነው። ሕግን የጣሰ ትግሬዎች ለሁለት ጊዜ የተሾሙበት ቤተእምነት “ሁለት ጳጳሳትን መሾም” ሕጋዊ አድርጎት ቆጥሮት “አስታርቄአቸዋለሁ” እና አመስግኑኝ ሲል ተናግሯል። ባህርዳርንን ለመተዋወቅ መጀመሪያ ሲጎበኝ የአካባቢው ካሕናት ተነስተው ሲወጥሩት ስለ አማራ እና ክርስትያኖች መገፋት መቆም እንዳለበት አቤት ሲሉ “ተመሳሳይ መልስ ነበር እያጣጣለ ጎጃሜዎችን የመለሰላቸው”። ዛሬም ደሴ ውስጥ ማጣጣሉን ደገመው። ባለፉት ወራትም የገዴኦ ተፈናቃዮች’ ከአምና ይልቅ ”ባንተ ጊዜ መፈናቀልና ግድያ በረከተ” ብለው ለሚያማርሩ ተመሳሳይ የማጣጣል መልስ ነው የሚሰጠው “ገና ግድያውና መፈናቀሉ ይጥላል!” የሚል መልስ ነው ‘በቃ’ ይህ ነው መልሱ!

ግድያ እና መፈናቀሉ እንደሚቀጥል እያወቀ ለማስቆም ምንም ነገር አያደርግም። ለምን አታስቆመውም፤ ተብሎ ሲጠየቅ ወይንም ‘ሲፈናቀሉ’ ደግሞ “አልሰማሁም አላያሁም” የሚል መልስ ይሰጣል። አጭበርባሪ መሆኑን ለማወቅ ቀላል ነው።መጽሐፍ ላይ ያነበበው ፍልስፍና በሰው ህይወት ሊፈላስፍበት የሚሞክር “እንዝህላል” ጀነሳይዳል” መሪ ነው።

ኦሮሞ ስልጣን ላይ ነው ብላ ላመረች ይህች ወጣትም፤ “ኦሮሞ ስልጣን ላይ የለም” ሲል “ባይነ ደረቅነት” ይመልሳል። ስለ ኦሮሞዎች ወያኔ ትግሬዎችን የመተካት ማስረጃ በተመስገን ደሳለኝ የቀረበ ሰነድም ሆነ በተለያዩ ምሁራን እና ቅሬታ እቅራቢዎች የተለቀቁ መረጃዎች ስላሉ እነሱን ተመልከቱ። ያንን ማስረጃ አብይም ሆነ ኦሮሞዎች በማስረጃ እስካሁን ድረስ አልመከቱትም። የወያኔ ትግሬዎች ሥልጣን እንደተቀራመቱ እንዲያ ያለ ጥያቄ ሲቀርብባቸው ቀጣፊነታቸውን ስለሚያውቁ ‘ማስረጃውን መመከት አልቻሉም”። አብይም እንደዚሁ! ሁለቱም በቅርምት ስለተጠመዱ ‘ያንን ማስረጃ መጋፈጥ አይችሉም!”። ሌባ ዘርፎ ሲያበቃ “ዝርፌአለሁ ብሎ ራሱን ለቅጣት አያቀርብም!

   ሌላው ርዕስ ከያኒት አስቴር በዳኔ እና የአገው አዝማሪ እና ዳንኪረኛው መኳንንት መለሰን ከነጭ ባንዴራ አውለብላቢ ቡድኖች’ ሥር መካተታቸው እንመለከታቸዋለን።

ሰሞኑን በርካታ አዝማሪዎች ወደ “ነጭ ባንዴራ አውለብላቢው ሰልፈኛው ቡድን” በመቀላቀላቸው እያስደመሙን ሄደዋል።ባለፈው ክፍል 2 ነ መስፍን በቀለን ተመልክተናል። ዛሬ ድገሞ ከነኚህዎቹ በከያኒነት (አርቲስት ይሉዋቸዋል መሰለኝ በወያኔ ዘመን አጠራራር ማዕረግ) የምትታወቀዋ ከአማራ እና ከኦሮሞ እወለዳለሁ የምትል ከያኒት “አስቴር በዳኔ” (ሰሞኑን) እና የአገውኛ አዝማሪና ዳንኪረኛው “መኳንንት መለሰ” (ብግንቦት ወር) ወደ ነጭ ባንዴራ አውለብላቢው ቡድን ተቀላቅለዋል።

የዘመኑ የዩቱብ ቱልቱላዎች “አስቴር በዳኔ ዛሬም የልቧን አፈረጠችው የምትገርም አርቲስትን ያለማድነቅ ከባድ ነው” እያሉ በዩቱቡ ሲዘረጉላት እያደምጥኩ ተገርሜኣለሁ። በዘንድሮ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ንቃት ሁሌም እገረማለሁ። በዚያ ‘የየዚያ-ትውልድ’ የ66 ቱ ‘ሴት ታጋዮችም’ ሀኑ  የ የዚያ ዘመን “ሴት ከያኒያን” ድፍረትና ቆራጥንት ያላየ የዘመናችን ወጣት “አስቴር በዳኔ” ወያኔዎች ጋብዘዋት “ደደቢት” በረሃ ሄዳ የተናገረቺው “ትርኪ ምርኪ” ሲያሞካሹላት እና ሰማይ ሲሰቅልዋት የመገረሜን ያህል ‘ዛሬም ልክ እንደ ታቻምናው “ትርኪ ምርኪዋን” እየሸጡላት ነው።

"ኢትዮጵያ የፈራረሰች የምትመስለው “ፌስ ቡክ” ላይ ነው” ትላለች አዲስ ዘመን ከተባለው የወያኔ ቱለቱላ ጋዜጣ ቃለ መጠይቅ ቀርባ የሰጠቺው ‘ትኩሲትዋ ፖለቲከኛ’። በላያቸው ላይ ተኝተው በቡልደዘር እየፈረሰባቸው ላሉት እና ለሚፈናቀሉት፤ለሚታረዱት፤ለታመጹት ልጃገረዶች እና ባለትዳር እመቤቶች “አገራቸው እየፈራራሰች እየሄደች መሆንዋን በፌስ ቡክ ላይ ያዩት የሕልማቸው ቅዠት ነው” ልትለን ነው ይህች ከያኒት። ፖለቲካ ገብቼ ልወዳደር ነው እያለች “አብይ አሕመድ “በአንድ አመት ውስጥ የሰራው ስራ የአሰር አመት ስራ ነው”  ስትል እያሞካሸቺው እንዴት ወደ ፖለቲካ ገብታ ይህንን ይዛ “እንደምትፎካከረው” አልገባኝም። ፖለቲከኛዋ በዚህ ብቻ አላበቃችም እንዲህም ትላለች፦

“ቆሻሻ ስለሚጠርግ ይሰደባል፤ ችግኝ ስለተከለ ይሰደባል፤ሰው ስለማያስር ይሰደባል፤ ሰው ስለማይገድል ይሰደባል፤ ሰው ስለማይሰደብ ይሰደባል፤ አንዳንድ ጊዜ ሕዝቡ ምን እንደሚፈልግ ግራ ይገባኛል!” ብላለች። “ወርቅ ቢያነጥፉለት ፋንድያ ነው የሚል ሕዝብ ነው”  እንዳሉት ሊቀመንበር መንግስቱ ሃይለማርያም ‘አስቴር በዳኔም’ የራሱን ዘረኞችን ከማጽዳትና ከማስቆም ይልቅ “ቆሻሻን” ማጽዳቱ “ቀዳሚ’ ቁም ነገር ተደርጎ ሕዝቡ ምን እንደሚፈልግ ግራ ይገባኛል ብላ “ወርቅ ላነጠፈለት ፋንድያ ነው ይላል ‘ የማሉትን አባዜ ደግመዋለች።

ሕዝቡ ምን እንደሚፈልግ ሳታውቅ ወደ ‘ፖለቲካ ተፎካካረነት’ እገባለሁ ማለትዋ የሚገርም ነው። ለመሆኑ እስክንድር ነጋ ምን እንደሚፈልግ የማያውቅ ወይንም በፖለቲካው  ዐለም ፍቅር ምን ማለት እንደሆነ አያውቅም ሆኖ ነው እንዲህ በአብይ ስርዓትም እየተንገላታ እና እየተዛተበት ያለው? ወይ ጉድ! “ፍቅር ያለሸነፈን ሕዝቦች ነን” ብላ ስትደመድም የሚገርም ነው። አብይ አሕመድ እስክንድር ነጋን ምን የሚሉት ፍቅር አሳይቶት ነው እንዲህ ስለ አብይ ፍቅር ሰባኪነት የምትነግረን? “የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይን የሰላም ስብከት ከይሁዳ ሰላምታ ለይተን አናየውም!” የሚሉ ተሰላፊዎች መፈክር አላነበብች ይሆን?

የሚገርመው ደግሞ እንዲህ ያለቺውን መልሶ አስገርሞኛል፦

“50 አርቲስቶች (ከያኒያን) ወደ ቻይና ለሥልጠና ሲላኩ እኔ አልተላክሁም። እኔ ዶ/ር አብይን ስደግፍ በነበርኩበት ወቅት፤ ከተላኩት ውስጥ አብይን ሲቃወሙ እና ሲሳደቡ የነበሩ ወደ ቻይና ሄደዋል። ስለመደመር እየተወራ ተቀንሻለሁ።” ስትል እሮሮዋን ገልጻለች።

ሕዝቡ እንደሆነ ሊረዳሽ አይችልም፤ ምክንያቱም “ምን እንደሚፈልግ ለራሱንም ስለማያውቅ!” ብለሽ ደምድመሻል። ምን እንደሚፈልግ ለሚያውቀው የአስር አመት ስራ በአንድ አመት ያጠናቀቀው ‘ፈጣን መልስ ሰጪው ፤አብይ አሕመድሽን’ አደልዎና ዘረኛነት ለምን “ዓይን አውጥቶ እየባሰበት እንደሆነ” ብትጠይቂው መልስ ልታገኚ ትችይ ይሆናል። እኛ ግን ቅሬታሽን አንብበናል። ቆሻሻ ከመጥረግ “የአድለዎ ቆሻሻ” ከማሪዎችን “ከየመስራቤቱ አጥራ” ብለን ያልንበት ምክንያትም ይህ ነው። ለመሆኑ “በዕምባ የታጀበው” የኢትዮጵያ ምርጥ የልብና የውስጥ ሕመም የጥገና ባለሞያ ሓኪሞች “አቤቱታ” ምን እንደሚፈልጉ አያውቁም’ ብለሽ “ሕዝብ” ከምትይው “ሕዝብ” አስገብተሻቸው ይሆን? እባክሽን ረጋ በይ! ትወና እና እውተኛ ህይወት ይለያያሉ።

የአስር አመት ስራ በአንድ አመት ውስጥ ያከናወነው አብይ “የተሽመደመደ መንግሥት” ከተባሉት 25ኘው ተራ ተመዝገቧል። እንዲህ ተቀምጦልሻል።

This is a list of countries by order of appearance in the Fragile States Index (formerly the Failed States Index) of the United States think tank Fund for Peace.

A fragile state has several attributes. Common indicators include a state whose central government is so weak or ineffective that it has little practical control over much of its territory; non-provision of public services; widespread corruption and criminality; refugees and involuntary movement of populations; and sharp economic decline.[1] በቃ ይህ ነው።

 “መኳንንት መለሰ”

በመጨረሻም አዝማሪና ዳንኪረኛው “መኳንንት መለሰ” ምርጥ ኢትዮጵያዊ እየተባለ  አገር ውስጥም ዋሺንግቶን መጥቶ በነበረበት ወቅትም “ኢትዮጵያዊ ቀናኢነቱን” ሲወራለት የቆየው ይህ የአገውኛ አዝማሪና ዳንኪረኛ በግንቦት ወር ጉድ አይተንበታል።  የውርደት ዘመን ተብሎ በአገር ወዳድ ምሁራን የተሰየመው “በግንቦት ወር ውስጥ ፋሺስታዊ ስርዓት” ይዞልን የመጣውን ወያኔ ወደ አዲስ አባባ የገባበትን ወር ለመዘከር እንዲጨፍርለት ሲል ይህ አዝማሪ “ዘር ማጥፋት ወደሚካሄድበት” “ራያ” ወደ ተባለው ወያኔ በጉልበት ወደ ትግራይ ወደ አጠቃለለው ‘አጨቃጫቂ’ ቦታ በመሄድ ሲጨፍር በቪድዮ አይተናል።ከታች የምትመለከትዋቸው ‘ጊታሪስቶች’ የወያኔ ሙዚቀኞች ናቸው።
እንኳን ለግንቦት በዓል አደራሳችሁ! በማለት በአገውኛ መድረኩን በመክፈት ወያኔዎችን አስጨፍሯል። በአገውኛ ምን እንዳለ ባለውቀም ከወያኔ ‘ጨፋሪ ጀሌዎች’ ሽልማቱን በገፍ ጎርፎለታል። አብይ አሕመድም “እንኳን ለግንቦት በዓል አደረሳችሁ!” ሲል ነጭ ባንዴረ አውለብላቢ አዝማሪዎችም የአብይን ቃል በመድገም “እንኳን ለግንቦት በዓል አደረሳችሁ!” በማለት ቤት ንብረቱ እየፈረሰበት ለሚፈናቀለው ዜጋም ሆነ በግደድ ትግሬ ሁን ተብሎ የዘር ጽዳት ለሚፈጸምበት የራያ ሕዝብም ሆነ የወልቃይት ሕዝብ ላይ የሚያሾፉ ‘ነጭ ባንዴራ አውለብላቢ አዝማሪዎችና ዳንኬራ መቺዎች’ በታሪክ መወገዝ አለባቸው።

ድሮስ እሺ ይሁን የኪነት ሰዎች “ፈርተው” አድርጉ የተባሉት በግድ ሲያደርጉ ነበር እንበል ፤ ዛሬ የመሰላችሁ ነገር ‘እምቢ” የማለትም ሆነ “ያለ መሳተፍ” ነፃነት ሰጥቻችሗለሁ ብሎ የነገራቸውን አብይ አሕመድን ፈርተው ይሆን ይህ ሁሉ “ኢሳያስ አፈወርቂን ይቅርታ የመጠየቅ” ፤ “ወያኔ መንደር ጋር ሄዶ ዳንኪራ መምታት” ፤ “እንኳን ለግንቦት በዓላችን አደረሳቸሁ” የሚለው የደንቆሮዎች ጩኸት እንዲያስተጋቡ “ማን አስገደዳቸው”?  እነኚህ አድርባዮች “ከሰለሞን ተካልኝ” በምን ይለያሉ?
ነጭ ባንዴራ አውላቢዎች ቁጥር 4 ይቀጥላል፡…………………\
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (አትዮ ሰማይ አዘጋጅ)  (getachre@aol.com)