ሕዝባችን ለጠላቶቹ ሸብረክ ብሎ እንዲገዛና ገዢዎቹን ማስወገድ ያልቻለበት ምክንያቱ ምንድነው?
መልስ ለዶ/ር ዮናስ ብሩ፡
ጌታቸው ረዳ
ክፍል 1
8/30/25
Disclaimer: The content on this page may contain material considered inappropriate for those under the age of 18. Viewer discretion is advised. By continuing to use this site, you acknowledge you are of legal age.
ይህ መልስ አሜሪካ ሀገር ለሚኖር የኢኮኖሚክስ ምሁር ለሆነው ለዶ/ር ዮናስ ብሩ ሲሆን ርዕሱ
ላይ የቀረበው ጥያቄ መልሱን ለማወቅ ለተቸገራችሁም ነው። ዶ/ር “ዮናስ የሃሳብ ገበታ” በሚባል ሚዲያ
የጋራ ህልውና? አዳዲስ ስብስቦች
https://www.youtube.com/live/UtuoYfAZfs4?si=QZQ3WtzgmtHyCwlc
በሚል ርዕስ እንዲወያይ ተጋበዞ “ከፕሮፌሰር መሳይ ከበደ” ጋር ባደረገው ውይይት “ሕዝባችን 60 አመት ሙሉ ለጠላቶቹ ተመቻቸቶ በግራ ትከሻየ ወይስ በቀኝ ትከሻየ ልሸከምህ እያለ ለገዢዎቹ ትመቻችቶ ሸብረክ ብሎ እንዲገዛና ገዢዎቹን ማስወገድ ያልቻለበት ምክንያቱ ምንድነው?” ሲል እራሱን ይጠይቅና ፤ ለዚህም ሁለት ምክንያቶች ይሰጣል። 1ኛው የቆየ የባሕልና 2ኛ የምሁራን ስንፍና ፤ በሚል ለሕዝቡ ያለመነሳት ምክንያት አቅርቧል። ይህ ሙሉ በሙሉ ባይሻርም መሰረታዊ ስሕተት አለበት (በተለይ 1ኛው ነጥብ ላይ)
በዚህ አስገራሚ በሆነ ሕዝብን የማንበርከክ ስልትና ትንቢት ልጀምርና የተሳሳተው የዶ/ር ዮናስ መላምት እገባለሁ። ጽሑፉን ከጨረሳችሁ በኋላ ገንዘብ እየተከፈላቸው ኢትዮጵያ የግብረሰዶም ሃገር እንድትሆን የሚያሳይ ቪዲዮ "ሊንኩን" አስቀምጫልሁ ያንን ተመልከቱት።
«አፍሪካን ከጫፍ እስከጫፍ በስፋት የተዘረጋው ይህ ክ/ዓለም ሁሉንም ተዘዋውሬ አይቻለሁ። አንድም ሌባም ሆነ ለማኝ ሰው አላየሁም፤ በዚህች ሀገር (አትዮጵያ ማለቱ
ነው) ያየሁት ሃብት እና እንደዚህ ያለ ከፍተኛ የሞራል እሴቶች ከቶውንም የትም አላየሁም ። እንደዚያ ያለ ማሕበረሰብ አከርካሪን
ሰብሮ ለማስገበር መንፈሳዊ እና ባህላዊ ቅርሶቿ በዘዴ እንዲሰበሩ
ካለደርግን በስተቀር ይህችን ሀገር እንቆጣጠራታለን ማለት ዘበት ነው።
ይህንን ለማድረግ አሮጌውን እና ጥንታዊውን የትምህርት ስርዓቷንና
ባህሏን ሁሉ በእንግሊዝ ባሕልና በአንግሊዛዊ የትምሕርት
ስርዓት እንዲተካ ሀሳብ አቀርባለሁ ፣ ምክንያቱም አፍሪካውያን የውጭ ባሕል ሁሉ ስልጡን ነው ብለው እንዲያምኑ ከተደረገ የራሳቸው
የሆነውን ባሕልና ትምሕርት ንቀው ከጣሉት ሌላው ከራሳቸው የሚበልጥ
ነው ብለው ስለሚቀበሉት፣ ለራሳቸው ያላቸውን ግምት በመቀነስ፣ የአፍ መፍቻ ባህላቸውንና ራሳቸው የሚገልጹበት ሃገራዊ ማንተቻውን ሁሉ ያጣሉ። በዚያ ጊዜ እኛ የምንፈልገውን ይሆናሉ፣ በእውነት የበታችና ተጨቋኝ የሆነ ህዝብ ይሆናሉ>>
(ትርጉም ጌታቸው ረዳ)
ይህ የተናገረው የእንግሊዝ ፓርላማ አባል የነበረው Thomas Babington
Macaulay በትንሹ ራስ አሊ ዘመን ኢትዮጰያን ጎብኝቶ ስለ ጉብኝቱ አስመልክቶ በፈረንጆች 2nd Feb 1835 (1827 ዓ.ም
በኛው ዘመን አቆጣጠር) የማይረሳ አራሱን የሚያውቅ፤ ባሕሉን አከባሪ በውጭ ባሕል የማይበገር ኩሩውን ሃገር ያለ ጠመንጃ እንዴት ማምበርከክ
እንደሚቻል የነገረን አመላካች መንገድ ነው።
1827 ዓ.ም የተጠነሰሰብን የውጭና የውስጥ ተባባሪዎች ሴራ ራሳችንን የምንገልጽባቸውን ሃገራዊ ማንነታችንን እንድናጣ እና እነሱ የምንፈልጉትን እንድሆንላቸው ሆነን እነሆ የበታችና ተጨቋኝ የሆንን ሕዝብ ሆነንላቸዋል። እዚህ ላይ ሁላችሁም ትስማማላችሁ በየ እገመታለሁ።
ያ ጥንስስ በ60 አመት ውስጥ
በሃገራችን ተከስቶ እያመረቀዘ መጥቶ በትግሬዎች በሶማሊዎችና በኦሮሞ ፖለቲከኞች ማዳበሪያ አግኝቶ እነሆ ዛሬ በ33 አመት ውስጥ
ሕዝባችን (በክፍል 2 ምታዩት የፎቶፍራፍ) ማስረጃና በክፍል 1 ይህ ዩ-ቱብ የምታዩት ገብረሰዶምነት እና በተለያዩ ዝገባዎች የሚዘገቡት
የዝርፍያ፤ ሱሰኛነት፤ ወላጅን በዱላ መቀጥቀጥ ፤ ህጻናትንና ሰውን አፍኖ በማስገደድ ኩላሊትን መሸጥ ተዋናይ ሆኖ ፤ ማንንቱን እንዲጥል
ተደረጎ የባሕል ወረራ የተፈጸመበት ማሕበረሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቶ ዓይኑን አፍጦ ለማየት በቅተናል። ይህ ማሕበረሰብ መብቱን
ለማስከበር ገዢዎቹን መቃወም እንደማይችል ተደርጎ ተቀርጿል።
ዶ/ር ዮናስ ሆይ!
ከታች ያሉትን መንገዶች እርሰዎም ሆኑ አንባቢዎቼ እንድትመረመርዋቸው ማሕበረሰቡን ተገዢ እንዲሆን
ዋነኛ ምክንያቶች ላሳየዎ።
ይህንን በሚመለከት ከራሴ መጽሐፍ ባጭሩ ቀንጭቤ ላስረዳ።
የተንኮል ቅየሳ (ሳብቨርሲቭ፟)
ሳብቨርሲቭ ምንድነው? “ሳብቨርሲቭ”
ተብሎ የሚታወቀው “ያስተሳሰብ/የፍትወተ ሥጋ/ የሃይማኖት/ የባሕል/ የአመጋገብ/ የቋንቋና ሉአላዊ የድምበር አዋሳኝ እሴቶች በሚጎዳ
መልኩ ለውጥ እንዲኖር፤ ሕዝባችን ከያዘው ትክክለኛ (ነባር) አቅጣጫ ለቅቆ ለጠላቶች ሸብረክ እንዲል” የሚያደርግ ዘዴ ነው። ለምሳሌ
ቋንቋን በሚመለከት እርሰዎ “አምርኛን ለመተካት ‘’በእንግሊዝኛ” እንዲተካ የጻፍት
“አድቮከሲ/ውትወታ” የጥቃቱ ስልት አንዱ መሳሪያና ሰለባ እርስዎ እንደሆኑ ሳልገልጽለዎ አላልፍም።
በጥቃት ላይ ያሉት ከላይ የተጠቀሱት እሴቶቻችን በሕዝቡና በተለይ በወጣቱ ሕሊና ዘመናዊ፤ ማራኪ የሚመስሉ አዳዲስ ክስተቶች በማስተዋወቅ ጠላቶች በሉአላዊነታችንና በወጣቶቻችን አስተሳሰብ ላይ የሚያነጣጥሩበት ነባር የማጥቃት ስልት ነው። በዚህ የማጥቃት ስልት የተጠቃው ሕዝባችን እራሱን እንዲያጣ በመደረጉ እየቀጠቀጡት ያሉት ገዢዎቹ መቃወም ቀርቶ “ግራ ትከሻየን እንድትቀመጥበት ልስጥሕ ወይንስ ቀኙን ትከሻየ ወይንሰ ማጅራቴ ላይ እሽኮኮ ልበልህ እያለ ተመቻቸቶ አለጥለጦ እየተገዛላቸው ያለበት ምክንያት ይህ ሲሆን ፤ 120ሚሊዮን ሕዝባችን እንዴት እንደተጠቃ ስልቶቹን ላስቀምጥ።
የውጭ እና የውስጥ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማጥቃት የተጠቀሙባቸው አራት የጥቃት ዘመቻዎች/ዘዴዎች
በ60 አመት ውስጥ በሕዝቡ ህልውና ላይ ተግባራዊ ሆነዋል። አነሱን አብራራለሁ።
ስለ እነዚህ ጥቃቶች አንስተን “መወያየት” ስለ አገራችን መሰረታዊ “ግንዛቤዎች” እንዲኖሩን
ይረዱናል።
መጀመሪያ በኢትዮጵያ ላይ የተቃጡ አራቱ የጥቃት ዘዴዎች ያልኳቸው ምንድ ናቸው?
“የአሁኑዋ” የወያኔ እና የኦሮሙማዎቹ
“ኢትዮጵያ” እና “ድሮ” የምናውቃት ኢትዮጵያችን በጣም የተለየች ኢትዮጵያ ነች። ልዩነታቸው ለማስረዳት መጽሐፍ ተጽፎም አይበቃም።
ሆኖም፤ ባጭሩ ለመግለጽ ፤
(1) “የሕዝቧ አንድነት ደፍርሷል፡
(2) ግዛቷ/ድምበሯ ተቆራርሶ
ለጠላት ተሰጥቷል፤
(3) ቋንቋን መሰረት ባደረገ
አፓርታይድ ስርዓት እየተገዛ “ሕዝቡ” በጎሳ ተከፋፍሎ እንደ የድሮዋ “ሩዋንዳ” የአምሐራ ነብሰ ጡር እናቶች ሆዳቸው በቢላዋ እየተተረተረ
ጽንሱን በጨው ነስንሰው የሚበሉ የሰው አራዊቶች ተከስተውባታል። በየክልሉ የራሱን ምልክት እና ሃገር መስርቶ አንዱ ባለ ሀገር፤ አንዱ በአድና ባይተዋር ሆኖ መንግሥታዊ ትብብር የታከለበት የህዝብ ማባረር ተከስቶ አስደነጋጭ ዘመን ደርሰናል።
(4) ሰይጣናዊ አምልኮ የሚያስፋፉ ኡሉሙናቲዎች መዲናዋ ውስጥ በመንግሥት እውቅና ጽ/ቤት ከፍተው
የስልክ ቁጥራቸው በደላሎቻቸውና በይፋ ለጥፈው ሕዝብ እየመለመሉ ሐሊናን በመጥለፍ ከቤተሰብ ጋር እንዲራራቅ በማድረግ ፤ ሰው አደንዝዘው
የሰው ደም እንዲጠጡ በማድርግ የሕዝብ ጭንቅላት የሚያኮላሹ ኡሉሙናቲዎች ተስፋፍቷል።
ነብይ ነን የሚሉ እጅግ አደገኛ ወረበሎች በሚሊዮኖች ተከታይ አፍርተው የተከታዮቻቸው ሕሊና
በመጥለፍ የነቃ ማሕበረሰብ እንዳይኖር አደድበውት፤ገንዘብ እየዘረፉ ፤ ባለ ትዳርና ያልተዳሩ ወጣት ሴቶችን በማባለግ፤ አልፎም ህጻናትን አርደው ለአምልኮ በመስዋዕት የተለያዩ አስደነጋጭ
ነገሮችን ማድረግ፤ በመንግሥት ወታደሮች እየታጀቡ በሕዝቡ ሕሊና ተቀባይነት እንዲኖራቸው መንግሥት ተብየው የዚህ የብከላ አባል ሆኖ
ይተውናል።
(5) ሕዝቧ ለስደት እና ለባርነት
ተዳርጓል፡
(6) ወጣቶቿ ለግበረሰዶም፤ለሽርሙጥና፤ለሱሰኛ
እጽ ተዳርጓል
(7) መሬቷ ለባእድ አገር ዜጎች
በስፋት ተሰጥቷል። ወዘተ… ወዘተ…
ባጭሩ የሕዝባችን ሕይወት ለክፉ ሕይወት ተዳርጎ ፤ ቀን ጨልሞበት እራሱን አጥቶ በመንከዋለል
ላይ ነው። ባጭር ቃል “በጠላቶች እጅ የተማረከ ሕዝብ ሆኗል”።
ታዲያ ይህ ሕዝብ እንዴት ገዢዎቹን መከቶ ሊጥል ይቻለዋል?
ይህ እንዴት ተከሰተ? ማንስ ነው የዚህ ሴራ አቀነባባሪ? የሚለው በጥልቅ መመርመር አለብን።
ባለንበት ዘመን፤አገሮች እየተናጉ ነው።ከመጠነኛ መረጋጋት ወደ የከፋ የሕዝብ እና የአገሮች
መደፍረስ ያለ ምክንያት አይከሰትም። ምክንያት አለው ማለት ነው። ምክንያቱን እንፈልገው እና እንወያይበት።
ለኢትዮጵያ መናጋት ምክንያቶች እና የተሰነዘሩብንን ጥቃቶች ወይንም ሌሎች አገሮች ሲደፈርሱ
ከመጋረጃ ሆኖ “ድፍረሳውን” ወይንም የመናጋቱ ትዕይንት የሚያንቀሳቅሰው እና የውስጥ ተቀባይና ፈጻሚው ክፍልስ ማን ነው? እንዴትስ
ይከናወናል?
የኢትዮጵያ ጥቃት ዓለም አቀፍ ተዋናዮች እና በውስጥ ወኪሎቻቸው በኩል የተከናወነ፤የተሰነዘረ
ጥቃት አለ። ያ ጥቃት ምንድ ነው?
አገሮች ሲደፈርሱ በአራት 4ት
ደረጃዎች ውስጥ ማለፍ ይኖርባቸዋል። እነዚህ የድፍረሳ ደረጃዎች
“ዩሪ ቢዝኖቭ” የተባለ የድሮ የሶቭየት ሕብረት የስለላ ክፍል ከፍተኛ ባለስልጣን የነበረው፤ በ1970 ዎቹ አካባቢ ወደ
አሜሪካኖች እጁ በሰጠበት ወቅት በቃለ መጠይቁ ጊዜ “የአሜሪካን ማሕበረስብ ለማፍረስ ሶቭየቶች የተጠቀሙባቸው ስልቶች በጠመንጃ
ሳይሆን “ideological-subversion" ወይንም “ሕሊናን ማጥቃት” የሚል የመንፈስ ጦርነት በማካሄድ ነበር።
ታሰታውሱ እንደሆን ከላይ መግቢያ እንደጠቀሰኩት ልክ የእንግሊዙ ሰውየ ያለው ዓይነት ነው።
ይህ “መንፈስን የማጥቃት ጦርነት”
ከአገራችን ሁኔታ ተመሳሳይነት ስላለው ግንዛቤ እንዲኖረን እንደ መረጃ አቀርባለሁ።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሕብረተሰቡን ነባር፤ የቆየ፤የተረጋጋውን ሰላማዊ ሕሊና፤ አሁን ካለው ከደፈረሰው
የማሕበረሰባችን ሕሊና ሲተያይ “ዩሪ” ከተናገረው ጋር ባስገራሚ ክስተት “መቶ በመቶ” ተመሳሳይነት አለው።
ይህ “ideological subversion” ይህ “ሕሊናን የማደፍረስ” ሴራ ተግባራዊ ለማድረግ፡ አራት ሂደቶች/ደረጃዎች ማለፍ አለበት።ማለትም ያለ ጠመንጃ
፤ያለ ጦርነት “ቀስ በቀስ/ በዝግታ” አንድ አገር ለማፍረስ የሚከተሉት አራት ደረጃዎች ማለፍ አለበት
1. Demoralization
የሞራል ዝቅጠት
2. Destabilization
አገርን ማናጋት
3. Crisis አገርን በቀውስ
ሂደት ማስገባት
4. Normalization የውሸት
እርጋታ የመጨረሻው የአገሪቱ ሕልፈተ ሞት (ልክ ወያኔ ወይንም ኒው ወርልድ ኦርደር የተባለው “አዲስ ሴራ” አገሪቱን/አለምን “ኖርማላይዝ”
አድርገናታል (አረጋግተናታል) እያለ ሀገሮች እዲፈራረሱ ፤ሕብረተሰቡ “በጎሳ ጽዳት” እንዲፋጅ እና አገሪቱ አንዳትኖር የማድረግ የመጨረሻው የአገሪቱን
“ግብአተ መሬት” አንዲጠናቀቅ የሚደረግ የመጨረሻው ዘዴ ማለት ነው።
እነዚህ አራት ደረጃዎች በኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ሕይወት በመከናወን ላይ ናቸው። አንዳንዳንዶቹ ተጠናቅቀዋል።
የመጀመሪያው “ዲሞራላይዘሽን”( የሞራል ዝቅጠት) ሂደቱን ስንመለከት፡
ዩሪ የሚለን አንድ ነገር አለ። በእንግሊዝኛው ልጥቀስ “You are what you eat, and your brain is the product of its perceptions. Americans consume data bits from television each night.፡ ሲተረጐም ካላበላሸሁት በቀር፡ እሱ የሚለው “ አንተነትህ የሚወስደው ቅርጽ አንተ በምትመገበው ምግብ የሚሰጥህ የአከላት ቅርጽ ሲሆን፤ ሕሊናህም የሚቀረጸው “ሆን ተብሎ” ያለ አማራጭ ሌት ተቀን ወደ ኣእምሮህ “በሚቀዳ” የቴሌቪዥን መረጃዎችን ነው።” ይላል። ይህ ዲሞራላይዘሽን (የሕሊና/የሞራል ዝቅጠት) ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን በማጥቃት ላይ ነው። ወጣቱ በምዕራቡ እና በዓረቡ ኣለም ባሕል፤ቋንቋ፤አለባበስ እና አስተሳሰብ ተዘፍቀዋል።
በውስጥና በውጭ ሃይሎች በሚመድቡላቸው ሥራ ማስኬጃ ውይንም በራሳቸው ጥረት ተደግፈው በቲቪ/በትያትር
ቤቶች/በመዝናኛ ማእከሎች/በስፖርት እና በሙዚቀኞች፤ በፊልም ተዋናዮች፤ በሚለብሱት፤ በሚናገሩት፤ በሚያጨሱት እና በሚያመነዥጉት፤ በሚጫሙዋቸው
ጫማዎች እና ልብሶች በኩል የሕብረተሰቡን ሕሊና በመለወጥ አገራዊ ባህሉን እና ቋንቋው አንዲነጠቅ ተደርጋል። “አንደበቱ እና አእምሮው”
ኢትዮጵያዊ ሳይሆን “አረባዊ ወይንም ምዕራባዊ” ባህል ለበስ ሆኗል።
የታሪክ ተንታኞች እንደሚሉት ‘ባሕሉ የተነጠቀ ማሕበረስብ’ “ጥዋት የወጣበትን ቤት” ማታ ሲመለስ
‘ጥዋት የወጣበትን’ ቤት አያውቀውም እንደ ማለት ነው ይላሉ። ጥቃቱ የሚያነጣጠረው ኢላማ አብዛኛው በወጣቱ ስለሆነ ወጣት አገር
ተረካቢ እንደመሆኑ መጠን ‘የተምታታ ሕሊና’ ያለው ወጣት ደግሞ “አገሩን ብቻ ሳይሆን፤ማንንቱን አያውቅም” ማለት ነው። ማንንቱን
የሳተ ሕሊና ደግሞ ስለ አገሩ ጥቃት ግንዛቤ የጐደለው ይሆናል ማለት ነው።
የዲሞራላይዘሽኑ/የሞራል ዝቅጠቱ
ሂደት በአንድ አገር ለማከናወን የሚወስደው እድሜ ከ 15 እስከ 20 አመት ይፈጃል። ይህ ሂደት ኢትዮጵያ ውስጥ ተጠናቋል።ዩሪ እንዲህ
ይላል። “Why that many years? መልሱን ይሰጠናል፦
ክፍል 2
ሰሞኑን ይቀጥላላል
አመሰግናለሁ
ከላይ የጠቀስኩት የሕብረተሰብ የሞራል መብሰበስ ቪዲዮውም እነሆ፤ ሕበረተስባችን ግበረሰዶማዊ ለማድረግ ከላይ በተደራጀ አካል ገንዘብ እየተረጨ፤ ግብረሰዶም ፈጻሚዎች ልክ እንደ "አሜሪካን ጋንጎች" በቡድንና በአለቃ ሴቶችና ወንዶች በማደራጀት በየመታሺያ ንግድ ቤቶች ደምበኞቻቸው አሰማርተው በገረሰዶማዊያን ተገደው እንዲደፈሩ እየተደረገ ያለው የጥቃት ዘምቻ እነሆ ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ።
ማሳጅ ሊሰራ ገብቶ ጉድ ሆነ //የቺቺኒያው የማሳጅ ቤት ጉድ ተጋለጠ
https://youtu.be/iYHcP1wtWdU?si=1y-z8_EJdO1gc42v

No comments:
Post a Comment