ጀግና ገዳይ እና ባንዳ አወዳሽ ልዩነቱ ምንድነው? ለትውስታችሁ
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
8/3/25
ቪዲዮውን ለማየት ግን ወደ Ethiopian Semay ፌስቡክ ኄደው ይመልከቱ።
ዱርቡሽን የተዋጋ ሃገር ወዳድ እንደነበረ ገልጸው፤ ሆኖም ከ50ዎቹ ወዲህ የተፈጠረው ትውልድ ግን “ጀግና ገዳይ” ነው ይሉና፤ ቆይተው ከመቅጽበት ያንን እነዲያ ያሉትን ትውልድ በመጻረር አፄ ምኒሊክን ከባንዳው መለሰ ዜናዊ ጋር አብሮ ባንድ ብዕር “ቅኝ ገዢዎች” ብሎ ምኒሊክን የተሳደበ ፤ ለዓረብና ለግብፅ ቅጥረኞች ለሻዕቢያዎች ወገኖ አምሐራን “ነፈጠኛ ወራሪ፤ 14 ክ/ሐገር ዘማሪ፤ የሰው ሃገር ተመኚ” ወዘተ... እያለ የተሳደበ ከብርሃኑ ነጋ ጋር አብሮ የባንዳነት ሥራ በዘላቂነት የቆየ ኤፍሬም ማዴቦ፡ በወቅቱ ግንቦት 7ን ለመቀላቀል ከዚህ አሜሪካ ወደ አስመራ ኄደ ሲሰሙ በየዋህነት (እኔ የዋህነት ነው የምለው) ዕምባቸውን አቅርረው “አዲስ ጀግና ተወለደ” ዓይነቱ ውዳሴ ባሰሙን ወቅት እኔም ኤፍሬም ማዴቦም ሆነ ብርሃኑ ነጋ ሁሉም ባንዳዎችና ጸረ አማራዎች ናቸው የአማራዎችን ጅግነነት የሚገድል ጀገና ገዳይ ኤፍሬም ማዴቦና ግንቦት 7ን ማወደስዎ “ባንዳ አወዳሽነት” አይሆንበዎትም ወይ? ብየ ከላይ የጠቀስኩትን ርዕስ ጽፌ ከግንቦት 7 ደጋፊዎች ብዙ ስድብ ማስተናገዴን አስታውሳለሁ።
በቅርቡ አንድ የዋህ ሰው ባንድ ገሮሰሪ ሱቅ አግኝቶኝ አድናቆት ከለገለጸልኝ በኋላ እንዲህ ሲል ወቀሳውን አከታትሎ “ባለፈው ወር ሰለ ጻፍከው ኤፍሬም ማዴቦም ሆነ ብርሃኑ ነጋ የተቸህበት ጽሑፍ ከነ ፎቶግራፋቸው ያቀረብከው ተመልክቸው ደስ አላለኝም። የጠቀስካቸው ሰዎች እኮ ብታዋቂው ሙሉጌታ ሉሌ ሳጠቀር የተመሰግኑ የተከበሩ ሰዎች ናቸውና ተችትህ በጣም የምወደው ብሆንም እዚህ ላይ ግን አልወደድኩትም... ወዘተ.. እያለ የግንቦት 7ቶቹ መወድስ አቅርቦልኝ ፡ በባሕሪየ ከማላውቃቸው ጋር አተካራ መግጠም ባሕሪየ ስላልሆነ፤ መጠነኛ ውይይት ባደርግለትም ችክ ሲልብኝ ትቸው በወንድማዊ ሰላምታ ተሰንበትኩት። ሰወየው እንደነገረኝ ተከታታየ ስለሆነ ለእርሱም ሆነ ሌሎሽቻችሁ የወቅቱ ፖለቲካ ባዳ ለነበራችሁ ሁሉ ታሪክ ነውና በተማሩበት እነሆ ተከታተሉኝ።
ዘመነ ካሴ ሲታገልለት የነበረው የብርሃኑ ነጋ እና የኤፍሬም ማዴቦ የግንቦት7 ምንነት በአቶ ተክሌ የሻው አገላለጽ ልጀምር፡
ግንቦት 7 በዐማራው ላይ የገነባው ጥላቻ የቱን ያህል የከፋና የከረረ መሆኑ ማሳያው የሚከተሉት ናቸው።
(ሀ) የግንቦት 7 አመራር አባል ለመሆን ከአማርኛ ውጭ ሌላ ቋንቋ የሚናገር መሆን እንዳለበት ይደነግጋል። ይህም ማለት አማርኛን
ሲያልፍ በየመንገዱ ማንም የሚናገረው የወል ቋንቋ ነው። ይህም የግንቦት 7ን ማንነት አይገልጽም። የግንቦት 7ን ማንነት ለመላበስ
ወይም ለመሆን፣ ዛሬ ደቡብ ተብሎ በተደራጀው የኢትዮጵያ ክፍል ከሚኖሩ ከ45 በላይ ነገዶች የአንዱ አባል የሆነ፣ ያን ቋንቋ የሚናገር መሆን አለበት። ይህ ሲሆን ብቻ ነው የግንቦት 7 መገለጫ። አማርኛ መናገር ለዚህ ድርጅት መገለጫውም መታወቂያውም አይደለም።ባዕድ ነው። ግንቦት 7 ዐማራውን የሚፈልገው የገጠሩን ለወታደርነት፣ ለጦርነት ነው። ከተሜውን ዐማራ፣ ለገንዘብ፣ ለወንበር ድርደራ፣ ለስብሰባ አድማቂነት ነው። ከዚህ ውጭ በውሳኔ ሰጭነትና ሀሳብ አፍላቂነት ኢትዮጵያዊነትን ስለሚያስቀድም አይፈለግም
ለዚህም በአመራሩ ውስጥ አንድ ዐማራ ተፈልጎ አይገኝም። አለን ካሉም በእሳት ውስጥ እንዳሉት ኤርትራውያን ወይም ይኸን ያህል በመቶ
ዐማራ ነን የሚሉ ናቸው። እነዚህ ደግሞ በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ የቱን ያህል እንደሚሆን አምላክ ይወቅ።
(ለ) በግንቦት 7 ልሣን በሆነው ጋዜጣቸው ቁጥር 25 ጥቅምት 2001
ዓም ርዕስ አንቀጽ፣ ለ250 ዓመታት በነጮች ሲገዙ የነበሩት
ጥቁሮች ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ከበቁ፣ እኛም ለአሥር ሺ ዓመታት በዐማሮችና በትግሮች ስንገዛ የኖርነው ኦሮሞዎችና ደቡቦች የኢትዮጵያ መሪዎች እንሆናለን፣ በማለት የገለጹት፣ ዐማራውን በገዥ እና ጨቋኝ ብሔረሰብ ፈርጀው ለመበቀል የተደራጁ መሆኑን ያሳያል።
(ሐ) የግንቦት 7 ሊቀመንበር ብርሃኑ ነጋ፣ ከእስር ተፈትቶ አሜሪካና አውሮፓ እንደገባ ለምን ቅንጅትን አፈረስክ ተብሎ ለተጠየቀው
ጥያቄ ፣ የሰጠው መልስ ትግሬ አውርጀ ዐማራ ሥልጣን እንዲይዝ ባለመፈለጌ ነው ማለቱ ይታወሳል። ከእሥር እንደተፈታ የእሥር ጓደኞቹን ተለይቶ ገሥግሶ የገባው ከኦነግ ጋር ግንኙነት ለመመሥረት የሚያስችለውን መሥመር ለመዘርጋት ወደ ዱባይ እንደሆነ ይታወቃል።
(መ) «የደራሲው ማስታዎሻ» በሚል ርዕስ የሻዕቢያው ሰላይ ተስፋዬ ገብረአብ የጻፈውን ዐማራን፣ ምኒልክንና ቴዎድሮስን በአጠቃላይ
የኢትዮጵያዊነት የወል ዕሴቶችን አራክሶና እንዳልነበሩ አድርጎ የጻፈውን፣ ያሳተመው ንብረትነቱ የግንቦት 7 የሆነው «ነፃነት አሳታሚ»ነው። ይህንም ትውልድ አጥፊ መጽሐፍ ብርሃኑ ነጋ እንዲህ ሲል በሽፋን ገጹ ላይ አድናቆቱን ሰጥቷል።
«ባለፉት 40 አመታት የፖለቲካ ስነጽሁፍ ተቀብሮ ከነበረበት፣ ተስፋዬ ገብረአብ ራሱም ባንድ ወቅት ተዘፍቆበት ከነበረው እንጨት እንጨት ከሚል የካድሬ ፖለቲካ መሳሪያነት አውጥቶ አድማሳዊ የሆኑ ሰብአዊ እሴቶችን መፈተሻ በማድረግ ነፍስ ሊዘራበት የጀመረው ሙከራ እየተሳካ ለመሆኑ`` የደራሲው ማስታዎሻ`` በቂ ምስክር ነው» ይላል ።ብርሃኑ ይህን ምስክርነት ሲሰጥ፣
ለተስፋዬ አድናቆቱን የሰጠው በጋራ የሚጋሩትን በመጽሐፉ በእያንዳንዱ ርዕስ ዐማራና ኢትዮጵያዊነትን ጥላሸት ስለቀባለት ነው።
ዐማራው ኢትዮጵያ ውስጥ አልተወለደም ወይ? ዐማራው ፍትሕ፣ ዕኩልነት ቀርቶ በአገሩ የመኖር መብት አለው ወይ? ዛሬ ለዐማራው ድምፅ እየሆኑ ያሉ ወገኖችና ኤፍሬም ማዴቦና ብርሃኑ ነጋ በዘውግ አራማጅነት የሚከሳቸው፣ በምሥራቅ እና በምዕራብ ሐረርጌ፣ በአርሲ አርባጉጉ፣ በምሥራቅ ወለጋ፣ በኢሉባቡር፣ በጃዊ፣ በመተክል፣ በጉራ ፈርዳ፣ በወልቃይት ፣ጠገዴ፣ ጠለምትና አርማጭሆ፣በራያና ቆቦ ይኖሩ በነበሩ ዐማሮች ላይ፣ ከዘር ማጥፋት እንስከ ዘር ማጽዳት ወንጀል ሲፈጸምባቸው እንደ ድርጅት ግንቦት 7፣ እንደ ዜና አውታር ኢሣት መግለጫ ሊያወጡ ቀርቶ፣ ሞረሽ ወገኔ ያወጣቸውን የአገዛዙን ገመና የሚያጋልጡ ሐቆችን ለመዘገብ አልሞከሩም።
ከሁሉም በላይ በተስፋዬ ገብረአብ የተጻፈው «የቡርቃ ዝምታ» የተሰኘ ፀረ- ምኒልክና ዐማራ የሆነው የሻዕቢያ የፈጠራ ድርሰት ዕውቅና ተሰጥቶት አገዛዙ የኦሮሞና የዐማራ መጭ ትውልዶች ጎን ለጎን እንዳይቆሙ፣ ዓይንና ናጫ ሆነው የወያኔን አገዛዝ ከማስረዘም አልፎ፣ኢትዮጵያ እንድትበታተን ዕውቅና የሰጠውን «የአኖሌ ሀውልት» የተሰኘ፣ በመሀል መዳፍ ላይ የተቆረጠ ጡት የተቀመጠበት ሀውልት በይፋ አርሲ ላይ ሲገነባ፤ግንቦት7ም ሆነ ኢሣት ያሉት አንዳችም ነገር የለም።
ይህን በተመለከተ የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የአማርኛው ክፍል አገልግሎት ዶ/ር ኃይሌ ላሬቦን፣ ዶ/ር ሹመት ሲሻኝን እና አቶ ቡልቻ ደመቅሳን አነጋግሮ ነበር። ሁለቱ የታሪክ ምሁራን ምኒልክ በዚያ ቦታ የኦሮሞ እናቶችን ጡት ስለመቁረጣቸው የሚያሳይ መረጃ አለመኖሩን ሲገልጹ፣ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ደግሞ «ምኒልክ የኦሮሞን እናቶች ጡት ቆርጧል፤ ምኒልክ የጥቁር ፋሽስት ነው» ሲል የታሪክ ዕውቀቱን ሳይሆን፣ የፖለቲካ አቋሙን መናገሩን እናስታውሳለን።
ይህን ተከትሎ እኔ ተክሌ የሻው ኢሣት ቢሮ ሂጀ፣ ስለአኖሌ ሀውልት የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተጋበዙ ሐቁ ከሀሰቱ፣ ፖለቲካው ከታሪክ፣ፈጠራው ከነባራዊ ተለይቶ እንዲታወቅ ፕሮግራም በሥፋት እንዲሠራ ላቀርብኩላቸው ጥያቄ፣ የወቅቱ የኢሣት ሥራ አመራር ኃላፊ የነበረው ንዓምን ዘለቀና ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን በአንድ ድምፅ «እኛ እኮ ኦሮሞ ነን» በማለት ዕውነቱን ለሕዝብ ለማሳወቅ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ማንም እንደሚገነዘበው ኤፍሬም ማዴቦና ዶ/ር ላጲሶ ጌድሌቦ የአንድ ነገድ አባል ባይሆኑም፣የአንድ አካባቢ ሰዎች ናቸው። ላጲሶ በፋሲል የኔዓለም
ጠያቂነት ረጅም ሰዓት ተሰጥቶት፣ ዐማራን፣ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን፣ ምኒልክን ፣ ነባርና ተያያዥ የኢትዮጵያዊነት የወል እሴቶችን፣ የሕዝቡን አኗኗርና ታሪክ ተረት ተረት ናቸው። የኢትዮጵያ ታሪክ እንደገና መጻፍ አለበት ሲል ለቀባጠረው አጸፋ ለመስጠት፣ ጋዜጠኛውን ጠይቄ ፈቅዶልኝ ባደረግነው ውይይት፣ ከሙያው ሥነ-ምግባር በወጣ መልኩ እኔን ያሳነሰኩ፣ ላጲሶን ያሳደገ መስሎት፣ እርሱ እንደነገረንም ሚስቱ እስከምትስቅበት ድረስ
የወረደ፣ በግንቦት 7 እና በኢሣት አመራሮች የተሰጠውን የቤት ሥራ ለመወጣት ያደረገው የተወላከፈ ተግባር ፕሮግራሙን ያዳመጡና ያዩ ያውቁታል።”
ሲሉ አቶ ተክሌ የሻው በወቅቱ በሻዕቢያ የተበረከተለት ባጀት ሲካሄድ የነበረው ጸረ አማራው የብርሃኑ ነጋ ኢሳይ ቲቪ።
በመቀጠልም የሻዕቢያና የብርሃኑ ነጋ አለቅላቂው ፋሲል ይኔአለም ይቅርታን በሚመለከት አቶ ተክሌ የሻውና ፋሲል መካከል የነበረው ጉድ አንብቡ፡ እነሆ፡
ይህ በኢሣት ዝግጅት ላይ የፈጠረው አሉታዊ ተጽዕኖ ማየል የተነሳ፣ የዝግጅት ክፍሉ ፋሲል እኔን ይቅርታ እንዲጠይቅ ያዘዋል። ፋሲልም በታዘዘው መሠረት ደውሎ ስለሁኔታው በማውሳት ይቅርታ አድርግልኝ ይለኛል። እኔም ይቅርታ መጠየቅ ታላቅነት ነው። መልካም አልኩት። ይህን በአየር ላይ አውለዋለሁ አለኝ። እኔ ስንነጋገር እየቀዳ መሆኑን አላውቅም ነበር። እርሱም የሚቀዳው መሆኑን አልነገረኝም ነበርና፣ ይህማ አይሆንም። ይቅርታው በእኔና ባንተ ብቻ ይበቃል ስለው፣ የለም በዚህ የተነሳ በድርጅቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ስለተነሳ ይቅርታውን ሕዝብ መስማት አለበት አለኝ። ጉዳዩ ይህ ከሆነና ይቅርታው በአየር ላይ እንዲውል ከፈለክ በእኔና በአንተ መካከል አንድ ሰው መኖር አለበት። ያ ሰው ስለጉዳዩ አብራርቶ የአንተን ይቅርታ ጠያቂነት፣የእኔን ይቅር ባይነት ማሳየት አለበት አልኩት። እርሱም
በሀሳቤ ተስማምቶ ማን ቢሆን ትመርጣለህ አለኝ። እኔም አቶ ሢሣይ አጌናን እመርጣለሁ አልኩት። በዚህም ተስማምቶ ተለያየን።
ብዙም ሳይቆይ ሢሣይ ደወለልኝ። በእርሱ አማካኝነት ፋሲል፣ እኔን ይቅርታ እንደሚጠይቅ ነግሮኝ ቀጠሮ ያዝን። በቀጠሮ ቀን ሁለቱም ጠፉ። ደወልኩና ምነው አልኩት ሢሣይን። ሁኔታውን እያመቻቸን ነው በቅርብ ቀን ይሆናል አለኝ። ጠበኩ፤ የውኃ ሽታ ሆነ። በመሐል አንድ ሲያትል እንደሚኖር የተነገረኝ ሱራፌል የሚባል ሰው ኢሜል ደረሰሰኝ። የኢሜይሉ መልክዕት «ኢሣት ተክሌን ይቅርታ ቢጠይ ካለፈው የከፋ ጉዳት ያደርሳልና ባይጠየቅ ይሻላል» የሚል ነው። ይህንም ለሢሣይ እንዲያውቀው ብየ ላኩለት። መልስ የለም። እያሉ አቶ ተከሌም ሆኑ እኔ በሻቢያ አለቅላቂዎቹ በግንቦይ 7 (በብርሃኑ ነጋ እና በኤፍሬም ማዴቦ) የነበረንን ትችት ፈጣሪ ነበሳቸውን በገነት ያኑልርን የተከበሩት የጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በወቅቱ ባንዳው ኤፍሬም ማዴቦና ብርሃኑ ነጋ በየተራ ከአሜሪካ አሥመራ ወደ አለቃቸው ወደ ሻዕቢያ ሲሄዱ ዕማባቸውን በየዋህነት ያፈሰሱላቸው እና “አዳዲስ ጀግኖች” ብለው ውዳሴ በማሰማታቸው “ጀግና ገዳይ እና ባንዳ አወዳሽ ልዩነቱ ምንድነው?” ብየ በመተቸቴ ከግንቦት 7 ደጋፊዎች ብዙ ዘለፋ ማስተናግዴን አስታውሳለሁ። ያኔ እውነት በመናገራችን በመሁሩም ባልተማረው መንጋ ስንሰደብ ኖረን፤ ዛሬ ግን የነ ብርሃኑ ነጋ እና ኤፍሬም ማዴቦ ማንነት ጠቂት ባይረዳቸውም በዙውኑ መንጋው ፊት በመጋለጣቸው ደስ ሲለኝ የሆይ ሆይ ፖለቲካችንን እንደገና ወደ መድረክ አምጥቼ ማስተማሪያ እንዲሆነን እንጂ ሙት ወቃሽ ለመሆን እንዳልሆነ ለማስታወስ እሻለሁ።
ዋናው ቁም ነገሩ ዛሬም ካለፈው ሳንማር ፋኖ ውስጥ በአመራር ደረጃ ተቀመጠው ፡ ምመህራንን፤ ጋዜጠኖችን የሚጠልፉ፤ የሚገድሉና የሚያሳድዱ ፤ ለጫካ ሥልጣን ሲሉ ትግሉን የሚያበላሹ ዘራፊ እና ጎጠኞች የሽምቅ ተዋጊ መሪዎች እንዲሁም “በየቲክቶኩ እና ዩ ቱብ” እየተኮፈሱ “ትግል ሜዳ ሂዱ ሲባሉ የማይሄዱ እዚህ ሆነው ግን ያልሆኑትን ለመሆነ የሚቀባጠሩ ወጣት የቲክታክና የ ዩ ቱብ አርበኞች ከማጀገን እንደንቆጠብ ነው።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ Ethiopian
Semay

No comments:
Post a Comment