Tuesday, August 26, 2025

የኢትዮጵያ ባንዳዎችና የኤርትራ ባንዳዎች ይህንን ጥያቄ መልሱ ! መልስ ለ EMS Special የኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የጋራ ውይይት Sat 02 Aug 2025 ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 8/26/25

 

የኢትዮጵያ ባንዳዎችና የኤርትራ ባንዳዎች ይህንን ጥያቄ መልሱ !

መልስ ለ EMS Special የኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የጋራ ውይይት Sat 02 Aug 2025

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian  Semay)

8/26/25

ፎቶ Eritrea in 1892 ይህ ሕዝብ ኢትዮጵያ ካልሆነ ማን ሊሆን ይችላል! 

ይህ ሕዝብና መሬት የኛ ነው የምንለውም ለዚህ ነው፤ ፎቶው ይናገራል፤ተመልከቱት እስቲ!

ኢትዮጵያዊያን ውጣቶች ሆይ! እባካችሁ ታሪካችሁን እወቁና አንብቡ። 

ካለፈው ሰሞን የገታነው ውይይት የቀጠለ።

 EMS (Ethio Media Service) በተባለው አፍቃሬ ሻዕቢያ ሚዲያ ላይ በተካሄደው “የኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያን የጋራ ዉይይት Sat 02 Aug 2025” የሻዕቢያው ጸሐፊና ፕሮፓጋንዲስት አቶ ዓለምሰገድ ተስፋይ “An African People's Quest for Freedom and Justice: A Political History of Eritrea, 1941-1962 Hardcover – April 15, 2025” የሚል በውሸት የታጨቀ መጽሐፉን እንዲገመግሙለት የኛዎቹ አለቅላቂዎች ጋብዘውት ሰለ ፍደረሺኑ ኢሕጋዊነት መፍረስ በውሸት ሲቀደድ የኛዎቹ አለቅላቂዎቹ በውሸቱ በመስማማት እንደልቡ እንዲቀደድ የለቀቁትን የውሸት ትርክቱን እንደሚከተለው አቀርባለሁ።  

በሚገርም ሁኔታ ከተወያዮቹ አንድ ዋሾ ኤርትራዊ "መለስ ዜናዊ ኤርትራ እንድትገነጠል ለተባበሩት መንግሥታት ዕውቅና ደብዳቤ አልጻፈም፤ መረጃም የለም" ሲል  "የሻገተው ሕሊናው ማስታወስ ባይችልም፡ እዛ የተገኙት አቅላቂ የኢትዮጵያ ባንዳዎቹ "ማስረጃ አለ" ለው ሳይመለሱለት እንደተለመደው አፋቸው ከፍተው ውሸት ሲቀበሉ ነበር። 

ማስረጃው TRANSITIONAL GOVERNEMENT OF ETHIOPIA OFFICE OF THE PRESIDENT 13 December 1991 የጻፈበትን ደብዳቤ ከራሴው መጽሐፍ ይመለከቱ ወይንም ጉጉል አድርጉት።

ፈደረሺኑ ሲፈርስ ሕጋዊ ነበር። ብዙ ኢትዮጰያዊያን ለብዙ አመታት ንጉሡን በምተቸት  ከዓረብ ራቢጣው ሻዕቢያዎቹ ጋር በመስማማት ንጉሡን ሲዘልፉና ሲቃወሙ አድምጠናል።ዛሬም በተጠቀሰው መድረክ ያንን መስመራቸው እንደቀጠለ ነው።

ወደ ጥልቁ ትንተና ከመግባቴ በፊት መገንዘብ ያለብን ፈደረሺኑ ሲፈርስ የተባበሩት መንግሥታት ተቃውሞ አላሰማም። ምክንያቱም ሕጋው ትራሶች እንደነበሩት ያቃሉ። አሁን ወደ ትንታኔ እንግባ።

የኤርትራኖቹ ጉራ እንደምታውቁት በፈደረሺን የተነጠቅነው ነፃነታችን በጉልበታችን አስመልሰነዋል የሚል ነው። ፋሺስቱ ወያነ በትግሉና ከዚያም መንግሥት ሆኖ ባይረዳው ነፃነት የሚሉት ባርነታቸውን አያገኝዋትም ነበር። የኤርትራ ገለባነት በቅርቡ እንዴት ተፈትሾ  እንዳየነው በዚህ እንጀምር።

 “Eritrea Licks its wounds” (BBC Focus on Africa) Report during the Badime war between Eritrea bandits and Ethiopia gallants ትርጉም ኤርትራ ቁስሏን አላምጣ ላሰች(ቢቢሲ ትኩረት በአፍሪካ- ዘገባ “ኢትዮ- ኤርትራ ዋር” ተብሎ በሚጠራው ስለ የባድሜ ጦርነት ሲዘግብ ኤርትራኖች 3/4ኛውን መሬታቸውን ጥለው ተሸንፈው ኢሳያስ ፋሎቹን እያቃጠለ ወደ ሳሕል ሊሸሽ ይዘጋጅ እንደነበር በወቅቱ ዘግቤአለሁ። ወታደሮቹም “ፈርጥጠው ወደ አስመራ እና ወደ ሱዳን” እየሸሹ በነበሩበት ለታሪክ የተዘገበ ርዕስ ነው፤ “Eritrea Licks its wounds”

አሁን ወደ ታሪካዊ ክርክራችን ትንታኔ ልግባ።

ወያኔና ሻዕቢያ በውጭ ሃይላት ተደግፈው በሕገ ወጥ መንገድ መንግሥትነት ተቆጣጥረው አንድ አገር ለሁለት ከፍለው፤ 1998 ተጠያቂነት በሌለው ጦርነት ውስጥ 70 ሺሕ ሕዝብ ህይወት አጥፍተው በተባለበት ጦርነት አንዳቸውም ተጠያቂ አልሆኑም። የድሃ ልጅ ሞቶ ቆስሎ እነሱ አሁንም ሥልጣን ላይ አሉ።

ትግሬዎችን የተካው የኦሮሙማው ጨቅላ “አብይ አሕመድ የሚመራው ተረኛው የኦሮሞዎች አፓርታይድ መንግሥት ከመጣ ወዲህ የጄዳ ስምምነት ተብሎ ሳውዲ ውስጥ የተፈረመው አንቀጽ 4 በጠቅላላ አወዛጋቢው የ1200 ኪ.ሜ የድምበር መስመር ባድሜን ጨምሮ ሕገወጡ “የአልጄሪሱ ስምምነት” መሰረት አድር ለኤርትራ ሊሰጥ በምዕራባውያን አለቆቻቸው የሚመሩት የተባበሩት መንግሥታት ሊቀመንበሩ አንቶንዮ ጉተሬዝና ቻዳዊው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ‘ሙሳ ፋቂ ሞሃመት” አፈራራሚነት ፈርሟል። ይህ ሴራ  በሕግም በታሪክም ዉሃ ባይቋጥርም፤ ሊጎዳን የተሴረ ሴራ ነውና ይጎዳናል። 

አንዳንድ ጅል ኢትዮጵያውያን ጦርነቱን ለማቆም ሰላም ለማምጣት ስለሚረዳ ባድሜ ለኤርትራ ያለ ቅድመ ኩነት/ሁኔታ መሰጠት አብይ የገባበትን ውል እንደግፋለን በማለት የመለስ ዜናዊን ሴራ እውን እንዲሆን በቀጥታም በተዘዋዋሪም ሲጪሁ እየሰማን ነው። ሆኖም ያለ ማንም ፈቃድ ኢሳያስ ባድመን ይዞታል። አሁን ደግሞ “ጽምዶ” በተባለ የትግሬ ባንዳዎች ስብስብ ኢሳያስን ወዳጃችን፤ አዳኛችን እያሉ አሥመራ ድረስ በመሄድ እየሰገዱለት እያየን የምናየው አሳፋሪ ክስተት ከላይ በተጠቀሰው EMS (Ethio Media Service) በተባለው አፍቃሬ ሻዕቢያ ሚዲያ ላይ በተካሄደው “የኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያን የጋራ ዉይይት Sat 02 Aug 2025” ላይ የድሮ የጦቢያ መጽሄት ብዕርተኛው ቋሚ ጸሐፊ የነበረው የዓፋር ተወላጁ የሱፍ ያሲን (የብዕር ሰሙ አሕመድ ዑመር ዓደላ) ጽምዶን በመደገፍ ከእርሱ ያልጠበቅኩትን ጅልነት ሲሰብክ ሰማሁት።

ኢትዮጵያን በመጉዳት የሚመጣ የሴረኞች ሰላም ከተጨባጩ ሃቅ የራቀ ስለሆነ፤ መነሻውና ማቆሚያው በቅጡ ካላወቅነው፤ ሰላም ፤ሰላም፤ሰላም ብቻ ስለተመኘን ሰላም ሊመጣ አይችልም። ሰላም ያመጣል ተብሎ መለስና ኢሳያስ በበረሃ ስምምነታቸው መሠረት ኤርትራን ካስገነጠሉ በኋላ እስከ 70 የሰው ህይወትን በርካታ ንብተረትና መፈናቀል ደርሷል። ምክንያቱም ግልጽ ነው። በሴራ የተፈጸመ  የድብብቆሽ ፌርማ ቀን ጠብቆ ይፈራርስና ጸቡ ያገረሻል። እንዳልኩትም የቅርቡ ትግራይ ውስጥ የታየው ጦርነት ህያው ምስክር ነው

በዚህ የውይይት መድረክ በተደጋጋሚ ኢትዮጰያ ነን ከሚሉ ወገኖች የሰማሁት በሁለቱ ሕዝቦች ሰላም እንዲመጣ ስሜት ብቻ ያጀበውሰላም፤ ሰላም፤ ሰላምየሚል ቃላት ብቻ ሲናገሩ፡ ኤርትራውያኖቹ ግን የተካኑበትና የሸበቱበት የውሸት ባሕላቸውን ሳይለቁ የኢሳያስ መሰሪ መሰመር የዘው ሲናገሩ ነበር። ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ፤ ያለ ሕግ የተነጠቅነውን የባሕር ወደባችንን በፈቃዱ ለኢትዮጵያ እንዲያስረክብ የሚፈቅድ ቡድን ወይንም የሚያስገድድ ፍስፍስ የማይል ቢንጨረጨርም ግድ የማሰጠ የኛ መሪ ወይንም ቡድን ሲፈጠርኤርትራውያኖቹ ለጠረጰዛ ውይይት ተገደው ይቀመጡናየእንካ አምጣያኔ ወሳኙና የሰላም ምንጩና መፍተሄው ይህ ይሆናል። ሌላው በተደጋጋሚ ተሞክሮ የከሸፈ ነው።

አናደርግም የሚሉ ከሆነ እና የኢሳያስና የሻዕቢያ  መንገድ እንከተላለን የሚሉ ከሆነ፤ ጊዜ ይፈጃል እንጂ በመጪውየነቃ ትውልድከባንዳነት የጸዳ አንድ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወደ ሥልጣን እንዲወጣ ሲደረግ፤ ወይንም የኢትዮጵያ አምላክ በአስገራሚና አስደንጋጭ ተአምራቱባንዳውመለስ ዜናዊናአበ ነብሱየነበሩት አባ ጳውሎስን በተአምር እንዳስወገዳቸው ሁሉ፤  “አብይ አሕመድም (ወደብ ወደብ ማለቱ ሩ ነበር ፤ ግን እስከምጨረሻ አይገፋም አይፈጽመውም ፤ ይህ ካለፈጸመ ግን) በተመሳሳይ ጥሪ  ወደ ሌላኛው ዓለምከተጠራ” በምትኩ አንድ አገር ወዳድ አርበኛ ኢትዮጵያዊ ወታደር ወይንም ሲቪል ስልጣን ሲቆጣጠር ባንዳዎች የወሰኑት ውሳኔ ሽሮ ከላይ የጠቀስኩትን የሰላም አማራጭ መንገድ አንወስድም ብለው የሚያንገራግሩ ኤርትራ ቡድኖች ከተከሰቱ፤ የናፈቁትን ጦርነት ከፍቶ፤ ባሕሮቻችንን መልስን በመቆጣጠር፤ የአሉላ አባ ነጋ፤ የንጉሥ ሰርፀድንግል ታሪክ በመድገም የመጨረሻው አማራጩ የመፍትሔ ሃሳብ ሲፈጸም ብቻ ነውሰላም እያልን የምንኳትተው ሕልም እውን የሚሆነው ዓለም የእልከኞች ነች

 የኤርትራኖች አቅምም ያው ባድሜ ላይ ያያችሁት ነው። “Eritrea Licks its wounds” (quoted BBC Focus on Africa “ኤርትራ ቁስሏን አላምጣ ሳች” (ቢ ቢ ሲ) የሚለው ይደገማል።

ካልሆነ ሰላም ስለተፈለገ፤ መነሻውና ምክንያቱ ሳንዳስስሰላም’ በገዛ ፈቃዱ በነዚህ ወረበሎች ጊዜ ሊመጣ አይችልም።ሁለቱም ወረበሎች የሚሰጡት መልስ ለጦርነቱ መነሻ እና ለሰላም ጠንቅ በመሆኑ፤ ያለ ሕግ የተነጠቅነውን የኤርትራ መሬታችንና በባርነት የያዙትን ሕዝባችንን በድርድር ያስረክቡን *ሕዝቡ ኢትዮጰያን አልፈልግም ካለ እዛ ሊጨቀይ ከፈለገ ይጨቅይ *። ካልሆነ ጦርነቱ መቼም ቢሆን አይቀሬ ነው።

  ደርግን በሴራ አስወግደው ኤርትራን ሲገነጥሉ “ጦርነት አይቀሬ ነው” ብየ ጽፌ ተናግሬ ነበር (ብዙ ወገኖቼ ይህንን ይመሰክራሉ) እንዳልኩትም በ1989 በኢሳያስ ፀብ ጫሪነት ዘግናኝ ጦርነት ተደረገ። አሁንም ይደገማል~~~~!!!  ባንዳዎችም ሆኑ የተቀራችሁ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን ኢትዮጵያ አገራችን እንዴት እና ለምን እንደተበደለች ምክንያት አለኝ፤ ምክንያቴን አንብቡ።

         ኤርትራኖችና የ “ድንጋይ ዘመን ዳቦ” ምናባዊ ሕልም

 በዚህ-ጽሑፍ ሻዕቢና ወያኔዎች (ዛሬም አብይ አሕመድ) 27 አመት-መልስ ያጡበትና ያሳፈራቸው አንድ አጭር እና ግልጽ ጥያቄ እንመለከታለን። ድሮ በልጅነታችንእንእኒ” (ሲነበብ ይጥበቅ) የሚባል ዘመን ነበር ሲሉ ወላጆቻችን ያጫውቱናል።  እኛም ያንኑ ትረካ ተቀብለንዝናብ ሲዘንብጓደኛሞች የሆንን ሁሉ ሁሌም በምንጫወትበት ሞቃታ ስፍራ ሰብሰብ ብለን ተጠጋግተን በብርዱ ላለመጠቃት ተኮማትረን ተቃቅፈን  ስለዘመኑ እውነተኛነት በዓይናችን ያየን ይመስል የራሳችንን ቅጥያ ጨማምረን አጣፍጠን ከፊት ለፊታችን የሚታዩ የድንጋይ ኮረቶች ሁሉ የዛው ዘመን የአምቧሻ ቅሪት መሆኑን በእርግጠኝነት እናወራ ነበር። ዘመኑምዘመን እንእኒይባል ነበር።

 በዛ ዘመን ምን ነበር? ብለን ስንጠይቅ ድንጋዩ ሁሉ አምቧሻ ነበር ማረስ መዝራት፤ መውጣት መውረድ አያስፈልግም ነበር።ድንጋይ ሁሉ አምቧሻ የነበረበት የጥንት ዘመን ኤርትራኖችምድሪ ባሕሪነፃ ስትወጣ ወደዘመ እንእኒተመልሳ ድንጋዩ ሁሉ አምቧሻ ሆኖ አንደሚቀየር ለእናቷ ኢትዮጵያም ከሚትረፈረፈው አምቧሻዋ አንደምታጎርሳት ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸው “ኢሳያሰ አፈወረቂ  ዓለምሰገድ ተስፋይና ዶ/ር በረኸት ሃብተስላሴ  አማረ ተኽለ ጆርዳን  ወዘተ..  ያልቀባጠሩት ዲስኩር አልነበረም። መጨረሻ ድንጋዮችዋን እየላሰች እነሆ ዓለም አንፈልግም ያላቸው ያስወገዳቸው በተስቦ በሽታ የተጠቁ የአውስትራሊያ በሽተኛ በጎች ተቀበለች። ከበሮ የደለቀው ሕዝብም እየተቆጨ ተመልሶ ወደ ሰደባት ወደ እኛው አገር ለምኖ ተጠለለ፤ ግማሹም ወደ ሊቢያ ወደ ሞትና ስደት ተበተነ።

  የጦቦያ ጸሐፊ (ሙሉጌታ ሉሌ) ኤርትራ ገና ነፃ ትወጣ፤ድሮ በጥንት ጊዜ ራሴን ችዬኤርትራስባል የነበርኩኝአገርነኝ  ታዲያኢትዮጵያየምትባል ከኋላየ የተፈጠረች 60 አመት ዕድሜ ያላት አገር በጉልበት አጠቃልላኝ ነው እንጂ አገር ነበርኩኝ፤ አሁን ግን ነፃ አውጡኝ፡ እያለች እረፍት ስለነሳችን “እግዚአብሔር ሆይ!” ነፃነቷን ለመስጠት ተዘጋጅተናል እና ኤርትራ የምትባል አገር በፈጠርካት በዚች ዓለም-ምድር ተዘግባ ታውቃት ነበር? ብለው እግዚሐርን ሲጠይቁት ኤርትራ? ኤርትራ? ኤርትራ ደግሞ ማናት? ብሎ መዝገቡን ሲፈትሽ ማግኘት አልቻለም። አንዲህ የምትባል አገር አላውቅም! ምነው ጊዜን ባታባክኑብኝብሎ እግዚሓርም ራሱ ተገርሞ ነበር ይባላል።

እነሆ ኤርትራ ዛሬ ወደ 34 አመቷ ነው ነፃ ከወጣች። እገምጠዋለሁ ያለቺውየዘመ እንእኒ የዳቦ ቅዠት ድንጋይ ብቻ ሆኖባት ፈዝዛ ቀረች።

ኤርትራ ሁሉም ሞክራዋለች። ግድያ ዘር ማጥፋት ሕዝብን ወደ ባርነት መለወጥ ጥቁር ገባያ ሌብነት ስም ማጥፋት ውሸት ጉራ ከሕደት ፥ ወንጀል  ጦርነት ሽብር ፥ስደትና ዕብደት ሁሉንም ሞክራዋለች። ከዚህ ወዲያ የሚቀራት መደምደሚያዋ ወደ አመድነት መጓዝ ነው።ከዚያ ጣረ ሞት መዳን ከፈለገችየቀራት አማራጭኢትዮጵያዊነትዋንበቁርባንተቀብላ ከዘላለማዊው ቅዠት (ደሉዥን) እና ሞት መዳን ነው። ካልሆነ ግን እንደምታስታውሱት “የኢሳያስ ኤርትራ” ከባድመ ጦርነት በኋላ “እጅግ ከፍቷት ስለነበር የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት እንዲቃጠሉ የወሰነባቸው በሽታ የለከፋቸው የአውስትራሊያ በጎችን በምጽዋት ተመጽውታ መሳቂያና መሳለቂያ እንደሆነቺው ሁሉ በውንብድና የፖለቲካ በሽታ የተለከፈች መንር በመሆንዋ የመጨረሻ ዕድልዋመበላሸት ፥ ስደት ፥ ጦርነት ሞት ፥ውርደትይሆናል። በውንብድና እና በውሸት በዘር ፖለቲካ ተለክፈው ለሚሰቃዩ ኤርትራኖች እና የወያኔ ትግሬዎች ፈውስ አለን። ኢትዮጵያነት!! የተሰኘ መድሃኒት ያንን ከነችግሩ መቀበል ነው

ኢትዮጵያዊነት ለምን? የሚሉ የኢሳያስ አለቅላቂዎችና የትግራይ ወያኔዎች የታሪክ አተላዎች ክቡር ፕሮፌሰር አስራት የተናገሩትን ልጥስላችሁና ልሸጋገር።

... 1991 (...) “ቻርተርበተሰኘው ስብሰባ ላይ ሰማዕቱ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ቃላቸው እንዲመዘገብላቸው እንዲህ ሲሉ ተናገሩ

 “ይህ ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም የመወሰን የመተው ወይም የመሰረዝ ስልጣን የለውም ፡፡ ሆኖም አንድ ሰው በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የወቅታዊ ሁኔታ ሁኔታ ይገነዘባል ይህም በወንድማማቾች መካከል የደም ጠብ መቋረጡን እንዲሁም የአሁኑን የሰላም እና የዴሞክራሲን ፍጥነት ይጨምራል ፡፡ ኢሕአዴግና ሕዝባዊ ግምባርም በወንድማማች እና እህትማማች (በኢትዮጵያ-ኤርትራዊ) ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በአፋጣኝ ለመስራት የኢትዮጵያን እና የይቅርታ መንፈስ እንዲመጣ ለማድረግ ልዩ የቅርብ ግንኙነታቸውን ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡..” በማለት ጠቃሚ ምክርና ተቃውሞ አቅርበው ነበር።

ሆኖም ጀሮ ስላልነበረ፤ ፕሮፌሰሩ የሰጉትን ነገር ተፈጸመ የባድመ ጦርነት ተከሰተ። አሁንም የሚያምነን የለም። አንዴ በክሕደት የተቀረጸ ሕሊና ጩቤው እስኪነካው ድረስ አይነቃም።

አትዮጵያዊነት!!!” የዘላቂ ሰላም መፍቻውና ቁልፉ እሱ ብቻ ስለሆነ በዛው ፈውስ ተዳኙ ነው ያሉት። ይኼ ፈስ በትዕቢት ንቃችሁ ወርውራችሁት እንደወትሮው ዘላቂ ሰላም ሳይሆን ዘላቂ ጦርነት ብቻ ነው የሚከተለው እውን “ኢትዮጵያዊነት” እየተናቀ፤ ባንዳነት እየጎለበተ ሰላም የሚባለው የነ ሻዕቢያ እና ወያኔ እንዲሁም አዲሶቹ  ኦሮሞ ባንዳዎች የሚዋሹትየሰላም መንገድ አጭበርባሪዎች የቀየሱት የባንዳዎች መንገድ ስለሆነ ሕዝባችን ለሁለተኛ ጥፋት እንዳትራመድ እነዚህን በጠራ ዓይን እና ሕሊና መርምሩት።

ታሪክ አለን! ታሪካችን ባንዳዎችም ሆኑ የተባባሩት ግሳንግስ መንግስታት ማሕብር”  ሊጠመዝዙት አንፈቅድም። ቢሞም ምንም አያደርጉም የድምበር ተመራማሪው እንግሊዛዊው አስተያየት አድምጡ” ኢትዮጵያ ካልተስማማች ማንም ሃይል ሊያስገድዳት አይቻለውም ብሎ ነበር’አገር ወዳድ ወይንም ባንዳ የሚያስብለን ታሪካችን እና መልህቃችበጊዜአዊ አስቸጋሪ ማዕበል ስንለቅ ወይንም አጥብቀን ይዝ ብቻ በዚያው ስያሜ እንጠራለን ሁለታችን የሚለየን ታሪክ በማጉደፍ እና የጸዳውን ታሪክ አጥብቆ በመያዝ ያለው ልዩነት ነው።

የወላጆቻችን አደራ አናስበላም። አርበኞች ነበሩን፤ ታሪክና ታሪካቸው አለንታሪካችን እና ጭብጦቻችንም እነሆ አንብቡ። ኢትዮጵያ አለቀላት ብለው ከጠላቶች ጋር የሚደባለቁ ከሃዲዎችኢትዮጵያ እንዳላለቀች”  ዛሬም ነገም አለን! አለን! አለን! እንላቸዋለን።፡ታሪካችን እነሆ። መልካም ንባብ….

ጣሊያኖች ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ Ethiopia E Finita !!!! (ኢትዮጵያ አለቀላት) የሚል መፈክር የያዙ ትሬንታ ኳትሮዎች አዲስ አበባን ወርረዋት እንደነበር ጆን ስፔንሰር Unity and territorial integrity (የግዛት ውሁድነት) በሚለው መጽሐፉ ጠቅሰው እንደነበር አንድ የዛሬው የቅርብ ወዳጄ የሆኑ በጦቢያ መጽሄት ላይ ጠቅሰው ነበር። የተጠቀሰው መፈክር፤ ዛሬ ያለምን ጥርጥር ኤርትራ ካለ ኢትዮጵያ መኖር የማትችል በጉራ ብቻ የተነዳች፤ ኗሪዎቿ ወደ ኢትዮጵያና ወደ ሰሓራ የሚሰደዱባት ደካማ ገጠራማ አውራጃዎችን የያዘች ያለቀላት የተበላሸች መንደር ነች። ሰርጓም ሞትዋም 34 አመት ውስጥ ተጠናቀቀ። ዕጣ ፈንታዋነፃነት” (የኤርትራ ባርነት) ብላ የገለጸቺውን ነፃነቷንከአመዳም ሕይወት ለመውጣት’ ስትል እንደገና “እራስዋን መፈተሽአለባት።ለ34 አመት የተሰጣትየኦክሲጅን ስሊንደርአልቋል! ከዚያ ወዲያ መቀጠል full of difficulties/ ነው። ብልሽት! ነው የምለው ዛሬ አይደለም። ቆይቷል

ባንዳዎችዓሰብ! ዓሰብ! የሚሉ የአማራዎች ጥያቄ ነውየሚሉን ባንዳዎች ሁሉ ይተለጠፉት እነዚህ ካርታዎች እንዲያጤንዋቸው እንጠይቃቸዋለን

ሦስት ካርታዎችን እንመልት

 የሚከተሉት 3 ታሪካዊ የተለያዩ የኢትዮጵያ መልክአ ምድሮችን እንመለከታለን። ይህ መልክአ ምደር/ማፕ ነብሳቸው ይማር የሟቹ የፕሮፌሰር ንጉሳይ አየለ የምርምር ውጤቶች ስለሆኑ አስቀድሜ ለሳቸው ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በእነዚህ መልክዓ ምድሮች የምንመለከተው ቁም ነገር ጣሊያን ከአፄ  ምንሊክ ጋር ያደረገው የድምበር ውል በማፍረስ እራሱ ያዘጋጀው 1888 እስከ1928  ኢትዮጵያን ያዋሃደ የመጀመሪያው የኮሎኒ/የወረራ መልክዓ ምድር /ካርቶግራፊን እንመለከታለን። ከዚያ 5 አመት ግራ እና ቀኝ በጀግኖች እየተዋከ ቆይቶ 1933 . ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ ተባረረ።

ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ጣሊያን በሠራው ካርቶግራፊ እና እራሱ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ አንድ ግዛት መሆናቸውን የሰራውን እና ውሉን አፍርሶ የሰራውን መልክዓ ምድር ተከትለው ሕዝቡን በማማከር እና ከላይ ባስነበብኳችሁ የኤርትራ ጥያቄና ፍላጎት እሳቸውም ጠቅልለው ሕጋዊ መልክዓ መሬታቸውን እስከ 1966 . ድረስ አስተዳደሩ።

 ከዚያ ደረግ 1966 እስከ 1991 . ድረስ የተረከበውን ሕጋዊ መልክዓ ምድር ሲያስተዳድር ቆይቶ በዚያ 17 አመት ውስጥ ውስጣዊ የድምበር አስተዳዳር ለውጥ አደረጎ ዓሰብን እና ሌሎችን በራስ ገዝጀሪ መንደሪ’ (ሪዲሰትሪክቲንግ) ሕግ በመከተል አስተዳደሩ ወደ ወሎ አዛውሮታል።

 የመረብን ወንዝ ጥሼ ወደ ኢትዮጵያ ወደ ትግራይ ድምበር ከገባሁ በጣሊያን እና በምንልክ የተደረገው ዉል አይጸናም ብሎ የፈረመበትን ዉል ድምበር ጥሶ 1928 . ኢትዮጵያን ለሁለተኛ ጊዜ በሁለት አቅጣጫዎች ኢትዮጵያን ወርሮ የኮሎኒ አዲስ መልክዓ ምድር የሰራበትን ብቻ ሳይሆን፤ እኔ በሆነ ምክንያት ኤርትራን ለቅቄ ስወጣ፤ ኤርትራ ለሕጋዊ ባለቤቷ ለኢትዮጵያ አስረክባለሁ፡ ያለውን ዉል ሁሉ ማጤን ያስፈልጋል።

 ከአክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ እስከ ደርግ ጊዜ በወላጆቻቸው አስተዳዳር ሥር በአጥንታቸውና በደማቸው ተከብሮ የቆየው የባሕር ነጋሽ ምድር ዛሬራሳቸውንወያኔብለው የሚጠሩ ትግራይ ውስጥ የበቀሉ ባንዳዎቹ የኤርትራ ጉዳይ የኮሎኒ ጥያቄ ነው፡ በቅኝ ግዛት የያዘቻት ደግሞ ኢትዮጵያ ነች፡ ስለሆነም መለክዓ ምድሩን ለማካለል በኮሎኒ/በቅኝ ግዛት ደምብ እና ካርታ ተደራድረን ኤርትራን ጉዳይ እንፈታለን ያሉትንም ቢሆንየኮሎኒሕግም ቢሆን አልተከተሉም። አሁን አሁን ከአልጄሪስ ስምምነት ወዲህ ብዙ የወያኔ መሪዎች እና ደጋፊዎቻቸው የነበሩ ስምምነቱ የወያኔ መሪዎች እንጂ የሕዝብ ውሳኔ እንዳልነበረ ሁለት ያታወቁ የትግራይ ተወላጆች እንዲህ ይገልጹታል፡-

 “Before anything else, the people living in the region called “Eritrea” are, Tigreans. The idea of “Tigreans” and “Eritreans” as separate peoples, was never ours. See editorial (December 1993) Ethiopian Commentator, Haile Mariam Abebe.).

ሻዕቢያዎች እየነገሩን ያሉት ኤርትራ ነፃ የወጣቺው በሕግ ሳይሆን በጉልበታችን ነው። ብለዋል። በትግሬ ምሁራን የሚገለጸው እውነታው ግን እንዲህ ነው፦

“When the EPLF was pinned down by Mengistu’s army in Nakfa, the Tigrean fighters arrived for its rescue twice. During the “Red Star Campaign” of 1982, for instance, Tigreans fought in Nakfa on the Eritrean side, for nine months. Furthermore, without the supreme sacrifice of the Tigreans, the demand for Eritrean independence would have been little more than a bargaining chip for a negotiated settlement.”  (Alem Abbay (1993) “An Unappreciated Gift Horse in the Mouth”, The Ethiopian Times, March/April 1,No. 2) 

አለም ዓባይ ከላይ የነገረን፤ “….ሻዕቢያ በመንግስቱ (ኢትዮጵያ) ወታደር ናቕፋ ላይ ተገፍቶ ትንፋሽ አጥሮት ከተራሮቹ ግድግዳ ተጣብቆ ሞቱን ሲያጣጥር  የወያኔ ትግሬ ተዋጊዎች ወደ ናቕፎ ገስግሰው ቶሎ ደርሰውለት ከፍተኛ መስዋዕት ከፍለው ከደርግ ሃይለኛ ብትር ባያድኑት ኖሮ የሻዕቢያ መጨረሻ ዕድል ከኢትዮጵያ ጋር በደርድር ይቋጨው ነበር።እንዳለው ሁሉ እውነትም ሻዕቢያ ዓሰብን ለመስጠት ዝግጅነቱን ለደርግ መግለጹ ይታወሳል። እንደው ስብሐት ነጋ እንደነገረንም ሆነ ሌሎች መረጃዎች እንደሚያሳዩት “ኢሳያስ ዓሰብን ለመስጠት”ዝግጁ ሆኖ መንግሥቱ እምቢ ስላለ ጦርነቱ ቀጠል ነው የተባለው።

ወያኔዎች የኰሎኒ የግዛት ማፕ ብለው ወደ ዓለም መድረክ ለድርድር (ለሴረው) ሲቀርቡ ይዘውት የመጡት ማፕየኰሎያሊስትዋ ጣሊያን እንጂ” “የኰሎኒያሊስትዋ ኢትዮጵያአይደለም። ምክንያቱ ምንድ ነው? ቢባል፤ የመጨረሻዋ ኢትዮጵያ ኮሎኒያሊስት ነች ሲሉ የደሰኮሩበትን ሁለቱወንበዴዎችበግብር ለመተርጎም የኢትዮጵያን ኮሎኒያል ካርታ ይዘው ከሄዱ ከታች የሚታየው 3ኛው ካርታ ሕጋዊ ሊሆን ነው። ደግሞ ዓሰብን ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገባ መሆኑን በደምብ ስለሚያውቁ እና ስጋት ስላደረባቸው፤ በለመዱት ዓመጽ እና ቅጥፈት ከውጭ ኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተመካክረውኢትዮጵያየት ትደርሳለችኢትዮጵያን አምበርክከናታልስለዚህ የበሰበሰ ጣሊያን ማፕ ብቻ ይዘን አንቅረብ ብለው ኤርትራን አስገነጠሉ።

 በጣም የሚገርመው ደግሞ ከጣሊያን ካርታዎችም ቢሆን መርጠው (ፒክ ኤንድ ቹዝ) ነው ለግንጠላ የሚያመቻቸውን የበሰበሰውን የድሮ ማፕ የተጠቀሙበት።እንደነገርኳችሁ በማፕ የሚገዙ ቢሆኑ ኖሮ ጣሊያን የሰራው ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ያዋሃደው 1928 እስከ 1933 . የመጨረሻውን ውሉን አፍርሶ የሰራውን አዲሱን የጣሊን ቅኝ ማፕ ሊጠቀሙበት በቻሉ ነበር። ሆኖም ገብሩ አስራት በመጽሐፉ አንደገለጸው በባንዳው አመራር ውስጥ ከኤርትራኖች በላይ ኤርትራኖች ሆነው ኤርትራኖችን ለመጥቀም ከነሱ ጋር ወግነው አገራቸውን ኢትዮጵያ ፍትሕ በተጻረረ ሁኔታ ኤርትራን አስገንጥለው 90 ሚሊዮን ሕዝብ ያለ ባሕር ወደብ አስቀርተው በጠላት አንደትከበብ አድርገው የፈርንሳይ ጥገኛ የሆነቺውን ከጅቡቲ እና ስርዓት ከፈረሰባት (ፈይልድ ስቴት) ከሶማሊዋ የሐርጌሳ የወደብ ተከራይ ቴናንት/ጥገኛ አደርገዋታል።

ሦስቱ ካርታዎች ወያኔዎች ለኤርትራ ጥብቅና ቆመው የባሕር በር ለኢትዮጵያ ሲዘጉ፤ የተጠቀሙባቸው ቢስ የሆኑየፈረሱ የቅኝ ግዛት መከራከሪያ ውሎችብለው የሚሞጉቱባቸው በምኒልክ እና በጣሊያን ፋሺስት መካካል ተደረጉ የተባሉ ሦስቱ ዉሎች 1900/19002/1908(እኤአ) ውሎች ናቸው። እነዚህ ውሎች ዋጋ ቢስ ናቸው አንቀበላቸውም ብልን የምንሞግትባቸው ምክንያቶች በሚከተሉት ነጥቦች ምክንያቶች ነው። በቀላሉ አንዲገባችሁ ባጭሩ ላስረዳ፤-

1)    May, 1889 (ኤዘአ) ውጫሌ ውል እየተባለ የሚጠቀሰው ምኒሊክ ለመሳሪያ እና ለገንዘብ ልውጥ ኤርትራን ለጣሊያን ሸጧት የሚባለው ውል የያዘ እና ኢትዮጵያ የጣሊያን ቅኝ ነች የሚለው በጣሊያን ቋንቋ የተጻፈው ከአማርኛው ትርጉም እና ውል የሚጻረር በመሆኑ ምኒልክ ውሉ እንዲስተካከል በትዕግስት እየጠየቁ አንዲስተካከል ቢጠይቁም ጣሊያን አልለውጠውም በማለቱ ምንሊክ 1893 ( ) በግልጽ አወጁ፡ ዋጋ አንዴሌለው ለጣሊያን እና ለዓለም አስታወቁ። ጣሊያን ኢትዮጵያን ካልገዛሁ ብሎ 1888 ድምበር ጥሶ ( አቆጣጠር) ዓድዋ ላይ ጦርነት ከፍቶ ውርደቱን ተከናንቦ እጁን ሰጠ። ከዚያ በፊት የነበሩት ውሎች በሙሉ ፈረሱ።ለጊዜው ለሁለቱ ተዋጊዎች ደምበር ሆነው የሚያገለግሉ ሦስት ወንዞችን መረብ፤በለሳ እና ሙና እንደ ድምብር አጥር ሆነው ተወሰኑ።

2)  ምኒሊክ ሰራዊታቸው ይዘው ወደ ኤርትራ መዝለቁ ፤ጣሊያን ተዋጊ ትኩስ ሃይል፤ስንቅና መሳሪያ በባሕር እየተላከለት አንደሆነ እና በተጨማሪም እዚህ ለመጥቀስ የማያመቹ ሰፊ የሆኑ የመሃል፤የደቡብ እና የምስራቅ ኢትዮጵያ ግዛት ክፍሎች ዝርዝር ትንተናዎች የሚሹ ሰፋፊ ያልተጠቀሱ ምክንያቶችም ጭምር ጦርነቱን መግፋት አደጋ አንዳለው በመገመታቸው ሰራዊታቸው ከድሉ በሗላ በደስታ ወደ እየ መንደራችን አንመለሳለን ብሎ መፍረስ በመጀመሩ እና በከብትና በሰውሕይወት ረሃብ እና በሽታ ትግራይ ውስጥ ግብቶ ብዙ ሰው ስላለቀ (የስንቅ ችግር) እና በመሳሰሉ ሁኔታው አመች ስላልነበረ ኤርትራ በጣሊያን እጅ ልትቆይ ወሰኑ። ይህንን ማስረጃ ባለፈው ሰሞን ጥቅሻለሁ።

ጣሊያን ኤርትራ ሲቆይ ከተሰማማባቸው ድም እንዳያልፍ ተፈራረመ። ኤርትራ ለቆ ሲወጣምኤርትራለባለቤቷ ለኢትዮጵያ አንደምታስረክብ 1896 እና 1900 (ኤአ) ውል ገባ። ኤርትራ ለማንም መንግሰት/ሃይል/ተዋዋይ አሳልፋ ለመስጠት ወይንም መሸጥ አንደማትችል ፈርማለች። (በሗላ ቃሉን አጥፎ ኤርትራ ለእንግሊዝ ሰጥቶ ወጣ፤ ወይንም አንግሊዝ በጉል ነጠቀች)

የተጠቀሱት ስመምነቶች አስመልክተው አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩት ታላቁ የታሪክ ምሁር / ሃይሌ ላሬቦ እንዲህ ይላሉ።

 

 “It should be emphasized that the treaties of 1902 and 1908 under which Eritrea claims the disputed territories are essentially flawed. These territories belong indisputably to Ethiopia and until Italy, in its attempt to provoke another war with Ethiopia annexed them in 1929 by force, they were administered by Ethiopia. What makes even more difficult the settlement of conflict between the two countries according to the colonial treaties is the fact that the geographical map of Eritrea has constantly changed during and after those treaties as the following instances highlight:

Even under Italian rule, considerable part of Eritrea was under the sovereignty of Ethiopia. This includes the huge expanse of land under the control of Dabre Bizen and its dependencies (daughter monasteries) that were directly administered by the imperial Ethiopian government. If Eritrea insists that the border should be marked according to the above-mentioned colonial treaties, it is within Ethiopia's power to claim back these territories and those forcibly annexed by Zolli in 1928 and 1929. In both ways, Eritrea is bound to lose substantial mass of its land. Moreover, the control of Dabre Bizen and its dependencies will give Ethiopia a safe gateway to the important port of Massawa. Understandably, this will have serious consequences for Eritrea as an independent state.

ጣሊያን ኤርትራን እያስተዳደራት እያለም ቢሆን ኤርትራ ውስጥ የሚገኘው ደብረቢዘን ገዳም ሳይቀር በኢትዮጵያ ኣስተዳደርና ንብረት ነበር (በውጫሌ ውስጥ ተጠቅሷል)

http://www.ethiopianreview.com/2001/Article_HaileMLareboAPRJUN_2001.html

3)   ጣሊያን ለሁለተኛ ጊዜ አልደፍርም ያለበትን የድምበር ውል እንደገና ጥሶ በመረብ እና በኦጋዴን ገብቶ 1928 (ኢዘአ) ኢትዮጵያን ወረረ። 5 አመት ሲዋከብ ቆይቶ ተሸንፎ ወጣ። ከዚህ በፊት የነበሩ ውሎች ሁሉ ፈረሱ።

4)  ከዚያ በኋላ በእንግሊዝ ተንኮል ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መዋሃድ ሲኖርባት ከሃያላኑ አንዱ በመኖሩ ኤርትራን እና ትግራይን ገንጥሎ ለማስተዳዳር እንዲመቸው ፍላጎት ስላደረበት  ኤርትራ ውስጥ እቆያለሁ ብሎ ተንኮል ሰራ። በዚህ ጭቅጭቅ ተነሳ። ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት በኋላ 4 ሐያላን መንግስታት ሲባሉ የነበሩት የመሰረቱት የኤርትራ እና ኢትዮጵያ ጉዳይ መርማሪ አካል በደረሰበት ጥናት መሰረት፤ የተባበሩት መንግሥታት ማሕበር ጉባኤ ኤርትራ በንጉሡ የዘውድ አስተዳደር ሥር ሆና የራስ ገዝመብት ተሰጥቷት 10 አመት ከቆየች በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ትዋሃድ ብሎ ውሳኔ ሰጠ። 1900/1902/1908 የነበሩ ዉሎች እንደገናለሦስተኛ ጊዜበዚህ ባዲሱ ሕይወት እና አስተዳደራዊ ለውጥ ተሻረ

5)  1944 . (ኢዘ ) ኤርትራ እላይ እንደተመለከታችሁት መሰረት በሕዝቡ ተወካዮች ኤርትራ ከኢትዮጵያ ሙሉ ውሕደት አደረገች። በዚህ ለአራተኛ ጊዜ የቆዩ ዉሎች በሙሉ ፈረሱ።

6)  ዓሰብ ከዋነኛው የኤርትራ ማሕበረሰብ 400 .ሜትር ርቀት ርቃ ትገኛለች። ለብዙ አመታት መላትም እስከ ደርግ ፍጻሜ ድረስ ከኤርትራ ይልቅ ምጣኔ ሐብታዊ (ንግድ) እና ማሕበራዊ ግንኙነት ከኤርትራ ይልቅ ከኢትዮጵያ ጋር ነበር። ዓሰብ ለደሴ 70/ ትርቃለች። የወደብ መጠቀሙ መብት እና ሂሳቡን በሕግ ምረኩዝ ስታሰሉትወያኔዎችባሕር ወደብ ለኛ መከልከላቸው ትግራይ ትግርኚ መደብ ሊጠብቁት የፈለጉት ሴራ አለ (ዓሰብ ወደብና አካባቢ አስቀድመው ወደ ትግሬ አጠቃልለውት እንደነበር በረሃ ውስጥ ያዘጋጁት ካርታ ይመሰክራል) ወይንም በሥልጣን ያሉ ትግሬዎች ወደ ኤርትራ የሚያደሉት፤ ሙሉ በሙሉ ወይንም የሁለት ደም ዲቃላዎች ሆነው ይበልጥ ለኤርትራ በማዳላታቸው ነው። ከሁለቱ አንዱ። 

7)   ወያኔዎች አልጀሪስ ሄደው ባቋቋሙት ፈራጅ አካል 1902/1905/1908/ ጠሊያን የሰራው ካርታ እና ስምምነት አንፈረዳለን ሲሉ በሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔይግባኝማለት እንደማይቻል የተፈራረሙበት ምክንያትም ከዚያ በኋላ የተሰሩ ካርታዎች እና ውሎች ካቀረቡይዘውት የሄዱት ውሉየበሰበሰ፤የማይሰራ መሆኑን አስቀድመው ስላወቁ፤ይግባኝየሚያግድ ስምምነት ሆን ብለው መፈራረማቸውለ፤ግልፅ ሴራ መሆኑን ያሳየናል ለወደፊቱም በሕጉ መሰረትአንድ የመንግስት ተወካይ/አካል/ ሆን ብሎ የአገሩን ጥቅም የሚጎዳ ስምምነት ከፈረመ ስምምነቱ እንደገና እንደሚመረመር የተባበሩት /ሕግ ይጠቅሳል። አለቅላቂ ባንዳ ኢትዮጰያዊያኖች ግን ይህንን አያነሱም።

ፕሮፈሰር / ሃይሌ ላሬቦ ንዳሉት

  1. “…the time gap that exists between these treaties and the Eritrean independence is so vast, and the change in status that Eritrea underwent during this same period is so intricate as to make any appeal to colonial treaties and OAU charter of no use beyond political gimmickry.”
  2.      አሁን፤ ለማስረጃ ያቀረብኳቸው 3 የተለያዩ መልክዓ ምድሮችን እነሆ ተመልከቱ::
  3.   ኢትዮጵያ የቅኝ ገዢ ነበረች “ከተባለ” በ1964 የካይሮ አፍሪካ ውል መሠረት በማድረግ ኤርትራ “የመጨረሻዋ” የቅኝ ገዢዋ የአሰመረችላትን የመልክኣ መሬት አስተዳደር ይዛ መገንጠል ነበረባት። ሆኖም የወያኔ ትግሬዎች ኢትዮጵያን ለመጉዳት በሕግ የተጣሰውን የኢጣሊያ ቅኝ ገዢ መስምርን  በመጠቀም በሴራ እንዴት እንደጐዱን ተመልከቱ። ለዚህም ነው  በሴራ የተፈጸመ ውል ነው ስለዚም አንቀበልም የምልበት ምክንያት።ይኼው ተመልከቱ። ካርታውን በትልቁ ለማየት በኪ-ቦርዳችሁ ላይ Ctr + የሚለውን ሁለቱን ቁልፎች አብሮ መጫን ነው።

እንደገና ልድገመው፡ በዚህ መረጃ መሰረት ኮሎኒዎች ነን ከተባልን የመጨረሻው የኮሎኒካርታ” የቀረጸው እና የመጨረሻው ኮሎኒያሊስት ማን ነው? የሚለው ጥያቄ እናቅርብ። ኢትዮጵያ የቅኝ ገዥ ባዕድ ነች በለውናል። በኮሎኒያሊሰት ካርታ/ማፕ እንዳኛለን ካሉ እኛ የሰጠናቸውን የመጨረሻዎቹ ቅኝ ገዢዎች የምንባለው የሰራንላቸው የኮሎኒ ማፕ ለምን ይዘው ለድርድሩ አልተጠቀሙበትም? 1964 የካይሮ ውሳኔም ተገንጣዩ የመጨረሻው ቅኝ ገዢ የሰጠው መሬት/ቅርጽ ይዞ ይሄዳል ይላል። መጨረሻ ቅኝ ብለው ወያኔዎች የሰየሙንም እኛ ከሆንን፤ ኢትዮጵያዊያን ቢሆኑ ኖሮ የኛን ካርታ ይዘው መከራከር ነበረባቸው። መልስ የሚያሻው ጥያቄ ነው።

ባንዳዎቹ በእውነተኛ ክርክር ጎሮራቸው ስለታነቁ ለዚህ ጥያቄ እስካሁን ድረስ መልስ ሲሰጡበት የሰማነው መልሳቸውኢትዮጵያ ያለ ወደብ 27 አመት ኖራለች ስለዚህ አያስፈልገንምወይንም በስብሐት ነጋ መልስ መሰረትዓሰብ ሳይሆን ጅቡቲ ነው ለኛ ለኢትዮጵያ የሚረባው” (ዓሰብን አትጠይቁ ወደ ትግራይ- ለትግራይ ትግርኛ መርሃ ግብሩ ስለሚጠቃለል ማለቱ ነው)። ወያኔዓሰብበትግራይ ክልል ያካተተ ካርታ ሰርቶ እንደነበረም ታውቃላችሁ):: ኤርትራኖችም ሆኑ የወያኔ ትግሬዎች  ለጥያቄአችን ቀጥተኛ መልስ ሊመለሱልን አልቻሉም።

27 አመት ያለወደብ ከጅቡቲ፤ከሶማሊ ወደብ እየተከራዬን ኑረናል፤ ስለዚህ ያለ ወደብ መኖር ይቻላል፤ የሚለውመልስ ሲያጡ የሚመልሱት መልስ ነው። ለነገሩ ኑሮ አይባልም እንጂ ኤርትራም  እኮ 34 አመት ወደቧ ባዶ ሆኖ ኖራለች። ጥያቄአችን አጭር፤ቀጥተኛና ግልጽ ነው!!!  34 አመት ዳክረው መልስ ያጡበት ጥያቄ አሁንም እንዲመልሱልን እንጠይቃቸዋለን።

ኤርትራ የደፈረሰች፤ ያለቀላት፤ የተበላሸች መንደር ጉራዋን እና ዕብደቷን ካላቆመች መጪው ዘመን የኢትዮጵያውያን ብርቱ ክንድ እየጠበቃት ነው። ምርጫው የራሷ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

No comments: