Wednesday, August 20, 2025

እግዚዞ! እግዚዞ! ምኒሊክ እንኳን ተወለድክ ዛሬ በልደትህ ቀን ከትግሬዎችና ከኤርትራኖች ክስ ነፃ ወጣህ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 8/20/2025

 

እግዚዞ! እግዚዞ! ምኒሊክ እንኳን ተወለድክ ዛሬ በልደትህ ቀን ከትግሬዎችና ከኤርትራኖች ክስ ነፃ ወጣህ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

8/20/2025

ኤርትራኖችንና ትግሬዎችን ያጋለጠ ምንሊክን ነፃ የሚያወጣ አዲስ መረጃ ወጣ! እንነጋገርበታለን። EMS በሚል የሚጠራ የሻዕቢያ ፍቅር ያልለቀቃቸው ሰዎች የሚያዘጋጁት ፤ አፍቃሬ ኢሳያስ የነበረው “ኢሳትን” የተካ የዩቱብ ቲቪ እና እንዲሁም ኢሳት በነበረቺበት የብርሃኑ ነጋ እና የሻዕቢያ ቱሪናፋ የነበረች “መታሰቢያ ቀጸላ” በምታዘጋጀው “ምናለሽ መቲ” በተባለ YoutTub ቲ ቪ የሚለቀቅ “An African People’s Quest for Freedom and Justice a Political History of Eritrea, 1941–1962 Alemseged Tesfai የሚል መጽሐፍ ጽፎ “በግምገማ ስም” በኛዎቹ በአንዳንዶቹ ባንዳ ምሁራን ምስጋና እንዲቸረው ከላይ በተጠቀሱት አለቅላቂ ሚዲያዎች ደራሲው በተገኘበት ቀርቦ የታሪክ ቅጥፈትና ውሸት እየቀላቀለ ቀምሞ የጻፈውን መጽሐፍን እንዲሰራጭለትና በሚያስደነግጥ መልክም ምስጋና ሲቸረውም ሰምተናል። ያንን ለማድመጥ  EMS Special የኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያን የጋራ ዉይይት Sat 02 Aug 2025 ብላችሁ ጉጉል ላይ ኮፒ ፔስት በታደርጉት ቪዲዮውን ታዩታላችሁ።

 አለምሰገድ ተስፋይ ማለት ገና በ12 አመቱ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አክብራ ተንከባክባ እርሱና ቤተሰቦቹን በነጻ መግባ ከፈተኛ ትምህርት እንዲገበዩ ያሰተማረቺውን “ጡት ነካሾች” ከሆኑት  ኢትዮጵያን ከከዱ  ካሓዲ ባንዳዎች ውስጥ አንዱ ነው። ስለዚሀ ሰው ማንነት በሰፊወ በሌላ ጊዜ የምመልሰበት ሰልሆነ ላሁኑ ግን  አለምሰገድ ተሰፋይ ማለት ወንጀለኛውን የሻዕቢያን መሪ በማገልገል በደም የተጨማለቀውን እጅግ ዘግናኝ የሆነ ጨፍጫፊና ወንጀለኛው የኢሳያስ አፈወርቂን መሪነት  የተቀበለ ፤ ኢሳያስ ቢሞትም ሥርዓቱን ለማስቀጠልና ለማገልገል ዝግጁ ከሆኑት ለታሪክ ውርደት ራሳቸውን ያጋለጡ ፤ በጣት ከሚቆጠሩት በህይወት ካሉት “አጎምባሽ የኤርትራ” ምሁራን አንዱ  አለምሰገድ ተስፋይ ነው።

የግምገማው መድረክ የመራው ደግሞ ንአምን ዘለቀ የተባለው የግንቦት 7 አመራር አባል የነበረ አሁንም የሻዕቢያን ፍቅር ያልተላቀቀው፤ “የኢትዮጵያ አንድነት ብቻ ሲባል (ያንቀኛል) ‘ሰፎኬት’ ያደርገኛል” በማለት የሚታወቀው ፤ ”ቪዥን ኢትዮጵያ” የሚል ጸረ አምሐራ የሆነ (ካሁን በፊት ያቀረብኩትን መረጃ ይመልከቱ) ድርጅት ከሚመሩት የምሁራን ስብስብ አንዱ ንአምን ዘለቀ-ነው።

“ቪዥን ኢትዮጵያ” ማለት አንድ ጸሐፊ እንዳሉት  

“ቪዥን ኢትዮጵያ” የሚባለው እንኳንስ “ቪዥን” ይቅርና ጭላንጭል ብርሃን የሌለበት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የተዋጠ የማየጨበጥ የተስፈኞች መድረክ ነው። ካዝጋጆቹ አንዱ ንአምን ዘለቀ የኢትዮጵያ አንድነት ሲባል የሚያንቀው ወይም የሚያፍነው “ሰፎኬት የሚያደርገው” ነገር ግልጽ ነው። ነአምን ዘለቀ በተለይም ኤርትራ ሄዶ ተጣብቶት የመጣው የኢትዮጵያ ጥላቻ ሆዱን ነፍቶት እያንዘፈዘፈውና እያንቀጠቀጠው ስለሆነ ነው የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ አንድነት ሲባል የሚያንቀው ወይም የሚያፍነው “ሰፎኬት የሚያደርገው።” ሲሉ የገለጹት ሰው ነው ንአምን ዘለቀ ማለት።

ስለ ግምገማ ተሳታፊዎቹ አገማገም ራሱን በቻለ ትችት እመለሳለሁ፤ እስከዛው ግን በርዕሱ ላይ የተጠቀሰው ደራሲው የነገረን አዲስ ነገር እና በለጠፍኩት ቪዲዮ ውስጥ ኢሳያስም ያረጋገጠው ጉዳይ እንመልከት።

ቪዲዮው ያየሁት ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን facebook ላይ ለጥፎ በተቸበት ጉዳይ ነው። ሠዓሊ አምሳሉ ደራሲውን በተቸበት ላይ እንዲህ የሚል ይገኝበታል፤

“ከውይይቱ ዶ/ር ዓለምሰገድ ተስፋይ ከተባለ የትግል ታሪካቸውን በመጽሐፍ ከጻፈ ኤርትራዊ የሰማሁት ነገር ብዙዎቻችን የማናውቀውና በጣም የገረመኝ ነገር ነበር። እሱም ምንድን ነው፤ ለካ ጣሊያን በኋላ ላይ ኤርትራ ብላ የሠየመችውን ባሕረ ምድር ተብሎ ይጠራ የነበረውን የሀገራችንን ክፍል ወራ እንድትይዝና ቅኝ እንድትገዛ ያገደረጓት እራሳቸው የባሕረ ምድር የየጎጡ ገዥዎችና ሕዝቡ ምጽዋ ወደብ ላይ ተንጠልጥላ የነበረችውን ጣሊያንን ጥበቃሽን (protection) እንፈልጋለን ብለው በመለመንና በመወትወት ነበር ለካ ጣሊያን ከምጽዋ ወጥታ እስከ መረብ ድረስ መሬታችንን እንድትወርና ከዚያም ቀጥቅጣ ቅኝ ልትገዛቸው የቻለችው ለካ‼️

📌 አብዛኞቻችን የምናስበው ግን ጣሊያን ሀገራችንን ቅኝ ለመግዛት በማሰብ መጀመሪያ አሰብን ከአንድ የአፋር ባላባት ገዝቶት ከነበረው ከአንድ የካቶሊክ ቄስ እጅ አሰብን በመግዛትና እግሯን በመትከል፣ ቀጥላም ምጽዋን ከእንግሊዝ እጅ በስጦታ በመቀበል እግሯን በሀገራችን መሬት ላይ እያንሰራፋች በመምጣት እስከመረብ ድረስ እየተስፋፋች በመምጣት ጣሊያን ይሄንን በምታደርግበት ወቅት ንጉሥ የነበሩት ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ጣሊያንን ሳያስለቅቋት ቀርተው ዕዳውን ለዐፄ ምኒልክ ትተው በመሞታቸው ዐፄ ምኒልክም ጣሊያንን ከሀገራችን ጠራርጎ ለማስወጣት ቆርጠው የኢትዮጵያን ሕዝብ አነቃንቀው ዘመቱ፣ የአድዋው ጦርነት ከመደረጉ በፊት ግን ሠራዊቱ ስንቅ ጨረሰ፣ ከአካባቢው ሕዝብ ስንቅ ለመግዛት ተሞከረ ነገር ግን ትግሬ አድሞ በግዥ እንኳ እህል ለሠራዊቱ ሊሰጥ ሳይችል ቀረ፣ የሠራዊቱ መራብ እየጠና በሔደበት ሁኔታ ላይ እያለ ነበር የአድዋው ጦርነት ተደርጎ በእግዚአብሔር ረድኤት ጣሊያንን አድዋ ላይ ድል ለመምታት የተቻለው። ያም ሆኖ የስንቅና ትጥቅ ችግሩ የሚያላውስ ስላልነበረ ሠራዊቱ በዚህ ችግር ምክንያት ለመመለስ በመገደዱ ጦርነቱን መግፋትና ጣሊያንን ይዛብን ከቆየችው ባሕረ ምድር (ኤርትራ) ከተባለው የሀገራችን ክፍልም ማስወጣት ሳይቻል ቀረ ለሌላ ጊዜ ቀጠሮ በመያዝ ሠራዊቱ ተመለሰ። የምናውቀው ታሪክ ይሄ ነበር። ለካ መጀመሪያ ቱርኮች በኋላም ግብጾች ከቱርኮች ተቀብለው ለምዕት ዓመታት ከወደቡ ሳያልፉ የምጽዋን ወደብ ተቆጣጥረው እንደቆዩት ሁሉ ጣሊያንም የምጽዋንና የአሰብን ወደቦች ከመያዝ የዘለለ ፍላጎትና ዓላማ አልነበራትም ነበረ ለካ። ባርነት ወይም ቅኝ መገዛት ኩራት፣ ክብርና ሥልጣኔ የሚመስላቸው ባርነት ናፋቂዎቹ የባሕረ ምድር ሰዎች ናቸው ለካ ከኢትዮጵያ ለመነጠልና ቅኝ ተገዥ ወይም ባሪያ ለመሆን በመፈለግ ጣሊያንን "ከኢትዮጵያ መንግሥት እንድትጠብቂን እንፈልጋለን፣ ጥበቃሽን እንሻለን እንማፀናለንም!" ብለው ጠርተውና ወትውተው ያንን የሀገራችንን ክፍል ቅኝ እንድትገዛው ያደረጓት ለካ። በጣም የሚገርም ነገር ነው‼️

🤔 እጅግ በጣም አስገራሚው ነገር ደግሞ አበው "ዶሮ ጭራ መታረጃዋን አወጣች!" እንዲሉ ወይም "አህያ አናፍታ ጅብን ጠራች!" እንዲሉ ኤርትራውያኑ እንዲህ አድርገው በገዛ እጃቸው ከጠላት ጋር ተመሳጥረውና ተሞዳምደው ለቅኝ ግዛት ተዳርገው ሲያበቁ በአድዋ ጦርነት ጊዜ ዐፄ ምኒልክ ሠራዊታቸው ስንቅና ትጥቅ ስለጨረሰና ለረሃብ በመዳረጉ ምክንያት በጦርነቱ መግፋትና ጣሊያንን ባሕረ ምድር (ኤርትራ) ይባል ከነበረው የሀገራችን ክፍልም ማስወጣት ሳይችሉ ለመቅረት በመገደዳቸው ጣሊያንን ከባሕረ ምድርም ሳያስወጡት ስለቀሩ ኤርትራውያኑ "ምኒልክ መረብን ተሻግሮ ጣሊያንን ከኤርትራም በማስወገድ እኛንም ነጻ ሊያወጣን ሲገባ ነፃ ሳያወጣን ቀርቷል፣ ለጣሊያን ሸጦናል!" እያሉ ዐፄ ምኒልክን ለመውቀስና blame shift ለማድረግ መላ ዘመናቸውን ሲያላዝኑ መኖራቸው በጣም የሚገርም ነገር ነው የሆነብኝ

በማለት በግሩም ምት መትቶ እሰከዛሬ ድረስ ኤርትራዊያኖቹና ትግሬዎቹ አፄ ምኒልክን ሲከሱበት የነበረውን የራሳቸው ገመና ደብቀው ለዘመናት እንደያዙት አሳይቶናል።

የኢሳያስ አሽከር አለምሰገድ ተስፋይ ከላይ እንዳነበባችሁት ከታች የምንመለከተው እራሱ ደራሲውንም ያሰገረመውና ኤርትራኖች ጣሊያንን ከምፅዋ ጎትተው ወደ ደጋው ኤርትራ እንዲመጣ ለምን እንዳደረጉ ብሎ የጠየቀውን ጥያቄ ራሱም እንዳልገባውና መልስ እንደሌለው-ይገልጻል።

እንዲህ ይላል፤

« ኤርትራ ከዘመነ አክሱም ጀምሮ የኢትዮጵያ አካል ነበረች የሚለው የ3 ሺሕ አመት ታሪክ “ሚስ” (ቅዥታዊ ምናብ) ነው እኛ አንቀበለውም። ለምሳሌ ጣሊያን መረብ ምላሽ ብቻ የያዘው? ለምንድነው የመረብ ምላሽ ሕዝብና መሪዎቹ ጣሊያን ወደ ማሳዋ ሲመጣ ለምን የጣሊያን “ፐሮተክሽን”(ከለላ) ጠየቁ? ጣሊያን እኮ ከመፅዋ ወደ ደጋማው ኤርትራ እንዲመጣ ኤርትራዊያነ ራሳቸው ናቸው አጅበው በእነ ብላታ ባራኺ (ራስ ባራኺ) በእነ ባህታ ሐጎስ የመሳሰሉ ታላላቅ መሪዎችና ባላባቶች ጥሪ ታጀቦ ነው ወደ መሃል ደጋማው ኤርትራ እንዲመጣ የተደረገው። ለምን (ኤርትራኖቹ ጣሊያን እንዲገዛቸው ጎትተው አመጡት)? ለምን እስክ ሰንዓፈ ድረስ ያለው ሕዝብ ድምበር ተበጅቶለት ኤርትኖቹ ለምን የጣሊያን ጥበቃ መረጡ? ለምን “ዓዲኻላ” የጣሊያን “ፐሮተክሽን” ከለላ ጠየቀ? ለምን የዓድዋ ሕዝብ የጣሊያን ከለላ አልጠየቀም? የሚለው ለኔም አልገባኝም። ይህ እራሱ የቻለ “food for thought” (ሕሊናን የሚጭር፤ሊታሰብበት የሚገባ ነገር ነው። (ማለቱ ነው እንግሊዝኛው ቃል ደራሲው የተጠቀመበት foof for thought ሲል)።

እንዲህ የላል አቶ ዓለምሰገድ ተስፋይ

I have not myself reach to any conclusion on what exactly happened on that time, I am not expert of that period of Eritrean and Ethiopian history. But, it incumbent upon us (it is our duty or obligation to do something) to what exactly happened at that time? እዛ የነበሩ መሪዎችና ሕዝብ የጣሊያን “ፐሮተክሽ” ከለላ የጠየቁበት ምክንያት ምንድ ነው? የሚለው አጽንኦት ለመስጠት ነው ትኩረቴ።

እንግዚዝኛው ትርጉም

“በዚያን ጊዜ በትክክል ስለተፈጠረው ነገር ለራሴ አልገባኝም። በክስተቱ ምንም መደምደሚያ የለኝም፣ የዚያን ወቅት የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ታሪክ አዋቂ አይደለሁም። ነገር ግን፣ በዚያን ጊዜ ለተፈጸመው ነገር በእኛ ላይ ዱብ ዕዳ ሆኖ የወደቀ ለወድፊቱ እንድንመራመርበትና እንድናተኩርበት የሚያስገድደን ክስተት ነው።” ይላል።

እንግዲህ አለምሰገድ የነገረን አዲስ ምስጢር፤ እኛ የዋሆቹ ኢትዮጰያዊያን ጣሊያን ከመፅዋ ወደ ደጋማው ኤርትራ ሲመጣ እራሱ ጣሊያን የመጣ መስሎን ነበር ሲነገርን የነበረው። አሁን ግን ጣሊያን ወደ መረብ ምላሽ እንዲመጣ ኤርትራዊያን ራሳቸው “አጅበው በብር” በእነ ብላታ ባራኺ (ራስ ባራኺ) እና በእነ ባህታ ሐጎስ የመሳሰሉ ተላላቅ መሪዎችና ባላባቶች ጥሪ ታጀቦ ነው ወደ መሃል ደጋማው ኤርትራ እንዲመጣ የተደረገው። እግዚዞ!!  እግዚዞ!! ምኒሊክ እንኳን ተወለድክ ዛሬ በልደትህ ቀን ከትግሬዎችና ከኤርትራኖች ክስ ነፃ ወጣህ!!!!   

ሁላችሁም እንደምታውቁት ከትግሬዎችና ከኤርትራኖች ሲቀርብ የነበረው አሰልቺና መሠረተ-ቢስ ክስ "አፄ ምንሊክ በዓድዋ የጣሊያን ጦርነት ወቅት ነጉሡ ጣሊያንን ቢያሸንፉም “ኤርትራ” ድረስ ዘልቀው ጣሊያንን መምታትና ማባረር እየቻሉ የሁለቱ ትግሬዎች  አንድነት ለሥልጣናቸው አስጊ ሆነው ሰላዩዋቸው ፤ አንድ አካል አንድ አምሳል የነበሩት ሁለቱንም ትግሬዎች ንጉሡ ሆን ብለው እኛን ለማዳከም ለሁለት ተከፍለን ተነጣጥለን እንድንኖር ከጣሊያን ጋር ውል ፈጽመው እነሆ ነጠሉን”። እያሉ ሲከሱዋቸው እንደነበር የታወሳል።

ሆኖም ንጉሡ መረብን ተሻግረው ጣሊያንን እንዳያባርሩ ያገዷቸው ሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ነበሩ። አንደኛው ዛሬ ከላይ የተመለከታቸሁት ዓለምሰገድ ተሰፋይ ያወጣው በጣሊያን መገዛት የኤርትራኖቹ ፈላጎት የነጉሡ ስጋት መኖሩን ከላይ ያየነው አዲስ መረጃ  ሲሆን ፤ ሁለተኛው ደግሞ Augustus Blandy Wylde  የተባለ የእንግሊዝ ማንቸስተር ጋዜጣ ጋዜጠኛ የነበረ ትግራይ ውሰጥ ሲኖር የራስ ዓሉላ የቅርብ ወዳጅ የነበረ፤ እነ ራስ መኮንን እና ራሰ ዓሉላና የምሳስሉ የወቀቱ ጦር መሪዎችን ሰለ ጦርነቱ ቃለመጠይቅ ያደረገላቸው፤ ሰለ የዓድዋ ጦርነት የመረጃ ቀረቤታ የነበረው እና ምን እንደተከናወነ የሚያውቅ ታላቅ ጋዜጠኛ የነበረው ይህ ዘጋቢ የሚለን ነገር፤- ነጉሡ መረብ ተሻግረው ጣሊያን ሊመቱ ያላስቻላቸው ነገር ምክንያት የነግረናል።

እንዲህ ሲል

 “The food supplies taken from the Italians enabled king Menelik to remain a few days longer in Adowa. Most of his soldiers however were hard pressed for food and many of them were sent off south at once….. (p.214 Modern Abyssinia by Augustus B. Wylde 1901)

"የዘውት የመጡት ስንቅ በማለቁ ‘ ከጣሊያኖች የተወሰዱት የምግብ አቅርቦቶች በመጠቀም ንጉስ ምኒልክ በዓድዋ ውስጥ ለጥቂት ቀናት እንዲቆዩ አስችሏቸዋል. ነገር ግን አብዛኛዎቹ ወታደሮቻቸው ምግብ ዕጦት በጣም ተቸግረው ነበር እና ብዙዎቹም በአንድ ጊዜ ወደ ደቡብ አቅጣጫ በመጉረፍ ወደ እየ አገራቸው አቀኑ… (p.214 Modern Abyssinia by Augustus B. Wylde 1901) የላል።

በመቀጠልም፤

ጉሥ ምኒልክን ፍጹም ድሉን ተከትሎ ወደ ርትራ ማቅናት የከለከለው ብቸኛው ነገር እጅግ ብዛት የነበረው ሠራዊቱን እና በርካታ የካምፑ ተከታዮችን ለመመገብ የሚያስፈልጉትን የምግብ አቅርቦት በቀላሉ ማግኘት ስለማይቻል ወደ ኤርትራ ለማቅናት ኪሳራ እንደሚያስከትልበት በመገምቱ በስንቅ እጦት ምክንያት መቀጠል አልቻለም።(p.212 Modern Abyssinia by Augustus B. Wylde 1901)

ንጉሡ መረብ ሊሻገሩ ያለፈለጉበት ምክንያት ትግሬዎችን ለሁለት ለመክፈል ሳይሆን (Augustus B. Wylde) ዋይልደ የታዘበውን የዓይን መስክርነቱና ያረጋገጠውን ነው የንጉሡ ምክንያት ላለመሻገር አንዱ ምክንያታቸው።  

ዋይልደ በመቀጠል እንዲህ ይላል፦ 

ዓሉላ ብቻውን ከነሠራዊቱ ወደ መረብ ቢሻገር ኖሮ ሙሉውን ቀጠና መሸፈን የሚያስችል የሰራዊት ብዛት ሰላለነበርው ጣሊያን ተጨማሪ የሠራዊት እገዛ ከጣሊያን እስኪመጣለት ድረስ (ሪ ኢንፎርስመንት) ከፊል ከተሞች ይይዝ ነበር ፤ ሆኖም የስንቅ ችግር ሰለሚገጠምው ድሃ ከሆነ ከተራቆተ አካባቢ እየዘረፈ ወታደሮቹን መመገብ ተጨማሪ ችግር ያመጣበት ነበር። ሲልም አክሏል።

እነሆ ኤርትራኖች በጣሊያን መገዛት ፤ መረገጥ ፤ መደፈር እጅግ በመውደዳቸው የተነሳ ጣሊያንን ከምፅዋ አጅበው ወደ መሃል ደጋው አካባቢ አመጥተው ራሳቸውና በእኛ ህይወት ላይ ምስቀለቅል ያለ ህይወት ቢያመጡብንም፤ ዓለምና አፍሪካ ያወቀው ሰለ ባንዳነታቸውም ይቅርታ ጠይቀው አያውቁም ፡ አያፍሩበትምም።  

ሆኖም ሌላው ተጨማሪ መረጃ ኢሳያስ ቪዲዮው ላይ እንደምታደምጡት ኤርትራዊያን አፍሪካን በቅኝ ገዢዋ ጣሊያን ለማስገዛት ባንዳነታቸው ምን ያህል እንደተጓዙ ሃቁን እንዲህ ይገልጸዋል፦

«ጣሊያን ሶማሊያንም፤ ኢትዮጰያ እና ሊቢያን አልገዛም። የተዋጉለትና 60 አመት ኤርትራ ውስጥ ጣሊያን ሊቆይ የቻለበት ምክንያት በኤርትራኖች ትብብር ነው። የእጣሊያን ቅኝ ገዢነት የሚባል አለነበረም።  በተለመዶ ጣሊያን “ኤርትራ ፤ ኢትዮጵያ፤ ሊቢያ  እና ሶማሊያን ገዝቷል ቢባልም፤ በራሱ ጉልበትና የጣሊያን ሠራዊት አሰማርቶ አልገዛም” ያንን እውን እንዲሆን ያደረጉት 150 ሺህ “የርትራ አሰካሪ”  ወደ ሊቢያ ሶማሊያ ኢትዮጵያ ዘምቶ የጣሊያን ቅኝ ገዢ አገልጋየነታቸውን በማበርከት ነው። ስለ እነዚህ ሰዎች ማንም ትንፍሽ ብሎ የሚናገር እሰካሁን ደረስ አልነበረም።” ይላል ኢሳያስም ጭምር።

እነሆ በጣሊያን መረገጣቸውና ጣሊያን ለማገለገል አጅበው አፍሪካን ማዋረዳቸው ራሳቸውን ሥልጡን አድረገው የሚቆጠሩ ኤርትራኖች ማፈር ይኖርባቸዋል። አሁን ንጉሡን “ለቀቅ” ማድረግ ያስፈልጋል።

ለዚህ ነው «እግዚዞ!!  እግዚዞ!! እግዚዞ!! ምኒሊክ እንኳን ተወለድክ ዛሬ በልደትህ ቀን ከትግሬዎችና ከኤርትራኖች ክስ ነፃ ወጣህ!!!!» የምለው።  

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

No comments: