Monday, September 1, 2025

ክፍል 2 ሕዝባችን ለጠላቶቹ ሸብረክ ብሎ እንዲገዛና ገዢዎቹን ማስወገድ ያልቻለበት ምክንያቱ ምንድነው? መልስ ለዶ/ር ዮናስ ብሩ፡ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 9/1/1953

 

ክፍል 2

ሕዝባችን ለጠላቶቹ ሸብረክ ብሎ እንዲገዛና ገዢዎቹን ማስወገድ ያልቻለበት ምክንያቱ ምንድነው?

መልስ

ለዶ/ ዮናስ ብሩ፡

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

9/1/1953

ባለፈው ፍል 1 ላይ ይህንን  በሚል ነበር ያቆምነው ፦ «Because this is the minimum number of years required to educate one generation of students in the country of your enemy exposed to the ideology of [their] enemy.” ለምን ያንን ሁሉ አመት ይፈጃል? ይላል ቤዝሜኖቭ” እራሱን በመጠየቅ ምክንያቱም ይላል ሲመልስ፡ ለማጥቃት የፈለግከውን አገር የተማሪዎቿን (ያንድ ተረካቢ ትውልድ) ሕሊና ለመለወጥ፤ የራስክን አስተሳሰብ በሕሊናቸው ለማስረጽ የሚፈጀው ጊዜ ያንን ያህል አመት እየተጓዘ መጠናቀቅ ስላለበት ነው።ይላል። በሚል ነበር በይደር ያቆየነው።

   ይህንን በምሳሌ ለማየት ከፈለጋችሁ በጣሊያን ፋሺስቶች ጊዜ በደርግ ጊዜ በወያኔ ጊዜ በኦሮሙማው ባሁኑ በአብይ ጊዜ የተከሰቱ የሕሊና ጥምዘዛዎች/ጥቃቶችን ስንመለከት፤ዝርዝሩ

በውጭ ሀገር ርዕዮት የተበከለው የ60ዎቹ የተማሪዎች አብዮት ለደርግ ያቀበለው የማኦ፤ማርከሲዝም ሌኒኒዝም አስተሳሰብ ማለትምየሶቭየቶች/ የቻይናዎች/ ፍልስፍና በማስገባት የማሕበረሰቡን ባሕላዊ ክሮች በመበጣጠስ "ወንድም በወንድሙ ልጅ በአባቱ ጎረት በጎረት "የግደል ተገዳደል" የጨካኔ ሕሊና እንዲኖሮው በማድረግ ለቀወስ የዳረገውን ሁኔታ ስንመለከት

ወይንም በወያኔ በኦሮሙማው ባሁኑ በአብይ  ጊዜ የከፋፍለህ ግዛ፤ አክራሪ የጎሳ ብሔረተኛነት ማለትምከደቡብ አፍሪካውክልላዊው ዘረኛ አስተዳዳር የማይተናነሰው የቋንቋ አስተዳደር ተግባራዊ በማድረግ ጐሳዎችን በተለይ አማራውን በግፍ ለጥቃት የተጋለጠበት ሁኔታ ስናይ 

ወይንም የፋሺስት ጣሊያኖች ሴራበወያኔዎች ፈጻሚነት “በኤትኒክ ፌደራሊዝም  አገርን የማፍረስ ሴራ ተግባራዊ እንዲሆን በዝግታ 17 እስከ 22 አመት ፈጅቷል። ይህንን ስታዩ ፤ ይህ ሁሉ ጥቃት በአገር በቀል መሪዎች በሕገመንግሥት ተደንግጎ ለምን እንደ ፈራረሱ ሕዝቦች ተሎ አልፈራረሰም? ትሉ ይሆናል። ምክንያቱም፤ ለሺዎች ዘመናት እንደ ሙጫ የዞት የነበረው የማሕበረሰቡ መስተጋብር ተሎ ለማላቀቅ ከባድ ሰለሆነ ሲንገዳገድ እሰካሁን ደረስ መንምኖም ቢሆን ላለመውደቅ እየተንገዳገደ ነው ሌላ አገር ቢሆን  ግን የኸኔ ፈርሶ ነበር። ሆኖም መጠነ ሰፊ የሆነ ጥቃት ደርሷል። ሁኔታውም ሳሳቢ ነው።

ይህ ሳብቨርዥን/ግዝገዛ ሲፈጸም ያለ ምንም ጠንካራ ሀገራዊ ወይንም ፓትርዮቲክ/ሀርበኛ” የተቃውሚ አጥር ሳይገጥመው የተከናወነ ነው። እርግጥ መጠነኛ ተቃውሞች ተደርገዋል፤እየተደረጉም ነው፡ ግን በቸልተኛነት ስለተለቀቀ ዲሞራላይዘሺኑ/የሞራል ዝቅጠቱ እና ለሃይማኖታዊ ሕግጋትና ለሞራላዊ ድንጋጌ እንዳይገዛ ጥልቅ ግዝገዛ በመደረጉበውስጥ ተዋናዮች በጠመንጃና በሕሊና አጠባ” ስለተከናወነበሦስት ትውልዶች እድሜ ሂደትውስጥ ተከናውኗል ማለት ነው፡ (ደርግን በልዩ ቦታ አስቀምጣችሁ)፤በዋናዎቹ የውጭ ተላላኪዎች በወያኔ እና በአሁኑ በአብይ አሕመድ "የኦነጋዊው ኦሮሙማ" አገዛዝ ወቅት ከፍተኛ ግዝገዛ ተከናውናል

 ከፋሺስት ጣሊያን የቋንቋ/የነገድ ቅየሳ ለ 60ዎቹ ተማሪዎች ተላለፎ ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በገዛ ልጆቿ የተቀየሰው አደገኛውኤትኒክ ፌደራሊዝምን /የቋንቋ/” አስተዳዳር ተዋውቋል ማለት ነው። ሁለቱንምርዕዮትበውጭ አገር የአይዲዮሎጂካል ሳብቨርዢን ተዋናዮች የተሰነዘሩበት የሕሊና አጠባዎች ናቸው ማለት ነው።

የዲሞራላይዘሺኑን ዝቅጠት ባጭሩ 15 እስከ 20 አመት ሲጠናቀቅ፤ አሁን ያለው ሕብረተሰብም ይሁን በመወለድ ላይ ያሉ አዳዲስ  ትውልዶች፤ያስተሳሰባቸው ሕሊና ከተቀየረ አገራዊ ፍቅር ስለማይኖራቸው ሁለተኛውን ደረጃ ማለትምዲስታብላይዘሽንአገርን የማናገቱ ሂደት በቀላላሉ እንዲከናወን ይረዳል ማለት ነው (ስለተከናወነም በትግራይ፤ በኦሮሚያ ፤ ሶማሊ ፤ ወዘተ...የምናየው ሐላፊነት የጎደለው ጀብደኛውና አደገኛው ሀገር የማፍረስ ግዝገዛ በቀላሉ ማየት ትችላላችሁ  

2ኛው Destabilization አገርን የማናጋት ሂደት ወጥመድ

የዚህ ሂደት ወጥመድ ደግሞ ምን አንደያዘ እንመልከተው፡

የሕብረተሰቡን የተረጋጋ ሕይወት (የተረጋጋ ገር) ለማናጋት የሕዝቡን አቅጣጫ/ቀልብን በማሳት የሚከናውን ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት አርበኞቿ፤አገር ወዳዶቿ ፤ ምሁራኖቿን በዝግታ ማስወገድ ለመናጋቱ ከፍተኛ ክፍተት ስለሚኖሮው በነዚህ ላይ ጥቃት መከናወን ስለነበረበት ጥቃት ተፈጽሟል። ከሕሊና አጠባ የተሸጋጋረው የዲስታቢላይዘሽን ሂደት በጣም አስፈሪ እና የአገሪቱን ማሰርያ /መልሕቅ የሚበጠስበት ወቅት ነው ማለት ነው።አገር ሲናጋ ማሰሪያ፤ሉጓም የሌለው ፈረስ ይሆናል ማለት ነው።

ሊቃውንቶች፤ምሁራኖች፤አገር ወዳዶች እና አርበኞች የአገሪቱ መሪዎች እና ሉጓሞች ናቸው።እነዚህእሴቶችናቸው። ማለትምዋናው የአገሪቱ አንጡራ ሃብት ናቸው ካፒታል /አሴት የሌለው ባንክባንክራፕት እንደሚሆነው ሁሉአገሪቱም ምሁራኖቿ ስታጣአገሪቱ ትናጋለችማለት ነው።እነዚህ በሰበብ አስባቡ በውጭ እና በውስጥ ተዋናያች አጥቂነት እየተጠቁ ከስራ እንዲፈናቀሉ፤ እንዲታሰሩ፤እንዲሰደዱ፤ አካላቸው አንዲጎድል፤ አንዳንዶቹም እንዲነቅዙ፤ ዱለት እንዲያምራቸው ሆዳሞችና አድርባዮች እንዲሆኑ ከተደረገ፡ አገሪቷ ጠባቂ፤ጠበቃ፤ተሟጋች፤ተዋጊ፤ተከራካሪ፤አስተማሪ፡ ስለማይኖራትአገሪቱን ለማናጋትለአጥቂዎቹ ስለሚቀል፤ የወጠኑትን የማናጋት፤የማፍረስ ሂደት በቀላሉ ይጠናቀቃል ማለት ነው።

የሕብረተሰቡኤክሶዳስስደት፤ሞት፤ባርነት፤ውርደት፤ ባይተዋርነት ውስጥ ይገባል ማለት ነው። እዚህ ደረጃ ሲደርስአገርን የማናጋትሴራው ተከናውኗል ማለት ነው።

እኛ ከአገራችን ወጥተን እዚህ ያለንበት ዋና ምክንያት የማናጋቱ ሂደት ሰለባዎች ስለሆንን ነው። 

ይህ ሲጠናቀቅ ተጫዋቾች አሉ። ተጫዋቾቹ በማወቅም ባለማውቅም በማናጋቱ ሴራ ውስጥ የየራሳቸው መጥረቢያ ይዘው በማናጋቱ ሂደት የሚተውኑ ተዋናዮች አሉ።

እነማን ናቸው?

ሃይማኖት ድርጅቶች፤ ነጋዴዎች፤ ሚዲያዎች፤ የሴት/ የወጣት/የምሁራን፤ እና የፖቲካ ድርጅቶች ወዘተ ወዘተ…. ይጨምራል። አነዚህ ተዋናዮች የአገሪቱ ዜጎች ስለሆኑ፤ የያራሳቸው ዓላማ/ አጀንዳ ግብ ለማድረስ የሚጓዙበት መንገድ አቀበቱን በጥንቃቄ ካልተጓዙት እራሳቸውን በማናጋቱ ሂደት ጠልፈው የማናጋቱ ሴራ ተጫዋቾች የሚሆኑበት ጊዜ አለ።


ባጭሩ እንመልከት።

ሕዝቡ/ድርጅቶችአጥቂዎቹ በሚሰጡት የፖለቲካ ጫዋታ/ካርድ እየተጠቀመ እርስ በርሱ በጣላትነት እየተፈራረጀ ፤እየገዛው ያለን ሥርዓትትቶ የየራሱን ባንዴራ እያሰራ በማውለብለብኢትዮጵያንማአከላዊ የጋራ ጠላት በማድረግ የተሰጣቸው የማናጋት ሴራ የየራሳቸው መጥረቢያ ይዘው በመገዝገዝ ላይ ናቸው

/ ዮናስ ብሩ ያልተረዳው ነገር ይህ ነው።

በፋሺስቶቹ የተሰጣቸውየኤትኒክ ፌደራሊዝም አስተዳዳርአገርን የማናጋትና ሕዝቡን የማምበርከክ ሴራ ለማከናወንጎሳዎችየጋራ ጠላት እንዲፈጥሩ ተደረጉና የተነገራቸው የጋራ ጠላት የተባሉት ደግሞ ኢትዮጵያ፤ አማርኛ፤ አምሐራ እና ኦርቶዶክስየሚባሉ እስቶች (ተቋማት) ወይንም ማሕበረሰቦች በጠላትነት ተፈርጀው ከፍተኛጥቃትተፈጽሞባቸዋል። ይህ ሴራ በጣሊያን እና ከዚያም በፊት የተሰነዘረ የጥቃት ዘመቻ ስለሆነጥቃቱአሁን በወያኔና ኦሮሙማ አብይ አሕመድ ጊዜ ደንዳና መሰረት ጥሎ አገሪቱን በማናጋት ሂደት ላይ ይገኛል ማለት ነው።

የወስጥ ተዋናዮቹ ማዕከላዊ የቅስቀሳ መርሆዎቻቸውላማ ኢትዮጵያ ትሆ የነፍጠኛ፤የጡት ቆራጭ አገር፤ ኋላ ቀር አገር፤የመቶ አመት አገርበማለት ኢትዮጵያንበማዋረድ፣በማንኳሰስየማናጋቱ ሂደትስሎው ፕሮሰሱ” (በዝግታ) እንዲከናወን እየተደረገ ነው። የብከላው ቅጥ ማጣትአጥቂም ተጠቂምአብረው ባንድ መድረክ ቁጭ ብለው ምንም እዳልተፈጸመ ሲተሻሹ ይታያሉ።....

ክፍል 3 ይቀጥላል

ታቸው ረዳ Ethiopian Semay

 

No comments: