ለራስ ከፍ ያለ ግምት በመስጠት አጉል የሚኮፈሰው የትግራይ በሔረተኞች ዕብሪትና ልቅሶ
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
8/15/25
ስለ ቪዲዮው “ዘመድኩን በቀለን” አመሰግነዋለሁ። ከሙሉው ቪዲዮ ለዚህ ጽሑፍ እንዲመች በማሰብ ቆርጨ (ትሪምድ) ያደረግኩት እኔው ነኝ። በቪዲዮው ላይ የምታይዋት ማይም “አጀብነሽ” ትባላለች። አክሱም ውስጥ ከቤታችን የ 10 ደቂቃ ርቀት ጠላ እየጠመቀች ትደዳደር የነበረች ነች። መጨረሻ ግን ወያነና ሻዕቢያ ያልተማሩ ማይም ሴቶችን በመመልመል አገልጋዮቻቸውና ተዋጊዎቻቸው በማድረግ ይታወቃሉና መጨረሻ በማታውቀው የፋሺስቶች ፖለቲካ ገብታ የወያነ አሽከር ሆና «እኛ ትግሬዎች እናስለቅሳለን እንጂ አናለቅስም» እያለች ራስን በማስገመት ፤ ለማይሞች ምንም ማለት ባይሆንም “ትዕቢት ውድቀትን ትወልዳለች” የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ደረሰና «እኛ ትግሬዎች እናስለቅሳለን እንጂ አናለቅስም» በማለት ስትታበይ ኖራ በመጨረሻ “አመድ መስላ፤ራሰዋን አዋርዳ ስታለቅስ አየናት”።
ይህ
የተዓብዮና የመከስከስ የዕብሪት ባሕሪ ባንድ ሁለት ሰዎች ብቻ የታየ ሳይሆን፤ ባብዛኛው የትግራይ ተወላጆች የሚታይ ባሕሪ ነው።
ወያነ የገጠርና የከተማ ሴት ማይም ሴቶችን በመመልመል እና መጠቀሚያው በማድረግ የታወቀ ድርጅት ነው። ከተማሩ ዶከተሮችና ማስተርስ
ካላቸው የወያነ “ባምቡላዎች” (ቶይ) አግዳሚ
ወንበር ላይ እኩል እንዲቀመጡ በማድረጉ “የስነሉቦና ልዕልና” እንዲሰማቸው በማድረግ፤ እስከመጨረሻ ሞት ድረስ
ለድርጅቱ እየተሰው ቆይተው ፤ ድርጅቱ ምሁራኖቹ ሲከዱት፤ እስካሁን
ድረስ በወያኔም ይሁን በሻዕቢያ ድግሶች (ፈሲቫል) ፤ ቡና በማፍላት፤ ምግብ በመሰራት ፤ በመዝፈን ፤ በመጨፈር ፤ የገንዘብ ምንጭ
በመሆን “መፈከሮችን በማስተጋባት” በውስጥ ሀገርም በውጭም ፤ ድምቀት የሆኑት እነዚህ ማይማን ናቸው።
ወደ ርዕሱ ልግባ፡
ሃቁን
እየደበቃችሁ የትግራይ ሕዝብ እንዳናስቀይም ፤ ሕዝብ አይወቀሰም “ገለመለ” እያላችሁ እነሆ ሃቁን የሚናገራቸው ከመቶ ምናመን ሚሊዮን
አትዮጵያዊ ፊደል የቆጠረ ሕዝብ ውስጥ፤ በጣት የምንቆጠር ጥቂት ሰዎች
ከሌሎች ነገዶች እና ከትግራይ ደግሞ እኔና የትግል ጓዴ አርበኛ ገብረመድህን አርአያ ለ27 አመት ሃቁን ለመግለጽ ስንሞክር የደረሰብን
ስድብና መገለል የተወለድንበት ማህበረሰብና አፈር ተነፍጎን ሁሉንም ዓይነት መከራ ተቀብለናል። መጨረሻ ግን እውነታው ቦግ ብሎ እያታያችሁ
ነው።
ግልጽ ግልጹን እንነጋገር፡
የትግራይ
ማህበረሰብ ባህል መገለጫ የሆነ እጅግ ወደ ውስጥ ተመልካች (inward lookin) የሆነ፤ ከራሱ ጎሳ ወይም ነገድ ውጭ ላለ ሕዝብ
ጥቅምና ደህንነት የማይጨነቅ ፤ ራስ-ወዳድነት ያጠቃው፤ ንቀት፤ ከሕደት፤ጎሰኛነት እና መንደረኛነት፤ ትምክሕትና ጉረኛነትና ዘረኝነት
የተጠናወተው ይሉኝታን የማያውቅ ባህል ተከታይ ከሆነ በጣም ፤በጣም ቆይቷል (ለዘመናት)።በቅርቡ ደግሞ የተፉትን ትፋት እንደገና
ተመልሰው የመላስ ባሕል እያንጸባረቁ ነው።
ይህ ለራስ ከፍ ያለ ግምት ወይንም ውስጥ ተመልካችነት(inward looking) እንዲተውት መከራ ውስጥ እንደሚከታችው መክረን ብዙ ርቀት ተጉዘናል፡ ሰሚ አጣን። (የጎረቤት
በሸታ ተላላፊ እንደሚባለው ፤ ይህ የትግሬዎች በሽታ በዚህ ሦስት አመት ውስጥ ወደ አማራው ወጣት በፍጥነትና በእርስበርሱም በሌላውም
አስጊ በሆነ ግስጋሴ እየተጋባው እያየሁ ነው፡ (በማሕበራዊ ሚዲያም፤ በፋኖ ውስጥም፤ ካሁኑ ካልታረሙ እነሱም የትግሬዎች ዕጣ ፈንታ
ይጠብቃችዋል ማለት ነው)።
በቪዲዮው
የምታደመጧት “ወ/ሮ አጅብነሽ” እውነትም ወላጆችዋ ምን እንደታያቸው አላውቅኩም እንጂ “አጀበነሽ” ብለው ስም ሲሰጥዋት፤ እውነትም
“አጃይብ” የሚያሰኝ ሐፍረት የተከናነበች “ይሉኝታ” የማታውቅ አስገራሚ ሰው ሆና ስሟን በተግባር አሳየችን። ከላይ የጠቀስኩት የትግራይ
ማህበረሰብ ባህል መገለጫ አንዱ ይሉኝታን የማያውቅ ፤ እጅግ ትምክሕተኛና ጉረኛ፤ እንደሆነ ገልጫለሁ። የተፉትን ተፋት እንደገና
ተመልሰው የመላስ ባሕሪያቸው ፤ በቅርቡ ያያችሁት “ጽምዶ” (ጥምረት) የሚባል እጅግ አሳፋሪና ይሉኛል የሌለው ክሕደት የተላበሰ
፡ እናቶቻቸን ፤ እሀቶቻችን ደፍሩብን፤ ሰብል አቃጠሉብን፤ ማንኪያ (ሹክያ) ሳይቀር የዘረፍን፤ ”ጀነሳድ ፈጸሙብን” እያሉ ሲከሱት
ከነበረው ሻዕቢያ ጋር “በፍቅር ለመጣመድ” ወደ አሥመራ ሄደው ኢሳያስ እግር ላይ ወድቀው ሲሰግዱና የተፉትን ትፋታቸው ተመልሰው
ሲልሱና የንጉሳቸው የዮሐንስ አንገት ቆርጦ ከወሰደው ከዱርቡሽ ዝርያዎች ጋር ወግነው ከኢትዮጵያ ይልቅ ዱርብሽና ግብጽ ወገኖቻችን
ናቸው ፤ ኢትዮጰያን እናፈርሳታለን የሚል “ይሉኝታቢስነታቸውና ዕብሪታቸው” በግሐድ አሳይተውናል።
የሄው“ይሉኝታቢስነታቸውና ዕብሪታቸው” በዓይናችን በአጅበነሽ ያየነው የትግሬዎች አክራሪ ብሄረተኛነት “ድንፋታና ልቅሶ” ትግሬዎች ለራስ ያላቸው ከፍ ያለ ግምት ያመጣው ሰበብ ነው።
ለራሳቸው ያላቸው ከፍ ያለ ግምት ተባብሶ የመጣው ወያነ የሚባል ፋሺስት ድርጅት ከተመሰረተ ወዲሀ ነው። ይህ ስር የሰደደ በስነ ልቦና የተጋነነ በራስ የመተማመን ስሜት የቆየ ባሕል ቢሆንም ፤ ወያን
ከተመሰረተ ወዲህ አከራሪ ብሄረተኛነት እጅግ
ጎልቶ እንዲታይ ምክንያቶቹ የሚገልጽልን በሙያው
‘የውስጥ አከላት እና የስነ አዕምሮ ሐኪም’ የሆነው ዶ/ር አሰፋ ይነግረናል፦
ዶ/ር
አሰፋ ነጋሽ እንዲህ ይገልጸዋል፤-
«፮(የኢትዮጵያን
አብዮት ተከትሎ የተፈጠረውና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከዚህ ቀደም ባልታወቀ መልክ ሰፊውን ህዝብ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ያሰገባ
ሁኔታ) በትግራይ ውስጥ ለአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት ስሜት ለሚመራና
ኋላ ላይ በሂደት ወደ ፋሽስታዊነት ላመራ ድርጅት መጠናከርና ለፋሽስት ስርዓት መፈጠር ምክንያት ሆነ ብዬ እሞግታለሁኝ። “የትግራይ
ማህበረሰብ ባለፉት 50 ዓመታት አክራሪ ብሄረተኛነት በፈጠረው አዲስ አስተሳሰብ ምክንያት አመለካከቱ በአዲሱ የትግራይን
አክራሪ ብሄረተኛነት መገለጫ በሆነው የፋሽስት ፍልስፍና በመቀረጹ ኢትዮጵያዊነት የምንለውን የጋራ ማንነት ተጻራሪ የሆነና የአንድን
አናሳ የትግራይ ህዝብ ማንነት በአምልኮ ደረጃ እንደጣዖት የሚያመልክ በአንድ ወጥ አስተሳሰብና ሃሳብ የሚመራ የፋሽስት ስርዓት ተሸካሚና
አራማጅ ሆኖአል ብዬ እሞግታለሁኝ።”
እንደ
ማንኛቸም አገር አክራሪ ብሄረተኞች ትግራይ ውስጥም ሶስት የአክራሪ ብሄረተኛነት ማጠንጠኛዎች በወያኔ ድርጅትና ተከታዮች ላይ ታይተዋል።
አክራሪ
ብሄረተኞች አንድን የቸገረው ህዝብ የሚከተሉትን ሶስት ነገሮች በመንተራስ የብሄረተኛ ዓላማቸው ተከታይ በማድረግ አንድን ህዝብ እንደ መንጋ ባንድ ሃሳብና ባንድ መሪ ድርጅት ስር
በማሰለፍ ይጋልባል።
፩)
በአፈ-ታሪክና በአብዛኛው በውሸት ላይ የተመሰረተ አዲስ ታሪክ በመፍጠር አንድ ህዝብ እጅግ ደማቅ የሆነ በእጅጉ ገናና የሆነ ታሪክ
ባለቤት እንደነበረ ይተርኩለታል።
፪
- ይህ ትላንት በታሪክ የደማቅና ገናና ታሪክ ባለቤት የነበረ ህዝብ በዛሬው ዘመን እየተፈጸመበት ያለውን በደል፤ ወርድትና ብሶት
ያስተጋቡለታል።
፫
- ይህ ትላንት ደማቅና ገናና ታሪክ የነበረው ዛሬ ደግሞ የውርደት፤ የበደል ሰለባ የሆነ ህዝብ ራሱን እነዚህን አዲስ የነጻነትና
የአክራሪ ብሄረተኛነት ዜማ የሚያዜሙ መሪዎችን ቢከተል ሊያገኝ የሚችለውን ሲሳይ ይተርኩለታል። ከዚህም በላይ ብሄረተኞች ወገናችን
ነው የሚሉትን አንድ ምርጥ ህዝብ አንተ የእኛን መሪነት ተቀብለህ በስራችን ታቅፈህ ከታገልክ ምድራዊ ገነት እናወርስሃለን፤ ከችግርና
ከጉስቁልና እናወጣሃለን ብለው የተስፋ መና በማስጨበጥ አንድን ምርጥ ህዝብ ወይም ነገድ በአዲስ ተስፋ ለትግል ያነሳሱታል። እነዚህ ሶስት ነገሮች የብሄረተኝነት ማጠንጠኛ ድርና ማጎች ናቸው።
እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ሶስት ነገሮች የፋሽዝም መሰረት የሆነው የአክራሪ ብሄረተኛነት ማጠንጠኛ
ድርና ማጎች ሆነው የሚያገለግሉ ዋና ዋና መሳሪያዎች ናቸው። የትግራይ ብሄረተኞችም እንደ ማናቸውም አክራሪ ብሄረተኞች ለትግራይ
ህዝብ ትላንት እጅግ ደማቅ የነበረ የአክሱማዊ ስልጣኔ ፈጣሪና ባለቤት ነበርክ፤ አንተ ጀግናው የትግራይ ህዝብ ከምንሊክ ጀምሮ ስልጣን
ላይ በወጡ የአማራ ተወላጆች ተዋረድክ፤ ተበደልክ፤ መሳለቂያና መዘባበቻ ሆንክ አሁን እኛን ብትከተለን ከዚህ ውርደት፤ መከራና ጉስቁልና
እናወጣሃለን፤ አዲሲቷን ትግራይን ገንብተን የትግራይን ህዝብ የበላይነት በማምጣት የትግራይን ህዝብ የቀድሞ ክብሩና ግርማ ሞገሱን
እናስመልስለታለን። ትግራይን የልማት፤ የእድገት፤ የእውቀት፤ የጥበብ፤ የደስታ፤የሀሴት ምድር፤ ዜጎቿንም እጅግ ኩሩና በሌሎች ህዝቦች
የሚፈሩ፤ የሚከበሩና የሚደገደግላቸው እናደርጋለን ብለው ተነሱ።» (አሰፋ ነጋሽ- ዶክተር)
እውነትም
ዶ/ር አሰፋ እንዳለው ፤ ወያኔዎች ትግራይን የልማት፤ የእድገት፤ የእውቀት፤ የጥበብ፤ የደስታ፤የሀሴት ምድር፤ ዜጎቿንም እጅግ ኩሩና
በሌሎች ህዝቦች የሚፈሩ፤ አስለቃሾች እንጂ
የማያለቅሱ የሚከበሩና የሚደገደግላቸው
እናደርጋለን ፡ ብለው እንዳሉት አማራውን
ከለማ እርሻውና የንግድ መተላለፊያና የሸቀጥ ምርት ከውጭ ማስገቢያ ከርስተጉልቱ ከመሬቱ ከወልቃይት አፈናቅለው በበዙ ሺሕ የሚቆጠር
ታጋዮቻቸውና አዲሰ ሰፋሪ ትግሬ
በጠመጃ ኃይል በሕገ ወጥ አሰፈሩበት ። ጋምቤላውንም አደህይተው ትግሬዎች ተጠቃሚ እንድሆኑ አደረገ።
ለምሳሌ
በጋምቤላ ክልል የመሬቱ ባለቤት የሆነው ኢትዮያዊው የጋምቤላ ተወላጅ እየተፈናቀለ የመዋዕለ ነዋይ ጌቶች ለሆኑት ኢንቨስተርስ የሚባሉ የውጭ ሀገር ዜጎችና ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት “የኢትዮጵያ ዋነኛ ባለሃብቶች” ለሆኑት የትግራይ ተወላጆች ተከፋፍሏል። ይህ ሲደረግ በልማት ስም ነባሩ የጋምቤላ ህዝብ ከመሬቱ ላይ እየተነቀለና እየተፈናቀለ እሱ ወደማይፈልገው ለምነት የሌለው ሥፍራ ላይ በግዴታ ተወስዶ አንድ ላይ እንዲሰፍር ተደርጓል። የጋምቤላ ህዝብ ይህ ሁሉ ነገር ከመደረጉ በፊት ፍላጎቱ አልተጠየቅም፤ በቅድሚያ ምንድነው ሃሳብህና ምኞትህ ተብሎ እንደ አንድ የሀገር ዜጋ ያማከረው የመንግስት አካል የለም። የጋምቤላ ህዝብ ህይወቱን፤ ህልውናውንና የእራሱንና የልጆቹን ዕጣፈንታ በሚወስን መሬቱ ላይ ከትግራይ ተነስተው የመጡ ባለጊዜዎች የፈለጋቸውን ሲያደርጉ ምንም ማድረግ አልቻለም። በጋምቤላ ክልል በኢንቨስተርነት ከተሰማሩት የሀገር ውስጥ ባለንብረቶች ከሰማንያ በመቶ በላይ የሆኑት ትግራይ ከሚባለው ነገድ የፈለቁ ባለጊዜዎች፤ ባለሃብቶችና ባለጠመንጃዎች ነበሩ። ከአንድ ሺህ በላይ ቁጥር ያላቸው የቀድሞ የህወሃት ታጋዮች የሆኑ የትግራይ ተወላጆች የጋምቤላን መሬት ተቀራምተው መያዝ ብቻ ሳይሆን በዚህ በያዙት መሬት ስም በቢሊዮን የሚቆጠር ብር በብድር መልክ እንዲሰጣቸው ተደርጓል። እነዚህ ባለጊዜዎች በጋምቤላ መሬት እናለማለን ብለው የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት ከሆኑ ባንኮች ስምንት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ተበድረው ብድሩም የተበላሸ ብድር ሆኖ ሳይከፈል ጠፍቶ ቀርቷል።
ሆኖም ለ27 አመት “ጠምንጃውም፤ ባንኩም ሥልጣኑም” በእጃቸው ያስገቡ ትግሬዎች በመላው ሃገሪቱ የተንሰራፋው የንግድና የባለሃብትነት የትግራይ ተወላጆች ማን ይይዘኛል ምዝበራና “ጥጋብና ዕብሪት” አላስችል አላቸውና በድንገት “አዱኛ በላያቸው ላይ ፈርሳባቸው” የመውደቂያ ወቅታቸው ደርሶ በአልጠግብ ባይነት “ሥልጣን አንለቅም” ብለው፤ ጦርነት ከፍተው ፤ “እኛ ትግሬዎች እናስልቅሳለን እንጂ አናለቅስም” እያሉ ሲያደነቁሩን ከርመው፤ እንደ ማይምዋ አጀብነሽ “ልቅሶና ሐፍረት ተከናነበው” እነ ስብሓትና እነ .... እነ..... ውስጣቸው ረጥቦ የቁም ሬሳ ሆነው ግብአተመሬታቸውን አየን።
በህይወት ያሉትም “ ከዚያ ዕብሪት ሳይማሩ አሁንም ወደ “ሃገረ ትግራይ ቀዥት
ገብተው ይቃዣሉ” ግማሹ ወደ “ተፉት ትፋታቸው ተመልሰው ለመላስ” ወደ አሰምራ ሄዱ፡ ግማሹ ጀነሳይድ ፈጸመብን ወደ አሉት የአብይ
አሕመድ ጫማ ላሽ ሆኑ። ለራስ ከፍ ያለ ግምት በመስጠት አጉል የሚኮፈሰው የትግራይ በሔረተኞች ዕብሪትና ልቅሶ ቀስ ብሎ እየተጋባበት
የምናየው የአማራ ወጣትም ከዚህ እንደሚማር ተሰፋ አደርጋለሁ።
ጌታቸው
ረዳ
No comments:
Post a Comment