አብዱ ክያር የሚባል ኤርትራዊ ባንዳ “ቦይኮት” በማድረግ አግልሉት
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
8/23/2025
እኔ ለኢትዮጰያ ሃገሬ ደህንነትና
ክብር ስል ለቡዙ አመታት በጠመንጃም በብዕርም ስታገል በስንት ግለሰቦችና
ድርጅቶች ጥርስ መግባቴ እውን ነው። ለዛች ሃገር ስል፤ በሃብት፤ በኑሮ፤ በትምህርት፤ብዙ መከራዎችና ጠላቶች ቢገጥሙኝም ለደረሰቡኝ
ፈተናዎች ሁሉ በደሰታ ተቀብያቸው እነሆ እስካሁን ድረስ ከነሱ በፊት ከዚሀ ዓለም ሳልለይ “የኢትዮጵያ ጠላቶች” ሁሉም ባይሆኑም
ዋና-ዋና የተባሉት ጠላቶች “ተፉረክረከው ፤ አፈር መስለው፤ ማቅቀው፤ ተገልለው ፤ ተዋርደውና አፈርድሜ በልተው፡ እነሆ ስላየኋቸው
ደስ ብሎኝ “ የኢትዮጵያን አምላክ “እያመሰገንኩ” እነሆ እየተራመድኩ ነው”።
ስለሆነም አንዳንዶቻችሁ ካለመብሰል የተነሳ ጠላቶቻችሁን ሰታመሰግኑ እና የነሱን ምልከቶችና ሙዚቃዎቻቸው እያውለበለባችሁ፤ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ናቸው ሳይሉዋችሁ ፤ ነን እያላችሁ እነሱ እያሾፉባችሁ፤ በየአደባባዩ ተሰልፋችሁ “ፐሮፕጋንዳቸውንና ዓላማቸውን” ሰታራግቡላቸው ለብዙ አመታተ አይቻለሁ።
ከዚያ አልፎ ይህንን በመቃወሜ ብዙ ዘለፋ አስተናግጃለሁ። ዛሬም አብዱ ክያር የተባለ ብዙ የዋሆችን “ኢትዮጰያዊ ነኝ” እያለ ያታለለ “እቤቱ ኤርትራዊ ደጅ ሲወጣ ኢትዮጰያዊ”
ሆኖ ለብዙ አመታት ሲቀልደባችሁ ኖሮ ፤ እነሆ አምሐራዎችን እና ብዙ ኢትዮጰያዊያኖችን በኢሳያስ አፈወርቂ አሽከሮች በግፉ ሲጨፈጨፉ
፤ በከርሰ -መቃብራቸው ላይ ከበሮ እየደለቁ ሲያውለበልቡዋት የነበረቺው ይህች “አሳካሪ-ባንዳው አብዱ ኪያር” ለብሶ እያላገጠብን
ያለቺውን
“የጀገኖች ባንዴራ፤ በበረሃ በዱሩ
ለነፃነት የታገሉ፤
በኩራት ቀና ብለው ደስታን ያበሰሩ...”
እያለ በኩራት የገጠመላት “ ሃገሩ ኤርትራ” እንጂ “እርሱ እና 10 ወንድሞቹና
እህት ዘመዶቹ የቀለዱባት፤ የተዋቡባት “ሀገሩ ኢትዮጵያ እንዳልሆነች
ሲነግራችሁ ፤ ለምን “ቦይኮት አድርጉት” አልክ በላችሁ እንደምትነጨረጨሩብኝ እገመታለሁ።
ምክንያቱም በዚህ አጭበረባሪ ባንዳ
ለብዙ አመታት የኢትዮጵያን “አህዮች” የሆናችሁ ልባችሁ ተሰልቧልና ለምን እንደምትንጨረጨሩ ይገባኛል። እንግዲህ የቀራችሁ “ጸሐየ
ዮሐንስ” ነው፡ እርሱም “ፈጣሪ ይማረው”።
ኢሳያስና ወያኔዎች ወደ አዲስ
አበባ አሰርገው ያስገቧቸው ሰደትኞች፤ ተማሪዎች፤ ነጋዴዎችና ሙዚቀኞች ብዙ የፕሮፓጋንዳ ስራ ሰርተዋል።ሙዚቀኞችን ለፕሮፓጋንዳና
ስለላ መጠቀም በነዚህ ድርጅቶች የተጀመረ አይደለም። በተለይ ቱጃሮች (ባለሃበቶች)፤ ስደተኞች፤ በሙዚቀኛነት እና ተማሪዎች ወደ
ሀገሮች ሰርገው የሚገቡ ቅጥረኞች የተደራጀ እና ሰፊ ስልት እንዳለው አመላካች ታሪኮች አሉ።
ቱጃሮች እና ሰላዮች “ሙዚቃን እንደ ሽፋን” ሲጠቀሙበት የተመዘገቡ አጋጣሚዎች
አሉ። የምታውቁት የሩሲያ ፓራሚሊተሪ ድርጅት፤ ዋግነር ግሩፕ ስሙን ያገኘው የሂትለር አቀነቃኝ የነበረው ጀርመናዊው እውቁ የሙዚቃ
ኮንዳክተር ‘ሪቻርድ ዋግነር’ ሲሆን ፤ የሩሲያ ዋግነር ተዋጊው ሃይል
“ሙዚቀኞቹ” ወይም “ኦርኬስትራዎቹ” የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቷቸው
ነበር። ይህ ቅጽል ስም ከተመዘገበው የሙዚቀኞች ታሪክ ጋር ተዳምሮ በሰላይነት ይሠሩ እንደነበር, ለዚህ አስተሳሰብ መነሻ ሆኗል። ይላሉ ሰለ ስለላ ዘርፍ አጥኚዎች።
በሙዚቃ ስራ እና በስለላ መካከል ያለው ግንኙነት ታሪካዊ ቅድመ ሁኔታ “ፖለቲካ”
ነው። የሙዚቀኞች እና የሰላዮች ታሪካዊ ምሳሌዎችን ልስጣችሁ፡
”ሌኦን ታሬሚን” - ፡
ልዩ የሆነ የኤሌክትሮኒካዊ የሙዚቃ መሳሪያ የሆነውን “የቴሬሚን” ፈጣሪ የሶቪየት
ሰላይ ነበር። በአዲሱ መሳሪያ ዓለምን እየጎበኘ ሳለ ለሩሲያ መረጃ እየሰበሰበ ነበር።
ጆሴፊን ቤከር፡-
አሜሪካዊት ፤ የተወለደችው ፈረንሳይ።
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለፈረንሣይ ተቃውሞ ሰላይ ነበረች፣ የሙዚቃ ዝነኛነቷን ተጠቅማ አውሮፓን ስትዞር ሳይታወቅባት እየሰለለች
እንድትዘዋወር አድርጓል።
ማይልስ ኮፕላንድ -ጁኒየር፡-
ይህ ሰላይ ታውቁታላችሁ። የሻዕቢያው
ኢሳያስን የቀጠረ “የሲአይኤ መስራች አባልና ስለዚህ ሰው በሰፊው የዘገቡት “ነበሳቸው ይማር” መምህሬና ወዳጄ ዶ/ር ዓለሜ እሸቴ ሰፊ ዘገባ የጻፉት
Ethiopian Semay ድረገጽ ላይ ታገኙታላችሁ) ማይልስ ኮፕላንድ የጃዝ ሙዚቀኛ ሆኖ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የስትራቴጂክ አገልግሎት ቢሮ
(OSS) የስለላ መኮንን ሆኖ በኋላም የሲአይኤ መስራች አባል የነበረ ነው።
አንዳንዶቻቸሁ እንደምታውቁት “በቀዝቃዛው
ጦርነት ወቅት” ፣ ሲአይኤ “የአሜሪካን ዲሞክራሲ” ለማስተዋወቅ እና “የሶቪየትን ተጽእኖ ለመመከት” ጃዝን እንደ “እንደ ዓለም
አቀፋዊና ባህላዊ መሳሪያ” ሆኖ ሙዚቃ ለፕሮፓጋንዳ መሳራርያ ሆኖ አገልግሏል (ልክ እንደ አብዱ ከያር ኢትዮጰያ ውስጥ አድጎ ፤
“እቤቱ ኤርትራዊ ደጅ ሲወጣ ኢትዮጰያዊ”
ሆኖ “የ ሻ ዕ ቢያ” ፐሮፓጋንዳ እየሰራ እንዳለው
“ግልጽ አግልግሎት” ማለት ነው)።
የምስራቅ ጀርመን ሚስጥራዊ ፖሊስ (ስታሲ) በተራው የጃዝ ክለቦችን ሰርጎ ተቃዋሚዎችን
ለመከታተል እና ለመመልመል ይጠቀም ነበር።
እንደ ኢሳያስና ወያኔ የመስሉ
መሰሪዎችም ሙዚቃን በመጠቀም አባሎቻችውና የየዋህ ሃገር ሕዝቦች “ማህበራዊ ትስስር በመፍጠር” የማህበረሰቡን ስሜት በማሞኘት ፤ ለተቃውሞም ሆነ ለፕሮፓጋንዳ ውጤታማ መሳሪያ ሆኖ አግልግሏቸዋል። ሙዚቃ እንደምታውቁት “በስብሰባዎች እና በሌሎች የፖለቲካ
ዝግጅቶች ላይ” ጥቅም ላይ መዋሉ ሰዎችን ከአንድ የተለየ ሀሳብ ወይም ምክንያት “ጀርባ” አንድ ሊያደርጋቸው የሚያስችል አደገኛ
የሕሊና መበረዣ ነው።
የ አብዱ ኪያር ማንነት በግልጽ
ቢወጣም የዚህ “ጡት ነካሽ” ኤርትራዊ ባንዳ የሙዚቃ ሥራው ለድብቅ እንቅስቃሴው አሳማኝ ሽፋን ሰጥቷል ። ኢትዮጵያዊያኖች ምን እንደነካን
ባልውቅም፤ ‘አህዮች’ ሲሉን የምንስቅ ፤ ‘’አባትህን ማረክሁት’’ ሲሉን የምናንጨበጭብላቸው” እውነትም “አህዮች” ነንና ፤ባሕር ወደቦቻችን ሲዘጉብን “አማራን፤ ጋምቤላን ፤ወላይታን፤ ኦሮሞን፤ ጉራጌን
፤ ጋሞን፤ ሶማሊን...ወዘተን ሲጨፈጨፉና ፤ ወታደሮቻችን ቀን ጥሏቸው ወደ ሱዳን ሲያፈገፍጉ ምድረበዳ ውስጥ በውሃ ጥም ሲሰቃዩ
፤ “የአብዱ ኪያር ጀግኖች” መስኪን ወታደሮቻችንን በመተረየስ እየቆሉ ከበሮ እየተደለቀ
በመቃብራቸው ላይ የተተከለች “አበዱ ኪያር”
“የጀገኖች ባንዴራ፤ በበረሃ በዱሩ
ለነፃነት የታገሉ፤ በኩራት ቀና
ብለው ደስታን ያበሰሩ...”
እያለ የዘፈነላትና የዘፈነላቸው ናዚዎችና ምልክታችውን ነው ለብሶ “እየዘፈነላቸው ያለው”። አብዱ ኪያር ከመዝፈን አልፎ ያላወቅናችው የስለላና መጥፎ ድብቅ ተግባሮች ሌላ ምን እንደሰራም ፈጣሪ ይወቀው።
አሳዛኙ ነገር አንድም ኢትዮጰያዊ እሰካሁን ድረስ ይህንን “አልበም” ሳይቃወም እንዳውም ይህንን ባንዳ ሲያወድሱት ስመለከት፤ ይህች ሃገር በዙ ሚሊዮን አህዮች እንዳላት አመላካች ነው። "አብዱ ኪያር" ካለ ፈቃዴ በሰው ሰራሽ (Artificial Intelligent) አልበም የተሰራ ነው ከተባለም፤ "አብዱ ኪያር" በራሴ ፌስቡክ Ethiopian Semay Facebook ላይ ሄዴ ወይንም እዚህ በመምጣት ማስተባበል አለበት። ካለሆነ የራሱ እንደሆነ ታስቦ ተለጥፎ ለታሪክ የተላለፋላል።
ታዋቂው ዳዊት
ጽጌ የተባለ የሸዋ አምሐራ ተወላጅ ኤርትራ እያለ ያደነቆረን “አዲስ ምልምል ባንዳ” እንዳይበቃን አሁን ደግሞ ተሸሽጎ የነበረው
የሻዕቢያው ምልምል አብዱ ኪያር እያሾፈብን ነው። አሳታሚዎቹም ማንም ሊሆን አይችልም “የኛው አህዮቹ” ካለሆነ ሌላ አሳታሚ አይደፍርም።
ሁሌም የነሱን ስድብና ጉራ የሚያትሙላቸው የኛዎቹ ናቸው።
ድሮ ከሃገር ሳልወጣ “ኤርትራኖች
አንዳንድ መልካም ሰዎች ቢኖርዋቸውም የበዙዎቹ ሽንፍላት ግን ማወቅ
አትችልም፤ ከሃዲዎች ናቸው ፤ እነሱን ማመን ቀብሮ ነው” ያለኝ አንድ ወዳጄ ያሁኑ የአብዱ ኪያር “ሽንፉፍላት” አስታወሰኝ። ይህ
ሁሉም ተነግሯችሁ እያለም ለዘመን መለወጫና በየእስፖርት ባዓላት “አበዱ
ኪያርን” እንደምትጋብዙት ጥርጥር የለኝም። ኢትዮጰያዊያኖች የባንዳዎች መጫወቻ ከመሆን ነፃ የምትሆኑት መች ይሆን? የሚል ጥያቄ ጭሮብኛል።
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay
Abdu Kiar - Eritrea | ኤርትራ | New Ethiopia Music 2025 [Official Video]
https://youtu.be/LvGxCVZKn6A?si=70dXO0fJhCyw-91u

No comments:
Post a Comment