ታላቅ
ሕዝብ በታላቅ ተራራ ላይ ቆሜ ማመስገኔ የሚጠሉኝ ካሉ ለኢትዮጵያ
እንግዶች ናቸው! ከጌታቸው ረዳ (Ethio
Semay ኢትዮ ሰማይ)
Amhara the guardian of Orthodox Christianity in Ethiopia |
ከታች ያለው ቪዲዮ ተመለከቱ! ትግሬዎች
በጠላትነት የፈረጅዋት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ አማራው እንዴት እንደተንከባከባት ይህንን ቪዲዮ እንድታዩ እጋብዛችኋለሁ።
አማራው “ተዋህዶ ኦርቶዶክሰ ቤተክርስትያንና
አማርኛ ቋንቋን” ጠብቆ አሁን እስካለነው ድረስ ተጉዞኣል። አሳዛኙ የዘመናችን ክስተት ግን ከምፅአተ-አክሱም “የቤጃ ወረራ በኋላ”
በትግሬነት የተከሰቱት ትግሬዎች” በ1967 ዓ.ም ወደ ጫካ በመሄድ
‘ኦርቶዶክስ ክርሰትናን፤ ባለ ሦስት ሕብር ሰንደቃላማችንን እና አማርኛን’ በጠላትነት ፈርጀው ዳግም ‘ምፅአተ -ኦርቶዶክስ’ ለማምጣት
የተነሱ “የወያኔ ትግሬዎች” በስብሓት ነጋ አንደበት የተነገረና በድርጅቱም በተግባር የተከናወነ በማስረጃ ያለ ህያው ምስክር ነው።
እኔ ከትግራይ መወለዴ “እስመ ኢአቀቡ ቃለከ” (ቃልህን አልጠበቁምና፤ግብዞችን አይቼ አዘንሁ” (መዝሙር 117) እንድል ተገድጃለሁ።
እኔው ራሴ ትግሬ መሆኔን አስጠላኝ ብላችሁ ይገርማችሁ ይሆናል፡ ለዚህ ምክንያት አለኝ። እነ ስብሓት ነጋን እነ መለስ ዜናዊን የሚያሞግስ
ተሸክሞ የሚሄድ ማሕበረሰብ ትግራይ ለመግለጽ ቃላት አበድሩኝ!
ትንሽ ተስፋ እየሰጠኝ የመጣ ነገር
ቢኖር፤ ዛሬ፤ ዛሬ በቅርቡ ያየሁት አዲስ ክስተት ‘ሴቱም ወንዱም ልብሱም፤አንገቱም ግምባሩም በተዋበ መስቀል ያጌጠው አማራን እያዩ”
ትግሬዎች አንገታቸው ላይ መስቀል ማንጠልጠል መጀመራቸው የነ ሰብሓት ነጋ አማራን እና ኦርቶዶከስን አከርካሪው ሰበርነው የሚለው
ጥላቻቸው ቦታ እያጣ መምጣቱ የሚበረታታ ነው። መገንዘብ ያለብን ሕዝብን በሚምበለበል የምድረበዳ እሳት አሻግሮ የኢትዮጵያን ሰንደቅና
ሃይማኖትዋን መሠረተ ድንጋይ አንዋሪው አማራው ዛሬም ሃያሉ ምድረበዳ ፊቴ ላይ ተጋርጦበታል። ሁሉም እንደልብስ ያረጃሉ እሱ ግን
እንደ ጥንቱ ምድረደባውን በድል ይሻገራል ብል አልተሳሰትኩም። ይህንን ታላቅ ሕዝብ በታላቅ ተራራ ላይ ቆሜ ማመስገኔ የሚጠሉኝ ካሉ ለኢትዮጵያ እንግዶች ናቸው።
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ
(Ethio Semay)
EOTC TV CHANNEL ደብረ ሐዊ መካነ ምሥዋር(ሊታይ የሚገባ የቅዱስ ያሬድ ገዳም)ሊያመልጦት የማይገባ ዘጋቢ ፊልም
No comments:
Post a Comment