Saturday, November 16, 2019

በየዓለማቱ መዞር የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ፈውሰቢሱ ሱስ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay

በየዓለማቱ መዞር የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ፈውሰቢ ሱስ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay
11/16/2019
ትችቴን በዚህ ጥቅስ ልጀምር

Cry my beloved country ! ዕርይ በይ ውዲትዋ አገሬ! በተባለው የደቡብ አፍሪካዊው ‘አላን ፓተን’ እንደፃፈው ፣ እንዲህ ይላል “ የተወደድሽ ሀገሬ ሆይ ፣ ላልተወለደው ልጅ ፣ የፍርሃታችን ውርስ ወራሾች ሆኗልና ምድርን በጣም በጥልቀት አትውደድ በይው። በጣቶቹ ውስጥ ውሃ ሲንቆሮቆር በድስታ አይፈንድቅ፤ ወይም ፀሀይ ስትጠልቅ ዙርያዋ በሚንቀለቀል ቀይ እሳት ስትከበብም ዝም አይበል ፡፡ ….”

ይላል በኔ አተረጛጎም። መጽሐፉን እንደ ‹ማህበራዊ መዝገብ› የጻፈው በነጭ እና በአገሬው ደቡብ አፍሪካውያን መካከል የነበረውን የዘር ልዩነት እና የዘረኝነት መድልዎ ከመጀመሩ በፊት የነበረውን ማህበራዊ ግጭት ክስተቱን ካየ ወዲህ ‘አላን ፓተን’ ስጋቱን የገለጸበት መጽሐፍ የተረጎምኩት ጥቅስ፡፡

ይህ ትችት ጀግናው እስክንድር ነጋን አይመለከትም። እየተቸሁ ያለሁት “ኢዜማ” ብሎ ራሱን የሚጠራው አንዱአለም አራጌና ባንዳው የብርሃኑ ነጋ ድርጅትን ነው። እዚህ ፌስቡክ ስመለክት “አንዱአለም አራጌና የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል Minnesota አሜሪካ ለ ኖቮምበር 23/2019 “በውጭ አገር ስላሉ ዜጎች ዕጣ ፈንታ ለመወያየት” ይመጣሉ የሚል ማስታወቂያ ሳነብ ጥያቄ ጫረብኝ።“በውጭ አገር ስላሉ ዜጎች ዕጣ ፈንታ ለመወያየት” ቀርቶ አገር ውስጥ እየተጨፈጨፈ እየተፈናቀለ የዘር ጭፍጨፋ- ጀነሳይድ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ዕጣ ፍንታ ማወቅ ያልቻሉ “ተደማሪ ተቃወሚዎች” እንዲህ የሚል ውይይት እንዴት ሊያስኬዱት እንደሚችሉ ገርሞኛል። ዋናው ትችቴ ግን ይህ አይደለም። ዋናው ትኩረቴ እና ጥያቄዬ እጅግ የሚገርምኝ ተቃወሚ የሚባለው ለ27 አመት ዛሬም መዞር ነው ሥራቸው? ሕዝብ የዘር ማጥፋቀት እየተፈጸመበት ፤በየቦታው የሚገኝ ወጣትና ኗሪ ያለቺውን ቁራሽ እንጀራ እና ውሃ ለተፈናቃዮች እያቀረበ ባለበት እጅግ አንገብጋቢ ወቅት እነዚህ ተቃዋሚ ተብየዎች ሕዝብን እያስተባበሩ እልቂቱን ከማቆም ይልቅ” በየዓለማቱ መዞር የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ልዩ ሲንድሮም ሕክምና አያስፈልጋቸውም ብላችሁ ታምናላችሁ?

እንቆቁልሹን ንገሩን እስቲ? ለመሆኑ ይህ ሁሉ የዘር ዕልቂትና በየ ቤተክርስትያኑ የሚንቦጎቦጎው እሳት እያየ እየወሰደ ያለው ዕርምጃ ምንድ ነው? ፌስ ቡክ ያለው ታጋይ እኮ ነው ሁኔታውን እያሳወቀ እያስተባበረ ያለው። የሚገርም ነው! ባሁኑ አስፈሪ ወቅት ካልተገኙለት ከጉዳት ወዲያ መለፍለፍ ምንየውን ይረቡታል? አመሰግናለሁ= ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay

No comments: