Friday, November 15, 2019

አብይ አሕመድ ክርሰትያኑን የተሳደበበት አንደበቱ


ውድ የኢትዮ ሰማይ ድረገጽ  አንባቢዎች ዛሬ  በሁለት ርዕስ አንወያያለን፡
1)        አብይ አሕመድ ክርሰትያኑን የተሳደበበት አንደበቱ

2)       ከአማራና ከኦሮሞ ፓርቲ “ተደማሪ ተቃዋሚዎች” የቤተመንግሥቱ ግብዣና ያደመጡት ዲስኩር
(ጌታቸው ረዳ - ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)
11/15/2019 (ጥቅምት 2/2012)
በሚቀጥለው ሰሞን ጀግናው ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ አማራውን ከጥቃት ለማውጣት ታጥቆ መነሳቱን ያወቀው አፓርታይዱ ዘረኛው የኦሮሞዎቹ ምንግሥት ዓይን ውስጥ ገብቶ እንደነበር ከቻሉ አስሮ ለመወንጀል፤ ካልቻሉ ለመግደል የታቀደ ዕቀድ ተይዞ እንደነበር ከአንዳንድ የአገሪቱ ከፍተኛ የመከላከያ ሓላፊዎች ሲሰነዝሩት የነበረው ውንጀላ በቃላቸው እናደምጣለን። ጥልቅ የሆነ ማስረጃ እንመለከታለን።ለዛሬ ግን ወደ ሁለቱ ርዕሶች እንሸጋገር።

በዚህ ርዕስ ሁለት ነገሮችን እንመለከታለን። አንደኛው መነጋገሪያችን ‘አብይ አሕመድ’ ለክርሰትያኑ ያለው ንቀትና ዘለፋ፡ ሲሆን ሁለተኛው መወያያ ደግሞ ተቃዋሚ ተብየዎች ወደ ፓርታይዱ ቤተመንግሥት ተጠርተው አሁን እየተካሄደ ያለው ጀነሳይድ/የዘር ጭፍጨፋውን/ ክስተት ተቃዋሚዎች የየክልሉ ብሶት ስለማታውቁት “ተደመሩና” እየሞተ ያለው ማዳን ትችላለችሁ በማለት የሕዝቡን “ብሶት” የማያውቁ ግብዞች አድርጎ አንኳስሶኣቸዋል። በቴ/ቪዥኑ (ዩቱብ) እንዳየነው ነፈዝ ተቃዋሚዎቹ በተዋበው የመደንዘዣ ጠረፔዛው ላይ ተቀምጠው ከመቁለጭለጭ ሌላ ምን መልስ እንደሰጡት አልታወቀም።

መጀመሪያ የአፓርታይዱ መሪ መኖርያ  ወደ ሆነው ቤተመንግሥት የተጠሩ አማራና ኦሮሞ ተቃወሚዎችን እንመለክት።

የጃዋር ወዳጅ ተረኛው የኢትዮጵያ አፓርታይድ ስርዓት መሪ አብይ አሕመድ በትናትናው ዕለት ቀንዷ እንደተመታች ላም ውስጣዊ ተንኮሉን እየበላው በተደበረ ድብርት ንግግሩ የአማራና የኦሮሞ ተቃዋሚ ድርጅቶችን

 (የአማራ ተቃዋሚ ፓርቲ ማን እንደሆነ አልገባኝም፡ ኦሮሞው ግን ተቃዋሚ ሳይሆን የአብይ/ጃዋር/ለማ ጥምር የኦሮሚማ መንግሥት የመሰረቱ የኦነግ/ኦሆዴድ/ኦፌኮ ፓርቲ ስለሆኑ ተቃዋሚ አይደሉም። ተጠሪው አማራ ብቻ ነው ቢባል ይሻላል።)

 ወደ ቤተመንግሥቱ ጠርቶ ‘አሁን የሰበሰብናችሁ ምክንያት በሁለቱ ሕዝቦች እና በሁለቱ ክልሎች መካክል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በነሱ ምክንያት በሌሎች ሃይሎችም ምክንያት “መቃቃር፤ጸብ ግጭት፤ የሰዎች ህይወት መጥፋት እየተባባሰ እንደ ዋዛ ሰው እየሞተ እየተባባሰ መጠቷል። እንዴት ነው በሕዝቦች መካክል ቅራኔ ሳይፈጠር በጋራ መኖር መዝለቅ የሚቻለው…” እያለ ለመመካከር ነው የተራሁዋችሁ እንነጋገርበት..ነው የሰበሰብኳቨችሁ…… “ ሲል በዚህ ንግግር መድረኩን ከፈተላቸው።

የሚገርመው ደግሞ እርሱ ግጭቱ የሚለው (እኛ ዘር ማጥፋት የምንለው) በሕዝቦች መካከል እንደሆነ ነው እየነገረን ያለው፡ (በሁለቱ ሕዝቦች እና በሁለቱ ክልሎች መካክል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በነሱ ምክንያት በሌሎች ሃይሎችም ምክንያት “መቃቃር፤ጸብ ግጭት፤ የሰዎች ህይወት መጥፋት እየተባባሰ ..) ለጭፍጨፋው ምክንያቶች ሥርዓቱ (ዘርን መሰረት ያደረገ አስተዳደር) እና በሥርዓቱ ውስጥ ያሉ ባለሥልጣኖች በሚያደርጉት ድጋፍና ቀስቃሽ የጥላቻ ንግግር እንደሆነ አያምንም። የጭፍቸፋው ምክንያት ሕዝብ ነው ብሏል (ሌሎች የሚላቸው ምክንያቶች አልገለጸም/አልፈለገም)። የሚገርመው ደግሞ ዛሬ እንደ ዋዛ እየሞተ ያለ ሕዝብ ‘እናንተ እርስበርሳችሁም ሆነ የክልሉ ሕዝቦች ብሶት ስለማትተዋወቁ’ ምናልባት አንዱ ወደ አንደኛው ክልል ቢሄድ እዛ ያለው ስሞታ ይረዳል ሌላኛውም እንደዚያ ቢሆን እርስ በርሳችሁ ብተዋሃዱ ‘ሞት’ ማስቀረት ይቻላል ብሎ እርፍ!
ልብ በሉ “መቃቃር፤ ጸብ ግጭት፤ የሰዎች ህይወት መጥፋት እየተባባሰ መጠቷል። “ዋዛ” የሚለው ቃል የተጠቀመበትን አጠቃቀም፡ (“የዘር ጭፍጨፋ/ጀነሳይድ” እንዳይለው  “እንደ “ዋዛ” ወይንም “ግጭት” በሚል አቃልሎ ነው የሚገልጸው፤ የዋዛ ትርጉሙ ቀልድ/ግደየለሽነት/ ማለት ነው። እየተጨፈጨፈና እያተረደ ያለው ሕዝብ  ‘በዋዛ ፈዛዛ’ ሳይሆን በጥንቃቄ ተጠንቶ፤ ሆን ተብሎ፤ ክርስትያኑ እና አማራው እንዲሁም ጋሞውና ወዘተ… ማሕበረሰብን ያነጣጠረ የዘር ጭፍጨፋ ነው)
በደቡብ ሓረርግ እመጫቶች (ያውም ሁለት ነብስ) እና ህፃናት ሲጨፈጨፉ ፤ቤተክርስትያናት ሲቃጠሉ ሰዎች በዘራቸው በሜጫ እና በቢላዋ ሲታረዱ/ሲሰቀሉ መነሻው ስርዓቱ የተዋቀረበት አስተዳደራዊ ስልጥ ነው።

አብይ አሕመድ መናሻና መፍትሄ ብሎ የሚማጸነው ተቃዋሚው በየክልሉ እየሄደ የሕዝቡን ብሶት ስለማያዳምጥ/አውቀት ስለሌላው ወይንም ሁለቱም ድርጅቶች ባንድ ፓርቲ ስላልተደመሩ ነው….. ብሎ ሲያሾፍ ማድመጥ፤ አንድም ይህ ሰው ለ18 ወራት የመንግሥትን አሰራር ምንም አልተማረም ወይንም ሆን ብሎ እያሾፈ ነው ማለት ነው። እነዚህ ሰዎች እኮ ይተዋወቃሉ! ብርሃኑ ነጋ እና እነ ሌንጮ ባቲና ሌንጮ ለታ አብረው በ አለማቱ ሲዞሩ የነበሩ ናቸው። በቀለ ገርባና እስክንድር እኮ አብረው ታስረው አብረው አብረው ተነጋግረው መፍትሄው ይህ ነው ብለው ተስማምተው ነበር። መጀመሪያ ከዚያ ሁሉ ወንጀለኞችን ለሕግ አቅርቦ ማስቀጣት ፤ዕርቅ ማውረድ. ኑዛዜ መናገር፤ከዚያ መተዋወቅ ይመጣል። ገዳይ፤ አስገዳይ እና ተገዳይ ባንድ ጠረጴዛ ቁጭ በሉ ብሎ ተደመሩ ማለት ቀልድ ነው።

መጀመሪያ ተቃዋሚው  ተዋሃደም አልተዋሃደም ወሳኝ አይደለም። የችግሩ ምንጭ አብይ እና አብረውት ያሉ የፍትህ አካለትና ባለስልጣኖች እንዲሁም አብረን እንሰራለን የሚላቸው አክራሪ ሃይሎች ተይዞ ሰላም አይመጣም።እራሱ አብይ ሰላምና ሕግ ማስከበር አልቻለም።ኦሮሞ ኦሮሞን አያስርም፤አይገድልም የሚል እምነት ስላለው አክራሪ ኦሮሞን መቆጣጠር አይፈልግም።
 ሽብርተኞች አገሪቷን በተቆጣጠሩዋት ወቅት ፤ ተቃወሚውም ሆነ ዜጎች ከከተማ ወደ አንድ ከተማ በሰላም መሄድ የማይቻልበት የሥርዓተ አልባ ዱርየ የሰፈነበት ወቅት ነው አሁን። ሌላ ቀርቶ እንኳን ከቦታ ቦታ ለመዘዋር፤ በምትኖርበት ገጠርና ከተማ ህልውናህ በሜንጫ የምታጣበት በስጋት በታጠረበት ኑሮ እንዴት ብሎ ነው የነዚህ ተቃዋሚዎች “መደመር” የክልሎችን ሕዝብ ብሶት ሊያደምጡ የሚቻላቸው? ስለዚህ እየታየ ያለው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በፓርቲዎች የተነሳ ነው እንጂ በመንግሥቱ ስልተና አወቃቀር አይደለም እያለን ነው። የራሱን ፖሊሶችና ዳኞች ሳይቆጣጠር ወደ ፓርቲዎች ፕረፓጋንዳ መሄድ ፌዝ ነው።

 ያውም እራሱ አብይ እንኳ ወለጋና ባሌ እንደ ልቡ መሄድ የሚሰጋ መሪ ባለበት አገር! እንደው ለመሆኑ፤ተቃዋሚው የሕዝቡ ብሶት ስለማያውቅ ነው ይህ ሁሉ ጭፍጨፋ እየተካሄደ ያለው? ተቃዋሚው ለየብቻ ሆኖ ስለታገለ (ስላልተደመረ) የዘር ጭፍጨፋው እንዴት ሊከሰት ምክንያት ይሆናል? ወይንስ እነሱ ምን ጉልበት አላቸውና ነው ጭፍጨፋውን ሊያስቆሙት የሚችሉት?

የሕዝቡ ብሶት ቢያስሰማም እኮ አብይ እራስህ ብሶትህን አልሰማም አታልቅስ አልሰማም “አልቃሽ ሕዝብ” የትም አይደርስም ብለህ ብሶቱ እንዳይናገር አዋርደኸዋል። ሓኪሞችን፤መምህራንን ሰደብክ ፤ ደሞዝ ይጨመርልን ኑሮ ከበደን ላለ ሁሉ “መፈንቅለ መንግሥት ነው” ብለህ አወገዝካቸው፡ ማን ቀረህ? እስኪ ያንተን ንግግር ልጥቀስና አንባቢዎች እውነቱን ይፍሩ፤
እንዲህ ስትል የነበረውን ታሪክ የመዘግበውን ላቅርብ፦
እንዲህ ይላል አብይ_
“ ኦሮሚያ ስታናግሩ እኛ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እንታያለን; እንደ አንደኛ ዜጋ አንታይም፡ አሁን  አማራ ጋር ብትሄዱ እንደ አንደኛ ዜጋ አንታይም እንደ ሁለተኛ ዜጋ ነን የምንታየው፡ አሁን ትግራይ ጋር ብትሄዱ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እንጂ እንደ አንደኛ ዜጋ አንታይም…….ሁሉም ሰው አንደኛ አይደለሁም፤ አንደኛ ሌላ ነው ይላል።

“ …….በቲቪ ሰምታችሁ ይሆናል፤ ሁሉም ቦታ ዞሬአለሁ፤ ሁሉም የሚለው እንደ እኛ የተበደለ የለም ነው። ሁሉም ክልል ስብሰባ ነበረኝ፤ ሁሉም ክልል የሚሉት “ሥልጣን የለንም” ነው።  ግማሹ አምባሰዳር ሥልጣን የለም፤ግማሹ ዋና ዋና ሚኒስትሩ ላይ ቦታ አልተሰጠንም፡ ግማሹ በጀት ላይ ተበድለናል፤ ይላል። አንድም ሰው የሚያመሰግን የለም።

ከእስላም አፍ አሓምዲላህ ተወስዶበታል፡ የለም፡  ከክርስትያናትም ማመስገን የሚባል የለም ማለቀስ ብቻ! አልቃሽ ሕዝብ ደግሞ አይሻገርም!
ችግር እያለ ችግሩን ለመፍታት ካላሰብን በቀር ‘ችግር’ ንገረኝ ካላችሁ እማ እንግዲህ ይኼው ‘’10 ወር ሙሉ አንድም ቀን ዕረፍት የለኝም፤ እያመመኝ ሕክምና መሄድ አልቻልኩም፤ ደሞዜ ትንሽ ነው፤ ኢትዮጵያን ማልማት እፈልጋለሁ ግን እናንት ግብር አትከፍሉም፤ ሥራየ እንዳልሰራ በየቦታው ክላሽ እየተኮሳችሁ ትበጠብጣላችሁ፤ እናንተን እያረጋጋሁ ሥራ ልሠራ አልቻልኩም፤… ልቀጥል..? ….፡(እዚህ ላይ አዳራሽ ውስጥ ተጋብዞ ንግግሩን ሲያደምጥ የነበረ ‘ከብት’ አድመጭ ጭብጨባ ሲያቀልጥ ይደመጣል)፤

 ከጭብጨባው በሗላ ንግግሩን በመቀጠል አሁንም እንዲህ ይላል፤-

“…ሕዝብ ሰላሙን ካልጠበቀ፤ አሁን ይህ ሁሉ ለቅሶ ብትሰሙት፤ ትናንትናም ብዙ ለቅሶ ስሰማ ነበር፤ አሁን እናንተን ሸኝቼ አዲስ አልቃሽ  ይመጣል፤ ያለቅሳል፡ የኔ ሥራ “ሶፍት” (ቲሹ) ይዞ መቅረብ ብቻ ሆነ።….’
ተመለክቱ  ዓፋር ሰላም ነው፤ ኢሳ እየረበሸው እንጂ፤ ሶማል ሰላም ነው ኦሮሞ ሚረብሸው እንጂ፤ ኦሮሞ ሰላም ነው አማራ እሚረብሸው እንጂ ፤አማራ ሰላም ነው ኦሮሞ ሚረብሸው እንጂ… ሁሉም እንዴት እንደዚህ ይሆናል?  እኔ ስገፋው እሱም ይገፋል፡ የለም ኢትዮጵያ ውስጥ ይኼ ? አንገፈፋፋም? ሁላችንም ሓለፊነት ካልያዝን በሚቀጥለው አመትም  አደራችሁ ለከርሞም መሐረም ይዛችሁ  እንዳትመጡ።  
“…ዓፋሮችና ኢሳዎች ወንድም ከወንድሙ ጋር ይጣላል፤ይጋደላል፤ ሃይማኖታችሁ ካልገዛችሁ እኔ ምን ላደርጋችሁ ነው?”
 በማለት ሓለፊነቱን ረስቶ “አላህን ካልፈራችሁ መንግሥት ምንም አቅም የለውም” እዛው ተላለቁ በማለት የሓላፊነት ትርጉም ሳይገባው ሕዝቡ ለእልቂት አጋልጦታል። ያ ስለሆነም፤ ባለፈው ወር ዓፋሮች ከጂቡቲ/ከሶማሌ/ጀቡቲ የመጡ ኢሳዎች (አልሸባቦች) ሕዝቡን አርደው ጨፈጨፉት። መከላከያ የሚባል ፍፁም ለሽታው ድምበሩ ላይ አልነበረም። ልክ አብይ እንዳለው ቃሉን አክብሮ  “እኔ ምን አደርጋችሗለሁ” ብሎ ለጥቃት አጋለጣቸው። ዓፋር ላይ በዚህ ወር የደረሰው ጭፍጨፋ ዜናውን ሰምታችሗል አደለም? አዎ፤

በመጨረሻም ያ ሁሉ ምን ላደርጋችሁ ነው የምታለቃቅሱብኝ ብሉ ሲሳለቅ ይቆይና “ሓለፊነቱን የሚወጣ ወሳኝ ሰው” ይመስል እንዲህ ይላል።

“….በለቅሶ ብዛት ሐገር አይገነባምና  ሓለፊነት የምንወስድ ሕዝቦች፤ ሰዎች መሆን መለማመድ አለብን፤ ሓላፊነት የማይወስድ መንግሥት፤ ሓላፊነት የማይወስድ ሕዝብ ችግር ሊፈታ አይችልም። ምክንያቱም ችግር መፍታት መወሰን ይጠይቃል፤ ከወሰናችሁ ደግሞ ተጠያቂነት ይመጣል። ለዚያ የተዘጋጀ አመራር፤ ለዚያ የተዘጋጀ ሕዝብ መሆን አለብን።”
 ሲል ወሳኝ እና ሓለፊነት የሚሰማው መሪ ይመስል እራሱን በከንቱ ሲያመጻድቅ ማየት እኛ ትግሬዎች ከመገረም አልፈን መርመም የምንለው የመጨረሻ የመገረም ስሜት ያስገባል።

 ለ27 አመት ሲዶቆስ የነበረ ሕዝብ አልቃሽ፤ሓለፊነት የጎደለው እያለ ራሱን ሳይወቅስና ለፍርድ ሳያቀርብ፤ ሰላመዊ ሰዎችን በሽብር እየከሰሰ፤ እርጉዞች ጭለማ ክፍል አስግብቶ ጽንስ እስኪያስወርድ ድረስ የሚበቀል በቀልተኛ መሪ ምንም ሳያፍር ሕዝብን “የኔ ስራ ‘ቲሹ/ናፕኪን’ ይዞ መምጣት ሆኗል” እያለ ባልዋን ያጣች ልጇ የታረደባት እናትን “አልቃሽ” እያለ በቁስሉ ላይ ጨው ሲነሰንስ መስማት ይገርማል።

የሆኖ ሆኖ ሕዝብ ክርስትያን ቤተጸሎትህ ተቃጥሏል፤ ምዕመናኖች ታርደዋል፤ ሰንደቃላማህ ከከበሮህ ተነጥቀሃል፤ ማተብህ እንድትበጥሰ የግራኝ አሕመድ ዘመን መጥቶብሃል (ጀግናው አሳምነው ጽጌ የተናገረው ልክ ነበር)፡ “ከክርስትያኑም መንግሥት ያደረገለትን ለአምላኩ የማያመሰግን ምስጋና ቢስ የሆንክ ማልቀስ ብቻ! አልቃሽ ተብለሃል፡ አልቃሽ ሕዝበ ክርሰትያን ደግሞ አይሻገርም! ተብለህ ተዘልፈሃል! ክርሰትያን ሆይ አሁንስ ማልቀሱን አቁመህ አልቃሽ የሚልህን መንግሥት ተብየው መሪ መልስህ ምን ይሆን?
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)


No comments: