Monday, November 25, 2019

ይኼ ነው ባንዴራው! የትኛው? የሻዕቢያ? ንገሩን እንጂ የአዲስ አበባ የየካ ወጣቶች? -ከጌታቸዉ ረደ Ethio Semay ኢትዮ ሰማይ 11/24/2019


ይኼ ነው ባንዴራው! የትኛው? የሻዕቢያ? ንገሩን እንጂ የአዲስ አበባ የየካ ወጣቶች? -ከጌታቸዉ ረደ Ethio Semay ኢትዮ ሰማይ
11/24/2019


ባለፈው ሰሞን አዲስ አበባ ውስጥ ለአካል ማጠንከሪያ ተብሎ የተዘጋጀው የሩጫ ዝግጅት የታዘብኩት አስገራሚ፤አሳፋሪ ትዕይንት አይቼ ለመተቸት እመለሳለሁ ብየ በወቅቱ አንዳንድ ጉዳዮች ስለነበሩኝ በይደር አቆይቼው ነበር። ዛሬ አጠር ባለቺው ይህችን ጥያቄ ለአዲስ አበባ የየካ ወጣቶች ያቀረብኳትን ጥያቄ እንዲመልሱልኝ የፌስ ቡክ ወዳጆች በተቻላችሁ መጠን አዲስ አበባ ድረስ እንዲሰራጭ “ሼር” (በመቀባበል) ጥያቄየን እንድታስተላልፉልኝ እጠይቃለሁ።  የኢትዮጵያ ወጣት ለ27 አመት የሃገሪቱን ታሪክ እና ተጋድሎ እንዳያወቅ በተከለሰ የጠላት ቅስቀሳ ተሞኝቶ በመቆየቱ ወቅቱ የማስተማርና የማነቃቃት ወቅት ነውና ‘ታሪክን ሪክለይም’” ታሪክን ቦታው ላይ ለማስቀመጥ እንዲመች ይህንን ጥያቄ ሁላችሁም ተቀባበሉትና አድርሱልኝ።  


አስቀደድሜ እንደጠቀስኩት ከታች ተያይዞ የቀረበው ቪዲዮ ውስጥ በዚህ የከተማ የሩጫ ዝግጅት ላይ በርካታ ወጣቶችና የውጭ አገር ዜጎችም ተካፍለዋል። በዚህ ሂደት የታዘብኩት ሁለት እጅግ ቅር ሚያሰኙ ክስተቶች ታዝቤአለሁ።

1)     አንደኛ በሴራ የተገነጠለቺውና የባሕር ወደብ እንድናጣ የተደረገበትን የኢትዮጵያን ሉኣላዊ መብት በሚሽርና በሚጻረር ውሳኔ የትግሬ ወያኔዎች በመሪነት የተካፈሉበት ሕገወጥ የግንጣላ ሴራ ያስገነጠልዋትድሮ የኢትዮጵያ አውራጃ የነበረቺው “ባሕረ ነጋሽ” (በጣሊያኖች አጠራር ”ኤርትራ”) የምታውለበልበው ሻዕቢያ የፈጠራት መለያ ባንዴራ የየካ ወጣቶች በኩራትና በክብር እያውለበለቡ “ይኼ ነው ባንዴራው” እያሉ እነሱም ከወያኔዎች እና ሻዕቢያዎች እኩል የጠላታችንን ባንዴራ እያውለበለቡ ዓለም የተዘበውን እኛ ያፈርንበትን አሳፋሪ ድርጊታቸውን ታዝቤአለሁ።

2)    የሩጫው ደመብልብስ የሆነው ጎመናዊው ሕብረ ቀለም ከናቴራ  የለበሱ (ምናልባትም የቄራ መንጋ ሳይሆኑ እንዳልቀረ የሚገመቱ) ወጣቶች ዜጎች በሚገበያዩበትና በሚንሸራሸሩበት ወይንም በሚኖሩበት መኖሪያ ቤቶች መደዳውን ሆን ተብሎ በርካታ ወጣቶች አጠር ላይ ሽንታቸውን ሺሸኑ በቪዲዮ የተቀጸው ፎቶግራፍ እንዳያችሁት አምናለሁ። እነዚህ ሁለት አሳፋሪ ስነምግባሮች ባጭሩ ልተች።

ተሰላፊዎቹ በጭፈራ እና በኩራት እየቦረቁ ሲያውለበልቡዋቸው የነበሩ ሁለት ምልክቶች አንደኛው የአገራችን ሰንደቅአላማ ሲሆን ሁለተኛው የሻዕቢያ ባንዴራ ነበር። መፈክራቸውም “ይኼ ነው ባንዴራው! እያሉ ነበር። እኔም ሆንኩኝ በሚሊዮኖች የምንቆጠር ዜጎች ለነዚህ ወጣቶች የምናቀርብላቸው ጥያቄ  የትኛው? የሚል ነው።

መልሳቸው ግልጽ ነው፤፡ “የሻዕቢያብለውናል። ይኼ ነው ባንዴራው ብሎ ኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ሲያሳይ ቆይቶ የአገር ገንጣይ የሆነቺው ወላጆቻችንና ወንድም እህቶቻችንን ደም ያፈሰሰቺው የጠላታችን የሻዕቢያ ባንዴራ አዲስ አበባ ውስጥ እያውለበለበ ይኼ ነው ባንዴራው እያሉ የጀግኖችን አገር የዘለፉ ወጣቶች ትንሽ ሓፍረት አልተሰማቸውም። ግብዝ ትውልድ ሁሉንም ያኝካል፤ወላጆቻቸውንም ያስቆጣል። ወላጅ ጀግና፤አገር ቢቆጣ ባይቆጣ ለነሱ ጉዳይ አልነበረም። የ27 አመት አዲስ ትውልድ አገሩን አላወቀም። ስለሆነም ሁሉንም ማግበስበስ ተያይዞታል። ሰውን ከነ ነብሱ ከፎም ሆነ ወደ ገደል ገፍትሮ  መግደል፤ የሴቶች እህቶቻችን እና እናቶች ጡትና አንገት መቁረጥ ነውር ሆኖ አላዩትም።


ሲደሰቱ  እየጨፈሩ የሚረግጧት ሲደክማቸው የሚያርፉባት ድንግል የኤትዮጵያ መሬት ያስረከበቻቸው ይህች ሰንደቅአላማ መሆኗን ዛሬም ብዙዎቹ ወጣቶች ልብ አላሉትም። ዓለም የሚያውቃት ሕብርዋን ከተለጠፈችበት ህንጻዎችና አብቶብሶች በምላጭ እየፋቁ የሰንደቅ አላማን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት እየሰሩ ያሉ ትናንት የተወለዱ “ሱሬአቸውን ቀበቶ እንኳ በቅጡ ማሰር የማይችሉ” የቆሙበት መሬት የት እንደሆነ የማያውቁ ወጣቶች እንዲህ ያለ እጅግ የሚያስቆጣ የውጭ ጠላት አድርጎት የማያውቅ ድርጊት እያደረጉ ስንመለከት፤ እኛ ለዚህ አገር የሞትንላት፤ያለቀስንላት እና ተራራ እና ሜዳ ሸንተረሩ በሕክምን፤ በጠምነጃ ፤በማስተማር፤በግብርና ፤በንገድ በባልትና እና በዲፐልኦማቲክ ሥራዎች ጥረን ግረን ያቆየንላቸውን አገርና ሰንደቅአላማችንነ ሲያዋርዱ ማየት ምነው ይህንነ ሳናይ በሞትን።

ባንፈጠር  ከዜጎች ትክሻ  መንጠቅ ነውር አድርጎ አልተመለከተውም።

አገር ሁሉንም በማግበስበስ አይቀናም፡ የሻዕቢያ ባንራ እያውለበለብክ የኼ ነው ባንዴራው ስትል በሚሊዮን የሚቆጠሩ የወታደር ቤተሰቦች ምን እንደሚሰማቸው ወጣቶቹ የገባቸው አልመሰለኝም።;ይህንን ሲያደርጉ ሊያስተላልፉት የፈለጉት መልዕክት ትርጉሙ ምን ማለት ነው? ዛሬ የሻዕቢያ ነገም የግብፁ የአልሲሲ ወኪሎች” ሲሰብኩዋችሁ የኼ ነው ባንዴራው ብላችሁ ከቦረቃችሁ ቀጥሎ የጣሊያን ባንዴራ፤ከዚያም የአልሸባብ ባንዴራ እንደማታውለበልቡዋቸው በእርግጠኛነት መናገር አይቻልም። እጅጉን አፈርንባችሁ! እጅጉንም ተቆጣን።

ለኢትዮጵያ ሰንደቅአላማ ሲሉ አካላቸው የጎደሉ ከዚህ ጽሑፍ ጋር የተያያዘው ፎቶግራፍ ተመለክቱዋቸውና እናንት በኢትዮጵያ ሰማየ ሰማያት እየዘለላችሁ የሻዕቢያ ባንዴራ እያውለበለባችሁ ስትቦርቁ የተመለከተች የነዚህ ጀግኖች ዓይን ምን እንደሚሰማቸው በሕሊናችሁ አምጡና ስሜታቸውን ተጋሩዋቸው። እንደተዘለፉ እንደናቀሁዋቸው ይቆጫቸዋል! ያልቀሳሉ! አዲስ አባባ ውስጥ በገዛ አገሬ ይህንን ውርደት ለማየት ነበር ወይ እግሬን   ይኔን ያጣሁት? ብለው ይጠይቁዋችሗል። “ይኼ ነው ባንዴራው” ብላችሁ ስታባሰጭዋቸው “የትኛው” ብለው ሲጠይዩዋችሁ ምን መልስ አላችሁ?


በዚህ አስለቃሽና አሳዛኝ አበሳጭ ታሪክ ልተዋችሁና ወታደሮቹ ለምን እንዲያ ያለ ኢትዮጵያዊ እልህና በአሳዛኝ እልቂት እንደተጎዱ ከዚህ የዓይን ምስክርነት ፤ላስነብባችሁና  መልስ ስጡ፡
 ይኼው ታሪኩ፤- በጥሞና አንብቡት (በተለይ ወጣቶች!!!!)


ከተረሱት ጀግኖቻችን ማህደር -አይ ምፅዋ !ሞት የተፈረደባቸዉ 17ሺህ የኢትዮጵያ ሠራዊት ደራሲ (ታደሰ ቴሌ ሰልቫኖ) (የብዕር ሥም)
 (ከ7 አመት በፊት በኢትዮ ሰማይ ድረገጽ -ጌታቸዉ ረደ TUESDAY, APRIL 3, 2012 የተለጠፈ) ሙሉውን ታሪክ ለማየት https://ethiopiansemay.blogspot.com/2012/04/blog-post_3.html መግባት ይቻላል። ባጭሩ ቀንጭቤ ላቅርብ፤፡ ይኼው


ሰዓቱ ለካቲት 9 አጥቢያ ከንጋቱ 1130 ሰዓት ነበር።በሁሉም አቅጣጫዎች የአብዮታዊ ሠራዊት አባላት በከባድ ጀግንነት ከሻዕቢያ ጋር በጥይት፤በእጅ ቦምብና ላዉንቸር ተጨፋጨፈ። መሬቱ እየነጋ ሲሄድ የምፅዋ ከተማ በአስከሬን ክምር፤በሰዉ ሥጋ ብጥስጣሽና በደም ጎርፍ ጨቅይታለች፡ ድመትና ዉሻ የመረጡትን አስከሬን ይጎትታሉ።አንዳንድ ቦታ ደግሞ የሰዉ እስከሬንና የዉሻ ሬሳ ጎን ለጎን ተኝቷል። በጣም የሚዘገንን ዕልቂት ነበር። የከባድ መሣሪያ ጥይት የቆራረጠዉ ሰዉ አካል በየቦታዉ ዕጣ ያልወጣለት የቅርጫት ሥጋ መደብ መስሏል……….



ጎበዝ ስሙኝ! ይህ አደራ መልዕክቴ ነገ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይደርስ ይሆናል። ምናልባት አምለክ ካለ ከእናነተ አንዱ መልዕክቴን ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት አደርስ ይሆናል። ዛሬ ሻዕቢያ ምፅዋን ተቆጣጥሬአለሁ በማለት የዓለምን መገናኛ ብዙሃን እንደሚያጨናንቅ ጥርጥር የለዉም። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ሀግርና ሕዝቧ ትልቅ አደጋ ነዉ። በቀይ ባሕር በራችን በኩል ብዙዉን ጊዜ ወረራ ፈጽመዉብን በተደጋጋሚ የሳፈርናቸዉና ፊት ለፊት ያልቻሉን ምዕራባዉያን ሀገሮችና ዓረቦች ዛሬ የሻዕቢያን ጊዜያዊ ድል ሰምተዉ ይፈነጥዛሉ።




 ምናልባትም የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ድንበር የሆነዉንና ለዘመናት በአባቶቻችን የደም ዋጋ ፀንቶ የቆየን የባሕር በራችንን በመዝጋት እንዲሁም ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ባሕር አይደለም በማለት በምድር ተወስነን እንድንቀር ይደረግ ይሆናል። ይህ ደግሞ የሞት ሞት ነዉ።ይሁን! ምንም ማድረግ አልችልንም። ሁሉም ነገር ከቁጥጥሬ ዉጭ ሆኗል። ከሙታን ዓለም መጥቼ ማረጋገጥ ባልችልም የፈለገ ጊዜ ይጠይቅ እንጂ ጀግናዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የባሕር በር አልባ ሆኖ ፤በኢምፔርያሊስቶችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸዉ ተሸንፎና እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም። ይህ ከሆነማ የአፄ ዮሐንስ የቀይ በሕር ተጋድሎ እና የጀግናዉ ራስ አሉላ አባነጋ አጥንት እንዲሁም የእኔን ጨምሮ የአበዮታዊ ሠራዊት አባላት አጥንትና ደም የኢትዮ ያን ትዉልድ ሁሉ እሰከዘላለሙ የፋረዳል። ኢትዮጵያ ሀገሬ የጀግኖች መፍለቅያና ገናና ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በመሆኑም ጀግናዉ ሕዝቧ ሕዝባዊ የባሕር በሩ በሻዕቢያ ተይዞና የጠላቶቹ መፈንጫ ሆኖ አይኖርም። የፈለገ ጊዜ ይቆይ እንጂ ሻዕቢያ ምፅዋን እንደያዛት ለዘላለሙ አይኖርም ጊዜዉ ጠብቆ የኢትዮጵያ ጀግና ጠላትን ደምስሶ ምፅዋን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚያስረክብ እምነቴ የፀና ነዉ።



አሉና ትንፋሽ ዋጡ: የትንሽ ፋታ ወሰዱ። የጀኔራል ተሾመ ዓይን የቆሰለ የነብር ዓይን መስሏል፡ ከንፈራቸዉ በዉሃ ጥም ደርቆ ቅርፊት ይዟል። ፊታቸዉ በደረቅ ላብ ዥንጉርጉር ሆኗል። ሆዳቸዉ ከወገባቸዉ ተጣብቋል። በተሰበሰበዉ አባል ዉስጥ በሰፈነዉ ጸጥታና ዝምታ መሃልእናንተ አብየታዊ መኮንኖች ባለሌላ ማዕረጎች! ስሙኝ አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ።አሉ ጀኔራል ተሾመ ቆጣ ብለዉ።አንድ ሰዉ ቤት ሲሰራ የሚሠራዉ ቤት በርና መስኮቶች አሉት። አንድ ሰዉ ደግሞ ሞተ እንበል። መቃብር በርና መስኮት የለዉም። በርና መስኮት የሕይወት ምልክቶች ናቸዉ። በመሆኑም ያለሀገር ነፃነትና ያለባሕር በር ብልጽግና ስለሌለ የኢትኦጵያ ሕዝብ የባሕር በር ተነጥቆ የሚኖር ሕዝብ አይደለም። ከሻዕቢያ ጀርባ ሆነዉ ቀይ በሕር የኢትዮጵያ አይደለም የሚሉ ሀገሮችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸዉ ሁሉ በቀጥታም ሆኑ በተዘዋዋሪ ፍላጎታቸዉ ኢትዮጵያ ሞት ነዉ።



ይህ ምሳሌ ከገባችሁ የባሕር በር የሌላት ሀገር ሞቶ ከተቀበረ ግለሰብ የምትለየዉ በትንሹ ነዉ። ምክንያቱም የባሕር ሀብት ከማጣቷ በላይ ምርቷን ወደ ዉጭ ለመላክ የግዴታ ወደብ ስለምትከራይ ለወደብ ክፍያ የምትከፍለዉ የገንዘብ ዉጭ ዜጎቿን ያደኸያል። በአኳያዉ ጠላቶቿን ባለወደቦቹን ያበለጽጋል። ይህ ዕድል ለኢትዮጵያ እንዳይደርሳት ቀይ ባሕር የኢትየጵያ ትዉልድ ይፋረድ።፡ቀይ ባሕር ለእኔ ዘላለማዊ ቤቴ እንዲሆን ወስኛለሁ። ደስተኛ እና ዕድለኛ ጀኔራል ነኝ። እኔ ብሞት ታሪኬ አይሞትም። የእኔ ታሪክ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሕሊና ዉስጥ እንደሚኖር አምናለሁ። ቻዉ! ቻዉ!ቻዉ!” አሉና ጀኔራል ተሾመ ፤መኮንኖቹን ከሰበሰቡበት ቦታ ተፈናጥረዉ ወደ ቀይ ባሕር ጠረፍ አመሩ። የባሕሩ፡ጠረፍ ከስብሰባዉ ቦታ በግምት ከስልሳ ሜትር አይበልጥም። በፍጥነት ወደዚህ በሕር ጠረፍ ገሰገሱ። ክላሺንኮቭ ጠመንጃዉን አቀባብለዉና አዉቶማቲክ ላይ አድርገዉ በቀኝ እጃቸዉ ጨብጠዋል፡ከምፅዋ ወደብ በስተቀኝ ከሚገኘዉ ወታደራዊ ወደብና መደብር ላይ ሲደርሱም ለቀይ ባሕር ዉሃ መገደቢያ በተሰራ ግንብ ጠርዝ ላይ ጀርባቸዉን ወደ ቀይ ባሕር ፊታቸዉን ወደ ምፅዋ ከተማ አድርገዉ ቆሙ። ቀጥሎ በእጃቸዉ የነበረዉን ክላሺንኮቭ ጠመንጃ ወደ ቀይ ባሕር ወረወሩት። ከዚያም በወገባቸዉ ታጥቀዉት የነበረዉን ኮልት ሽጉጥ አወጡና የሽጉጡን አፈሙዝ በአፋቸዉ ጎርሰዉ የካቲት 9 ቀን 1982 . ከጥወቱ 210 ሰዓት ሲሆን ቃታዉን ሳቡት። የሽጉጥ ቶክስ ድምፅ እንደተሰማ ወደ ጀርባቸዉ በቀይባሕር ዉሃ ላይ ወድቀዉ ሰጠሙ። ከጭንቅላታቸዉ የሚፈስ ደም በቀይ ባሕር ዉሃ ላይ ቀልቶ ይታይ ነበር።



ወዲያዉም ይህን የጀኔራል ተሾመ ሞት በምስክርነት ቆመዉ ከአዩት መካከል 150 የማያንሱ የጦር መኮንኖች ባለሌላ ማዕርጎች በሽጉጥ፤ በእጅ ቦምብና በክላሽ ጠመንጃ ሕይወታቸዉን አጠፉ። ከእነዚህም መካከል ሻለቃ ሮሪሣ ዳዲ በእጅ ቦምብ፤ሻምበል ሸዋንታዮ ዓለሙ በማካሮቭ ሽጉጥ፤ሻምበል አዲሱ በማካሮቭ ሽጉጥ፤ሻምበል ባሻ አማረ ናጂ በክላሽ፤ሻምበል ወንድወሰን በሽጉጥ የሃምሳ አለቃ ፈቃዱ ቦጋለ በክላሽ፤ወታደር ሽንገረፋ በክላሽ ሕይወታቸዉን አጠፉና በስም የሚታወሱ ናቸዉ። ሌሎችም በብዛት ራሳቸዉን ገድለዋል። በአጭር ደቂቃ ዉስጥ አካባቢዉ ሬሳ በሬሳ ሆነ።



ሌሎች ደግሞ ሻዕቢያን ገድየ መሞት አለብኝ እያሉ ወደ ጠላት ወረዳ በመገስገስ ገድለዉ የሞቱትም ነበሩ። ወደ ጠላት እየሮጡ በእጅም በቦምብም ታንክ ተሽከርካሪዎችን እያቃጠሉ ራሳቸዉን የገደሉ በሻዕቢያም የተገደሉ ጥቂት አልነበሩም።ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ 3 ሜካናይዝድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ከጀኔራል ተሾመ፤ከሌሎች መኮንኖችና ባለሌላ ማዕረጎች ሞት በሗላ የተረፉትን አሰባስበዉ የሻዕቢያን ከበባ ሰብሮ ለመዉጣት ሞከሩ።




 የአምሳ አለቃ ታደሰን (ደራሲዉ) እና 300 ያላነሱ የአብዮታዊ ሠራዊት በቀጥታ በመምራት ከምፅዋ ከተማ ዋናዉን የመኪና መንገድ ይዘዉ አዋጉ። ዉጊያዉ ከባድ ዕልቂት አስከትሎ ነበር። ሸዕቢያን እያባረሩ እየገደሉ ፤ሻዕቢያም የአብኦታዊ ወራዊት አባላትን እያባረረ እየገደለ የእጅ በእጅ ዉጊያ ጭምር ተደረገ። የኮሎኔል በላይ ሠራዊት በዚህ መራራ ፍልሚያዉ ከምፅዋ ዓለም አቀፍ ወደብ በግመት በሁለት ኪሎ ሜትር ርቃ ወደ ምትገኘዉ በረዶ ፋብሪካ ወይም ጠዋለት ወደተባለችዉ የምፅዋ ክፍለ ከተማ 70 ደቂቃ ዉጊያ በማድረግ ሻዕቢያን ሰብሮ ለማለፍ ቀይ በሕር ሆቴል ደረሰ። ግማሹ ሃይልም ቀይ ባሕር ሆቴል ያዘ።ይሁን እንጂ በዚህ አካባቢ የተከማቸዉ የሻዕቢያ ሃይል በጣም ብዙ ስለነበር የሠራዊቱ ሙከራ ተገታ። ሻዕቢያን ሰብሮ ወደ ዕዳጋ ከተማ ለመሻገር አልቻለም። በዚህም ሁለተኛ ትራጀዲ ተከሰተ።




ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ለብሰዉ ከቀይ ባሕር ሆቴል በረንዳ ላይ በአንዲት ጥልፍልፍ የቃጫ ወንብረ ላይ ተቀምጠዉ አጠገባቸዉ ለነበሩት ጥቂት አባላት መልዕክት ያስተላልፋሉ።ጀግና ቢሞት በእልፍ እአላፍ ጀግና ይተካል።የእኔ ታሪክ ለትዉልድ ይቀራል። ታሪክ ይናገራል እንጂ እኔ አልናገርም።የምትል መልዕክት ነች። መልዕክታቸዉም አንደጨረሱ ፊታቸዉን ወደ ምፅዋ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስትያን አዙረዉ አማተቡና የክላሽንኮቭ ጠመንጃቸዉን አፈሙዝ ጎርሰዉ ቃታዉን ሳቡት። ለጥቂት ሰኮንዶች አዉቶማቲክ ክላሽንኮቭ ድመፅ አስተጋባና ፀጥታ ሆነ።



ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ ክላሽንኮቭ ጠመንጃቸዉ እንደያዙ ወንበር ተደግፈዉ ተዝለፍልፈዋል። የለበሱት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ባንዴራ በላያቸዉ ላይ ደምቆ ይታያል።ይህነን ትዕይንት ሻዕቢያ በፎቶግራፍ አንስቶታል። በቪዲዮ ካሜራም ቀርጾታል፡ የወታደዊ ሸሚዝና ሱሪያቸዉን ኪስ ሻዕቢያ ሲበረብርም ከንጽህና ወረቀት በስተቀር ምንም አላገኘም። አንድ የሻዕብያ ተዋጊ ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ ለብሰዉ የተሰዉትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ባንዴራ ካላያቸዉ ላይ ገፈፈና ክብሪት ጭሮ አቃጠለዉ። የኮሎኔሉ አስከሬን ከወንበሩ ላይ ገፍትሮ በመጣልም በደም የተጨማለቀዉን ወንበር በአንድ እጁ ወደ ላይ አነሳዉ። ይህ ድርጊት ጋብ ያለዉን ተኩስ በመጠኑ ቀሰቀሰዉ።



ከአንድ አቅጣጫ የተተኮሰች ጥይት ያን የሻዕቢያ አባል ከወንበሩ ጣለችዉ።ከዚያ በሗላም የሻዕቢያ ተዋጊዎች ተደናግጠዉ አካባቢዉን ማሰስ ጀመሩ።ፎቅ ላይ እየወጡና ምድር ቤቱን አሰሱ ቁስለኛም ይሁን ጤነኛ በየቤቶቹ ፍርስራሽ ሥር ተደብቆ ያገኙትን የአብዮታዊ ሠራዊት አባል ጭምር በየቦታዉ መረሸን ጀመሩ። የአብዮታዊ ሠራዊት አባላትም ሻዕቢያን ገድሎና የራሳቸዉን ጥይት እየጠጡ ሞቱ።ኢትዮጵያ ወይም ሞት! ቀይ ባሕር ኢትዮጵያ ዘላለማዊ ባሕር ነዉ!” እያሉ መፈክር በማሰማት…………



እያለ አሰዛኝ ታሪክ ይተነትነዋል። ሙሉውን ታሪክ ከላይ የሰጠሁዋችሁን ድረገጼ ላይ አፈናጣሪ (ሊንኩን) በመጠቆም መንበብ ትችላለችሁ።

Ethiopia: ጀግናው የሸገር ህዝብ ግልብጥ ብሎ ወጣ! ጃዋርን ልክ ልኩን ነገረው

No comments: