Friday, November 1, 2019

ሀገር የእዝን ድንኳን አይደለችም። ያዝ፣ ወጥር፣ ፌሮውን ምታው እና ምሶሶው መሐል ይሁን ብለህ የምታቋቁማት! (Ethio Semay) 11/2/2019


ሀገር የእዝን ድንኳን አይደለችም። ያዝ፣ ወጥር፣ ፌሮውን ምታው እና ምሶሶው መሐል ይሁን ብለህ የምታቋቁማት! (Ethio Semay) 11/2/2019

ጋዜጠኛ መስፍን ማሞ ተሰማ ጥር 2010 ዓ/ም (ጃንዋሪ 2018) ሲድኒ አውስትራሊያ ስለ ሟቹ ጋዜጠኛ  ኢብራሂም ሻፊ ሰፋ ያለ የሀዘን ማስታወሻ ጽፎለት ነበር። ሟቹ ኢብራሂም (ኢብሮ) በህይወት እያለ “መንግሥት ሲኖረኝ ቀስቅሱኝ” ብሎ ስላጸፋት ጽሑፍ ቀንጭቤ ስለ አገር ምንነትና እንዴትስ እንደተገነባች ላስነብባችሁ። ትግርኛ ለምታነብቡ የትግርኛ ትርጉምም የራሴው ከ እግርጌ ታገኙታላችሁ። መነበብ ያለበት ጥቅስ ነው!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

“ሀገር የእዝን ድንኳን አይደለችም። ያዝ፣ ወጥር፣ ፌሮውን ምታው እና ምሶሶው መሐል ይሁን ብለህ የምታቋቁማት። ሀገር የዘመናት ሂደት ነች። በዚህ ውስጥ ደግሞ ብረት አለ፤ ጦርነት አለ። ማስገበር መገበር አለ። በዘር፣ ሀይማኖት፣ ቆዳ ቀለም እና አመለካከት ተቧድኖ ያልተጋደለ የለም። የትኛውም ሀገር ይኸን ሂደት አልፏል። በጦርነት ተተራምሷል፣ እርስበርስ ተጋድለዋል። ኢትዮጵያም ስትመጣ ይሄው ነበር። ብረት ነበር፣ ጦርነት ነበር፣ ገባሪ እና አስገባሪም ነበር። ይህን ታሪክ ወደኋላ መለስ ብለን የምናጠናው፣ የምንመረምረው፣ ማስረጃ የምንሰበስበው፣ የምናደራጀው እና ከግኝታችን ተነስተን የምንተረጉመው ቂም ወርሰን እንደገና ለመጋደል አይደለም። ታሪክ ያለቀ ነው፤ የተፈፀመ። ስለዚህም ስህተት ከነበር ለይተን ልናርመው፤ በጎውን አውጥተን የበለጠ ልናጎለብተው እንጂ። ‘ቴዎድሮስ ካሳሁን አፄዎቹን ያወድሳል። አፄዎቹ ደግሞ ሙስሊሙን ጨቁነዋል…ሙስሊም እንደ መሆንህ መጠን ልትቃወመው ይገባል’ የሚል ‘ምሁር መካሪን’ ራሴው ዓቃቤ ህግ ሆኜ፣ ክስ መስርቼ፣ ጥፋተኛ አስብዬ፤ ራሴው ደግሞ ዳኛ ሆኜ እስር ቤት ብወረውረው ደስ ይለኛል…ምኞቴ ነው። ይሄንን ‘ምክር’ እንኳን ለዕድሜ አቻዎቼ ለመጠቆም አደባባይ ልወጣ አይደለም አብረውኝ ላደጉት በጣም ለምወዳቸው በዕድሜ እጅግ ታናናሾቼ ለእህቶቼ ልጆች ዘኪዬ እና ኢብሮዬ አይመጥንም። ሳት ብሎኝ ይኽን ስል ቢሰሙ እንኳን (ፍፁም አልልም እንጂ) በእነርሱ የግንዛቤ አቅም እንኳን እየነሆለልኩኝ መሆኔን ልብ ብለው የሚስቁብኝ ይመስለኛል…አጎቴ ምን ነካው? ብለው ክትከትከት…አምላክ ይዘንላቸው እና ጋሼ አሰፋ ጫቦ በአንድ ቃለ ምልልሳቸው ‘ስለ ኢትዮጵያ አንድ መጽሐፍ አንብበህ ከሆነ…ሁለት አድርገው…ሁለት ከሆነ ሦስት…ሦስት ከሆነ አራት አድርገው። ኢትዮጵያ የብዙ ሺህ ዓመታት ውጤት ነች። በጣም በርካታ መጽሐፍትም ስለ ኢትዮጵያ ተጽፏል። ከተለያዩ አቅጣጫዎች እና ፍላጎት ጋር’ ሲሉን ነበር። አዎን ኢትዮጵያ ብዙ ነች። ያለፍንበት ዘመንም ረጅም ነው። ያለፍንበት ዘመንን የሚገልፁልን ብዙ መጽሐፍትም አሉን። እነዚያን መጽሐፍት የምናነበው፣ የምንመረምረው እና የምናጠናው አሁን እኔ ቂም ወርሼ፣ ጥላቻን በልቤ አርግዤ፣ በቀልን በመሻት ከወንድሜ ጋር ልጋደልባቸው አይደለም…ዘኪዬ እና ኢብሮዬም ጊዜያቸው ሲደርስ ከወንድሞቻቸው ጋር እንዲፋጁ አይደልም… አንድ የሚያደርጉንን ነጥቦች ነቅሼ፣ የሚያስማማንን አበጥሬ እና በጋራ የሚያኮሩንን ለይቼ ብላቴናው የሚመኛትን በፍቅር የተሞላች ምርጥ ሀገር ለማየት እንጂ…!!! ለማንኛውም ወደ ፍቅር ጉዞ እያላችሁ ደግሞ ዛሬ………..!!!” በማለት ፅፏል፤ ኢብራሂም። ‘ብላቴናው የሚመኛትን ሀገር’ ማለቱም ቴዲ አፍሮን ሲጠቅስ ነው።"

የትግርኛ ትርጉም ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

 “ሃገር ከም ሽኻል መርዓ ዳስ ‘ገቲርካ ገታቲርካ’ ብቃንጫ ፥ ብዴጎይ ፥ ብልሕጺ ፥ ብሳዕሪን ፥ ብታህሶስን ወቲፍካ ወታቲፍካ ዝትከል ኣይኮነን። ናብ’ዚ ሳሓብ ፥ በ’ትይ ገትር ፥ ተባሂሉ ዝትከል ዓንዲ ኣይኮነን። ሃገር ናይ እልፍ ኣእላፍ ዘበን ከይዲ እያ። ኣብ’ቲ ከይዲ ብረት (ነፍጢ) ኣሎ ፥ ውግእ ኣሎ ፥ ገብር ኣይግብርን ፥ ቅተል ተቓታተል ኣሎ። ብዘርኢ ፥ ብዓልየት ፥ ብሕብሪ ቆርበት “ ብቕይሒ ፥ ብጽልሚ” ፥ ብሃይማኖት ፥ ብርእይቶ ፥ ብከባቢ ተሰሪዑ ዘይተዳመየ የለን። ዝኾነ ሃገር በዚ ከይዲ እዚ ተሳጊሩ እዩ “ሃገር” ተባሂሉ። ሃገርና እውን ከምኡ። ብረት ነይሩ፥ ውግእ ነይሩ ፥ ገባርን መገበሪን ነይሩ፥ ሕዚ ንድሕሪት ገማዕ (ቆላሕ) ኢልና እቲ ዝነበረ ከይዲ እንዳዘከርና ፥ ከም ከይዲን ከም ህግጋት ‘ህንጸት ሃገርን’ ገይርና ንክንማሃረሎም እምበር ፤ ሕድሕድና ብዓልየት ተኣኻኺብና ሰነዳት እንዳኣከብና ፤ ኣብ ዘይነበርናሎም ከይዲታት “ኒሕ ንምፍዳይ” “ዒሕታ” ወሪስና ነንሕድሕድና ንክንቃተለሎም ንምግባር ኣይኮነን።” (ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ)

No comments: