Saturday, November 16, 2019

ጃዋር በየዓለማቱ የሚንሸራሸርባት ክርስትያን ታደለ የሚታሰርባት አገር ትርጉሙ ንገሩኝ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)


ጃዋር በየዓለማቱ የሚንሸራሸርባት ክርስትያን ታደለ የሚታሰርባት አገር ትርጉሙ ንገሩኝ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

የ75 አመት አዛውንቱ የክርስትን ታደለ ወላጅ አባት ታስረው ልጃቸው የጻፈው ማስታወሻ (ፎቶ ክርስትያን ታደለ እና ወላጅ አባቱ) Ethio Semay)

Christian Tadele Tsegaye (ገብርዬ)ፈ
May 28, 2019
ወላጅ አባቴ ታደለ ፀጋዬ በቋሪት ወረዳ አመራሮች ታፍኖ ከታሰረ ዛሬ 5ኛ ቀኑ ነው። በወቅቱ ጉዳዩን ስሰማ ቀልድ መስሎኝ ነበር። ያው በስህተት ያሰሩትም መስሎኝ ነበር። በኋላ መረጃዎችን ሳጣራ ግን ቀልድም ስህተትም አልነበረም። ታስቦበት፤ ወርደው ሊያወርዱን ያጠመዱልን ወጥመድ መሆኑን ተረድቻለሁ። ለዚህም የወረዳው ም/አስተዳደሪና የአስዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆነው ግለሰብ (ስሙ ኤርሚያስ ባይነስ የሚባል) «እስኪ ልጅህ መጥቶ ሲያስፈታህ እናያለን» የሚል መዘባበቻ በ75 ዓመቱ አዛውንት አባቴ ላይ መሰንዘሩ፤ የወጥመዱን መነሻ ብቻ ሳይሆን የዚህ ሴራ ጎንጓኞች ግብንም ፍንትው አድርጎ አመላካች ነው።

ለመታሰሩ የቀረበው ሰበብ የመንግሥት መደበኛ ተግባር የሆነውን ሁከትን የማረጋጋት ሥራ በአገር ሽማግሌነቱ መስራቱ መሆኑ ደግሞ የበለጠ ገራሚ ነው። የብልግናችሁን ጥግ፤ ነውራችሁንም አዝማሪዎቻችሁ እንዲያውቁት ጭምር እንጂ ለእኔስ ወላጅ አባቴ ታደለ ፀጋዬ ላይ ያደረጋችሁት ሁሉ በሌላው አማራ ያደረጋችሁትና የምታደርጉትም ስለሆነ ድንቄም አይደለ! ፍትኅን ከጨቋኝ ሊያውም ከጃንደረባ መለመን ለነውራችሁ እውቅና መስጠት ነው። ብቻ ግን አንዳችስ እንኳ የሞራል ተጠያቂነት እንደሌለብኝ እንድታውቁት ይሁን።”

በማለት በወቅቱ በ May 28, 2019 አባትየው በግፍ ሲታሰሩ የጻፈው ማስታወሻ ነው አሁን ያቀረብኩላችሁ። ዛሬ ተረኛው የኦሮሞ አፓርታይድ መንግሥት አሳምነውን ሲገድል ባለቤቱን አሰረ፤ ክርስትያን ታደለን ለማሰር ሲፈልግ አባትየውን አሰረ፡ አንዲህ ያለ ግፍ ሲፈጸም አስፈጻሚው አማራው እራሱ ብአዴን/አዴፓ/ የሚባለው ወንጀለኛ ድርጅት ነው። ታዲያ አሜሪካዊው ጃዋር እንደፈለገው የሚፎልል፤ ሲፈልግ ሐረር ፤ ሲፈልግ ጎጃም ፤ ሲፈልግ አዲስ ሲፈልግ መቀሌ ፤ ሲያሻው አሜሪካ እየተዘዋወረ የሚፈነጭበት… ኢትዮጵያዊው ክርሰትያን ታደለ ግን የሚታሰርባት አገር ትርጉሙ ንገሩኝ?! አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)

No comments: