Saturday, November 8, 2025

ሰሜነኞች ዕርቅ ብትፈጥሩ ችግራችሁ በሣምንታት ውስጥ ዕልባት ያገኛል! ዳግማዊ ጉዱ ካሣ Ethiopian Semay 11/8/25

 

ሰሜነኞች ዕርቅ ብትፈጥሩ ችግራችሁ በሣምንታት ውስጥ ዕልባት ያገኛል!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Ethiopian Semay

11/8/25

ርዕሴ ሁሉን ነገር ይናገራልና የምለው የገባው እዚሁ መቅረትም ይችላል፡፡ እኔ ግን ትንሽ ልቀጥል፡፡

ሰሜነኞች ስል የማይገባው ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡ በዋናነት ትግሬንና አማራን ማለቴ ነው፡፡ እነዚህን ነገዶች ለሥልጣንና ለኢኮኖሚያዊ ጥቅማቸው ሲሉ በሤራና በሸፍጥ ያጣሉትና ያጫረሱት በቁጥር አንድ ተጠያቂነት ሕወሓቶች መሆናቸው የሕወሓቱ የ1968 ዓ.ም ማኒፌስቶና ያንንም ተከትሎ ባለፈው ግማሽ ምዕተ ዓመት የተከሰተው ሰቆቃወ አማራ ኅያው ምሥክር ናቸው - በዚያ ማኒፌስቶ ውስጥ “አማራንና ኦርቶዶክስን ከኢትዮጵያ እናጠፋለን” የሚለው የሕወሓት የትግል ማዕከል ጉልኅ ሥፍራ እንዳለውና በዚያም ምክንያት ባለፉት 50 ዓመታት ኤድስን በመሰሉ በማይድኑ በሽታዎች መበከልንና በመርፌ ማምከንን ጨምሮ በተለያዩ ግልጽና ኅቡዕ ሥልቶች በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር አማራ እንዳለቀ ለአዲሱ ትውልድ ማስታወሱ አይከፋም፤ ለዕርቁም ሆነ ለተጠባቂው ስምምነት የማይደገም ህፀፅ ተደርጎ በተለይ በተጋሩ ግንዛቤ ያገኝ ዘንድ ነው ያ ግፍ እዚህ መጠቀሱ፡፡ ጥሩ ዕርቅ ደግሞ ስህተትን ማመንንና ወደዚያም ላለመመለስ ቃል መግባትን ያካትታል፡፡

ከፍ ሲል የተጠቀሰው የታሪክ ስብራት ተብሎ ተብሎ ያለቀ ጉዳይ ነው፡፡ አሁን በስልሣዎቹ ዕድሜ አካባቢ ያለን ቀደም ያልን ትውልዶች ብዙ መክረናል፤ ዘክረናል፡፡ የሚመጣው ውርጅብኝ ሳይቀር ማንንና ምን ያህል ሊጎዳ እንደሚችል ሳይቀር ጠቁመናል - ይሁንና ሰሚ ጆሮና አስተዋይ ልቦና አልተገኘም፡፡ የተናቀ ነገር ግን ከእውነተኛ ውስጣዊ ስሜት የመነጨ ቃል እውን መሆኑ ብዙውን ጊዜ የሚታይ ነውና ብዙ ነገር ታዘብን፡፡ የሚቀረን ደግሞ ካለፈው ይበልጣል፡፡ እሱም አክራሪ ኦሮሞዎች በንጹሑ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ላይ የሚያስከትሉት ከፍተኛ አደጋ ነው፡፡ ያም ጊዜ በእጅጉ ቀርቧል፡፡ ቅብጠታቸው ሰማየ ሰማያትን ሳይቀር በደምና በዕንባ የሞላው ጥቂት የማይባሉ ማይማንና ጭራቅ ኦሮሞዎች የዘሩትን የሚያጭዱበት ጊዜ እየመጣ ነው፡፡ ሀገርን እያስራቡ ብርን እንደሣር በመጎዝጎዝ ያልደከሙበትን ገንዘብ እየረገጡ የሚጨፍሩ፣ በአህያዋ የለመደበትንና እሱ ሲሰክር አህያዋ ወደምታውቀው ቤቷ ስለምትሄድ - መሄድ አለመሄዷን ለማረጋገጥ ለሚስቱ ስልክ ደውሎ በራሱ ቋንቋ “ሃሬን ዱፍቴ” ብሎ መጠየቅ በለመደው ዘይቤ አሁን ደግሞ በዊስኪ ጠምብዞ ሪቮሉሽን የሚባለውን በተረኝነት የሙስናና የምዝበራ ገንዘብ የገዛውን ዘመናዊ መኪና ያቆመበትን ቦታ በመሳት ወደቤቱ ስልክ በመደወል “ሪቮን ዱፍቴ” በማለት የሚጠይቅ የአህያን ጠባይ ከመኪና ተፈጥሮ የማይለይ ማይም ጥጋበኛ ኦሮሞ፣ አማራን ከቀሪው እንስሳም ባነሰ ሁኔታ በካራ እየዘለዘሉ ጥላቻቸውን የሚገልጹ፣ መግደል ብቻውን አላረካቸው ብሎ የሰውን ልጅ አርደው በመኪናና በጭነት እንስሳት ሬሣን በመጎተት በደስታ ጮቤ የሚረግጡ፣ የተማረከና የቆሰለ ተዋጊና ከሆስፒታል የተኛ ቁስለኛ አማራ በጉልበት አውጥተው በላዩ ላይ መኪና እየነዱ የሚጨፈላልቁ፣ የቆሰለችን ፋኒት ጡት ቆርጠው ትርጉም የለሽ ዳንኪራ የሚረግጡ፣ በጥቅሉ ሰይጣን እንኳን የማያውቃቸውንና የሚጠየፋቸውን ጭካኔዎችና ወንጀሎች በተለይ በአማራ ላይ የሚፈጽሙ ኦሮሞዎች አሣራቸውን የሚበሉበት ጊዜ በየደጃቸው ቆሟል፡፡ ማመን አለማመን የራስህ ጉዳይ ነው፡፡ እውነቱ ግን ይሄው ነው፡፡

“ውድ ዐረመኔ ኦሮሞ ‹ወንድሞቼ› - ጊዜያችሁ ቀርባለችና በጭካኔያችሁ ቀጥሉ፤ ተዝናኑበትም፡፡ እናንተንም በጠማማ ቀን የፈጠረ አምላክ አማራንም በዚያው ቀን ፈጥሯልና አይረሳውም፡፡ ቀን ተለዋዋጭ ነው፡፡ ከአማራ በበለጠ የምታለቅሱ እናንተ ናችሁ፡፡” ልበልና ትንሽ ልቀጥል፡፡

ትግሬና አማራ በተለይ ትግሬዎች ጅሎች ናችሁ፡፡ ምክርና ሰማያዊ ተግሳጽ አይገባችሁም፡፡ ንክር ያላችሁ ንክሮች ናችሁ፡፡ ይህንን ስል አዝናለሁ፡፡ ነገር ግን እውነትን ተናግሮ እመሸበት ማደር ደግ ነውና የሚሰማኝን አልደብቅም፡፡ አሁን አሁን ደግሞ አማራው ብሶበታል፡፡ ፋኖ የምንለው ተዋጊ ኃይል ሦስት ወር የማይፈጅ የነፃነት ትግል እርስ በርስ ባለመስማማትና ለምድራዊ አዱኛ በመንበርከክ ይሄውና ሦስት ዓመት ሊሆነው ነው፡፡ ሞኝነት ነው፡፡ ከበደኖ እስከ ባሌ፣ ከሻሸመኔ እስከ ወለጋ፣ ከአሩሲ እስከ ኢሉባቦር … ያለቀውና እያለቀ ያለው ወገኑ ጩኸትና የመከራ ዶፍ ሳይሰማው ባልተጨበጠ ሥልጣን ጫካ ውስጥ ሆኖ እርስ በርሱ ይናቆራል፡፡

ከዛሬ 50 ዓመት ወደፊት በምናብ ተጓዙና ያንን ጊዜ አስቡልኝማ፡፡ አሁን የ40 ዓመት ጎልማሣ ያኔ የ90 ዓመት ሽማግሌ ነህ - ልጥህ የተራሰ፤ ጉድጓድህ የተማሰ - ሊያውም እስከዚያም ከቆየህ፡፡ በሌላ ‹ያኔ› ሌላ ነገር ላርዳህ - ያኔ አንደበትህም፣ ጉልበትህም፣ የዱሮ ጓደኞችህም … ከድተውህ በምርኩዝ እያዘገምክ ወይም በዊልቼይር እየተገፋህ የቁም ጣርህን የምታገባድድና ለምንም ዓይነት ቁም ነገር የማትታጭ ሰው ነህ - በአብዛኛው፡፡ አዎ፣ በዚያን ጊዜ ልጆችህና የልጅ ልጆችህ “ይሄ ሽሜ ጉጉ መቼ ነው የሚጭረው?” እየተባልክ በቤተሰብ ሳይቀር ሞትህ የሚናፈቅ ከንቱ ነህ፡፡ ለዚህ ነው አንግዲህ አሁን እሽቅንድር እያልክ ለሰው ሞት ጉድጓድ ስትቆፍር የምትውለውና በሰው ሞት ሃሤት ስታደርግ ውለህ የምታድረው፡፡ የምልህ ይግባህ፡፡

ሌላ ቁም ነገር ልንገርህ፡፡ አርጅተህም ሆነ ሳታረጅ ብትሞት ትግርኛህንም፣ ውበት ቁንጅናህንም፣ ግርማ ሞገስህንም፣ የዘመናት አንጡራ ሀብትህንም፣ ተወዳጅነትና ተጠይነትህንም፣ … ባጭሩ አለኝ ከምትለው የሚታይና የማይታይ ቁሣዊና አእምሯዊ ንብረት ሁሉ አንዱንም ይዘኸው አትሄድም፡፡ ጥለኸው ነው እምትቀበር፡፡ ያንተ ብቸኛ ሀብት ሦስት ክንድ መሬትና ጥምቡ ሰውነትህ የሚጠቀለልበት ሁለት ሜትር የመግነዝ ጨርቅ ናቸው፡፡ ሞተህ ከተቀበርክ ከጥቂት ወራት በኋላ አፈር ነህ፤ የሚያስታውስህ ሰው ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰ ይመጣና በመጨረሻም ትረሳለህ፡፡ ገንዘብንና ሥልጣንን (ማናቸውንም ዓይነት ጥቅምን) በውስጡ አርግዞ አሁን ከወንድም እህቶችህ ጋር የሚያጣላህ ሃይማኖትም ሆነ ቋንቋ  ከአንተ ጋር አይሄድምና ያኔ ስትሞት ከአንተ ጋር አይኖርም፡፡ ያኔ ወልቃይትና ራያ እያልክ አሁን የምትጃጃልበትና መላ ሕይወትህን ከነቤተሰብህ የምትገብርበት ቁራሽ መሬት ከአንተ ጋር የለም፡፡ ያኔ “ትግራይ አደይ፤ መዓረይ ሸኮሪናይ” እና “እኔ የጎንደሪቱ ልጅ፤ እኔ ሞረቴዋ!” ብሎ ፉከራና ፉገራ አይሠራም፡፡ ብዙ የሚገርም ነገር እኮ ነው ያለው በእውነቱ፡፡ ያኔ የፕሪቶሪያ ስምምነት ካንተ ጋር የለም፡፡ ምድረ የአእምሮ ሸፋፋ ሁላ አንዱን ጎድቶ ሌላውን የጠቀመ እየመሰለው ባልጠፋ ሀገራዊ ከተማና ቦታ አንዴ አልጀርስ ሌላ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ፣ አንዴ ኬንያ ሌላ ጊዜ ታንዛኒያ እየተንከወከወ የማያዛልቅና የማይከበር ድርድርና ስምምነት ቢያደርግም ዕልቂቱና ሁለንተናዊ ትንግርቱ ግን አሁንም ልክ እንደትናንቱ ሊያውም በስፋትና በጥልቀት እንደቀጠለ ነው፡፡

በነቀርሣ ህመም ለሚሰቃይ ሰው አማራጩ ሁለት ነው - ይሄውም ነቀርሣውን ቆርጦ በማውጣት የሰውነቱን ጤንነት ወደቀድሞው መመለስ አሊያም ሞትን በፀጋ መቀበል፡፡ ኢትዮጵያም መዳን ከፈለገች ያላት ብቸኛ አማራጭ ፖለቲካውን ይዘው ሀገሪቷን እየበታተኑና ሕዝቧን እየጨረሱ የሚገኙ የየትኛውም ነገድ ደናቁርትን በልዩ “ሰርጂካል ኦፐሬሽን” ማስወገድና ተለያይቶ የማይለያየውን ሕዝብ ኅልውና ማረጋገጥ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ ያለው አማራጭ ትርፉ እንዘጭ እንዘጭ ነው፡፡

ትግሬና አማራ በላይ ላይ ሲያዩዋቸው የተማሩና ዕውቀት የገባቸው ይመስላሉ፡፡ ውስጣቸው ግን ቢከፍቱ ተልባ ናቸው፡፡ የዛሬውንና አብዛኛውን ኦሮሞ ሳይሆን የዱሮውንና የዋሁን ኦሮሞ ሳንዘነጋ የኢትዮጵያ መሠረት የሆኑ እነዚህ ታላላቅ ነገዶች እዚህ ግባ የማይባል በሁሉም ነገሩ የወረደ አንድ ጎልማሣ በኦሮሞ ስም ተነስቶ ከመሰል ደናቁርት የኦሮሞ ወታደራዊ ምርኮኞችና የአማራ ባንዳዎች ጋር ሲቀልድባቸው ያን ቀልዱን ተባብረው በማስቆም ኅልውናቸውን እንደማስጠበቅ በማይረቡ ጥቃቅን ጉዳዮች ሲወዛገቡና ለጋራ ጠላታቸው ምቹ ሲሆኑ እንደማየት አሣፋሪና አሳዛኝ ክስተት የለም፡፡ ነገ ለሚደረስበት የቁራጭ መሬት የይገባኛል ክርክር ወይም የሥልጣን ክፍፍል ዛሬ ጄኖሳይድ ያወጀባቸውን ኦሮሙማ ትተው እርስ በርስ መጃጃላቸው በርግጥም የጤና ሳይሆን የአፍዝ አደንግዝ ድግምትም ይመስላል፡፡ በትምህርትም፣ በወታደራዊ ዕውቀትና ጥበብም፣ በልምድም፣ በምንም በምንም እጅግ ዝቅተኛ በሆኑ እነአቢይ አህመድንና ምርኮኛ አሥር አለቃ ብርሃኑ ጅሎን በመሰሉ ሰው መሳይ ሰዎች መታለል የበሽታ እንጂ የጤና ሊሆን አይችልም አለበለዚያም ትግሬንና አማራን አላውቃቸውም ነበር ማለት ነው፡፡

ብርሃኑ ጁላን ሲናገር አድምጡት፤ አቢይንም አራምባና ቆቦ የሚረግጥ ሀሰተኛና አስመሳይ ንግግሩን ሲወሻክት ስሙት፤ ሸመልስ አብዲሣም በየጊዜው ከስድ አንደበቱ የሚያመልጠውን እውነተኛ የኦሮሙማን ፍላጎት ሳትንቁ አጢኑት፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ አማራንና ትግሬን ሰነጣጥቀው እየተጫወቱባቸው ያሉት፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ በነጌታቸው ረዳና በነፃድቃን ገ/ትንሣኤ ቦረንቲቻ አዙረውባቸው ታዛዥ ባርያ አድርገው የሚቀልዱባቸው፤ መሣቂያ መሣለቂያ አደረጓቸው፡፡ የምትገርም ኢትዮጵያ ሆናለች፡፡ ትናንትናና ዛሬ ለዬቅል እየሆኑ ማሣቅና ማሣቀቃቸውን ቀጥለዋል፡፡ ብርሃኑ ጁላ ወይም በልጅነቱ መሽረፊት እያዞረ ሲጋራና ጫት ምናልባትም ሴት ለማምጣት ሲላላካቸው የነበረ ጮርቃው አቢይ አህመድ ጎምቱዎቹን የቀድሞ የሕወሓትና የአሽከሩ ብአዴን አባላት ፃድቃንንና ጄኔራል አበባውን ተላላኪ ሲያደርጓቸው ይታያችሁ፡፡ “ጊዜ አይጣልህ” የሚባለው ምርቃት አሁን ነው በደምብ የገባኝ፡፡ ሆድ መጥፎ ነው!!

ወጣቱ አማራና ትግሬ ነቃ በል፡፡ በአሮጌ አስተሳሰብ አንጎላቸው የጨቀዬ የሥነ አእምሮ ደዌ ልክፍተኞችን አታዳምጥ፡፡ በአዲስ መልክ ተባበር፡፡ የመጣብህ ጠላት ሁልህንም የሚጨርስ ነው፡፡ አንተ ወልቃይት ወልቃይት ስትል አድዋና ሽሬንም ቀምቶ አንተንም በመርዝ ጨርሶ ኅልውናህን ከናካቴው የሚያጠፋ ኦሮሙማ የሚባል እጅግ ዐረመኔ ጠላት ነው የመጣብህ፡፡ አዲስ አበባ የሚኖር ትግሬን ጠይቅ፤ አዲስ አበባ የሚኖር አማራን ጠይቅ፡፡ በአዲስ አበባ በአሁኑ ሰዓት ከኦሮሙማ ባህልና ቋንቋ ውጪ ሌላው እየተዳፈነ ነው፡፡ በሁሉም ነገር የኦሮሞን ባህልና ቋንቋ ለማንገሥ የፌዴራል ተብዬውና የኦሮምያ ክልል በሙሉ ኃይላቸው ወደ ሥራ ተሰማርተዋል፡፡ ቡና ቤት ሳይቀር ካለኦሮምኛ እንዳይዘፈን የውስጥ መመርያ የተላለፈ በሚመስል አኳኋን ሕዝብን የማኦረም እንቅስቃሴው እየተሳለጠ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ የተፈናቀለውንና ቤቱ እየፈረሰበት ራሱን ያጠፋውን፣ አብዶ ጨርቁን ጥሎ የሚባዝነውን ቤቱ ይቁጠረው፡፡ በየቀኑ በሚወጣ ህግና ደምብ አዲስ አበባውያን ድራሻቸው እየጠፋ ነው፡፡ ስለዚህ እንደዝንጀሮዋ ቀድሞ የመቀመጫየን በልና አማራ ከትግሬ፣ ትግሬም ከአማራ በንጹሕ ልቦና ተወያይ፤ ለራስህ ኅልውና ስትልም ተስማማ፡፡ በቋንቋ፣ በነገድ፣ በባህል፣ በሥነ ልቦና፣ በኑሮ ዘይቤ አንድ የሆነ ሕዝብ በአጭበርባሪዎች ሤራ ተከፋፍሎ የገዛ ሀገሩን ባንዲራና ሃይማኖት ማጥፋት የለበትም፡፡ ተጋሩ በተለይ በዚህ ነጥብ ዙሪያ ተነጋገሩና ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ፡፡ እናንተው ያቆማችኋን ሀገር እናንተው ስታፈርሷት ሳይ ምንም ማድረግ ባለመቻሌ በጣም አዝናለሁ፤ እናደድማለሁ፡፡ “ደህና ሰው ሲበላሽ ቅራሪ የለውም” የሚባለው ተረትና ምሣሌ እውነት ነው፡፡

 ትግራይ ውስጥ ኦርቶዶክስን ለማጣመምና ከኢትዮጵያ ለመለየት የተደረገውን የእውር ድምብር ሩጫ ሳስበው ሃይማኖትም በሣጥናኤል ልዑካን እንዴት እየተሰቃየች እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ ይህ ዋናውን ቤተ ክህነት ሳይቀር በዘርና በቋንቋ የከፋፈለ ግብረ ዲያቢሎስ በአፋጣኝ ካልተወገዘና ካልቆመ የሀገራችን ዕልቂትና መፈራረስ መቀጠሉ የማይቀር ነው፡፡ ሰይጣን ሁሉን ተቆጣጥሯል፡፡ 

እስካሁን ማንም ያጥፋ ማንም ከአሁን ወዲያ ግን እንጠንቀቅ፡፡ ጥፋት የሰው ልጅ መለያ ባሕርይው ነው፡፡ ማንም ያጠፋል፡፡ አእምሮ ስላለው ግን ይጸጸታል፤ አንገት ያለው ሰው ደግሞ ዞሮ ማየትን ያውቅበታልና ለእኛ የሚዋጣን ወደቀደመው ፍቅራችን መመለስ ብቻ ነው፡፡ ወደ ደገኛው መንገድም እንመለስ፡፡ ስለዚህ ከአማራ ጋር በከንቱ አትገዳደሉ፡፡ አማራም ወደቀልብህ ተመልሰህ ከወንድም እህቶችህ ጋር ምከር፤ ተስማማ፤ ዕልቂትን አቁም፤ በይቅርታና በ“ይቅር ስለፍቅር” ባህላዊ ትውፊት እንደቀድሟችሁ ሁኑ፡፡ በእናንተ መተላለቅ የሚደሰተው ብዙ ነው፤ በተለይ ግን ኦሮሙማ ዕቅዱን ተግባራዊ ያደርጋልና በጀት መድቦ እያጨራሳችሁ እንዳለ ሁሉ ከውጪ ሰው ቀጥሮና መሣሪያ በገፍ ሸምቶ እንደሚያፋጃችሁ ዕወቁ፡፡ በእልህ ደግሞ አትነዱ፡፡ እልህ ቤት ያፈርሳል፡፡ እልኸኞች የጋራ ቤት ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ብዙ ትዳሮች የሚፈርሱት በእልህና በትዕቢት እንዲሁም አለመደማመጥ በሚፈጥረው የግትርነትና መንቻካነት ጠባይ ነው፡፡ Avoid arrogance and aggressiveness. በቃ፡፡ እናንተ አንድ በሆናችሁ ማግሥት ኢትዮጵያ እንደእባብ አሮጌ ቆዳዋን ገሽልጣ ጥላ በአዲስ ቆዳና ቀለም እንደአዲስ ትፈጠራለች፡፡ “ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን” ብላችሁ የእስካሁኑን መበዳደል በይቅርታ አልፋችሁ ለወደፊቶቹ ትውልዶቻችሁ ስትለ፤ ዕርቅን ፍጠሩ፡፡ በዚህ ትጠቀማላችሁ እንጂ አትጎዱም፡፡

 ያለፈን መርሳት ደግሞ አንደኛው የሕይወት ትልቁ ቅመም ነው፡፡ ዋናው ነገር ወደትፋቱ ከሚመለሰው ውሻ ተምሮ ወደቀደመ ጥፋት ላለመመለስ ቆራጥ መሆን ነው፡፡ … የእስካሁኑን መከራችንን ቆጥሮልን መጪውን የዕልቂት ዘመን አንድዬ ያለዝብልን፤ አሜን፡፡   

 

No comments: