Thursday, November 13, 2025

ነፃ እና ኩሩው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁንም በፋኖ ፤ በወያኔ፤ በኦነግና በአብይ ኦሮሙማ በጣሊያናዊ የጎሳ አስተዳደር ሰንሰለት ታስሮ እየተጎተተ እሰከመቸ ይቀጥላል? ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/13/2025

 

ነፃ እና ኩሩው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁንም በፋኖ ፤ ወያኔ፤ በኦነግ እና በአብይ ኦሮሙማ በጣሊያናዊ የጎሳ አስተዳደር ሰንሰለት ታስሮ እየተጎተተ እሰከመቸ ይቀጥላል?

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

11/13/2025

በዓለም ጂኦግራፊያዊ ክልል ውስጥ ራሱን የቻለ፣ ነፃ እና ኩሩ ሕዝብ ሆኖ እስከ 1966 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጵያውያዊ ዜጋ አንዳንድ ችግሮች ቢሮሩትም እንደዛሬው ለክፋት የሚጥል የዘር እና የባህል ወረራ ሳይደረግበት ህልውናውንና ነፃነቱን ተጠብቆለት ቆይቶ ሳይታሰብ በድንገት በ1966 ነባሩን ሥርዓት ተወግዶ “በኮሚዩኒዝም” ሥርዓት ሲተካ ወደ ጥቃት ገበያ ተጎትቶ ገባ።

ከዚያ ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ነጻነቱ ተወስዶበታልለጥቃት ገበያ ያዘጋጁት ደግሞ ደጋገመን እንደገለጽነው «ወያኔ ኦነግና ሻዕቢያ» ሲሆኑ ያንን የፋሺስቶች ፖለቲካ አፈሳለሁ ብሎ ፤ በብዙዎቻችን  ግምት ለኢትዮጵያ ሕልውና መከታ ይሆናል ብለን ስንጽፍለት የነበረው “የአማራ ፋኖ”  ኢትዮጵያዊ የትግል ፐሮግራም እና አመራሮችን ሳያዘጋጅ በወያነ ጦርነት የማረከውን ጠመንጃ ሳያስበው “ጠመንጃህ ፍታ” ሲባል ንገት ባንኖ ወደ ጫካ ሲገባ ለ27 አመት ሲጋተው የነበረው አውራጃዊና መንደርተኛዊነት በሽታ ተጋብቶበት  “የነገድ ፖለቲካ” ተረካቢ ሆኖ «የንገሥታት ልጆች ነን በእናቶቻችን ማሕጸን እያለን ለመሪነት የታጨን ልዩ አፈጣጠር ያለን አማራዎች ነን ፤ወደ እሚል ፈጹም በቅዠት የሚፎልል ፋሺስታዊ የሆነ “ኢትዮጵያውነን” የሚያኮሥስ መንደርተኛ በመሆን “ሞቴ ከወያነ እና ከሻዕቢያ በፊት ያድርገው” እያለ ለጸረ ኢትዮጵያ ኃይላት (ፕሮክሲ) ወኪ ነኝ የሚል አዋጅ አውጆ የአገራችን አደጋ ተጨማሪ አካል ሆኖ ተከስቷል

 

 የኢትዮጵያ ሕዝብ በአዲሰ አበባ እና በየ ክፍለሃገሩ “በኡሉሙናቲና በግበረሰድማዊ ቡደኖች” እየታፈነ በረንዳ አደር ሕጻናትና ጎልማሶች “ኩላሊታቸውና ልባቸው” ለሽያጭ፤ ለግድያ እና ለወረበሎች እገታ እየተዳረገ ጭንቅ ውስጥ ሲገኝ ፡ ጫካ ውስጥም  ፋኖ የተባለ “ፐሮክሲ ሚሊሺያ” ጫካ ከገባ ጀምሮ የአማራ ሕዝብ ስቃይ አባብሶ እርስበርስ በቡድን ተከፋፍሎ ሲጋደልና ባንክ ሲዘርፍ ሕዝብ ሲያግት፤ ትምሕርት ቤቶች በመዝጋት “የጫካ አናርኮ ፋሺስት” ወደ መሆን ተሸጋግሯል ስንል “አማራዎች” ይህንን ሃቅ ላለመቀበል “ኮግኒቲቭ ሪዞናንስ” ውስጥ ገብተዋል።

 

 “ነባሩ የአማራ ማሕብረሰብ” ከጥንት ጀምሮ ስፍር ቁጥር በሌላቸው መከራዎች  ከውስጥም ከውጭም ባላንጣዎች በተደጋጋሚ በገሃድና በተዘዋዋሪ ለጥቃት የተመዘገበ ማሕብረሰብ ነው ቢሆንም አንድም ሆነ ሌላ መልክ ያጋጠሙት  ፈተናዎችን መጋፈጥ ተግዳሮቶች ምላሽ በመስጠት በጽናት የቆየ ሕዝብ ነው።

ባለመታደል ሆኖ (የገዛ ጆቹ) የአምሐራ እና የአገው ወጣቶች በጥቃቱ ተዋናይ እና “ፐሮክሲ/የወያነና ሻዕቢያ ወኮሎች” ሆነው ዛሬ በዛው የአደጋ ጉዞ እይተጓዙ እያየሁ ነው። ይ ማሕብረሰብ ለመታደግ እንደ ዜጋ ያለኝን ያህል መራራ የግል አስተዋጽኦ አበርክቻለሁ። ሆኖም ልጆቹ ባሳዛኝ ክስተት ዛሬም ለበካታ አመታት ጭቃ ውስጥ ሲጨማለቁበት በነበረው የ27 አመት መዳከር ዛሬም ‘በጫካም ‘በቲክ-ቶክ እና ‘ዩ-ቱዩብ’ ካንደበታቸው የምንሰማው ክርክርና መዕት ካለፈው ሊማሩ አልቻሉም።

የአማራ ጠላቶች “ወኪል” (ፐሮከሲ) ከመሆን በመቆጠብ ፤ «ወላጆቻችን ተማርከዋል እኛም ተደግመናል» በሉ እያሉ ኢትዮያዊያን (ሙርከኞችን) (የገዛ ነገዳቸው ጭምር) ባልተቀጣ ስድ የወረበላ ባሕሪ በማስጨነቅ፤ እንዲሁም የሽፍቶች ባሕሪ የተላበ የትግል ጔድን ከማሳደድና ከመግደል ተቆጥቦ፤ በራስ ትግልና በሕዝብ በመተማመን የአማራ ተግዳሮቶች በብቃት መክቶ ኢትዮጵያን ቀዳሚ የትግል ዓርማ አድርጎ ካልታገሉ በድል ለመጣት አይቻልም።

ፋኖዎቹ በብሔራዊ ሰንደቅ-ዓላማ ከመጠቅለልና ግድንግድ መሰቀል ደረታቸው ላይ ከማንጠልጠል ባለፈ አገራዊ ዓላማ የላቸውም።

 በአውራጃና በመንደር የተከፋፈሉ ፋኖዎች ተግባራዊና ዘላቂነት ያለው አገራዊ ራዕይ ሰለሚጎድላቸው እኛ አማራዎች ተጨቁነናል በሚል “ሽፋን” ብቻ ጠመንጃ ለታጠቁ መሪዎች እና “የገቢ ምንጭ ለሆነላቸው 24 ሰዓት “በቲክ-ቶክ” ተጥደው በነገድ ስም ሚነግዱ  ‹‹የነገድ ኢንተርፕረነሮች›› (ethnic entrepreneurs) ሲሳይ ሆኖ እያየን ነው። (ለምሳ ለመጥቀሰ “ንድ አማራ /አኪላ... ወዘተ የሚባሉ RT-Ethiopia በሚል “ዩ ቱዩብ” የሚተላለፈው እጅግ አደገኛ ፋሺስት ኤለመንቶችን አድምጡዋቸው ፤ትገረማላችሁ።

ሰማይ ሰማያት የሚንሳፈፉ   መሃይምነታቸውና ጉራቸው “Snobbishness”, “naked egoism” “hubris”, “Chaotic mind” የሚያስተጋቸው የተመሰቃቀለ  አዕምሮአቸው ለከት የለውም።)

አሁን እያየና ያሉት ፋኖዎች ጨቆኑን ከሚሉዋቸው ጨቋኞቻቸው ተሽለ ሊወጡ አልቻሉም። እየጠፋ ያለውን ሕዝብ ሸክሙን እና ስቃዩን የሚያቃልል አመራርና ቡድን ይፈልጋል። አሁን ያለው ፋኖ ራሱን ካልፈተሸና “አማራ” “አማራ” የሚለውን የመነገጃ  “መፈክር” ሰከን አድርጎ “ሃገራዊ ራዕይ” ያነገበ “ፈቃደኛ የሆነ” ሁሉንም ዜጋ ይሚያሳትፍ ትግል ካልጀመረና ካላሳተፈ  በተያያዘው  የዕብደት መንገድ ከቀጠለ የጫካ ጀብደኝነት ከማሳየት አፎ እየጠፋ ያለውን ሕዝብና የታሰሩ ሃገራዊያን መሁራንን ማዳን አይቻልም።

ለሕብረተሰቡም ምክር አለኝ፡

 የተንሰራፋውን ጎሰኝነት ለመቋቋም ከነገድ ፖለቲካ የፀዳ ቅድና የተባበረ ክንድ ማድረግና በጠመንጃ ለሚያስፈራሩ ፋኖዎችም ወያንዎችም፤ ኦነጎችም ሆኑ የኦሮሙማው ወኪሎችን በቃችሁ ማለትና ምግብ መከልከልን አካባቢያቸው እንዳይደርሱ ማድረግን ራስን አስትባብሮ መሪን መፈለግና “አገራዊ ራዕይ” የሌላችውን የጠላት ወኪሎችን “ፕሮክሲዎችን” መጋፈጥን መለማመድ አለበት። በደርግ ጊዜ ትግራይ ውስጥ እያለን ይህንን ነበር ሰናደርግ የነበርው። ያለ ድፍረት ምንም መራመድ አይቻልም።

በአሁኑ ጊዜ በሕብረተሰባችን ሕይወት እየታየ ያለው ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግር ለመፍታት የፖለቲካ መሪ በመታጣቱ (ታላቁ እስክንድር የተቻለውን አድርጎ ሕዝቡ አልነሳም ሲለው ጥሎት ወደ ጫካ መዱ ሊመሰገን እንጂ መውቀስ አይቻልም። እስክንድር በጀመረው “ትግል ድፍረት” ሕዝቡና “ፖለቲካ/ተቃውሚ/ መሪዎች” ተሳታፊዎችና አጋሮቹ ሆኖው ቢገኙ ኖሮ “መጠነኛ ኦክሲጅን” እንተነፍስ ነበር።አሁን ባሳዛኝ ሁታ እስክንድርን ከማመስገን ይልቅ ጥላሸት መቀባትና እሰከ መግደል ተመኙት።የፖለቲካ ረዢም አመታት የትግል ትዝብ እንደ እስከንድር ነጋ ያለ ሃገራዊ ፖለቲከኛ የስም ማጥፋትና የሃሰት ዘመቻ (በግራም በቀኝም በፊትም በኋላም) የደረሰበት ፖለቲከኛ አይቸም ቸም አላውቅም። ሕዝቡ መርዘኛና ቀኛ ፤ የታገለለትን አርበኛ የሚጥል፤ አበኛ ገዳይ መሆኑ የታዘብኩብት አጋጣሚ ነው።

 የእስክንድር ወፍራም ቆዳነትና የፖለቲካ Astute ነት “ሸብረክ አለማለቱ” የሚገርም ጥንካሬው ሳያደንቁ ማለፍ አይቻልም። የጽናቱ የመንፈስ ብርቱነት በሃገራችን ታሪክ ከቶ ታይቶ አይታወቅም!! ታዲያ እዲሀ ያለ ጠንካራ ሰው በጫካም፣ በሃገርም ተከታይ አለማግኘት “በፖለቲካ መዝገብ አዲስ ክስተት” ያደረገዋል።

ለ35 አመት የታየው ይህ የመሪ እጦት (leadership bankruptcy) አፋጣኝ መፍትሄ ካላገኘ የኢትዮጰያ ሕዝብ ካለው ቀውስ ወደ ባሰ ቀውስ ገብቶ “እንደ ሱዳን” የሃገራችን የመኖር ዕድዋም አስተማማኝ አይሆንም።

መሪ ካጣ ሕዝቡ ከታጠቁም ካልታጠቁም ፤ በጎሳ የጣሊያናዊ ፖሊሲ እያያስተዳደረን ካለው ከመንግሥት ኝ ገዢ ሥርዓትም ራሱን ከነዚህ “የመከራ መሪዎች“ ራሱን ነፃ ለወጣት በራሱ መንገድ መወጣጫው መፈለግ ይኖርበታል።

ነፃ እና ኩሩው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁንም በፋኖ ፤ በወያኔ፤ በኦነግና በአብይ ኦሮሙማ በጣሊያናዊ የጎሳ አስተዳደር ሰንሰለት ታስሮ እየተጎተተ እሰከመቸ ይቀጥላል?

ጌታቸው ረዳ   Ethiopian Semay

No comments: