Wednesday, October 22, 2025

የአእምሮ በሽተኛ አለመሆኑን የሚጠራጠር ሰው ራሱ የአእምሮ በሽተኛ ነው! ዳግማዊ ጉዱ ካሣ 10/22/25

 

የአእምሮ በሽተኛ አለመሆኑን የሚጠራጠር ሰው ራሱ የአእምሮ በሽተኛ ነው!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

10/22/25

እንደምን ሰነበታችሁ፡፡ ተጠፋፋን፡፡ ሀገር በጠፋችበት ዘመን “እገሌ የት ጠፋ?” ብሎ የሚጠይቅ የሚዲያ ተከታታይ ሰው እንዲኖር መጠበቅ የዋህነት መሆኑን እረዳለሁና በየትኛውም የሶሻል ሚዲያ አውታር የእኔን ከሚዲያ መራቅ በሚመለከት አንድም ሰው አለመጠየቁ እምብዝም አላሳሰበኝም፡፡ እንደመግቢያ መሆኑ ነው፤ ደግሞም “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” ይባል የለም? እንደዚያ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ላይ የተበተነው አፍዝ አደንግዝ ግን ቀላል አለመሆኑን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡

 አቢይ አህመድ አሊ ለቅጣት መምጣቱን በተደጋጋሚ ስንገልጽ የቆዬን ዜጎች አለን፡፡ ይህ ሰው “እንደሚነግሥ”ም ቀደም ብለን የምናውቅ ጥቂቶች አይደለንም፡፡ የተቸገርነው የጊዜው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ለራሱም ለኛም ሲባል በእናቱ ማሕጸን ሳለ ውኃ ሆኖ መቅረት የሚሻለው ሰው መንበረ ሥልጣኑን ቢያንስ ለሦስት ቢበዛ ለሰባት ዓመታት ይዞ ሀገርንና ሕዝብን መቀመቅ እንደሚከት በቀደምት አባቶች በትንቢት መልክ ይነገር ነበር፡፡ የንግርትና የእውነት ጊዜያት ስሌቶች ስለሚለያዩ ይመስላል ይህ መፃጉዕ ሰውዬ ሰባት ዓመቱን ጨርሶ ስምንተኛውንም ዓመት እያገባደደ የመሆኑ ምሥጢር አንዳንዶችን ግራ ቢያጋባ ትክክል አይደሉም አንልም፡፡ ትንቢተኞችንና ትንቢት አስተላላፊዎችንም ለትዝብት መዳረጉ አልቀረም፡፡ ይሁንና የተባለው አይቀርምና የእኛና የሀገር መደቆስ እውን እንደሆነ ሁሉ የአቢይ መንጋም መፈጠሩን እስከሚጠላ አራት ኪሎ መግባቱን የሚራገምበት ጊዜ እየመጣ ነው፡፡ መንጋው ብቻ ሳይሆን መንጋው እወክለዋለሁ የሚለው የኦሮሞ ሕዝብም አሣሩን ሊያይ ዋዜማው ላይ ደርሰናል፡፡ ይህን አጠቃላይ እውነት መጠራጠር የፈጣሪን ብቻ ሳይሆን የታሪክንም ፍርድ እንደመካድ ነው፡፡ሥልጣን በሸክላና በብርጭቆ ሊመሰል ይችላል፡፡ በእጅ የያዙት ሸክላና ብርጭቆ ደግሞ እጅ ሲዝል ወድቆ መሰበሩ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የሚጠበቅና የማይቀርም ነው፡፡ የቀ.ኃ.ሥ እጅ ዝሏል፤ የደርግ መንግሥት እጅ ዝሏል፤ የሕወሓት እጅ ዝሏል - በዚያም ምክንያት ሁላቸውም በሠፈሩት ቁና ተሰፍረዋል፡፡ አበድሮ ብድሩን ያልተከፈለ የለም፤ ከዚህ ሂደት ሊወጣ የሚችል ማንምና ምንም የለም፡፡

“እማዬ ጣቴን አሳከከኝ” አለቻት አሉ አንዲት ሕጻን ለአካል ጉዳተኛ እናቷ፡፡ እናትም “ልጄ፣ እኔም በአንድ ቀን አልተቆመጥኩም” በማለት መለሰችላት፡፡ አዎ፣ ሥልጣን ይዞ ሞቶ ያንን በሚሊዮኖች ደም የተጨማለቀ ሥልጣን ለማቆየት ሲልም ከደናቁርት ቢጤዎቹ ጋር ቀን ከሌት ውር ውር የሚለው አቢይ አህመድም ጣቱን ከማሳከክ ባለፈ አንጀቱና አንገቱ ተቆራርጦ የመጨረሻ እስትንፋሱ ሊዘጋ ግማሽ ግፋ ቢል አንድ ሐሙስ እንደቀረው እሱ ባያውቅ እኛ እናውቃለን፡፡ መጥፎነቱ አንዳንድ ጣሮች ረጂም ጊዜ፣ ብዙ ወጪ፣ ብዙ ትግስት፣ ብዙ ጸሎት … መፈለጋቸው ነው፡፡

  አቢይ አህመድ በሚዲያ ከተነገሩለት በመቶዎች የሚቆጠሩ የውሸት ንግግሮቹ ውስጥ እነዚህን የሚስተካከል የለም፡፡ እነዚህን የሰማ የሰው ዘር ደግሞ ይህን ሰው እንደዕብድ ከመቁጠር ባለፈ እንደአንድ ጤናማ ዜጋ እንኳን የሚቆጥር ከሆነ ራሱ ሰው ስለመሆኑ ያጠራጥራል፡፡ አንድ ሰው ጤነኛ መሆኑና አለመሆኑ ከሚረጋገጥባቸው መለኪያዎች አንደኛው የንግግሩ ይዘት ነው - እውነት ሀሰትነቱ ማለቴ ነው፡፡ አቢይ ሥልጣን በያዘ ሰሞን “አዲስ አበባ ውስጥ ኦሮሞ ጠል ሕዝብ ይበዛል” ብሎ ሲናገር ያኔ ነበር ከሥልጣን መባረር የነበረበት - አማራንና ኦሮሞን ለማጣላት መፈለጉን ያሳበቀበት ንግግር ነበር፡፡ ለዚህ ሰው ከሥልጣን መወገድ ያቺ ብቻ በቂ ነበረች፡፡ ግን በሚገርም ሁኔታ የላከው የአጋንንት ጭፍራ ሽፋን እየሰጠው ይመስላል ከእርሱም አልፎ ስንቱን ምሁርና ትልቅ ሰው አበለሻሸውና የርሱ ባርያ አደረገው፡፡ ስም መጥቀስ አይገባም፤ አያስፈልግምም፡፡ እንጂ ፕሮፌሰር አልማርያም፣ ዶር. ብርሃኑ ነጋ፣ ዶር. ዳኛቸው አሰፋ፣ ረ/ፕሮ. ጌትነት አልማው … እያሉ መቀጠል በተቻለ፡፡

ከፍ ሲል “እነዚህን የሚስተካከል የለም” ወዳልኩት ሃሳብ ስመለስ አቢይ በዚያን ሰሞን “ ‹በ2030 ኢትዮጵያ ከሁለት የዓለማችን ኃያላን ሀገራት አንዷ ትሆናለች› የሚል ዕቅድ ነድፈናል፡፡ ከዚያም በተጨማሪ በ2100 ኢትዮጵያ ከዓለማችን ሰባተኛዋ በኢኮኖሚና በሥልጣኔ የዳበረች ሀገር ትሆናለች፡፡” ማለቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ ቅዠቱ ይቀጥልና ሰሞኑን በሶፎሞር ዋሻ ባደረገው ንግግር ደግሞ “በቀጣዮቹ ስድስት ዓመታት ውስጥ ሀገራችን ከአፍሪካ በዕድገትና ብልጽግና ስድስተኛዋ ሀገር ትሆናለች፤ በአሥር ዓመት ውስጥ ደግሞ ሰባተኛዋ ትሆናለች” በማለት ደረቱን ነፍቶ ቅንጣት ሳያፍር ደስኩሯል፡፡ እንዲህ የሚወሻክተውም እኛንም አጠገቡ የሚገኙ አሽከሮቹንና ደንገጡሮቹንም በሚገባ ስላወቀን ነው፡፡ አቢ በተፈጥሮው ከማያፍርባቸው ነገሮች ውስጥ ዋነኛው ውሸት በመናገር ማታለሉንና የሚጠላውን ሰው በግልጽም ሆነ በሥውር ማስገደሉንና ወደዘብጥያ አውርዶ ቁም ስቅል ማብላቱን ነው፡፡ ዓለም ታልፋለች እንጂ በነዚህ አይደራደርም፡፡ ጎሣን ከጎሣና ሕዝብን ከሕዝብ ማባላቱንም እንደሃይማኖት የያዘው የሚኮራበት ጌጡ ነው፡፡ የሚገርመው ይህን መሰሉን ሰው መሣይ የአጋንንት ውላጅ አድባር ተቀብላው ስምንተኛ ዓመት የሥልጣን ዘመኑን ሊያከብር መቃረቡ ነው፡፡ ዓለም እንዲህ ናት፡፡ ትገርማለች፡፡

እንደዚህ ያለ ቅዠትና ዕብለት የሚናር ሰው ዘመድ ቢኖረው ወዲያውኑ በሰንሰለት አሥሮ ወደሚቀርበው ጠበል ወይም ክርስቲያን ከሆነ ወደ ጠበል ነበር መወሰድ የነበረበት እንጂ በሞተርና በመኪና ታጅቦ ወደቤተ መንግሥት መሄድ አልነበረበትም፡፡ ይህ የሚያሳየን ሀገራችን ለይቶላት በዕብዶችና በወፈፌዎች የምትመራ መሆንዋን ነው፡፡ የሀገሩን ሰንደቅ ዓላማ የሚጠላና ይዞ የተገኘን ዜጋ የሚገድልና የሚያስር፣ እመራዋለሁ የሚለውን ሕዝብ በዘርና በቋንቋ ከፋፍሎ የሚያባላ፣ ከመናገሻ ከተማዋ ወጥቶ ዐርባና ሃምሣ ኪሎ ሜትሮችን መጓዝ የማይቻልባትን አገር እየመራሁ ነው የሚል ብቸኛው የጉልቤ ጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ አሊ ነው፡፡ ይህን ሰው ሳስብ ወደአእምሮየ የሚመጡብኝ የልቦለድ ገጸ ባሕርያት የ“ዲክቴተሩ” ጄኔራል አላዲንና የደራሲ ሰርቫንቴስ ዶን ኪሾት ናቸው፡፡   

በ2030 ኢትዮጵያ ከዓለማችን ሁለት ኃያላን ሀገራት አንደኛዋ የምትሆነው እንዴት እንደሆነ ለአብነት እንመልከት፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ 37.98 ትሪሊዮን ዕዳ እንዳለባት የሚነገርላት አሜሪካ እና 15 ትሪሊዮን ዕዳ እንዳለባት የሚነገርላት ቻይና በዓለም ሁለቱ በኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ የበላይነት ኃያላን መንግሥታት ናቸው ተብሎ ቢወሰድ (እነራሽያ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን ወዘተ. ቀርተው ማለት ነው) ከ12 ዓመታት በኋላ በ2030 ኢትዮጵያ አሜሪካንን ነው ወይንስ ቻይናን ገልብጣ የሁለተኝነትን ቦታ የምትረከበው? ይህን መጠየቅ የሚያስችል ጭንቅላት ያለው ሰው በአቢይ አካባቢ አለመገኘቱና እንዳይገኝም ሆን ተብሎ በአቢይ መሠራቱ በጄ እንጂ ነገሩ እጅግ አስጨናቂ ነው፡፡ ሀገራችን እየተነዳች ያለችው በምን ዓይነት ደናቁርት እንደሆነ ሲያስቡት ያሳብዳል፡፡ እንደዚህ ያለ ሰው እየመራት ይህች ሀገር አሁን ባለችበት ሁኔታ ራሱ ውላ ማደሯ ይገርማል፡፡ ፈጣሪን ምን ብንበድለው ይሆን ይህን ሰው የሰጠን ግን? ለቁርስ እንኳን የማይበቃ ደሞዝ ለበርካታዎቹ የመንግሥት ሠራተኞች እየከፈለ “ሀገሬ በልጽጋለች ከአፍሪካም በልጣለች” የሚል ወፈፌ ጠ/ሚኒስትር እኮ ነው ያለን፡፡ ጎበዝ እንጸልይ እንጂ!!

አቢይ የአእምሮ ጤናው የተቃወሰ ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ያበደ ነው፡፡ ይህ ጥርጥር የለውም፡፡ አዲስ አበባ ስለተብለጨለጨች የአቢይን ዕብደትና የኢትዮጵያን መፍረስ ልንክድ አንችልም፡፡ እግዚአብሔር ባይጠብቀንና እንደአቢይ የተጣመመ አካሄድ ቢሆን ኖሮ ይሄኔ ለይቶልን ነበር - አሁን ለይቶልን ካልሆነ ማለቴ ነው፡፡ የሰው አንደርባዊ ፀጥታና መከራና ስቃይ ቻይነት ግን ይገርመኛል፡፡

በመጨረሻም አቢይን በጥቂት የእንግሊዝኛ ዐረፍተ ነገሮች እንድገልጸው ይፈቀድልኝ፡፡

Psychologically speaking, Abiy Ahmed Ali is a victim of both possession and obsession which mostly show the psychopathic illnesses of an individual. He is obsessed with his own nightmarish delusional thoughts because of which Ethiopia is almost at the verge of its death, God forbid.

Abiy Ahmed is surely possessed by demons, and as a matter of fact a person who’s possessed by such celestial beings has nothing to do out of his own will. Any person who is possessed by such beings may have little or no control over their own actions, as the being takes over their will”. Disappointingly, Abiy is under the servitude of the negative energy. As most of us understand, a person who has given in to the negative energy is loyal to Lucifer. Here on earth, there are hundreds of luciferian and satanic organizations which stand for the spiritual destruction and deterioration of human beings so much so that humans are denied their heavenly life after their death in the third dimension on earth. This Abiy Ahmed, their puppet in East Africa, who is the master of all kinds of treacheries, is hence the best instrument of the so called Beast, aka, 666, that is responsible for the suffering and massacre of Ethiopians, especially the Amharas, due to the fact that most of the Amharas were, to some extent still are, followers of Christianity.

ለማንኛውም አለሁ ለማለት ነው፤ ቸር ያሰንብተን፡፡ መጪውን የመከራ ጊዜ ቀለል አድርጎልን የማይቀረውን ብርሃነ ትንሣኤ ዘኢትዮጵያ ያሳየን፡፡ በማንኛውም ሚዛን ቢለኩ እርባና በሌላቸው የመከፋፈያ ሰበብ አስባቦች የሚለያዩና እስከመታኮስም የሚደርሱ የአማራ ፋኖዎችንና የትግራይ ጀግኖቻችንን ፈጣሪ አንድ አድርጎልን የቀድሞውን ደግ ዘመን ለማየት ያብቃን፡፡ ምኞት አይከለከልም መቼም፡፡ የጠብንና ግጭትን መንስኤ እያስታወሱ ዝንታለም መናፈር የዕውቀት መለኪያ አይደለምና በቀደመው ዘመን የተጣላችሁና የተበዳደላችሁ ሰሜናውያን ወደቀልባችሁ ብትመለሱ ሁላችሁንም ገድሎና አገዳድሎ በእናንተ ከርሰ መቃብር ላይ በምሥራቅ አፍሪካ ታዋቂ የሆነች የኦሮሞ ሪፓብሊክን ለመመሥረት የቋመጠ ኃይል አራት ኪሎን በመያዙ በጠባችሁ የምታተርፉት እናንተ ሳትሆኑ የጋራ ጠላታችሁ ነውና አስቡበት፡፡ ጊዜ ደግሞ የላችሁም፡፡ የገጠማችሁ ጠላት የሚናቅ አይደለም፡፡ ለመቃብራችሁ እንኳን በማይበቁ ቁርጥራጭ መሬቶች እርስ በራሳችሁ ስትጨራረሱ በማየት ዳር ቆሞ እየሳቀባችሁ ነው፡፡ መሳቅ መሳለቁ ሳያንስ በጀትም መድቦ እያጨራረሳችሁ ነው፡፡ ስለዚህ ንቁ፡፡ ወደኅሊናችሁም ተመለሱ፡፡ ባለፈ ነገር ይማሩበታል እንጂ በንዴት እየተንጨረጨሩ ሌላ የመከራ ወቅት እንዲመጣ የሤራ ጥንስስና የነገር ቁርሾ አያበጁበትም፡፡ ያለፈ አለፈ፡፡ ዕርቅና ሰላም ይውረድ፡፡ በዳዮችና ተበዳዮች ተለይተው በይቅርታና በካሣ ስምምነት ይፈጠር፡፡ ዘላለም ለማይኖርባት ምድር ጠብን አውርሰን ትውልዶችን አናባላቸው፡፡ ጎጃም አቸፈር የነበረን ትግሬ፣ ትግራይ ተምቤን የነበረን አማራ፣ ጎንደር አዘዞ የነበረን ኦሮሞ በመሬትና በእርሻ ምክንያት ማን ነክቶት ያውቃል? በኔ ዘመን ሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀብትና ንብረት ነበር፡፡ ያን ዘመን እንመልሰው፡፡ ያኔ መኖር እንጀምራለን፤ ያለፉትን 35 ዓመታት ከነጦስ ጥምቡሳቸው መርሳት ለደገኛ ኑሮ መሠረት ነው፡፡ አጠፋሁ? ዋሸሁ?

No comments: