የታማኝ በየነ ድግምግሞሽ እና ኢትዮጵያ ጠሊታው በረከት መንግሥትአብ
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay 11/19/25
የጣሊያን
ሙሶሎኒ ፋሺስቶች "የፋሺስት ባህል" ለመፍጠር ሙዚቃ ዓይነተኛ መሳሪያቸው ነበር። ያንን ለማሳካት ታዋቂ ዘፋኞችን
ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታቸው ለማድረግ በሚገባ ተጠቅሞባቸዋል። ኤርትራ ውስጥም
«የሳሕል ፋሺስቶች» ሙዚቃን ጨምሮ ሁሉንም የባህል ዘርፎች ለመቆጣጠር እና “ፋሺስታዊው የሳሕል ፖለቲካ” በኤርትራ ወጣቶች ሕሊና
ውስጥ በመቅረጽ፣ ሚሊዮን ደናቁርት ምሑራን ወጣትና ሽማግሌ የሳሕል ባንዲራ አውለብላቢዎችን ፈጥሯል።
የተረከቡት የፋሺስት ጣሊያንን ፖሊሲ ለማዘመን እና ሕዝቡን «በፋሺስዝም ኤርትራዊ ርዕዮተ ዓለም» ቀርጾ ፋሺዝም እንዲቀበል አስተዋጽኦ ካላቸው የፋሽሲት ሙዚቀኞች ውስጥ አንዱ በረከት መንግሥት አብ ነበር። የዛሬ ጣሊያኖች የፋሺስት አገዛዝ ማብቃቱን ለማስታወስ በየአመቱ ሚያዝያ 25 ቀን የነጻነት ቀን "BELLA CIAO” (ቤላ ቻው/ደህና ሁኚ ቆንጂት) የሚለው ሙዚቃ “ጸረ ጭቆና” በሰፊው ጣሊያን ሃገር በጸረ ፋሺስት ሃይላት ሲዘመር፡ በተቃራኒው ኤርትራ ውስጥ “የሳሕል ፋሺስቶች” ከነፃነት ወደ ባርነት የገቡበትን “መዓልቲ ባርነት” የባርነት ቀን ሲያከብሩ ያሰተማረቻቸው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አፈር ላይ እየረገጡ፤“እንደ ነፃነት” በመቁጠር ባርነትናን ስደትን እያከበሩ እይተናል። ለዚህ ሁሉ ስደት፤ ባርነት፤ ወርደት እና ዕልቂት መሳሪያ ሆኖው ካገለገሉ ሙዚቀኞች አንዱ በረከት መንግሥት አብ ነው።
በዚህ ትንታኔ በበረከት መንግሥትአብ ሕልፈት ምክንያት በኢሳያስ አፈወርቂ መንጋዎች የተዘጋጀ የበረከት የሐዘን አዳራሽ ውስጥ በመገኘት የኛው ሰው ታማኝ በየነ “ትንሹን ሰው በረከት መንግሥት አብን” «ታላቅ ሰው>> «ሙሉ ሰው» ፤ «ባምነውም ባላምነውም
ዓላማውን እና የሚያምንበትን በረሃ ድረስ ገብቶ፤ የሚፈልገውን አሳከቶ ያለፍ ‘ሙሉ ሰው ነው!!» በማለት ስቅጥጥ ሳይለው ስለ የፋሺስቱና ጸር አማራው፤ ጠላታችን ሰለነበረው «የሳሕል ሙዚቀኛ ፕሮፓጋንዲስቱ «ሙሉ ሰው - ሰለ መሆን» ሰለ ነገረን «ወዲ ኣቦይ በየነ» (ታማኝ
በየነ) እንመለከታለን።
ሰላምታ ላስቀድም!! ለብዙ አመቶች የእኔ ጽሑፍ የተከታተላችሁ አንባቢዎቼ እንደምታውቁት በፋሺስት የመንግሥት ወረበላ መሪዎች ፤ በተገንጣዮች ፤ ፖለቲከኞች፤ በተቃዋሚ ሚዲያዎች ፤ ተቃዋሚ መሪዎች እና በሽምቅ ተዋጊ ሃይሎች ላይ የምሰነዝራቸው ትችቶችና ዕርምቶች ሁሉ ጠንከር ያሉና ከተለመደው “ማሞካሸትና መቅለስለስ” ወጣ ያለ ስለሆነ ለብዙዎቹ ጎምዘዝ ሲልባቸው ነበር፤ ዛሬም ያሉ አሉ።
ታማኝ የታወቀ
የመድረክ ሰው በመሆኑ የሚናገራቸው ቃላቶች የሚያበጥራቸው የለም። ሕብረተሰቡ የሊሂቅ ሙርከኛ ስለሆነ፤ የጌታ ቃል ይመስል
ከነገለባው መቀበል ነው። በየስብሰባው እየተገኘ የሚያደርጋቸው አንዳንድ የታሪክ ውሸቶችና መጣረሶች ተከታትሎ የሚያበጥራቸው ብዙም አልነበርም።ጠንከር ያልኩበት እኔ ነብርኩ።
ለምን ጌታቸው ረዳ ብቻ የሚለው ጠያቂ ሊኖር ይችላል። ጌታቸው ረዳ ለተቃዋሚም፤ለጮሌ የመድረክ ሰውም ሆነ ለወያኔ ፤ለሻዕቢያ፤ ለኦሮሙማው መሪ ለአብይ አሕመድ አቃጣሪና እግር
አጣቢዎች ድጋፍ የቆምኩ ሰው አይደለሁም። እኔ የቆምኩት በዚህ አደገኛና ፈታኝ ዘመን ውሸት እያደገች በሄደችበት ዘመን ዕውነት
እንዳትደበቅ ዘብ የቆምኩ የታደልኩኝ ዕድለኛ ግለሰብ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ስለሆነም፤ ማንም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በሚከተለውና በሚሰብካቸው
ንግግሮቹ እውነትና ውሸት ለይቼ ሕዝብን ማስተማር ከወጣትነቴ የጀመርኩት መርህ ነውና ያላወቃችሁኝ እንግዶች ካላችሁ እነሆ ከነ መራራነቴ
ተቀበሉኝ።
አንተ ትችት
እንጂ ሌላ ነገር አታመጣም ተብየ ብዙ ተከታዮቻቸው ተችተውኛል። ለምሳሌ የሻዕቢያው ቱልቱላ ኢሳት እና የብርሃኑ ነጋ አሽቃባጭ
ምሁራን እና 95% በውጭ አገር ኗሪ የሆነው በስሜት የሚጨፍር ኢትዮጵያዊ “ከሻዕቢያና አገር ውስጥ የዘር
ጭፍጨፋ እየፈጸመ ካለው ‘ኦነግ’ ’ የተባለው ደም የጠማው ኢንተርሃሙዌው ወረበላ ቡድን ሲያቆለጳጵሱና “ይግረማችሁ” ብለው አንዳንዶቹም
“ባንዴራቸውን እየያዙ ፎቶግራፍ ሲነሱ ነበሩ” (ለምሳሌ የዘሓበሻ አዘጋጅ “ሔኖክ ዓለማየሁ” ከኦነግ አሽቃባጮች ጋር ሆኖ ባንዴራቸውን
ይዞ የተነሳው ፎቶግራፉን አስደግፌ የተቸሁበትን ተመልሳችሁ አንብቡት-፤
“አርቲስቶች” የሚል ስም የተሰጣቸው ከመጣው ነፋስ ጋር የሚንፍሱ “አዝማሪዎችም”
ጸረ ኢትዮጵያ እና ጸረ አምሐራ አዝማሪ የነበረው እብሪተኛው እና ኦነጉ “ሓጫሉ” ሲገደል ዕምባ እየተናነቃቸው እንዴት ያሽቃብጡ እደነበሩ ታስታውሳላችሁ)፡ ሆኖም እነዚህን የማሞገስና የማሽቃበጥ ባሕሪ ዕርምት መደረግ የነበረባቸው ነገሮች ስጠቁም ጀሮ አጥተው የነበሩ ብዙዎቹ እውነታዎች ‘ግንቦት 7 አጥፊ ነው
ኦነግ፤አጥፊ ነው፤ አማራን ከጥቃትና ከሞት ታደጉት ወዘተ…ወዘተ…’
ስላቸው የነበሩትን የትችቶቼ ዋና መከራከሪያዎቼ ሆነው የነበሩትን ዛሬ ላይ ዕውነት ሆነው ተገኙ።
(ዛሬም ያ
በሽታ በእነ ልደቱ እና «ኢትዮጰያዊ ሆኖ መቀጥልን ልሁን አልሁን ገና ውሳኔ ላይ አልደረስኩም» የሚለን ቴዎድሮስ ጸጋየ (ርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ) ወዘተ መሪነትና አስተባባሪነት እነ ኦነግና ወያነ (ስብሓት ነጋ) ፤ ሕዝቄል ጋቢሳ.....
ወዘተ... ጋር ለመሥራት ያ በሽታ እያገረሸ መምጣቱ ክስተቱ እያየን ቢሆንም) ። ዛሬም ከዚያ ባሕል መላቀቅ አቀብ የሆነባቸው እንደ እነ ታማኝ በየነ የመሳሰሉ
ታዋቂዎች ፤ አሁንም ንቃት የጎደላቸው ወንድሞችና እህቶች “ለምን ዛሬ” እንደሚሉ አውቃለሁ።
ድሮ ያኔ
“ግንቦት 7 ፤ ኦነግ ፤ ሻዕቢያና ልፍስፍስ መሁራንን” አስመልክቼ ስተች “ጊዜው አሁን አይደለም አትተቻቸው ፤ አንዲት ጠጠር ወደ
ወያኔ የወረወረ ሁሉ ወዳጃችን ነው፤ መተቸት የለበትም’’ እያሉ ሲቆጡኝ የነበሩ “መጋኛዎች” ሁሉ ዛሬ ጠጠር ወደ ወያኔ ሲወረውር የነበረ ሁሉ ወዳጃቸው
እንዳልነበረ ግልጽ ሆኖላቸዋል። ያኔ ታማኝን ለተለያዩ
ቀይ መስመር የጣሡ ስሕተቶቹን ስተቸው “ዓይናቸው የሚያጉረጠሩጡብኝ” እንደነበሩ ሁሉ ዛሬም አንደማይታጡ አውቃለሁ። ሆኖም
መራራዋን ዕውነታ ቢከፋችሁም መጎንጨትን አትርሱ።
አሁን ወደ ትችቴ ልግባ፡
ታማኝ በየነ
በኢትዮጵያዊነቱ ጥሩ በጎ ነገሮችን ሰርቷል። በዚያው አንጻር ደግሞ አብይ የተባለው የዘር ጭፍጨፋ ዋና መሪን በማድነቅና በመከላከል
“አል ማርያም” (ከጠበቃ አለማየሁ ገ/ማርያም) ጋር በመሆን መቆየቱና የ2012 የአመቱ ምርጥ ባንዳዎች ተብለው ከዘገብኩዋቸው ምርጥ
ባንዳዎች መካከል በድረገጼ እንደ ለጥፍኩዋቸው ታስታውሳላችሁ።
“ዕድሜየን ሙሉ በሙሉ በፈቃደኛነት እርስዎን ለማገልገል ፈቃደኛ ነኝ” ብሎ ቃለ የገባለት አብይ አሕመድ ሳይውል ሳያድር «እኔ የኢትዮጵያ ጠቅላይሚኒሰትር ሆኜ የማገኘው ደሞዝ በወር $400.00 ምናምን ዶላር (አራት መቶ ምናምን ዶላር) ነው እምበላው። እንደምታውቁት አልሰርቅም፤ ይኼ ሁሉ የሰፈር ጣጣ ለመስማት ግዴታ የለብኝም!” (የአብይ አሕመድ ንግግር) ሲለን፤ ታማኝ ስቅጥጥ ሳይለው አብይ አሕመድ ረግጦ እንዲገዛን ለመተባበር “ከዚህ ወዲያ እኔ ሰላማዊ ሰልፍ ውስጥ አታዩኝም” በማለት «ዶ/ር አብይ የተሸከመው ችግር እኛ ለአንድ ቀን መሸከም አንችልም፡ ዶ/ር አብይ በገዛ ፈቃዴ ለቅቄያለሁ ቢለን ምን ሊውጠን ነው!!?» በማለት የፍርሐት ፖለቲካ (ፊር ፖለቲክስ) በማሰተጋባት እርሱ እና አል ማርያም ሆነው በርካታ ማሃይም መሑር እና ያልተማረው ማሕበረሰብ አብይን እንዲያመልኩ አጃጃሉ/ሰበኩ።
አብይ አሕመድ “ገና ከዚህ በባሰ ደረጃ ሰው ያልቃል ፤ ከዚያ በኋላ
ይረግባል” እያለ የዘር ጭፍጨፋ እንሚቀጥል የጭፍጨፋው ተባባሪ እንጂ ጭፍጨፋን የሚያስቆም መሪ እንዳለሆነ ሳያፍር
ሲናገር፤ “ሞትን ለምንድ ነው የምታካብዱት፤
የዘር ጭፍጨፋ (በራሱ ቃል “ግጭት”) ሲፈጸም ለምንድ ነው የምታጋንኑት፤የምትጮኹት፡ “ግጭት የሚባል ግድያ የሚባል መስማት፤መታየት
የለበትም የምትሉ ሰዎች ‘ብታሰቡበት ጥሩ’ ነው።” በማለት አብይ አሕመድ ግድያና ጭፍጫፋ መቀጠል እንዳለበት እንጂ
መቆም እንዳለበት አትናገሩ ብሎ ሲል ፤ ታማኝ
በየነ ድግሞ «ሂደት ነው፤ሚራክል አንጠብቅም» እያለ ለአብይ
የገባለትን የአገልግሎት ቃል ኪዳን ፈጽሞ አብይ አሕመድን አገልግሎ ከወጣ በኋላ በሐፍረት ይሁን በራሱ ልዩ ምክንያት ድምፁን ሲያጠፋ
“ታማኝ የታለ! ታማኝ ምን ነካው??!!” እየተባለ ጥያቅ ሲቀርበለት ነበር።
ታማኝ ማነው
ነው? ስል ታማኝ መጥፎና በጎ ጎኑ ለመጻፍ መጻሕፍቶች ይወጡታል።ታማኝ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ እኩልነት እንዲረጋገጥ፣
ብሄራዊ አንድነት እንዲጎለብት፣ ፍትህ እንዲሰፍን፣ ዴሞክራሲ እንዲመሰረት እና ሰብአዊ መብት እንዲከበር ያለምንም ማቋረጥ ሲታገል
ቆይቷል፡፡ይህ አልክደውም።
እዚህ ላይ ስለ ታማኝ ማንነት ለመጻፍ አልሞክርም፤ በዙ መልካም ጎኖች ያሉትን ያህል ፤ታማኝ በየነ ለአገሩ ያለው ሁነኛ ፍቅር እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የፖለቲካ ብስለቱና በንግግሩ ውስጥ የሚዘባርቃቸው ንግግሮች የሰዎችን አመለካከት የሚያዛቡ ሆነው የታዘብኳቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው። ከጠላት ጋር መተሻሸተና የማድነቅ በሽታ በፖለቲከኞች እና በታማኝ ብቻ ሳይወሰን በዙዎቹ አዝማሪዎች አብይን ፤ ወያኔ እና ሻዕቢያን በማወደስ መከራችን አሳይተውናል።
ዳዊት ፅጌ የተባለ ዘመን
የወጣለት ወጣት አዝማሪ ዕርቃኑ የወጣ የሻዕቢያ አጭብጫቢ ሆኖ ስለ ሞቱት ሻዕቪያ ፋሺስት አዝማሪዎች እየደጋገመ ልቡ እየደማ ብዙ አሽቃብጧል።
“ካሁን ወዲህ ኢትዮጰያዊ አይደለሁም፤ ልሆንም አልፈልግም! መብቴ ነው” እያለ የሚቃዠው የጎንደሩ ጠባብ ጎሰኛ
አዝማሪ “ፋሲል ደሞዝ” ወዘተ
አብይን እና ሻዕቢያን የሚያወድሱ ዘፈኖችን በመዝፈን ሕዝብን በማሳሳት እያንዳንዳቸው መሳሪያ ሆነዋል።
ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች በሚል ርዕስ ካካተትኩዋቸው አዝማሪዎች መካከል ሐመልማል አባተ የተባልቺዋ አዝማሪት አብይ አሕመድ በቀደደላቸው ቦይ ተጠቅመው ወደ አስምራና ከረን ከተማ በመጓዝ ያሰደመጠችን ዘፈን ታስታውሱ ከሆነ በወቅቱ የሚከተለው ትችት ለጥፌ ነበር፡
« የነ ሓመልማል
ወደ ‘ባሕረ-ነጋሽ’ ዘልቆ የጠላት ባንዴራን ማውለብለብ መሰሪው ‘መለስ ዜናዊ” አዝማዎሪዎቹን ወደ አስመራ እየላከ “ኤርታዊት
ኣዶ እዚ’ኹሉስ ኣይሳላኽንዶ” (ኤርትራዊት እናት ይህ ሁሉ ጀግንነትና ድል ያንቺው ማህጸን ያስገኘው ፍሬ ነው” እያሉ፤ የኤርትራ እናቶች ማሕጸን ጀግኖች የሚያፈራ፤ የኢትዮጵያ እናቶች ማሕጸን
ግን የተኮላሸ “ጀግኖች የማይወልድ” እያሉ ወንጀል ሲሰሩት እንደነበረው የወያኔ አዝማሪዎች ሁሉ ፡ ዛሬ በባለተራዎቹ በኦሮሞዎች መንግሥት
የተላከቺው ሓመልማልና መሰል አለቅላቂዎች “በወንድማማችነት
ሴራ ስም” የጸረ ኢትየጵያ ፕሮፓጋንዳዊ ዘፈን የሰራቺው
‘ሓመልማል አባተ’ “ከረንን ያላያ፤ምፅዋን ያላየ ይፍረደኝ” እያለች
በተሰውት አርበኞቻችን ስታላግጥ ነበር (እስዋ ያየቺው መጽዋና ከረን
እኛ ካየነው መጽዋና ከረን ለየቅል ናቸውና)። ሻዕቢያዎችና ወያኔዎች
በመተባበር በሠራዊቶቻችን እና በኢትዮጰያዊያን ሕይወት ላይ በነዚህ
ከተሞች የተፈጸመው ዘግናኝ “ጀነሳይድ እና ክሕደት” ስለ ከረን ጀግንነታቸውና እና ስለ ምፅዋ ስታወድስላቸው መስማት እጅግ አንጅት ያሳርራል።
ይህ እንዳይበቃት ሲነማ ኦዴን በተባለው ጣሊያን በገነባው የሲኔማ አዳራሽ ተገኝታ
“ፈልጌ እጥቼው
የነበረው ጉብል ፤ በሩ ሲከፈት አገኘሁት ጉብል“ (ፓራፍሬዝ)
እያለች “በረከት
መንግሥትአብ” እንወዳሃለሁ! እናከብርሃለን!” እያለች ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ ግጥም ሳይጨምርበት የማይዘፍነውን የሻዕቢያው ሎሌ “ በናፍቆት ስትቃጠል የነበረቺው
የበረከት መንግሥትአብ ጉብልነትና መልከ ውብነት ድንገት ስታገኘው” በሕዝብ ፊት እየዘለለች ስታሽቃብጥለት መስማት የማሃይምነትዋ
መጠን ቀይ መስመር ያለፈ ነበር።(ምንጭ - የሐመልማል
አባተ ባንዳዊ ተልዕኮ በኤርትራ! ከጌታቸው ረዳ Ethio Semay - January 1, 2020)
እንግዲህ ከታማኝ ጀምሮ ፤ ነዋይ ደበበ እሰከ ታች ድረስ ያሉት አዝማሪዎችና ተዋናያን እንዲሁም የእስፖርት ባለሞያዎች እነ ሃይለ ገ/ሥላሴ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለጠላት ሲያለቅሱ፤ ሲያወድሱና ሲያሽቃብጡ አይተናል።
ወደ ዋናው
ተዋናይ ወደ ታማኝ ልመለስና ካሁን በፊት ሰለ ታማኝ በርካታ መጥፎ ጎኖቹን በትችቶች መልክ ሰላሳተምኩ እዚህ አልሞክረውም። ሆኖም
ከብርካታ መጥፎ ጎኖቹ ሁሌም ከሕሊናየ የማይረሱኝ አንድ ሁለቶቹን ልጥቀስና ታማኝ ስለ በረከት መንግሥት አብ ሕልፈት የተናገረውን
መወድስ `እገባለሁ።
1ኛ-«ከሚሊዮን አማራ ይልቅ ለአንድ አንዳርጋቸው ጽጌ»
በሚል ርዕስ» በ2014 “በፈረንጅ አቆጣጠር” አንድ ትችት ጽፌ ነበር። አቶ ታማኝ በየነ በ2014 ካሊፎርኒያ/ሰናሆዘ ከተማ የኢትዮጵያዊያን
የአመቱ የስፖርት በዓል በተከናወነበት ወቅት ‘የሞረሽ ወገኔ አማራ ድርጅት’ መሪዎች ባዘጋጁት ሕዝባዊ ስብሰባ/ኮንፈረንስ/ በእንግዳ
ተናጋሪነት አኔ እና እውቁ የታሪክ ምሁር ዶ/ሃይሌ ላሬቦ፤እና እውቁ ሊቀ ሊቃውንት ዶ/ጌታቸው ኃይሌ ተጋብዘን ነበር። በወቅቱ እኔ
ያቀረብኩት ጥናት “የትግሬ ልሂቃን በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው?” በሚል ርዕስ ለጉባኤው አቅርቤ ነበር። በወቅቱ
የታማኝ በየነ “አንበሳ” የግንቦት 7 መሪው ‘አማራ የሆኑ ወታደሮችን በመምረጥ ሲገድል የነበረው የኢሳያስ አፈወርቅ’ አሞጋሽ የሆነው
አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ታፍኖ ከየመን ወደ ኢትዮጵያ ተወስዶ በነበረበት ወቅት ስለነበር፤ ግንቦት7/ ኢሳት/ ባዘጋጀው ሕዝባዊ
ጉባኤ ለመሳተፍ አቶ ታማኝም በጉባኤው አዳራሽ ተገኝቶ ነበር።
በወቅቱ ታማኝ
በየነም ሆነ የታማኝ በየነ ኢሳት “ሚዲያ” ለነብርሃኑ፤ ለነ አንዳርጋቸው፤
ለነመሳይ ከበደ….ለነ…ለነ….. ጉባኤ እየጠሩ ሕዝብ ሰብስበው ሲጮሑ ፤መድረክ ሲከፈትና በየአገሩ ተደጋጋሚ መድረክ ሲዘጋጅ፤እኔ
እስከማስታውሰው ውቅት ስለ አማራ ጉዳይ የተዘጋጀ “አስቸኳይ ልዩ ሕዝባዊ መድረክና የምሁራን ጥናቶች የተደረገበት መድረክ” ብዙም
አላስታውስም። ያውም እዚህ ሳንሆዘ ካሊፎረኒያ ውስጥ፤ ስለ አማራ ጉዳይ “ሞረሽ” ያዘጋጀውን መድረክ አማራዎቹ እነ ታማኝ በየነ
እና የመሳሰሉ ታዋቂ የኢሳት ሰዎች የአማራውን መድረክ ለመነጋጋር የተዘጋጀውን አዳራሽ እየረገጡ፤ በጎሪጥ አዳራሹን እያዩ በማለፍ
ኢሳት ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ አዘጋጀው መድረክ እና አዳራሽ ነበር የሄዱት (አዳራሾቹ/ከፍሎቹ/ ደግሞ በሚገርም ሁኔታ በግድግዳ
የተያያዙ ጎን ለጎን ናቸው። እንደምጠረጥረው (በጥናት ወይንም ባጋጣሚ?) አዘጋጆቹ ሆን ብለው የአማራውን መድረክ ሰው እንዳይገባበት
በሚመስል መልኩ ሞረሽ ባዘጋጀው ሰዓት፤ቀን እና ቦታ አዘጋጅተው፤ ሕዝቡ ጎን ለጎን በሁለት አዳራሽ ባንድ ሆቴል ባንድ የጊዜ ሰለዳ
የመሰብሰቢያ አዳራሽ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለየቅሉ ተከፍሎ ነበር የተሰበሰበው።
በዚህ ላይ
እኔ የሞረሽ ተናጋሪ እንግዳ ሆኜ ተጋብዤ ስለነበር፤ የተጠራሁበት አዳራሽ ደጃፍ አጠገበ ሰዎች እያነጋገሩኝ ቆሜ ስለነበር ፤ ልቅሶ
ደራሽ የመስል እንበደ በግ ግር በሎ እየተጋፋ እኛን እየጣሰ ወደ አንዳርጋቸው «ልቅሶ» ሲንጋጋ አይቸ ጉዳዩ ትኩረት ሰለሳበኝ፤
እየተገርመኩ እያለሁ፤
“ታማኝ በየነም” አብሮ ከመነጋው ተንጋጊው ጋር ለጸረ አማራውና ለኢሳያስ ፐሮፓጋንዲስቱ ለአንዳርጋቸው ጽጌ ጩኸትና ድጋፍ ለማስተጋባት ወደ አዳራሹ ሲያመራ፤ የሚጮኽለት ያጣው ለሚሊዮኖች የሚቆጠር አማራ ሕብረተሰብ የተዘጋጀው ሕዝባዊ ጉባኤ እንደጠላት ጉባኤ በጎሪጥ ዓይኑ ሰረቅ አድርጎ እያየ ረግጦት ከመሳሰሉ ታዋቂ ሰዎች ጋር ነበር ወደ አንዳርጋቸው አዳራሽ ሄዶ ንግግር አደረገ። በሚያስዝን ሁኔታ ያንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ መያዝ ታማኝን ለማድመጥና ቁጣውን ለምግለጽ የመግቢያ ገንዘብ እየከፈለ የተንጋጋው “የበግ መንጋ” አዳራሹ ጠብቦት 99% አማራ ነበር። ስለ አማራ ሕዝብ ሰቆቃ ፤ መታፈን፤ መርዶ ፤ መጨፍጨፈና መከራ ለመስማት እኛ ጋር የተገኘው ምናልባት 20 ሰው አይሞላም *ያውም ይመግቢያ ክፍያ በነፃ ነው)።
አንዳርጋቸው
ጽጌ ለታማኝ በየነ በአፍሪካ ምድር ውስጥ ያልታየ የዘር ማጽዳት ከተካሄደበት እልፍ ሚሊዮን አማራ ሕዝብ ሕይወትና ብሶት በልጦበት
ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ ሲያለቅስና የኔ አምበሳ እያለ ‘የራሱን ሽልማት’ አውልቆ
ለአንዳርጋቸው ጽጌ ሲሸልመውና ሲያለቅስለት መኖሩን በኔ
በጌታቸው ረዳ በኩል ታሪክ ዘግቦታል። ያንን ትችት በመተቸቴ፤ አጎብዳጅ ሁላ፤ተታዋቂ ፖለቲካ መሪ፤ ታዋቂ ጸሐፊና ደራሲ ፤ታዋቂ
የሚዲያ ሰው፤ ዝነኛና የመድረክ ሰው መንካት/መተችት አይገባም እያልክ የምታነፈንፍ የሊሂቃን እግር አጣቢ ሁላ ከዚህ ባሕሪ ውጣ።
እያልኩ የወቅቱ ምሬቴን እግለጽ እንደነበር ታስታውሳላችሁ።
የማልረሳለት ሁለተኛው ትዝታየ
2ኛ- አገራችን ላይ እስካሁን ድረስ መከራችን እያሳየን ያለው በዘር የተመሰረተው፡ አፓርታይድ፤ በአማራና በጋሞ እና በተቀሩት ሕዝብ ላይ ጀነሳይድ እንዲካሄድ ኢትዮጰያ እንድትፈርስ በመዋቅር ተዋቅሮ የተንሰራፋ ኩፉ ሰዎች የሚመሩት የወረበሎች መንግሥት መሪው መለስ ዜናዊ በሕዝብ ተከስሶ በኢትዮጵያ አምላክ ፊት ቀርቦ ከዚህ ዓለም እንዲወገድ ሲፈረድበት ፤ ብዙ ሰዎች ልባቸው ደንግጦ አልቅሰውለት መኖሩን አስታውሳለሁ። ከነሱ መካከል “ልቡ ተንቀጥቅጣ በድንጋጤ እና በሐዘን ባለበት ደርቆ መቆሙን” የከያኒያኖቹ ቁንጮ ታማኝ በየነ በመለስ ሞት የተሰማው የእስቶክሆልም ሲንድሮም ድንጋጤ እና እሱ ሳይታወቀው ከሕሊናው ውስጥ ገብቶ የተለማመደው፡አንዳች ነገር ከሕሊናው የተነጠቀ ነገር የመሰለው የተሰማው “ባዶነት፡ በሚገርም ሁኔታ በመራራ ሐዘን እንዲህ ሲል ስሜቱን ሳይደብቅ ገልጿል::
ታማኝ እንዲህ ላይል::
"አውነቴን ነው የምለው ደነገጥኩ፡
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰውነቴን መቆጣጠር አቃተኝ።(ከው ብየ) አዘንኩ። አውነት እንዴት እንደምገልጸው አላውቅም፤በጣም
ደነገጥኩ።አዘንኩ።ምንም ይሁን ምንም ባደግንበት ሠፈርም ይሁን “የለመድነውን ነገር ስናጣ” የተሰማኝ ስሜት አለ።ለሃያ አንድ አመት
በእኚህ ሰውየ ዙርያ ብዙ ነገር አይቻለሁ፤አድምጫለሁ፤ብዙ ብዙ ነገር ….እና….በጣም ለምጃቸዋለሁ፡ እና ሞቱ ሲባል የተሰማኝ
ነገር ቀላል አይደለም።…..የተሰማኝ ስሜት ሐዘን ነበር።“ (ታማኝ በየነ (ስለ ጸረ አማራው ፋሺስቱ መለስ ዜናዊ ሞት ከኢሳት ጋር
የደረገው ቃለ መጠይቅ)፡ «በመለስ ሞት ልባቸሁ ጥቁር ለለበሰ የተቃዋሚ መሪዎች ጽናቱን ይስጣችሁ እንላለን! ጌታቸው-ረዳ (Ethiopian Semay)
9/9/12)» ከሚል ትችት የተቀነጨበ መረጃ።
ታማኝ ዛሬም ያንን ስሕተቱን በመድገም የሻዕቢያው ታጋይ የአምሓራ ሕዝብና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ታሪክ የወጋ ፤ የበላበትን የኢትዮጵያ ድስት ሰባሪው በረከት መንግሥት አብ በመሞቱ ምክንያት «ላመነበት እስከ መጨረሻ የቆመ ሙሉ ሰው” ሲል የሻዕቢያ አለቀላቂ አዝማሪዎች በተገኙበት አዳራሽ ድረስ በመሄድ አስነዋሪ ቅልውጥናውን አስደመጠን። እሰኪ «የሙሉ ሰው» መሆን ትርጉም ምንነት የምታውቁ ካላችሁ እባካችሁ እሰኪ አስረዱኝ?!!!
አልገባችሁ
ሰዎች ካላችሁ ዛሬም ከኤርትራኖች (ከጥቁር ጣሊያኖች ጋር) ጦርነት ላይ ነን፤ ሰላም የለንም። ስለዚህ በጦርነት ወቅት ጠላትን መርዳት ክህደት ይባላል። ይህም በተለይ 'ከጣሊያን እና የጣሊያን
ፖሊሲ ከሚያራመዱ ኦንጎች ፤ ሻዕቢያዎች እና ወያኔዎች’ ጋር መቀላቀል፣ ሙገሳን ማስተጋባት ፤ ዕርዳታ እና ማጽናኛ መስጠትን' ይቅር
የማይባል ክሕደት ነው።
ታማኝ እንዳለው
መለስ ሲሞት ““የለመድነውን ነገር ስናጣ” የተሰማኝ ስሜት አለ።ለሃያ አንድ አመት በእኚህ ሰውየ ዙርያ ብዙ ነገር አይቻለሁ፤አድምጫለሁ፤ብዙ
ብዙ ነገር ….እና….በጣም ለምጃቸዋለሁ፡ እና ሞቱ ሲባል የተሰማኝ ነገር ቀላል አይደለም።…..የተሰማኝ ስሜት ሐዘን ነበር።” ያለበትን
ሰታገናዝቡት ታማኝ መለሰን ለመዶታል (ዲካተሮች ሲውል ሲያድር የለመዳሉ) አሁንም በረከት መንግሥት አብ ሲሞት ከልጅነቱ ጀምሮ
ሲያደመጠው የነበረው ሙዚቀኛ ሞተ ሲባል የተሰማው ሐዘን የመለስን ያህል ድንጋጤ የተሰማው ቢሆንም “ሙሉ ሰው ነበረ ያለበትን ምክንያት
ባይነግረንም “ስሜት ኮርኳሪው ሙዚቃውን እንጂ” ሙዚቃው ያስከተለው “ውድመትና በኤርትራ ወጣቶች ሕሊና ላይ ስለ ጠላቻና ኢትዮጵያ
ቅኝ ገዢነት የሰበከና ሚሊዮን ኤርትራዊያን ወጣቶችን በሙዚቃው ሰብኮ ወደ ጫካ ያሰኮበለላቸውን የሙዝቃ ሥራዎቹን ” ለታማኝ አልታየውም።
መደምደሚያ፡
አንዳንድ
መሁራን እና ሐያሲያን፤ አምባገነኖች እና የአምባ ገነኖች መሳሪያ ሆነው ያገለገሉ ሰዎች ሲሞቱ ሐዘኔታቸው በመራራ ሐዘን ለምን እንደሚገልጹ
መላምታቸው ሲነግሩን “የፖለቲካ ሰዎች ስለሆኑ፤ የዲፕሎማቲክ ቋንቋ በመጠቀም መግባባትን ለማስፈን ‘ለሽፋን’ መጠቀማቸው ነው” ሲሉ
ይደመጣሉ። ይህ በጣም የተሳሳተ መላምት ነው። በአምባገነኖችና አገልጋዮቻቸው የተገነባው ግምብና አንድነት በሕዝብ ሕሊና ውስጥ የተዘረጉ
የስነ ኣእምሮ እና የሕሊና ክሮችን ባለመፈተሽ፤ ነገሮችን ካለመረዳት የመጣ ድምዳሜ ስለሆነ ነጭ ባንዴራን ከማውለብለብ እንቆጠብ።
ጌታቸው ረዳ
(Ethio Semay አዘጋጅ)
No comments:
Post a Comment