የኢትዮጵያዊው እስከንድር ነጋ ቃለ መጠይቅ ኢትዮጵያ ጠሊታው የአምሐራ ብሔርተኛው ፋሺስት
ቡድንን ኩፉኛ አስቆጥቶቷል
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
11/28/2025
በፎቶግራፉ ላይ የሚታዩት ሁለት የፍኖ መሪዎች የአምሐራ ተወላጆች የኢትዮጵያ ቁርጥ ቀን ልጆች የሆኑ «ጸረ አምሐራ ጠላቶች ወያኔና ኦንግ ያረቀቁት በሥራ ላይ ያለው አፓርታይዳዊ ሕገ መንግሥት አንቀበልም ብለው ያኮሩን አረበኞቻችን «እስክንድር ነጋ እና ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ» ናቸው።
ፋኖ ውስጥ የተሰገሰገው ይህ የተቆጣ ብሔረተኛ ፋሺስታዊው ቡድን ማንነቱን በተደጋጋሚ ሳይደባብቅ ነግሮናል። ይህ ቡድን የአምሐራን ጥቃት አስቆማለሁ በሚል ማታለያ ገብቶ ለአምሐራ ጥቃት ቀንደኛ ተጠያቂዎች የሆኑት ወያኔዎች እና እና የሻዕቢያ መሪዎች ከነ ተከታይ ሕዝባቸው ለማጥቃት ከሚመጣው ማንኛውንም አጥቂ ለመከላከል እነሱ ከመሞታቸው በፊት የአምሐራን ሕዝብ ለነሱ ሲል መስዋዕት እየከፈለ “ሞትና ውድመት” እየተጎነጨ ሕልውናው እንዲያከትም እናደረገዋለን ወደ እሚል ግልጽ የጸረ አማራ ሕዝብ ቡድን ተቀጣሪዎች እንደሆኑ ያወጁት አዋጅ ወደ ሕዝብ ጀሮ ከተዳረሰ ሰንብቷል።
ከዚህስ ወዲያ ወዴት ነን? ብሎ የተቃወማቸው የራሳቸው ተራ ታጣቂ ሲያምጽና ሲጠይቃቸውም አልሰማሁም።
ለጸረ አምሐራ ቡድኖች ባርያ
መሆን ብቻ ሳይሆን የአምሐራን ማሕበረሰብ የዘር ጥቃት ማስፈጸሚያ የሆነውን የወያነ *አፓርታይዳዊ*
ሕገመንግሥት በብዙ የፋሺስት ነገዶች ሰለተደገፈ እኛም ከፋሽስቶቹ ጋር በመወገን *አፓርታይዳዊ* የነገድ ሕገመንግሥት እንዲቀጥል
እንታገላልን ብለዋል (ሁለተኛ ውርደት)።
እስክንድር ከሁለት ሦስት ሳምንት በፊት ከውጭ አገር ሚዲያ በሰጠው የመታገያ አቅጣጫ ማስፈንጠሪያው የአምሐራ ሕልውና ሲሆን ማጣቀሻው ግን ኢትዮጰያዊነት ፤መሆኑን በመግለጹ ምክንያት ፤ ፋኖ ውስጥ የተሰገሰጉ «የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ሰለባቸው ከብሄር ፖለቲካ ውጭ ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካ የማይታሰብ ነው የሚሉ ጨለምተኞችና በአፍቅሮ ወያኔ ጭንቅላታቸው የተሰለቡ ግለሰቦች እስክንድር በሰጠው ቃል መጠይቅ ውሃ የማይጨብጥ ትችት አቅርበዋል» (አበበ ካሳሁን)፤
ይህ ደግሞ የወያኔ ፖለቲካ እንቀበላለን የሚለው ኢትዮጵያ ጠሊታው የአምሐራ ፋሺስቱ
ቡድን፡ ኢትዮጵያዊው እስክንድር ነጋን አምሐራ ሳይሆን “ኢትዮፒያኒስት ነው” በማለት (እኛንም ጭምር ሲጠሩን እንደዚያ
ነው የሚጠሩን) ሲንጨረጨሩ በየሚዲያው ሰምተናቸዋል።
“አንተ ብሔርተኛ ነህ?” የሚል ጥያቄ ቀርቦለት « “ብሔርተኛ አይደለሁም” ፡ “በአምሐራ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረው የዘር ማጥፋት ህልቀት ለማስቆም ወደ ጫካ የገባሁ ኢትዮጵያዊ ነኝ» ብሎ በመመለ;
“የአምሐራ ፋሺስቶች” እስክንድር ነጋን «አምሐራ አለመሆኑን ይኸው ነግሮናል። እሱ ኢትዮጵያዊ እንጂ አምሐራዊ አይደለም ስንል አልሰማም አላችሁ። አሁንስ ኢትዮጵያዊ ትግል ለማራመድ እንደወጣ አሁን
ግልጽ ይሁንላችሁ!!» ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ‹የለመዱትን የብልግና ስድባቸውን ሲያዘንቡበት አድምጥኩ»።
ኢትዮጵያዊ ነኝ በማለቱ የታወቁ የፋኖ መሪዎችና ሚዲያዎቻቸው እና ውጭ አገር የሚኖሩ የ“ቲክ-ቶክ” (የአየር
ሞገድ ጠጅ ቤት) ሰካራሞችን አላስደሰተም።
በፋኖ ስም ጭምብል ያጠለቁ የወያኔ እና የሻዕቢያ ተቀጣሪ የፋኖ ታጣቂ መሪዎችን ብቻ ሳይሆን ያስቆጣ፤ ወያነ 27 አመት በየትምሕርት ተቋማትና ማሕበራት ሰለ “ብሔርተኛነት መሆን” እየቀጠቀጠ ባሕሪያቸው ለውጦ የቀረጻቸው ወደ ውጭ ሃገር የተሰደዱ ሃያ አራት ሰዓት ቀንና ማታ በየአየር ሞገድ ጠጅ ብቶች ተጠምዶ ዘረኝነትን ሲያሰራጭና ሲጋት የሚወል የአምሐራ ወጣትም (7 ትውልድ የደም ጥራት ጠያቂዎቹ እነ አቶ ተክሌ የሻው እና በኢሳያስ አፈወርቅ “ፍቅር ልቡ የነደደው” ማሃይሙ “ኢንጂነር” ይልቃል ጌትነት፤ የመሳሰሉ ነጭ ጠጉር ያበቀሉት ጭምር ሳይቀሩ) እስክንድርን ‘ኢትዮፒያኒስት” እያሉ የሰው ልጅ ገዳይ ‘’ኩፍኝ በሽታ’’ የሆነው «ጠባብ ብሔርተኝነት» እያሰራጩ እያደመጥናቸው ነው።
ባልጠበቅነው ክስተት ዘረኝነት ወደ “አምሐራ ወጣት” ሕሊና ተሸጋግሮ እርስበርስ “ኢትዮፒያኒስት ፤ ምስራቅ ጎጃሜ ፤ ምዕራብ ጎጃሜ ፤ ወሎየ ፤ሽዌ፤ ጎንደሬ ፤ ጎጃሜ ታች ጋይነቴ....ወዘተ ወዘተ.. በሚል እየተጋደሉ እነሆ ኢትዮጵያዊነትን “በማውገዝ” እስክንድርን “ኢትዮፒያኒስት” የሚል ቅጽል መስጠት የሚያሳየን ጠቋሚ ድምፅ ነፍጥኛ ሲባሉ የነበሩበትን የሕልና ቁስል ዛሬ ያንን በግልባጭ “ኢትዮጵያዊውን” እስክንድር ነጋን እና እኛን “ኢትዮፒያኒስት” የሚል መጠሪያ (ኮድ) ሰጥተውናል። ዕድሜ መስተዋቱ!!!! የሚባለውም ለዚህ ነው።
እስክንድር ነጋ፤ ከተማ ውስጥ ሰላማዊ ትግል ሲያካሂድም ሆነ ጫካ ውሰጥ ገብቶም ብዕርና ፖለቲካዊ ትምሕርት ከማንገት ውጭ «ጀርባው ላይ ብረት አንግቶ አይቸው አላውቅም»። የእስክንድር መሰረተ ድንጋይ (ባሕሪ) የሰውን ልጅ ላለመግደል የሚጠነቀቅ፤ እጅግ ትሁት፤በሙሉነት መተማመን (ኮንፊድንስ) የሚያሳይ፤ ተጻባኢዎቹን በጸያፍ ቃል አጸፋ ከመመለስ የሚጠነቀቅ; ብርቱ “ሞራሊስት” ነው። ይህ ደግሞ በተግባር አሳይቷል።
በእስክንድር ዙርያ ብዙ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተደርጎበታል፤ ከተማ ውሰጥም ፤ ጫካ ውስጥም የመግደል ሙከራ በሥርዓቶቹ እና በፋሺስት አክራሪ የፋኖ መሪዎች
የግድያ ዛቻ ደርሶበት ታዝበናል። የእስክንድር ራዕይ የፋሺስት ፋኖ መሪዎቹም ሆኖ አከራሪ ደጋፊዎቻቸው የእስከንድርን ራዕይ አይቀበሉም፡ የገቡበት ፖለቲካዊ ረቂቀነትንም
አላውቁበትም (ሰላላውቁበትና በራስ መተማመን ሰለጎደለባቸው የወያኔ እና ሻዕቢያ
አቧራ ወልዋይ ሆነው አረፉት)።
በዙዎቹ እየተነበረከኩ ለጠላት እየሰገዱ በየወቅቱ ልሳናቸው ሲለዋውጡ እስክንድር ከተማም ሆነ
ጫካ ለሚቀርብለት ቃለ መጠቅይ ልሳኑን ለውጦ አያውቅም። ለምሳሌ ከሁለት አመት በፊት እስክንድር ለካናዳዊው ጋዜጠኛ ‹ለጀፍ ፒርስ› የሰጠው ቃለ መጠይቅ ምን ነበር ያለው? አምሐራ ብለን የተነሳነው “ኢትዮጵያዊነታችንን ለመጣል ሳይሆን”
<< እኛ የብሄር ስም እና ማንነታችን ያገኘነው የዘር ማጥፋት ሰለባ ከሆኑትሰዎች ነው። ሰለሆነም የእኛ ትልቁ ተልዕኮ እና ራዕይ የዘር ማጥፋት መከላከል ነው>> Sep 8, 2023 ከጄፍ ፒርስ ቃለ መጠይቅ። ይላል እስክንድር። ግልጽ ነው?
አንዳንድ ይፋኖ ፋሺስት መሪዎች ግን (እንደ ዘመነ ካሴ የሚባል ልብ ወለደኛ) ያንን ራዕይ በመጣስ ፤«እኛ የመንታገለው ለሥልጣን ነው» ፤ “መነሻችንም መዳረሻችንም አማራ ሆኖ 4 ኪሎ ለአምሐራ ሰጥተን የተቀረው ኢትዮጵያ ደግሞ ለኢትዮጵያዊያኖቹ እንሰጣለን” ይላል።
ምክንያቱንም ሲሰጥ ጨካኝ ሰው መሆኑን እና ጀግንነቱነም በዕትብት የወረሰው መሆኑን ይገልጻል፡
እንዲህ ሲል፡
«እኔ ሚሊዮን ቢከመርብኝ ዝሆን እና ጨካኝ ነኝ» ፣ «አሽናፊነትን ከእናቴ ማህጸን ነው ያገኘሁት» ፣ «እኔ የነጋሾች የቀዳሾች የነጋሾችና አንጋሾች ዘር ነኝ» (ይህችኛዋ ከወያኔ ዘፋኞ የቀዳት ፋሺስታዊ ስንኝ ነች) ይላል የፋሺስት ባሕሪውን ለአምሐራ ሕልውና ሳይሆን ለሥልጣን እንደሚታገል እና 4 ኪሎም ለራሱ ወስዶ የተቀረቺው ለኢትዮጵያዊያን (ለኛ እና ለእስክንድር ነጋ) በገመድ እየለካ ለማከፋፈል እንደሆነ ፣ ወደ ጫካ ገብቶም ሕዝቡ እንደጠበቀው ሳይሆን ፤ በሥሩ በዙ ሺሕ ታጣቂ ያስከተለ ወደ ድርጀቱ ሥር ያልገቡለት የጎጃም ታጣቂዎችንም እያሳደደ በመግደልና በግድ እንዲቀላቀሉት በማስገደድ የሚያሸብር ተራ ሽፋታ መሆኑን በተግባርና በአነጋገሩ ሲፈጽመው አይተናል።
“የዘር ማጥፋት መከላከል የሆነውን ትልቁ ተልዕኮ እና ራዕይ” እስክንድር ሲነግረን፤ ዘመነ
እና በሥሩ ያሉ አሽከሮቹ ግን «የነጋሽ እና የአንጋሽ ልጆች ስለሆኑ አሽናፊነትን ከእናት ማህጸን ሳይወጡ ሰላገኙት ‘4 ኪሎን ይዘው’ የተቀረቺውን
ቁራሽ መሬት ለኢትዮፒያኒስቶች አንሰጣለን የሚሉን ሕክምና ይሚፈልጉ ቅዠታሞች ናቸው» ።
እስክንድር ያለበት ድርጀትና የከበቡት የታጣቁ ደንቆሮ መሪዎች ብዛት ብዙም የተማሩና የነቁ ታጣቂዎች አለመኖር ምቾት እንዳልሰጠውና ለሱ የሚመጥኑ አለመሆኑን መገምት ይቻላል። ያለው አማራጭ ከውስጥ መከራውን እየተቀበለ፤ እዛው ሆኖ ዓላማው እያዳበረ በዙሪያው ያሉትን ደናቁርት “ችሎ” እያስተማረ ከጊዜ ዕድገት በኋላ እንዲቀበሉት ለማድረግ የወሰደው ጊዜያዊ መጠለያ ይመስለኛል።
መክንያቱም የተከበበውና ያለበት ሁኔታ እጅግ በደነቆሩ ታጣቂዎች ውስጥ ነው
(እስከንደር ማለት ምድረበዳ ውስጥ የበቀለች ቅጠል ማለት ነው)።
እስክንድር በአምሐራ ድረጅት (ብሄሔረተኝነት ከሚያቀነቅን ድርጅት) ውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያዊ ራዕይ
(አጀንዳ) ለማረማድ እና ያንን አገር ለማዳን ይቻላል ሲለን ፤ አይጋጭም
ወይ? የሚሉ ሰዎች አሉ፡ ለምሳሌ በፖለቲካ አበላለት (አተናተኑን) የምወድለት
ድሮ የ Hamer media አዘጋጅ አሁን የ ዘ-Ethiopia መዲያ አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ አምሃ ደገፋ ይህንን ጥያቄ
ደጋግሞ ይጠይቃል። እስክንድር ነጋን በሚመለከት ፈጹም አይጋጭም። ለምን እንደማይጋጭ ምክንያት ላስቀምጥ ።
1ኛ እስክንድር በተለያዩ ወቅቶች በቃለ መጠይቁ ደጋግሞ እንደነገረን በአምሐራ ሕዝብ ላይ የተነጣጠረን ጥቃት ለማስቆም ተጠራርተን ሕዝባችንን ለማዳን እና የአምሐራ ሕልውና ለማስቀጠል እንጂ እንደ ጠባብ ብሔርተኞቹ «የአምሐራ ሪፑብሊክ ለመመስረት የተደራጀን አይደለንም» ሲል ግልጽ ያድረገው ቢሆንም፡
ባለፈው ሰሞን
«አበበ ካሳሁን» የተባሉ ጸሐፊ መከራከሪያየን በጥሩ አገላለጽ እንዲህ አቅርበውታል።
የብሄር አደርጃጀት ሁለት አይነት የራሱ የሆነ አላማ አለው፤
Tribal movements embody two
contrasting dynamics: -
one seeks to oppress others, advancing the
interests of its own group at the expense of outsiders, often by scapegoating
and demonizing others to rally internal support.
In contrast, the other side
consists of those who are targeted—demonized, persecuted, and even killed by
the oppressors—who are left with no choice but to organize and defend
themselves in pursuit of freedom.
አንደኛው ብሄረተኛው መልክ እና አካህይድ፡
የራሱን ብሄር አደራጅቶና ሌሎችን በመወንጀልና የችግሩ ምክንያት
አድርጎ በማቅረብ ህዝቡን አንቀሳቅሶ ስልጣን በመያዝ የራሱን ብሄር የበላይነት ማስጠበቅና
መዝረፍ የሚፈልግ፤ የከሰሰውንም ብሄር ለማጥፋት በግልጽ ጀኖሳይ የሚያካሂድ የፋሽሽት እንቅስቃሴ ነው፤
ይህ አይነት እንቅስቃሴ ከጀርመን ናዚ ጋር የሚወዳደር፤
ልክ ናዚዎች አይሁድ ጠላት ነው፤ የጀርመን ህዝብ የበላይ መሆን አለበት፤
የሌሎችን ቦታ ወስዶ ለራሱ ማድረግ አለበት የሚለው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው፤
በሃገራችንም የትግራይና የኦሮሞ ጠባብ ሄርተኞች ያደረጉት
አማራን ሰይጣን አድርጎ ማቅረብ መክሰስ መግደልና ማረድ፤ ከዛም ስልጣን ይዞ ሃገርንና ህዝብን መዝረፍ ነው፤ ይህ ብሄርተኛ ጸረ
ህዝብና ጸረ ሃገር ስለሆነ፤ ሁልጊዜ መቀጠል የሚችለው በህዝቦችን መካካል ጥላቻን በመፍጥርና ሁሌ እኛና እነሱ በሚል የፖለቲካ አካሄድ
ነው፤
ከነሱ ውጭ የሆነውን ጠላት ብሎ ፈርጆ፤ የራሱን ህዝብ ጠላት
መጣብህ በሚል ማስፈራሪያ ከጎን የሚያሰልፍ ከጥላቻ ውጭ ምንም ነብስ መዝራት የማይችል አደገኛ አካሄድ ነው፤ ህዝብና ሃገር የሚለው ምንም ትርጉም አይሰጠውም፤
ሁለተኞው የብሄር እንቅስቃሴ
ደግሞ
ተገዶ ማለትም በጠባብ ብሄርተኞች ተለይቶና በበሬ ወለደ ዉሸት ተከሶ በጅምላ
የሚገደልውና የሚታረደው ህዝብ የራሱን ስለባ የሆነውን ህዝብ አሰባስቦ ህልውናውን ለማዳን የሚያደርገው ትግል ነው፤
ይህ ብሄር በራሱ አነሳሽነት ብሄራዊ እንቅስቃሴ ጀምሮ
ሌሎችን በመዝረፍ የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስብ ሳይሆን፤ ብሄርተኝነትን ተገዶ እንዲቀበል የተደረገ ነው፤
ይህ ሰለባ የሆነው ብሄር እንደሌሎች ማለት ፋሽሽት ብሄርተኞች
ሌሎችን ጠላት የማድረግ ምንም ፍላጎት የለውም፤ ምክንያቱም አነሳሱም እራሱን ማዳንና ዋናው ጠላቱ ጠባብ ፋሽስት ብሄርተኛ እንቅስቃሴ መሆኑን ሰለሚረዳ ምንም በብሄር ይደራጅ እንጅ ዋናው አለማው በሃገሪቱ የብሄር ፖለቲካን አጥፍቶ ህዝቦች እንደዜጋ በሃገራቸው
ተስማምተውና ተከባብረው ፍትህ ያለበት ስር ሥርአት መመስረት ነው፤
ለዛም ነው የአማራ ብሄራዊ ትግል ከሌሎች ከትግራይና ከኦሮሞ ፋሽስቶች ማለትም አማራን ጠላት ብለው ሃገሪቱን
ከሚዘርፉና አማራን በጅምላ ከሚያርዱ ናዚዎች የተለየ ፍትሃዊ
ትግል ነው የምንለው። ሲሉ ሁለቱ የብሔረተኞቹ ለዩነት አብራርተውታል።
ስለሆነም
የኢትዮጵያዊው እስከንድር ነጋ ቃለ መጠይቅ ለኢትዮጵያ ጠሊታው የአምሐራ ብሔርተኛው ፋሺስት ቡድንን ኩፉኛ ቢያስቆጣውም፤ “ኢትዮጵያኒስቱ”
ቡድን ለወያኔ እና ለሻዕቢያ እንሰዋለን ለሚለው ማፈሪያው «አቅል ጥበት እና ሆድ ቁርጠት» መሆኑን ይቀጥላል።
መልካም ሳምንት
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

No comments:
Post a Comment