ክፍል 3
ሕዝባችን ለጠላቶቹ
ሸብረክ ብሎ እንዲገዛና ገዢዎቹን ማስወገድ ያልቻለበት ምክንያቱ ምንድነው?
መልስ
ለዶ/ር ዮናስ ብሩ፡
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay
9/6/25
ባለፈው ክፍል 2 እንዲህ በሚል ነበር ያቆምነው፡ «የወስጥ ተዋናዮቹ ማዕከላዊ የቅስቀሳ መርሆዎቻቸው ዒላማ ኢትዮጵያ ስትሆን ፤ ‘የነፍጠኛ፤የጡት ቆራጭ አገር፤ ኋላ ቀር አገር፤የመቶ አመት አገር’ በማለት ኢትዮጵያን ‘በማዋረድ፣በማንኳሰስ’ የማናጋቱ ሂደት “ስሎው ፕሮሰሱ” (በዝግታ) እንዲከናወን እየተደረገ ነው:: የብከላው ቅጥ ማጣት “በፖለቲካው እንቅስቃሴ ያሉት መሪዎችና መሁራን “አጥቂም ተጠቂም” አብረው ባንድ መድረክ ቁጭ ብለው ምንም እዳልተፈጸመ ሲተሻሹ ይታያሉ።....።.... በሚል ነበር ያቆምነው።
ወደ ክፍል3 እናምራ፤-
ሃገር በማናጋት ሕዝቡ በገዢዎቹ እንዳይነሳ የወያኔ ትግሬው እና ኦነጋዊው የአብይ አሕመድ የኦሮሞ አገዛዝ በሕዝቡ ላይ የዘረጉት የሕሊና ብከላ በክፍል 1 እና በክፍል 2 ከተጠቀሱት ውሰጥ ሌሎች ያልተጠቀሱ ሕዝብን የማደንዘዙ ብካል እንመልከት።
ዶ/ር
ዮናስ ብሩ ሕዝቡ 60 አመት ሲረገጥ ለምን ተመቻቸቶ ተገዢ ሆኖ ጥቃቱን ለመቃወም ፍላጎት አላሳየም ሲል እራሱን በተጠያቂነት ሳያቀርብ ፤
ያቀረበው መልስ፤ ወቀሳና አቃቂር ከመሰረታዊ ምክንያት ያልፈተሸ እንደሆነ በክፍል 1 እና 2 በሕዝቡ ላይ የተሰሩ የሕሊና ብከላዎች ገልጫለሁ።
ሕዝቡ እንዳይነሳባቸው ካጠመዱት ወጥመድ ውስጥ “የባሕል-ብከላ” ቀዳሚው ነው። የጠቀሰናቸው የግበርሰዶም መሰፋፋት፤ በውጭ ሃገር “የበጎ አድራጎት” (NGO) ድርጅቶችና ቀጥረኞቻቸው ብዛት ያላቸው ደላሎችንና ደፋሪዎችን ገንዘብ በመስጠት ኢትዮጰያ ውስጥ የተጫወቱት ብከላ እንደነበር ተመልክተናል።
በተሰቃየንበት የ27
አመት በትግሬዎች መንግሥት ውስጥም ፤
የሴት ፖሊሶች ፡
ለምሳሌ “እቴነሽ ወልደሩፋኤል” የተባለች በአማራ አብዮት ማነሳሳት በሚጠረጠሩ እስረኞች ፊት “ሙታንታዋን በማውለቅ” ዕራቁትዋን በመውጣት “ብልትዋን እያሸች” እስረኛውን በማጓጓት የተወለዱበት አካባቢና ዘራቸውን እየሰደበች ስትገርፋቸው የነበረች የትግራይ ወያኔ ሴት ፖሊስ ምርማሪት የገረፈቻቸው እስረኞች አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ለሕዝብ ይፋ ከተደርጉ ቪዲዮዎች ውስጥ በአዲስ
አበባ አምሐራ እስረኖች ላይ የተነገረ ታሪክ ታስታውሱ ይሆናል።
በማሕብረሰቡን ሞራል በመግደሉ ርቀት ብቻ ሳይገታ ደምብና ሥርዓት ለማስከበር የተሰማሩት መርማሪ ፖሊሶች ጭምር የባሕልና የሞራል ዝቅጠት እንደበከላቸው ያሳያል።
ይህ ነውር እስረኞች ላይ ሲፈጸም በወቀቱ አድራጊ ፈጣሪ የነበሩት የወቅቱ ባለሥልጣናት እንደ እነ አባይ-ጸሐየ፤
አዲሱ-ለገሰ በግብረሰዶማዊያን ፖሊሶች የተደፈሩ እስረኞች እንደነበሩ ሲደርሱበት ወደ ታሳሪዎቹ ድረስ በመሄድ የተደፈሩ እስረኞች ምስጢር እንዳያወጡ ካወጡ ግን ሕልውናቸው እንደሚያከትም ያስፈራርዋቸው እንደነበር የእስረኞቹ የቃለ መጠይቅ ምስክርነት አድምጠናል። ይህ ሁሉ የሚያሳየን ድረጊቱን የፈጸሙት ፖሊሶች ሕዝብ ፊት ከመቅጣት ይልቅ ተበዳዮቹን ማስፈራራት የመረጡበት ምክንያት ፤
ሕብረተሰቡ በሥርዓቱ ላይ እንዳይነሳና የተቃዋሚው አፍላ ጉልበት ለማኮላሸት የሥነ ልቦና ሥብራት እንዲደርስበት የተደረገ ነው። የውስጥና የውጭ ቅኝ ገዢዎች ይህንን ሕሊናን የመግደል ሥልት ይጠቀማሉ። ስለዚህ እንዲህ ያለ ሕዝብ ሕሊናው ስለሚቃወስ ገዢዎቹን መቃወም ከቶ አይቻለውም።--
ሌላኛው
ስልቶቻቸውን ደግሞ እንመልከት።
ሕዝቡ አንድ እንዳይሆን የማናጋቱን ሂደት ለማከናወን “በሕግ የተፈቀደ” የጥላቻ ቅስቀሳ አለ።
የማናጋቱን ሂደት ለማከናወን “በሕግ የተፈቀደ” የጥላቻ ቅስቀሳቸው በክርስትያን ማሕበረሰብ፤ በአማርኛ
ቋንቋና ሕብረተሰብ ላይ የጥላቻ ዘመቻ አንዲጻፍ፤ አንዲነገር፤ በየበዓላት ቀን ምልከቶቻቸውና ማተባቸው እንዲነጠቁና እንዲበጥሱ ፤ በመንግሥት ሥምሪት ተደርጎ በየ አደባባዩ ፖሊሶችን በማስቆም ደርጊቱን እንዲፈጽሙ በሕግ ተፈቅዷል።
ዛሬ የመንግሥት ፖሊሶች ቀሳውስትን እያስቆሙ በጥፊ ሲያጮሉ ፤
ያነገቡት መንፈሳዊ መጽሐፍት እየነጠቁ መሬት ላይ ሲጥሉና ሲቀዳድዱ ነውር አይሰማቸውም።
በዚህ ሳይገደቡ፤ መሪዎች በይፋ በቴሌቪዥን፤ በራዲዮ፤ በጋዜጦች የጥላቻ ንግግር በመናገር ሕብረተሰቡን ማዋረድና ማሸማቀቅ ሕጋዊ እንዲሆን አድርገዋል።
መለስ ዜናዊ ፤ ስብሓት ነጋ፤ አብይ አሕመድ ፤ ሺመልስ አብዲሳ ወዘተ……ወዘተ… የመሳሰሉት በይፋ አገሪቱን እና የኢትዮጵያ ታሪክ ፤
ሰንደቃላማና አምሐራን በመዝለፍ እነሆ ከትግሬዎች መንግሥት ጀምሮ እስከ አብይ ኦሮሙማ መንግሥት የዘለቀ የሚታወቁበት የፖለቲካ ማስታወቂያቸው “ጥላቻ” ሆኖ ዘልቋል።
እነሱን እየተከተሉ፤ የሃይማኖት፤የጎሳ መሪዎች ነን የሚሉ እንደ አሸን በመፍላት፤ አገሪቱን እንደ ባዕድ አገር ቆጥረው፤ አንደ ባዕድ ዜጋ እራሳቸውን ቆጥረው “ኢትዮጵያ አገራችን አይደለችም” እያሉ ያልወረወሩት ነውረኛ ቃላት የለም።የሳይኾሎጂካል ሳብቨርዢኑ ዘመቻ አገሪቱ ላይ በግልጽ እየተካሄደ ነው ማለት ነው።
አጥቂዎቹ- በጥናት የሚሰሩት የሃገሪቱ ጠንካራ ተቋማት፤ የሕዝቡ አብሮነት፤የተረጋጋ ማሕበረሰብ እንዳይኖር ፤ ፈሪሃ እግዚአብሔር ቦታ አንዳይኖረው ፤ የወያኔ መሪዎች በሕዝቡ ሃይማኖት ፤ በፈጣሪ እየተሳለቁ በፓርላማ መድረካቸው ላይ በአምላክ ላይ ሲስቁ/ሲያፌዙ/ አድምጠናል።
አንድ በወያኔ ፓርላማ ውስጥ የነበሩ ብቸኛ ተቃዋሚ (አቶ ግርማ ሰይፉ) “አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ” ብለው ንግግራቸው ሲደመድሙ “አባ ዱላ ገመዳ” የተባለው “የፓርላማው አፈ ጉባኤ” ላንቃው እስኪሰነጠቅ የሳቀበትን እና የወያኔ ፓርላማ አባሎችም እሱን በመከተል አዳራሹ ሳቅ በሳቅ አንዴት እንዳስተጋቡት በቴሌቪዥናቸው የተላለፈውን የውስጥ ገመናቸውን ያሳዩንን አስታውሱ።
ሆን ተብሎ የአገሪቱን ሃይማኖቶች ማዋረድ የሕዝቡን አምላክ እና በሃይማኖት አስተማሪዎቹ ላይ እያፌዙ የሕዝቡን “ኤቲክስ/ግብረገብነት” አንዲሰበር በማድረግ ማሕበረሰቡ ወደ አረመኔነት ከተለወጠ “ግድያ ፤ ስርቆት ፤ ውሸት፤ይሉኝታ፤ክሕደት” እንዲሰፍን ሆን ብለው ያቀዱት የማናጋቱ ሴራ ነው።
ምክንያቱም ሃይማኖት የማያከብር እና ታሪኩን የማያከብር ሕብረተሰብ አረመኔ ከሆነ ለሃገር ነጻነት ለማስጠበቅ ከውጭ ወራሪዎች
ጋር ታግለው ሃገር ያቆዩን አርበኞችና መሪዎች ሃውልታችው እንዲፈርስ ማድረግ ፤ “ሰው በቁመናው ወደ ገደል መወርወር፤ ሰው ገድሎ ቆዳውን መግፈፍ፤ባደባባይ ዘቅዝቆ መስቀል፤ ነብሰ ጡር እናት አጋድመው የጸነሰቺውን ሕፃን ከማሕጸንዋ በቢላዋ ቀድዶ በማስወጣት እናትየዋን ገድለው በሞትቺው እናት አፍ ላይ ማጉረስ” ፤ የመሳሰሉትን አረመኔያዊ ባሕሪዎች እንዲታዩ ተደርጓል።
በ1991 አካባቢ ኦነግና ወያነ አንድ በነበሩበት እቅት በበደኖ እና ሒርና (ሐረር) አሁንም በወለጋ በአብይ አሕመድ ዘመን በአማራው ሕብረተሰብ ላይ የጎሳ ተኮር ጅመላ እስራት እና ግድያ (ጀነሳይዳል) እያየን ያለነው የአረመኔነት ባሕሪ “የዲስታብላያዘሺኑ” የማናጋቱ ሂደት ዋናው አካል መሆኑ ነው።
ለዚህ ነው “የሕዝብ ተጠሪዎች” ነን እያሉ “የአምላክ ስም” በጠራ የፓርላማ ተቃዋሚ አባል ላይ የወያኔ ፓርላማ አባሎች እና አፈጉባኤው “ሲሳለቁ ያየነው” ፓርላማው በአረመኔዎች የሞላ ሰለሆነ ነው።
የተረጋጋ ሃይማኖትና የቆየ ማሕረሰበን አኑሮ ያቆየ ባሕል” እንዳይቀጥል፤ ሴራው በዚህ እና በመሳሰሉት ዘዴዎች በማከናወን ሕብረተሰቡ ፈጣሪው እንዲንቅ እና “ዲሲፕሊን” ወይንም ግብረገብ አንዲጎድለው በማድረግ፡ “ክሕደት እና ግድያ” የመሳሰሉ ሕብረተሰቡ በነውርነት ሲመለከታቸው የነበሩትን “ነውሮች” አንደ “ነውር” አንዳያያቸው አድርጓል ማለት ነው።
ለዚህ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቶቸዋ በአደንዛዥ ዕጽ ተበክለው ዘራፊና ቀማኛ ሆነው ማሕበረሰቡን ሲያዉኩ፤ የመንግሥት ሠራተኞችና ደላሎች “በካት ትሮት ሜንታሊቲ” (ይሉኝታ በሌለው) ዘረፋ/”ኰራፕሽን/ ተዘፍቀዋል። “አንተ የኔ ጎሳ ቋንቋ ተናጋሪ ስላልሆንክ ከክልሌ ውጣ” እየተባለ፤ አገሪቱ በማናጋት ሂደት ውስጥ “እየተናጠች” የምናያት ምክንያት በሕዘቡ ሕሊና ውሰጥ የተሰራ የባሕል ወረራው ውጤት ነው። ሰለሆነም ሕሊናው የተቃወሰና የተሰለበ ማሕበረሰብ በሽተኛ ነውና አምአገነን ሥርዓትን የመቃወም አቅም አይኖሮውም።
ሰለሆነም ነው “የፖለቲካ፤ የሚዲያ፤ የሃይማኖት፤የጎሳ ወዘተ..ወዘተ….ተቋማት “ያገሪቱን ግንዶች” በመገዝገዙ፤በማናጋቱ ተዕይንት /ውስጥ እራሳችውም እጃቸውን በማስገባት በጥቃቱ ዘመቻ እየተመሩ ወደ አስፈሪው ሂደት እየወሰዱን የምናያቸው።
የሃይማኖት ተዋናዮችን ስትመለከቱ የተዘረጉላቸው የ“ideological
subversion” ሴራ እየተመሩ ፤ ከምዕራቡ
ዓለም ደግሞ በጴንጤ፤ ከዓረቦች በአላህ ስም በዋሃቢም ስም ፤ ከምዕራቡ ዓለም ደግሞ በጴንጤ፤
በአይሁድነት ወዘተ….. እየተጠመደ በማያውቀው መርዝ እየተመረዘ “በማናጋቱ ሂደት ተጭኖ” መዳረሻው እንደማያውቅ
ጎርፍ ሲጓዝ እያየነው ነው።
አይሁዶች ነን እንጂ ኢትየጵያዊያን አይደለንም በማለት ኢትየጵያዊነታቸው፤ አፍሪካዊነታቸው እንዲክዱ ተደርጐ፤ አይሁዶች ነን እያሉ የገዛ አጋራቸውንና ጥቁሩን ዓለም አውግዘው ህጻናትና የተዳከሙ የ90 አመት እናቶችና አረጋዊያን በወሳንሳ (በቃሬዛ) እየተሸከሙ ወደ አይሁዶቹ አገር ወደ እስራል በሕገ ወጥ ሴራ ተላልፈው እዛም የዘር መድለዎ እየደረሰባቸው ሲሆን ፤ የተቀሩት ወጣቶች ደግሞ ከፍልስጥኤም ጋር በመዋጋት ጦርነት ወዳጅ የሆነው የጠ/ሚ ነተኛሁ የጥማት ማርኪያ በመሆን የጥይት ማብረጃ እየሆኑ በዙ ወጣቶች በሚያሳዝን መልኩ በጦርነት እሳት እንዲማገዱ እየተደረጉ ነው።
የቀለም መድልዎ እየደረሰባቸውም ቢሆን አዲስ ባርነትን ተቀብለው ጦርነት ወደ ማያባራበት የአይሁዶች ሀገር” እራሰቸውን በማዘጋጀት “አይሁድነትን” ተቀብለዋል።
በዚህ ሳያባራ በርካታ እህቶች እና ወንድሞች በዓረብ አገር በወያኔና በአብይ ዘመን አስፈጻሚነት ወደ ግርደና ግማሹም እየታፈኑ ተገድደው በምድረበዳማው የዓረቦች ምድር ወደ ፍየል እና ግመል ጥበቃ ባርነት እየተላኩ ለመግለጽ በሚያዳግት ግፍ እየተገደሉ እና እየተረገጡ ይገኛሉ። ሊረሳ የማይገባው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ወንድም ሴትም “የሃይማኖትና የባሕል ለውጥ በማድረግ” ተጠቂዎች ሆነዋል።
የሞሳዶች፤ የሲአይኤ እና የዓረቦች ሴራ “የሳብቨርዥን/የጥቃት ደረጃ” ስትመለከቱ “ከውጭ” እነዚህ ተዋናዮች “ከውስጥ” ወያኔዎችና የአብይ ኦሮሙማ ሥርዓት በጋራ ሆነው በመተባባር የሕብረተሰቡን እና የተረጋጋውን ማሕበረሰብ “በማናጋቱ ሂደት” የሰነዘሩብንን ጥቃቶች ስትመለከቱ የጥቃቱና የማናጋቱ ከባድነት በግልጽ የታያቹሃል።
አክራሪ እስላሞቹም ቢሆን ካሁን በፊት ያላየነው በክርስትያኑ ማሕበረሰብ ላይ፤ በቤተክርስትያን፤ አለፍ ብሎም በመስጊዶች ላይ ቃጠሎ፤ እና ግድያዎች ተበራክተው ይታያሉ። አለባበሳቸው ቋንቋቸው፤ስማቸው ፤
ጺማቸው ኢትዮጵያዊ ሳይሆን “ዓረባዊ” ወይንም “ፓኪስታናዊ” አስመስሏቸዋል። አንዳንዶቹ በዲሞክራሲ ጥያቄ እየተነሱ “አገራቸውን” በሁለተኛ ደረጃ በማስቀመጥ “ሃይማኖታቸው እስላም አገራቸው እና መሪያቸው አላህ” በማለት ኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤታቸው እንጂ ደም እና አጥንታቸው አንዳልሆነች በመስበክ፤ እራሳቸውን “የሃይማኖት ብሔረተኞች” አድርገው በማሰለፍ “ከጎሳ ብሔረተኞች” ጋር ፍጥጫ ገብተው አገሪቱን በማናጋት ሂደት ላይ ይገኛሉ።social code of behavior ተለውጧል።
ሚዲያዎቹም ስንመለከት መንገዳቸው የጠፋባቸው የተቃዋሚዎቹ ቀኝ እጅ በመሆን በእውርነት እየተጓዙ፤ እራሳቸውን በጤነኛ ተቃዋሚነት ሽፋን ገብተው የደበቁ ተገንጣዮች እና የመሳሰሉ ጸረ ኢትዮጵያ ሃይላት በብዕራቸው እና በየዌብሳይታቸው እየቀባቡ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ሚዲያዎቹ የሕዝቡን ሕሊና በማጠብ በጥቃቱ ዘመቻ እጃቸውን አስገብተዋል።
ይግረማችሁ ብለውም ኢትዮጵያዊያን ነን የሚሉን ጋዜጠኞቻችንና ፖለቲከኞች “የኢሳያስ ሰብአዊነትና ዲሞክራሲነት” ለሕዝባችን ለመሸጥ በፕሮፓጋንዳ ገበያ በማሻሻጥ ስራ ላይ ተጠምደው፤ የዲስታብላይዘሺኑ ዘመቻ /በማናጋቱ ዘመቻ ተዋናዮች በመሆን የራሳቸውን
መጥረቢያ ይዘው በግዝገዛው ስራ ላይ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው።
የፖለቲካ ድርጅቶችም ወያኔ እና የውጭ አገር ተዋናዮች በሚሰጧቸው የዲሞክራሲ ጨዋታ ገብተው እራሳቸውን በማስገመት 34 አመት የረባ ስራ ሳይሰሩ የታሰሩትንም ሳያስፈቱ ፤ ሓኪሞች አድማ ሲመቱ ተቃውሚና ሕዝብ ድጋፍ ሰላላገኙ ድንገት ብቅ ያለው የሃኪሞች ተቃውሞው ከሸፈ። አብይ አሕመድ የልብ ልብ ተሰምቶት እነሆ የማናጋቱ ሂደት እየቀጠለበት እሱም በሐኪሞች ላይ እያሾፈባቸው ይገኛል።
ውድ ዶ/ር ዮናስ በሩ ሆይ!
ይህ ሁሉ ስንመለከት ምሁሩም ማይሙም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የየራሳቸውን መጥረብያ በመያዝ አገሪቱን በመገዝገዝ በቆረጣ ሂደት ላይ ናቸው። ስለዚህም የማናጋቱ ሂደት እየተጠናቀቀ ሲሄድ ሕዝቡ ገዢዎቹን ይረሳል። ሕዝቡ እነሆ ለባርነትና ለግፍ ትከሻው አለጥልጦ አመቻችቶላቸው አጎንብሶ በጸጥታ እየቀጠለ ነው። ተከሻው ለገዢዎቹ ምቹነት ምን ያህል ርቀት ተጉዞ በየትኛው ደረጃ እንዳለ ለመደምደሚያ በክፍል 4 ሰሞኑን ለማሳረግ እመለሳለሁ።

No comments:
Post a Comment