ክፍል 5
ሕዝባችን ለጠላቶቹ ሸብረክ ብሎ እንዲገዛና ገዢዎቹን
ማስወገድ ያልቻለበት ምክንያቱ ምንድነው?
መልስ ለዶ/ር ዮናስ ብሩ፡
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
9/15/25
የግብረሰዶም አስተባባሪዎች በኢትዮጵያ ⚠️! ከአርቲስት እስከ ባለስልጣን የተዘረጋው የተደራጀ መስመር | በድብቅ እየተንቀሳቀሱ ነው!
https://youtu.be/JDMD1pX6SJg?si=sDGEUa2t_rDsvlL6
ቀውስ/Crisis
Crisis /ቀውስ/ ሲከሰት ስርዓተ አልባነት ይከሰታል።
ለምሳሌ ሁሉም የየክልሉ ጎሰኛ ሓላፊ፤ ፖሊስ፤ የሕግ ዘርፎች ሁሉ፤ የየራሳቸው ስልጣን በመያዝ ማእከላዊው የፌደራሉ መንግሥት ተብየው
ከቁጥጥርና ግንኙነት ውጭ ስለሆኑ ተበደልኩ ብሎ አንድ ዜጋ ወይንም ማሕበረሰብ/ ቡድን/ድርጅት ወዘተ…ወደ ፌደራል መንግስት አቤት
ሲል፤ የፌደራሉ መንግስቱ የማናጋቱ “ፐሮጀክት” (ዕቅድ) ዋናው ቀያሽ
በመሆኑ ለተበዳዮቹ የሚሰጣቸው መልስ «”የክልሉን ሥልጣን መጋፋት ስለማንችል እንደፈረደብህ እዛው “ተጋፈጥ”» ይሉታል። ለዚህም ነው “በሺዎቹ የሚቆጠሩ የአማራ
ሕብረተሰብ ገበሬዎች፤ ሽማግሌዎች፤ ሕፃናት እና እናቶች ከጉራ ፈርዳ፤ ከጋምቤላ ከኦሮሞ ክልሎች እየተጨፈጨፉ፤ ንብረታቸው እየተነጠቁ
እንዲባረሩ ተደርጐ “የጎሳ ጽዳት” /ኤትኒክ ክሊንሲክ” ሲፈጸምባቸው እያየን ያለነው።
አቤት ወደ እሚሉበት የመንግሥት ሠንሰለታዊ ተዋረድ የለም።
ይህ ክራይሲስ (ቀውስ) ቀደም ብየ እንዳልኩት “አስቸኳይ እርማት ካልተደረገለት” ፤ በሌላው ወገን ያለው ተጠቂው ክፍል ትዕግስቱ
እያለቀ በሄደ ቁጥር “የመልስ- ምት” ለማጥቃት ሲገደድ፤ ሩዋንዳ ያየነውን አስከፊ የእርስ በርስ የመተላለቅ ግጭት (ጦርነት) ሊነሳ
ይችላል (የተበደሉት ወገኖች ወደ ጠላታቸው ክማነጣጠርም አልፈው ሀገራዊ “ፓን
ኢትዮጵያኒዝምን” (አትዮጵያዊነትን) አጀንዳን በማጣጣል (በማራከስ) ወደ ነገዳቸው በማተኮር “ጎሰኞች” በመሆን አሁን በፋኖ ድረጅቶች
እና ደጋፊዎቻቸው እንደምናየው “ከክልላዊነት ከዚያም ወደ አውራጃዊነት፤ ጎጥ እና ወንዛወንዝ-ወረዳ ያገር ልጅነት፤ አለፍ ብሎም
ዘመዳዊና ቤተሰባዊ ሐረግነት “በመቀናጀት” ወደ ታች ወርደው እርስ
በርስ ሲካሰሱና ሊዘላለፉ አለፍ ብሎም ሊገዳደሉ ወደ እሚችሉበት ደረጃ ይደርሳሉ (ይህ ክስተት በወያነ እና በፋኖ ታጣቂዎች ውስጥ
እያየን ነው)።
ለዚህም የቀውስ ደረጃ እንዲከሰት የወያኔ መሪዎች እና በወያኔ እና በኦሮሙማ ሥር ተጠልለው የመገንጠል
ዓላማ ለማካሄድ ያደፈጡ የተገንጣይ አባሎች አማካይነት ቀውሱ እንዲከሰት በመግፋት ላይ ናቸው።ይህ /ፕሮቨኬሽን/ ትንኰሳ/ አስቀድመው
ላቀዱት አገርን የማፍረስና የመገንጠል ዓላማ እውን እንዲሆን የግድ ሕብረተሱቡን ማስቆጣት/ መተንኮስ/ ሕብረተሰቡን “ግራ ማጋባትና መበከል” አለባቸውና ያ እያደረጉት ነው።
እዚህ ላይ በዚህ የቀውስ ደራጃ የምንታዘበው “ግራ መጋባት”
የሚለው መሠረታዊ የቀውሱ ማዕከላዊ ወለል መርሳት የለብንም። ማሕበረሰቡ ግራ ሲጋባ፤ፍትሕ ሲያጣ ‘የቀውሱ ደረጃ ፤ግራ በተጋባበት
ሂደት “ቁጣው” በቂም በቀል ወደ መልሶ ማጥቃት አድጎ ሕዝቡ ይተላለቃል። ከውጭ አገር ጠላቶች የታቀደው “የብላ ተበላላው” አገርን እንዴት ማፍረስ
እንደሚቻል ያቀዱትን ግብ በውስጥ ተዋናዮች በኩል ተከናውኗል
ማለት ነው። የህም እየታየ ነው።
(4ኛው) ኖርማላይዘሽን (እርጋታ የሌለው እርጋታ- A calm
without a calm) በኢትዮጵያ
ይህ በማናጋት ሂደት ያለፈው “እርጋታ የሌለው እርጋታ” በተጠቀሱት የዲስታብላይዘሽኑ ሦስቱ የጽንስ ደረጃዎች አልፎ የተወለደ ‘የምጨረሻው ልጅ’ (last born child)
ነው። ኢትዮጵያና ኤርትራን ስትመለከቱ በዚህ ደራጃ ውስጥ ይገኛሉ። እርስ በርስ ተላለቆ “አገር ተበታትኖ
፤ እህት ፤ እናት ወንድም ዘመድ
አዝማድና ጋብቻ ተለያይቶ ፡ የመጨረሻው የአገሪቱ
ግብዓተ መሬት የሚከናውንበት ደረጃ ነው ማለት ነው። የኤርትራ ሕዝብ በኖርመላይዘሽን ሂደት እየተራመደ (ማለትም በነፃነት ስም/
በማረጋጋት ስም) የራሳቸውና የኛን ኑሮ በማያባራ በምስቅልቅል ጦርነትና ቀውስ ውስጥ አስገብቶ ፤ ሕይወቱ ተናግቶ የተረጋጋ የሚመስል በቀውስ ውስጥ እየተናጠ “አበባ ይዘው ሆ!
ሆ!” ሲሉ የነበሩ ዜጎቿ
ወደ ሲኦል አቅንተው “እራሳቸው እና ቤተሰቦቻቸው” በማይወጡት አረንቋ ውስጥ አስገብተው በጨረሻም
ለሲናይ በደዊን ዘላን ዓረቦች መጫወቻ ሆነዋል።ኢትዮጵያም በዚህ ሂደት ላይ በ3ኛው እና በ4ኛውም ደረጃ “እርጋታ በሌለው
እርጋታ «A calm
without a calm»” ውስጥ በ “pendulum” ተቀምጣ በዥዋዥዌ ሂደት ላይ ትገኛለች።
አሁን የምናየው ዜጎች ከሚኖሩባቸው መንደሮች እየተባረሩ በባይተዋርነትና ድንጋጤ ውስጥ የሚገኙት ማሕበረሰቦች የዚህ ደራጃ ሂደት ውጤት እያለፉ ስለሆነ ነው።ወያኔና ሻዕቢያ ሲገቡ ደርግ አስወግደን “ሰላም” ለሕዝባችን
አጎናጸፍን ብለው “በኖርማላይዘሽን”
በማረጋጋት ስም ዕርጋታ የሌለው እርጋታ A calm without a calm ፈጠሩ።
ስለሆነም ከዓረቦችና፤ ከፋሺስት ጣሊያን ጀምሮ እስከ ምዕራባውያን የቅኝ አገዛዝ ዕቅዳቸው የተበተቡልንን የማናጋትና ኢትዮጵያን ማፍረስ ወይንም በባሕላቸው በቁጥጥራቸው ስር የማድረጉን ዕቅድ ተሳክቶላቸው ይኼው ሕብረተሰቡ ባህሉ፤ ሃይማኖቱ፤ ቋንቋው፤ አለባበሱና ባሕሪው፤ አነጋገሩ ተለውጧል። በሚያሳዝን መልኩ አንዳንድ የፋኖ ድርጅቶችና ደጋፊዎቻቸው “ኢትዮጰያዊነት/ፓን-ኢትዮጵያኒዝም” የሚለው መሰረታዊ ሃገራዊ መርህ በማሳነስና በመዝለፍ በተጠቀሱት የማናጋት ዕርከኖች ውስጥ ተሳታፊ ሆነው “የጎሳ አከራሪ የናሺናሊዝም ፖለቲካ” ተከታይ በመሆን “አንዱን “እስኩዋድ” አንዱን አንደኛውም ምንትስ ነው ምናምን ነው እያሉ እየተቧደኑና እየተዘላለፉ ዋናውን ጠላታቸው በመርሳት «የተያዘው ትግል ቀልድ አይደለም የያዝነው ትግል ሰውን ማገትና ንብረትን ማቃጠል ነው ትግላችን” የሚል መሪ የሚመራው “ጠመንጃ የታጠቀ የወረበላነት ባሕሪ በ Mob Violent” ፕሮጀክት የሚንቀሳቀስ ቡድን ስትመለከቱ፤ እነዚህ ታጣቂዎች የመታጠቂያቸው አላማ ስተው በዲስታብላይዘሺኑ የብከላው ጨዋታ ገብተው ሲተራመሱ ይገኛሉ።
በስሜት ውስጥ እየዋኙ ያሉት የማሕበረ ድረገጽ ተሳታፊ ደጋፊዎቻቸውም ይህንን ስትጠቁማቸው ፤ በዕውር ድምብር ስሜት ስለሚገፉ አይቀበሉትም፤ ካለመቀበል አልፈው ይሰድቡሃል፤ ይዝትቡሃል)። ስለዚህ የፖለቲካ ድርጀቶችና ታጣቂዎች በረዢሙ የተጠመደላቸው “የሳቨርዥን ወጥመድ” ስለተጠመዱ የ35 አምቱ ገዢው መንግሥት ለመጣል የተሳናቸው ምክንያት በክፍል ፤ በክፍል አስቀምጨ በጠቀሱኩዋቸው ወጥመዶች በመተብተቡ ምክንያት ነው።
ባጨሩ ተቃዋሚው
ገዢውን ሥርዓት መጣል ሳይችል ቀርቶ «እርጋታ የሌለው እርጋታ (ኖርማላይዘሺን/ A calm
without a calm" ) ውስጥ «ዞምቢ» ሆኖ እየተንቀዋለለ የአዲሱ ዓለም ዕቅድ ተሳታፊ እና ተጎጂ (Participant
and victim) ሆንዋል።
በመጨረሻም
ለማጠቃለል የዘረዘርኩዋቸው አራቱ የግዝገዛ ደረጃዎች
ማለትም
(1ኛ) ዲሞራላይዘሽን (ሕሊናን ማዳከም/የሞራል ዝቅጠት)
(2ኛው) Destabilization (ማናጋት)
(3ኛው) ቀውስ/ Crisis
(4ኛው) የአዲሱ ዓለም ዕቅድ ኖርማላይዘሽን/ A calm without a calm" (እርጋታ የሌለው እርጋታ)
የሚባሉ ሃገርን የማዛባት ደረጃዎች ለሳያችሁ የሞከርኩት ይህ በዓይነቱ ለየት ያለ ትምህርታዊ ትዝብት ከአገራችን ጋር በማዛመድ ያደረግኩት ማገጣጠም፤ የሳይኮሎጂካል
ሳብቨርሲቭ (አገራዊውን አስተሳሰብ በባዕድ አስተሳሰብ መተካት) የሕሊና ጥቃቱ ያለ ጠመንጃ በተጠቀሱት ዘዴዎች አማካይነት እንዴት
እንደተከናወነ እና ሕዝቡ ገዢዎቹን የመቃወም አቅሙ ለምን እንደተዳከመ ለማሳየት የታዘብኩትን
ለማስጨበጥ ያቀረብኩላችሁ ትንታኔ በግዝገዛው
ሂደት የሁላችንን ሚና ምን ይመስል እንደነበረና አገሪቱ እየተፈታተናት ያለው ከባድ ፈተና ለማየት እንደረዳችሁ ተስፋ አለኝ።
ስለተከታተላችሁኝ አመሰግናለሁ፤
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay

No comments:
Post a Comment