Friday, September 12, 2025

ክፍል 4 ሕዝባችን ለጠላቶቹ ሸብረክ ብሎ እንዲገዛና ገዢዎቹን ማስወገድ ያልቻለበት ምክንያቱ ምንድነው? መልስ ለዶ/ር ዮናስ ብሩ፡ ጌታቸው ረዳ ክፍል 4 9/12/25

 

ክፍል 4

ሕዝባችን ለጠላቶቹ ሸብረክ ብሎ እንዲገዛና ገዢዎቹን

ማስወገድ ያልቻለበት ምክንያቱ ምንድነው?

መልስ ለዶ/ር ዮናስ ብሩ

ጌታቸው ረዳ

ክፍል 4

9/12/25

 

ሃይማኖትና ፖለቲካ በመኖሪያ ቤት ግንባታዎች (Subversion in real estate) ሚና ሁለት ነገሮችን እንመልከት፤

 

1ኛ- የእስላሚክ መንደር

 

2ኛ-የኦሮሞዎች መንደር

 

የሚሉ ጉዳዮች እንመልከት።

  የእስላሚክ መንደር

በሃገራችን በዚህ 34 አመት ውስጥ ሃይማኖታዊ ወይም ፖለቲካዊ ቡድኖች "በሪል እስቴት ውስጥ የሚጫወቱት ሚና  " የተለያዩ ቅርጾችን ሲጫወቱ ታዝቤአለሁ። በመሬት እና  በቤት ግንባታ (ኮንደሚኒየም) ዕደላ አጠቃቀም ግልጽ ሕገ-ወጥ መድልዎ በማድረግ ባለሃብቶችም ሆኑ  እራሱ መንግሥት በማን አለኝነት ሥልጣኑን በመጠቀም  ለፖለቲካና ሃይማኖታዊ ፍጆታ ለማዋል የታቀዱ ስውር እርምጃዎችን ሲፈጽሙ አይተናቸዋል።

ኢትዮጰያ ውስጥ እየተደረገ ያለው የመሬት እና  የቤት ግንባታ (ኮንደሚኒየም) አጠቃቀም ዜጎች እኩል ከማገልገል ይልቅ በነገድና በሃይማኖት እንዲሸነሸኑ ወይም እንዲሸጡ ማድረግ በዓለም አቀፍ የዜጎች መብት ደምብ የሚጥስ የአንድ ሀገር ሕዝብ አንድነትን የማፈራረስ ድርጊት ሰልሆነ ለኪራይና ለግዥ  የሚቀርቡ  ግንባታዎች፣ በሌሎች አገሮች በፖለቲካ በእምነት እና በነገድ ተንተርሶ የሚሰጥ ዕደላና ሽያጭ ጥንቃቄ ይደረጋል።

በሀገራችን ግን ለኪራይና ለግዥ  የሚቀርቡ ግንባታዎች ፖለቲካዊ ሃይማኖታዊና ነገድ ተኮር አገልግሎት ተንተርሰው ሰሊሚፈጸሙ በመካከላቸው የተከሰቱ የቅራኔ መስተጋብሮች ወደ ውስብስብ ውጥረት እያመሩ ይገኛሉ።

“የእስላሚክ መንደር” የሚል ስያኔ ተሰጥቶት እየተላለፍ ያለው የንግድ ማስታወቅያ መልዕክት እንመልከት።

ይህ የንግድ ማስታወቂያ የተላለፈው ዋና መሰረቱ ካሊፎርኒያ አሜሪካ የሆነ ለትርፋማ ሥራ ኢትዮጰያ አዲሰ አበባ ውስጥ የሚሰራ “DMC” የተባለ የመኖሪያ እና የንግድ ድርጀት “የእስላሚክ መንደር” የሚል ማስታወቂያ ሰምታችህ ይሆናል።ሰምታችሁ ስንቶቻችሁ ቸል እንዳላችሁትም እግዚሐር ይመዝግበው።

ማስታወቂያው እንዲህ ይላል፤=

«እንኳን ደስ አለዎ!~ በድጋሚ  የ“DMC” እስላሚክ መንደር ለሽያጭ ቀረበ። ቤቶቻችን የሸሪአን ሕግ ተከትለው  ዲዛይን  የተደረጉ መሆናቸውን ተመራጭ ያደርገዋል። አዛን እየሰሙ፤ ሳላት እየሰገዱ ቁርአን እየቀሩ .. የሚያድጉበት 60% ከወለድ ነፃ የባንክ ብድር የሚያገኙበት ልዩ የመኖረያ መንደር ለሽያጭ አቅርበናል»

የላል የማስታወቂያው ይዘት።

ይህንን ስንመለከት ኢትዮጵያ ወደ ፊት ከመራመድ ይልቅ እሰላሙ ክርስትያኑም ሃይማኖት የሌለውም ማሕብረሰብ እየተፋቀረ፤ እየተረዳዳ፤ እየተወያየን እየተገባበዘ አብሮ ባንድ መንደር የመኖር ልምዱን በማስተው ፤ እንደ “ወፍ” እራሱን ከመሰሉ ጋር ብቻ ባንድ መንደር ታጉሮ እንዲኖር  ማድረጉ ለማህበራዊ የሴራና የአድማ አደረጃጀት እንዲያመች፤ ወይንም “ለከፉ ቀን” ጥቃትም ተጋላጭ እንዲሆን፤ እየተደረገ ያለመሆኑ እርግጠኞች ልንሆን አንችልም።

የሸሪአን ሕግ ተከትለው  ዲዛይን  የተደረጉ ቤቶች መሆናቸውን በግልጽ ሲነግሩን ጥልቅ ምስጢሩን ስንመለከት “ክርሰትያኖች እዳይከራዩ የሸሪአን ሕግ ተከትለው  ሰለታነጹ፤ ከርስትያኑና እሰላሙ ተሰባሰቦ ሲኖር የነበረው አብሮነት  “ክሩን” የመበጣጠሻ መንገድ ነው።

በዚህ መልክ ቀሰ በቀስ በርካታ “እሰላማዊ መንደሮች” እየታነጹ “እሰላሞችና ክርስትያኖች” አብረው እንዳይኖሩ እየተራራቁ ፤ መንደሮች የእሰላሞች ፤ የአይሁዶች፤ የፕሮተሰታነቶች፤ የተዋህዶዎች ፤የሺዓ፤ የሱኒ፤ የዋሃቢ “መንደሮች” በሚል  መኖርያ መንደሮችን በሃይማኖት የመሰየም  ሴራ የተጀመረ መሆኑን አመላካች ነው።

በአዲስ አበባ ውስጥ የእስላሞች የመኖሪያ ቤት (እሰላሚክ መንደር የማስፋፋት) ግንባታ ቀስ በቀስ የመኖርያብቶች የሸሪዓ ግንባታ በሚከተሉና በማይከተሉ ማሕበርሰቦች  የመጫን ድብቅ አጀንዳና ክእስልምና ውጭ የሆኑ ዜጎች እንዳይከራዩ “በሸሪአ ግ” ዲዛይን ሰለተደርጉ ፤ ግንባታው አግላይ (ዲስክርሚናቶሪ ፕራክቲስ) ስለሆነ ይህንን የሚመለከታቸው “መብት ጥበቃዎች” የተለየ አትኩሮት እዲያደርጉ እየጠየቅኩ፡

አክሱሞች የአክሱም ከተማን የክርስትያኖች ከተማ እንዳደረጉት ሁሉ፤ እነዚህም ነገ አዲስ አበባ እና በተቀሩ ከተሞች “እሰላሚክ ሲቲ”  “የእስላሞች ከተማ” መስርተው ፤ እንደ “ከልል ባለቤቶች” ሁሉ “የሸሪዓ ህግ የተገነባ እሰላማዊ ከተማ” መስርተው የባለቤትነት ስሜት አድሮባቸው  «የመኖርያ መንደሮችን» ወደ “ሃይማኖታዊ ከተሞች” ለወጠው ማንም “ኩፍሪል/ኢንፊደል/ ወደ መንደሮቻቸውና ከተሞቻቸው እንዳይገቡና እንዳይከራዩ ቀሰ እያሉ መከልከል እንደማይጀምሩ ማረጋገጫ የሚሰጥ ሰው የለም።

“DMC የተባለ መሰሪ “ሪል እስቴት” በ ሳብቨርሲቭ የብከላ ጨዋታው መወገዝ አለበት። ለዚህም ምክንያቴ የሚከተለው  ነው፤

በመኖርበት ሀገር አምሪካ  <<Congratulations to all Muslim house buyers, this is Exclusively only to Islamic residents built by DMC real estate designed by Sheria Law>>የሚል እዚህ አሜሪካ ሀገር በሪል እስቴት ወኪሎቹ ስም ማስታወቂያ ወጥቶ ቢሆን ኖሮ ድርጅቱ ይከሰሳል።

«ለኢስላሚክ ነዋሪዎች» ብቻ መኖሪያ ቤት የማከራየት ወይም የመሸጥ ፖሊሲ  (ማስታወቅ) አድሎአዊ አሰራር በመሆኑ በፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ህጎች ደም ውስጥ ህገወጥ ነው። ነገር ግን፣ በሃይማኖት ድርጅቶች ለሚተዳደሩ አንዳንድ ንግድ ነክ ያልሆኑ ቤቶች ልዩ ሁኔታ አለ። ሆኖም ለሌሎች የሃይማኖት ተከታይ አባሎች እንዳያገሉ ይፈርማሉ።

በአጠቃላይ ለአብዛኛዎቹ የመኖሪያ ቤት አቅራቢዎች፣ የግል ባለንብረቶች፣ የሪል እስቴት ወኪሎች እና የንግድ ቤቶችን ጨምሮ፣ ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ  ማስተዋወቅ (ማስታወቂያ፤ ማግባቢያ...) አይፈቀድም ህገወጥ ነው። ኢትዮጵያ ግን በቅኝ ግዛት የተያዘች ፤መሪ አልባ ቤተሙከራ ሆናለችና የፈለገው እየመጣ የድፍረሳ ማስታወቂያውን ያለሰጋት ያሰራጫል።

የሳብቨርሲቩ የማናጋቱ ደረጃ በreal estate ውስጥም “ሃይማኖታዊ መንደሮች” በመገንባት ቀሰ እያለ በማዝገም  የማናጋቱ ደረጃ  በሃይማኖታዊ መንደርና በከልል ድምበሮች እያጠረ የግዝገዛ ሚናው የት እንደደረሰ ማየት ትችላላችሁ።

2ኛ-የኦሮሞዎች መንደር

አዲሰ አበባ ውስጥ በመኖሪያ ቤት ግንባታዎች እና የመሬት ዕደላ ላንድ  ምርጥ ነገድ (ለኦሮሞ) በገፍ መታደሉን ታሳውሳላችሁ (በወያነ የትግ ሥር ዓተ-መንግሥትም ትግሬዎችን በገፍ በመጥቀም እንደተጀመረ ሳንረሳ) ። በ 2019 እና 2020 (በፈረንጅ አቆጣጠር) ጀምሮ ይህ ምርጥ “ነገድ” ብለው የሚጠሩት ሕዝብ  አዲሰ አበባ ውስጥ የኦሮሞ ቁጥር እንዲበዛና አዲስ አበባን “ኦሮማይዝድ” ለማድረግ ‘ዲሞግራፊውን ለመቀየር’ እንዲያመቻቸው፤ አካባቢዎች በተነሳ ግጭት ሳቢያ ከመኖርያ ቀዬአቸውበኦሮምያ እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ  ከተፈናቀሉት ኦሮሞዎችና ከአቅራቢያ አካባቢዎች በአብቶቡስ እየጫኑ ወደ አዲስ አበባ በማስመጣት የኗሪ መታወቂያና 21 ሺ  ኮንደሚኒየም በነፃ እንደታደሉ Ethio 360 እና ዋዜማ ራዲዮ በተለያዩ ወቅቶች እንደዘገቡት ይታወሳል።

የተሰጡት ኮንድሚንየሞች ላይኛዎቹ ፎቅ ክፈሎች መኖርያቸው ሲሆን በሚኖሩበት ኮንድሚንሞች (የታችኛው ከፈሎች) ደግሞ “አንድ ለአምስት” ጥርናፈ በሚል ዕቅድ (በሃገሪቱ ወጭ/ገንዘብ) ተደራጅተው “1 ሱቅለ 5 ሰዎች” ንግድ እንዲከፍቱ በነፃ መሰጠቱ በውቅቱ Ethio-360 ሚዲያ ያዘጋጀው በሃበታሙ አያሌው ጥንቅር መቅረቡ ይታወሳል።

ይህ ስልት “የስነሕዝብ መፈራረስ “Demographic subversion” ወኪሎች የፕሮጀክታቸው ሌላኛው ክፍል ነው ማለት ነው።

ታዲያ እንዲህ ባለ ገዢዎቹ በሚጫወቱት የግዝገዛ ሴራ በምትናጥ ሀገር የሚኖረው የተናጠ ወጣት ተሎ ነቅቶ ገዝጋዦቹን የማስወገድ አቅሙ ከሌሎች ሀገር ወጣቶች እጅግ የደነዘ እና ዝግመተኛ ያደረጉት ምክንያቶች በተከታታይ ክፍሎች የጠቀሰኳቸው ምክንያቶች ናቸው።

በሚቀጥለው ክፍል ቀውስ/ Crisis/ እና

“እርጋታ የሌለው እርጋታ” የምባሉት የማናጋት ሂደቶችን ተመልክተን ጽፉፌን እደመደማለሁ።

እስከዚያው መልካም አዲስ ዓመት እያልኩ ጥሩ  የጀሮ ማድመጫ (Headphone stereo) ይዛችሁ ይህንን ስዕለ ድምፅ (አውዲዮ-ቪዲዮ) እየተመለከታችሁ አድምጡና እምባችሁን በመቆጣጠር ስሜታችሁ ሳይነካ ያ ዘመን ለሚናፍቃችሁም ሆነ ያ ዘመን ለምትቃወሙት የባንዳ ውጤቶች ሁሉ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ! 

ቪዲዮውን አቀናበሮ የለቀቀልን ስንታየሁ ቸኮልን አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay


 

 


 

 

 

 

No comments: