በኢጣሊያ ቅኝ አገዛዝ ሥር ማንነቱ ከመሰረተ ሕዝብ ጋር መኖር አንችልም
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
9/19/25
ባንድ ወቅት እንደ ወንድሜ የማየው ወዳጄ ስለ አንድ የበላበትን ምጣድ ሰባሪው ባንዳውና ዘረኛው
“ኤርትራዊ ነኝ” ማለት የማያሳፍረው ጣሊያን ከ4ኛ ክፍል በላይ እንዳይማር ያገደቺው፤ ወደ ኢትዮጰያ መጥቶ እምየ ኢትዮጵያ “ሃርቫርድ
ዩኒቨርሲቲ” ድረስ ለከፈተኛ ትምህርት ልካ ያሰተማረቺው ሰለ ከሃዲው “አስመሮም ለገሰ” አንስተን ስናወራ፤ ወዳጄ እንዲህ አለኝ፦
«....ከኤርትራውያን ጋር ያለንን ግንኙነት በቁም ነገር አሰብኩና ከ35
ዓመታት በፊት እንደ ሕዝብ እንኳን ከእነዚህ የኢጣሊያ ቅኝ አገዛዝ ሥር ማንነታቸው ከተመሰረተ ሕዝብ ጋር መኖር አንችልም ብዬ ደመደምኩ። This new
Eritrean identity is inimical to everything that is Ethiopian. ይህ አዲስ ኤርትራዊ ማንነት «ኢትዮጵያዊ የሆነን ሁሉ የሚጠላ ማንነት ነው።»
ይልና በመቀጠልም እንዲህ አለኝ፤
የኢትዮጵያ መሪዎች፣ ፖለቲከኞች እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ተራው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያልተረዳው ትምህርት ይህ ነው። በዙዎቹ
በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ወደ ሃርቫርድ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲዎች ተልከው ከፍተኛ ትምሕርት ቀስመው ሲመለሱ ላስተማራቸው
የኢትዮጵያን ሕዝብ የከፈሉት
ብድር ያስተማራቸውን ሕዝብ በጥላቻ ማየትና የባሕር በር መዝጋት ነበር። በዚህ ዓይነት
የጥላቻ መንገድ የፍረጀህን ሕዝብ ወንድማማቾች ነን የሚል ቃላት መጠቀም ራስን ለሁለተኛ ጊዜ ማሞኘት ነው ።
በመቀጠል አዳንዶቹ ኢትዮጵያን ይወዳሉ የሚባልላቸው ሳይቀር እይታቸው የተበከለ ነው። ይልና
ወዳጄ በእውነት ወቅቱ ሲፈቅድ በሕይወቴ ዘመን ስለዚህ ጉዳይ መጻፍ እፈልጋለሁ አለኝ። ኢትዮጵያዊ ማንነትን እናከብራለን የሚሉት እንደ ተከስተ ነጋሽ ያሉ ኤርትራዊያን እንኳ እንደ እነ አፄ ምኒልክ ባሉ ታላላቅ መሪዎች ላይ ጥላቻ እና ምሬት ያላቸው ናቸው። ከጥቂት አመታት በፊት በቤልጂየም በተደረገ ስብሰባ ላይ ተከስተ አፄ ምኒልክን እንደ ሰካራም (የአልክሆል ሱሰኛ) አድርጎ ለመሳል ሞክሯል። በኋላ በስዊድን በተካሄደው የአድዋ በዓል ላይም ምኒልክን ለአድዋ ድል ማሞገስ ስህተት ነው ብሏል። ክሬዲቱን መውሰድ ያለባት ጣይቱ ነች ብሏል።
እሰክዚህ የወረዱ ትንንሾች
ናቸው (This is the leven of these small individual Eritreans.)። ካለ ብኋላ፦
ኢትዮጵያ ቅኝ ገዝታናለች የሚለው በንጉሡ ዘመነ እንግሊዝ አገር “ኦክስፎርድ” ዩኒቨርሲቲ ተልኮ
የኪስ ገንዘብና የሚማርበትን ወጪ ኢትዮጵያ ከፍላ ያስተማረቺው ከዚያም “የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ” ሆኖ የኢትዮጰያ ዜጎችን
በተሰጠው የመጨረሻው ከፈተኛ የፍትሕ ሰጪ ሥልጣን የማሳነቅ (ስቅላት የማስፈረድ) ወይንም የማዳንና እና እሰከ ዕድሜ ይፍታ ማስፈረድ
የሚችል ሥልጣን ተሰጠቶት የነበረው “በረከት ሀበተ ስላሴም” ስትመለከት የባስው ከሃዲና የ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት ነው።
በ1987 ወይም 1988 አካባቢ ስዊድን በተካሄደው የኤርትራ ስብሰባ ላይ «እኛ ኤርትራዊያን ለኢትዮጵያ “የአንድ መቶ ዓመት የቤት ሥራ” ሰጥተናቸዋለን ሲል ተናግሯል። ይህ አባባል ‘ከግብረ አበሮቹ’ ከወያኔዎች ጋር
ሆነው የሰሩትን ኢትዮጵያን በጎሳ የሚከፋፍል የፖለቲካ ፕሮጄክት መሆኑ ነው።
እንግዲህ የበረከት ሀበተ ስላሴ አባባል ስትመለከት ፤ ህወሓት የሚባል የትግሬ cabal (ምስጢረኛ መሰሪ) ቡድን እና እንደ ኦነግ ያሉ ቡድኖችን አስታጥቀውና ደግፈውት የነበረውን ለኛ የሰሩልንን “የአንድ መቶ ዓመት የቤት ሥራ” ፕሮጀክት ተጠቅመው ምን ያህል እንደተሳካላቸው ተመልከት።
እነዚህ በሕሊና የቀጨጩ ትንንሾች (little
men) ጥላቻቸው በወገኖቻቸው ላይ ያደረሰውን ጉዳት እንኳን ማየት አልቻሉም። ለማንኛውም የኤርትራ ብሔረተኞች ሻቢያም በለው ጀብሃ ለኢትዮጵያ በጎ የማያስቡ ክፉ ሰዎች ናቸውና ፤ ከሁለቱም ለኢትዮጵያ የሚመጣ በጎ ነገር አለ ብዬ አላምንም፡፡ ተለያይተን በጉርብትና ከመኖር ውጭ አንድነት፤ አብሮ በአንድ ሀገር ውስጥ ከእነሱ ጋር እንኑር የሚለውን ሃሳብ እጅግ የምቃወም ነኝ፡፡»
ሲል ስለ እነዚህ “የእናት ጡት ነካሾች” አብሮ መኖርነት ወዳጄ ያጫወተኝን አቋም ለናንት አቅርቤ
አለሁ።እኔም የወዳጄ ሐሳብ እጋራለሁ።
እናንተስ “ወንድሞቻችን፤ እሀቶቻችን” ስለ እምትልዋቸው ያስተማረቻቸውን ሃገር በጠላትነት የሚያዩ ከሃዲዎች ምን ትላላችሁ?
ከኤርትራውያን ጋር እየተጋፈጥን ያለነው የቸገረን ነገር የነፃ ሀገር ድፍረት ይዘው ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመጡ ተስለው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለሱ የጉረኞች ድንጋይ ወርውረውብንና ተሳልቀውብን ሄደው ስያበቁ ነፃነት የተባለው ነፃነታቸው የጉስቁልና ነፃነት መሆኑን ሲያውቁ ሳንፈልጋቸው ወደ ገራገሮቹ ወደ ሞኞቹ አገር ወደ ኢትዮጰያ እንደገና ተመልሰው ለምነው እየመጡ ሃብታችንና የኢትዮጰያዊያን መኖርያዎችና ሥራዎች እየተጋሩ ወንጀል እየሰሩ፤ መሸጋገሪያቸው አድርገዋት “በዓይነ ደረቅ ልብ ያደርቅ” ሳያፍሩ “ኢትዮጰያ ወደብ ያጣችበትን የነፃነት ቀናቸው ለማክበር” በመላው የኢትዮጵያ ከተሞች የኢሳያስ ባንዴራ እዲያውለበልቡ በመለስ እና በአብይ አሕመድ ተፈቅዶላቸው 35 አመት ሙሉ ምን ታመጡ እያሉን ነው።
እኛ ሳንደርስባቸው እነሱ እየመጡብን ተቸግረናልና “የምጠላት ዓይጥ ምን ታመጪ ብላ እፊቴ ላይ ቆመች” የምትለው የእናቴ አባባል ደረሰብንና ሳንፈልጋቸው ወደ እኛ እየመጡ ይህ ድፍረትስ እንዴት እንከላከለው? ነው ለአንባቢዎቼ የምጠይቀው።
ኢትዮጵያን በጠላትነት ከሚያይ በኢጣሊያ ቅኝ አገዛዝ ሥር ማንነቱ ከመሰረተ ሕዝብ ጋር መኖር አንችልም። የባሕር በራችን በሃይል
እና ሕግ በጣሰ ሴራ ተወሰዶብናል። በሃይል የተዘጋብንን በር በሃል እናስከፈተዋለን። ይህንን እውን የሚያደርጉ ደጎሞ የወለድናቸው
የኛ ኮቴ የተከተሉ አዳዲስ ትውልዶች ሰንደቃላማችንን አንስተው ኢትዮጵያዊ ብሔረተኛ መሪ ሲነሳ ይፋለማሉ፤ ጊዜ እየጠበቀ እንጂ ያለ ጥርጠር ያንን
በር ያሰከፍቱታል። ከበባውና ሴረኛው ቢበዛም ሕግ ያልገዛው ነፃነት ‘ሃይል ይገዛዋል።
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay

No comments:
Post a Comment