ሎሚ ተራተራ የዝናሽ ታየቸውን ነገር
አደራ
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
4/27/23
ከላይ ፎቶ የሚታዩት የሸዋ ክ/ሃገር ሁለቱ “ጎስታፖዎች” የነበሩ የሽዋ
ሮቢት ከንቲባ የነበረው “ውብሸት አያሌው” እና ዛሬ የተሰናበተው ሌላው “የጎስታፖዎቹ” አመራር አባል የነበረው የብልግና ፓርቲ ጽ/ቤት ዋና ፀሓፊ
የነበረው ግርማ የሺጥላ።
ዛሬ የተሰማው ዜና አማራን ሲያሰቃይ የነበረው የአብይ አሕመድ ልዩ አሽከር
የነበረው ነብሰገዳዩ “ግርማ የሺ ጥላ” እርምጃ ተወስዶበታል። ማን
ገደለው? የገደለው ይግደለው አያገባኝም! የሚያገባኝና ደስ ያለኝ ሕዝብን ከማሰቃየት ተሎ ብሎ በፈጣሪ ትዕዛዝ በመወገዱ ነው።
ዲያብሎሱ የ666 ቅጥረኛ የነበረው የወያኔው መለስ ዜናዊ ሲሞት ደስታችንን
የገለጽን በጣት የምንቆጠር ሰዎች ነበርን፡ እኔ እራሴ (ጌታቸው ረዳ) እና ታዘበው አሰፋ እንደሁም ስማቸው የማላስታውሳቸው ጓዶቹ
ዋሺንግተን የወያኔ ኤምባሲ ፊት ለፊት ተገኝተው ደስታቸውን የገለጹ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ስንደሰት፤ እነ ታማኝ በየነ እነ…
እነ….፤ እነ ወ/ሮ እና ወ/ት ምድረ አዛኝ ሁላ”ልቤ ቆመች፤ ውሃ ስጡኝ፡ ልቤ ተሰበረ፤ መቆም አልቻልኩም፤ ተቀማጥ ተቅማጥ አለኝ፡
ተንፈረፈርኩ፤ አስፕሪን ስጡኝ፤ የጨጓራ መድሃኒት አቀብሉኝ…. እያሉ ያለቃቀሱ ሴቶችና ወንዶች አይተናል። ይህ የዋህነት ሳይሆን
ምነው ቢቆይና ሕዝባችንን ባሰቃየ ከማለት አያልፍም።
እነ ያሬድ ጥበቡ እነ ልደቱ አያሌው በጓዳቸውና መሪያቸው በመለስ ዜናዊ
ሞት ልባቸው መሰበሩን መግለጻቸው ብቻ ሳይበቃ “ኢትዮጵያ አንድ ሰው አጣች” እያሉ በሕዝብ ህይወት ሲያላግጡ ነበር። ዛሬም ሳያፍሩ
ስለ ሕዝብ ደህንነትና ፖለቲካ ሲየወሩ ትንሽ አያፍሩም። ዛሬም ግርማ የሺ ጥላ የተባለ ማሃይም ሲቀጭ በየሚዲያው “ኡ ኡታ ያቀለጡ”፤
ልባቸው የተሰበረ ማሃይማን ሰዎች አይቻለሁ። ይገርማል። የነዚህ መሃይማን ርቀት የሄዱበት ግርማ የሺ ጥላን 360 ነው ያስገደለው እያሉ በመወንጀል የድርጅት ስም ማጥፋት አሜሪካ ውስጥ
እንደሚያስከስሳቸውም ሳያውቁ ድንቁርና ሲያስተጋቡ መስማት የማሃይሞች መበራከት የሚገርም ነው።
አንዳንድ አስተዋዮችም እንዲሁ ከዚህ ዓለም በመወገዱ ደስታቸውን የገለጹ አርበኞችም አሉ። ደስታ ምንም ማለት ሳይሆን
ስሜት ነው። ስሜት ደግሞ ምክንያታዊ ነው። ደስ የሚልህ ፤ እንቅፋት የነበረው ሲወገድ የሚታይ ነጽብራቅ ነው። ሰዎች በሞት ሲያዝኑም
ለሰውየው ቀረቤታ ለማሳየት የአንጸባርቁት ስሜት ነው ማለት ነው። “በጎስታፖዎቹ” አስተባባሪ ሞት ሊያዝን የሚገባቸው ሰዎች ካሉ
አብይ አሕመድና አሽከሮቹ ብቻ ናቸው። እኛም፤ ደስታችን እየገለጽን እናንተም መንፈራነቃችሁን ቀጥሉበት። ሕዘብን የሚያሰቃዩ ሰዎች
ምክር የምንሰጠው ከባሕሪያችሁ ካልታረማችሁ የጊዜ ጉዳይ እንጂ እናንተም ዕጣ ፈንታችሁ የግርማ የሺ ጥላ እና “የውብሸት አያሌው”
ፅዋ ትጎነጫላችሁ።
ይህ ሥርዓት እኮ ጸረ አማራዎችን እየፈለገና እያበረታታ እነ “አለምነህ
መኮንን” የመሳሰሉት ቅጥረኞች አሁንም ከሹመት ሹመት እየሸለመ እያስኖራቸው ነው። አለምነህ መኮንን ታስታውሱታላችሁ? የአማራው ገበሬ እንዲህ ሲል ሲቀልድበት የነበረ ሰው ነው፡
<<…ስንፋጭ ትምክሕቱ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ተግባብቶ መኖር የማይችል፤
የሸተተው እግሩ እንዳይሸት ከጫማው ስር ‘የባሕር ዛፍ ቅጠል ያደረግበታል”፤ /ዚስ ኢዝ ቴክኖሎጂ!…>> እያለ ሲያሾፍ
የነበረ ሰው ነው። ዛሬም በሕይወት አለ። ዛሬ ተራው የግርማ የሺ ጥላ ሆነ እንጂ አለምነህንና ደመቀ መኮንን አሊን ነበር አስቀድሞ
ማስወገድ። ሆኖም ሸዋ እርምጃ በመውሰድ ቀዳሚ ነች።
ግርማ የሺጥላ ከንቲባ ተብየው ከነበረው “ከውብሸት አያሌው” ሞት አልተማረም። ትዝ ይላችሁ እንደሆነ፤ ሽዋ ውስጥ ከግርማ የሺ ጥላ በፊት እርምጃ የተወሰደበት
የአብይ አሕመድ “የጎስታፖ የቤት ስራ ደፈጻሚ” የነበረው የብልግና ፓርቲ አባል የሽዋ ሮቢት ከንቲባ የነበረው “ውብሸት አያሌው”
ነበር አሁን ባለ ተራው ግርማ የሺ ጥላ ነው። ሰዎች ካለፉት ሰዎች አይማሩም ስለሆነም በዚህ በይነጋል በላቸው የወደድኩለት ጥቅስ
ልሰናበት። ይነጋል እንዲህ ይላል
<< (የግርማ የሺ ጥላ) የሚያሣዝነው ሞቱ ሳይሆን አሟሟቱ ነው።
ፀረ አማራዎች ለሤራና በሤራም ይሁን፤ከአቢይም ሆነ ከአቢይ ተቃዋሚም ይሁን መገደላቸው አይቀርም”፡ ይህ የዛሬው አሣዛኝና አስደሳች
ክስተት የሚጠቁመው ይህንን ነው። አስደሳች ያልኩት ሟች ፀረ አማራ ስለነበርና የአማራን ዕልቂት ከሚያሣልጡ ወገኖች ስለሚያካትት
ነው። አሳዛኝ ያልኩት ማንም ሰው ከሕግ ውጪ ባይሞት የሚሻል በመሆኑና ገዳዩ ለሸር ሲል አቢይ ከሆነ ነው። በተረፈ አቢይን ያመነ
ጉም የዘገነ ነው። ይጠቅመኛል ካለ ነገ ጧት “ጋንኤል ክስረትን”
ከነገወዲያ ደግሞ “ዝናሽ ታያቸውን” ይደፋና “ሓሳብን በሓሣብ ማሸነፍ ያቃታቸው ጽንፈኞች የአቃጣሪየንና ‘ማነው’ የአማካሪየንና
የባለቤቴን ነፍስ ነጠቁኝ’ ሊል ይችላል።
……ከቅርቦቹ ከኢንጂነር ስመኘውና ዶር አምባቸው ጀምሮ እንኳን የሚገድላቸውን
ዜጎች ብንቆጥር ሥፍር ቁጥር የላቸውም። የሚገርመኝ ይህን ሁሉ ሕዝብ የሚጨፈጨፈውና አማራና ትግሬን በሚሊዮኖች የሚረፈርፈው እሱ
ስንት ዓመት መሬት ላይ ሊኖር አቅዶ ይሆን???>>
ይላል ይነጋል ይህንን አስመልክቶ። እኔ ደግሞ የሚቀጥለውስ
ባለ ተራው ማን ይሆን? <<ሎሚ ተራ ተራ የዝናሽ ታየቸውን ነገር አደራ>> እያለ ሞቱን እና ውርደቱን እየተጠባበቀ
ያለው አቢይ አሕመድ ይሆን? “ለሁሉም ጊዜ አለው” አለ ሰለሞን ጠቢቡ!!
በሰላም እንሰንብት!
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
No comments:
Post a Comment