Monday, April 10, 2023

እንኳን ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ዋዜማ አደረሰን!! ዳግማዊ ጉዱ ካሣ Ethiopian Semay 4/10/23


እንኳን ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ዋዜማ አደረሰን!!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Ethiopian Semay

4/10/23

የመጨረሻ ተጋጣሚዎቹ ሁለት ኮርማዎች በግልጽ ሜዳ ተጋጥመዋል፡፡ ፉርሽካውና የተመጣጠነው መኖ ቀርቶበት ደረቅ ሣር እንኳን እንዳይግጥ አፉን ተለጉሞ ከ50 ዓመታት በላይ በየሄደበት እንዲሳደድ እንዲገደልም ተፈርዶበት የነበረው ከሲታ ኮርማ ጠላቶቹን አንበርክኮ እንደ ዳልጋ አንበሣ የሚያገሣበትና መላ በረቱን ነጻ የሚያወጣበት፣ ፍትኅንም የሚያሰፍንበት ጊዜ ላይ ደርሷል፡፡ ሃሌ ሉያ በል ክርስቲያን፤ አልሃምዱሊላ በል ሙስሊም፡፡ ሁልህም በየእምነትህ ፈጣሪህን አመስግን፡፡

 ከሩብ ምዕት ዓመት በላይ የጮህንበት ሀገራዊ ነጻነትና ትንሣኤ እንዲህ ከፊት ለፊታችን በክብር ቆሞ ማየት በእጅጉ ያስደስታል፡፡በውጪ ያላችሁ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ወደሀገራችሁ ለመግባት ዕቃችሁን ሸካክፉ፡፡ በሀገራችሁ የዘመናት ምስቅልቅሎሽ ተስፋ በመቁረጥ ከሀገራችሁ ለመውጣት ተስማሚ ወቅትና ምቹ ዕድል ትጠብቁ የነበራችሁ ወገኖች አሁን ላይ እንድትጽናኑና የሀገራችሁን ነጻነት እዚሁ ሁናችሁ እንድትጠባበቁ በእምዬ ኢትዮጵያ ስም እጠይቃለሁ፡፡

 አዎ፣ ብዙውን ጊዜ በምጽፋቸው መጣጥፎች ጨለምተኝነት በብዛት ይንጸባረቅብኝ እንደነበር እኔ ራሴም አልክድም፡፡ አሁን ግን በመለኮታዊ ተስፋ ተሞልቼ የምለውን እላለሁ፡፡

ኢትዮጵያ የትግሬን አገዛዝ እስኪያንገሸግሻት አየች፡፡ በዚያም አገዛዝ ክፉኛ ተጠበሰች፤ ተንገበገበች፡፡ የማታውቀው የዘርና የቋንቋ ፖለቲካም አመሰቃቀላት፡፡ በዚያም ሳቢያ ወደፈጣሪዋ አምርራ አለቀሰች፡፡ ዕንባዋ መና አልቀረም - በ26ኛው ዓመት በ10ኛው ወር በ4ኛው ቀን አንድዬ ገላገላት፡፡ ግን የዕዳ ደብዳቤዋ ሊቀደድ ያልቻለበት የምታወራርደው ውዝፍ ዕዳ ስለነበር ግፍና በደሉ በሌላ ተረኛ ተባብሶ ቀጠለ፡፡ ያም ዮዲት ጉዲታዊና አህመድ ግራኛዊ የግፍ አገዛዝ ቅጥያ ይሄውና አምስት ዓመቱን ደፍኖ ስድስተኛውን ያዘ፡፡

ኢትዮጵያ የነጻነትንና የሀገራዊ ትንሣኤን ምንነት ታጣጥም ዘንድ የትግሬን አገዛዝ እንዳየች ሁሉ በኦሮሞ ስም የሚመጡ በዘር ግን በአብዛኛው ኦሮሞ ያልሆኑና ለሥልጣን እርካብ መረገጫ ሲባል ብቻ ኦሮሞነትን እስከጥግ የሚጠቀሙ ኦሮሙማዎችን ማየት ነበረባት - ብሂሉም እኮ “አንዱን ካላዩ አንዱን አያመሰግኑ” ይላል፡፡ ምክንያቱም ትግሬ ከታዬ ኦሮሞም መታየቱ አንደኛ በሃይማኖቱም በመንግሥታዊ ሥርዓቱም መረን የለቀቀንና ከፈጣሪ መንገድ የወጣን ሕዝብ መቅጣት አሁን የተጀመረ ባለመሆኑ፣ ሁለተኛ አንዱንና የተሻለ ነው የሚባለውን ካዩ ዘንዳ ሌላውንና የከፋ የከረፋውን ማየቱ የወደፊቱን ወርቃማ ዘመን ለማመስገን ስለሚረዳ የሆነው ሁሉ ሆነ፡፡ ገና ብዙ የሚሆን ነገርም አለ፡፡ ተጀመረ እንጂ አላለቀምና፡፡

በነገራችን ላይ የሕወሓትን ዘመን አሁን ላይ ሆነን ዘወር ብለን ስናስበውና ካለንበት የኦሮሙማ ዘመን ጋር ስናነጻጽረው የሲዖልና የኤዶም ገነትን ያህል ልዩነት እንዳለው ለማተባችን ያደርን ወገኖች እንመሰክራለን፤ ወያኔ ሆይ! ያኔ በጽሑፎቼ የሰደብኩሽ ሁሉ እውነት ቢሆንም ቅሉ ይቅር በይኝ፡፡

ትግሬዎች ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ እንደተቆጣጠሩ ሶማሌ አካባቢ ሄደው ውክቢያና ሀለው ቀጠው ሲፈጥሩ አንዱ አረጋዊ ሶማሌአይ፣ አገር አገዛዝ እንኳን እንደ አማራ የለም” ማለቱን በጊዜው ሰምቻለሁ፡፡ እውነቱን ነው፡፡ አማራን በአስተዳደር ሥራ የሚያማው የለም፡፡ አማራ እንደአጠቃላይ በአማራነት የጎሠኝነት ጥምብ ገመድ ስለማይሳሳብ በችሎታና ብቃት ለተመሠረተ አስተዳደር ይበልጥ የቀረበ ነው፡፡

መለስ ዜናዊ አንድ ወቅት “ሥልጣን ለኦሮሞ መስጠት ብርጭቆ ለሕጻን ልጅ እንደመስጠት ነው” ብሎ እንደተናገረ ሰምቻለሁ፡፡ እዚህ ላይ የኦሮሞ ስም በማይረባ ወይንም በሚያስወቅስ ነገር ሲነሳ ወዳጄ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣ ወይንም ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ የሚያኮርፍ ከሆነ፣ የትግሬ ስም በሕወሓት ምክንያት በክፉ ሲነሳ ከአማራ በላይ ለአማራ የሚታገለው የቅርብ ወዳጄ የኢትዮሰማይ ብሎግ አዘጋጅ ትግሬው ጌታቸው ረዳ ከተቆጣ፣ አማራ በመጥፎ ሲነሣ ዘመነ ካሤ ከተቀየመ መግባባት ላይኖር ነው፡፡ ስለሆነም የትግሬም ሆነ የአማራና የኦሮሞ ስም በመጥፎ የሚነሣው ይበልጡን የሕወሓትን፣ የመሸጦ ባርያውን ብአዴንና የኦነግ/ኦህዲድን ዓላማና ፍላጎት እውን ለማድረግ ላለፉት ሦስትና አራት አሠርት ዓመታት ኢትዮጵያን ያንገላቱ የሁሉም ነገድ ዜጎችን ለማጣቀስ እንጂ አብዛኛውንና ጤናማውን እንደማይጨምር አስምሬበት ማለፍ እልፈጋለሁ፡፡ ከመሬት እየተነሱ “አይ፣ ይሄማ እኔን ለመሳደብ ነው” የሚል ጠባብ ግልፍተኛ ካለ መብቱ ነው፤ ይንተክተክ፡፡ እንጂ በስመ ኦሮሞ፣ ኦሮሞዎቹን አፄ ምኒልክንና አፄ ኃ/ሥላሤን ለመሳደብ የሚቃጣኝ ደደብ አይደለሁም፡፡

የወይዘሮ ባፈናና የማንትስ ጉዲሣ ልጅ የሆኑትን የአፄ ምኒልክን ኦሮሞነት ማንሳት መቼም በአክራሪ ኦሮሞዎች ዘንድ ወንጀል ነው፡፡ አቢይ ባቅሙ “አይ ኦሮሞ!” እያለ እወክለዋለሁ በሚለው ነገድ ላይ ሲያፌዝ አንድም ሰው ያልተቃወመው ለምን እንደሆነ ግን አልገባኝም፡፡ ድንገት ትዝ ብሎኝ ነው፡፡ ምን ዓይነት ዕንቆቅልሸ የሆነ ልጅ ጣለብን ግን!!

የመለስን ትንቢታዊ ንግግር ባለፉት አምስት ዓመታት አረጋገጥን፡፡ ማብራሪያም አያስፈልገውም፡፡ እንዲያውም ኦነግ/ኦህዲድ ከያዘው ሥልጣን ይልቅ ሕጻን የሚይዘው ብርጭቆ የበለጠ ዕድሜ አለው ማለት ይቻላል፡፡ ያለፉት አምስት ዓመታት ያላሳዩን ጉድ የለም፡፡ ለዚህም እማኝ መቁጠር አያስፈልገንም፡፡

የሰሞኑ ግን ይብሳል፡፡ የኦሮሙማ ተጨፈኑ ላሞኛችሁ ከማሳቅም አልፎ ጤናማ ኦሮሞዎችን ሣይቀር በሀፍረት የሚገቡበትን አሳጥቷል፤ የሰውን ዘር በመላው አንገት ያስደፋል፡፡ ብዙ ኦሮሞዎች በሚዲያ እየወጡ ሲቃወሙትም አያለሁ፡፡ አንድ ሰው ካላበደ በቀር ጠላት የከበበውን ሕዝብ “መሣሪያ አውርድና በባዶ እጅህ መክተህ ከታወጀብህ ዕልቂት ትረፍ” አይባልም፡፡ የኦሮሞ “ምሁራን” ምንም እንኳን ልክ እንደትግሬ ምሁራን ሁሉ፣ አማራን ከአፋርና ከሱማሌ እንዲሁም ከሲዳማ ሕዝብ በቁጥር እጅግ ያነሰ አናሳ ብሔር ነው ቢሉትም እንደውነቱ ግን ይህን በ40 እና በ50 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ ለማጥፋት እስከዚህ ድረስ የዕውር ድንብር ጉዞ መጓዝ የዞረ ድምር እንዳለው ሊያውቁት በተገባቸው ነበር፡፡ ልዩ ኃይሎች መፍረስና ወደማዕከላዊነት መዛወርም ካለባቸው በሚታወቁ በርካታ ምክንያቶች የተነሣ ሥራው መጀመር የነበረበት ኦሮምያና ትግራይ እንጂ አማራ ላይ አልነበረም፡፡ ይህ የሆነው ግን ለበጎ ነው፡፡

ወለጋና ሻሸመኔ አማራን የጨረሱ ሲመስላቸው ቤቱን ማፍረስና ንብረቱን መቀማት ወይም ማውደም ሲሻቸውም መግደል የጀመሩትን አዲስ አበባና አካባቢዋ የሚገኝን አማራ መጨረስ አማራቸው፡፡ ያን ለማድረግ ደግሞ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ነበረባቸው፡፡ ምክንያቱም አዲስ አበባና አካባቢዋ ለጎጃምና ለሸዋ ቅርብ እንደመሆናቸው የአዲስ አበባን እሪታ ሲሰሙ ታጣቂዎች መምጣታቸው አይቀርም፡፡ ስለሆነም አዲስ አበቤዎች ሲታረዱ ደራሽ እንዳይኖር አማራው ባለበት ትጥቅ እንዲፈታና ሌላው ግን በተለይም ኦሮሞ እንደሁኔታው ወደፊት እንደሚታይ የኦሮሞው ፌዴራል መንግሥት በአንደኛው ሎሌው መግለጫ ሰጠ፡፡ የሚገርም ክፍለ ዘመናዊ ቀልድ፡፡ እኔ ዱሮ እነዚህ ሀፍረትና ይሉኝታ የሚባሉ ቃላት በትግርኛ መዝገበ ቃላት ብቻ ነበር የሌሉ የሚመስለኝ፡፡ ለካንስ በኦሮምኛም የሉም፡፡ ንግግራቸው ሳይቀር እንዴት እንደሚከረፋ!

እዚህ ላይ መነሳት ያለበት አንድ ዋና ነጥብ አለ፡፡ የሩዋንዳ ጄኖሳይድ ከተፈጸመ በኋላ ፈረንጆቹ “እናውቅ ነበር” የሚል ልግጫ ቢጤ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ የኛም ሲያልፍ ልክ እንደዛው መናገራቸው አይቀርም፡፡ ነገር ግን መናገራቸው መብታቸው ሆኖ እኛ ደግሞ በአማራና በኦርቶዶክሳውያን ለሚደርሰው ሁሉ ተጠያቂዎቹ እነሱ መሆናቸውን ፍጂቱ በተሟላ አቅሙ ከመጀመሩ በፊት እንነግራቸዋለን፡፡ ለዚህ ፍጂት ምድራዊ ፍርድ ቤት ባይኖረን ለምድር ለሰማዩ ጌታ ለኅያው እግዚአብሔር ከአሁኑ አቤት እንላለን፡፡ የኛ አቤቱታ ደግሞ ምን እንደሚያመጣባቸው እናውቃለን፡፡ እንጂ እየሆነ ያለውን ሁሉ አሳምረው ያውቃሉ ብቻ ሳይሆን ለፍጂቱ ሁለንተናዊ ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡ እነሱም የዘሩትን ያጭዳሉ፤ ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር፡፡

ሁሉንም ቢያወሩት ሆድ ባዶ ይቀራል፡፡ መከላከያ፣ ፌዴራል ቅብጥርስዬ የሚለውን ተውት፤ ከናካቴውም እርሱት፡፡ አሁን የገጠሙት ኦሮሞና አማራ ናቸው፡፡ ኦህዲድ ፌዴራሉን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረውና ኦሮምያን ከአንድ የአውሮፓ ሀገር ባልተናነሰ ምናልባትም በበለጠ በዋናነት የጦር ሠራዊቱን ጨምሮ በሁሉም ረገድ እንደአንድ ሀገር እንዲሆን ያደረገው አለምክንያት አይደለም፡፡ የኦነግ/ኦህዲድ የዘመናት ቅዠት እውን እንዲሆን ዕቅድ የተያዘው ኦነግ በጉዲፈቻ ባሳደገው አህመድ አቢይ አማካይነት መሆኑ ከታወቀ ሰንብቷል፡፡ እናም ይህ በማንነት ቀውስ የሚንገላታውና በእናቱ ትንቢት የሰከረው ወፈፌ ልጅ አራት ኪሎን ሳይለቅ በቅርጽ አሜባን መሰሉ የኦሮምያ ኢምፓየር በአስቸኳይ መመሥረትና ምሥራቅ አፍሪካን መቆጣጠር አለበት፡፡ ለዚህ ግብ ስኬት ደግሞ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ሀብት ወደኦሮሙማ ዞሮ ከምድር ተሽከርካሪ እስከሰማይ በራሪ አማራን ለማምሸክ ዝግጅቱ ተጠናቆ የጦርነቱ ፊሽካ ተነፍቷል፡፡

የቀበሮዋንና የበሬውን ተረት የምታስታውሰን ሕወሓትም ከሁለቱ ጦርነት እርዚቅ አገኛለሁ ብላ አንዴ በሞራል አንዴ በጦርነቱ ሱታፌ የበኩሏን ለማገዝ ዊኒጥ ዊኒጥ እያለች ነው፡፡ ያለሰው ደም ግብር የማይኖሩት ወያኔና ኦነግ ከገቡበት የጦርነት አዙሪት እንዴት እንደሚወጡ በቅርቡ የምናየው ነው፡፡ ብአዴንን እርሱት፤ እሱ የጦስ ዶሮ ነው፡፡ ከኦነግ ካመለጠ ከሕዝቡ አያመልጥም፡፡ አሁን ጣር ላይ ነው፡፡

እንዲህ ይሁን እንዲያ አይሁን የምለው ምክር የለኝም፡፡ ደግሞም እኔን ብሎ መካሪ፡፡ ግን ግን አወዳደቅንም ማሳመር ብልኅነት ነውና በተለይ አማራን ለማጥፋት የተሰለፋችሁ ሁሉ በጊዜ ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ ለማለት እወዳለሁ፡፡ ይህን የምለው በሁለቱም ወገን የሚደርሰውን የሰውና የንብረት ውድመት ከመቀነስ አኳያ እንጂ ሁን ያለው ሳይሆን ይቀራል ከሚል የዋህነት አይደለም፡፡ ትልቁ ነባራዊ እውነት ለማሸነፍ ከፈለግህ ከግፈኝነትና ከበደለኛነት ራስህን አግልል፡፡ ጎልያድ በዳዊት ወንጭፍ የተሸነፈው ለምን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ሣምሶን በአህያ መንጋጋ በ300 እና 400 የሚገመቱ ጠላቶቹን እንደዝንብ ያረገፈው የተለዬ ፍጡር ሆኖ ሳይሆን በፈጣሪ ፀጋና ሞገስ ነበር፡፡ አማራም የሚያሸንፈው ልክ እንደዚያው ነው ጅሌ፡፡

አቢይ አህመድ ድሮን መጠቀሙ አይቀርም፡፡ ያለ የሌለ ሰብኣዊና ቁሣዊ ኃይሉን አሰልፎ አማራን ለማንበርከክ ይሞክራል፡፡ በዚያም ሳቢያ በርካታ ታኅታይ መዋቅሮች ይወድማሉ፡፡ በዚህም በዚያም ብዙ ሕዝብ ይረግፋል፡፡ በበርካታ ዙሮች የሰለጠነውና ከአማራው አፍ ሳይቀር እየተነጠቀ በተሰበሰበ ግብር የተገዛ ዘመናዊ መሣሪያ በመከላከያና በፌዴራል ስም የታጠቀው የኦሮሞ ጦር በአማራው ክልል ተሰራጭቶ ብዙ ጥፋት ያደርሳል፡፡ ግን አይወጣም፡፡ ያለቀው አልቆ፣ የወደመው ወድሞ በመጨረሻ አማራና አማራውያን ያሸንፋሉ፡፡ እንደነገርኩህ አማራ የሚያሸንፈው በምትሃት ሣይሆን በብልኃት ነው፤ ታየዋለህ፡፡ ተገፍቷላ!!

ግርታን ለማስወገድ ያህል - አማራ፣ አማራ የሆነው አሁንና ተገዶም ነው፡፡ ነፍሱን ለማዳን ሲል ነው አማራ፣ አማራ ለመሆን የተገደደው፡፡ አማራ አማራነቱን ቀደም ሲል ቢያውቅ ኖሮ እዚህ ዕዳ ውስጥ ባልገባ ነበር፡፡ ዘረኝነት መጥፎ በሽታ ነው፡፡ ዘረኝነት ያሰባስባል፤ ሤረኛ ያደርጋል፤ ተንኮለኛና ስግብግብ ያደርጋል፡፡ አማራ የዚህ ደዌ ልክፍተኛ ባለመሆኑና በዘረኝነት መግነጢሳዊ ኃይል ባለመሰባሰቡ ለጠላቶቹ ምቹ ሆነ፡፡ አሁን ግን ዘሩን ከምድር ሊያጠፉት ከአራቱም አቅጣጫ ስለወጠሩት የግዱን ተንጠራርቶ መሣሪያ ጨበጠ፡፡ እናም ከአሁን በኋላ ኒኩሌርና አቶሚክ ቦምብም ይዘህ ብትሄድበት ሞት ጓደኛው እንድትሆን አንዴውኑ ፈርደውበታልና ለማንም አይመለስም፡፡

 ፍርሀትን ፈርቶ ፈርቶ የጨረሰ ሰው በጉብዝናውና በደፋርነቱ እንደማይታማ ሁሉ አማራም ለዘመናት ታግሶም እንበለው አብሮነትንና ኢትዮጵያን ላለማጣት ሲል ሲፈራ ሲቸር ቆይቶ አሁን ላይ በመነሳቱ ከአራት ኪሎ መልስ የሚያቆመው የለም፡፡ ይህን እውነት ማንም ይገንዘብ፡፡ “ወደቁልቁለት ሰው ስታባርር የምታባርረው የዞረ እንደሆነ አቀበቱ ላንተ ይሆናል” የሚባለውን ብሂል በወፍ ዘራሽ ሀብትና ሥልጣን ሰክረው ያደርጉትን ያሳጣቸው ኦሮሙማዎች ቢያውቁት ለነሱም መልካም ይመስለኛል፡፡ ለማንኛውም በድል መባቻ ለመገናኘት ያብቃን፡፡ ግን ስንቶች እንሆን የምንተርፍ ጎበዝ? የተለቀለቀው ዐውድማ መቼስ ልዩ ነው!! ያውጣን ከማለት ሌላ፣ ሌላ ምርጫ የለንም፡፡

አምላክ ሆይ! ኢትዮጵያን በቸርነትህ ጎብኛት፤ ከቀደሙ አገዛዞች ጀምሮ የደረሰብንን ግፍና በደል ቆጥረህ የጨለማውን ዘመን አሳጥርልን፤ የታዘዘብንን መቅሰፍትም አብርደህ ወርቃማውን ዘመን ነገ ዛሬ ሳትል አሁኑኑ ስጠን፡፡ ደግሞም እንደክፋታችንና እንደኃጢኣታችን መጠን ሣይሆን እንደምሕረትህ ብዛት ይሁንልን፡፡ አሜን፡፡

Ethiopian Semay

No comments: