ትጥቅ
መፍታት ያስከተለው መዘዝ ከማይ ካድራ ሊወሰድ የሚገባው ትምህርት
ጌታቸው
ረዳ
Ethiopian
Semay
4/11/23
በዚህ መልኩ በዚህ ምስክርነት የምታደምጡት በአማራው ላይ የተፈጸመ የዘር ጭፍጨፋ ሳያንስ፤ ዛሬ እንደ ወላጅ አባቱ የትግሬ ወያኔ ቡድን ኦሮሙማው መንግሥት መሪው አብይ አሕመድ አማራዎች በተለየ ሁኔታ ለምን ትጥቃቸው እንዲፈቱ ፈለገ? የሚለው ጥያቄ፤ መልሱ እንደገና የዘር ማጥፋት እንዲፈጸምበት ስለፈለገ ያቀነባበረው ሴራ ነው።
ይህንን ምስክርነት ስታደምጡ የወልቃይት አማራዎች ትጥቅ እንዲፈቱ ከተደረጉ
በኋላ ካሁን በፊት ወልቃይትና ማይካድራ ውስጥ አማራዎች ላይ ምን እንደተፈጸም ይህ ምስክርነት
አሁን ላላው ማስጠንቀቂያ ደወል ነው በሚል በማስረጃ ለማቅረብ የፈለግኩበት ምክንያት የዓይን ምስክርና የሰቆቃው ተጠቂ እየነገረን
ያለው አማራዎች ብትር (ሽመል) እንኳ እንዳይዙ ተደርጎ 30 አመት ሙሉ “ትጥቅ ከፈቱ በኋላ”
ምን እንደደረሰባቸው ለማሳየት ነው። አማራው ተለይቶ ትጥቅ እንዲፈታ ማድረግና ለዚህ ተባባሪ መሆን በራስ ላይ መፍረድ ነው ስል
የነበረውም ለዚህ ነው። አለዘመናት ቀስቅሰን አልነሳም ያለንን የአምሓራ ሕዝቡ ዛሬ ቀስ እያለ እየተረዳው ሴራው ግልጽ እየሆነለት
የመጣ ይመስለኛል።
እስኪ በዚህ ልደምድም፡
የዓይን ምስክር ከማይካድራ እስከ አብርሃ ጂራ
<< ሁሉም ጎረቤቱን ገድሏል፡ ሚሰት ባልዋን ገድላለች።በሚስቱ
በገጀራ ተመትቶ ሳይሞት የደረሰ ታካሚም አለ። ከሞቱት ውስጥ 12 የሚሆኑት ነፍሰጡር እናቶች ናቸው። ማይካድራና አካባቢው ይኖሩ
የነበሩ አማራዎች በሙሉ በሚባል ሁኔታ እዛው ነዋሪ በነበሩ ጎረቤቶቻቸው ታድነው ተገድለዋል። ከ500 በላይ ያልታጠቁ አማራዎች በጎረቤቶቻቸው
ተጨፍጭፈዋል።>
ከዓይን ምስክሮች የተጠናቀረ ዘገባ።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay
No comments:
Post a Comment