Sunday, April 2, 2023

ሱሬ መፍታትን እንደ መግባባት የሚያዩ ፖቲከኞች ዛሬም ቀጥለውበታል፤ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 4/2/23

 

ሱሬ መፍታትን እንደ መግባባት የሚያዩ ፖቲከኞች ዛሬም ቀጥለውበታል፤

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 4/2/23

ሱሬ መፍታት በፖለቲካ ውስጥ መጥፎ ቃል ነው። ፈረንጆቹ “ኮምፕረማይዝ” ይሉታል። ያገራችን ፖለቲከኞች “ሰጥቶ መቀበል/መግባባት” በሚል ይተረጉሙትና “ቀበቷቸው ፈትተው” አገራዊ እሴቶችን ለሴረኞች በማስረክብ ክርክራቸው ያጠናቅቁና “ሰላም” አሰፈንን ይላሉ።

በዚህ ቀበቶ አስፈቺ “አገራዊ መስማማት” (እስካሁን ድረስ ያነው) መጨረሻ አገሪቷ ባሕር በርዋን፤ ድምበሮችዋን፤ እና ሃገራዊ ሉአላዊነትዋን አስረክባ “በነገድ ፤በቋንቋ” ተሸንሽና አሁን አንደምናያት ሁኔታ መልህቋን አስፈትተው ያለመሪ ትንቀዋለላለች ማለት ነው። 

በቅርቡ የፖለቲካ ሚዛን አላቸው የሚባሉ ጥቂት ምሁራን ስለ ብሔርና ኢትዮጵያዊ ብሔረተኛነት ትርጉም ፍለጋ ሲዳክሩ እራሳቸውን ሲያደክሙ ሰምቻቸው ገርሞኛል። ብሔር የሚለው ቃል አከራካሪ ሳይሆን ለምን አከራካሪ እንደሆነባቸው ይገርማል። ቃሉ ግዕዝ ነው፡ አገር ማለት ነው። ከሆነ ለምንድነው ስለ ብሔር ትርጉም አከራካሪ የሚሆንባቸው። አስገራሚው ደግሞኢትዮጵያዊ ብሔረተኛንእንቃወማለን ሲሉ ይደመጣሉ። ኢትዮጵያዊ ብሔረተኛ ማለትአገራዊማለት ነው። ይህ ለመረዳት እንዴት ዳገት ይሆናል።

ብሔረተኛእናአገራዊ ብሔረተኛ” (ኢትዮጵያዊ ብሔረተኛ) ሁለቱም ጽንፈኞች ናቸው እያሉ ይከራከራሉ/ይኮንናሉ። ግልጽ ለማድረግየኦሮሞ ብሔረተኞችና፤የትግራይ ብሔረተኞችብሔረተኞች ተብለው ሲጠሩ ከኢትዮጵያዊያን ብሔረተኞች ትርጉም (ቡድንነታቸውም ሆነ ሰልፋቸው) ለየብቻ ነው። ሁለቱም ጽንፈኞች ሳይሆኑ የመጀመሪያዎቹ ናቸው ጽንፈኞች። ለምን? ኢትዮጵያዊ ብሔረተኛ ከሆነ ስለ አገሩ ስለ ኢትዮጵያ ነው እያወራ እና እየተከራከረ ያለውሃገረኛ/ሃገራዊ/ ማለት ነው። ሌላኛው ግን ስለ ትግራይ አገር (ትግራዋይነት)፤ስለ ኦሮሞ አገርነት (አሮሙማ/ኦሮሚያ) እንደ አገርስለሆነ ባንድ አገር ውስጥ ብዙ አገሮች እንዳሉ ስለሚከራከር አገር አፍራሽ በመሆናቸውጽንፈኞች ነው

 ብሔረተኛ ማለት ስለ አገሩ የቆመ ማለት ነው። ብሔረተኛ ማለት አገርኛ ማለት ነው። አገራዊ ማለት ነው። በየትኛው አገር ነው እየተጠራ ያለው ስንልብሔረተኛከሚለው ቃል በፊት የሚነበበውስምለወሳኝ ትርጉም ግልጽ ያደርጋል ማለት ነው። ታዲያ ብዙዎቹ ፖለቲከኞቻችን እነዚያ ጽንፈኞች በፈጠሩት የተሳሳተ የግዕዝ ቃል አጠቃቀምና ከተሳሳተ ትርጉም ፈጣሪዎች ጋር ለምን ለመስማማት እንደፈለጉ አልገባኝም?

የነገድ ብሔረተኞች በግዕዝ ኢትዮጵያዊ ስያሜነገድ አይደለንም፤ ጎሳ አይደለንም፤ ህዳጣን አይደለንምነገር ግን እኛብሔርነን ካሉ አገራዊያን ፖለቲከኞች ማወቅ ያለባቸው እነዚህ ጽንፈኞች እየነገሩን ያለውአገርነን እና እንደ አገር ጥሩን ነው የሚሉት። ይህ ከሆነ ፖሊሲያቸው ከግባቸው ጋር ሲነጻጻርሃገረ ትግራይ” “ሃገረ ኤርትራ” “ኦሮሙያማለት ከኢትዮጵያ የተለዩ ራሳቸው የለዩ አገሮች ናቸው ማለት ነው። 

በሚገርም ሁኔታ ነገዶችንእያንዳንዱ ብሔርእያሉ የሚጠርዋቸው ኢትዮጵያዉያን ፖለቲከኞች አድመጫለሁ። ለዚህ ነው ኦሮሞዎቹ ተሽቀዳድመው ሰው እንደሚለማመደው ስላወቁ ፤በታሪክ የማይታወቅኦሮሚያብለው ስያሜ ሰይመው ዛሬ ለምደነዋል። ኢትዮጵያዊያን ብሔረተኞች ግን አልገባቸውም። ዛሬምየኦሮሞ ብሔር የትግሬ ብሔር፤ የአማራ ብሔር፤ ብሔረሰብ፤ ሕዝቦች” …. እያሉ በቀደዱላቸው ቦዮች ሲነጉዱ እያየን ነው። ማወቅ ያለብን፤ብሔረሰብየሚል ቃል ትክክልኛ አጠራር ነው ግን ለነገዶቹ/ለጎሳዎቹ/ኤትኒክ/ “በብሔርና አና በሕዝቦችመጥራት ግን ጭራሽ መላቅጡ ያጣ 70ዎቹ ተማሪዎች የፈለሰፉት የጨቅላ ቃላቶች ትርጉም ነው

 “ሃገራዊያንስንልኢትዮጵያዊያን ብሔረተኞችማለት ነው። ስለ ኢትዮጵያ ነው እያወራን ያለነው ማለት ነው። እነሱ ግን በምናባቸው ስለሚስሉዋቸው አገራቸውትግራይና ኦሮሞነው ማለት ነው።ኢትዮጵያዊ ብሔረተኛነት/ ኢትዮጵያዊ ሃገራዊነት/ ለጽንፈኞች እንደጠላት ያዩታል። ምክንያቱም እነሱብሔር” (አገር) ነን ስለሚሉ። 30 አመት በዚህ አጠራር እየተጠሩ አገሪቷን ጭለማ ገደል አስገብተዋታል። በውሸት ተነስቶተገፋሁባለ ቁጥርአዎ ተገፍተሃልእያልን ፈረሱና ሜዳው እንደፈለገው እንዲጋልብ መፍቀድ እንግዲህ በቃችሁ ማለት አለብን። ጽንፈኞች ያሰመሩት መሰመር የለም። ልቅ ናቸው። አይጠግቡም፤ ሁሉም የኔ ያም የኔ (ትግሬዎችና ኦሮሞ ፖለቲከኞችን ጥሩ ምሳሌ ናቸው)

ለዚህ ተሞዳሟጅ ደግሞ ልደቱ አያሌው ግምባር ቀደም ነው። ጥርጣሬ እንኳ ቢኖረኝም፤ ልደቱ መልህቁ የለቀቀልቅመሆኑን ያወቅኩት በቅርብ ነው። በቅርቡ ልደቱ አያሌው በዛው ጎሰኞቹ በፈጠሩት ጭቃ ላለመቦጫረቅ ይሞክርና እንደገና እራሱ በዛው ጭቃ ውስጥ ላለመቦጫረቅ ሲጥርብሐረተኞችይልናንኡስ ብሔረተኞች/አናሳ ብሔረተኞችእያለ ምድብ ማውጣት ጀምሯል። የግዕዙ ትርጉም ብሔር ማለት አገር ማለት ከሆነአገር፤ንኡስ አገር፤አናሳ አገርወደ እሚል የልደቱ አዳዲስ የትናንሽ አገሮች ትርጉም አስገብቶናል ማለት ነው። ይህ ደግሞ ለገበያ ቀርቦ አንዱ ተንታኝ ተስማምቶት ተቀብየዋለሁ ሲል ሰምቼውወየ ጉድአልኩኝ። መከራችን መቆም ያልቻለው ሱሪ አስፈቺዎች እንደአሜባእየተራቡ መሄዳቸው እጅግ የሚያሰጋ ነው።

የትግራይ ወይንም የኦሮሞ….. ብሔረተኞች ነገዳቸው በነገድ፤በጎሳ፤በህዳጣን ላለመጠራት መርጠውብሔርንነ ስላሉበመግባባትስም የግድሱሪ ፈትተህእነሱ በመፈጠሩት አዲስ ትርጉም መጓዝ አይጠበቅባችሁም። በመግባባት ስም እስካሁን ድረስ ቀይ መስመር ታልፎ ያጣናቸው ጉዳዮች እዚህአርማጌዶንድረስ ያደረሰን በመግባባት ስም ነው። (ኮምፐረማይዝ) እየተባለ መጣስ የሌለባቸው እሴቶች በመጣሳቸው ነው። አገርን ለማዳን ቀይ መስምር እንዲጣሱ በመስማማት ወይንም ቸል ማለት አገር አያድንም። አንድ ጊዜ የጎሳ ፖለቲካ ለማስወገድ ብንሞክር ጠርነት ውስጥ እንገባለን ከዚያ እንጠንቀቅ ይላሉ እነዚህ ቀበቶ አስፈቺዎች። ልደቱ አንዲህ ይላል፡ፖለቲካማለትኮምፕረማይዝማለት ነው ከሆነየማትፈልገውን ነገር መቀበልማለት ነውይላል ቀበቶ አስፈቺው ልደቱ አያሌው።

 በዲሞክራሲ ስምሁሉም ይደመጥ፡ የሚለው እጅግ አስገራሚ ማጃጃያ ነው። << አገር ለመገንጠልም ከፈለገ ለመገንጠል ወኪሉን ፓርላማ ውስጥ አስገብቶ አገር መመስረት ይችላል>> ብሎ አብይ አሕመድ እንዳለው ሁሉ፤ እነ ልደቱም የተረገዘ ህጻን ከዕርጉዝ ሴት ሆድ ቀድዶ የሰው ሥጋ የሚበላ ጸረ አማራ፤ ግብረሰዶማዊው የኦነግ (ሸኔ በሚል የሚጠራው የመጠሪያ ሽፋን) ስለሚባለው ሽብርተኛ ቡድን ልደቱ አያሌው ተጠይቆ እንዲህ ይላልሽብርተኛብየ አልጠራውም፤ ወያኔም ሽብረተኛ አይደለም የፈረለጋቸው አጀንዳ ማራመድ መፈቀድ አለብን’’ በማለት በዲሞክራሲና በመቻቻል ስም “30 አመት የፈታነው ሱሪያችንዛሬም እነ ልደቱበመግባባት ስምለዳግም ሱሪ መፍታት እየሰበኩ ነው።

ብረት ታጥቆ አገር የሚያፈርሰው አብይ አሕመድም ሆነ ኦነግ በሰላማዊ ትግል እንጂ ሃይልን ብረትን በብረት ሰንዝሮ ለድርደር ማቅርብ አገርን ማስቀጠል አይቻልም በማለት እነ ልደቱና መሰልሰላማዊያንስብከት ከጀመሩ 30 አመት ሆኗቸዋል።

በዚህ ሰላማዊ ትግል ስም ተታልለው ሃይለኛን በሃይል ላለመመከት ፈዝዘው አዲስ አበባ እና ባሕርዳር ውስጥ በዱላ እየተቀጠቀጡየረዳት ያለህ ይጮሃሉ አማራው አዲስ አበባ ገብቶ እንዳይታከምና እንዳይመጣ ባኦሮሙማው መንግሥት ታግዷል። ቀይ መስመሩ ተጥሷል። ባለፈው የዘመነ ነገሥታትም ሆኑ የዘመነ ወታደራዊ ግ ትግሉ በጨቋኝና ተጨቋኝ ብሔር አልነበረም። እውነታነት የለውም። ዛሬ ግን አለ። አማራው ተደፍጥጧል። ጋሞው ተደፍጥጧል። ጉራጌም እንዲሁ።

ያለፈው ካልተመለከትን መጪው አያስኬደንም።አገራዊ እሴቶች የሚባሉ በቀይ ምስመር የተሰመሩ መጣስ የሌላባቸው አገራዊ አጀታዎች ባሕርን ያክል አስነጥቆናል። 30 አመት በመግባባትናሦሰትኛ መንገድበሚል ገዢዎችን የሚያሞግስ (ልደቱ መለስ ሲሞት የተናገረውን ባለፈው ጠቅሻለሁ) ቀበቶ አስፈቺ መንገድ ከተከትል 30 አመት ሆኖናል።

 ዋናው ችግራችን ሁለት ነገሮች በማጣታችን ነው።

1) እንደ ጽንፈኞቹ እነሱን የሚመክት አገራዊ ሽምቅ ተዋጊ ባለመኖሩ፤

2) ኢትዮጵያዊ/ሃገራዊ ብሔረተኛ መሪ በማጣታችን

ይህን በማጣታችን፡ ቀይ መስመር እንዲጣስ ያደረጉ ወንጀለኛ በለሥልጣናትን ዛሬም እየደጋጋሙ፤ 30 አመት በሚሊዮኖች ነብሳት እያሳለቁ እርስ በርስ በመተቃቀፍ አንደኛቸውም ሳይታሰሩ ዛሬም እየገዙን ነው።ተሾመ ቶጋየሰላም ኮሚሽነር ሆኖ ሲመጣ፤ ሬድዋን ሁሴን ስለ ኢትዮጵያዊነት ተደራዳሪ ሲሆን ማየት መሪ ማጣታችን ነው። እነዚህ ናቸው ሁለቱ ወሳኝ ዕጦታችን።

 ለዚህ ነው ጽንፈኞቹ ሥልጣን ላይ ስለቀጠሉ ኢትዮጵያ ብሔረተኛነት እንደ ጨፍላቂ እየታየ በማይገባ ትርጉም ተሰጥቶት፤ ተገፊ እያለ እንደ ገፊ እየታየ፤ ያንን ትርጉም የተሳሰተ ነው ብሎ ከመከራከር ይልቅ በተስፋ ቆራጭነትና ተሞዳማጅነት ባሕሪ ምክንያት እነ ልደቱ አያሌውና መሰሎቹብሔርንኡስ ብሔር”…. ብንል ጽንፈኞቹ ይቀዘቅዙ ይሆን ወይ እያሉ ራሳቸውን አሞኝተው ቀበቶ ለማስፈታት አጠባ ጅመረዋል።

የተለያዩ ፓርቲዎች ፖለቲከኞች ለመደራደር ሲቀርቡ ቀይ መስመር መጣስ የለባቸውም። በተለይ 30 አመት በኋላ!! ኢትዮጵያዊ አገራዊያን የራሳቸው ፓርቲ ፖለቲከኞች ከሌላኛው ወገን ጋር መስማማት ቢጀምሩ መደረራደሪያ ነጥባቸው በጥርጣሬ መመልከታቸው ያለ ነው። 30አመት ሙሉ ተሞኝተናል እና!!!

የአሜሪካን መራጮች ስንመለከት ዛሬ ኮንግረስ በአሜሪካ ሕዝብ ዘንድ የሚሰጠውን ደረጃ ስንመለከት፣ ቀይ መስመራቸውን አሳልፎ የሰጠ ተወካያቸው በሚቀጥለው ምርጫ አይመርጡትም።

እኛ ኢትዮጵያዊያን ከሁን ወዲህ ምንም የሚቀረን የለም። ተጎድተናል፤የሚጎድለን ነገር የለም። እኛ መመከት ስንጀምር ብቻችን ሳንሆን ግን ተጎጂዎቹ ጽንፈኞቹም ናቸው። እንደ ሰዎች ስምምነትን እንፈልጋለን፣ ነገር ግን አሁን ባሉት ፖለቲከኞች ስምምነትን የምናየው፣ እንደ ዋሻ ነው የምነያው።

መግባባትን የምንፈልገው ያጣነውን ለማሰመለስና ተጨማሪ ላለመስጠት ነው። ይህ ደግሞ ጥሩ አገራዊ መሪ ያስፈልጋል። ሩዋንዳን የሚያክል አስፈሪ መበላላት የተፈጸመባት አገር ዛሬ ጥሩ መሪ ስላገኘን ለማንኛቸውም አፍሪካ በከፍታ ትታያለች። መሪ ወሳኝ ነው። ችግሩ የኛ ፖለቲከኞች 70 ዎቹ የነበረ ጊዜው ያለፈበት ማርክሳዊራስን መወሰን እስከ መገንጠልዛሬም 21ኛው /ዘመን ይዘውት የነበረው ያልበሰለ እንጭጭ ፖለቲካ አገራችን ጉድጓድ ውስጥ ገብታ እንዳትነሳ ማነቆ የሆኑ የጫካ ሰዎች ሥልጣን ላይ ስላሉ ነው።

አድማሱን ማየት የሚችል በተወዛገበ እይታነት ራሱን የማያምታታ ብርቱ መሪ መሻት አለብን። አሜሪካም ሆነ እስራኤል አንድ የተከበሩበት መንገድ በውይይት ሳይሆን በብረት ነው። ሰላም ያልገዛው ነጻነት ሃይል ይገዛዋል። ሱሬ መፍታት በፖለቲካ ውስጥ መጥፎ ቃል ነው:: ዛሬም ጽንፈኞችን ወደ መሃል ለመሳብና ለማለሳለስ በሚል ቀበቶን የሚያስፈታ 30 አመት ከንቱ መሞዳሞድ ሱሬን ፈትቶ እንደ መግባባት የሚያዩ ፖቲከኞችን ባይነ ቁራኛ ማየት አለብን። ሽምቅ ተዋጊዎች ያስፈልጉናል!!

የሽምቅ ተዋጊዎችህን ከጀርባ መያዝ አስፈላጊነቱ ለምን ቢሉ የኦሮሞና ዩትግራይ ጽንፈኞች ጉልበት እስካላቸው ድረስ አንድ ኢንች ስትሰጣቸው ስንዝር ይጠይቃሉ ከስንዝር ወደ ክንድ ከዚያም የፈለገ ብትሰጣቸውም ምንም የሚረኩበት ማቆሚያ የላቸውም። መለሳለስ፤መሞዳሞድ ማቆሚያው ዛሬ ነው!

አመሰግናለሁ!

ጌታቸው ረዳ

 

 

No comments: