ጌታቸው ረዳ
ቃለ መጠይቅ ( Ethiopian Semay)
ለማስታወሻዎ!
1-1-23
ይህ ቃለ መጠይቅ የቆየ ነው። ቃለ መጠይቁ ያደረግኩት የኢትዮጵያ ራዲዮ ከሚባለው ሲዊድን አገር ሲኖር ከነበረው ነብስ ይማር “ቃለ መረዋ” እያልኩ ስጠራው የነበረው ሸጋው ወጣት ከሟቹ ጋዜጠኛ ወርቁ ጋር ነበር። የጋዜጠኛው ሞት ከሰማሁ የቆየ ቢሆንም በዚህ አጋጣሚ የተሰማኝን እጅግ እጅግ ሐዘን ለቤተሰቡ እየገለጽኩ አምላክ በእጅ ይቀበልህ፡ እያልኩ እነሆ ለትውስታ ያደረግኩትን ቀለ መጠይቅ በርካታ ጠቃሚ ምስጢሮችን ስለምታገኙበት እነሆ። ጋዜጠኛው በአካል ሳላውቀው በመለየቱ እጅግ ነው ያዘንኩት። የድምጽ ቅጂ በጽሑፍ ላቀርብላችሁ የፈለግኩት ምክንያት ሰነዶች ስላሉት እናንተም ለመጥቀስ እንዲመቻችሁ በሚል ነው። በዚህ ሰነድ ላይ የቀረቡ አንዳንድ ግለሰቦች ስም በወቅቱ የነበረው ሁኔታ የሚገልጽ ሲሆን የተጠቀሱት ሰዎች ዛሬ ወደ መልካም ስራ በመግባት እኔ ስወተውተው የነበረው አጀንዳ በመስራት ላይ ስላሉ ያንን ረስቼ ዛሬ በተሰማሩበት በምሁራዊ ትግል ስራ የኮራሁባቸው መሆኑን ለመግለጽ እሻለሁ። ሰዎቹም ለመጥቅስ ያህል ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ እና ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻ ናቸው። ፌስቡክ ለማንበብ ከተቸገራችሁ Ethiopian Semay ላይ በጎላ ፊደል ስለተለጠፈ እዛው ማንበብ ትችላላችሁ።
ጋዜጠኛ ወርቁ
1 በቅርቡ የትግራይ ብሔርተኝነት በአማራ ላይ ስላላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው የሚል መፅሐፍ ለኢትዮጵያውያን ለንባብ አበርክተዋል። በየጊዜው እንደሚያቀርቧቸው ፅሑፎች በማስረጃ ላይ የተመረኰዘ የምርምር ውጤት በመፅሐፍ መልክ አቅርበዋል። ለመፅሐፍዎ ርዕስ ያደረጉትን ብርቱ ጉዳይ ሊገልፁ ጥላቻው ዘመናዊነት ያልቀበረው የጨለማ ዘመን የትግራይ መሳፍንቶች የስልጣን እና የጥቅም ሽኩቻ ጋር ተያያዥነት እንዳለው ተንትነዋል። አብዛኛው አማራውም ሆነ ኢትዮጵያዊው የወያኔዎችን የመረረ ጠላትነት አልተረዳውም ነበር። ይህ ለምን ሆነ ይላሉ?
ጌታቸው ረዳ
ጥያቄህ ሁለት ነጥቦችን ይዟል። ሁለቱም በየተራ በዚህ መልክ ልመልስ። የሰው ልጆች ኑሮና አስተሳሰብ ከዘመኑ ጋር አድጓል በሚባልበት ዘመን የትግራይ ብሔረተኞች ከጭለማው ዘመን አስተሳብ አልወጡም። የሚለው እና ዐማራውም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔዎች የመረረ ጥላቻ ለምን አልተረዳውም? የሚሉትን ላብራራ።
ለተያያዢነታቸው ሁለት ግልጽ ነጥቦች አሉ። ሥልጣን ከትግሬዎች እጅ ተነጥቆ በአጼ ምኒሊክ እጅ መግበቱ የተከሰተ ባሕሪ ኣለ ። ያ የተከሰተው ባህሪ “ጥላቻ” ነው። መነሻና መድረሻዎች አሉት። መነሻው “ሥልጣን ተነጠቅን” የሚል ሲሆን “ያነጣጠረው የመድረሻ ዒላማው” ደግሞ “ስልጣን መልሶ ለባለቤቱ ለትግሬዎች እንዲመለስ ትግል ማድረግ” የሚሉ ናቸው ።
እስከ መድረሻው ያለው ርቀት ይዟቸው የሚሄድ ነዳጅ “የጥላቻ” ባህሪ መያዝ ነበረባቸው። ስለዚህ እነዚህ ሁለት ነጥቦች ማለትም ሥልጣን እና ጥላቻ ለዛሬ ወያኔዎች ተያያዥነት የሚያሳዩን አሁንም እነዚህ ሁለት ባህሪዎች ናቸው። የትግራይ መኳንንቶች ንጉሳቸው ዮሐንስን ሲያጡ ሃይላቸው ተዳከመ። በሌላ ጉልበተኛ ተነጠቁ። ሲነጠቁ- “ጥላቻን፤ ንቀትን፤ እና “አንገዛም ባይነትን” አስከተለ።
እዚህ ላይ ‘የአንገዛም ባህሪ’ መሰረቱ “ትዕቢት” ነው። (የበላይነት ስሜት ማለት ነው)። እኛ አስታጣቂዎች እንጂ ታጣቂዎች ስላልነበርን በእጃችን ሲነግሱ የነበሩ አገልጋዮችን ተመልሰን በስራቸው ሆነን አንታዘዝም ነው። “የአንጋሾች ነበርን” ባህሪ (የባላይነት ስሜት) ማለት ነው።
ሌላኛው ጥያቄህ፦ አብዛኛው ዐማራውም ሆነ ኢትዮጵያዊው የወያኔዎችን የመረረ ጠላትነት አልተረዳውም ነበር። ይህ ለምን ሆነ? ነው ያልከኝ።
ይህን ለመረዳት በሰፊው የጻፍኩበትን መጽሐፍ ማንበብ ሰፊውን ግንዛቤ ያስጨብጣል። ሕዝቡ እየጠላው ያለውን ቡድን እንዳይረዳው “ብዙ ተንኮሎች” ተሸርበዋል። አማራን እና ኢትዮጵያን የሚባሉትን እንመልከት።
ሁለቱንም በየራሳቸው ልዘርዝር።
1ኘው ኢትዮጵያ የምንላት አገራችን ስንመለከት የሕዝብ፤ የሰንደቃላማ ፤የሉዓላዊነት፤የታሪክና የባህል ስራ ነች። አከላትዋን የገነቡዋት እነኚህ ናቸው (ኦቶኒሚዋን እና ፊዚኦሎጂዋን ውስጣዊና ውጭአዊ አከላትዋ ከነዚህ ጋር የተቆራኘው ሐረጋዊ ትብትብ) የገነቡት እነዚህ ናቸው)። እነዚህ የአከላትዋ ክፍሎች ናቸው በትግራይ ብሄረተኞች የማጥቃት ስልት ከፍተኛ ብትር የደረሰባቸው።
ሕዝባችን የሚሉትን ማሕበረሰብ “አማራ” በተባለ ነገድ ‘ምክንያት’ የትግራይ ሕዝብ ለዘመናት ተጨቁኖ ለድህነትና ለበሽታ የዳረገው አማራ ነው ብለው ወንጅለውታል። በዛው ነገድ ላይ ትግሬዎች ሁሉ ጥርሳቸው እንዲነክሱበት ከፍተኛ ቅስቀሳ ተካዷሂል። የውጭ ሃይሎች እና አማራ ያልሆኑ ነገዶችን ወደ ጎን አስቀምጠን፡ -- በሚገርም እንቆቁልሽ ለዚህ ሴራ መሪ ተዋናይ ሆነው “አማራውን “በፊውዳልነት’፤ “በገዢ መደብነት” እና “በጨቋኝነት” መድበው የከሰሱትና የኮነኑት” ከራሱ አብራክ የወጡት እነ ‘ዋለልኝ መኮንን’ የመሳሰሉት ናቸው። የሚገርም ነው!! አይደለም እንዴ? በአማራ ከመጨቆን ይልቅ መገንጠል ይሻላል ብሎ ዋለልኝ ጽፋል።
ፕሮፌሰር እንደርያስ እሸቴ፤ የእነ ዋለልኝ መኮንን እና የበርካቶቹ አማራዎች ሕሊና በማጠብ፤ ኢትዮጵያ የ100 አመት ዕድሜ ያላት፤ በሚኒሊክ ጭቃ እና ድንጋይ “ተጠፍጥፋ” የተሰራች “ኢምፓየር” ነች፤ አማራ የገነባች አገር ነች… እያሉ አፍራሽ ስራዎችን ከውጭ ሃይሎች ቅስቀሳ ተቀብለው ለዛሬ ሰበብ ሆነዋል። ሰንደቃላማዋም በወያኔ ዘመን “የአማራ” ነች፡የኦርቶዶክሶች ነች፤ የጠላት ባንዴራ ነች ሲሉ አውግዘዋታል። የሰንደቃላማዋን ክብር ለማውረድ በወያኔ ትግሬዎች የተመራው ሴራ ለወያኔዎች ያደሩ በርካታ “አማሮችም” በሴራው ላይ ተካፍለውበታል። አሁንም እንቆቅልሹ ለመፍታት የሚያስቸግረው ይኼ ነው።
ከዚያ በላይ የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግራ ዘመም ርዕዮት ሲያስፋፉት የነበሩትና በከፍተኛ አመራር እና እንቅስቃሴ ከፊት ሆኖው ሴራውን ሲያካሂዱ የነበሩት ትግሬዎችና ኤርትራኖች ናቸው። መጽሄቶችን የሚመሩት ብዙዎቹ ‘ትግሬዎች፤ ነበሩ። በዚያ ስም በመንቀሳቀስ የኢትዮጵያ ታሪክ፤ ባህል እያንኳሰሱ ወያኔዎች ሲገቡ በሰንደቃላማ ላይ የሰሩት ወንጀል በመጽሐፌ በሰፊው ከነማስረጃው ተዘግቧል። ያንን መመልከት ነው። የትግራይ ብሔረተኞች የጻፏቸው መጽሐፍቶች “ደ/ር አሰፋ ነጋሽ” ሲነግረኝ ቁጥሩ አሁን በትክክል ባላስታውሰውም “ካልተሳሳትኩ” ከ57 በላይ እንደሆኑ እና ሁሉም በእጁ ይገኛሉ (የኔን ሳይጨምር)። ሁሉም በጸረ አማራ፤ በጸረ ሚኒሊክ፤ በጸረ ኢትዮጵያነት የተጻፉ የጥላቻ እና የትዕቢት መጽሐፍቶች እንደሆኑ ይገልጻል። ባጣቃላይ “ባሕሉም” ምኑም “አዲስ ትውልድና አዲስ ባህል” እየፈጠሩ ጎዳናው፤ ወንዙ፤ከተማው፤ሁሉ በታጋዮቻቸው ስም በመሰየም የነበረው ታሪክና መጠሪያ ደምስሰውታል።
ለምሳሌ የፖሊሶችን የማዕርግ መጠሪያ ስትመለከቱ (መጽሐፌ ላይ በሰፊው ገልጫለሁ) አማርኛን እና የአማራ ጥላቻቸውን ለመግለጽ “አስር አለቃ፤አምሳለቃ፤መቶ አለቃ፤ሻምበል፤ሻለቃ…..” የሚል ማዕረግ ሳጅን ፤ ኢነስፔከተር፤ ሱፕረ ኢንስፔክተር፤ ኮማንደር፤ ኮሚሽነር……ወዘተ” እያሉ በቅኝ ግዛት እንደተያዙት የኬኒያ እና የናይጄሪያ ፖሊሶች መጠሪያ ማዕረግ ሰይመዋቸዋል።
ሕዝብን ለማገልገል (ኢትዩጵያዊያንን ለማገልግል ) የተቀጠሩ ፖሊሶች ስማቸውም በደረታቸው ላይ የሚነበበው በአማርኛ ሳይሆን “በእንግሊዝኛ” ነው የተጻፈው። ይህ ለምን ሆነ ስንል “አማርኛ እና አማራን ከምድረ ኢትዮጵያ ላማጥፋት” የተወጠነ ከታላቁ ሴራቸው አንዱ ክፍል ነው። ይህንን ሴራ ተንትኜ ለመጀመሪያ ጊዜ “ታሪክ እንዳይረሳው” በመጽሐፍ ውስጥ አካትቼዋለሁ።
ወያኔዎች ይህ ሁሉ ሴራ በላዩ ላይ ሲሸርቡ ለምን አልተረዳውም? የሚለው ጥያቄህ መልስ ለመመለስ “መጽሐፌ” ብዙ ክፍሎችን በተጠያቂነት ይከሳል። ከጣሊያን ጀምሮ፤ከውጭ ሃይላት ጀምሮ፤ ኤርትራኖችን፤ትግሬዎችን፤አማራዎችን እና ተቃዋሚዎችን ይከሳል። እያንዳንዳቸው ምን ድርሻ እንደነበራቸው በሰፊው ገልጬዋለሁ። በቃለ መጠይቅም አሲምባ በተባለው ፓል ቶክ ተዋናዮቹ እያንዳንዳቸው ያደረጉት ሴራና ድርሻ በዝርዝር ፤በጥልቀት ገልጫለሁ። ስለ “አማራ” ያነሳኸው ነጥብ ልጥቀስ፤ አማራና ኢትዮጵያ
አሁንም የተያያዙ ለጥቃት የተመዘገቡ ናቸው። አማራ በራሱ ላይ ሲሸረብበት ለምን አልነቃም? ለሚለው ‘አማራ’ በራሱ ላይ ሲሸረብበት
በጣት የሚቆጠሩ ጥቂት ሰዎች ካልሆኑ በስተቀር ወያኔን ሊጋፈጡ አልፈለጉም። ፕሮፌሰር አስራት እና ታማኝ በየነ፤ ሻለቃ አድማሴና
በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው ወያኔን ፊት ለፊት ሲጋፈጡት ያየናቸው (የዩኒቨርሲቲውንም ተቃውሞ ሳንረሳ። አገር ውስጥ ማለቴ ነው። የተቀረው
ግራ ገብቶት ይሁን ወይንም “ልጆቻችን ናቸው እስኪ ፋታ እንስጣቸው ፤ወይንም ጠመንጃ ደህና ሁኚ የሃሰባ ፍጭት ተፈቅዷል…..” ወዘተ….ሲሉ
በነበሩት ወይንም አማራ የሚባል የለም ሲሉ በነበሩት በእነ መስፍን ወልደማርያም ሕሊሊናው ተጃጅሎ ይሁን፤ እንቆቅልሹ በማይገባ ሁኔታ
“ግራ ተጋብቶ” ሲሰደብ ፤ሲባረር ዝም ብሎ ተቀብሎታል።
ልሂቁ የመጀመሪያው ብትር ቀማሽ ነበር። ከየመስራ ቤቱ ከየትምህርት ተቋማቱ እየተባረሩ አንዳንዶቹም በጥይት ጎዳና ላይ በጠራራ ጸሃይ እንደ ጅግራ ሲታደኑ ነበር። ቀስ እያለ እንደገና ወያኔዎች በፓርላማ አማራውን በሚያስደነግጥ ሁኔታ እያንኳሰሱ “ሦስቱ ጠላቶች” ብለው በሰየሙዋቸው “አማራ፤ ኦርቶዶክስና ሰንደቃላማን” በቴ/ቪዥን እየተላለፈ ጠላቶች ተብለው ተወነጀሉ።ከጨርቁ (ከሰንደቃላማው) በስተጀርባ ያለው ማን ነው? እያሉ “አማራውን ኦርቶዶክስን” ነው ሲኰንኑት የነበረው።
በትግራይ ብሔረተኞች የተሰነዘረው ‘ጥላቻ’ ብቻ ሳይሆን “ሲረሸንም፤ሲባረርም” ዝም ብሎ ተቀብሎታል። ምክንያቱም - በተደጋጋሚ ከራሱ ልጆች ጀምሮ ፤ የትግራይ ምሁራኖች እና ኦሮሞ ተገንጣዮች ባደረጉት ከፍተኛ ርብርቦሽ ፤ የበርካታ ዜጎች “መርዘኛ ምላስ” በአገሪቱ ታሪክ እና በአማራ ላይ ተሰንዝሯል። እራሱም ቢሆን “ጨቋኝ ነህ” ሲባል የሚያስተምረው፤ የሚከላከልለትና የሚያበረታታው ምሁር ስላጣ “ማመን ጀመረ” ወይንም ዝምታን መረጠ ። በቅርቡ ያነበብኩት እንኳ “አማራው “ኦሮሞውን” “ይቅርታ መጠየቅ አለበት” በማለት “የአማራዎች አብዮት” ከመነሳቱ ከአንድ አመት በፊት ይመስለኛል ‘ዘሓበሻ’ በተባለው ድረገጽና በበርካታ ድረገጾች ላይ ለምሳሌ (“ዶ/ር ዘላለም” በታበለ ‘አማራ ግለሰብ’ “አማራው ኦሮሞውን ይቅርታ መጠየቅ አለበት” ሲል ጽፋል። የተማረውም በዚህ መንገድ ማማን ብቻ ሳይሆን “ይቅርታ እንጠይቅ እያለ መጻፍ ጀምሮ ነበር።
ይህ ሰውየ በተቃዋሚ ጎራ ያለ የሚያውቁት ሰዎች አማራ መሆኑን በሚገባ ገልጸውልኛል። ስለዚህ አማራ እንደ ግፈኛ ማሕበረሰብ እና ገዢ ተደርጎ የተወነጀለ ሕብረተሰብ ስለሆነ፤ የብሔረተኞቹ ክስም ሆነ ጥላቻ ሊረዳው አልቻለም። አንድ ግለሰብ በተደጋጋሚ ሲወገዝ ‘ማመን’ እራሱን መጠራጠር ይጀምራል። በቅርቡ እንኳ ቤንሻንጉል ጉምዝ ላይ በአማራ ኗሪዎች ህይወት ላይ የደረሰ አሰቃቃ ግድያና በሰው የመበላት ሁኔታ ሲደርስ፤ ነገሩን ለማስተባበል እና ለማሳነስ ግምባር ቀደም ሆነው በሞረሽና በኔው ላይ የጉምዝ ሕዝብ ስም ለማጥፋት ነው ሲሉ እየሰደቡን የነበሩ “አሲምባ ድረገጽ አዘጋጆችና የኢሕአፓ” ጀሌዎች ናቸው። እስከዚህ ድረስ ነው። ዛሬም ዘመቻው እንዳለ ነው። እነዚህ ደግሞ አንዳንዶቹ በነገዳቸው “አማራዎች” እንደሆኑ የሚያውቁዋቸው ሰዎች ነግረውኛል።
ታስታውሱ እንደሆነ፤ አንድ ምስኪን ገበሬ “በጉን” ገበያ ወስዶ ለመሸጥ ተሸክሞ ሲሄድ፤ መንገድ ላይ ያጋጣመውን ምሳሌ ሲያትል የሚኖሮው ወዳጄ ደራሲ “አቶ አማረ ቢሻው” “የሁለት ሺሕ ዘመን ውጣ ውረድ በኢትዮጵያ” በሚለው መጽሃፉ ውስጥ የጠቀሰውን ታስታውሳላችሁ። ሦስት ሌቦች፤ መንገድ ላይ እየጠበቁ ገበሬው የተሸከመውን በግ “እንዴት ውሻ ትሸከመህ ወደ ገበያ ለመሸጥ ትሄዳለህ?” እያሉ በተራራቀ ርቀት ሆነው መንገድ ላይ እየጠበቁ ሲያሞኙት ሦስተኛው ጋር ሲደርስ “የገዛ በጉን የተሸከምኩት እውነትም ውሻ ነው እንዴ?” ብሎ የተሸከመውን የገዛ በጉን አውርዶ ትቶላቸው ወደ ቤቱ መመለሱና የሌቦቹ ሲሳይ እንደሆነ ገልጾልናል። አማራውም ባልተናነነሰ መንገድ እንዲያ ሆኖ ነው የተሸወደው።
እውነትም ጨቋኝ ነበርኩኝ እንዴ? ገዢ ነበርኩ እንዴ? ማለት ጀመረ። ከተማሪው አብዮት ጀምሮ ለረዢም ዘመን ተደጋጋሚ የሆነ ፕሮፓጋንዳ ሲካሄድበት “ገዢ ነህ” ነህ “ፊውዳል” ነህ፤ “የመሬት ከበርቴ ነህ፤”ጡት “ቆራጭ ነህ” እያሉ አደነዘዙት ።
ሳይኪያስትሪስቱ እና የሕክምና ምሁር ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ የነገረን ነገር አለ። “ተደጋጋሚ ቅስቀሳ ሲደረግበት አንድ ሰው እራሱን ወደ መጠራጠር ይገባል” ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው። አንድ ሰው “እባብ ረገጥክ ሲሉት ‘ባያየውም በድንጋጤ ይዘላል”፤ የተባለውን ያለ ምንም ጥያቄ ይቀበላል። ጥርጣሬ ውስጥ ስለሚገባ መሮጥ ይጀምራል ወይንም ደንግጦ ይዘልላል። ያምናል። አይደለም እንዴ? በተለይ ወጣቶቹ የድሮን ኢትዮጵያ ስለማያውቋት ይህ የነፕሮቻስካ፤ የነ ጣሊያኖች፤ የትግሬዎች እና የነ ዋለልኝን ጸረ አማራና የእስከ መገንጠል ሴራ አምኖ ተቀብሎት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሴራው ሳይረዳው የመቆየቱ ምክንያት አንዱ ይህ ነው። ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነች ተብሎ ተደጋጋሞ ሲነገር፤ “ተቀባይ አገኘ” እስካሁን ድረስ የሚያምኑ ሰዎች አሉ (እንደ ዱሮ ባይሆንም) ወያኔ ተስፋየ ሃቢሶ የተበላ ወላይታ ወደ ኤርትራ ልኮ በአማራ ስም ኤርትራኖችን እስከ ከረን ድረስ እየተኬደ ይቅርታ እንዲጠይቅ ተደርጓል። በጣም አስገራሚ ነው።
አማራና የኢትዮጵያ ሕዝብ በወያኔ ትግሬዎች የተሸረበበትን ሴራ ሳይረዳው መቆየቱ ዝርዝር ምክንያቶቹ መጽሐፉን አግኝቶ ማንበብ ነው። ተቃዋሚው አማራ እራሱን እንዳይከላከል እንዳይነቃ አፍነው የያዙት ከወያኔ ቀጥሎ ቀዳሚ የውዥምብሩ ተጠያቂዎች ተቃዋሚዎች ናቸው።
አንድ ነገር ልበል እና እዚህ ላቁም።
ታስታውሳለህ “ቪዥን ኢትዮጵያ” የሚባል? በግንቦት 7፤ በጌታቸው በጋሻው (ዶ/ር ዜሮ የምለው ሰውየ) (ጌታቸው በጋሻው ማለት በትውልድ አርባ ምንጭ ያደገ “አማራ” ድሮ ኢሕአፓ የነበረ፤ ዛሬ ደግሞ ስለ ኦነግ ጥብቅና ቆሞ “ኦነግ ለግንጣለ ጠይቆም ቀስቅሶም ኣያውቅም፤ ኢትዮጵያዊነቱም ክዶ ኣያውቅም ” በማለት ይፋ ጥብቅና ሲቆም የነበረ አጉል የኦነግ “የኦሮሚያ ኬኛ” ቲፎዞ) እና የደርግ ባለሥልጣን የነበረው ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ በመሳሰሉ፤ እነ ሻለቃ ዳዊት ‘ዓሰብ ዓሰብ’ አትበሉ፤ በ “ዩ ኤን” ያለቀለት ጉዳይ ነው ፤ መብት የላችሁም፤ እንዳትጠይቁ “ኢሳያስ ኢትዮጵያዊነቱን አልተወም…” እያሉ ከግንቦት 7 ጋዜጠኛ ኢሳት ላይ ከሲሳይ አገና ጋር ሆኖ በቴ/ቢዥን ማሰራጫ ጣቢያ ቀርቦ ሕዝብን በማጃጃል ስራ የተጠመዱ በኢሳያስ አፈወርቂ አለቅላቂ ከሃዲ ግለሰቦች የተሞላ ድርጅት ነው ይህ ቪዥን ኢትዮጵያ የሚባለው።
ይህ ስብስብና መድረክ ኢሳትና እነ ንአምን ዘለቀ ለሻዕቢያ የሚቆሙለት መናሃርያ መድረክ ነው። ይህ ድረጅት በአማራ ላይ ያደረገው ሴራ ልግለጽልህ። ልክ ወያኔ በሽግግሩ ጊዜ አማራውን እንዳገለለው ይህ ሴራም በቪዥን ኢትዮጵያ በሚያስደነግጥ ሁኔታ በግልጽ ሳይሸማቀቁ የወያኔ ስራ ደግመውታል። አማራ ወደ ማሕበራቸው አባልነት አንዳይገባ ምን እንዳደረጉ ልንገርህ።
“የአማራ” ተወካይ ወይንም ‘አማራ’ የሚባል ‘ድርጅት’ እንዳይሰተፍ የተደረገበት ሴራ ነበር። ዓፋሮች ኦሮሞዎች ሲዳማዎች….. ወዘተ..አባሎች ሆነው በየአዳራሹ ተሰብስበው ጉዳያቸው ለሕዝብ ሲቀሰቅሱ፤ አማራው ባለመጋበዙ ምክንያት ፤ ቪዥን ኢትዮጵያ ላይ ብዙ ሰዎች ሲጮሁበት፤ መልስ ሳይሰጥ ሲቀር፤ የሞረሹ አቶ ተክሌ የሻው” በዚህ ጉዳይ የሚያውቁት ካለ ይንገሩን ብሎ “ሲቪሊቲ” በሚባል ፓልቶክ ጋብዞአቸው ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ ይላሉ። {{ “ጥሪ እንደደረሰኝ፤ እሺ ብየ ስጠብቅ ፤ ጠፉብኝ/ዝም አሉ። በኋላ ሻለቃ ዳዊት ደወለና እኔም ምነው ጠፋህ? ስለው፡ እሱም “ኣይ እኔ አንድ ነገር ገጥሞኝ ነው።” አለኝ”፡ ምን ገጠመህ? ስለው “አማራን አናስተናግድም፤ በተለይ ሞረሹ ሊቀመንበር “ምጽአተ አማራ” የሚለው መጽሐፍ ጽፎ “ኦነጎችን” በጸረ አማራነት ስለወነጀላቸው፤ እንዲቀርብ አንስማማም ብለው ነው፡ በዚህ ነው የጠፋሁት እና ይቅርታ” ብሎኝ፤ “ኦንግን የሚቃወም እና የሚከስ አማራ የሚባል ድርጅት የማሕበሩ አባል እንዲሆን አይፈቀድም አሉኝ።}} ሲሉ ነግረውናል።
እዚህ ላይ ተቃዋሚው አማራውንም ከወያኔ ባልተናነሰ ምን ያህል በጠላትነት ጥርሳቸው ውስጥ እንደገባ መገንዘብ ይኖርብናል። በጣም ቅጥረኛ ፤ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ ከወያኔ ያልተናነሰ ከጠላት ጋር የሚሽኮረመም ከጠላት ጋር የሚተኛ ተቃዋሚ ነው “አማራ” ጠላቱን “ለይቶ እንዳያውቅ” ከሚያደርጉት ተጨማሪ እንቅፋቶች እና ርብርቦሽ አንዱ ይህ ሴራ ነው።
ጨርሻለሁ!!!!!!
ጋዜጠኛ ውርቁ፡
ወያኔ ለዘረጋው ዘረኛ አገዛዝ በከፍተኛ ደረጃ የተጠቀመበት ፀረ-ዐማራ ቅስቀሳን እና የዘር ስሜት ማጠናከር ነው። በዘር ላይ የተመሰረተ ጥላቻን ማስፋፋት ነው። የወያኔ ዘረኝነት በሃገራችን ታይቶ የማይታወቅ ርዕዮተዓለማዊ ልባስ አግኝቷል።
የመስራች የወያኔዎች ወላጆች ከአለፉም በኋላ የዛሬው ትውልድ ይህንኑ ጥላቻ ወርሶ የአገሪቷን ህልውና እየተፈታተነ ነው። ወያኔዎች
ትውልዱን (የትግሪኛ ተወላጆችን) በጥላቻ መኰትኰትና ማሳደግ ብሎም በአንድ አስተሳሰብ ላይ እንዲወድቁ ማድረጉን እንዴት ይመለከቱታል?
ጌታቸው
በጠላትነት ካልፈረጀ እና ካልተጓዘ፤ አለዚያ እማ 'ፍቅር' እኮ የፋሺስት ርዕዮት ለሚከተል ቡድን ስልጣን አያስገኝለትም። ፍቅር ከፋሺስቶች ጋር አይሄድም። ፍቅር ጸረ ስልጣን ነው፤በተለይ ለፋሺስቶች። ስልጣን አምባገነን የመሆን ፍላጎት ማንጸባረቂያ ሰገነት ነው። ፋሺዝም ተቃናቃኞቹን በፍቅር መመለስ አይችልም። የስልጣን ባህሪ አንደኛው “ካራክተሩ’ ጸባዩ ይህ ባሕሪ ነው። ስልጣን ላይ ለመድረስ ከሚጠይቁ ወሳኙ ሦስት ነገሮች የመዋሸት-ጥበብ (ተንኮል) ሃይልና ጥላቻ ናቸው። ጥላቻ የሃይል ማስገኚያ (drive) ቀስት ነው። ሃይል ደግሞ የስልጣን ማስገኛው የመወጣጫው መሰላል ነው። ስለሆነም ትግሬዎችም ሆኑ የኦሮሞ ተገንጣዮችና ማንኛውም ተገንጣይ ተከታዮቻቸውን በጥላቻ እና በውሸት ስብከት ማስከትል አለባቸው። በተለይም አንደ ወያኔ እና ኦነጎች የመሳሰሉ “የፋሺስት ቡድኖች”። ካልሆነ ተቀናቃኞቻቸውን በፍቅር ዓይን ሕብረተሰቡን ባንድ አስተሳሰብ እንዲወድቅ ማድረጉ አስቀድሜ የገለጽኩልህ - ለጥላቻው መነሻ ያደረገው ነገር አለ። መነሻ ያደረገውም ሥልጣን ለመመለስ ነው። ድሮም ዛሬም። ተነጠቅን ያሉትን የሥልጣን የባለቤትነት ማጣት ተከታዮቹን በጥላቻ መቀስቀስ ነበረበት፤ስለሆነም ነገዱን በጥላቻ እንዲከንፍ አደረገ። ድርጅቱ የፋሺስቶች ቡድን ነው።ሦስት ነገሮችን ተከተለ። “ቀሰቀሰ፤ አደራጀ፤ አስታጠቀ”። ነጠቀኝ የሚለውን ነገድ/ከተመለከቱት እንዲያ ያለ ባህሪ የሚሰራው ፤ በአክራሪ ብሔረተኞች ሳይሆን “በአገራዊ ፍቅር” የታነጸ፤ “ልቡ በአገር ክብርና ፍቅር የነደደ” ዲሲፕሊን የተላበሱ ድርጅቶችና መሪዎች ሲሆኑ ብቻ እንጂ ኢትዮጵያን በጠላትነት የሚመለከት አንድን ነገድ በጣላትነት ፈርጆ የተንቀሳቀሰ እንደ ወያኔ የመሳሰሉ ፋሺስቶች የተገነቡት “በጥላቻ” ስለሆነ ተከታዮቹን ባንድ የጥላቻ አስተሳሰብ መኮትኮት ባህሪያቸው ነው።
የትግራይ ተወላጆችን በጥላቻ
ኮትኩቶ ባንድ አስተሳሰብ እንዲከተልና እንዲወድቅ የማድረጉን ክስተት ደ/ር አሰፋ በደምብ ገልጾታል። በመጽሐፌም ውስጥ አትሜዋለሁ።
ደ/ር አሰፋ ነጋሽ (አምስተርዳም) የነገረን “ወያኔ” ፋሺስት ነው “ብሎናል”። ወያኔ በፋሺስት ባህሪያቱና አነሳሱ ከሌሎቹ አምባገነኖች
ወይንም ወደ ስርዓት የሚመጡ ቡድኖች ፍጹም ልዩ ነው።
ዶ/ር አሰፋ አንዲህ ይላል፤-
“ፋሽስቶች የአንድን ህብረተስብ
ነባር እሴቶች ቀይረው አንድ-ወጥ በሆነ አስተሳሰብ የታነጸ ማህበረሰብ ለመፍጠር ይፈልጋሉ። ስለዚሁ አይነት የፋሽስቶች ወይም የናዚዎች
ፍልስፍና “The Nazi Conscience”, በሚል ርዕስ ጥናት አድርጋ በእንግሊዘኛ መጽሃፍ የጻፈችው Claudia Conz የሚከተለውን
ትለናለች። ይላል ደ/ር አሰፋ። በመቀጠልም
<<አስፈላጊውን የእሺታ
ወይም የስምምነት ደረጃ ለማምጣት መሰረታዊ የሆኑ እሴቶች መለወጥ ወይም መቀየር ነበረባቸው” “ፋሽዝም ማህበረሰባዊና የሞራል አብዮት
በማስነሳት፤ አንድን እወክለዋለሁ የሚለውን ጎሳ ወይም ሕዝብ አስተሳሰብና አመለካከት ሥርነቀል በሆነ መንገድ ይቀይራል። ይህ ሥር
ነቀል የፋሽስት አብዮት የሚያስከትለው የባህልና የእሴቶች ለውጥ ፋሽዝም እንደ አዲስ በሚፈጥረው ስርዓት ውስጥ የሚኖሩትን ያንድ
ጎሳ ተወላጆች አስተሳሰብ፤ ግብረገብ፤ ስነምግባርና የሞራል እሴቶቹን ሙሉ በሙሉ በመለወጥ አዲስ ሰዎችን (ሆሞ ፋሺስቲካስ)
(homo fascisticus) ለመፍጠር ያለመ ነው።>> (አሰፋ ነጋሽ)።
አስተሳብ መውደቁ ምክንያቱ
ዶክተር አሰፋ የነገረን ዋናው ምክንያት ይኼ ነው። መጽሐፉ ላይ በጥልቅ ትግራይ ሰዎችና የትግራይ ብሔረተኞች ግንኙነት በዝዝርዝር
ቀርቧል። እዛው መመልከት ይጠቅማል። ደርጅቱ ከሙዚቀኞቹ፤ ከካድሬዎቹ፤ ከሽማግሌዎቹ ወጣቶቹ፤ምሁራኖቹ፤የሃይማኖት ተቓማቶቹ፤ እና
ባህሎች ወዘተ… በዝርዝር አስቀምጬዋለሁ። እዛው ማየት ይቻላል።መልሴን ሳልጨርስ አንድ ነገር ልበል። እኔ እንደ ትግሬነቴ የታዘብኩት
ልነግርህ ነው። ይህ በትግሬዎች የተገነባ ስርዓት “በአንጻሩ” በጣም የተጠላን ማሕበረሰብ ሆነን እንድንታይ እንዴት እንዳደረገን
ከኢትዮጵያዊያን ዜጎች የሚንጸባረቁትን ነጸብራቆችና የትግራይ ምሁራን ነፀብራቁን እንዴት አንደሚያዩት አንድ ምሳሌ ልስጥህ።
<< ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ ይባላል። እዚህ እኛ ጋር አሜሪካ ውስጥ Associate Professor of African and
African American Studies at Lehman College City University of New York ነው የሚያስተምረው። ባለፉት አመታት ብዙ ጽሑፎች ሲጽፍ ነበር (በኢትዮ-ሚዲያ እና ደቂ-አሉላ በሚባሉ ድረገጾች) ዛሬ ጽሑፎቹ የሚስተናገዱትበት በ በጣም አክራሪ በሆነው በጸረ አማራነት የታወቀው “ትግራይ ኦን ላይን” በተባለ ድረገጽ ላይ በተደጋጋሚ ትችቶችን ፤ታሪኮችን ይጽፋል። “ወያኔ ሰላም አምጥቷል፤ ወያኔ ኢፒ አር ዲ ኤፍ” በሉት እንጂ ወያኔ ብላችሁ አትጥሩት፤ ከሚለን አንዱ ነው። ታዲያ “ውራይና’ (ጉዳያችን) በሚባል የትግርኛ መጽሔት ላይ በ31 እትሙ ላይ በጣም የገረመኝ ነገር በቃለ መጠይቁ እንዲህ ሲል ዶ/ገላውዴዎስ አርአያ የጠቀሰውን አስቀድሜ ለነገርኩህ “ጥሩ ማሳያ” ነው ብየ የታዘብኩትን ለራዲዮ ተከታዮችህ ላስታውስ፤
ዶ/ር ገላውዴዎስ እንዲህ ይላል፡-
<< አንዳንድ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የተዘጋጁ ለሕዝብ ሚቀርቡ መዝናኛዎች አያለሁ። አንድ ቀን “የሰይፉ ሸው” መዝናኛ እመለከት ነበር። የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰይፉ አንዲት የትግራይ ልጅ የሆነች ድምጻዊት ቃለ መጠይቅ ያደርግላት ነበር። ሰይፉ ለተመለካቾቹ እንድትዘፍንላቸው ጠይቋት፤ እሷም እሺ ብላ በጣም ቢመገርም ድምጽ የትግርኛ ዘፈንዋን
አቀረበች። አዳራሹ ውስጥ የነበሩት ተመልካቾች ግን እያንጨበጨቡ፤ እስክስታ-አይመቱም፤ እጆቻቸውን-አጣምረው/አጣጥፈው ዝም፤ዝም-ብቻ
ዝም ብለው ይመለከትዋታል።እኔ ያኔ በጣም ገረመኝ። በጃንሆይ ጊዜ እኮ ትግርኛ ሲዘፈን ጉራጌው፤አማራው፤ኦሮሞው ከኛ ጋር አብሮ ነበር
አስከስታውና ደስታው ሲያስኬደው የነበረ። እስከዚህ ድረስ ትግርኛ ሙዚቃ እንኳ እስከመጥላት የሚደርስ ሁኔታ እየተከሰተ ነው። እኛ
ብቻ ካልገዛን የሚለው አስተሳሰብ መወገድ አለበት።>> ይላል ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ።
ይህ የሚያመላክተን ቀደም ብየ የገለጽኩትን ትግሬዎች በመላ ኢትዮጵያ እንድንጠላ የወያኔ ብሔረተኞች ያመጡብን ሰበብ ነው። ገላውዴዎስ እንኳ አሁንም በዚህ አመት የተናገረው በዚህ ንግግሩ እንኳ ተመልካቾቹ “ለምን?” ዝም አሉ የሚለው ጥያቄ ሲመልስ << እኛ ብቻ ካልገዛን የሚለው አስተሳሰብ መወገድ አለት>> በሚል መልሶታል። አየህ መልሱ? እኛ ካልገዛን ከሚል ነው ቁጣቸውን ያንጸባረቁት ብሎናል። እስካሁን አስገርሞኛል። ዶ/ር ገላውዴዎስ በተመልካቾቹ የተንጸባረቀ ጥላቻ በአማራ ማላከኩ እንጂ ሰርዓቱ
ምን ያህል በሕዝብ እንደተጠላ እና ግፍ እየሰራ እንደሆነ ዛሬም ሊገባው አልቻለም። ወይም እየካደ ነው ማለት ነው። ኦሮሞዎችን ሊል
እንደማይችል እርግጠኛ ነኝ። ካሁን በፊት ኦሮሞዎችን ጥበቅና ቆሞ በጫማቸው እንጓዝ ሲለን የነበረ ነው። ስለዚህ << እኛ
ብቻ ካልገዛን የሚለው አስተሳሰብ መወገድ አለት>> ተብሎ እየወቀሰው ያለው አዳራሹ በሙሉ ያለው እና እነማን ናቸው ዝም
ያሉ እና እኛ ካልገዛን የሚሉት ብሎ ገላውዴዎስ እየገለጸልን ያለው? “አማራዎችን እያለ ይመስለኛል”። ተመልካቾቹ በሙሉ አማራ ብቻ
አድርጎ የፈረጃቸው ትግርኛ ሲዘፈን “ዝም ያለው” “አማራ” ነው ብሎ ደምድሟል ። ሕዝቡ ግን ወያነ በሚባል ስርዓተ መንግሥት
“ምክንያት” በመላ ትግሬዎች ላይ ጥላቻ እንደሳደረ አልገባውም ወይንም ሆን ብሎ በአማራ ላይ አላክኮታል (አማራ ‘’ፓንቺንግ ባግ’’
የሚባለው ነገር ሁሉም ያላንዳች ገደብ የቁጣው መወጣጫ አድርጎታል)። የተማሩት የትግራይ ተወላጆች ዛሬም ከሁኔታው ሊማሩ አልቻሉም
እያልኩ የምናገረው ለዚህ ነው።
ጨርሻለሁ።
ጋዜጠኛ ወርቁ
ኢትዮጵያ በወያኔ አምሳያ ከተዋቀረች ወዲህ አገዛዙ የዘውግ አፓርታይድ በመገንባት በዘር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ የተፈረጁ ዜጐች ለመፍጠር ችሏል። ለዚህ ለዋነኝነት የኢኰኖሚውን (መሬት፣ ከፍተኛ የንግድ ዘርፎች፣ ከባድ ኢንዱስቲሪዎችን ወ.ዘ.ተ) በነማን እንደተያዙ መመልከቱ በቂ ነው። ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ትግርኛ ተናጋሪዎች ያስተባብሉታል። እርስዎ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የሚሰጡት አስተያየት ካለዎት?
ጌታቸው ረዳ
ይኼ ትግሬዎች አልተጠቀሙም የሚለው ክርክር ያሰለቸን ነው።በደምብ ተጠቅመዋል እንጂ። በዚህ ላይ ብዙ አገር ወዳዶችና ምሁራን ደጋግመው ገልጸውታል። በዚህ ላይ ግምባር ቀደም ትምህርት የሰጠን አሁንም ወዳጄ ዶክተር አሰፋ ነጋሽ ነው። የተቀሩት ብዙ ምሁራን ያለማመን ሲያጎበድዱ አንዴም ጸረ ትግሬነት ነው ሲሉ በርካታ የስድብ መልሶች ተስተናግዶብናል። ይህንን የሚያስረዱ በበቂ የጥናት ማስረጃ የተደገፉ በምጸሐፍ መልክ ሁለት መጽሐፍቶች
ለሕዝብ ቀርበዋል። The pillage of Ethiopia, by Eritreans and their Tigrean Surrogates”
በ1984ዓ.ም (በፈረንጅ ዘመን አቆጣጠር 1996) በዶ/ር አሰፋ ነጋሽ የተጻፈ መጽሐፍ እና ሌለው በቅርቡ በ2009 ዓ.ም የተጻፈ
፡ምጽአተ ዐማራ- ተገድሎና ተገዳድሎ የማያልቅ፤ ተነቅሎ የማይደርቅ” በሚል በሞረሽ ወገኔ ድርጅት (በአቶ ተክሌ የሻው መሪ ደራሲነት)
የተጻፉ መጽሐፍቶች ስታነቡ በግልጽ ከነማስረጃዎች እዛው ተዘግበው ይገኛሉ። እዚህ ላይ ለመግለጽ ያን ያህል መጽሐፍት ገጾች ተናግሮ
መጨረስ አይቻልም። የተደረገው አድልዎ እጅግ በጣም በዝባዥና ወገንተኛ ነው።
የትግራይ ብሔረተኞች ማወቅ ያለባቸው በተለይ ‘ትግራይ” አልተጠቀመም የሚሉ ሰዎች የድርጅቱ አነሳስ ትርጉም እና ዓለማ ማወቅ ይኖርባቸዋል። የወልቃይትን ሑመራ ለም መሬቶች እና የመሳሰሉ ሰፋፊ የለሙ መሬቶች ለማን ተብሎ ነው የተነጠቀው? ለትግሬዎች ጥቅም ተብሎ ኣይደለም እንዴ? ያውም እዛው በእርሻ ተሰማርተው እየኖሩ ያሉት “እድሜ ለህወሓት/ “ዕድመ ንውድብና” እያሉ አደለም እንዴ በየሚዲያው ሲናገሩ የምንሰማው? ከዚህ ወዲያ አድልዎ እና ጥቅም ሌላ ምን አለ?
ወያኔዎች ሲነሱ ሦስት ነገሮች የዘው ተነስተዋል። (1)አማራን ማስወገድ፤ (2)ትግራይን በምጣኔ ሃብት ማነጽ፤ (3)ስልጣን ለባለቤቱ ለትግራይ ማሰመለስ” የሚሉ ናቸው። ይህንን ለመፈጸም ባህልን፤ሃይሞኖትን በቁጥጥሩ ስር አድርጐ ከላይ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ እንዳስቀመጠው አስተሳሰባቸው ባንድ እንዲሄድ በማድረግ- “ወያኔ “ለትግሬዎች ለይቼ አልጠቀምኩም” “ለሁሉም እኩል አስተዳደሬአለሁ” ሲል ተከታዮቹም አብረው መዋሸት አለባቸው። አንዳንዶቹም፤ በተቃራኒ በሚገርም ሁኔታ “ትግራይ የባሰውኑ ከደርግና ከሃይለስላሴ ዘመን” የባሰ ኑሮ እና ድሕነት ውስጥ አለች ይላሉ። በመቀሌ ዩኒቨርሲ አስተማሪዎችና ዶክተሮችም በሚዲያ ቀርበው “ወያኔ ለሌቹ ነገዶች ሲያበለጽግ ትግራይን በኢኮኖሚ ረስቷታል። የወላጆቻችን መስዋእትንት በከንቱ አስቀርቶታል።” እስከማለት ደርሰዋል። ይህ ደግሞ መረጃውን ለመምታት ሆን ተብሎ በጥናት የተደረገ አሳሳች ዘመቻ ነው።ትግራይ ከተቀሩት አካባቢዎች በመጨረሻ ደረጃ እንደምትገኝ እሮሮ ሲያሰሙ ቃለ መጠይቆቻቸውን ቀድተነዋል።ድሮ አስመራ ውስጥ
ሲኖር የወያኔ የከተማ ደጋፊ አባል የነበረ ሱዑዲ ውስጥ የሚኖር ‘ሚሊዮነሩ” የፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር ታላቅ ወንድም በቃለ
መጠይቁ የነገረን “ጭራሽ ትግራይ ከማንኛውም የአገራችን ኗሪ ዜጎች በባሰ በድህነት የምትኖር የማቀቀች ክልል ነች” ሲል ያለ ማፈር
ተናግሯል።
እውነታው ግን ሌላ ነው የተቃራኒው ነው። ይህ ሆን ተብሎ ሁኔታውን ለማስቀየር የተደረገ “ዲተረንት” የሚሉት ፈረንጆች “ኣተንሽን” (ትኩረት) ማስቀየሪያ ዘዴ ነው። በጣም ብልህ ዘዴ ነው ብየ ነው የማምነው።
ጋዜጠኛ ወርቁ፡
ወያኔ ለ40 ዓመታት በላይ ያህል የፈፀማቸውና እየፈፀመ ስላለው የፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ዐማራ ቅስቀሳዎች የማታ ማታ የሚኖረው አስከፊ መዘዝ ምን ሊሆን እንደሚችል የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ቆይተዋል። ወደማይፈለገው መተላለቅ እንደሚያመራ ተተንብዮዋል። ዛሬ እዚያ ደረጃ ላይ ደርሰናል። አገራችን ኢትዮጵያና ሕዝቧ የተጋረጡትን አደጋ ለመሸጋገር ምን የትግል ዘዴ ብንከተል ከሚፈለገው አደጋ መትረፍ ይቻላል ይላሉ?
ጌታቸው ረዳ
የማታ ማታ የምንለው፤ ይኸው
የማታው የመጀመሪያው መግቢያ በር ላይ ነን ያለነው። እየሆነ ያለው እና ትግሬዎች ከየቦታው እንደ ውሻ እየታዩ ከየጓሮው እየታደኑ
ይደበደባሉ፤ ይገደላሉ። ወንድሜ ከተደበደቡት ውስጥ አንዱ ነው። ምን ያደረገው ነገር የለም። ትግሬ በመሆኑ ሰለባ ሆኗል። እኔም
እዚህ በየፓልቶኩ እየተዘለፍኩ ነበር። ትግሬ ትግሬ ነው የሚል ስም ለኔም ለገብረመድህን አርአያም ተሰጥቶናል። አይደልም እንዴ? ሞረሽ ፓልቶክ ውስጥ ለ4 ሰዓት ተኩል የሚሆን የሰጠሁትን ቃለ መጠይቅ ማድመጥ ነው።
የማታ ማታ ትግሬዎች እንዲህ
ያለ ዕጣ ፈንታ እንደሚደርሰን አስቀድሜ ትግሬዎቹን እንዲህ ያለ መዘዝ እንደሚመጣብን ስላወቅኩ የተቻለንን ያህል ትግሬዎችን ለማስረዳት
ጥረት አድረጌአለሁ። ሰሚ አልነበረም። አሁንም ከዚያ የወጡ አልመሰለኝም (የዶ/ር ገላውዴዎስን ትዝብት በማስረጃ ሰጥቻሃለሁ)። በኔ
ብቻ ሳይሆን በዘር ማጥፋት ምርምር ጥናት ያካሄዱ ግሬጎሪ ስታንሰንም ለወደፊቱ የማዝነው ለማንኛውም ሳይሆን ለትግሬዎች እፈራላቸዋለሁ”
ብለው ነበር የተናገሩት። ያ ማስጠንቀቂያ ግን እንደ እነ ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ የመሳሰሉ የትግራይ ምሁራን ሰውየውን በድረገጽ
ሲያበለጠልጥዋቸው ነው ያነበብኩት።
ያ ሁሉ እንግዲህ ለኔም ሆነ
ለነኚህ በሙያው ብዙ ጥናት ያካሄዱ የሰብኣዊ መብት ጠበቃና ምሁር የተሰጠው መልስ ጀሮ ዳባ እና ስድብ ነው። ያ ሁሉ በዝግምታ እየተጓዘ
መጥቶ ያልነውን ነገር እውን ሆኖ ዛሬ በየዜና ማሰራጫ የምትሰሙት “ትግሬዎች ተባረሩ፤ ትግሬዎች-ተደበደቡ፤ ተገደሉ፤ ንብረታቸው-ተቃጠለ..”
የሚሉ ዜናዎች መስማት የተለመደ ዜና ሆኗል። ይህ እርምጃ ዝም ብሎ እራሱ የመጣ አይደለም። ወያኔዎች በጥላቻ የካቡት ሕሊና ተመልሶ
በተጠቂው ወገን ምላሽ የምናይበት “ረሲፕሮካል/አጠፋ” ነው። መረዳት ያለብን ነገር፤ ይህ ነገር ወደ ከፋ ክስተትና መገዳደል ከመሸጋገሩ
በፊት ገና ወደ የመገዳደሉ አዳራሽ ከመገባቱ በፊት አሁኑኑ “በሩን ካልዘጋነው”፤ የምድሪቱ አዳራሾች የግድያ ማከማቻዎች እንዳይሆኑ
ከፍተኛ ስጋት አለኝ።
ያለ ምንም ቁጥጥርና ሃላፊነት በየፌስቡክና ዩቱብ ላይ እቤታቸው ላይ ሆነው የሚያሰራጩት ሕዝብን ለማጋደል የሚጮሁ በርካታ መንጋዎች በብዛት ወደ ዕበደቱ ዓለም ገብተዋል። ይህ Collective narcissism የጋራ ዕበደት የሚሉት ሕብረተሰብ በቡድን ስሜት እየጋለ የሚያብድበት የህሊና መበስበስ ለግድያውና ለመተላለቁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ነው። ይህ በዩቱብና በፌስ ቡክ እየተሰራጨ ያለ የቃላት መወራወርና አልፎም አገር ውስጥ ግድያ ሲካሄድ ያለ ቁጥጥር እንዲቀጥል የሆነበት ምክንያት አለው።
ብዙዎቹ ከኔ ጋር ላይስማሙ ይችሉ ይሆናል፤ ግን ሆን ተብሎ በመናገርና የመጻፍ ነፃነት ስም ባንድ ኔት ወርክ (በአንድ የእዝ ሰንሰለት ማለትም ግሎባል ኮማንድ) የሚመራ ሴራ ነው። ይህ ሴራ “ሕዝቦች እርስ በርሳቸው” በመጨራረስ እና በመናናቅ ሰላምና አንድነት ሳይኖራቸው ሲቀር “ተጨራርሰው፤ተራርቀው አዳዲስ አገሮችና ደካማ መንደሮች” በመፍጠር ለብዝበዛና ለቅኝ ግዛት እቅዳቸው አመቺ ሆኖ ያገኙት አዲስ የቅኝ ገዢዎች የረቀቀ ስልት ነው የሚል ሃሳብ ኣለኝ።
የውጭ ሃይሎች ድሮ መሳሪያ በመስጠት እንድንተላለቅ ያደርጉ ነበር፤ ዛሬ ግን ያለምንም የጠምንጃ እርዳታ እና “ጣልቃ ገብነት” ጥቂት አክራሪዎች ጥላቻቸውን ወደ ሰላማዊው እና የተረጋጋው ማሕበረሰብ እንዲያሰራጩት በመፍቀድ ሕዝቦች እና አገሮች የነበራቸው የጋራ ትስስር በሃይማኖት፤ በፖለቲካ፤ በነገድ፤ በቀለም፤ በዘር እየተወራረፉ እንዲተላለቁ የቀለለ መንገድ ሀኖ ተገኝቷል። ስለዚህ ሕዝቦችን የማበጣበጥና አገሮችን የማፍረስ የቀለለ መንገድ የተገኘው ይህ ያለ ቁጥጥር እየተካሄደ ያለው የዩቱብ እና የፌስቡክ ዕብደት በራሳቸው ዓለም ውስጥ ገብተው ብቻቸውን የሚያወሩ ጤነኞች የሚመስሉ ግን በዕብዶች ሆስፒታል መጠበቅ የነበረባቸው፤ እንደ ዕድል ሆኖ ከዕብዶች ሆስፒታል ያመለጡ እነኚህ የሕሊና ታማሚዎች ለመተላለቁና ለጥላቻው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው። ይህ ደግሞ የውጭ ሃይሎች ሕሊናን እና አገርን የማፈራረስ ሴራ ነው ብየ አምናለሁ።
ማውቅ ያለብን ግን እነኚህ ጤነኞች የሚመስሉ ግን ያበዱ ሰዎች ወደ እንደዚህ ያለ የጋርዮሽ ዕብደት (Collective narcissism) እረሳቸውም ሊዳርጉ
የሆነበት ምክንያት እነዚህ ዜጎች አገራቸው ውስጥ ሊኖሩ ስላልቻሉ፤ ወያኔ ባመጣው የጎሳ ፖለቲካ ተማርረው አንዳንዱ ታስረው ተደብድበው፤
ቤተሰቦቻቸው አጥተው፤ ተዋርደው ወደ ስደት ሄደው ፤ ስደት ላይ ከመድረሳቸው በፊት በባርያ ፈንጋይ ዓረቦች ተገፍተው፤ ተጠልፈው፤ተደብድበው
ብዙ የሕሊና ችግር ተጋርጠው ሲሻገሩ፤ በቀጥታ የሚገጥማቸው የብቸኛነት ኑሮ ተጨምሮበት የሕሊና ቀውስ የተዳረጉ ናቸው።
አሳዛኝ ከሚያደርገው ደግሞ፤
እነኚህ ምስኪን ዜጎቻችን “ወያኔች፤ ኦነጎች፤ ሻዕቢያዎች፤ ኦብነጎች፤ አክራሪ እስላሞች፤ ጴንጤዎች፤ ይሁዶች…ወዘተ…” ይጠቀሙባቸዋል።
እዛም አልጥም ሲላቸው፤ ከሚሰቃዩት ሕሊና ችግር ለመወጣት ሲሉ አንዳንዶቹ ካንድ ሃይማኖት ወደ ሌላ ሃይማኖት፤ካንድ ድርጅት ወደ
ሌላ ድርጅት፤ካንድ የፖለቲካ እምነት ወደ ሌላ በመንከብከብ የሕሊና እረፍት ያጣሉ (በዩቱብ ከሚናገሩት መገንዘብ ትችላለችሁ)።
መጨረሻ የራሳቸውን ንግሥና በማወጅ በቤታቸው ዙፋን ላይ ተቀምጠው ሕዝቡን እንዳለ ሲገድሉ ሲጨፈጭፉ በሕሊናቸው የሚያስቡት ቅዠት ሁሉ ያንን በቃላት ተርጉሞው ሲነግሩን እናደምጣለን።
ስለዚህ ይህ “የጋራ ዕብደት” የተከተለው በወያኔ የተባባሰ ቢሆንም ፤ ሁሉም የግንጠላና የነገድ ርዕዮት የሚከተሉ ድርጅቶች ባሰራጩት እና ባስተዋወቁት አደገኛ ፖለቲካ ያስከተለው ውጤት ነው። ስለዚህ ይህ የማታ ማታ የምትለው ነገር ፤አልተሳሰትክም እውነትክን ነው። ግን የህ የማታ ማታ ግን በሩቅ የምናየው ምሽት ሳይሆን “አሁን ደጃፉ ላይ ቆመን” ለመገዳደል በሚያመች መልኩ “በሩ” ገርበብ ብሎ አንዳንድ የመገዳደል ደዎሎች ሲደወሉ እያንን እና እያደመጥን ነው። ምክንያቱም አንዳንዶቹ “ለወደፊት ይህች አገር….” ሲሉ አደምጣለሁ እኔ እራሴ በስህተትን ከእውነታው ለመሸሽ የምጠቀምበት ቃል ነው። ለወደፊቱ የሚባል ነገር የለም። አማራዎች በሚሊዮኖች ካለቁ 26 አመት ሆኖታል። ወደ ገደል ከነ ነብሳቸው የተጣሉ በቢላዋ በቆጨራ የተገዘገዙ ህጻናትና እርጉዞች ዓለማቸው አብቅቷል። ለወደፊት የሚባል የላቸውም። እኛ ብቻ ነን እኮ ቅዠት ላይ ሆነን የነሱን ሞት ስላልተሰማን “ለወደፊቱ እና ስለወደፊቱ” የሚሉ ቃላቶች እራሳችንን ስንሸመግል የሞቱትን “አልሞቱም፤ አልተጨፈጨፉም፤ አልተዋረዱም” የምንልበት የክህደት ማመልጫ አገላለጽ ነው። ስለዚህ ይህ የማታ ማታ የሚለው እና ለወደፊቱ የሚል አገላለጽና ስጋት ብቀበለውም ፤”ማታ” የሚባለው ለኛ ሊሆን ይችላል፡ ከ26 አመት በፊት ግን ከኢትዮጵያ ምድር የተወገዱ ሚሊዮን አማራዎች እና የኢትዮጵያ ነብሳት የማታ ማታ
የሚባለው አጥፈቶአቸው ሄዷል። ጥያቀው ግን ለደፍጠጮቹስ ምን ይጠብቃቸዋል ለሚለው እነሱም “ምሽት” ላይ ነው ያሉት። ጥያቄህ ትክክለኛ
ነው። በጥሩ አስቀምጠኸዋል። በትክክል ብለሃል።” ዛሬ እዛ ደረጃ ላይ ደርሰናል”። ያልከው ትክክለኛ እውነታ ነው።
ሌላው ጥያቄህ “ዛሬ እዚያ ደረጃ ላይ ደርሰናል። የተጋረጡትን አደጋ ለመሸጋገር ምን የትግል ዘዴ ብንከተል ከሚፈለገው አደጋ መትረፍ ይቻላል ያልከኝ መሰለኝ።
ከዚህ አስፈሪ አደጋ ለመሸጋጋር ለጥፋቱ ምክንያት የሆኑትን ማስወገድ ነው። ይህች አገር ታማለች ብለናል። ጣረሞት ላይ ያደረሳት መነሻውን ምክንያቱ ማወቅ የመጀመሪያው የምርመራው ጥያቄ ነው። ሰው ሲታመም ወደ ሓኪም ይሄዳል። ሓኪም ያንን ነው የሚጠይቀው፤ አይደለም እንዴ? አገሪቱ ለዚህ ሁሉ ብጠብጥና እልቂት የዳረጋት ሌላ ሳይሆን “የነገድ ፖለቲካ” ነው። በአክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ በክረስትያኒቷ አክሱም እና በእስላም ዓረቦች የተሰነዘረው ጥቃት፤ከዚያ በግራኝ አህመድ እስልምና ለማሰፈን ክርስትናና እና ክርስትያናዊ ስልጣኔ ማፍረስ፤ ማቃጠል፤ማረድ የተጀመረው ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ፤ ከዚያ “ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል” የሚል መጽሐፍ የጻፈው ናዚው አውስትርያ ተወላጅ “ባሮን ሮማን ፕሮቻዝካ” ያነጣጠረው የማፍረስ ፕሮፓጋንዳ፤ ከዚያ በጣሊያን፤ከዚያም ያንኑን በሚገርም አቀራረብ ተስፋፍቶና በከፋ መልኩ በጸረ አማራ ቅስቀሳና አገር ለማፍረስ የተፈበረከው የሌኒንስቶች ርዕዮት እየተጠቀሰ በኢትዮጵያ ላይ በእነ ዋለልኝ መኮነን (On the Question of Ethiopian nationalities 1969) የታተመው የማበጣበጫ ማኒፌስቶ፤ ከዚያ ወያኔ የተባለ በጥላቻ የሰከረ ቡድን ያንን መነሻ በማድረግ ሆዱ ውስጥ አስቀምጦት የነበረው ከወላጆቹ ያገኘው ጸረ ሸዋ አማራ ጥላቻውን በማጠናከር ስልጣን በአማራ ተነጠቅኩ በሚል ሥልጣን ለባለቤቱ ለትግሬ መመለስ አለበት ብሎ 17 አመት በጠምንጃ ታግሎ “ስልጣን” በትግሬዎች እጅ ገባች ። የበሽታው መነሻ ተጠናክሮ መጣ። በጥላቻ የፈረጃት ኢትዮጵያ እና ሰንደቃላማዋ (የነፍጠኛ አርማ ፤ወላጆቻችን የገደለች አርማ ወዘተ ወዘተ….) እያሉ በመዝለፍ፤ ኢትዮጵያን እያመሳት ያለው በሽታ የጎሳ ፖለቲካ ነው። ስለሆነም ያንን መጣል ነው።
አሁን በሽታውን አውቀናል።
አሁን ደግሞ ወደ “መፍትሄው እንሂድ” ።መነሻውን ካወቅን፤ ሌሎች ወያኔ የሚመስሉ ምናልባትም ከነሱ የከፉ ቡድኖች አሉ። እዚህ እውጭ
አገር ያሉትን እንኳ ስንመለከት ኦነጎችና እና የኮሚኒሰት ትምህርት ናላቸው ያዞራቸው አማራን በማረድ የተሳተፉ ደም የጠማቸው የሰው
አውሬ መንጋዎችም በሌላ ዘዴ ሊፈትኑን መሆኑን አትዘንጉ።(አክራሪ ኦሮሞ እስላሞችና እና ኦጋዴኖችንም እንዳሉ አትዘንጉ) እዚሁ ፓኬጅ
(ከነሱ ጎተራ) ውስጥ አስገቡዋቸው። አላማቸውን ለማሳካት የሚጠቀሙበት ዘዴ ደግሞ ልክ ወያኔ የተጠቀመበትን ስልት ነው የሚጠቀሙበት
“ራስን በራስ ማስተዳዳር” የሚለው ሌለው የወያኔዎች ግልባጭ በሽፋን መልክ በየመድረኩ የሚሰብኳችሁ በፈረቃ ሊገዙን የተዘጋጁ ግንባሮችም
ይህ አሳሳች ጥያቄ ከመቀበላችሁ በፊት ፍርጥርጡ ወጥቶ ለውይይት መቅረብ አለበት። እስካሁን ድረስ መነገጃ የነበረው ይህ “ራስን
በራስ የመወሰን” የሚለው የነዋለልኝ የነ ሌሊን የነ ፕሮቻዝካ የነ ወያኔ ዛሬ ደግሞ የነ ኦነግና የግንቦት 7 “ራስን በራስ ማስተዳዳር”
ቅስቀሳ በግልጽ ፍርጥርጡ ወጥቶ ትርጉም እና በምንስ መልክ ነው የሚለው ለውይይት መቅረብ አለበት። ይህ መፍተሄው ነው። ምክንያቱም
ይህ ሐረግ ነው ብዙ ሰዎችን አሳስቶ ወያኔ እንዲቀበሉት ያደረገው የማሞኛ ዘዴ የነበረው። ዛሬም ያንኑ ማሳሳቻ ተጠቅመው ብዙ የዋሆች
በየአዳራሹ ተሰብስበው ባልገባቸው ሐረግ እያንጨበጨቡ ሲጃጃሉ እያየን ነው። ይህ ራስን በራስ ማስተዳዳር የሚለው “ብዙሃን ይመውኡ”
(ማጆሪቲ ሩልሰ) ከሆነ ፈረንጆች mob rule" የሚሉት ብዙሃኑ የጥቂቶች ወይንም የግለሰቦች መብት የሚረግጡበት ጸረ ግለሰባዊ
ነፃነት የሆነ የብዙሃን አምባገነኖች መሳሪያ ነው። ዲሞክራሲ ነው ብለው በዚህ መንገድ ይገልጹታል። ያ ከመብት ጋር ጭራሽ የሚጻረር
ነው። ያ ከሆነ መቀበል የለባችሁም። ያ ዲሞክራሲ ነው ሊሏችሁ ይችላሉ። የግሩፕ የብዙሃኑ የነገድ መብት ለማስከበር ተብሎ “በውስጣቸው
በሚኖር” ሌላ ነገድና ዜጋ ግለሰብ መብት የሚረግጥ ነው። ለምሳሌ አንዳንድ የፖለቲካ ደላሎች (እኔ አቃጣሪዎች የምላቸው) ለኦነግ
ሊሸጡን ሲፈልጉ “ኦነግ ወይንም ግንቦት 7 ወይንም ማንም መጪው ስርዓት “ዲሞክራቲክ ፌደራሊዘም እንጂ ኤትኒክ ፌራሊዝም አይደለም
የሚከተለው” ሲሉ አድምጠናል። ይህ ግን ሞኝህን ፈልግ በሏቸው።
ኦነጎች ለማን ነው እየታገሉ
ያሉት፤መጠሪያ ስማቸውስ ምን ይባላል? ስቪክ አይደለም፡ የፖለቲካ ድርጅቶች ናቸው። ለኦሮሞ ፖለቲክስ ነው የቆሙት አይደለም እንዴ?
ኦሮሞ ደግሞ ወያኔ የተባለ ጸረ ኢትዮጵያ ቡድን ስልጣኑን ተጠቅሞ ¾ የሆነውን ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ መሬት (ከልል) “የኦሮሞ
እንጂ የማንም መሬት አይደለም” ብሎ ሸንሽኖ በካርታ አጽድቆ ሰጥቶታል። አይደለም እንዴ? ኦሮሞዎች ያንን ባለቤትነት ቢሞቱ ለሌላው
ሊሸነሸኑባቸው አይፈልጉም/አይፈቅዱም። ሪፑብሊካቸውን አግኝተዋላ!!! በዛው ኦሮሚያ በተባለ የአፓርታይዶች ማፕ ስለጸደቀለት ኦሮሞ
እንጂ ማንም ዜጋ በዋናነት መሬትም ሆነ ስለጣን ኦሮሞ ካልሆነ በዋናናት ሊይዝ መብት የለውም ብለው አሁንም መላው ኦሮሞዎች አምነዋል
(ኦሮሞ ኬኛ ማለት ያ ነው)።
አሁን እኮ ከሶማሌው ጋር የሚገዳደሉት
በቁርጭራጭ መሬቶች ነው። ታዲያ ለወደፊቱ ይህ ያንተ ነው ተብሎ የተሰጠው መሬት እና ሪፑብሊክ “ሊሰጥ ነው”። ሞኝነት ነው። ይህ
ዲሞክራቲክ ፌደራሊዘም፤ ምናምን የምትሉት 3/4ኘኛው መሬት ለኦሮሞ የሚያጸድቅ ስርዓት ብዙ ጦርነቶች ያስከትልብናል። ጥርጥር የለውም።
ይህ አሁን አሮሞና አማራ አንድ ሆኗል ምናምን “ጂኒ ጃንካ” በኔ ላይ ቦታ የለውም፤፡ ጊዜአዊ እንጂ ፈረንጆች “ሪል ዲል” ወደ
እሚሉት “ዲል” ድርድር ስንገባ ያ ሁሉ “እቦታው ላይ አይገኝም” ። ጌታቸው ረዳ እምነቴ የህ ነው።
ያ ከሆነ፤ ዲሞክራቲክ ፌደራሊዝም
ኦሮሞ በዋናነት በሚያስዳድረውና በያዘው መሬት ላይ ሌሎች ዜጎች መብት የላቸውም። ኦሮሞዎች ክፉኛ ተጃጅለዋል (በምሁራኖቻቸው እና
በልጆቻቸው ምክንያት ፤አገራቸው ክደዋል)። የላቲኖችን ፊደል ተበድረው የናንተ ፊደል ነው ሲሏቸው ተቀበሉት። ለወደፊቱም ቢሆን ኢትዮጵያ
ውስጥ ዲሞክራቲክ ፌደራሊዝም እየተረጎሙት አለው ከነገድ ጋር በማያያዝ ነው። ከሰብአዊነት ከዜግነት አይደለም። ከነገድ መስተዳዳር
ጋር ስለሚያያይዙት “ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ነው”።
ለወደፊቱም በዚህ ቋንቋ መተዳዳር
አለብህ ይላሃል። ምክንያቱም ራስን በራስ ማስተዳዳር ማለት በቋንቋው መተዳዳር፤ ነው ብለው ወስነዋል። የተሰጠው ¾ መሬት በዋናነት
የኢትዮጵያ ዜጎች ሳይሆን ምርቱ ሃብቱ ለኦሮሞወችና በኦሮሞዎች ፈቃድ ብቻ ነው የምትተዳዳረው “ራስን በራስ ማለት ይህ ነው” ይላሃል
። ከተስማማህ በኋላ ምን ትላለህ።
የሕዝብ ድምጽ ሲሰጥ ማጆሪቲ (ብዙሃን) ድምጽ ተጠቅሞ “አማርኛ” በኦሮሞ መሬት እንዳይደመጥ፤እንዳይጻፍ፤መጥፋት አለበት ካለ በብዙሃን ውሳኔ ተወስኗል እና ይጠፋል (አሁን እንዳለው ማለት ነው) ራስን በራስ መላት ይህ ነው ይላሃል።እምቢ ያለ ኗሪ ለብዙሃን ድምፅ አልተገዛም እና ይባረራል ወይንም ይቀጣል። ወይንም መብት የለውም (ንግድ ቤቶች በአማርኛ ያስተዋወቀ ይቀጣል እንደዛሬው ማለት ነው) በማጆሪቱ (በብዙሃን ኦሮሞዎች) የሚጸድቅ ከሆነ፤ ማጀሪቱ ብሏል እና ማይኖሪትው (ግለሰብ እና ጥቂቶቹ) ገደል ይግባ “መቀጣት” አለበት ይላል። ይህ የራስን በራስ ማስተዳደር መብት ነው ሊልህ ይችላል። የአኖሌ ሃውልት በማጆሪቱ/በብዙሃን ኦሮሞ/ ደምጽ የተወደደ ስለሆነ በዚህ ሃውልት ምክንያት ግድያ ሊፈጸምብኝ ነው፤ ስድብ እየደረሰብኝ ነው “መፍረስ አለበት” የሚል አማራ ካለ “ማይኖሪቱ/ንኡስ ድምጽ” ነውና ለአምባገነኑ ለፌደራል ዲሞክራቲክ ለብዙሃኑ mob rule" መገዛት አለበት ፤ ወይንም ካልጣመው ወደ ባሕርዳሩ ወደ ደሴው ወደ ጎንደሩ ወደ አዲስ አበባው መሄድ አለበት ይላሃል። ምክንያቱም ማጀሪቱ ኦሮሞ ነውና ማጆሪቱ ሩል መጠቀሙ አይቀርም። ሌላ መካካለኛ ፈራጅ የለም። ራስን በራስ ማስተዳዳር ኢትዮጵያ ውስጥ “ከነገድ” ጋር የተያያዘ ስለሆነ “mob
rule" ያሰፍናል ማለት ነው።
ከዚያ ጥፋት ለመውጣትና ዳግም የወያኔ ጥፋት በመሰሎቹ እንዳይደገም ሁለቱ የጠቀስኳቸው (የጎሳ ፖለቲካ እና ራስን በራስ ማስተዳደር መብት) በጥንቃቄ ማጥናት ነው። ይህ የኦሮሞ መሬት ነው እና መንካት የለብህም ብሎ ሌላውን ዜጋ ከከለከለው ‘በራስማስተዳዳር ስም” አፋኝ
የቡድን የበላይነት “mob rule" ማስፈን ማለት ነው።
እኔ መፍትሄ ብየ የምሰጥህ ኦሮሞ አማራ ምናምን የሚለው የክልል ስም አስወግዶ እንደ ዱሮው በክፍለሃገር መጥራት እና በጂኦግራፊያዊ/ኢኮኖሚ/ቅርበት በመሳሰሉ “በጀሪ ማንደሪ” መልክ እያቀራረቡ አስተዳዳር ማስፈን እንጂ ይህ አማራ ነው፡ ይህ ክልል ኦሮሞ ነው፡ ብለህ የራሱን ባንዴራ ሰጥተህ እንዲውለበለብበት ከፈቀድክ፤ ሌላ አገር ፈጥረህ አሁን እየተደረገ እንዳለው ማፋጀት ነው። በክፍለሃገር ማስተዳዳር አለበት ብለው የተነሱ በርካታ ዜጎች እንዳሉ ለኔም ያነጋገሩኝ ሰዎች አሉ። ድሮ በአውራጃ በወረዳ በክፍለሃገር ሲተዳዳር እንዲህ ያለ የጥላቻ እና መተላላቅ ክስተት ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። ይህ ከሆነ፤ አንዳንድ ማሰሻሻያ አድርገህ ወደ ድሮው አስተዳዳርና አስተዳዳር መዋቅር ጥሩ መመለስ መፍትሔ ነው። ስለዚህ ይህ ራስን በራስ ማስተዳዳር የሚለው “ዲሞክራቲክ ፌደራሊዝም” የሚባል ማጃጃያ አስተዳዳር ሖድ ዕቃው የያዛቸው ነገሮች ማየት፤ መጠየቅ አለባችሁ።
ጨርሻለሁ።
ጋዜጠኛ ወርቁ፡
የታላቋ ትግራይ ምሥረታ ድንጋይ መጣሉን በመፅሐፍዎ ላይ ትንታኔ ሰጥተውበታል። ይህን ጉዳይ የሚያረጋግጡ ብዙ ጉዳይዎች እየተከናወኑ ነው። የዘር ማጥፋት እርምጃ በመውሰድ ከፊል ጐንደር፣ ጐጃምንና ወሎን የሚያካትተው መሬት ወደ ታላቋ ትግራይ ተከልሏል። ከዚሁ አናት ላይ ደግሞ ወያኔንና-ሻቢያን አስታርቆ በታላቋ ትግራይ ግንባታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዕልቂትን ለመጋበዝ እየሰሩ ነው። ይህን ሁኔታ እንዴት ያዩታል? በመፅሐፍዎ ላይ ከሰጡት ትንታኔ ላይ የሚጨምሩት አስተያየት ካለዎት?
ጌታቸው ረዳ፡-
አዎ ይኼ የቆየ የትግሬዎች እና ኤርትራ ውስጥም በተለይ የአኮለጉዛይ ተወላጆች ልሂቃን ሲቃዡበት የነበረው ቅዠት ነው። በብላታ ሃይለማርያም ረዳ የተመራው “ቀዳማይ ወያኔ” ተብሎ የሚታወቀው ትግራይ ውስጥ ብቅ ብሎ የጠፋው የ1935ቱ ዓ.ም ‘የገበሬዎች አብዮት’ ውስጥም ቢሆን ይፋ የወጣ ባሆንም ይህ ቅዠት ይንጸባረቅ እንደነበር ብላታ ሃይለማርያም እና ሌሎቹ በምጸሀፌ ውስጥ የተጠቀሱ ሰዎች ያደረጉት ቃለ መጠይቃቸው ይነግረናል። ትግራይ ትግርኚ በእንግሊዞች የተጀመረ “ፖለቲካ ትግርኛ” የሚበለው ቢሆንም፤ እንግሊዝ የሴራው ጠንሳሽ ቢሆንም እንግሊዝ እንዲያ ያለ አዝማሚያ ያለቸው ሰዎች ባያገኝ ከነፋስ ተነስቶ እንዲያ ያለ ሴራ ሊጠነስስ ይችላል የሚለው አካራካሪ ነው (ቢያንስ ለኔ ማለት ነው)። አነሳሾቹ የኛዎቹ እንጂ ብዙ ምሁራን ጠንሳሹ እንግሊዝ ነው እንደሚሉን “ሊሆን አይችልም”. የውጭ ሃይል እንዲያ ያለ ጥንስሰ ለመጠንሰስ የአካባቢ ባሕሪ ሲንጸባረቅ ካላየ ከሰማይ ሊፈጥረው ኣይችልም።
ባጭሩ በሚኒሊክ ጊዜ ከትግሬዎች እጅ የተነጠቀው መንግሥት በሗላም “አከለጉዛዮች እና ትግሬዎች የሸዋ/አማራ መንግሥት ብለው ከሚጠሩት “ከሃይለስላሴ ስርዓተ መንግሥት” ተላቅቆ ሁለቱ ትግርኛች ተናጋሪዎች የምጽዋን እና ሌሎቹ ወደቦች በቁጥጥር አድርጎ ‘ትግራይ ትግርኚ’ የሚባል አገር ለመመስረት ነው ዋናው ፍላጎትና ትርጓሜው። ትርጉሙ “በሸዋ” አንገዛም ነው። ትንት የነበረ መነሻ ነው። ብላታ ሃይለማርያም እራሳቸው “እነኚህ ሽዋዎች ምን አድርጉ ነው የሚሉን?” ይላሉ በንግገራቸው። ሥርዓቱ እንደ መንግሥት ሳይሆን እንደ የሸዋ እና ትግራይ ቅራኔ አድርገው ነው ከጥንት ምኒሊክ ሥልጣኑን ከያዙ በኋላ ይህ ስያሜ የሰየሙት።
ስለዚህ ከሸዋ ለመላቀቅ ትግራይ ትግርኚ መመስረት አማራጭ አድርገው የያዙት በአንደኛ ወይም በሁለተኛ ደረጃ “አማራጭ” መንገድ ነበር
(ልክ እንደ ዛሬው ወያኔዎች እየተከተሉት ያለው አማራጭ ስልት)።
ያ “ስልት” ወደ “ዳግማዊ
ወያኔ” ተሸጋግሮ በረቀቀ መንገድ ተጉዞ ኤርትራን ነጻ በማውጣት “ኢትዮጵያ የጋራችን፤ ኤርትራና የግላችን” ሲሉ ትግሬዎቹ ደግሞ
“ትግራይ እስክትለማ ሌላው ክፍል ይድማ” የሚል (ይህ ንግግር ስብሃት ነጋ ይበለው አይበለው በተግባር ግን የታየው ያ ነው። (በወቅቱ
የጻፈው የዶ/ር አሰፋ ነጋሽን - ዘ ፒለጅ ኦፍ ኢትዮጵያ እና “ምፅአተ አማራን” ስናነብ ንግግሩ እውን ያደረግዋል።) ስለዚህ
“አገር” ለመመስረት የሚያስችል አስፈላጊ የሚባሉ “ሱፕራ ስትራከተሮችና -ኢንፍራስተራክተሮች” ዘረግተዋል። ከጤና፤ ከትምህርት እስከ
ኢንዱሰትሪ እና ወታደራዊ ቤዞች ወደ ትግራይ ማዛወርና ማጠናከርን የሚያመለክተው ያንን ውጥን ተግባራዊ ለማድርግ ነው።
መርሳት የሌለብን ወያኔ ከመነሻው “ትግራይ የኢትዮጵያ ኮሎኒ ስለሆነች ‘ሪፑብሊክ’ እንመሰርታለን ብሎ የተነሳ ቡድን መሆኑን አትዘንጉ። ከ10 አመት በኋላ ኤርትራኖች ጋር ሲጣሉ የነበረው ሴራ ቀዘቀዘ። ግን በሌላ ስልት ተካው። ትግራይን በምጣኔ ሃብት፤በወታደራዊና በትምህርት ግንባታ ለማጠናከር እንዲሁም ለወደፊቱ ይጠቅማታል ብለው ያቀዱት የውጭ መውጫ በር ደግሞ ቤንሻንጉልን ከትግራይ ጋር አያይዞ “አማራ” የሚባለው አካባቢ ከሱዳን ሆነ ከውጭ አገር እንዳይገናኝ ወደ ውስጥ ሶርጉዶ ገፍቶ ትግራይን በአማራ
ጀርባ በማለፍ ከጋምቤላ እና ቤን ሻንጉል የሚደርስ አዋሳኝ ድምበር (ካርታ/) ሰረቷል።
ይህ ደግሞ ሁላችሁም የሰማችሁት
ዜና እንደሆነ እገምታለሁ። ካርታው በራሴ መጽሐፍም አውጥቼዋለሁ። ሆኖም “ማን ያርዳ የቀበረ ፤ማን ይናገር የነበረ” የሚባለው አማራዎች
የሚመሰሉት ጥሩ ምሳሌ በማስረጃ ለቅርብላችሁ። ማስረጃው ወያኔን ሲያገልግል የነበረው ፤ወያኔዎች “ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒሰትር”
የሚሉት የሚኒሰተርነት መጠሪያ ማዕረግ የነበረው ዛሬ የግንቦት 7 የኢሳት ቴ/ቪዥን ቋሚ አምደኛው ኤርሚያስ ለገሰ ከጋዜጠኛ መሳይ
መኮንን ጋር ስለ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ድምበር ጉዳይ አንስተው ሲወያዩ የተናገራቸውን ነገሮች ልጥቀስልህ።
እንዲህ ይላል፤=
“ይህ የቦርደር ጉዳይ አጀንዳ
ፓርቲው ውስጥ እያለሁ አውቀዋለሁ። ያኔ የሱዳን እና ኢትዮጵያ የድምበር ኮሚሽን እና ልዩ ኮሚቴ” የሚባል ተቋቁሞ ነበር፤ ለተወሰኑ
ጊዜያት መስርያቤቴን ወክየ ተገኝቼ ነበር።ኮሚሽኑ “ፎርማል” አይደለም። በፓርላማ የጸደቀ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀው አይደለም።
እዘው ድምበር ኮሚሽን ከስዩም መስፍን ጀምሮ በሙሉ “ቲ ፒ ኤል ኤፎች” ናቸው። ኢትዮጵያን የወከሉ በሙሉ TPLF ፎች ናቸው።የጸጥና
የድምበሩን ጉዳይ በሚመለከት በሃላፊነት የያዙት ተደራዳሪዎች በሙሉ ወያኔዎች ናቸው። ስለዚህ 2001 የተደረገው፤ ሰምምነቱንም ዳታውን
ዴቨሎፕ የተደረገው ውይይት በTPLF እና በሱዳን መንግሥት መካከል ነው የሚያሳየው። የኮሚኒኬሽን መምርያ ፤የኢኮኒሚ መምሪያ ወዘተ
የሚባሉ ኮሚቴዎች አሉ። ብእዴኖች (በኢኮኖሚ ኮሚቴ ውስጥ ናቸው) እኔ በኮሚኒኬሽን
ቲም ውስጥ ወክያለሁ። 5 ዘርፎች አሉ። የፀጥታውና የድምብሩ ጉዳይ የሚወያዩት ግን በስዩም መስፍን የሚመራው የወያኔዎች ቡድን ነው።
በማለት ኤርሚያስ ሰፊ ትንተና ከሰጠ በኋላ መሳይ መኮንንም የደምበሩን ጉዳይ እስከ ጋምቤላ ድረስ የተመለከተው መስመር ወያኔ የተደራደሩበት
ምክንያት አዳዲስ ድምበሮችን ከቤንሻንጉልም ሆነ ወልቃይትን ወደ ትግራ እንደተከለለ አሁን በቅርቡ በቅማንት እና አማራ መካካል ግጭቶች
እነዚህ ሁሉ አጀንዳዎች አሉዋቸው በዚህ እስኪ ተንትንበት? ብሎ ይጠይቀዋል።
የኢሳቱ ኤርሚያስ ለገሰም እንዲህ ይላል።
“መቸም ነገረ ስራቸው በጣም የሚገርም ነው። የተደበቀ ዓላማ ስላላቸው ነው።” ያ የተደበቀ ዓላማ ደግሞ ይኸው እኮ ቅደም ያልኩህ
ነው። አንዱ ይነሳ የነበረው ይህ ነው። ጊዜ ከሰጠኸኝ ላሳይህ ብሎ
በቴ/ቢዥኑ ካርታ እያሳየ እዛም ክርክር ሲነሳበት የነበረው ይኼ ነው ይህ
ካርታ በማለት ካርታወን ያሳያል። ካርታውን ለተመልካች እያሳየ እንደምታየው “በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ምርጫ ኮሚሽን
በ1986 ዓ.ም የወጣ ካርታ ነው። ይህ ካርታ ወያኔዎች ከገቡ ከ3 አመት በኋላ ማለት ነው። ምርጫ ኮሚሽኑ የኢትዮጵያን ድምበር
ካርታ ሲያወጣ “የኢትዮጵያ ካርታ ድምበሮች ይህን ይመስላል” ብሎ ነው ያወጣው። ካርታው ላይ እንደምታየው፤ በትግራይ እና በሱዳን
መካከል፤በጋምቤላና በትግራይ መካከል ድምበር እንዲኖር አድርጓል። በድሮ የኢትዮጵያ ካርታ ትግራይ ከሱዳን ጋር ድምበር አልነበራትም።
አንድ ድምበር ፈጥሯል ማለት ነው። ሦስት ቀለሞች ይታያሉ። ቀይ ሰማያዊና የወይን ጠጅ። ጋምቤላ “ቤኒሻንጉልና ትግራይ” እዚህ የወይን
ጠጅ ቀለም የተደረገበት ‘ቤኒሻንጉል’ ነው፤ በትግራይ እና በቤንሻንጉል መካካል ድምበር በሙሉ አውጥተውታል።>> ሲል ኤርሚያስ
የዓይን ምስክርነቱና የነበረበትን እና ያየውን ካርታ በማስረጃ ነግሮናል።
ስለዚህ ይህ ዓላማ እና አዲስ
ካርታ መፍጠርን የሚነግረን ፍንጭ ለጥያቄህ ደምበኛ ማስረጃ ነው። አማራውን ወደ ውስጥ ሰርጉደው የትግራይ ድምበር በአማራዎች ድምበር
በስተጀርባው አልፎ ከቤንሻንጉል እና ጋምቤላ የሚገኙት ለኢንዳስተሪ የሚጠቅሙ የኬሚካል ንጥረ ነገሮች እና የእርሻ ውጤቶች በማጋበስ
ትግራይን አስተማማኝ ቀጣይ ህይወት እንዲኖራት ለማድረግ ነው (ሳስተይን ለማድረግ፤ ጠንካራ መደላድል ላይ ለማስቀመጥ ማለት ነው።
ይህ ደግሞ በዚህ ሰሞን የምጣኔ ሃብት ምሁራኖቻቸው በሚሰጡት ቃለ መጠይቆቻቸው አውነታውን ማየት ይቻላል)።
ከዚያም ወደ ውጭ ማስወጫ በር ከሱዳኖች ጋር በወልቃይትም በቤንሻንጉልም በሁሉም በኩል መውጣት የሚችልበትን ካርታ አውጥቶ በጠላትነት የፈረጀውን አማራን አደህይቶ ወደ ውጭ አገር መተላለፊያ እንዳይኖሮው ሁሉ በማድረግ ‘የትግራይ ትግሪኝን” አገር መስርቶ አማራን የትግራይ ትግርኚን” የጥሬና የሸቀጥ ማራገፊያ ለማድረግ ነው የሚል እምነት አለኝ። ሰዎች ሊወቅሱኝ፤ሊቃወሙኝ፤ ሊጣጥሉት ይችሉ ይሆናል። ግን የድምበሩ መካለል ሴራ እና አማራውን ያለ በር ማስቀረት ትርጉሙ ምንድነው?
እኔን የሚቃወሙ ሰዎች ካሉ መልሳቸውን ለመስማት ዝግጁ ነኝ።
ኤርትራኖች ኢትዮጵያን የሸቀጣቸውና
ምርታቸው ማራገፊያ እናደርጋታለን ሲሉት እንደነበረው የትግሬወ ወያኔዎችም “አማራ” ይምትባል ብሔር “ሕበረተሰባዊ ሰላም” አታገኝም
“ብለው ፈክረው የተነሱበትን አማራን ድምበር ዘግቶ “አምበርክኮ” የትግሬ ሸቀጥ ማራገፊያ ማድረግ ነው የተወጠነው አጀንዳ። ከወሎ
ከጎንደር ከጎጃም መሬቶች እየነጠቀ ለምን አላማው ነው ብለህ የጠየቅከኝ ከነዚህ ቦታዎች ብቻ ሳይሆን እስከ ጋምቤለና ቤንሻንጉል
ሁሉ የተዘረጋ የትግራይ አዲስ ካርታ እየሰራ ያለው ውጥኑ ለዘረዝረኩልህ ዓላማ ነው።
ጨርሻለሁ። አመሰግናለሁ።
ጋዜጠኛ ወርቁ-
የማጠቃለያ ሐሳብ ካለዎት፤
ጌታቸው ረዳ
መባል ያለበት ብያለሁ። ሕዝቡን ልነግረው የምፈልገው ግን የተቃዋሚ ድርጅቶች እና ምሁራን “ለወደፊቱ” የወያኔን ስርዓት ለመተካት “ዲሞክራቲክ ፌደራሊዝም” ነው የሚያዋጣው “ራስን በራስ ማስተዳደር” ነው የሚያዋጣት” ብለው ፖለቲካቸውን ሲያናፍሱ ሰምተናል። ይህ ግን የሚያያይዙት ከነዜግነት እና ከግለሰብ ነጻነት ሳይሆን ከቡድን መብት ጋር ስለሚያይዙት መፍተሄው የወያኔ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ የነገድ ፌደራሊዝም ግልባጭ ነው”። ይህ 3/4ኛ ስፋት ያለው ከግማሽ ኢትዮጵያ በላይ የሆነ መሬት ለኦሮሞዎች በባለቤትነት “ለቡድን” ሰጥትህ በውስጡ የሚኖሩ ዜጎች መብት ይከበራል ማለት “ቀልድ” ነው። ይህ አትጃጃሉ። የቡድን እና የግለሰብ መበት ማስከበር የሚባል “ድብልቅልቅ ያለ” አስቂኝ ዲሞክራሲም እየነገሩን ነው።
እጅግ አመሰግናሉ
እኔም አመሰግናለሁ!
No comments:
Post a Comment