Thursday, January 5, 2023

እዚህ ድረስ ልንደርስ እንዴት ቻልን? የትግሬ ምሁራን ቁዘማ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/5/2023

 

እዚህ ድረስ ልንደርስ እንዴት ቻልን?

የትግሬ ምሁራን ቁዘማ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

1/5/2023

ይህ የቪዲዮ ንግግር ትርጉም ያንድ የትግራይ “ምሁር ተብየ” ንግግር ነው። “ትግራዋይ” ማለት “ባለ ሃገር” ማለት ነው የሚል ተሰምቶም በታሪክ ተዘግቦም የማያወቅ ትርጉም ሲሰጥ ታደምጣላችሁ። 

ከትግርኛ የቪዲዮ ንግግር ወደ አማርኛ ልተረጉመው የፈለግኩበት ዋናው መንስኤ፤ የትግራይ ማሕበረሰብ ያፈራቻቸው ምሁራን ተብየዎቹ “ማንም ኢትዮጵያዊ ያልጨመረ የአክሱም ሥልጣኔ የትግሬዎች ብቻ ነው” የሚለው እልባት ያልተገኘበት የትግሬዎች ትምክሕትና ከታሪክ ያፈነገጠ የድንቁርና ጉራ ምን ያህል “የነቀዘ የትግራይ ምሁር” በብዛት እንደተራባ ለማሳየትና በዚህ ጉዳይ መጽሐፍ በመጻፍ ላይ ያለ ወዳጄ ስላለ እርሱም ለምርምር ሰነዱ እንዲጠቅመው ከሚል ነው የተረጎምኩት።እናንተም እግረ መንገዳችሁ ትምህርት ታገኙበታላችሁ እና እነሆ ከትግረኛ ቪዲዮ ወደ አማርኛ የተረጎምኩትን የወጣቱ የፋሺስቶች ንግግር እነሆ።

መርስኤ ኪዳነ የባላል። ከትግራይ ርቆ ሕዝባችን ከሚለው የትግራይ ሕዝብ ስቃይ ከመካፈል ይልቅ የአሜሪካ ምቾትን መርጦ ሜነሶታ ውስጥ የሚኖር በሕዝብ ስም ከሚያላግጡ ትግራይን አገር እናደርጋለን ከሚሉ ትግሬዎች አንዱ ነው።

ባንድ የትግራይ ማሕበረሰብ የእራት ግብዣ ተጋብዞ በነበረት ወቅት ያደረገው ንግግር እንዲህ ሲል ይጀምራል።

“ እኛ ተጋሩ በዘመናችን (በአክሱም ዘመን) 4ቱ ሃያላንና የሰለጠኑ አገሮች ተብለው ሲጠሩ ከነበሩት አገሮች እኛ ትግሬዎች አንደኞቹ እንደነበርን ይታወቃል። ዛሬ ከ4ቱ ውስጥ ተለይተን የመጨረሻ ሆነን ዛሬ አሁን ወዳለንበት የመጨረሻ ጭራ ሆነናል።እስከዚህ ድረስ ልንደርስ ያስቻለን ምክንያቱ ምንድ ነው?” በሚል  ለፋሺስት ተከታይ አድማጮች ንግግሩን ይከፍታል።

በስዕሉ የምትመለከቱት 4 ጣቶቹን ሲያመለክት የሚያሳያው ከ4ቱ ሃያላን እኛ ነበርን እያለ ሲያመላክት የሚያሳይ ጣት ነው።

በመቀጠል እንዲህ ይላል።

“ከዚያ ስልጣኔ ወርደን ወደ መጨረሻ እርከን መመደባችን ያደረሰን ነገር መመርመርና ወደ ነበርንበት ሃያልነታችንና ሥልጣኔ ለመመለስ መፍተሄ ለመስጠት ነው ሃሳብ የማካፍላችሁ።እኛ ትግሬዎች እስከ 8ኛው ክ/ዘመን ከሰለጠኑ አራቱ አገሮች ነበርን።ከ8ኛው ክ/ዘመን ግን ምን ተከሰተ፤ ምን መጣ? የሚለው ጥያቄ መመለስ አለብን።

ለውድቀችን ምክንያት መልሱም የሚከተለው ነው። እኛ ትግሬዎች ከ8ኛው ከ/ዘመን በላ ማንነታችን ትተን አዲስ ማንነት መፈለግ ጀመርን። ሲያቀብጠን ከነበረን ዝቅ ካልንበት ደረጃም ቢሆን የባሰ የዝቅታ ማንነት የሚጋብዝ አዲስ ማንነትን ማፈላለግ ጀመርን። “ከአውተንቲሲቲ ሊደርሽፕ/ከራስ መር አስተዳደር” ወጥተህ ከውስጥህ ከእውነተኛው ማንነተህ ያፈነገጠ ሌላ ማንነት ውስጥ ገብተህ ስትሰራ የመውደቅ ዕድልህ ሰፊ ነው። የገጠምነ ነገር ያ ነው።

 ‘Authentically we are Tegaru’ ትግራዋይ ማለት “ባለ ሃገር” ማለት ነው። እኛ ትግሬዎች የሥልጣኔ ብቸኛ ባለቤቶች ነን። ትግራዋይ ማለት ደግሞ “ባለ ሃገር” ማለት ነው። ሃገር ማለት ደግሞ ትርጉሙ“ሥልጣኔ/ሲቪላይዘሽን/” ማለት ነው።

ከሃገራዊነት ወርደን “ኢትዮጵያዊነት” የሚባል ሌላ የኛ ያልሆነ ማንነት ፍለጋ ገባን። የሚገርመው ደግሞ ያንን የኛ ያልሆነ ማንነት ለማነጽ ያውም ማዕከሉ “ሸዋ” የሆነ፤ ያውም “አውተንቲክ” ስላለሆነ “መሰረታችንና” የውስጣችን ስላልሆነ “ሊሳካልን” አልቻለም። But , we did all we can do! እስኪ አንዲት ማስረጃ የሌሎች ኢትዮጵያዊያን አስተዋጽኦ ነው ብላችሁ የሚታይ ቁምነገር ያለው ስሪት ጥቀሱልኝ? አታገኙም፤ ሑሉም እኛ የትግሬች ነን የሰራነው። Anything! ጅግንነት የሚባለውም፤ even modern history ስልጣኔ የሚባለውም፤ ከዓድዋ ጦርነት ጀምረህ ሦስቱም መሪዎቻችን ራስ ሓጎስ፤ ራስ አሉላ፤ ራስ መንገሻ እነዚህ ናቸው ጦርነቱን የመሩት። የተቀሩት ከቤተክርስትያን አጥር ግቢ ከላ ተሸሽገው ናቸው የነበሩት።

ላም በሃይለስለሴ ዘመን ፤ያው “ኤየርላይንስ” የሚባለውም ማን ነው የገነባው? ራስ መንገሻ ናቸው የገነቡት። Organization For African Union –“the same person Ras Mengesha” ናቸው የመሰረቱት። የአሰላ የብቅል ፋብሪካ፤ “የዓሰብ ሪፋይነሪ” ወዘተ የፈለጋችሁት ጥሩልኝ፤ ትግሬዎች የገነባነው ነው። ኢትዮጵያ አላት የሚባሉ resources እኛ ትግሬዎች የገነባናቸው ናቸው። We were the cultivators የግንባታው መስራች “ንቦች” እኛ ነን።

 የቂጣ ማር ታሪክ ነው የነበረን። እኛ እንጋግራለን እነሱ ይበሉታል።

ስለዚህ ወደ እዚህ የመጨረሻ ውድቀት ለምን ወደቅን ለሚለው ጥያቄ “እውነተኛው አውተንቲክ” ማንነታችንን ጥለን አዲስ ማንነት ፍለጋ ሰንባዝን ስለነበርን “ወደቅን”። የእኛ አውተንቲክ ያልሆነ “ኢትዮጵያዊነት’’ የሚበል አዲስ ማንነት ፍለጋ ስንሄድ ኤርትራኖችም ጣሊያን የሰጣቸው አዲሰ “አርትራዊነት” የሚባል ማንነት ተረክበው ሁለታችን ለውድቀት ተዳረግን። ምክንያቱም አሸዋ ላይ የቤት መሰረት መጣል ማለት ነው።

ስለዚህ ከዚህ ለመውጣት ምን መደረግ አለበት? ማድረግ ያለብን፤ እንደ ጥንቱ አክሱማዊያን ወላጆቻችን ለመሆን ከፈለግን “rediscovery of ourselves” ነው ማድረግ ያለብን። Nation ስለሆን ጦርነት ውስጥ ሁሌም እናሸንፋለን፡ ምክንያቱም already Nation አገር ስለሆን። አንድ ስነ ልቦና የጋራ ታሪክ እና የሚያስተሳስሩን ክሮች ስላሉን አገር ነን።አገር ስለሆን ሁሉቸውን እናሸንፋቸዋለን።

የጋገርነው ቂጣ ግን መብላት ላይ ሁሌም ደካሞች ነን ፤ ተመጋቢዎቹ ሌሎች ሆነው እናገኛቸዋለን። Why? ለምን? ምክንያቱም Nation ነን ፤ ግን  ራሳችን የቻልን State መንግሥት አይደለንም፡ “ብሔር” ነን ግን “መንግሥት” አይደለንም። መንግሥት ስላልሆን የገነባነውን ሌሎች ተጠቃሚዎች ይሆናሉ። ብሔረ ትግራይ ከሸዋ መንግሥት ሥር በመሆኑ ነው ይህ ሁሉ ችግር እየገጠመው ያለው። ስለዚህ ወደ Nation State ማደግ አለብን።

ስለዚህ ብሔረ መንግሥት ለመሆን ምን ያስፈልገናል? አንደኛ ወደ አውተንቲክ ማንነታችን ለመመለስ “Nation State building” የአገረ መንግሥት ግንባታ ማትኮር። ይህንን ለማፋጠን ደግሞ Social Capitalን መመዝመዝ ነው። ማንነትን ማወቅና ማሳወቅ ያስፈልጋል። ይህንን ለማድረግ ደግሞ “የሚዲያ” ግንባታ አስፈላጊነት ግምባር ቀደም ትኩረት ማድረግ አለብን።

እንደምታውቁት እስራል ከተገነባች ወደ አርባ ወይንም 50 አመትዋ ይሆናታል። Exodus (ዘጽአት) የሚባል መጽሐፍ አንባብቸሁ ይሆናል፤ በዛች ‘Exodus’ በምትባለዋ መርከብ ሁሉም እስራኤሎች የርሃብ አድማ ስያደርጉ ዓለም እንዲያውቀው የተጠቀሙበት ዘዴ “ሚደያ” ነው። ሚዲያው ነፃታቸውን ለማምጣት በሚገባ ተጠቅመውበታል። እኛ ትግሬዎች ሚዲያ አይኑረን እንጂ ዕድሜ ለ ቲ ዲ ኤፍ (Tigray Diaspora Force) ማለቴ ነው፡ እያደረብን ያለው ስቃይ እንደምንም ብለን ዓለም እንዲሰማን አድርገናል።

ሀኖም ሚዲያ ለማነጽ ሁለት ችግሮችን ተመልክቻለሁ። እንዴት ወደ እዚህ የመውደቅ እርከን ደረስን ብየ እራሴን ስመራመር፤ ከወራሪው የሽዋው ምኒሊክ ወረራ ወዲህ የጋገርነው ቂጣ እ እየበሉት፤ የትግራይ ማሕበረሰብ ከ“Self Actualization” የወረደበት ዘመን ነው። ማለትም አንድ ማሕበረሰብ የተለያዩ “የፍላጎት ስነልቦናዎች” 5 ፍላጎቶች አሉት። እነሱም መብላት፤ safety net-ደህንነቱን መጠበቅ፤ Social need, ከዚያም “Self Actualization” ወደ ሚባለው 5ኛው የላቀው ደረጃ ይደርሳል።በዘመነ ያሬድ አክሱም  “Self Actualization” ደረጃ ደርሰን ስለነበርን ወደ ፈጠራ ምርምር ነበር ስንጓዝ የነበረው። ምጡቅ ፍለጋዎች የላቁ ምርምሮች ነበር ስንፈልግ የነበረው።

እንደምታውቁት በዘመነ አብርሃ እና አጽብሃ ዘመን ጀኔራል አብራሃ  እስከ መካ ሳውዲ እና የመን ድረስ ሄዶ ነበር። ምክንያቱም ወቅቱ የመስፋት የማደግ “Self Actualization” ደረጃ የደረስንበት ዘመን ስለነበር። ዛሬ ከዚያ ደረጃ ወርደን ማለትም ከአጼ ዮሐንስ በላ ወደ “safety” ደረጃ ወረድን። መከላከልና ዲፌነሲቭ ውስጥ ገብተን ስለ ማንነታችን አጉልተን አንናገርም። ይህ ደግሞ በተገኙት ሚዲያዎች ማንነታችንን በኩራት የመግለጽ የማሰራጨት ችግር አለብን።

አማራዎች እኛን ጮክ ብለን እንደምንናገር አድርገው ይስሉናል። እኔ ይገርመኛል። ጮክ ብሎ የሚናገር ትግሬ ሰምቼ አላውቅም፡ ብዙዎቻችን ድምጻችን ስንናገር በለሆሳስ (low tone) ነው የምንናገረው። ስለዚህ ከዚህ ወጥተን ወደ “self esteem” በራስ መተማመን እና “Self Actualization” (ራስን ወደ ከፍታ ማሸጋገር) እና አስፍቶ የማሰብ፤ አዳዲስ የግንባታ ፈጠራ ውስጥ መግባት አለብን።

ሁለተኛው ችግራችን “አብሮ የመስራት ችግር” አለብን። እንደ ግለሰብ እያንዳንዳችን ትግሬዎች አብረን ባንድ ልብ ነው የምንሰራውና የምንግባባው፤ እንደ ድርጅት መስራት ግን ችግር አለብን።  ይህንን ከፈታነው፤  The Nation State of Tigray መመስረት ያስችለናል። The Nation State of Tigray ስንል ስለ የትኛዋን ነው የምንነጋገረው? አሁን ያለቺው “በክልል” የምትጠራው ትግራይን ነው ወይስ የትኛዋን ነው? ብዙ ክርክር ያስገባን ይሆናል፤ መከራከር አይከፋም። ግን “Self Actualization” የደረሱ የትግራይ ማሕበረሰብ አሁን አለን።

እነዚህም ብዙዎቹ ዲያስፖራ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ናቸው። ምናልባት ከኔ ዕድሜ ባለይ የሆኑት አገር ውስጥ ያሉ ግን “ችግርና  በጦርነት ህይወት” ስላሉ በደርግ ጊዜም ስላለፉ ራስን በመከላከል “safety Oriented” ውስጥ ናቸው ያሉት። ከኔ ዕድሜ በታች ላለን ወጣቶች ግን ስለ ምግብ እና ደህንነት አያሳስብንም። ከዚያ ባሻገር የመምጠቅ Self Actualization” ፍላጎት ያለን ትውልዶች እዚህ ውጭ አገር አለን።ስለዚህ ለነዚህ ወጣቶች ወደ ድርጅቶች ስበን እንዲቀላቀሉ ማድረግ ለትግራይ አገረ ግንባታ ጠቃሚዎች ናቸው።>>

በማለት “ኢትዮጵያና አክሱም” ምን እና ምን እንደነበሩ የማያውቅ ይህ ወጣት ከሕዝቡ ኑሮና ሁኔታ አብሮ የማይሄድ የተሰለበ የወጣት ስሜት ፍላጎት የሚያንጸባርቅ፤ ሞትን፤ ጦርነትን፤ ድህነትን በሽታን፤ ዘላቂ ግጭትን የሚጋብዝ አደገኛ የፋሺስቶች “ቁዘማ” ውስጥ የገባው የትግራይ አዲሱ ትውልድ ይህንን ይመስላል።

ትርጉም

ጌታቸው ረዳ              

አመሰግናለሁ!

1/5/2023

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

No comments: