በፋሺዝም ፍቅር የወደቀው የሰዎች ቅሪተ አካላት ሊቅ ዘረአሰናይ ዓለምሰገድ
ጌታቸው ረዳ
ETHIOPIAN SEMAY
2/30/23
ትናንት ማታ ይህንን ጽሑፍ በማዘጋጅበት ወቅት ፕሮፌሰር ዘረአሰናይ አለምሰገድ አዲስ በተዋቀረው የትግራይ ካቢኔት ከተመረጡት የውጭ አገር “ዲያስፖራ ትግሬዎች” አንዱ ነው። ሌላኛዋ ድግሞ በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ስራ የነበራት እዚህም እዛም ወያኔን ወክላ ስትንቀዠቀዥ የምናያት ዶ/ር አክሱማዊት የተባለቺዋ ሌላኛዋ ወያኔ መሆንዋን የትግራይ ወያኔ ዜና ማዕከሎች አስተጋብተዋል።
በዚህ የተነሳ ሳይንቲስቱ ዘርአሰናይ አለምሰገድ “ከጦርነት መከላከል ወደ ሙከራ ሰላም” በሚል ርዕስ ትግሬዎች በተሰበሰቡበት አዳራሽ የተናገረውን ለታሪክ ጸሐፍትና እንዲሁም ለጋዜጠኞችና አወያዮች ይጠቅም ዘንድ ለማሕደራችሁ ይዘገብ ዘንድ እነሆ ከትግርኛ ወደ አማርኛ ተርጉሜ አባባሎቹ ፋሺሰታዊ/ ናዚአዊ መሆናቸውን እያመሳከርኩ እተነትናለሁ።
ካሁን በፊት ሰለ ዘርአሰናይ አንድ ጽሑፍ አቅረቤአለሁ። ዘርአሰናይ አለምሰገድ
ትውልዱ የእኔ እትብት በተቀበረባት እኔ ከተፈጠርኩ በሗላ የተወለደ ወጣት አክሱማዊ ነው።
በምርመራዬ በተመለከትኩት መሰረት ወያኔ ከመመስረቱ በፊት ዕድሜው የ4 አመት ህጻን ነበር። በሙያው ዓለም በአንደኛ ደረጃ እውቅና ያወቀው paleoanthropologist ነው ። ፖሊዮንተሮፖሎጂስት ማለት ከመሬት ጥናት ጋር የተያያዘ የጥንት ሰዎች “ቅሪተ አካላትን” ያጠና ሊቅ ማለት ነው። ግኝቱ እንደምታውቁት ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ 3 ሚሊዮን ዕድሜ በላይ ያላት የመጀመሪያዋ የሰው ልጅ የሆነች ህጻን “ሰላም” የተባለች ሙሉ አካላዊ አጥንቶችዋን ያገኘ ነው። ስለዚህ ተማሩ ከሚባሉት ክፍሎች በላይኛው እርከን የሚገኝ ምሁር ነው።
ታዲያ ይህ ምሁር በሚያሳዝን
መልኩ የወያኔ ፋሺሰት ርዕዮትን የሚከተል ወጣት ሆኖ ሳገኘው በጣም አዘንኩ።
ወያኔዎችን “መሪዎቻችን” በሚል ያቆለጳጵሳቸዋል። ለምን በፋሺሰቶች ርዕዮት ፍቅር ሊወድቅ ቻለ የሚለው መልሰ ለማግኘት፤
የጀርመን አለም አቀፍ የሃይማኖት፤ የሳይንስና የፍልስፍና ሊቃውንት ለምን በናዚ ፍቅር ሊወድቁ ቻሉ የሚለው ጥናት አብሮ ስለሚመለስ
ያንን በተመለከተ የሕሊና እና የልቦና ሊቃውንት የጻፍዋቸውን በርካታ መጻሕፍቶችና የጥናት ወረቀቶችን ኣግኝቶ ማንበብ ይረዳል።
ይህ ምሁር መሪዎቼና መንግሥታችን ሚላቸው መሪዎቹ የሚናገሩትን በመድገም ጦርነት ጀማሪዎቹ “ወራሪዎች” በሚላቸው እንደተጀመረና የደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጀልም በትግራይ እንጂ በአፋሮችና አማራዎች እንደተፈጸመ አያምንም ወይንም ተናግሮ አያውቅም።
ከሦስተኛው “ራይክ” ውድቀት
በኋላ ጀርመኖች ለሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሌሎች አገሮችን በሰፊው ተጠያቂ አድርገዋል። የናዚ ጋዜጠኛ ሂልዴጋርዴ ሮዝሊየስ የተባለ
በ1946 ‘ጦርነት በመጀመራችን ጥፋተኛ እንዳልሆንን እያንዳንዱ ጀርመናዊ ያውቃል’ ሲል ተናግሯል። ፕሮፌሰር ዘርአሰናይም ከዚህ
አልተለየም።
ስለ ዶ/ር ዘርአሰናይ
ዓለምሰገድ ካሁን በፊት ጥቂት አስተያት ሰርቼ ነበር። ድንገት ድረገጽ ስመለከት ወጣቱ በወያኔ “ፈሲቲቫል” ተገኝቶ ብዙ ምሁራን
እና ደናቁርት ትግሬዎች የተገኙበት አዳራሽ ላይ ተገኝቶ የተናገረውን ንግግር የዜና ማዕከሎች እንደ አዲስ ለጥፈው ፕሮፓጋንዳውን
ሲለጠፉለት አይቼው፤ እኔም ሳደምጠው ካንድ የተማረ ሰው የማይጠበቅ ያውም የሰው ልጅ ቅሪተ አካል ተመራማሪ ከሆነ ምሁር ፋሺሰቶችን
ሲያወድስና ትግራይ ውስጥ ያሉት ታሪካዊ ቅርሶችና ድንቅ የአክሱማዊያን ዘመን ውጤቶች ከትግሬዎች ሌላ ባለቤት እንደሌላቸው ሲናገር
እርግጠኛ ሆኖ ነበር በሃይለኛ ቃል እየተናገረ አድማጮቹን በግርምታና አድናቆት ሲያንጨበጭባቸው የነበረው።
እስኪ የዚህ ምሁር ክርክር እውነታ ካለው አንድ ባንድ እንምልከት።
<< በሺዎች አመታት ያስቆጠረ የአክሱም፤ የይሓ፤ የገረዓልታ ፤ የማይ ጋዕዋ፤ የመዛብር እና የተምቤን ጥንታዊ የዓለት ምሽጎች በዚህ ወረራ አፍርሰውታል ወይንም የራሳቸው ሊያደርጉዋቸው ላይ እና ታች እያሉ ነው።
ረዢም ፍልስፍና፤ኪነጥበብ፤ የንጉሥ ካሌብ፤ የቅዱስ ያሬድ ፤ አባ እስጢፋኖስና
ዘርአያዕቆብ ትርጉሙ ምን እንደሆነ ሳይረዱት የራሳቸው ሊያደርጉዋቸው በመድከም ላይ ናቸው። ያልተረዳቸው ነገር ግን ይህ ሁሉ የትግራይ
ባህልና ክብር በብዙ ደምና መስዋዕት የተገነባማ የተጠበቀ አንደሆነ አላወቁም። >>
ሲል የተጠቀሱት ጥበቦችና ዕድገቶች የትግሬዎች እንጂ ማንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ነገድ የአክሱም ዘመን ሥልጣኔ ክብርና ጥበቃም ሆነ ለግንባታውም ለህለውናው ቀጣይነት መስዋዕት ወይንም አስተዋጽኦ ያደረገ ማንም የለም። ይላል ዓይኑን በጨው አጥቦ። (አማራውም አገውም… ሌላውም አይመለከትም፤) ሲል ደምድሟል።
በተመሳሰይ መልኩ ባለፈው ሳምንት መቀሌ ውስጥ እነ ጻድቃን ወ/ልደተንሳኤና
ፋሺሰቱ ምግበይ የተባለው የወያኔ አዋጊ በተሰበሰቡበት አዳራሽ “ጌታቸው አረጋዊ” የተባለ የወያኔ ጋዜጠኛ እንዲህ ሲል የነ ዘርአሰናይ
አባባል ደግሞታል፤-
<< ከአክሱም ውድቀት በኋላ የትግሬዎች ፈጠራ የሆነው የቤተክሕነት ትምህርት ከደብረዳሞ፤ አክሱም ወዘተ.. ጠቅልሎ ወደ ጎንደር ነው የሄደው፤”ዋልስ ባጅ” የተባለ የታሪክ ጸሐፊ “ዋልድባ” በሚል መጽሐፉ ውስጥ ትናንት ስመለከት እያሱ ቀደማይ የተባለ የጎንደር ንጉሥ በየሳምንቱ ሊቃውንት የተባሉ ከትግራይ ከማንኛውም ቦታ እየሰበሰበ ጠጅ እየጋበዘ ሊቃውንቱ ሁሉ ወደ ጎንደር እንዲከማቹ አድርጎ ትግራይ በተገላቢጦሽ ወደ እዛው እየሄዱ መማር ጀመሩ። ስለዚህም እውቀታችን ሌሎች የራሳቸው አደረጉት ይላል።
አንግዲህ ያሬድ አንኳ ወደ ጎንደር የሄደው በ6ኛው ክ/ዘመን አካባቢ ነው ይህ ጋዜጠኛ የሚያወራው ደግሞ አክሱም ውድቀት በኋላ ይላል ጋዜጠኛ ጌታቸው አረጋዊ።
ዶ/ር ዘርአሰናይም ይሁን እርሱን የመሰሉ ስለ ቅዱስ ያሬድ ስራዎች ትርጉማቸው እናውቃለን አማራው አያውቅም የራሱም አይደለም ለሚሉት ሁሉ ይህንን ጥያቄ ላቅርብለት።
ቅዱስ ያሬድ ስራ የትግሬ እንጂ የአማራ አይደለም ስትል ማስረጃህ ምንድ ነው? የሚል ልጠይቅና ወደ ማብራራቴ ልግባ። ወዳጄ ሰዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን የጻፋቸው ጽሁፎችን እየተመለከትኩ አንዳንድ ጉዳዮች እንዲያብራራልኝ ሁሌም እጠይቀዋለሁ። አምሳሉ የኪነት ምሁር ነውና ሁሌም እጠይቀዋለሁ። አምሳሉ እንዲህ ይላል።
<<፡አክሱም የትግሬ የሚመስላቸው ሰዎች ቅዱስ ያሬድ አክሱማዊ ነው ሲባል ትግሬ ይመስላቸዋል፡፡ በእርግጥ ቅዱስ ያሬድ በተነሣበት ዘመን ትግሮቹ ወደ ሀገራችን ከገቡ ብዙ የቆዩ ባይሆኑም እዚህ ሀገራችን ውስጥ ነበሩ፡፡ ይሁንና ከዓመታት በፊትም እንደገለጽኩት ቅዱስ ያሬድ አማራ እንጅ ትግሬ አይደለም፡፡ ይሄውም ይታወቅ ዘንድ የዜማ ምልክቶቹን ሥያሜዎች “ቅናት፣ ድፋት፣ ደረት፣ ጭረት፣ ይዘት፣ አንብር፣ ሒደት፣ እርክርክ፣ ድርስ፣ ቁርጥ” ብሎ በመሠየም አማርኛ አድርጓቸዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ አማራ ለመሆኑ ይሄ ግልጽ መረጃ የማይበቃው ካለ ራሱን ቅዱስ ያሬድን ጎንደር ተሠውሮ ካለበት ቅዱስ ቦታ ደብረ ሐዊ ከተባለው ዋሻ (የማያምኑ ወገኖች ያረፈበት ቦታ ይሉታል) ሔዶ በሱባኤ ሊጠይቀውና ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡ >>
እንግዲህ ዶክተር ዘረሰናይ አለምሰገድ ይህንን እንዴት ይመልሰው ይሆን? በጎሰኛነት ስሜትና በተሳሳተ የፋሺሰት ትምህርትና የተሰበከው ለወጣቱ ዘርአሰናይ ብቻ ሳይሆን በውሸት ያደጉ የፋሺሰት ካድሬዎችና ባልሆነ ትምክህት ስትወጣጠሩ ትዕግስት ይኑራችሁ እያልኩ የምመክረው ይህንን ፈታና እንደሚደቀን ስለማውቅ ነው። እውነታው ይኼው ሰጥቻችኋለሁና መልስ ካላችሁ ሜደውም ፈረሱም እነሆ! አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል! ስለሆነ በዚያኛው ወገንም “ሹል” ብዕር አለና እየተስተዋለ ይሁን! የምለው ለዚህ ነው።
ዘርአያዕቆብም ለምን ከአክሱም ወደ ሸዋም ሆነ ወደ ኢምፈራንዝ (ጎንደር) ሄዶ “ዘርአያዕቆብ ኢምፈራንዛዊ” ተብሎ ትዳር መስርቶ እንደኖረ የሚነግረን ነገር እነዚህ አካባቢዎች የጥንታዊዋ አክሱም ሕዝቦች መኖራቸው ማሳያ ነው። ለዚህ ነው ሁሌም ለትግራይ ወገኖቼ የምመክረው “እየተስተዋለ እንጂ” የምለው።
አክሱም የትግሬዎች ነው የሚለው የዘርአሰናይ የታሪክ ስግብግብ የኔነት ብቻ ባሕሪ መልስ እንዲሆነኝ የማቀርበው ጥቅስ ተመራማሪው የምጣኔ ሃብትና የታሪክ ምሁር የሆነው አቻምየለህ ታምሩን ነው።
አቻምየለህ ከታች የጻፈው መልስ በእንግሊዝኛ ሲሆን አቻም የጻፈውም ተገንጥለው “ሃገረ ትግራይ” የሚባል አገር ለመመስረት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ለተገነጠሉ ፋሺስትነትን የተከተሉ ለወያኔ የፖለቲካ ቄሶችን የሰጠው መልስ ነበር። ልክ አንደ ዘርአሰናይ እነዚህ ቄሶችም “ግዕዝም ሆነ ሃይማኖትና ስልጣኔ” ብቸኛ የአክሱም ስልጣኔ የትግሬዎች ብቻ ነው የሚል የግንጠላ አዋጅ ሲያስነግሩ የሰጣቸው መልስ ነበር። ይህንን ወደ አማርኛ ተርጉሜ ላቅርበው። እነሆ አቻም እንዲህ ይላል፦
<< የአክሱም ታሪክ እና ስልጣኔ በቡድን ቢከፋፈል የማይሆነው ለትግሬ እና ለትግራይ ብቻ ነው። የአክሱም ማዕከል የሆነው የኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥልጣኔ ከትግሬ ወይም ከትግራይ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። የኢትዮጵያ መንግስት ማዕከሉን አክሱም ከተማ ሲያደርገው ትግራይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢም ሆነ ትግራይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ “ትግሬ” (ትግራዎት) የሚባል ሕዝብ አልነበረም።,,,፣>> ይልና በመቀጠል
እንደ እነፕሮፌሰር ዘርአሰናይ የማሳሰሉትን አርኪዮሎጂሰቶችንም አንዲህ ሲል ይማጸናቸዋል።
<< በነገራችን ላይ አክሱም የትግሬ ሥልጣኔ እንደነበረች የሚያሳይ አንድ የታሪክ ማስረጃ (የድንጋይ ጽሑፍና የአርኪዮሎጂ ማስረጃ) አለኝ የሚል የትግሬ ብሔርተኛ ፕሮፌሰርና ዶክተር አርኪዮሎጂሰት ካለ እኛ ስህተተኞች ሆነን እነሱን የምናምን መሆናችንን ለማሳወቅ እንወዳለን። ይህ የሚያቀርብ ተመራማሪ ካለ ምስጋናችን ወደር የለውም። >> ሲል የእነ ዘርአሰናይ ዓለምሰገድ “ፉፋነት” በባዶ አስቀርቷቸዋል።
እነሆ በተጠየቀው መሰረት ዘርአሰናይ እስካሁን ድረስ አንድም የድንጋይ
ምርምር አክሱምም ሆነች የአክሱም ስልጣኔና ግዛት የትግሬዎች ብቻ መሆንዋን ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም።
እንቀጥል፡-
ዶ/ር ዘርአሰናይ በሚገርም አገላላጽ ስለ ትግራይና የትግራይ መሪዎች በፋሺስታዊ አንደበት እንዲህ ይላል፡
<< እኛ ከትግራይ ውጭ የምናመልከው ሕዝብ የምንምበረከክለት የምንሰግድለትና የምንሳሳለት ሕዝብ ማንም የለም!! >> ይላል። በተመሳሳይ “Tembrant als Erzieher” የተባለ የናዚዎች ጋዜጣ
“German for the Germans. A Jew can no more became a German than a plum can turn into an apple. There is no one outside of Nordic race that we bow down to.”
ይህ አባባሉ፤ ናዚዎች ከኖርዲክ ዘር ሌላ የምንሰግድለትና የምናመልከው ሌላ ዘር ወይንም ሕዝብ የለም የሚሉት ኣይነት አባባል አንድ ነው።
ከዚህ ሌላ ዘርአሰናይ ሽልማቱን ለመቀበል ቫቲካን ጣሊያን አገር ሄዶ የአለም ሊቃውንት በተሰበሰቡበት አዳራሽ “ስለ ትግራይ ጦርነት ነበር ብዙውን ንግግሩ ያጠፋው። እዛ ላይ አንደ ምሁር ትግሬዎች በአፋሮችና በአማራ ሕዝብ ላይ ያደረሱት ጉዳት አንዲትም ቃል አልተነፈሰም። በሚገርም ሁኔታ ደግሞ በመግቢያው እኔ “ኢትዮጵያዊ ትግሬ” ነኝ እያለ ሲናገር ትግሬዎች ስብሰባ ላይ ሲህድ ግን “እኔ ከትግራይ ሕዝብ ውጭ የማመልክውም ሆነ ደጅ የምጠናበት ወይንም የምሰግድለት ሕዝብ (ዘር) የለም ይላል።
በመቀጠል ፕሮፌሰር ዘረሰናይ እንዲህ ይላል፡
<< ወራሪዎቻችን ብዙዎች ናቸው። መንግሥታችን (የወያኔ የትግራይ ማለቱ ነው) ስለ ሰላም ሲማጸኑ ከፍራቻ ኣይደለም …..ዛሬ የገጠመን ጦርነት የዘር ማጥፋት ውጊያ ነው። መጀመሪያ በመሪዎቻችን ሕሊና ውስጥ ያለውን አስተሳሰብ ለማጥፋት ሞክረዋል፤ ሳይሳካለቸው ሲቀር መሬታችን ንብረታችን ለመዝረፍ ሞክረዋል ፤ በከፊል ተሳክቶላቸዋል። ያለተሳካላቸው እና ምስጢሩን ያለወቁትና ሊያገኙት የማይቻላቸው ማንነታችንን ነው። ትግራዎትነታችን በሻንጣ ውስጥ ወይንም በአለት ምሽግ ውስጥ የተደበቀ በቀላሉ የሚገኘው ማንነት አይደለም።ማንነታችን ‘በልባችን፤ በአንጎላችን የተጠበቀ ነው። ይህ ነው ያልተረዳቸው>> ይላል፡
በተመሳሳይ ሂትለር “መይን ካምፕፍ” (የኔ ትግል) በሚለው መጽሐፉ እንዲህ ይላል፤
<< የኖርዲክ ማንነት ማንም ዘር ሊያገኘው የማይቻለው በሕሊናቸው ውስጥ የታቀበ ማንነት ነው። ሰዎች የአፈጣጠር (ፋካልቲ) ልዩነታቸውን ሳይረዱ Pug-Dog (ድንክዬ ውሻ) የ“Grayhound” (ቀጭን፤ ሸበላ፤ ፈጣን ሯጭ እና አዳኝ የሆነ ውሻ ) ሥራ ተክቶ እንዲሠራ እንደማሰልጠን መሞከር ዓይነት ነው። ፑድል (ትንሽየ ውሻ) በማንኛውም የሥልጠና ዓይነት ብታሰለጥናት በአንዱ ወይም በሌላ መልኩ የታቀበን ነገር ቆፍራም ሆነ አሽትታ ልታገኘው የማይቻላት ምክንያት የአፈጣጠር ጥራቶች ልዩነት እንዳለ ሰዎች ሊረዱ አልቻሉም >> ይላል ሂትለር።
ዶ/ር ዘርአሰናይም እኛ “እና እነሱ” በሚለው አመለካካቱ ከሂትለር አልተለየም።
ይህ ሁሉ ጽንፈኝነት የማየው ብዙውን ጊዜ በትግራይ በምሁራን ላይ ነው። ታዲያ የትግራይ የምሁራን ባህሪ እንዴት እንደምተረጉመው ስጥር ይጨንቀኛል። የትግራይ ቀደማይ እና ዳግማይ ወያነ በእነ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ አለምሰገድ አድናቆት ተችሮአቸው ሲመለኩ በመጀመሪያውም ሆነ በሁለተኛው ወያኔ አማራ፤ አማራ፤አማራ የሚለው መነሻ እንደነበርና፤ “የአማራን ብሔር እስከዘላለሙ ሰላም እንድያጣ” በመመሪያ ተነድፎ የገዛ ደም አጥንታቸው የሆነውን ማሕበረሰብ እስከዛሬ ድረስ በመጥላትና ደም በማፍሰስ መነሻ ያደረገ የትግራይ ናዚዎች እንቅስቃሴ ወደ ስልጣን መጥቶ “መንግስታችን እና መሪዎቻችን” የሚል ምሁራን በሚባሉት በእነ ዘርአሰናይ አላምሰገድ አንደበት የሙገሳ ማዕረግ ሲቸራቸው የነዚህ ምሁራን “ድውይነት” ባህሪ ለመግልጽ ብሞክርም ምን ብየ አንደምገልጽአቸው እቸገራለሁ።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment