Saturday, January 22, 2022

ክፍል 2 የወያኔ ትግሬዎች ለምን ታሪክ ይሰርቃሉ ጌታቸወ ረዳ ETHIO SEMAY 1/23/2022

 

ክፍል 2

 የወያኔ ትግሬዎች ለምን ታሪክ ይሰርቃሉ

ጌታቸወ ረዳ

ETHIO SEMAY

1/23/2022

ወደ ክፍል 2 ከመግባቴ በፊት በክፍል 1 የታሪክ ምሁር ነኝ የሚል ታሪክን በቅጡ ያልተረዳ የትግራይ ምሁር  የተናገረው የቂል ንግግር በቪዲዮ ሥርጭት ብዙዎቹ የወያኔ ጀሌዎች እየተቀባበሉ እራሳቸውን ሲክቡ  አቅርቤኣለሁ። በዚህ ክፍል 1 ቪዲዮው በማስረጃ አቅርቤአለሁ።

ካለፈው የቀጠለ ክፍል 2 የማቀርበው ማስረጃ በተጠቀሱት የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍልችን ትግሬዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ጭምር የተካፈሉበት አውደ ውግያ እንደነበር 3 ጸሐፍትን አቀርባለሁ።

አበክራችሁ ልታውቁልኝ የምፈልገው ነገር ፡ 2 ነገሮችን ላስጨብጥ

 “ወያኔዎች በዶጋሊ የትግራይ ብቻ ነው የተካፈለው እያሉ የሚያወሩት ወሬ የሚነግረን ነገር ፤ በወቅቱ ጎጃም፤ወሎ ጎንደር እና ሌሎች ግዛቶች ዮሐንስ አያስተዳድርዋቸውም ነበር ማለት ነው። ስለዚህ ዮሐንስ የትግራይ ገዢ ሆነው የተወሰኑ ነበሩ” እንደማለት ስለሚቆጠር፡ ንጉሡ ከቴድሮስ ቀጥለው ትግራይን ብቻ ነበር ያስተዳደሩት ወደ እሚል ቂልነት ይወስደናል ማለት ነው። 

2ኛው- ዶጋሊ ላይ ሳሓጢ ላይ በምሰጣቸው ማስረጃዎች የወሎ የጎጃም የጎንደር ጦሮች የተካፈሉ ሲሆኑ፤ በወቅቱ የንጉሡ አዋጅ 

ጣሊያን ወደ ዶጋሊ ሲጠጋ፡ አዋጁ “የትግራይ ልጅ ሆይ” አይልም፡

የሚለው ኢትዮጵያ ልጅ ሆይ.. ነው። 

“የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልክት  ኢትዮጵያ የተባለች አንደኛ እናትህ እህትህ አውድህ ሚሰትህ ልጅህ መቃብርህ ናት የናት ፍቅር ያውድ ክብር የሚሰት ደግነት………….መሆኑን አውቀህ ተነስ የሚል አዋጅ ባስነገሩት መሰረት ሁሉም ከመላ ግዛታቸው ተሰብስቦ ዘምቶ ዶጋሊ ላይ ከዚያም  በፊት ሳሓጢ (1879) ላይ ጠላት ድል አድርገዋል። የበላይ ግደይ መጽሐፍን አንብቡ።

    ሃቁን ከማየታችን በፊት ለትውስታችሁ እንድያመች የወያኔ ዘፈኖች በክፍል አንድ የጠቀስኩትን አትርሱ።  ያ ውሸት ወያኔዎች በሁለተኛ ጉባኤያቸው ጭምር የሳለፉት መግለጫም ነው።

በታሪክ የተጠቀሱ የሰሜን ጦርነቶች (ከጥንት ጀምሮ) ኢትዮጵያውያን በሙሉ የተካፈሉበት ጦርነት እንጂ ትግሬዎች ብቻቸውን አልተካፈሉበትም። እንኳን ያኔ በባድሜ ጦርነትም ብቻቸውን አልቻሉትም። 

በዘፈናቸውና በሁለተኛ ጉባኤያቸው ያሳለፉት የዓድዋ፤በምኒሊክና በጣይቱ የተመራው ጦር የሚክድ፤ ሽሬ፤እንዳባጉነ እና ሰለኽለኻ፤…. የነበረው ጦር የኛ ነው ይላሉ። ሃቁ ግን  የጎጃም የጎንደር የወልቃይት አርበኞች እነ አዲስ አለማዮህ የተካፈሉበት አንዳንዱ ቦታ “ትግሬዎች” ያልተካፈሉበት ቦታ ሲሆን ጦርነቱ እንደተካሄደና እንዳባጉና ጦርነት በአዛዥነት የመሩት የጎጃሙ ፊታውራሪ ክንፌና በሽሬ ግምባር ለተደረገው ጦርነት ታካፈይ የነበሩት ደራሲ አዲስ አለማየሁ መጽሐፍ “ትዝታ” ማንበብ በቂ ስለሆነ እሱን አልፈዋለሁ። 

ሌላው የአበሻ ጀብዱ የሚለው በጦርነቱ የተሳተፉት ቼክ ሪፑብሊክ ተወላጅ የሆኑት በነዚህ ጦርነቶች እራሳቸው የተካፈሉ ሚስተር አዶልፍ ፓርላክ የጻፉት “ተጫነ ጆብሬ መኮንን የተረጎሙትን ማን እየዋሸ እንደሆነ ማንበብ ግንዛቤ ይሰጣል።

  የደደቢት ዘፋኞች ግን ዓድዋም ሽሬም በዶጋሊ ጦርነቶች በምኑም በየትም “ትግሬ ብቻ” ነው እያሉ ለሚዘፍኑ ዘፋኞቹ ማስረጃ ከዛ በላይ በቂ ነው።

ሦስት ጸሓፈት አቀርባለሁ። አማራው አዲስ አለማዮህ ፤አላቀርብም። ወያኔዎች የአማራ ጸሐፍት አንቀብልም ስለሚሉ፤ አንድ ማስረጃ በሁለት ፈረንጆች የተጻፈ፡ አንድ ከትግሬ ታሪክ ጸሐፊ ፤ አንድ ከወላይታ ታሪክ ፀሐፊ የተጻፉ ሰነዶችን አቀርባለሁ። የአማራ ፀሐፍት እያጣመሙ የትግሬን እየነጠቁ ስለሚሉ፤ ሦሰት የተለያዩ አማራ ያልሆኑ ጸሐፍትን አቀርባለሁ ማለት ነው።  

አሁን ስለ ግብፅ እና ኢትዮጵያ ጦርነት አስመለክቶ “ጉራዕ” ላይ ማን ተከፈለ ወደ እሚለው እንግባ፡     

« ለዚህ የግብፅ ወረራ ምላሽ ዮሐንስ 4ኛ በሞሐመዳውያን ላይ ``የመስቀል ዘመቻ`` አዋጅ አስነገረ። ንጉሡ “ከጎጃምና ከሸዋ” የማጠናከሪያ ኃይል እንዲመጣ አድርጎ ፣ጠቅላላው የሠራዊቱ ቁጥር 60,000 ደርሶ ነበር። ሁለቱ ሠራዊቶች በመጋቢት ወር 1876 ጉራዕ ላይ ተጋጠሙ። ግብፆች ምሽጋቸውን ዙሪያውን በጉድብ ሰንሰለት ስላጠሩት የኢትዮጵያውያኑን ጥቃት ለመከላከል አመችቷቸው ነበር። ከግጥሚያው መጀመሪያ ላይ ስለቀናው ተደፋፍሮ ሙላይ ሐሰን በልምድ የበሰለውና ሽማግሌው ወታደር “ራቲቭ ፓሻ” ተው እያለው ጠላቱን በግላጭ ገጥሞ እደመስሳለሁ ብሎ ከምሽጉ ወጣ። ይህ ውሳኔ ለግብፆች መጥፊያቸው ሆነ። የኢትዮጵያ ወታደር በቁጥሩ ከወራሪው ጦር እጅግ ከፍ ያለ ነበርና የውጊያውን ሰልፍ ጥሶ እየተወረወረ ከጠላቱ ምሽግ ውስጥ ገባ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጊያው ወደ መተላለቅ ተለውጦ የግብፅ ጦር በድንጋጤ ተውጦ ፈረጠጠ። ሙላይ ሐሰን ፓሻ ሩጦ ለማምለጥ ሲሞክር ተይዞ ከንጉሡ ፊት ቀረበ። ንጉሡም ድል የሆነበትን ቀን እንዳይረሳው ሲል “ከክንዱ ላይ ሁለት መስቀል እንዲተኮስበት” አደረገ። በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል የሰላም ውል ከተደረገ በኋላ ከዲቭ እስማኤል ፣ ሙላይ ሐሰን ፓሻና ሌሎችም “በጉራዕ” ጦርነት ላይ ከሱ ጋር የተማረኩትን ከፍተኛ መኮንኖች ማስለቀቂያ ከፍሎ አስፈታቸው።»

(ገጽ 289 እስከ 299፣“የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን፣ጸሐፊዎች፦ አንድርዜይ ባርትኒስኪ እና ዮዓና ምንቴል-ኒየችኮ)

አስቀድሜ እንደገለጽኩት ዮሐንስና አሉላ እያሉ ወያኔዎች የሚጠቅሱዋቸው ኢትዮጵያዊያን መሪዎች ከመፈጠራቸው በፊት የሸዋው አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ከደብረብርሃን ተነስተው “ዱዋርባ” (መንደፈራ) ዋና የማዘዣ ከተማው በማድረግ የግብፅ ማምሉክ ባለሥልጣኖች ጂኦፖለቲካዊ ጥቅምና ግፊት ወኪል በነበረውና በወቅቱም ከአዎስጣጤዎሳውያን አማጺያን ጋር ተሻርኮ  በኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ጉዳይ የራሱን ተፅእኖ ለማሳደር በጀመረው “በዳህላክ -ምፅዋ ሥዩመ ባሕር” ላይ (ገዢ /ሹም/ ማለት ነው) ብርቱ ወታደራዊ እርምጃ ወሰደ።” (ላጵሶ.ጌ ድሌቦ -ገጽ 67 ደራሲው የጠቀሱት ምንጭ “ፋቂሕ”) 

ይቀጥልና  ቱርኮች ጋር፡- ቱርኮች በ1557 እስከ 1589 ለሦስት አሥርታት ከምፅዋና ከሱዋኪን ነስተው በአርኪኮ፤ሓማሴን፤በሠራዬ፤በዱባርዋ፤አከለጉዛይ በቡር በትግራይና በመዘጋ ከተሞች፤ቀበሌዎች አውራጃዎች ላይ የወረራ ጦርነት ከፈተ:: (2)

ቱርኮች በሰሜን ሀገር ወረራ በከፈቱበት ወቅት አጼ ገላውዴዎስ በደቡብ ኢትዮጵያ በአዋሽ-ዝዋይ አካባቢ ከኦሮሞ የምችሌ ሉባ (1554-1562) ጋር ጦርነት ላይ ነበር። በመሆኑም  በ1558 አጼ ገላውዴዎስ በሰሜን የባህረነጋሽ ይስሐቅን ጦር በቱርኮች ላይ አዘመተ፤ በዚህ ሁለቱም ተባብረው በየግምባራቸው  በጠላቶቻቸው ላይ ድል ከተቀዳጁ በሗላ በመጋቢት 1559 በዋጅ ጦርነት አጼው በአዳሉ ኤሚር ኑር ተገደለ። ድንገተኛ ሞት ከሆነ በሗላ ቤተመንግሥቱ በሁለት አንጃዎች ተከፈለ። በዚህ ቀዳዳ ፐርቱጋሎችና ቱርኮች ጣልቃ መግባት ጀመሩ። የገላውዴዎስ ወንድም ሚናስ ዙፋን ወጣ።

ከሚሲዮናውያን ፖረቱጋሎች አገር የቀረበ ግንኙነት በማድረግ ባህረነጋሽ ይስሓቅ የሚናስን ንግሥና በመቃወም  በ1561 የመሳርያና የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት ሲል ባህረነጋሽ  ይስሐቅ ለቱርኮቹ የክፍለ ሃገሩን ግዛት ከምፅዋ እስከ ደባርዋ ድረስ የሚገኘው ቀበሌ ሰጠ። (3) 

ሚናስ ሞተ። ወጣቱ ሠርፀ ድንግል መጣ። አጼ ሰርፀ ድንግል ከሓረሩ እስላማዊ የአዳሉን መለሳይ የተባሉ የጦር ባለሞያዎች ምንደኞችን ቀጥሮ የራስ ሐመልማልን የሥልጣን አንጃ ደመሰሰ። እንዲሁም በሰሜን ባህረነጋሽ ይስሐቅ በ1562-1563 በቱርኮችና በፖርቱጋሎች ድጋፍ በሚናስ ዘመን የጀመረው የሥልጣን በሰርፀ ድንግል ላይም አመፅ ቀጠለበት።

ወያኔዎች ዮሐንስ እረፍት ሳያገኝ ብቸኛ የነገሠ ንጉሥ ነበር የሚሉት ኢትዮጵያን ለዮሐንስና ለሌሎቹ መሰረት ጥሎላቸው የሄደው አጼ ሰርፀ ድንግል በሃዲያ  አዳሎች፤ጉምዞች ፈላሻዎች፤ ዳሞት እንርያ፤ ቢዛሞች፤ በጋፋት፤ በሺናሻ፤ አንፊሎ፤ ጎንጋ፤ በቦጃ… ድል አድርጎ ያለ እረፍት ሁሉንም ‘ጸጥ’ አድርጉ ግብር እንዲገብሩ ያደረገ ንጉሠ ነገሥት ነበር። ወያኔዎች ይህንን አያውቁትም። ካወቁትም እንዳይታወቅ ይደብቁታል።

ያንን ካረጋጋ በሗላ ወደ ሰሜኑ ግዛቱ በመገስገስ በተቀሩ ኢትዮጵያ ግዛቶች የዘመቱ ጦረኞችን ክርስትያን እስላም የአዳሉ የመለሳይ ወታደሮች፤ አዋማ፤ ኦሮሞ የሉባ ወታደሮች በአንድነት ተባብረው ከአፄ ሠርፀ ድንግል ጋር በመዝመት እንዲሁም  እነ “ቀርባን” ፤ አቄትርዝ ጨረቃ፤ጊዮርጊስ ሃይሌ ፤ ቱርክ፤ አፍሮ አይገባ፤ ..ወዘተ የተባሉ ጦረኞዩን ወደ ባሕረነጋሽ ይዞ በመሄድ በባንዳነት ያፈነገጠው ባሕረነጋሽ ይስሓቅና ቱርኮችን ቁጥጥር ሥር ባመድረግ ድል አደረጋቸው። የወቅቱ የአፄ ሠርጸ ድንግል የዘመኑ ዜና መዋዕል ጸሐፊ “ወልደ ሃይማኖት” በዝርዝር ገልጾታል።

እነዚህ “የጨዋ ንጉሳዊ ወታደሮች” (ሪፑብሊካን ጋርድ እንደሚባለው) ከ1557 እስከ 1558 ድረስ በሦስት አሥርታት ውስጥ በተለይ በሓማሴን በሠራዬና በትግራይ ከቱርክ ወራሪዎችና አካባቢ ወኪሎች ጋር ከአሥር በሚበልጡ ጦርነቶች ከውጭና ከውስጥ ሃይሎች ጋር ተዋግተው የአገሪቱን ብሔራዊ ነፃነትና ህልውና ከውጭ ጥፋት አድነው አልፈዋል።  

እንግዲህ ትግሬዎች እኛ ብቻ የሚሉትን ውሃ የማይቋጥር ትምክሕት ሌሎች ነገሥታቶቻችንም ያንን ክፍልና የትግራይን ሕዝብ ከወራሪ እንዴት እንዳዳኑት ማሳያ ነው።

አሁን ደግሞ በትግሬው ምሁር በአቶ በላይ ግደይ አምሐ “ኢትዮጵያ ሀገሬና ትዝታዬ” በሚለው መፅሐፋቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፡

በዚያ ሦስት ቀን በፈጀው ጦርነት ከጠላት ወገን ከአሥራ ሁለት እስከ ሃያ ሺህ (12000-20000) ሃይል የተደመሰሰ ሲሆን 39 መድፍ፤አሥራ አምስት ሺ (15000) ጠመንጃና አርባ ሺ (40000) ግመሎችና በቅሎችመማረካቸውን የሙዚንጀር የብዙ ጊዜ ወዳጅ የነበረው ፍራንዚ ሐሰን ገልጾታል። ዳርዋ እሳት መኻልዋ ገነት የሆንችውን ለምለም ኢትዮጵያን ለመያዝ “ጉንደት” ላይ ጦርነት ገጥመው ወዲያውኑ በመሸነፋቸውና በመደፈራቸው ከፍተኛ ቁጭት ስላደረባቸው እንደ ገና “ጉራዕ” ላይ ጦርነት ገጠመ፡ 

ተደጋጋሚ የጠላት ወረራ ሲመጣበት በአጠፌታ መመለስ ልማዱ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወረራውን ከኢምንት አልቆጠረውም። በጉራዕ ጦር ሜዳ ከአፄ ዮሐንስ ጋር የተሰለፈው ሠራዊት የትግራይ ብቻ ሳይሆን የጎንደር፤የላስታ፤የየጁና የጎጃም ጭምር ነበር። 

ምንም እንኳን በትጥቅና በመሳሪያ ከሠለጠነው የገብፅ ጦር ጋር ተመዛዛኝ ሊሆን ባይችልም የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለው ንቃት፤ ወያኔና ጀግንነት ይልቁንም በነፃነት ቀናዒነቱ ተነሳስቶ አኩሪ ድልን ለማስመዝገብ በቅቷል። (በላይ ግደይ አምሐ ገጽ ኢትዮጵያ ሀገሬና ትዝታዬ 160)

በጉራዕ፤በጉንደት፤በስዋኪን፤በዶጋሊ፤በዓድዋ፤በማይጨው፤መመሳሰሉት ጦርነቶች እና በቅርቡም የትግሬው ወያኔ እና የኤርትራው ሻዕቢያ በጫሩት 70,000 የሚገመት ተጠያቂ የሌለው ሕይወት የበላ የባድሜው የጥላቻ ጦርነት ከሁሉም የኢትዮጵያ ግዛቶች የሚኖር ሕዝብ የተካፈለበት ጦርነት ነበር። 

እንግዲህ ታሪካችን የትግሬ ብቻ ሳይሆን ጦሩ በዚያን ዘመን ኢትዮጵያ ተብላ በምትታወቀው አገር ይኖሩ የነበሩ ዜጎች በጦርነቱ ተካፋይ እንደነበሩ፤ሌሎች መጽሐፍቶች አሉ፤ ላሁኑ ግን ከላይ ለመከራከሪያ ያቀረብኩት የመረጃ ሰነድ ማለትም- 

“የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን፣ጸሐፊዎች፦ አንድርዜይ ባርትኒስኪ-----------------------------------

እና ዮዓና ምንቴል-ኒየችኮ” ተርጓሚ፦ ዓለማየሁ አበበ 2003 )

የኢትዮጵያ የመከራ ሥርዓትና የኤርትራ ጥያቄ  (ዶክተር ላጵሶ ጌ. ድሌቦ)-----------

የአበሻ ጀብዱ የሚባል መጽሐፍ የጻፉት የቼክ ሪፑብሊክ ተወላጅ የሆኑት በነዚህ ጦርነቶች እራሳቸው የተካፈሉ ሚስተር አዶልፍ ፓርላክ የጻፉት “ተጫነ ጆብሬ መኮንን የተረጎሙትን ማን በጦርነቱ ላይ እንደተካፈለ ወይንም  እየዋሸ እንደሆነ ማንበብ ግንዛቤ ይሰጣል።-------------------------

 ኢትዮጵያ ሀገሬና ትዝታዬ (በላይ ግደይ አምሐ)

እነዚህ ከውጭና ከአገር ተወላጆች ምስክርነት የተገኙ ሰነዶች ናቸው።-----------------------------------------------

እንግዲህ ወያኔዎች ለምን ታሪክ ይሰርቃሉ ያሰኘኝ ምክንያት ይህ ነው። ከቱርክ፤ከግብጽ፤ከጣሊያኖች፤ከዱርቡሾች ጋር የተደረጉ ውግያዎች በሙሉ አጼ ዮሐንስ ያስተዳደርዋቸው አካባቢዎች መላው አዋጅ ተደርጎ ኢትዮጵያዊያን የተካፈለበት እንደነበር የትግሬው በላይ ግደይ እና ሌሎቹ መስክረውበታል። የነ ሠርፀ ድንግል ታሪክም ምን እንደሚመስል አይታችሗል፤ የነዘርኣ ያዕቆብም ሌላ ጊዜ አቀርባለሁ።

እኔ የታሪክ ማጭበርብርን ለማጋለጥ ድርሻየን ተወጥቻለሁ ወያኔዎች ውሸታቸውን እንደሚያሰራጩ ሁሉ እናንተም ውሸት ለማጋለጥ በመቀባባል ላላወቁት አድርሱ፤ ድርሻችሁን ተወጡ። እንዝህላልነት ይብቃችሁ!!

አመሰግናለሁ

ጌታቸወ ረዳ

ETHIO SEMAY



No comments: