ኩሊው
የት ብንከስሰው ይሻላል?
ጌታቸው
ረዳ
ETHIO
SEMAY
7/8/22
ዶክተር እንዳንለው ኦነግ እና ወያኔ ያሰለጠኑት የጭፍጨፋ ዶክተር ነው። ኮለኔልም አይደል የወያኔ ኮለኔል ነው። ይኼ የወያኔና የኦነግ “ኩሊ” የት እንክሰሰው?
ወዳጄ ሠዓሊ
ገብረኪዳን አራጋው “አብይ አሕመድን “ኩሉ” ይለዋል። አልፎም “አቶ” ይለዋል። ይህ “አቶ ኩሊ አብይ አሐመድ” አናዳጀም አስገራሚም
የሆነ ኢትዮጵያን ወደ ሲኦል ያስገቧት የወያኔ ቁንጮዎችን ከእስር ፈትቶ
ከየትም ፖለቲካ ንኪኪ ያልሆኑ ምስኪን ወንደሞቼን እና እህቴን አሁንም “የናዚዎቹ የኦሮሙማ ኮንሰንትሬሸን” ማጎርያ ካምፖች ውስጥ እያሰቃያቸው ነው።
እነሱ ባይበቀሉቱም እኔ እንደምበቀለው አላወቀም። እየነካካ ያለው ሰው
ከአገር ከሱዳን ከሱዳን እስከ አሜሪካ ድረስ የመለስን ስርዐትና ጀሌዎች መቀመቅ ያስገባ አክሱማዊው አርበኛ መሆኔን አላወቀም ይመስለኛል።
የኩሊው ስርዓት ተከስሶ መጠለያ እስኪያጣ ካለደርግኩ አምላክ ይታዘበኝ።እንቅልፍም የለም። ይህ እንዳይሆን ግን “አሽቃባጮች” አሉ፤
ካሁን ዕርቅ እየሉ ሊያድኑት እየሰማን ነው።
ኩሊው ኣእምሮ ቢስ ሆኖ እንጂ ‘ከወቀሳ ለመዳን አንኳ” እነ ሰብሓት ነጋ ከመፍታታቸው በፊት ከሥራቸው እንዲባረሩ አድርጎ አስሮ ያሰቃያቸው “ንፁሃን” የትግራይ ተወላጆችን “መጀመሪያ ቢፈታቸው እና ከዚያ የድሮ አለቆቹን ቢለቅ ምን ነበረበት?
ወንድሞቼን እያሰቃያቸው ያለው በኔ ምክንያት መሆኑ አውቄአለሁ። አሁን
ከትግሉ ሸብረክ የለም። አብይና ጀሌዎቹ ተያይዘናል።
ስለ ምሰኪኖቹ ወገኖቼን ካሁን በፊት ብዙ ስላልኩ ስለ እነሱን እዚህ ላቁምና
ስለ ተፈቱት እነ ሥብሓት ነጋና “የጦር አዝማች” የነበረቺው ስንቱን ወጣት ገፍታ ወደ ጦርነት እንዲቀላቀሉ ስትገፋቸው የነበረቺው
“ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የተነሳው የራስዋ በቪዲዮ”፡ ያየናት “ቅዱሳን ነጋን” ለምን እና እንዴት ተፈቱ የሚለው ትንሽ ልበል።
ምስኪኖች
ፈትቶ ኩንታል ተሸክመው እንዲኖሩ ያልፈቀደላቸው ወገኖቻችን አሁንም አስሮ ሲያቆይ እነ ሥብሓት የለቀቀበት ዋናው ከበስተጀርባ ፡
“ሲ አይ ኤ” ትዕዛ እጅ ስላለበት ነው።ይህ ምስጢር እንዴት አወቅክ ብትሉኝ ይህንን ልንገራችሁ።
መጀመሪያ የማስነብባችሁ “ባገኘበት ሣር ፎቶ መነሳት የሚያምረው” የኩሊውን
ንግግር ላስነብባችሁ ከዚያም መቀሌ ሆነው ድርድሩን ሲመሩትና ሲያዙት የነበሩት “የአሜሪካ ማአከላዊ የሥለላ ድርጅት” ምን ይሰራ
እንደነበር ወደ መቀሌ እወስዳችሗለሁ።
መጀመሪያ፤ አብይ አሕመድ ሕዝቡ ሳያውቅ በሕዝቡ ጀርባ እና ፍርድ ቤት
ሳይወስን፤ ፓርላማ ተብየው በማያውቀው እና ባላጸደቀው (ለስሙ ፓርላማ እንበለው ብየ ነው) የሰሜን ፣መከላከያ እዝ ላይ አሸባሪው
እና ወራሪው የህወሓት ሠራዊት ያልተጠበቀ ጥፋት ከፈጸመ በሗላ (በዚህ አጋጣሚ ጥቃት እንደሚፈጽም ጠርጥሬ ነበር_። ትግራይና ኤርትራ
ደምበር ላይ ያለው ሠራዊት ወደ ሌላ ቀጠና እንዲዛወር ሲታዘዝ ወያኔ ሕዝብ አስሰልፎ እንዳይንቀሳቀስ ሲያደርግ ለክፍት እንዳሰበ
በደምብ ገብቶች “ትችት” ልጽፍ ያዘጋጁት መግቢያ ጀምሬ ድንገት አሁን በመላስታውሰው አንድ ነገር ያዘኝ መሰለኝ ‘ጽሑን” በግርድፍ
ትቼ ሳልመለስበት በዛ ቀረ።)
ወታደሩ ድንገተኛ ጥቃት ሲደርስበት፤ ጦርነት ተክፍቶ ወያኔዎች ጫካ ውስጥ
እንዳሉ ከአሸባሪ ጋር አንደራደርም እያለ ሲዋሽ ከርሞ ኩሊው ግን በወታደሩ ጀርባ “የድርድር ሴራ” ይፈጽም ነበር። በሚገርም መዘባረቅ
“ድርድር” አያደርግም እያሉ የሚሉኝ ውሸት ነው “ስደራደር ነበር” እያለ “የዓለም መንግሥታት አንቀው ጀኔቫ እስር ቤት እንዳያስገቡት፤
እባካችሁ እወቁልኝ፤ ስሙልኝ” እያለ በፈርሃት ተወጥሮ “ሲዘባርቅ” ካንደበቱ ይህንን ስሙ (በጽሁፍ ላቅርበው)
“ድርድር
አልተደረገም የሚባለው ውሸት ነው።ድርድር ስናደርግ ነበር። ባለፉት ሁለት ሦስት ሳምንታት ውግያ ላይ እያለን ድርድር ነበር። የዓለም
መንግሥታትም እንዲያውቁት። ይህ ድርድር የተደረገው “ከዶክተር ሙሉ ጋር ነው።ሕጋዊው የትግራይ አስተዳደር ጋር። እርሱ በሚመራ ኮሚቴ
በኩል በዶ/ር ሙሉ ነጋ በኩል ድርድር እንዲካሄድ ሆኗል። ከወንጀለኛ ጋር ድርደር የለም ብለሃል፤ የሚባል ይኼ ስሕተት ነው” እያለ
በመጨነቅ ሲዘባርቅ ነበር።
ይህ ድርድር በሚስጢር ሲካሄድ ካለ አብይ እና ዶ/ር ሙሉ ነጋ የሚያወቅ
አልነበርም (ለዚያ ነው የትግራይ ሰዎች የሆኑ የኩሊው ደጋፊዎች “ሙሉ ነጋን ወያኔ ነው ሲሉት የነበረው፡ እርምጃ እንዳትወስድ ብሎ
ኩሊው ተደራዳሪ አድርጎት ስለነበር”) ብዙ…ያልተነገሩ ጉዶች ይወጣሉ።
በሌላ አሳዛኝ ነገር በጎን በኩል እርሱ ሲደራደር “እነ ኢንጂኔር እምብዛ
በቁሙ አካላቱ ተቆራርጦ ሲታረድ ኩሊው ግን ውስጥ ለውስጥ ወያኔን
“እሽሩሩ” ሲል ነበር።
ሦስተኛው
ሚስጢረኛው ግን አሜሪካኖች መቀሌ ጽ/ቤት ተከፍቶላቸው ደርድሩን ይታዘቡ ነበር ሳይሆን “በመሪነት የድርድሩና የጦርነቱ አዛዦች”
ነበሩ።
ትዝ ይላችሁ እንደሆነ ብዙ ሰው በወቅቱ ልብ ያላለው አንድ ቃለ መጠይቅ
ላስታውሳችሁ። ናትናኤል አስመላሽ ይባላል። የዓድዋ ተወላጅ ነው። በባድሜ ጦርነት ውትድርና ገብቶ ፡ፓራ ኮማንዶ” ሰልጥኖ የዘመተ
ወጣት ነው።
ከወያኔ ጋር ጸበኛ ነው። የአብይ አሕመድ ከፍተኛ ደጋፊ ነው። ትግራይ
ውስጥ ለተፈናቀሉ ወገኖች ለመርዳት ከሚኖርበት አሜሪካ ከበጎ አድራጊዎች ገንዘብ በማዋጣት ወደ ትግራይ መቀሌ ድረስ ሄዶ ዕርዳታ
ሲያከፋፍል የታዘበው ነገር አዲስ አባባ ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት የተናገረውን ላስታውሳችሁ።
“ጦርነቱን የሚመሩት ሲ አይ ኤዎች ናቸው። መቀሌ ውስጥ ጽ/ቤት ከፍተው
ጦርነቱን ይከታተሉታል። መቀሌ ውስጥ እኔ አነጋግሬአቸዋለሁ።ከመቀሌ ወደ አዲስ አባባ አይሮፕላን ላይም አብረን መጥተን እያወራን
በርረናል፡ አግኝቼአቸዋለ…” ይላል ናትናል አስመላሽ።
“ኩሊው አብይ” አሕመድ ግን አሜሪካኖች ገብተውበት መሆናቸውን እያወቀ፤
ለየዋሁ ሕዝባችን ግን “ከሽብርተኞቹ ጋር ድርድር ብሎ ነገር የለም፤ አልደራደርም” እያለ ሲያሞኛችሁ ከርሞ ተመልሶ በድብቅ በወኪሉ
በትግሬው ዓድዋዊው ዶ/ር ሙሉ ነጋ በኩል ከሽብርተኛው ጋር ሲደራደር ነበር።
በሌላ በኩል የገበሬ እህል አጨዳ እና አምበጣ በማባረር ዘመቻ ውሎ “ደክሞት
እንቅልፍ በተኛበት ውድቅት ሌሊት”፤ ድምበር ሊጠብቅ የተመደበን የአገሪቱ ሠራዊት “አርዶ” ሴቶች ሙታንታቸውን ብቻ እንዲለብሱ አስቀርቶ
“ወለል ላይ” እርቃናቸው እንዲተኙ ያደረገ፤ ሠራዊቱ ልብሱን ገፍፎ “እራቁቱ” ወደ ኤርትራ እንዲሸሹ ያደረገ ከአረመኔዎቹ “የትግሬ
ታሊባኖች” ጋር “ድርድር የለም፤ ደርድር የሚባል የለም” ሲላችሁ ከርሞ ይኼው አሜሪካኖቹ ሲመሩት የነበረውን ድርደር ይካሄድ እንደነበር
ነግሮናል።
አሁን እነ ሰብሓት ማን ፈታቸው? ፍርድ አልተፈረደባቸውም። ፍርድቤት ስለ
ፍታቸው አላዘዘም፤ ምክንያቱም መርምሮ ውሳኔ አልሰጠም። ምን ፈታቸው? ኩሊው ግን አይደለም። ፈቺዎቹ “አሜሪካኖቹ- ሲ አይ ኤዎች”
ናቸው።
ኩሊው ትግራይ ውስጥ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን ያውቃል። ስለዚህ
በሱዳኑ መሪ የነበረው “አል በሽርን” በዳርፎር “ምክንያት” አግኝተው
እርሱን አስጨንቀው ደቡብ ሱዳን” እንድትገነጠል ፈርም ወይንም በዳርፎ ጃንጃዊት ሠራዊትህ የፈጸመው ወንጀል “ገመድዋ አንገትህ ላይ
እናጠልቃታለን” ብለው እገዳ አደርገውበት፤ከዚያም ሲጨንቀው “ተስማምቶ ደቡብ ሱዳን” አንድትገነጠል እንዳስፈረሙት ሁሉ፤ የኛው ኩሊም
“ከመጀመሪያ አስከ መጨረሻ “ሲ አይ ኤዎች” የገቡበት ስለሆነ “የበሽር ገመድ” ወደ አንገቱ አንደምትዞር ስለሚያውቅ፤ የ ሲ አይ
ኤ የውስጥ አባሎችና አገልጋዮቻቸው የነበሩት እነ ስብሓት ነጋ ፤ እነ አባዲ ዘሞ ተፈትተዋል።
በዚህ ላይ ሰፊ ማስረጃ አቀርብላችሗለሁ ጠብቁኝ።
ምስኪኖቹ የኔ ወንድሞች እና እህት ግን ምንም በማያውቁት ታፍሰው ሰውነታቸው
ከስተው፤ታመው እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ወንጀለኞቹን ፈትተህ፤ ሲ አይ ኤ ስለማያውቃቸው “ሰለማዊ ዜጎች” አሁንም በኮንስትሬሽን ካምፕ
እየማቀቁ ማድረግ ኩሊው “መነቅነቅ የሌለበትን ግንድ እየነቀነቀ ነው”።
እናንተው ፍርዱ! የትግራይ ታሊባኖች ከሲ አይ ኤ ጋር ግንኙነት ስለነበራቸው
ከነ ወንጀላቸው ሳይፈረድባቸው ሲፈቱ ፤ ምስኪኖች ግን ታስረዋል። ኩሊው የት ብንከስሰው ይሻላል? ሃሎ! ኩሩርርር!!! ይሰማል!!
ቅጣት ለወንጀለኞች! ፍትሕ ለምስኪኖች።
ጌታቸው
ረዳ
ETHIO SEMAY
7/8/22
No comments:
Post a Comment