Thursday, May 17, 2018

Ethiopia should close the Finland & Denmark Embassy in Addis Ababa for violation of Ethics!


Ethiopia should close the Finland & Denmark Embassy in Addis Ababa for violation of  Ethics!

አዲሱ ጠ/ሚኒስተር የዴንማርክ እና የፊንላንድ ኤምባሲ ጽ/ቤት ከአገሩ እንዲያባርር እንጠይቃለን!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)

ኢትዮጵያ ሕዝብ ከማንኛዎቹም አገሮች የተለየ ባሕል እና የሞራል መርህ የሚከተል ሕዝብ መሆኑ ለሺዎች አመታት በዚህ ዓለም የታወቀበት ስነ ምግባር አለው። ከተቀሩት ሕዝቦች ለየት ከሚያደርጉት ባሕሪው አንዱ ግብረሰዶማዊ ስነምግባርን አጥብቆ ይኮንናል።

ኢትዮጵያ የእስልምና እና የክርስትና እምነት ተከታዮች አገር ናት። ሁለቱም ሃይማኖቶች ግበረሰዶማዊ ባህሪ በየእምነታቸው መመሪያ መሰረት አጥብቀው ያወግዙታል። ስለሆነም በመላ ዓለም ግብረሰዶማውያን ቀን ተብሎ በሚከበርበት ሰሞን ኢትዮጵያ ውስጥም የግብረሰዶም ባሕሪ የሚያበረታቱ ሁለት ኤምባሲዎች የግብረሰዶማውያኑን መለያ የሆነው ጨርቅ በኤምባሲዎቻቸው ጽ/ቤት ደጃፍ በማውለብለብ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሕግ እና ባሕል በማንኳሰስ ኤምባሲዎቹ ሊያከብሩዋቸው የሚገባቸው የአገራችን ደምቦች እና የባህል ውሎች በመጻረራቸው ከአገራችን እንዲባረሩ ካልሆነም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ የሆነ ይቅርታ እንዲጠይቁ የኢትዮጵያን ሰማይ ዋና አዘጋጅ ዋሺንግቶን ውስጥ ላለው ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ይህንን ጽሑፍ በግልባጭ አሳውቆታል።
 ከሰላምታ ጋር
 ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com

No comments: