Notice from the Editor;
፩
፬
Though the author of the document is a friend who argued his position to bring a solution on the problems facing Eritrean and Ethiopian people with good intention to trying a peaceful settlement between the two people- I totally disagree with him or with anyone including with some mediocre Ethiopians who wants to settle less than recognition of Ethiopia the legitimate owner of the Red sea ports. If Eritreans want their BS independent, that too is fine, they can live the hell they are living currently, but, hey cant have two sea ports claiming with no legitimate, legal, historical or moral reasons. In fact, we should not settle or recognize Eritrea's independent, because, they did not get their Freedom ("slavery") in a legitimate avenue. They told us, they got their independent through means of force and conspiracy supported by the mercenary TPLF who is ruling Ethiopia currently. So, if force was the tool for their independent- it is only FORCE not a talk that will bring nihilist Eritreans to the table too.
Since their educated class are habitually distorted and liars, nothing will Eritreans understand but force. We are only waiting for nationalist and patriotic Ethiopian leader or leaders to popup from the Ethiopian womb and use force to encounter the force the Eritreans claimed (which was of course a total myth-which fooled the world with empty propaganda - you can see their myth force scared to death to take away Badime as we speak). So, for all Ethiopians to read the perspective of Eritreans I have posted this for your research battle of knowledge. Please read Professor Tesftion Medhane's argument and agree or to disagree with his position. Please recognize his decency and integrity to bring peace to the our people. Do not include him with other total detracted and ignorant Eritrean scholars. He is unique and good nature with good intention towards Ethiopia. (Ethiopian Semay)
ሁለት አገሮች፣ አንድ ማህበረ-ሰብ፤
የኮንፈደረሽን ጐዳና ለኢትዮጵያና ለኤርትራ
ተስፋጽዮን መድሃኔ (ፕሮፈሰር)
ብረመን ዩኒቨርሲቲ፣ ጀርመን
የኢትዮጵያና ኤርትራ ወዳጅነት ኮንፈረንስ
ዋሺንግተን፣ ዲ. ሲ. ሚያዝያ (አፕሪል)
22፡ 2018
ማብራሪያና ምስጋና
የሚከተለው ጽሁፍ የኢትዮጵያና የኤርትራ ወዳጅነት መድረክ ሚያዝያ (አፕሪል) 22 2018 ዓ. ም. በዋሺንግተን
ከተማ ላደራጀው ዓመታዊ ኮንፈረንስ የተዘጋጀ ነው፡፡ በኮንፈረንሱ ያቀረብኩት ንግግር፡ ያኔ እንደገለጽኩት፡ የዚሁ ጽሁፍ አጠር
ያለ ሀተታ ነበር፡፡ ጽሁፉ በሙሉ በተለያዩ ድህረገጾች እንደሚወጣ በንግግሬ ጠቅሼ ነበር፡፡ ባልኩት መሰረት ሙሉው ጽሁፍ
እነሆ፡፡
ይህንን ጽሁፍ በማዘጋጅበት ጊዜ ስማቸው መጥቀስ የማያስፈልግ
ወዳጆቼ አስተያየቶች በመለገስና በሌሎች የተለያዩ መንገዶች ተባብረውኛል፡፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ ወዳጅነት መድረክ ኮንፈረንሱን
አዘጋጅቶ በዚህ ጽሁፍ አማካይነት ሃሳቤን ለማሰራጨት ዕድል ሰጥቶኛል፡፡ ለተባበሩኝ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡
በዚሁ ጽሁፍ ላይ የሰፈረውን ይዘት በሚመለከት ሃላፊነት የምወስደው እኔ ራሴ ብቻ መሆኔን ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡
ተስፋጽዮን
መድሃኔ ብረመን
ዩኒቨርስቲ፤ ጀርመን፡፡ግንቦት
(መይ) 2018
ሁለት አገሮች፡ አንድ ማህበረ-ሰብ፤
የኮንፈደረሽን ጐዳና ለኢትዮጵያና ለኤርትራ
ተስፋጽዮን
መድሃኔ (ፕሮፈሰር)
ብረመን
ዩኒቨርስቲ፣ ጀርመን
በዚሁ የኢትዮጵያና ኤርትራ የወዳጅነት መድረክ የሁለቱ አገሮች
ዝምድና ምን ይሁን የሚለውን ጥያቄ ደጋግመን ጐብኝተነዋል፡፡ በ2009 እና በ2010 በሳንሆዘ ከተማ እኔና ወንድሜ ፕሮፈሰር
ዳንኤል ክንዴ የተሳተፍንባቸው ስብሰባዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ተካሂደዋል፤ ውጤታቸውም አመርቂ ነበር የሚል እምነት አለኝ፡፡
ኤርትራ ተገንጥላ የተለየች አገር ከሆነች አንስቶ ለሁለቱ
አገሮቻችን የሚበጀው ዝምድና ኮንፈደረሽን ነው የሚለውን ዕይታ ሳስተጋባ ነበር፡፡ የኮንፈደረሽንን ሃሳብ የሚያራምዱ ጥናቶችም
በተለያዩ ስብሰባዎችና በጽሁፍ መልክ አቅርቤአለሁ[1]፡፡
የኮንፈደረሽን ሃሳብን የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያንና
ኤርትራውያን ነበሩ፤ ባሁኑ ወቅት ግን ስለ
ኮንፈደረሽን ያለው አመለካከት እየተሻለ መጥቷል፡፡ በመሰረቱ አሁን ስለ ኮንፈደረሽን፡ ገና በቂ ባይሆንም፡ ከበፊቱ የላቀ
ግንዛቤ ያለ ይመስላል፡፡ ኮንፈደረሽን ለሚለው ሃሳብ የነበሩት ዕንቅፋቶች እየደከሙ መጥቷል፡፡
የሁለቱ አገሮች ተነጣጥሎ መኖር ካለው ዕውነታ ጋር የማይጣጣም
መሆኑ ባሁኑ ጊዜ በተግባር እየታየ ነው፡፡ ከአስር ዓመት በፊት ባሳተምኩት አነስ ያለ መፅሃፍ የጠቀስኩት አንድ ፀሃፊ ያለው
ይህንን ነጥብ የሚመለከት ሃሳብ አለ፡፡ ፀሃፊው ኤርትራና ኢትዮጵያ ተለያይተዋል እንጂ አልተፋቱም ሲል መጐተ፡፡ እኔ ግን
የፀሃፊው በጎ መንፈስ ቢገባኝም ነገሩ የተገላቢጦሽ መሆኑን ለማሳየት ሞከርኩ፤ ማለቴ፡ እውነቱን ለመናገር፡ ኤርትራና ኢትዮጵያ
በይፋ ተፋትተዋል፤ ኤርትራ ሉዓላዊ አገር ተብላ፡ ፀረህዝብ ቢሆንም፡ የራስዋ መንግስት አላት፤ ከ1993 አንስታ የተባበሩት
መንግስታት ድርጅት አባል ሆናለች፤ ከብዙ አገሮች ጋርም ዲፕሎማስያዊ ግንኙነት አላት፡፡ በህግ የኢትዮጵያ አካል የሚያደርጋት
ዝምድና አብቅቷል፡፡
ኢትዮጵያና ኤርትራ በይፋ ቢፋቱም በመሬት ላይ
ያለው ዕውነታ የሚመሰክረው በተግባር ያልተለያዩ መሆናቸውን ነው፡፡ ኤርትራውያን ገና በብዛት ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ፤
ከኢትዮጵያውያን ጋር ተሳስረዋል፡ ተዛምደዋል፡፡ በስደት ያሉ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን በወንድማማችነት ይኖራሉ.፤
አንዳንዶቹማ ተጋብተው ትዳር እየመሰረቱ ናቸው፡፡ በባህል ረገድ የነበረው ግኑኝነታችንና ጋራነታችን ያው እንደቀጠለ ነው፡፡
በይፋዊ ፍቺ ምክንያት ኤርትራም ኢትዮጵያም ብዙ ችግር እያሳለፉ ናቸው፤ ይኸም ለራሱ አለመለያየት ነው ማለት ይቻላል፡፡ ከዚህ
ተነስቼ፡ እኔ ሁለቱ አገሮች በተግባር አልተለያዩም ብቻ ሳይሆን፡ እንድያውም ሊለያዩ አይችሉም ማለት እደፍራለሁ፡፡
ኮንፈደረሽን አስፈላጊ ይሁን እንጂ አሁኑኑ
እውን ሊሆን ይችላል ማለት አይደለም፡፡ አሁን ያሉት መንግስታት ለኮንፈደረሽን ፍላጎቱም ሆነ ብቃቱ የላቸውም፡፡ በሁለቱ
አገሮችና ዝምድናቸውን በተመለከተ፡ ቆየት ብዬ እንደምገልፀው፡ መሟላት ያለባቸው ቅድመ-ሁኔታዎች አሉ፡፡
ስለ ኮንፈደረሽን ትርጉም ያለው ግንዛቤ አሁን
የተሻለ ቢሆን እንኳን ገና በቂ አይደለም፡፡ የኮንፈደረሽን ትርጉም ወይም ፅንሰ ሃሳብ በኤርትራና ኢትዮጵያ ሁኔታ ደመቅ ያለ
ተራ ያላቸው ጐኖች አሉት፡፡ ኮንፈደረሽን ምን ማለት ነው? ባጭሩ ሲገለፅ ኮንፈደረሽን ማለት የሁለት ወይም በቁጥር ከዚያ
የበለጡ ሉዓላዊ አገሮች ህብረት (ዩኒዮን) ማለት ነው፡፡ አባል አገሮቹ ለህብረቱ የተወሰነ ሃይል ወይም ስልጣን ይሰጡታል፤
ህብረቱ እነርሱ ካስተላለፉለት በላይ ሃይል ወይም ስልጣን የለውም፡፡
አንዳንዱ ኮንፈደረሽን ለአንድ የተወሰነ የጋራ
ጉዳይ ለማጠናቀቅ የሚቋቋም ትስስር ነው፡፡ ይህ ብዙውን ጊዜ አገሮች ከወራሪዎች ለመከላከል የሚያቆሙት ጊዜያዊ ህብረት ነበር፡፡
የጋራው ችግር - ወራር ይሁን ሌላ - ካቆመ በሗላ ኮንፈደረሽኑ ያበቃል፡፡ እንዲህ ዓይነት ኮንፈደረሽን ወደ ፈደረሽን ይሁን
ወደ ሌላ ዓይነት ውህደት ሊመራ አይችልም፡፡
ሌላው ዓይነት ኮንፈደረሽን ደግሞ ለተወሰነ
ጉዳይ ተብሎ የሚቋቋም ትብብር ሳይሆን በይዘቱ ሰፊ ወይም አጠቃላይ የሆነ ነው፡፡ ጊዜያዊ ሳይሆን ቀጣይ ነው፡፡ ይዘቱ እየጨመረ
ሄዶ የአገሮቹ ዝምድና እያደገ፡ እየሰጠመ እና እየጠነከረ ይመጣል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ኮንፈደረሽን እስከ ፈደረሽን፡ እስከ ሙሉ
ውህደትም ሊደርስ ይችላል፡፡ የዚህ ዓይነት ኮንፈደረሽን አብነቶች በአሜሪካና በጀርመን ታሪክ የታዩት ናቸው፡፡
ፈደረሽን ግን ከኮንፈደረሽን የተለየ ነው፡፡
በፈደረሽን የሚተሳሰሩት አካላት ወይም አገሮች ሉዓላዊ አይደሉም፤ ለማእከላዊው መንግስት ተገዢ (ማለት የበታች) ናቸው፡፡ አገሮቹ በሙሉ ተደምረው የሚያቆሙት አንድ አካል ነው ሉዓላዊው
አገር፡፡
የኮንፈደረሽን ዝምድና በተለያዩ ስሞች ነው የሚጠራው፤ ለምሳሌ
ማህበረ-ሰብ (አውሮጳ)፡ህብረት (አውሮጳ)፡ የነፃ ሀገሮች
ኮሞንወልዝ (ሩሲያና ሌሎች)፡ ሊግ (በተለይ በድሮ ዘመን) ወዘተ፡፡. የዝምድናው ይዘትም ይለያያል፤ አባል አገሮቹ የተስማሙበት
ነው የሚሆነው፡፡ በዘመናችን ግን አብዛኛውን ጊዜ ኮንፈደረሽን ሲባል መከላከያን ውጭ ጉዳይንና አለማቀፋዊ ንግድን በተመለከተ
የጋራ ተቋማትና የጋራ ፖሊሲ ይኖሩታል፡፡ እንዲሁም በአውሮጳ ህብረት ታሪክ እንደታየው የአገሮቹ ድንበሮች በበለጠ ክፍት እየሆኑ
መጥተው ዜጎቹ በተዛመዱት አገሮች ሁሉ ሊኖሩ፡ ሊሰሩ፡ ሊነግዱ፡
እና ንብረት ሊያፈሩ ይችላሉ ማለት ነው[2]፡፡
የአንድ ኮንፈደረሽን ግብ ዝምድናው እያደገ መጥቶ በሂደት እስከ
ሙሉ ውህደት መድረስ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ግን ግቡ ምን እንደሆነ በስምምነቱ ይጠቀሳል ማለት አይደለም፡፡ አንዳንዴ ግቡ ምን
እንደሆነ ሳይጠቀስ ከይዘቱ መገንዘብ ይቻላል[3]፡፡
ኮንፈደራላዊ ዝምድና አስተማማኝ ጠንካራና ታዳጊ
የሚሆነው የአወቃቀሩ ሂደት ህዝባዊ መሰረት ያለው ሲሆን ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ኮንፈደራላዊ ዝምድና በህዝብ ፍላጎት ላይ
የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ ይህ ማለት ባጭሩ ኮንፈደረሽን ማቋቋም የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት አንድ ክስተት ወይም
ሁኔታ ነው፡፡ ህዝቡ ይህንን መብት የሚገለገልበት ደግሞ ብዙውን ጊዜ በረፈረንደም ወይም ህዝበ-ውሳኔ ነው፡፡
፪
የራስን ዕድል በራስ መወሰን ማለት ምንድን
ነው? ይህ ማለት በአንድ ጉዳይ ህዝቡ ይጠቅመኛል ብሎ የሚያምነውን ሁናቴ ይገልጻል ማለት ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ መታወቅ
ያለባቸው ሁለት ነጥቦች አሉ፡፡
ይህንን ነጥብ በበለጠ ለመረዳት በዋና ግብ
ወይም ራዕይና በስትራተጂ መሃከል ያለውን ዝምድና ማብራራት ያስፈልጋል፡፡
ዋና ግብ ወይም ራዕይ ማለት፡ በቀላል
አነጋገር፡ የመጨረሻው ወይም መሰረታዊ ዓላማ ማለት ነው[4]፡፡
ይኸውም የህዝቡን ኑሮ ወይም የአኗኗር ሁኔታ ማሻሻልና ማሳደግ፤ በአጭሩ ሁለንተናዊ የህይወት እርካታ ነው፡፡ ይህ ሰው ሲባል
በህይወት እንዲሟላለት የሚያስፈልግ ሁሉን የሚመለከት ሆኖ፡ ማህበረ ኤኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ እና ሰብአዊ መብቶችን በሙሉ፡ ከሁሉም
በላይ በህይወት የመኖር መብትን ያካተተ ነው፡፡ ይህ አንድ ሰው ለጤናማ ህይወት የሚፈለገው ሁሉ እንዲሟላለት፡ ቤተ ሰብ
ለመመስረትና ለመደሰት፡ ደህንነቱ እንዲጠበቅ፡ የንብረት ባለቤት የመሆን፡ የመማር፡ የመናገር የመምረጥ የመመረጥና የመንቀሳቀስ መብቶቹን ወዘተ. ያጠቃለለ ነው፡፡
ስትራተጂ ወይም ብልሃት ማለት ግን የመጨረሻ
ግቦችን ለማሟላት ያገለግላል ተብሎ የተወሰነ ሁናቴ ማለት ነው[5]፡፡
ለምሳሌ የህዝቡ ምርጫ አንድነት ከሆነ አንድነቱ የመጨረሻ ግብ አይደለም፤ ግቦቹን ለማሟላት የሚያገለግል ስትራተጂ ወይም
የተመረጠ ብልሃት ብቻ ነው[6]፡፡
እንደዚሁም መገንጠል እና ተገንጥሎ ሉዓላዊ አገር መሆን አንድ ሰትራተጂ ወይም ብልሃት ነው፡፡ ይህ ስትራተጂ ሲመረጥ የመጨረሻ
ግቦችን ያሟላል ተብሎ ስለታመነበት ነው ወይ መሆን ይገባል፡፡
ስለዚህም ሉዓላዊነት ጨርሶ የማይነካ ወይም
የማይደፈር ነው ማለት አይደለም፡፡ ሱዳናዊው ምሁር፡ ፕሮፈሰር ዓብዱላሂ አን ናዒም፡ እንደፃፈው ሉዓላዊነት “በቀላሉ ሊደፈር
ወይም ሊጣስ አይገባም”፤ ነገር ግን ከበስተጀርባው ያለውን ግብ ለማጨናገፍ ማገልገል የለበትም[7]፡፡
በሌላ አነጋገር፡ በሉዓላዊነት ስም መንግስታት ህዝቦቻቸውን መጨቆንና በማንኛውም ረገድ መጉዳት አይገባቸውም፤ ይህንን በማድረግ
የሉዓላዊነትን መሰረታዊ ግብ ሲያጠቁ ሌሎች መንግስታት የህዝቦቹን መብት ለማስከበር የሚደረገውን ጥረት ቢደግፉ ሉዓላዊነትን
ጥሳችሗል ተብለው አይወቀሱም፡፡
2.
የተመረጠው
ስትራተጂ - ለምሳሌ መገንጠል - በሂደት ግቡን የማያሟላ ወይም ለማሟላት የማይችል ሆኖ ከተገኘ፡ ወይም ሁኔታው ተለውጦ
ዝምድናው መስተካከል አለበት ከተባለ ሊሻሻል ወይም ሊለወጥ ይችላል፤ ይህ ማለት እንደገና ረፈረንደም ተካሂዶ ይሁን ወይም በሌላ
መልክ ህዝቡ ፍላጎቱን መልሶ ይገልጻል ማለት ነው፡፡
ከስትራተጂ ጋር በተያያዘ ነፃነት - ማለት
ፖለቲካዊ ነፃነት - የሚለውን ፅንሰ-ሃሳብ መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ ይህንን ፅንሰ-ሃሳብ በተመለከተ የተሳሳተ ግንዛቤ አለ፡፡
ብዙ ወይንም አብዛኛው ያገራችን ሰው ነፃነት ሲባል ከመገንጠል ጋር ብቻ ያያይዘዋል፡፡ ሙሉ አንድነት፡ ፈደረሽን ወዘተ. የህዝቡ
ፍላጎት ቢሆንም በልማድ ነፃነት ተብሎ አይገለፅም፡፡ ይህ መሰረታዊ ስህተት ነው፡፡ አንድ አገር ወይም ህዝብ ከሌሎች ጋር
የሚኖረውን ዝምድና በተመለከተ ነፃነት ሲባል ህዝቡ በሙሉ ፍላጎት የመረጠው ወይም የተቀበለው ሁናቴ (status) ማለት ነው፡፡ ህዝቡ ያለ ምንም ተፅእኖ ወይም ማጭበርበር የመረጠው
ወይም የተቀበለው አሀዳዊ ውህደት ይሁን ፈደረሽን ይሁን ኮንፈደረሽን ይሁን ወይንም መገንጠል ሁሉ ፖለቲካዊ ነፃነት ነው፡፡
አንድነት ሲባል መልኩ አሃዳዊ ይሁን ፈደራላዊ፡ እንደ ባርነት አድርጎ ማቅረብ ትልቅ በደል ነው፡፡ እንዲህ ከሆነማ የስኮትላንድ
ህዝብ ከጥቂት ዓመታት በፊት በነፃ ረፈረንደም መገንጠልን ተቃውሞ ከእንግሊዝ አገር ጋር በአንድነት ለመቀጠል በመወሰኑ ባርነትን
መረጠ ሊባል ነው፡፡ እንደዚሁም የኮቤክ ህዝብ ደጋግሞ በነፃ ረፈረንደም መገንጠል አንፈልግም ብሎ ከካናዳ ጋር በአንድነት
መቀጠሉ ባርነትን መረጠ ሊባል ነው፡፡
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ዋናው ጥያቄ
የተመረጠው ስትራተጂ በህዝቡ ነፃ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነው፡፡ ህዝቡ ያለ ምንም ተፅእኖ ወይም
ማጭበርበር የመረጠው እስከሆነ ድረስ ማንኛውም ውጤት ነፃነት ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ህዝቡ በተፅዕኖ ወይም በማታለል ወይም
ተገድዶ የተቀበለው ከሆነ አንድነት ይሁን መገንጠል ነፃነት አይደለም፡፡
ስትራተጂ የመጨረሻውን ግብ ለማሟላት
የሚያገለግል ብልሃት ነው ከሚለው ሃቅ ተነስተን ስለ ኮንፈደረሽን ልንገነዘበው የሚገባ መሰረታዊ ነጥብ አለ፡፡ ኮንፈደረሽን
-ለተወሰነ ጉዳይ የሚቋቋም ጊዜያዊ ትብብር ዓይነቱ ካልሆነ በስተቀር- በይዘት ባለበት የሚረጋ ወይም የማይለወጥ አይደለም፡፡
ይሻሻላል፤ ይቀየራል፡፡ አንዳንዱማ በየጊዜው የሚታደስ ኮንፈደረሽን ነው[8]፡፡
Renewable
confederation ይባላል፡፡ ለምሳሌ
የኮንፈደረሽኑ ዕድሜ አምስት ዓመት ነው ተብሎ ይደነገጋል፡፡ ይህ ግን ከአምስት ዓመት በሗላ ግንኙነቱ ያከትማል ማለት
አይደለም፡፡ ይህ ማለት ከአምስት ዓመት በሗላ የኮንፈደረሽኑ ዝምድና ምን ያህል እንዳገለገለ፡ እንደስትራተጂ ዋናውን ግብ ወይም
ራዕይ ለማሟላት ምን ያህል እንደረዳ ይገመገማል ማለት ነው፡፡ በዚሁም መሰረት የኮንፈደረሽኑ ይዘት ይሻሻላል፡ ያድጋል፡፡ ህዝቡ
እንደገና በነጻ ረፈረንደም የታደሰውን ኮንፈደረሽን ወይም ያጸድቃል ወይም ይቃወማል፡፡ ረፈረንደም በየጊዜው እየተደጋገመ
ኮንፈደረሽኑ ፈደረሽን እስከ መሆን ድረስ ሊያድግ ይችላል፡፡ የአውሮጳ ህብረት ይህንን ሂደት ተከትሎ ነው አያደገ መጥቶ አሁን
ፈደረሽን ለመሆን ተቃርቦ ያለው፡፡
በሌላው በኩል ደግሞ አንድ አባል አገር
ከኮንፈደረሽኑ በቂ በሆነ መጠን አልተጠቀምኩም ብሎ ከህብረቱ ሊወጣ ይችላል፡፡ ለምሳሌ እንግሊዝ አገር በ1973 የአውሮጳ
ህብረት አባል ሆነች፤ ባለፈው ዓመት ደግሞ ረፈረንደም ተካሂዶ ጥቅምዋን በበለጠ ለማራመድ ብላ ከህብረቱ ወጣች፡፡ ይህ ሊሆን
የቻለው ኮንፈደረሽን የሉዓላዊ አገሮች ህብረት በመሆኑ ነው፡፡
፫
እንኳንስ ኢትዮጵያና ኤርትራ የአፍሪቃ ቀንድ
አገሮች በሙሉ በኮንፈደረሽን ሊተሳሰሩ ሁኔታቸው ያስችላል የሚል አስተያየት ያላቸው ምሁራን አሉ፡፡ በአፍሪቃ ደረጃም
ኮንፈደረሽን ቢያንስ እንደ ራዕይ ይታሰባል[9]፡፡
በተጨባጭ ኮንፈደረሽንን አስመልክቶ ውይይት የተካሄደበት ጉዳይ ግን የደቡብ ሱዳን ጥያቄ ነበር[10]፡፡
ሞዋቹ ዶክ. ጆን ጋራንግ የኮንፈደረሽን ስርዓት ለሱዳን በጠቅላላ መፍትሄ ይሆናል የሚል አቋም ነበረው፡፡ በቂ ድጋፍ አላገኘም[11]፤
ስለዚህም በረፈረንደም ሂደት ደቡብ ሱዳን ተገነጠለ፡፡
ኮንፈደረሽን በቀጠናችን ምን ያህል ስኬታማ
ይሆናል በሚል ጥያቄ ላይ የሃሳብ ልዩነት ሊኖር ይችላል፡፡ አንድ ነገር ግን ግልፅ ነው፡፡ ከአፍሪቃ ቀንድ አገሮች ሁሉ
በኮንፈደረሽን ለመተሳሰር ታሪካቸውና ሁኔታቸው በእጅጉ የሚፈቅድላቸው ወይም የሚያስችላቸው ኢትዮጵያና ኤርትራ ናቸው፡፡
በጂኦግራፊያዊ አቀማመጥና ባላቸው የተፈጥሮ ፀጋ እርስ በርሳቸው የሚፈላለጉ ወይም ተደጋጋፊ (ኮምፕሊመንታሪ) ናቸው፡፡ ለምሳሌ
ኢትዮጵያ መሬትና ውሃ ሲኖራት፡ ኤርትራ ደግሞ አስፈላጊ የሆኑ የባህር በሮች አሉዋት፤ በጠቅላላው አነጋገር ህዝቦቹ አንድ ዘር
ወይም ነገድ ናቸው፤ ባህሎቻቸው በአብዛኛው አንድ ካለበለዚያ እጅግ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ በሁለቱ አገሮች ዋናዎቹ ሃይማኖቶች
ክርስትናና እስልምና ናቸው፤ በሁለቱም የክርስትያኑና የእስላሙ ቁጥር ተመጣጣኝ ነው፡፡ ድንበሮቻቸው አውሮጳዊ ቅኝ ግዛት
የፈጠረው ነው፤ ሁለቱ አገሮች “የነገድ ወይም የባህል ክልሎች” አይደሉም፡፡ ህዝቦቹ ታሪካቸው በአብዛኛው አንድ ነው፤ እርስ
በርሳቸው የተዋወቃሉ፡ ይግባባሉ፤ ለዘመናት አብረው ኖሯል፡ ተዛምዷል ተዋልደዋል፡፡
እነዚህ ሁሉ ኮንፈደረሽንን የሚቻል የሚያደርጉ
ናቸው፡፡
በተቀራኒው ደግሞ ለኮንፈደረሽን ዕንቅፋት
የሚሆኑ ወይም ኮንፈደረሽንን አስቸጋሪ የሚያደርጉ ነገሮች አሉ፡፡ አንዳንዱን ለመጥቀስ፤
- የኮንፈደረሽንን ራዕይ - በኢትዮጵያና ኤርትራ መሃከል ይሁን በአፍሪቃ ቀንድ ደረጃ - የሚያራምድ ሃያል ወይም በህዝቦቹ ተቀባይነት ያለው መሪ ይሁን ንቅናቄ የለም፡፡
- ይህንን ጥያቄ በተመለከተ በኢትዮጵያና በኤርትራ ልሂቃን መሃከል በቂ መግባባት የለም፡፡
- እያንዳንዱ አገር ከኮንፈደረሽኑ እንዴትና ምን ያህል ይጠቀማል በሚለው ጥያቄ ላይ አለመግባባት ያለ ይመስላል፡፡
- አገሮቹ ወይም መንግስታቱ ስለሉዓላዊነታቸው - እያነሰ ቢመጣም - ገና እጅግ ቀናተኞች በመሆናቸው ለኮንፈደራላዊ ውህደት የተወሰነ ስልጣን ማስረከብ በሚለው ሃሳብ ይሰጋሉ፡፡
- አገሮቹ መረጋጋት ይጐድልባቸዋል፡፡ ኤርትራ እጅግ የተጠላ መንግስት የሚቆጣጠራት የተንኰላሸች አገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ በዚሁ ጊዜ የተቃውሞ ንቅናቄዎች ያየሉባት፡ ጽናቱ የሚያስተማምን ህዝባዊ ተቀባይነት ያለው መንግስት ገና የሌላት፡ የመገነጣጠል አደጋም ያንጃበበባት አገር ናት፡፡
- በአሁኑ ጊዜ በሁለቱ አገሮች - በተለያየ መጠን ቢሆንም - ከባድ የዲሞክራሲ ዕጥረት አለ፤ ለመረጋጋት ጉድለቱ ዋና ምንጭም ይሀ ነው፡፡
እነዚህ ችግሮች ይኑሩ እንጂ ኮንፈደረሽን
የሚፈለግና ለወደፊቱም የሚቻል ነው፡፡ እንድያውም ያሁኑ ወቅታዊ ዕውነታ ኮንፈደረሽን በኢትዮጵያና በኤርትራ መሃከል አማራጭ
የሌለው አስፈላጊ ዝምድና መሆኑን ነው የሚያመለክተው፡፡
1.
ኢትዮጵያም ኤርትራም የጎሳ ፖለቲካና ተዛማጅ ችግሮች ካስከተሉት ቀውስ የተነሳ የመገነጣጠል አደጋ አለባቸው፡፡ በኢህአዲግ ወሳኝ
ሚና የተነደፈው ህገ-መንግስት በሚፈቅደው መሰረት ወያኔ ትግራይን አስገንጥሎ ከኢሳያስ መንግስት ጋር ሆኖ የትግራይ-ትግርኚ
አገር የመመስረት የተደበቀ አጀንዳ እንዳለው ለዓመታት በተደጋጋሚ የተፃፈበት ነው፡፡ ይህ ወያኔ ኢትዮጵያን ለመግዛት
በማይችልበት ሁኔታ ሲገባ የሚስበው ካርታ አሁኑኑ ለብዙ ታዛቢ ግልፅ እየሆነ መጥቷል[12]፤
አጀንዳው በሚተገበርበት ጊዜ ኢትዮጵያም ኤርትራም ይገነጣጠላሉ ማለት ነው፡፡
ኮንፈደረሽን
የመገነጣጠልን አደጋ በማስቆም ላይ ትልቅ ሚና ይኖረዋል፡፡ በኢትዮጵያና በኤርትራ መሃከል የሚቋቋመው ኮንፈደረሽን አቅጣጫው
አንድነታዊ ነው፡፡ ጨርሰው በህግ የተለያዩ ሁለት አገሮች በኮንፈደረሽን መተሳሰር ሲጀምሩ ወደ አንድነት እየመጡ ናቸው፡፡
በሁለቱ አገሮች መሃከል የሚሰፍነው የፖለቲካ አየር የአንድነት ሆኖ በውስጣቸው ባለው የህዝቦች ወይም ብሄሮች ግንኙነት ላይም
እንድምታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ አነጋገር ኮንፈደረሽኑ የብሄሮች ዝምድናን በተመለከተ አርአያነት ይኖረዋል፡፡ የመለያየትንና
የመገንጠልን ስነ-አእምሮና አዝማሚያዎች እያዳከመ መቀራረብንና ወንድማማችነታዊ ዝምድናን ያበረታታል፡፡ ስለዚህ ኮንፈደረሽን
ለሁለቱ አገሮች ቀጣይ ህልውና አስፈላጊ ነው ማለት ይቻላል፡፡
ኮንፈደረሽን፡ ከሁለቱ አገሮች አልፎ በቀጠናው፡
እንዲያውም በአፍሪቃ አህጉር በጠቅላላ አዎንታዊ እንድምታ ይኖረዋል ማለት ይቻላል፡፡ ኮንፈደረሽኑ በደንብ ስራ ላይ ከዋለ፡
ሁለቱን አገሮች ያበለፅጋል፡ ያሳድጋል፡፡ ይህም ሲሆን ልዓላዊነታቸው ይጠነክራል፡፡ በዚሁ ወቅት ብዙ የአፍሪቃ አገሮች በተግባር
እንደገና ቅኝግዛት እየሆኑ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ በኮንፈደረሽን ተሳስረው በመጠንከር ሉዓላዊነታቸውን በማውለብለብ
ለአፍሪቃ ኩራት ተስፋና አብነት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ስለ ኮንፈደረሽን በኢትዮጵያውያንና
በኤርትራውያን በኩል ከባድ የአመለካከት ችግሮች አሉ፡፡ እነዚህን ችግሮችና ዕንቅፋቶች ከ10 ዓመት በፊት ባሳተምኩት መጠነኛ
መፅሃፍ[16]
በሰፊው ገልጫቸዋለሁ፡፡ በዚሁ ፅሁፍ ዋናዋናዎቹን አጠር አድርጌ እገልፃለሁ፡፡
በኢትዮጵያውያን በኩል ከሚሰተዋሉት ችግሮች
አንዳንድ አብነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- ኤርትራ አንዴ መገንጠልን መርጣለች፤
በኮንፈደረሽን ይሁን በሌላ መልክ እንደገና መዛመድ አያስፈልገንም የሚሉ ኢትዮጵያውያን - ቁጥራቸው እያነሰ ቢመጣም - ገና
አሉ፡፡ እንዲህ የመሰለ አመለካከት በመገንጠል የተቋጨውን የተወሳሰበ የኤርትራ ጉዳይ - በተለይ ስነ-ኣእምሮአዊ ጐድኑን -
በሚገባ ያላጤነ ይመስለኛል፡፡ ጦርነት እኮ ደስ የሚል ነገር አይደለም[17]፡፡
አንድ ህዝብ የትጥቅ ትግል የሚያካሂደው ወዶ ሳይሆን ተገዶ ነው፡፡ የኤርትራን ንቅናቄ ያነሳሱት በአፄው ዘመንና ከዚያም በሗላ
የተደረጉትን የፖለቲካ ስህተቶች ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡
ብዙዎች እንዲህ አመለካከት ያላቸው፡ ሌሎችም፡
አስተዋይና አገር-ወዳድ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ጨምሮ፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የወደብ ጉዳይ፡ በተለይ ዓሰብን በተናጠል፡ ያነሳሉ[18]፡፡
ለኔ እንደሚመስለኝ፡ አንዴ ኮንፈደረሽኑ ይጀመር እንጂ ይህ ጉዳይ አከራካሪ አይሆንም፡፡ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ያሉት
አለመግባባቶች ኮንፈደረሽኑ ከተቋቋመ በሗላ የሚፈቱበት ዘዴዎች ይፈጠራሉ፡፡ ለነገሩማ አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፋዊ
ህግ መሰረት ዓሰብን ብቻ ሳይሆን ምፅዋንና ሌሎች ወደቦችን ለመጠቀም የሚያስችላት መብት አላት፡፡ ችግሩ ኤርትራ ውስጥ ይህንን
መብት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ጨዋ ጤነኛና ለህግ ተገዢ የሆነ መንግስት የሌለ መሆኑ ነው፡፡
- ኤርትራ አንዲት ድሃ አገር ናት፤ እኛ ይችን
አገር ማዳን የለብንም የሚሉም አሉ፡፡ አንዳንዱማ ኤርትራ ያልተሳካላት-አገር (failed state) ናት ይላል፡፡ እርግጥ
ኤርትራ በአሁኑ ጊዜ ለህዝብዋ ስቃይ ናት፡፡ ከዚህ ነጥብ ጋር በተያያዘ ግን መታወቅ ያለባቸው ሁለት ነገሮች አሉ፡ 1. የወቅቱ
የኤርትራ ችግር አስመራ ያለው መንግስት የፈጠረው ነው፡፡ የኤርትራ ህዝብ ታታሪና ሰራተኛ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ በ90ዎቹ
መጀመርያ ታጥቆ ተነስቶ እንደነበረ ብዙ የተዘገበበት ነው፡፡ 2. ኤርትራ በአሁኑ ጊዜ የተንኰላሸች አገር መሆንዋን
እቀበላለሁ፡፡ ይህ ሁኔታ ግን ኮንፈደረሽንን አላስፈላጊ ሳይሆን በበለጠ ጠቃሚና ተፈላጊ ነው የሚያደርገው፡፡ ለኢትዮጵያ
የሚበጀው ኤርትራ ከዚሁ የድህነት እና የውድቀት ሁኔታ ብትወጣ ነው፡፡ ሁለቱ አገሮች ርዝመቱ ሺ ኪሎመተር የሆነ የጋራ ድንበር
ያላቸው ጎረቤቶች ናቸው፤ ኤርትራ የተንኰላሸች ወይም ያልተሳካላት አገር ብትሆን ለኢትዮጵያ አደገኛ ነው፡፡ ኤርትራ ከተንኰላሸች
ህዝብዋን በሀይል የምታሽቆጠቁጥና የምታሰቃይ ግፈኛ ሥርዓት (fierce state)[19]፡ብቻ
ሳይሆን ቀጠናውን የሚያውኩ ወረበሎች እምብርትም ልትሆን ትችላለች፡፡ ስለዚህ ኮንፈደረሽኑ ኤርትራን ከመንኰላሸት ቢያድናት
ለኢትዮጵያ ጠቃሚ ነው፡፡
- ሌላው ነጥብ ደግሞ ኮንፈደረሽን ኤርትራን
ነው እንጂ ኢትዮጵያን አይደለም የሚጠቅመው የሚል ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በ90ዎቹ መጀመርያ ላይ ኤርትራ ኢትዮጵያን
እንደበዘበዘች ይጠቀሳል፡፡ በዚያን ጊዜ የኢሳያስ መንግስት ከኢትዮጵያ ብዙ ሃብት እንደዘረፈ ሀቅ ነው፡፡ ይህንን በተመለከተ
መታወቅ ያለባቸው መሰረታዊ ነገሮች አሉ፡፡ 1. በዚያን ጊዜ ይሁን ከዚያ በሗላ በሁለቱ አገሮች ኮንፈደረሽን አልነበረም፡፡
ስለዚህ የተደረገውን ብዝበዛ የኮንፈደረሽን አብነት አድርጎ ማቅረብ ትክክል አይደለም፤ ቅን አቀራረብም አይመስለኝም፡፡ 2. ቅሚያው እንዲፈጸም ያስቻለ
መለስና ኢሳያስ ሲመሩት የነበረው በወያኔና በሻዕብያ መካከል የነበረው ሽርክና ወይም ጓዳዊ ዝምድና ነው፡፡ ከኮንፈደረሽን ጋር
የሚያገናኝ ምንም የለውም፡፡ የማቀርበው ያለሁት የኮንፈደረሽን ሃሳብ በአገሮቹና በህዝቦቹ እኩልና ፍትሃዊ ዝምድና ላይ
የተመሰረተ ነው፡፡
እርግጥ ነው፡ ክኮንፈደረሽኑ በተወሰነ ረገድ
አንዳቸው በበለጠ ሊጠቀም ይችል ይሆናል፡፡ ይህ ግን ችግር አይደለም በመሰረቱ ሌላውም የሚጠቀም እሰከሆነ ድረስ፡፡ ለምሳሌ
ኢትዮጵያ በበለጠ ብትጠቀም ችግር የለውም፤ነገር
ግን ኤርትራም ያነሰም ቢሆን መጠቀም አለባት፡፡ ችግር የሚኖረው አንዳቸው የሚጠቀም፡ ሌላኛው ደግሞ የማይጠቀም ሲሆን ነው፡፡
- አንዳንዶቹ ደግሞ የባድመን ጦርነትንና ሌሎች
የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ያበላሹ ችግሮችን በማስታወስ ኤርትራ ጠበኛና ወራሪ ናት፡ ስለዚህ ከኤርትራ ጋር ኮንፈደረሽን
አያስፈልግም ይላሉ፡፡ ክሱ ፈጽሞ መሰረተ-ቢስ ባይሆንም፡ ኮንፈደረሽንን ላለመቀበል ፈጽሞ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡
መረሳት የሌለበት አንድ ነጥብ አለ፡፡
ኮንፈደረሽኑ የሚጀመረው አሁን ሳይሆን በሁለቱ አገሮች ዲሞክራስያዊ ወይም ህዝብ የተቀበለው መንግስት ሲቋቋም ነው፡፡ አንዴ
በኤርትራ ህዝባዊ መንግስት ከተቋቋመ አገሪቱ ቢያንስ ለራሷ ጥቅም ስትል ከጎረቤቶችዋ ጋር ሰላማዊና የትብብር ዝምድና እንደምትመርጥ
ጥርጥር የለውም፡፡
በኤርትራውያን በኩልም የተሳሳቱ አመለካከቶች
አሉ፡፡ ከዋናዎች አንዳንዱ የሚከተሉት ናቸው፡፡
- ብዙ ኤርትራውያን በፈደረሽንና ኮንፈደረሽን
መሃል ያለውን ልዩነት አያውቁም፡፡ ስለዚህ ልክ ፈደረሽንን እንደሚቃወሙ ኮንፈደረሽንንም ይቃወማሉ፡፡ አስታወሳለሁ፡ ስለ
ኮንፈደረሽን መፅሃፍ ባሳተምኩበት ወቅት ብዙ ኤርትራውያን አሁን ደግሞ ፈደረሽንን እንቀበል እያለን ነው ብለው ረግመዉኛል፡፡
በነገራችን ላይ ፈደረሽንን የሚቃወሙት “ፈደረሽን” ሲባል የሚያስታውሱት ያ በአፄ ሃይለስላሴ ዘመን የነበረውንና የፈረሰውን
አውቶኖሚ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ኮንፈደረሽን ከፈደረሽን የተለየ መሆኑን ማስተማር ሊኖርብን ነው፡፡
- አንዳንድ ኤርትራውያን ደግሞ በኮንፈደረሽን
ዝምድና ኢትዮጵያን ልናምናት አንችልም፤ ድሮ ፈደረሽኑ እንዲፈርስ እንዳደረገች ሁሉ አሁንም ከኤርትራ ጋር ስትነፃፀር ትልቅና
ሀያል በመሆንዋ ኤርትራን ልትውጣት ትችላለች ይላሉ፡፡ ይህ ፍርሃት መሰረተ-ቢስ ነው፡፡ የድሮውን ፈደረሽን በማፍረስ ምን ያህል
እንደከሰሩ ኢትዮጵያውያን ያውቃሉ፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ሁሉን የሚወክል ህዝባዊ መንግስት ስታቋቁም ከኤርትራ ጋር የሚኖራትን
በህግ የተመሰረተ የኮንፈደረሽን ቃል ኪዳን ለማክበር ብቃት እንደሚኖራት ጥርጥር የለውም፡፡
- ኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላታችን ናት ብለው
የሚከራከሩ አንዳንድ ኤርትራውያንም አሉ፡፡ ይህ አመለካከታቸው በጣም የተሳሰተ ነው፡፡ በፖለቲካ እንኳንስ እንደ ኢትዮጵያና
ኤርትራ በመሰሉት ወንድማማች ህዝቦች፡ በታሪክና በባህል በተራራቁ ሀገሮች መሀከልም ቢሆን ቋሚ ወይም ነዋሪ ጥላቻ የሚባል
የለም፡፡ እንዲያውም ጠላቶች የነበሩ አገሮች ወዳጆችና ተባባሪዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ በታሪክ ብዙ ጊዜ ታይቷል፡፡ የፈረንሳይና
የጀርመን ታሪክና ያሁኑ ዝምድና አንድ አብነት ነው፡፡
- ታሪክን በተመለከተ ብዙ ኤርትራውያን
የተሳሳተ አስተሳሰብ አላቸው፡፡ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን - በተለይ የደጋው ኤርትራውያን - ረጅም የጋራ ታሪክና የተሳሰረ
ባህል እንዳላቸው አያውቁም ወይም ይክዳሉ፡፡ ሌላውስ ይቅርና ኤርትራውያን ለኢትዮጵያ ነፃነትና ዕድገት ያደረጉት አሰተዋፅኦ ምን
ያህል ታላቅ መሆኑን እንኳን አያውቁም፡፡ ይህ ከባድ ጉድለት ነው፡፡ የኤርትራ ልሂቃን ይህንን ጉድለት ለማረም ብዙ ጥረት
ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- በኤርትራውያንና በኢትዮጵያውያን በኩል ባሁኑ
ጊዜ የሚስተዋሉ ስነ-አእምሮአዊ ችግሮች አሉ፡፡ ኤርትራውያን - በተለይ እነዚያ የኮንፈደረሽንን ትርጉም የማያውቁ - ከዚህ ሁሉ
ጦርነት፡ ሞትና ኪሳራ በሗላ እንዴት ከኢትዮጵያ ጋር በኮንፈደረሽን ይሁን በፈደረሽን እንዛመዳለን! ይላሉ[20]፡፡
በኢትዮጵያውያን በኩልም - አንዳንድ “አክራሪዎች” የሚባሉትን ጨምሮ - ኤርትራውያን እኮ አንፈልጋችሁም ብለው ሄደዋል፤ አሁን
ኤርትራ ያልተሳካላት አገር በመሆንዋ ከፍቷቸው ከኢትዮጵያ ጋር በኮንፈደረሽን መዛመድ ቢፈልጉ መቀበል የለብንም ይላሉ፡፡
እነዚህ አመለካከቶች ትክክል አይደሉም፡፡
የኤርትረያኖቹ አመለካከት ያለፈውን ብቻ የሚያስታውስ፣ ባለፈው ሁኔታ የሚገዛ፣ ለራስ ጥቅም የማያገለግል፡ እንዲያውም የሚጐዳ
ነው፡፡ ነገሩ መታየት ያለበት በቁጭትና በስሜት ሳይሆን ከጥቅም አኳያ ነው፡፡ የሚፈለገው ወደፊት ያቀና ለሁለቱ አገሮች
የሚጠቅም አካሄድና ዝምድና ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት ብዙ ጉዳት ደርሶብናል ብሎ አሁን ለሁላችን የሚጠቅመውን ዝምድና አንቀበልም
ማለት ሞኝነት ነው፡፡ የኢትዮጵያኖቹም እንደዚሁ ስህተት ነው፡፡ ማንኛውም ህዝብ በተሞክሮና በሂደት ተምሮ አመለካከቱን ሊለውጥና
ሊያሳድግ ይችላል፡፡ አስተዋይ የፖለቲካ ሰዎች ተለያይቶ እንደገና መተሳሰር ያልተለመደ እንዳልሆነ ነው የሚመሰክሩት፡፡
እንዲያውም ተለያይቶ እንደገና ወደ አንድነት ጐዳና መምጣት የመገንጠሉ ሂደት ቅጥያ ሆኖ የሚገኝበት ሁኔታ አለ፤ በሌላ
አነጋገር፡ መገንጠል ራሱ፡ አንዳንድ ጊዜ፡ ሂዶ-ሂዶ የአንድነትን መንፈስና ፍላጎት ሊወልድ ይችላል[21]፡፡
፭
ኮንፈደረሽን እንዲሁ በችኰላ በማንኛውም ሁኔታና
ጊዜ የሚቋቋም ነገር አይደለም፡፡ አስቀድመው መሟላት ያለባቸው ነገሮች አሉ[22]፡፡
ከላይ እንደተጠቀሰው ኮንፈደረሽን ዝምድናው የሚመለከታቸው
ህዝቦች ትርጉሙ ገብቶዋቸው በሙሉ ፈቃድ የሚቀበሉት መሆን አለበት፡፡ ጉዳያችንን በሚመለከት የኢትዮጵያና የኤርትራ ዜጎች
ኮንፈደረሽን ምን ማለት እንደሆነና እንዴትስ እንደሚጠቅማቸው መጀመርያውኑ መረዳት ያስፈልጋቸዋል፡፡
ይህ እንዲሆን በሁለቱ አገሮች ነጻ ውይይትን
የሃሳብ መለዋወጥን እና ለፖለቲካዊ ዓላማ መደራጀትን የሚፈቅድ ሁኔታ ወይም የፖለቲካ ሁዋ መኖር አለበት፡፡ ይህ ማለት በሁለቱ
አገሮች የበለጸገም ባይሆን በመሰረቱ ዲሞክራስያዊ የሆነ ስርዓት መኖር አለበት ማለት ነው[23]፡፡
ይህንን ስርዓት በሚመለከት ትንሽ ማብራርያ አስፈላጊ ነው፡፡
ካሁን በፊት በአንድ ጽሁፌ እንደገለጽኩት ለዚህ
ጉዳይ ይሁን ወይም በጠቅላላው ለኢትዮጵያና ለኤርትራ - እንዲያውም ለማንኛውም አፍሪቃዊ አገር - የሚበጅ ስርዓት የብሄራዊ
አንድነት መንግስት (Government of National Unity) የሚባለው ነው፡፡ ይህ ማለት ያሉት እንጋፋ የፖለቲካ
ቡድኖች ላላቸው ድጋፍ ተመጣጣኝ በሆነ መልክ ተወክለው የሚሳተፉበት ሰፊ ጣምራ መንግስት ማለት ነው፡፡
በኢትዮጵያና በኤርትራ እንዲህ ዓይነት ስርዓት
ሲሰፍን ህዝቦቹ የኮንፈደረሽንን ጥያቄ በተመለከተ ሃሳባቸውንና ፍላጐታቸውን በሙሉ ነጻነት ሊገልጹ ይችላሉ፡፡ ኮንፈደረሽን
እንዲህ በመሰለ ሁኔታ ሲከሰት አጥጋቢ፡ አስተማማኝ እና በውህደት አቅጣጫ የሚያድግ ይሆናል፡፡
የኮንፈደረሽንን ሂደት ለማስተጋባት መሟላት
ስላለባቸው ሁኔታዎችና ቅደም-ተከተላቸው ምን እንደሚመስል መጠነኛ ሃሳብ በማቅረብ መልእክቴን ማጠቃለል እወዳለሁ፡፡
1.
በኢትዮጵያም
በኤርትራም ባሁኑ ወቅት ሁኔታዎቹን ሊያረጋጋ የሚችል ተቋም አንጋፋዎቹን የፖለቲካና የሲቪል ህብረተ-ሰብ ቡድኖች ያካተተ
የሽግግር መንግስት ነው፡፡ ግቡ ምን እንደሆነ በትክክል አልታወቀም እንጂ በኢትዮጵያ አሁን የለውጥ ሂደት የተጀመረ ይመስላል፤
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በአገር ውስጥም በውጭም ከፍ ያለ ተቀባይነት አግኝተዋል፡፡ የዶክ. ዐቢይ
አስተዳደር የለውጡ ሂደት እንዲቀላጠፍና የሚፈለገው የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ብልህና ቆራጥ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ኤርትራ ውስጥ ያለው ሁኔታ
ግን ጭፍን አምባገነንነት ነውና ከበድ ባለ ትግል ካለፍን በሗላ ነው የሽግግር መንግስት የሚቋቋመው፡፡
2. ከዚያ ቀጥሎ በይዘቱ ከብሄራዊ አንድነት መንግስት፡ ከዲሞክራሲ እና
ከአድማሳዊ የሰብአዊ መብቶች አዋጅ ጋር የሚጣጣም ህገ-መንግስት ተነድፎ በህዝብ ይፀድቃል፡፡ በህገ-መንግስቱ መሰረት ምርጫ
ተካሂዶ መለያው የብሄራዊ አንድነት መንግስት የሆነ ስርዓት አገሮቹን ያስተዳድራል፡፡
3. የሁለቱ አገሮች ህገ-መንግስታትና ሌሎች ህጎች እንዲሁም መሰረታዊ
ፖሊሲዎች የሚጣጣሙ ወይም ተመሳሳይ እንዲሆኑ ይደረጋል[24]፡፡
4. ሁኔታው በተመቸ ጊዜ መንግስታቱ የኮንፈደረሽን መቋቋምን በተመለከተ
ድርድርና ተዛማጅ ሂደቶች ይጀምራሉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ስለኮንፈደረሽን ትርጉምና ሊገኙ ስለሚችሉት ጥቅሞች የሁለቱ አገሮች
ህዝብ አስፈላጊው ግንዛቤ እንዲኖረው ህዝባዊ ውይይት - ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን አብረው የሚሳተፉበትን ጨምሮ -
እንዲደራጅና እንዲካሄድ ይደረጋል፡፡
5. ኮንፈደረሽንን በማቋቋም ላይ በሁለቱ አገሮች ረፈረንደም ይካሄዳል፤
ውጤቱ ሃሳቡን የሚደግፍ ሲሆን የኮንፈደረሽኑ ጉዞ ይጀመራል፡፡
6. ኮንፈደረሽኑ ዕውነታው በሚፈቅደው ከፍተኛ የጋራ ተቋማትና የጠበቀ
ግኑኝነት እንዲነሳ ተደርጎ ይነደፍና የመጀመርያው ኮንፈደረሽን ዕድሜ 5 ዓመት ይሆናል፡፡
7. አምስት ዓመት ሲያልቅ እንደገና ረፈረንደም ይካሄዳል፡፡ በ5ቱ ዓመታት
ዝምድናው ምን ያህል የህዝቦቹን ህይወት ለማሳደግ እንዳገለገለ ይገመገማል፡፡ ኮንፈደረሽኑ አጥጋቢ ፍሬ ሰጥቷል ከተባለ፡ ይዘቱ
ከፍ እንዲል ተደርጎ በሁለቱ አገሮች ህዝቦች ነፃ ፍላጎት ይሻሻላል፤ ይህ ማለት ኮንፈደረሽኑ አገሮቹን በበለጠ በሚያቀራርብ
መልክ ይታደሳል ማለት ነው፡፡ እንዲህ እያለ ኮንፈደረሽኑ በውህደት አቅጣጫ ያድጋል፡፡
ይህ ቅደም ተከተል በጎና ደግ በሆነ አመለካከት የተመሰረተ ነው፡፡ ካለበለዚያ ሁኔታው
ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነው፡፡ ችኰላን ማስወገድ አለብን፡፡ በቅርብ ታሪካችን በችኰላ የተወሰዱ አላስፈላጊ እርምጃዎች ገና
እያጉላላን ያለውን ችግር ፈጥረውብናል፡፡
የኮንፈደረሽን ሃሳብ ብዙ ለኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ለኤርትራ ህዝብ በጎ የማይመኙ ጠላቶች
አሉት፡፡ በደቡብ ሱዳን ጉዳይ እንደታየው ጠባብ አመለካከት ያላቸው አንዳንድ ተንቀሳቃሾች መገንጠልን ነፃነት ብለው ወደሱ፤
ኮንፈደረሽንን ደግሞ ባርነት ብለው ኰነኑ[25]፡፡ እንዲህ የመሰለ አሉታዊ አመለካከት ባባከለው
ሁኔታ ደቡብ ሱዳን ተገንጥላ አሁን ጨለማ የነገሰባት አገር ሆናለች፡፡
በኤርትራውያን በኩልም እንደዚሁ ኮንፈደረሽንን ተቀባይነት እንዳያገኝ ለማድረግ የሚጥሩ
አልታጡም፡፡ ከነርሱ አንዱ በቅርብ ጊዜ በስዊድን አገር በትግርኛ በሰጠው ቃለ-መጠይቅ አንዳንድ ዜጎች የሚያቀርቡትን
የኮንፈደረሽን ሃሳብ “ዓዘፍዘፍ” (ማለት መዋዠቅ ወይም የማይረባ ንግግር) ብሎ ለማጣጣል ቃጥቷል፤ ከዚያም አልፎ ኤርትራን
በተመለከተ ኮንፈደረሽንን እንደ “ባርነት” አድርጎ አቅርቦታል፡፡ ሰውዬው የኮንፈደረሽን ትርጉምና ጥቅም ጠንቅቆ የሚያውቅ
የዕድሜና የዕውቀት ባለፀጋ ነው፡፡ ይህንን ውሸት ማራመድ - ትክክለኛ ዓላማው ምን ይሁን ምን - ከርሱ የማይጠበቅ አደገኛና
እጅጉን የሚያሳዝን ተግባር ነው፡፡
እንዲህ የመሰሉ ሃላፊነት የማይሰማቸው ምሁራን ህዝቡን ግራ የሚያጋባ ውሸት እያሰራጩ
መሆናቸውን አውቀን ብዙ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብን ግልፅ ነው፡፡ ለምሳሌ አስቀድሜ እንዳልኩት ኮንፈደረሽኑ በየጊዜው እየታደሰ
ያድጋል፤ ሁለቱ አገሮች ይቀራረባሉ፤ እሰከ ፈደረሽን ሊጓዙ ይችላሉ፤ የሂደቱ የመጨረሻው ግብ ፈደረሽን ነው ተብሎ ግን አስቀድሞ
አይታወጅም፡፡ ማንኛውም የመቀራረቡ ዕድገት ተግባራዊ ዝምድናው በሂደት የወለደው ሆኖ ነው መምጣት ያለበት፡፡ ግቡ ፈደረሽን ነው
ተብሎ ከታወጀ ጠላቶቻችን ይበዘብዙታል፤ ህዝቡም ይበረግጋል፤ ኮንፈደረሽኑ ተቃውሞ ገጥሞበት ሊፈርስ ይችላል፡፡
በጥንቃቄ ከተተገበረና አካሄዱ ካማረ፡ ማለት ህዝቦቹን በበለጠ ካረካ፡ ካቀራረበ፡
ካፋቀረና ካስተማመነ ኮንፈደረሽኑ በውህደት አቅጣጫ ያለማቋረጥ ያድጋል፡፡ በህዝቦቹ ሙሉ ፈቃድ መጨረሻው ፈደረሽን ሊሆን
ይችላል፡፡
ዋቢ
ጽሁፎች
John A. Akec,
“To confederate or not to confederate isa matter of strategy”, Sudan Tribune, Septemvber 14, 2010, <http://sudantribune.com/spip.php?iframe&page=imprimable&id_article=36261 >accessed on January 10, 2018, ;
John A. Akec, “Confederation; A Better Tool for Good
Neighborliness and Prosperous Relationship between Sudan and South Sudan”, UNISCI
Discussion Papers, Nr. 33, October 2013 (Madrid Spain), p. 158
;
John Apuruot
Akec, “Why confederation in Post-Referendum Sudan is key to prosperous,
stable, and good neighbourliness”, Sudantribune.com, 18 November, 2010 <http://sudantribune.com/spip.php?iframe&page=imprimable&id_article=36978 > accessed on January 10, 2018
John A. Akec, “South Sudan self-determination is the
gateway to an enduring and stable united Sudan”, Sudan Tribune, < http://sudantribune.com/spip.php?article33137 accessed on January 11, 2018
John A. Akec, “A call for renewable confederation in
post 2011 Sudan”, Sudan Tribune June 8, 2010 <http://sudantribune.com/spip.php?iframe&page=imprimable&id_article=35326> accessed on January 10, 2018
Hamid Eltgani Ali, “How to govern Sudan: A questv for
confederation”, Sudan Tribune January 11, 2010
<http://sudantribune.com/spip.php?iframe&page=imprimable&id_article=33735> accessed on January 3, 2018
Abdullahi Ahmed An-Na’im, “Third World Perspectives”,
in Elizabeth Ferris (ed), The Challenge to Intervene: A New Role for the
United Nations, (Uppsala: Life & Peace Institute, 1992), p. 145
Negasi Beyene , “Talk of ‘Tigrai Secession’ is Talk of
the Idle, Not the Concern of the People of Tigrai, says Activist Negasi
Beyene”, ethiomedia.com March 5, 2018
Zechariah Manyok Biar, “Confederation for Sudan: Is it
a good idea?”, Sudan Tribune, June 4, 2019, <http://sudantribune.com/spip.php?iframe&page=imprimable&id_article=35572> accessed on January 10, 2018
Talkmore Chidede, “The African Continental Free Trade
Area (AfCFTA) and other other African Union (AU) initiatives for economic
integration”,
,
accessed on March 22, 2018
Carl James Chol, “Mr. Malik Agar and Confederation”,
Pachodo.org,
,
accessed on January 10, 2018;
Francis M. Deng, “Prospects for Reconciling
Self-Determination with Unity in Sudan”, (Khartoum,: Symposium on Unity and
Self-Determination, November 2, 2009)
<http://www.un.org/en/preventgenocide/adviser/pdf/SAPG%20statement%20in%20Khartoum.%20Nov%2009.pdf >accessed on March 7, 2018
Abdullahi Osman El-Tom, “Towards Confederation between
Independent South and North Sudan”, Sudan Tribune 12 July 2010, <http://sudantribune.com/spip.php?article35633>, accessed on January 3 2018
Jeggan Grey-Johnson, “Is the AU blinded by its own
vision?”, (Open Society Initiative for Southern Africa OSISA), April 8, 2015, <http://www.osisa.org/openspace/regional/au-blinded-its-own-vision > accessed
on January 3,
Al Mariam, “A Rejoinder to Seyoum Mesfin’s call to
Arms to the People of Tigray”, Al Mariam’s Commentaries, February 4, 2018 <
http://almariam.com/2018/02/04/a-rejoinder-to-seyoum-mesfins-call-to-arms-to-the-p…;
l>
Tesfatsion Medhanie, Towards Confederation in the
Horn of Africa: Focus on Ethiopia and Eritrea, (Göttingen: Cuvillier Verlag
2009)
James Okuk, “Confederation for Southern Sudan a
Betrayal to Self-Determination”, Pachodo.org, January 17, 2008
accessed on January 10, 2018
Mahmoud A. Suleiman, “Confederal System for Sudan”,
Sudan Tribune, January 8, 2008 < http://sudantribune.com/spip.php?page=imprimable&id_article=25592> accessed on Janury 10, 2018
University of Pretoria, “Supranationalism in the
African context; A critical look at past and present attempts at building
supranational organizations in Africa”,
ያዕቆብ ሀይለማርያም፡ “አሰብ የማን ናት? የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ“ (አዲስ አበባ፣ 2003 ዓ. ም.)
ጌታቸው ረዳ፡ “ግብረ-መልሲ ንዶ/ር ሙሉወርቅን ገረኺዳን ደስታን”፡ togoruba.org 25 March 2018;
ጌታቸው ረዳ፡ ““ግብረ መልሲ ንዶ/ር ሙሉወርቅ ኪ/ማርያም” 2ይ ክፍሊ togoruba.org 06 April 2018
[2] . John A. Akec, “To confederate or not to
confederate is a matter of strategy”, Sudan
Tribune, Septemvber 14, 2010, < http://sudantribune.com/spip.php?iframe&page=imprimable&id_article=36261 > accessed on January 10, 2018, ; John A.
Akec, “Confederation; A Better Tool for Good Neighborliness and Prosperous
Relationship between Sudan and South Sudan”, UNISCI Discussion Papers,
Nr. 33, October 2013 (Madrid Spain), p. 158
; Mahmoud A.
Suleiman, “Confederal System for Sudan”, Sudan Tribune, January 8, 2008 http://sudantribune.com/spip.php?page=imprimable&id_article=25592
accessed on Janury 10, 2018
[3] . University of Pretoria, “Supranationalism in
the African context; A critical look at past and present attempts at building
supranational organizations in Africa”, p. 115,
[4] . John
A. Akec, “To confederate or not to confederate is a matter of strategy”, op.
cit.
[6] . የአንድነትን ምርጫ በተመለከተ የሚከተለውን ዕይ፡፡ Francis M. Deng, “Prospects for Reconciling
Self-Determination with Unity in Sudan”, (Khartoum,: Symposium on Unity and
Self-Determination, November 2, 2009)
<http://www.un.org/en/preventgenocide/adviser/pdf/SAPG%20statement%20in%20Khartoum.%20Nov%2009.pdf > accessed on March 7, 2018
[7] . Abdullahi Ahmed An-Na’im, “Third World
Perspectives”, in Elizabeth Ferris (ed), The Challenge to Intervene: A New
Role for the United Nations, (Uppsala: Life & Peace Institute, 1992),
p. 145
[8] . John A. Akec, “A call for renewable
confederation in post 2011 Sudan”, Sudan Tribune June 8, 2010 available online
at <http://sudantribune.com/spip.php?iframe&page=imprimable&id_article=35326>
[9] . ለምሳሌ የአፍሪቃ አንድነት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የነበሩት ሚስስ ድላሚኒ ዙማ እንዲህ የመሰለ አመለካከት አላቸው፡፡ Jeggan
Grey-Johnson, “Is the AU blinded by its own vision?”, (Open Society Initiative
for Southern Africa OSISA), April 8,
2015, <http://www.osisa.org/openspace/regional/au-blinded-its-own-vision >
accessed on January 3, 2018 ከዚህ ጋር በተያያዘ የአፍሪቃ
አገሮችን ለማዛመድና ለማወሃሃድ ተብለው ያለፉ ውሳኔዎችና የተነደፉ ዕቅዶች መኖራቸው ሊጠቀስ ይገባል፡፡የመጨረሻው የዚህ ዓይነት
ውሳኔ ባለፈው ወር የአፍሪቃ ህብረት በኪጋሊ ስብሰባው
ያሳለፈው “የአፍሪቃ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና”
የተባለው ነው፡፡ የኪጋሊ ውሳኔ ከመወሰዱ በፊት የታተመ ቢሆንም የሚከተለው ፅሁፍ ጠቃሚ ነው፡፡ Talkmore Chidede, “The African Continental Free
Trade Area (AfCFTA) and other African Union (AU) initiatives for economic
integration”, < https://www.tralac.org/discussions/article/12790-the-african-continental-free-trade-are…
> accessed on March 22, 2018
[10] በዚህ ፅሁፍ በደቡብ
ሱዳን ልሂቃኖች መሃከል ስለኮንፈደረሽን ከተካሄዱት የፅሁፍ ክርክሮች ብዙ ሃሳቦች ወስጄ ተገቢውን ዕውቅና (ምስጋና) በመስጠት
ተጠቅሜአለሁ፡፡
[11] . Carl James Chol, “Mr. Malik Agar and
Confederation”, Pachodo.org, <
https://pachodo.org/latest-news-articles/pachodo-english-articles/515-mr-malik-agar-a…>
accessed on January 10, 2018; John A. Akec, “Confederation; A Better Tool for
Good Neighborliness and Prosperous Relationship between Sudan and South Sudan”,
op. cit., John Apuruot Akec, “Why
confederation in Post-Referendum Sudan is key to prosperous, stable, and good
neighbourliness”, Sudantribune.com, 18 November, 2010 <http://sudantribune.com/spip.php?iframe&page=imprimable&id_article=36978 >
accessed on January 10, 2018
[12] . በዚሁ ጊዜ አንዳንድ ኤርትራውያንና የትግራይ ተወላጆች የትግራይ-ትግርኚን ዕቅድ
በተለያየ መልክ እያራመዱት ነው፡፡ እነዚህ ካድሬዎች አንዳንድ ጊዜ “አግዓዝያን” በሚል ስም ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ይህንን አፍራሽ
ዓላማ በማጋለጥ የEthiopian Semay አዘጋጅ ጌታቸው ረዳ ብዙ ፅሁፎች አበርክተዋል፡፡ ለምሳሌ እነዚህን ተመልከት፡፡
“ግብረ-መልሲ ንዶ/ር ሙሉወርቅን ገረኺዳን ደስታን”፡ togoruba.org 25 March 2018; ““ግብረ መልሲ ንዶ/ር ሙሉወርቅ ኪ/ማርያም” 2ይ ክፍሊ
togoruba.org 06 April 2018. እንዲሁም የሚከተለውን ዕይ Al Mariam, “A Rejoinder to Seyoum
Mesfin’s call to Arms to the People of Tigray”, Al Mariam’s Commentaries,
February 4, 2018 available online at
http://almariam.com/2018/02/04/a-rejoinder-to-seyoum-mesfins-call-to-arms-to-the-p…; እንዲሁም የሚከተለውን የአክቲቪስት ነጋሲ በየነን ቃለ-መጠይቅ አዳምጥ Negasi
Beyene , “Talk of ‘Tigrai Secession’ is Talk of the Idle, Not the Concern of
the People of Tigrai, says Activist Negasi Beyene”, ethiomedia.com March 5,
2018
[13]. Abdullahi Osman El-Tom, “Towards
Confederation between Independent South and North Sudan”, Sudan Tribune 12 July
2010, < http://sudantribune.com/spip.php?article35633 > accessed on January 3 2018
[15] . Zechariah Manyok Biar, “Confederation for
Sudan: Is it a good idea?”, Sudan Tribune, June 4, 2019, <http://sudantribune.com/spip.php?iframe&page=imprimable&id_article=35572 > accessed on January 10, 2018
[16] . Tesfatsion Medhanie, Towards
Confederation in the Horn of Africa: Focus on Ethiopia and Eritrea,
(Göttingen: Cuvillier Verlag 2009)
[17] . ደቡብ ሱዳንን በተመለከተ ዶክ. ፈራንሲስ ደንግ ይህንን ነጥብ አስምረዉበታል፡፡ Francis M. Deng, “Prospects for Reconciling
Self-Determination with Unity in Sudan”, op. cit.
[18]. ለምሳሌ የሚከተለውን ዕይ፡፡
ዶ/ር ያዕቆብ ሀይለማርያም “አሰብ የማን ናት? የኢትዮጵያ
የባህር በር ጥያቄ“ (አዲስ አበባ፣ 2003 ዓ. ም.)
[19] . ደቡብ ሱዳንን በተመለከተ ስለዚህ ፅንሰ-ሃሳብ የሚከተለውን ዕይ፡፡ Hamid Eltgani Ali, “How to govern Sudan: A
questv for confederation”, Sudan Tribune January 11, 2010 <http://sudantribune.com/spip.php?iframe&page=imprimable&id_article=33735 > accessed on January 3, 2018
[20] . እንዲህ ዓይነቱ ስሜት ባንዳንድ የደቡብ ሱዳን ልሂቃንም የነበረ ይመስላል፡፡ ለምሳሌ
ይህንን ተመልከት፡፡ James Okuk,
“Confederation for Southern Sudan a Betrayal to Self-Determination”,
Pachodo.org, January 17, 2008 <
https://pachodo.org/latest-news-articles/pachodo-english-articles/516-confederation-fo…>
accessed on January 10, 2018
[21] . John A. Akec, “Confederation; A Better Tool
for Good Neighborliness and Prosperous Relationship between Sudan and South
Sudan”, op. cit
[22] . ደቡብ ሱዳንን በሚመለከት የሚከተለውን ዕይ፡፡ John A. Akec, “South
Sudan self-determination is the gateway to an enduring and stable united
Sudan”, Sudan Tribune, <http://sudantribune.com/spip.php?article33137 > accessed on January 11, 2018
[23]. University of Pretoria, “Supranationalism in
the African context; A critical look at past and present attempts at building
supranational organizations in Africa”, op. cit. p. 115
[24]. ይህንን ለሚመስል ሃሳብ የሚከተለውን ተመልከት፡፡ Jeggan Grey-Johnson, “Is the AU blinded by its
own vision?”, op. cit.
[25] . John A. Akec, “To confederate or not to
confederate isa matter of strategy”, op. cit.
No comments:
Post a Comment