Note from the Editor ;
Our Blog was dormant
for a while without updating our readers all current issues written by the
Editor and his associates. This is because, the editor's articles were sent to
other media for distribution. From now on, my readers will only read the articles
here on Ethiopian Semay only. Those who wants to distribute to their readers
can email the editor and get the article directly from the editor. My Tigringa
commentaries will be still send to Ethiomedia (this is because the Amharic
website editors do not want to post a language they are not comfortable to
understand- that means they have no confidence what is written there!!!) I like
to thanks those media who cooperate with Ethiopian Semay for posting Ethiopian
Semay commentaries all these years in the past. I have come to this conclusion
due to some website editors felt uncomfortably of the following critique of
mine. I still argue there are some bogus Amhara who are also themselves a
fascist propagandists and racists as well who wants us to believe they are
genuine when they are not. We are here to stay and fight all racists and
secessionists regardless their affiliation or ethnicity Amhara , Tigre, Oromo
and so on... We fight for the benefit of the nation not for a group
please read the following.
ፕሮፌሰር መስፍን ስለ አማራ ፋሺዝም ትችታቸው ትክክል ናቸው
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian
seamy)
ባለፉት ቀናት አቻምየለህ ታምሩ እና ጸረ ትግሬዋ ወጣት ቬሮኒካ መላኩ (ሁለቱም አማራዎች ናቸው) መተማ ውስጥ ለአጼ
ዮሐንስ ሃውልት ሊቆም ከሆነ ንጉሡ ጎጃም ውስጥ ላደረሱት ጭፍጨፋ መጀመሪያ ሃውልት መቆም አለበት ሲሉ በሚያስገርም መንደፋደፍ ወደፊት
መጥተው ተቃውሞአቸውን አስሰምተዋል። ለሁለቱም የሰጠሁት መልሴን “ለዮሐንስ ሐውልት
ከተነፈገው፤ ለቴዎድሮስም ለምኒሊክም ለሃይለስላሴም አይገባቸውም! ለጸረ
ትግሬዋ ለቬሮኒካ የተሰጠ መልስከጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)” በሚል የጻፍኩት መልስ በራሴ ድረገጽ እና welkit.com ወይንም
Ethiopatriots.com ወይንም Ethiopanorama.com
ድረገጾች ገብታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። የቬሮኒካ እንጂ የአቻምየለህ ጽሑፍ ያየሁት ቆይቼ ነው። ሆኖም ሁለቱም አንድ አይነት አመለካከት
ስላላቸው መልሴ ሁለቱንም ይመለከታል። ቬሮኒካ የተባለቺው ይህች ወጣት ስለ ትግሬ ጥላቻዋ የቆየ ስለሆነ በዚያው ብትገፋበት አልደነቀኝም፤
አቻም የለህ ታምሩ ግን በዚህ አልጠረጠርኩትም ነበር እና ከ129 ምናምን አመት በፊት የተደረገ የነገሥታት ሥልጥን ሽሚያና የዘመኑ
ድንቁርና ስልት በዛወሬው ዓይን (ያውም ዘሬ የሚባለውም ከዛው የባሰበት ዘመን) ተምልከቶ ለምን በዚህ ጉዳይ እራሱን ለመክተት እንደፈለገ
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢሰጠን ጥሩ ነው።
እንዲያ ከሆነ የጎጃም ሕዝብ በሃለስላሴም ሆነ በአጼ ቴዎድሮስ
የተፈጸመ (ያውም አንጂባራ ውስጥ በቴዎድሮስ የተፈጸመ) (እንዲሁም ሸዋ እና ወሎ ውስጥ በቴዎድሮሰ የተፈጸሙ)ጭፍጫፋዎች ሃውልቶች
እንዲቆም ካልሆነ ግን ጎንደር ላይ ወይንም አዲስ አበባ ላይ ያለው የቴውድሮስ አደባባይም ሆኑ ሃውልቶች እና ስመ ጥር ታሪካቸው ክለሳ ሊያስፈልገው ነው
የሚሉ ክርክሮች ሊከሰቱ ነው። እነ አቻምየለህ ወደዚያው እየከተቱን ነው።
አቻምየለህ ታምሩን የምጠይቀው ጥያቄ አለኝ ፡ ይኸውም “ዮሐንስን
ለመቃወም ያበቃህ ምንድነው? ንጉሡ ጸረ አማራ ስለሆኑ ነው የሚል አቋም አለህ? ወይስ ሕዝብ ስለጨፈጨፉ ነው?..” ማብራራት ይጠበቅብሃል።
እንዲያ ከሆነ እያንዳንዱ ጀግና የተባለ ንጉሥም ሆነ አርበኛ የየራሱ ገመና ስለያዘ ልንከራከርባቸው ልንገደድ ነው ማለት ስለሆነ-
ከእንግዲህ ወዲህ እባካችሁ አደራ የምላችሁ ‘እንዲህ ያለ የኛ ንጉሥ የነሱ ንጉሥ’ እየተባባለ የሚደረግ የጎሰኛነት ክርክርና ቂም
አሁኑኑ እንዲቆም እና አንገብጋቢ ወደ ሆኑት የዛሬ ጥቃቶች ብንከራከር የተሻለ ነው። በዚህ ንትርክ ተጠቃሚው ማንም ሳይሆን የውስጥ
አክራሪ ሃይላት እና አማራን እናስገንጥል የሚሉ አፍራሽ እና የአማራ ጠባብ ሃይላት ብቻ ናቸው። ይህ እንዲቀጠል የሚፈልጉ ተጠቃሚዎችና
በዚህ የሚገፉ እነዘኚህ ናቸው። ስለዚህ ማለቂያ ስለማይኖሮው አሁንኑ ይቁም! አሁን ወደ ርዕሴ ልግባ።
ሰሞኑን ቆንጂት ስጦታው በተባለች ዜጋ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም “የአማራ ፋሺዝም (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም) May 13, 2018 – Konjit Sitotaw) ብለው በጻፉት ላይ የሚከተለው ብለዋል ብላ የለጠፈቺው እውነትነት ካለው ጋር የጠቀሱት ጥቅስ እውነትነት
አለው። ጥቅሱም እንዲህ ይነበባል፡
“አንድ ፋሺስት በቀደደው ዛሬ ብዙ ፋሺስቶች ተከትለውታል፤ አንዲያውም በዚህ ጉዳይ መለስ ዜናዊን የሚያስንቁ ፋሺስቶች ፈልተዋል፡፡ ካሉ በሗላ በመቀጠል
አንድ የታዘቡት ፋሺስታዊ ጽሑፍ በመጥቀስ እንዲህ ሲል አንብቤአለሁ ያሉትን እንዲህ የነበባል
ይላለሁ «የአማራ ብሄርተኝነት ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ስጋት የማይሆንበት ተጨማሪ ምክንያት የብሄረሰቡ ትክለ ስብዕና ነው፡፡ዐማራ የጥበብ መሃንዲስ ነው፣ ታሪክ ሰሪ፣ ድንበር አስከባሪ፣አሰተዋይ መሪ ነው፡፡ ለአከርካሪው ሲቃጡት አናት የሚያፈርስ የጀግኖች አውራ ነው፡፡ እንደ ኢትዮጰያ አማራ የአግዜር የበኩር ልጅ ነው፡፡ በሃይማኖቱ፣ በቁርጠኛነቱ በደግነቱና በትዕግስቱ ያሰበበት ደራሽ ነው፡፡…..» ሲሉ ያነበቡትን ጥቅስ ፋሺስታዊ መሆኑን በትክክል አስቀምጠውታል።
መለስ
ዜናዊን የሚያስንቁ ተገንጣይ ፋሺስቶች አማራ ነን ከሚሉ ፋሺስት አማራዎች ወደ መድረኩ ብቅ ማለት መጀመራቸው ሃቅ ነው። እኔም
በዚህ ጉዳይ ካሁን በፊት ጉዳዩን አንስቼ ስጋቴን ገልጫለሁ። አማራ በመጠቃቱ እራሱን የሚከላከልበት ዘዴ ፈልጉ አልን እንጂ “አማራን
በትምክህት እንዲከሰስ ወይንም ተነጥሎ እንዲኖር የሚደረግ ጥረት እንዳይከሰት ጥንቃቄ ይደረግ” ብየ ተከራክሬአለሁ። አሁን ያ
ስጋቴ እውን ሆኖ ፋሺስት አማራዎች ብቅ ከማለታቸው አልፈው ተደራጅተው ማህትም አበጅተው አማረውን ማሕበረሰብ ከኢትዮጵያ
አገራቸው ለማስገንጠል የተነሱ አሉ። በየመድረኩም እየተጋበዙ እና እራሳቸውም ሕዝብ እየሰበሰቡ ስብከታቸው እና አላማቸውን
ማስተዋወቅ ጀምረዋል። ይህን አስመልክቶ አንድ ምሳሌ ልስጥ።
ቤተ አማራ
የተባለ ድርጅት ለጆሮአችሁ አዲስ አይደለም። ከተመሰረተ ብዙ ጊዜ ሆኖታል።ይህ ከኦነግ ፤ ከኦብነግ እና ከኤርትራ ተገንጣዮች
እንዲሁም ከፋሺስቱ ወያነ ትግራይ (ህወሓት) በአላማ የማይለየው ቤተ አማራ የተባለው ድርጅት ፕሮግራሙን እና የመነሻ አላማውን
እንዲህ ሲል ይነግረናል፡
“ቤተ አማራ የአማራ ብሔረተኝነትን አነቃቅቶ ታሪካዊ ቦታዎቹን ያስመልሳል፤ ማንነቱን ያስጠብቃል፤ ታሪኩን ያስከብራል፤ ነጻ መንግሥትነቱን ያውጃል” ይላል።
ይህንንም ለማየት ይህንን በማሕተሙ ላይ ተያይዞ የሚነበብ አቋሙን ተመልከቱልኝ፤
ይላል። ይህ ፋሺስም ካልሆነ ምን እንደሆነ የሚነግረን ሰው ካለ መልሱን እጠብቃለሁ።
ስለ ፋሺዝም ትርጉም እና አቋም በመጽሐፌ ውስጥ የተካተተ የዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ጽሑፍ ወይንም ስዊድን (ካልተሳሳትኩ አምስተርዳም
ይመስለኛል) በተካሄደው የአማራዎች ስብሰባ ላይ እራሱ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ያቀረበው የፈሺዝም ንቅናቄ አጀማማር/መነሻ እና ግብ በሰፊው
ያብራራበትን ምሁራዊ የሆነ ትምህርታዊ ምርምር አሁንም በወልቃይት ድረገጽ ስለሚገኝ አውድዮው/ቪዲዮው መመለክት ይጠቅማል።
ፕሮፌሰር መስፍን
የጠቀሱት ፋሺዝምን የሚሰብኩ አማራዎች የሚከተለውን ጥቅስ አንብቤአለሁ ብለዋል፡ ጥቁሱም “«የአማራ ብሄርተኝነት ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ስጋት የማይሆንበት ተጨማሪ ምክንያት የብሄረሰቡ ትክለ ስብዕና ነው፡፡ዐማራ የጥበብ መሃንዲስ ነው፣ ታሪክ ሰሪ፣ ድንበር አስከባሪ፣አሰተዋይ መሪ ነው፡፡ ለአከርካሪው ሲቃጡት አናት የሚያፈርስ የጀግኖች አውራ ነው፡፡ እንደ ኢትዮጰያ አማራ የአግዜር የበኩር ልጅ ነው፡፡ በሃይማኖቱ፣ በቁርጠኛነቱ በደግነቱና በትዕግስቱ ያሰበበት ደራሽ ነው፡፡…..»
እንግዲህ
እንዲህ ያለ ጥቅሶች የትግሬ ብሔረተኞችም ጭምር ሲጠቅሱት ሰምተናቸዋል። ተመሳሳይነታቸው እጅግ ይገርማል። ይህ የአማራ ፋሺዝም
የሚሰብክ ጥቅስ አንድን ጎሳ በመሪነት የሚያስቀምጥ፤አንድን ጎሳ በየእግዚአብሔር የቦክር ልጅነት እና ሌላው ፍጡር ……ልጅነት
የሚሰብክ ‘የአማራ ብሔረተዊ ፋሺዝም’ የሚሰብክ፤ ላቅ ሲልም “አማራን ለማስገንጠል” ሕጋዊ ጀሮ እና ድረገጽ ተለግሶለት
በየስብሰባው እየተጋበዘ ግንጠላና ፋሺዝምን ሲያሰተምር፤ እንዲሁም ይህ ድርጅት ከሌሎቹ ጤነኞች አማራ ድርጅቶች በማህበርተኛ
በጋራ ግምባር ማሕበርተኛ ሆኖ ተመዝግቦ እንደተቀላቀለ የሚነገርለት (እውንተ ውሸት አላውቅም ግን ይወራል) የምንሰማበት ወቅት ስለሆነ ፕሮፌሰሩ “አንድ ፋሺስት በቀደደው ዛሬ ብዙ ፋሺስቶች ተከትለውታል፤ አንዲያውም በዚህ ጉዳይ መለስ ዜናዊን የሚያስንቁ ፋሺስቶች ፈልተዋል፡፡” ማለታቸው ለነ ቤተ አማራ ብሔረተኛነት
የሚስማማ ትክክለኛ ትችት ነው። በዚህ ላይ መንጫጫት የሚሻ አይመስለኝም። እንደውም በአማራ ስም ግንጠላን እና አክራሪ
ጎሰኝናትን የሚሰብኩ አማራዎች ብቅ ሲሉ “አማርን ለምን አትረዱም” እያልን ለምንወቅሳቸው አማራዎች ይበልጥ እንዲሸሹ
ስለሚያደርግ ትኩረት ቢደረግለት የተሻለ ነው እላለሁ። መካድ የማንችለው ሃቅ አለ- እሱም - የአማራ ፋሺስቶች በየፓልቶኩም ሆነ
በየፌስ ቡክ በየ ዩቱብ እያስደመጡን ያለውን እጅግ አሳፋሪ እና አስፈሪ የአማራ ጉግ ማንጉጎች እየተባዙ መምጣታቸው ሃቅ ነው። ከነዚህ ጉግ ማንጉግ
የአማራ ፋሺዝም አቀንቃኞች ሕዝባችን ከሚመኙለት እልቂትና ግንጠላ አምላክ ይጠብቃት። ሙሶሎኒ እና ግራዚያኒ ግለሰቦች ናቸው፤
ሆኖም ወደ ሰፊው ሕዝባቸው በመጠጋት ያስደመጡት ፕሮፓጋንዳ መላውን ጣሊያን እና ጀርመን አስከትሎ የተፈጸመው ዕልቂት
ለኢትዮጵያም የደረሳት መሆኑን ማስታወስ አስፈላጊ ነው። ሕዘብ የሚባል የግለሰቦች ጥርቅም መጠሪያ እንጂ ሕዘብ የሚባል ልዩ
ፍጡር የለም። ስለዚህ ሕዝብ ስንል ግለሰቦች ያለቸውን ተራ እና ወሳኝነት ማጤን አስፈላጊ ነው። ግለሰቦች የሚቀሰቅሱት ቅስቀሳ
መላውን የግለሰብ ስብስብ (ሕዝብ) የሚያቀጣጥል ችቦ ሊሆን እንደሚችል ማስተዋል ጠቃሚ ነው። አንድ ቅማል ሱሪ
ያስፈታል አንድ ውሸት አገር ያፈርሳል! የሚለውን እናጢን። ግለሰቦች ናቸው እየተባለ በንቀት ማየት
የሄድንበት ባህል መቆም አለበት!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) getachre@aol.com
No comments:
Post a Comment