በሂደት ላይ ያለው የዘመነ ካሴ ረዢሙ የቢላዋ ምሽት
Zemene Kassie’s night of the Long Knives in the making
ጌታቸው ረዳ
የኢትዮጵያ
ሰማይ አዘጋጅ
8/1/24
መነሻችን አማራ መዳረሻችን አማራ እያለ <አራት ኪሎ ለአማራ ይሰጥ> የሚለው አማራን አራት ኪሎ አምጥቶ በላያችን ላይ ለመጫን ብረት ያነሳው የጎጃሙ ዘመነ ካሴ እና መዳረሻችን
ኢትዮጰያ በማለቱ በብዙ ደደብ የአማራ ምሑራን ብሔረተኞች እየተወገዘ ያለው እስክንድር ነጋ ካዲስ አበባ ባልደራስ
ተሰወረ ሲባል እንዲህ ብዬ ነበር፡-
<<የእምዬ
ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ እስክንድር ነጋ በትግሬ የፋሺሰቶች ሥርዓት (27) አመት፤ በኦሮሞ ፋሺሰታዊ ሥርዓት (4) አመት ጠቅላላ 31 አመት
በፋሺሰቶች ዘመን ሲታገላቸው፤ ሲያስሩት፤ ሲደበድቡት፤
ሲያንገላቱት፤ ሲሰድቡት፤ ስሙን ሲያጠፉትና ዕድሜ ይፍታ ሲበይኑበት የኖረ እርሱን መሳይ ለማግኘት የሚቸግር፤ ብቅ ብላ
እንደምትሰወር ብርቅ የመስከረም ወፍ አይነቷ ወጣ ያለ ፍጡር ነው። ብዙ ደደብ
መሁራን የዚህ ብርቅ ታጋይ ማንነት አልገባቸውም፡፡ ይታያችሁ' እስክንደር በይሁዳዎቹ የብረት
ብትር እየተቀጠቀጠ ይህንን መስዋእት ሲከፍል ባለቤቱና ልጁን ለፈጣሪ አስረክቦ ስለ ሕዝብ እና አገራዊ ልዕልና ነበር
(ይህንን አስፈሪ መስዋእትም ሲያሳንሱ ሰምቸ ያንዳንድ ሰዎች ጮርቃነትና ዝቃጭ ሕሊና አስገረመኝ)። ታዲያ ምን ያደርጋል ፤ምሁሩም፤ ሕዝቡም ከዳው!! ካሐዲ ሕዝብ ድሮም የነበረ “እምየ ኢትዮጵያ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” ተብሎላታል አደል?!
አንዳንድ
ጭቃ ሕሊናዎች “ከጋዜጠኛነት ወደ አክቲቪሰትነት” መዞሩ ለውድቀቱ ምክንያት ተከታይ አጥቷል እያሉ ጭቃ ሲያቦኩ ገና ወደ ጫካ ሳይወጣ ነበር ያደመጥኩዋቸው።
ይገርማል። ጋዜጠኛም ሆነ አክቲቪስትና
ፖለቲከኛም ሆንክ ፀሐፊ በቁሙ የሞተን አሕያ መጎተት አስቸጋሪ መሆኑን አላወቁም ። ጫታሙ ማፊሪያው የኢትዮጵያ ወጣት “27 አመት”
ያልነቃ ከአፍሪካ ወጣቶች በባሰ የደደበ በቁሙ የሚጎተት አጋሰስ ነው” ከዳውና ብቸኛነት አጠቃው! በመጨረሻ
አበቃ! እሰይ አንኳን በቃኝ አልክ! ለዚህ ከዳተኛ እና አድርባይ ሕዝብ መስዋእት መሆን በፍጹም የማይገባውና ባርያ የሆነ
ማሕበረሰብ ቤዛ መሆን አያስፈልግም ነበር! በጣም አዘንኩ! ዕምባ ፤ ዕምባም አለኝ! እንዲህ ያለ ቆራጥ ፍጡር ለሕዝብ ብሎ ሲሞትለት ፤ በማዶ ቆሞ የሚመለከት ማሕበረሰብ ለባርያ ገዢዎች ሰጥቶ መቀመጥ “አማራጭ
የለውም”። ይቀጥቀጥ ፤ ይሙት ፤
በመኪና ይጎትቱት የራሱ ጉዳይ! እስኬው
ባለህበት ፈጣሪ ይጠብቅህ ሰላምታየና ምስጋናየ ይድረስህ፡ እስክንድር በፅናትህ መስክረናል! ዓለም አውቆሃል! ሽልሞሃል! ባንተም ኮርተናል! ባለህበት ሁሉ ሰላም እና
ምቾትና ጤና እመኝልሃለሁ!>> ብየ ነበረ እሰክንድር
ካዲሰ አበባ ተሰወረ ሲባል፡፡ በኋላ ጫካ መሄዱን አወቅኩ፡፡
ዛሬ ደግሞ ፋኖን ተቀላቅሎ ከአከራሪው (ኢክስትሪም ናሺናሊስቱ) ዘመነ ጋር ሲጋጭ ጠቡ ወደ አወራጃዊ በማድረግ እስክንድርን ቀርቶ እኔኑንም እዚህ አብረውኝ ከሚኖሩ የጎጃም አማራ ብሔረተኞች
(የዘመነ ካልት) የጥላቻቸው ዒላማ አስገብተውኝ መዛትም መዝለፍም ጀመረውኛል (ልክ ወያኔዎች ጋር እንዳሳለፍኩት ማለት ነው)፡፡ ሆኖም
እስክንድርን የግድያና የዘለፋ ዒላማ ውስጥ እያስገባው ያለው ይህ ልፍስፍስ የ30 አመት ትውልድ ስንት
ታጋይ ቆሞ አስበልቷል። ከዚህ ወዲያ ቆራጥ አታጋይ ከየት አባትህ
ሊፈጠርልህ ትሻለህ? ዘመነ ካሴ ነው ነጻ የሚያወጣህ? ነበሰ ገዳዩና ጋዜጠኛ አፋኙን ዘመነ ካሴን
እየካብክ እስክንድርን ማዋረድና ለመግደል መዛት ከጀመረክ አዲስ አበባ መግባት መከልከል ቀርቶ ፤ ሚሰትህን ነጥቆ
ቢያማግጡልህም በቁጭት የማትነሳ ሕዝብ ነህና ‘መቸውም ጊዜ ከባርነትህ አትላቀቅም፤ በጫካው አውራዘልል በዘመነ
ከተመራህ እያሳደደ እያፈነና እየገደለህ የባርነት ምቾትህን እንደተመቸህ ተመችቶህ ይኑር! ለዛውም የጎጃም አማራ ሕዝብ ጥናቱን
ይስጥህ! እኛስ የካልቶች ስድብ ለዘመናት
ለምደነዋል (ተነስ ታገል ሰንላቸው ሰድበውናል አክራሪነትና አፋኝነትን አስወግዱ ስንላቸውም ይሰደቡናል)፡፡
ይህ የባሮችና የባርያ ገዢዎች ፤ የአሳዳጅና የተሳዳጅ ፤ የአፋኝና የታፋኝ የጫካ ዘመን እየመሠረተ ያለው ዘመነ ካሴ በቅርቡ ጎጃም የኔ ንብረትና ይዞታ ነው ሰለዚህ ከኔ ሠራዊት ውጭ ማንም እንዲንቀሳቀስና እንዲታገል አልፈቅድም አለበለዚያ ግን እርምጃ ይወሰድበታል በማለት ሻእቢያ በጀብሃ ፤ ህወሐት በኢዲዩና በኢሕ አፓ የማጥፋት እርምጃ እንደፈጸሙት ዘመነም ያንን በመድገም (መረጃው ከሥር አቀርባለሁ) ልክ የጀርመንን ናዚ ዓይነት አፈና እና ማሳደድ ጀምሯል (ርሸናም ጭምር)፡፡
ጀርመን ውስጥ የዓለም ታሪክ የለወጠ ሌሊቱን ሙሉ የደም ገመቦ የፈሰሰበት ረዢሙ የቢላዎች ምሽት (The Night of the Long Knives) ተብሎ የሚጠራ የግድያና የአፈና
ዘመቻ ሂትለር አምባገነን ሆኖ ለሥልጣን እንዲበቃ ካደረጉት ሁለት ነገሮች ረዢሙ የቢላዎች ምሽት (The Night of the Long Knives) ተብሎ የሚጠራው የማፈን ፤ የማስበርገግ ፤ የግድያና የማሳደድ እርምጃ ነው፡፡
ማጽዳትና ወሳኝ ይለዋል ሂትለር (‘የሌባና የፖሊስ፤የድመትና የዓይጥ ዘመቻ፤ ይለዋል ዘመነ)፡፡
ረዢሙ የቢላዎች ምሽት በጀርመን ታሪክ በሰኔ (June) 30, 1934 ዓ.ም ሂትለር
SA (ቡናማ ለባሽ/ Brown Shirt) በመባል የሚጠራውን ሂትለር በ1921 ያደራጃቸው የመጀመሪያው መፈንቅለ መንግሥቱን ሲሞክር
የረዱት “ኃያልና ጉልበተኛ” እየሆነ በመምጣቱ ይህንን ልዩ ሃይል የሚመራው ለሥልጣኑ አስጊ ሆኖ ያየው የ SA መሪ ኤርነስት
ሮኽምን ጨምሮ ፤መሰል ተቀናቃኞችን ጭምር እንዲገደሉ የግል ጠባቂዎቹ የሆኑት <<ኤስ.ኤስ (SS)>>
(Gestapo) በመባል የሚታወቀው አፋኝና ገዳይ ቡድንን አሰማርቶ እርምጃ እንዲወስዱባቸው በማድረግ አንድ ወር ሙሉ የፈጀ ግድያና
ማሳደድ የፈጸመበት ድርጊት ነው ።
በተለይ የመጀመሪያዋ ምሽት ሙሉ ሌሊት የደም ገመቦ ሲፈስባት በብዙ ቢላዋ/ሳንጃ ፤ ገጀራና ጥይት
ሰው የተጨፈጨፈበት ንግድ ቤቶችና የተጠርጣሪ መኖርያ ቤቶች የተደፈሩበት አፋኝና ታፋኝ የተሳደዱበት ሌሊት ስለነበር ረዢሙ የቢላዎች ምሽት (The Night of the Long Knives) ተበሎ
ይጠራል፡፡
በዚህ መንገድ ሂትለር ጭፉጨፋና አፈና የገባበት ምክንያት ለሥልጣኑ አስጊ ናቸው ያላቸውን ተቃዋሚዎችንና የጠረጠራቸውን ነው
ጠራርጎ የሥልጣኑን መንገድ የጠረገው፡፡
ዘመነ ካሴም በተመሳሳይ ጎጃም ውስጥ ካለ የራሱ ታጣቂ በቀር ሥልጣኔን ይጋሩኛል የሚላቸውን በሥሩ የተደራጁ የጠረጠራቸው መሪዎችም ሆኑ ጎጃም
ውስጥ ከራሱ ውጭ የተደራጁ ታጣቂ ፋኖዎችን እያደነ መያዝ መገድልና ማሳደድ ጀምሯል፡፡
በሚገርም ክስተት “ከጎጃም አማራ ፋኖ” ለማፈንገጥ የጀመሩትን እያሳደደ ስላዋከባቸው፤በብቸኝነት
በጭንቅ ተገፋፈቶ የተቀላቀለው ብዙ ታጣቂ ሰላደራጀ መሸሺያና መደበቂያ ሲያጡ ምለው
ጥለው መሪያችን ዘመነ ነው በማለት ሕዝብ ፊት እንዲምሉ አድርጎ ቪዲዮ አሰራጭቷል፡፡ <<መሪያችን ዘመነ እኛም በዘመነ ሥር>>
በሚል አባሎቻቸውን ሲያስምሉዋቸው ነበር፡፡ ይህ አባባል አንዳንድ የሂትለር ተሿሚዎች መሪያቸውን ለማስደሰት ሲሉ <<under
the leadership of Hitler, Hitler for Germany-the whole Germany for Hitler” (The
third Reich in power -Richard J evans የሚለው መጽሐፍ አንብቡ፡፡ <<በሂትለር መሪነት! ሂትለር
ለጀርመን - መላ ጀርመን ለሂትለር!>> ይህንን መፈክር ከሰማ በኋላ ደራሲው (The leaders cult knew no more limits) “የካልት መሪዎች ሲጎነበሱ ዳርቻቸውን አያውቁም” ሲል ወርፏቸዋል፡፡ አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ሁሉም አማራ ላንድ
አማራ የሚለው የዘመነ የሁን የክርስትያን ታደለ ዓይነት ቅጂ፡፡
ሂትለር እንዳደረገው ዘመንም ጠበቃ ነው የሚባልለት አስረስ ማረ እንዲመለሱ አስፈራርቶ ያስገባቸው አፈንጋጮችን (አንጃዎችን) ሰብስቦ እንዲሁም ሌላ ካድሬም እንዲሁ አዳዲስ ምልምል አባል ወጣቶች ሰብስቦ (ያልታጠቀው ተሰብሳቢው ሕዝብም ጭምር) ክእስላሞች የቀዱት “ተክሪር ! አላህ ወ አክበር!” እያሉ እሰላሞች እንደሚጠቀሙበት አመልካች ጣታቸውን እየቀሰሩ የሚነገራቸው መፈክርና መሃላ “አርበኛ ዘመነ መሪያችን ነው” እያሉ የመሪ ቀረጻ እንዲያስተጋቡ የሕሊና አጠባ ለማከናወን እንዲህ እያለ የመራቸዋል፡-
<<በመርያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ የሚመራ የአማራ ፋኖ በጎጃም
እና በመሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ሥር ሆነን አባል
ለመሆን ቃል እንገባለን፡፡ በአርበኛ ዘመነ ካሴ የሚመራው የጎጃም አማራ ፋኖ ውጭ ማንንም ላንከተል ቃል
እንገባለን>>፡ ይላል፡፡ በዚያች ትንሽ አረፍተ ነገር የመሪያቸው ተከለ ሰውነት ቀረጻ ለማረጋገጥ 3 ጊዜ ስሙ
ተጠቅሷል፡፡
አስረስ ማረ የተባለ የዘመነ ምክትል ደግሞ ኮሎኔል ጌታሁን ሲመራው
የነበረው “የፋኖ አንጃ” (ብለው እነ ዘመነ በጠላትነት የመደቡት) ሠራዊት ከብበው አስፈራርተው በዘመነ ሥር እንዲሰለፉ ካስገደድዋቸው
በኋላ እንደ ሂትለር፤
ተሓህት እና ሻዕቢያ በአካቢያቸው ማንም ፋኖ እንዲንቀሳቀስ እንደማይፈቅድ እንዲህ ይላል፡
<< እኛ የቢትወደድ አያሌው ክ/ጦር አባልና አመራሮች ስንሆን ከዛሬ ጀምሮ ‘’በአማራ ፋኖ በጎጃም” ውስጥ ሆነን ለመታገልና በአማራ ፋኖ በጎጃም መተዳደርያ ደምብ መሠረት የምንመራ ሲሆን ከዛሬ ቀን 19/11/2016 ዓ/ም ጀመሮ በአማራ ፋኖ በጎጃም ሥር ባሉት ብርጌድ በመሆን በመሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ አመራር ሥርና በየደረጃው ካሉት አመራሮች አማካኝነት የሚሰጠንን ግዳጅ የምንቀበል መሆኑን በተሰውት ጋዶቻቸን ሥም ማረጋገጥ እንወዳለን፡፡ይህንን የማናደርግ ከሆንን ተቅዋማችን ማለትም የአማራ ፋኖ በጎጃም የሚወስድብን እርምጃ የምንቀበል መሆኑን በቃላችን እንገለጻለን፡፡ የአማራ ፋኖ በጎጃም ተቅዋማችንን እንጠበቃልን!>> አመሰግናለሁ! >>
በማለት የዘመነ ምክትል ጠበቃ “አስረስ ማረ” ከላይ ለዘመነ እንዲያድሩ እያንዳንዱን እሱ ያነበባችውን ቃል ኪዳኖች እንዲደግሙት "በሉ" እያለ ቃል እንዲገቡ
አስማላቸው፡፡ አስረስ ማረ ሆን በሎ ጡንቻው ለማሳየት
እስክንድር ነጋን የመረጡ ጦሮች (በመሪያቸው ተወካይ ድመጽ) ሰለሆኑ በራሱ አጃቢዎች እየተጠበቁ ፊት ለፊታቸው ባዶ እጃቸውን
አሰቁሞ በግድ እንዲቀላቀሉ ሰለተደረጉም ገጽታቸው
ላይ ድብቅ “የኢንቲሚዴሽን” የመሸነፍ ሃዘንና የተጨፍላቂነት ስሜት ይታይባቸዋል፡፡
ማስረጃውን ላቅርብ:-
በጎጃም ብሔረተኛነት የተቃኘ ምናላቸው ስማቸው የተባለ በገባበት ሚዲያ ሁሉ ሚስጢር
እያወጣ የሚገነጠል “ደካማ ሰው” (ብርቅየና ተወዳጅ አርበኛችን ሚስቱን እንዳትቀየመኝ ይቅርታ እየጠየቅኩ) Ghion TV /
Amhara News - Ethiopia- በሚባል <<ኮሎኔል
ጌታሁን የት ደረሰ?>> በሚል ርእስ ታጋዮቹ በግድ ተከብበው እጃቸው ሰጥተው ዘመነን እመኑ ተበለው
“ዮ ቲዩብ” ላይ ማፈሪያው ምንአልካቸው የለጠፈው መመልከት ትችላላችሁ፡
እንዲህ ሲል ይጠይቃል፤
<<የአውደው አበሻና የአቸፈር ወንድየ ብርጌዶች አዛዥ ሻምበል ደረጀ
አመሰግናለሁ፡ ለመሆኑ ኮሎኔል ጌታሁን ያዛችሁት ወይስ የት
ደረሰ?>>
መልስ - ሻምበል ደረጀ
ከኮረኔሉ ጋር የነበረው ወደ 70 የሚሆን ጦር ነበረው 8 ብረይንና 3 ስናይፐርና
2 ላውንቸሮች ነበሩት፡፡በዚህ ሰዓት ላይ አንድ ላውንቸርና አንድ ሻለቃ የሱ ምክትል የነበረ በቁጥጥር አውለነዋል፡፡ከዚያ
በተረፈ የኮረኔሉ ጦር እየፈረሰና በከበባ እጅ እንዲሰጡ አድረገን አሁን አብረውት ያሉ 3 ቤተሰቦቹ ናቸው፡፡ ከዚያ ዙርያውን ከበነዋል፡
በረሃ ለበረሃ እየዞረ ይገኛል፡፡በዚህ ይሄዳል ፤ በዚህ አለ ፤ እየተባለ እያሳደድነው ነው፡፡ዋናው ሃሳባችን ሰውየውን
ለመግደል ሳይሆን ተመከሮ እንዲቀላቀለን
ነው፡>> በማለት እስክንድርን ደግፈሃል በሚል ጦሩን አፍርሰው በዘመነ ካሴ ሥር እንዲሆን በማድረግ አዛዡን በማደን ላይ
ናቸው፡፡
በሚገርም ነገር ይህ ኮሎኔል ይህንን ሠራዊት እየመራ ከተቀላቀላቸው 1 አመት ሲሆን፤
እንድ አመት ሙሉ ምንም ስይነኩት አሁን እስክንድርን ደግፎ ድመጽ በመስጠቱ <<የጎጃሙ ሙሶሎኒው ዘመነ>> ልክ
እንደ ሂትለር ለሥልጣኑ ጠንቅ ናቸው የሚላቸውን ታጣቂዎችን በማፈራረስ፤ የፋኖ መሪዎችንና አባሎች እያሳደደ በማፈን
የደም ገመቦ የፈሰሰበት ሰኔና ሐምሌ ወር የናዚው መሪ ሂትለር ባዘዘው <<ረዢሙ የቢላዎች ምሽት (The Night of the Long Knives) ተብሎ የሚጠራ የግድያና የአፈና ዘመቻ፡ ሰኔ የጀመረ ሐምሌ ወር በኢትዮጵያ ምድር ጎጃም ውስጥ ዘመነም “በ ሌባና በፖሊስ፤ በዓጥና በድመት> የሚደረግ ጦርነት ነው በማለት የዛተበትና የሰየመው ዘመቻውን ያልተገዙለትንና ለወደፊቱ ያሰጉኛል የሚላቸውን <<ከአማራ ጠላቶች የተመሳጠሩ የአማራ ጭምብል ያጠለቁ ፤ ከአብይ ጋር እየሰሩ>> እያለ በውሸት “ስማቸውን በማጠፋት” እያሳደደና እያፈነ አንዳንዱም እየረሸነ ፤ ይባስ ብሎም “አያቶቹ የሚሆኑ ሽማግዎችን” ሕዝብ ፊት በእምብርክክ እያሰኬደ በማዋረድ የጫካ ሥልጣኑንና ጡንቻውን በማሳበጥ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ላሳርግ፤፟
Bella Fromm የተባለች አይሁዳዊት ‘ጀርመን ውስጥ’ ያየቺው የነ ሂትለርና ተከታዮቹ ባሕሪ Drunken on Genocide Alcohol and mass murder in Nazi Germany” (Edward B. Westemann) የሚል መጽሐፍ ሳነብ እንዲህ ትላለች “በሆሆታ መፈክር ፤ በድል መቦረቅ ፤ ማራኪ የሠራዊት ሰልፍ ፤ በዳንኪራ በጩኸትና በጭበጨባ የታጀበ ጡንቻ “Powerful Drug” (አስካሪ ዕጽ) ነው ትለዋለች፡፡
ጌታቸው ረዳ
የኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ
No comments:
Post a Comment