Wednesday, August 14, 2024

አማራ ውስጥ ገንግኖ እያቆጠቆጠ ያለው ፋሺዝም ካሁኑ ካልተወገዘ ለአገርም ለአማራ ሕዝብም አደጋ አለው! ጌታቸው ረዳ ETHIOPIAN SEMAY 8/14/24

 

አማራ ውስጥ ገንግኖ እያቆጠቆጠ ያለው ፋሺዝም ካሁኑ ካልተወገዘ ለአገርም ለአማራ ሕዝብም አደጋ አለው!

ጌታቸው ረዳ 

 ETHIOPIAN SEMAY

8/14/24

የሰው ልጆች አብረው በማህበረሰብ ለመኖር ይቻላቸው ዘንድ ለአብሮ መኖር ፀር የሆኑ ምግባሮችንና ባህሪዎችን ማስቀረት መቻል አለባቸው። አለበለዚያ ማህበራዊ ኑሮ ሊታሰብ አይችልም። ሰውን ከእንሰሳ የሚለየው ከስሜት ባሻገር የማሰብና የማመዛዘን ክህሎቱ ነው።   (አሰፋ ንጋሽ  / - የዓዕምሮ ሐኪም - አምሰተርዳም)

ከዶከተሩ የምንማረው ምከር ሰዎችከስሜት ባሻገርየማሰብና የማመዛዝን ከህሎት ካልተከተልንስሜትስዎችንግለታምና ችኩልስለሚያደርግቅጽበታዊ  ዕርምጃበመውሰድ ለራሳቸውም ሆነ ለአካባቢያቸው ዘላቂ ጉዳትን ያመጣሉ ማለት ነው። ሰው ሰው የሚያደርገው ምልከቱከግንፍል ስሜት ሲርቅ ብቻ ነው

አሁን እያየሁት ያለው የአማራ የጠመንጃ አብዮት ባብዛኛው በተለይም ባንዳንድ የጎጃም ታጣቂዎች የሚሰነዘሩ ንግግሮች፤ የማየው ስሜትና ንዴት ያጠለቀ፤ የፖለቲካ ምጥቀት (ሶፊስትሪ) ያጣ  በጠመንጃ ድልና በተከታይ ብዛት የሰከረ  ከኔ ሌላ ታጣቂ ("አንጃ" ብሎ የሚጠራው) በዙርያየ እንዳላይ የሚል ዕብሪት የወጠረው  ካለ እኔ አማራ ላሳር በሚል በደምና አጥንት ጥራት እየተኮፈሰተቃዋሚዎቹን አማራ አይደሉምበማለት ብሔረተኝነት እንደ በጎ ፖልቲካ በመከተል ዓለም አቀፍ ሕግ በሚያወግዘው 14/13 አመት የሆኑ ወጣት ልጃገረዶች በማስታጠቅ (የአማራ ፋኖ በጎጃም የሙዚቃ ባንዱን እዩ) ብሔረተኛ ቡድን በማደራጀትና በማስታጠቅ የትግራይና የኤርትራ ብሔረተኞች የተከተሉዋቸው ባሕሪያቶች ሁሉ ያለ ምንም ሰቀቀን ሲያደርግ ይታያል፤ (ያልተከተሉትን በማፈን በማሳደድ በመግደል፤ ስም በማጠፋትና በማሰፈራራት….) ይህ በማቆጥቆጥ ላይ ያለ አደገኛ ቡድን ካሁኑኑ የአካሔድ ዕርማት ካላደረገ ደምበኛ አዋኪና የፋሺስት ቡድን ይወጣዋል።

ይህ ቡደንና መሰሎቹ  መነሻየ አማራ መድረሻየ አማራ በማለት ብሔረተኛ ነኝ ብሎ በገሃድ በማወጅ በጎሳ ብሄርተኝነት የተለከፈ በመሆኑ ምሁራንና ያልተማሩ በጎሳ ብሄርተኝነት የተመረዙ ሰዎች ያለምንም ይሉኝታ ይህ ቡድን የሚወስዳቸው ዕበሪተኛ ዕረምጃዎች ሁሉ በማጨብጨብ ሲከተሉት አያለሁ።

በዚህ አጋጣሚ አንድ ያልጠበቁኩዋቸው ትልቅና ምሁር ሰው <<ከቴድሮሰ እስከ መንግሥቱ ኃይለማርያም>> ድረስ የተድርጉ ጭፍጨፋዎችና ጭካኔዎቸ ሁሉ ፋኖም (የዘመነ ካሴ ድጋፊ ናቸው ሰወየው) ለሥልጣን ሲባል መደረግ አለባቸው ሲሉ በሚያስተላልፉት ዩቱባቸው አደምጬአቸው በጣም ነበር የደነገጥኩት (ሰውየው አማራን በማደራጀት እዚህ አሜሪካ ቀዳሚ ሚና የነበራቸው በበጎ ሳያቸው የነበሩ ሰው ናቸው) ብሔረተኛ መሆን አደገኛና ድንገት ደራሽ ጎርፍ ነው የምለውም ለዚህ ነው።

ይህ የሚያሳየን / አሰፋ ነጋሽ ደጋግሞ እንዳስገነዘበን፡

<<በዚህ አይነት በጎሳ ብሄርተኝነት አይምሮአቸው የተመረዙ ሰዎች የግል ማንነታቸው መገለጫ የሆነውን እንደ ሰው የማሰብ ችሎታቸውን ለጎሳ መሪዎቻቸው አሳልፈው ስለሚሰጡ የአንድ በጎሳ ብሄርተኝነት አስተሳሰብ የተመረዙ ሰዎች በሙሉ የጎሳ መሪዎቻቸው የሚነግሯቸውን እየሰሙና እየተከተሉ እንደ አንድ ሰው ወይም እንደ ጎሳ መሪያቸው ማሰብ ይጀምራሉ። ይህ ፈረንጆች “group thinkingየሚሉትና የአንድ አክራሪ የጎሳ ድርጅት ተከታዮች አንድ ወጥ የሆነ አስተሳሰብ (homogenization of thought) ተሸካሚዎች የሚሆኑበት ሂደት ነው። በዚህ ምክንያት በአክራሪ የጎሳ አስተሳሰብ የተመረዙ ሰዎች በጎሳ መሪዎቻቸው ትዕዛዝ(ውሳኔ) ህይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል። የጎሳ መሪዎቹ የወደዱትን ይወዳሉ የጠሉትን ይጠላሉ የጎሳ መሪዎቹ የመረጡለትን ነገር ሁሉ ለመቀበል ይገደዳል። ምን እንደሚያስብ፤ ከማን ጋር ቡና መጣጣት እንዳለበት፤ ከማን ጋር መወያየት፤ ማንን ማፍቀር ማንን መጥላት፤ በየትኛው የፖለቲካ ስብሰባ ላይ መሳተፍ ወይም አለመሳተፍ እንደሚገባው ወዘተ የጎሳ መሪዎቹ ይነግሩታል በዚህ አይነት የግል ማንነቱን ያጣ ሰው ይሆናል።>> (ሰረዝ የተጨመረ)

እያየሁ ያለሁት ይህ ነው። በቡድን መክነፍ በአማራ ብሔረተኞች ውሰጥ ምሁሩም ማይሙም በአውራጃዊና በአምሐራዊነት የዘር ቆጠራ ጥራት group thinking” ገብቶ ሉጋም የበጠሰ ፈረስ ሆኖ በስሜት ሰክሮ ሲጋልብ ይታያል። (ወያኔዎች እንደዚያ ነበሩ)

ለምሳሌ ይላል ውዳጄ / አሰፋ ንጋሽ-

‘’በናዚ ጀርመን ውስጥ ሰዎች እንደ ሰው ለሕሊናቸው መገዛትን አቁመው ሕሊና ቢስ በመሆን በጥላቻ የሰከሩ መሪዎቻቸውን እነ ሂትለርን፤ በጣሊያን እነ ሞሶሎኒን በጭፍን የተከተሉበት ሁኔታ እንደነበር በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት አይተናል። በዚህ ወቅት በናዚ ፍልስፍና መስፋፋት የተነሳ ብዙ ጀርመኖች ሕሊናቸውን ስተው የሂትለር ፓርቲ ደጋፊና አጫፋሪ ሆነው ስለነበር አብዛኞቹ የጀርመን ተወላጆች ሰው የሚያሰኛቸውን የሕሊና ዳኝነት ክህሎት አሽቀንጥረው በመጣል የግል ማንነታቸውን አጥተው የናዚን ፋሽስት የፖለቲካ ፍልስፍና ስርዓት ተከታዮችና አቃፊ ደጋፊዎች ሆነው ነበር። የናዚም ሆነ የፋሽስት አክራሪ የጎሳ ብሔርተኝነት ተከታዮችን ከሰውነት ተራ በመውጣት የግለሰብ ማንነታቸውን አጥፍቶ እንደ እንሰሳት መንጋ የአንድን የጎሳ ድርጅት መሪዎች በጭፍን እንዲከተ ያደርጋል።’’

ራስን መከላከልና የሕልውና ትግል ከብሔረተኛነት ፖለቲካና ባሕሪ (በካራከተር) ይለያሉ አብረው አይሄዱም እነሆ አገራችን ውሰጥም በሔረተኛነትና በቡድን መክነፍንና መዘመርን ቁቡል ሆኖ አማራውም ራስን በመከላከል ስም ያለምንም ማንገራገር ወደ በሔረተኞች ጭቃ ውስጥ ገብቶ ሲምቦጫረቅ ማየት ሁላችንም በተለይ እኔ ከገምትኩት በላይ ነው።

ብሔረተኛነት በኩራት ተቀብለውት ምሁሩም ማይሙምየፖለቲካ ጥበብ (ሶፊስትሪ) ባጠረው ባንድ ዕብሪተኛናጠመንጃ ነካሽየሆነ ወጣትዘመነ ካሴበሚባል (ከላይ የጠቀስኩዋቸው ለለሥልጣን ሲባል ጭፍጨፋ መካሄድ አለበት እንዳሉት ሰውየ) ካለ የራሱ ጀሌዎች ታጣቂ በቀር ሁሉንምመጨፍጨፍ” “ማጥፋት” “ማሰር” “ማስፈራራት” “ማጥራትአለበኝ ብሎ በግልጽ ባወጀ ብሔረተኛ እየተምሩ ማየት የሚገርም የኋሊት ጉዞ ነው።

ጀርመን ውስጥ በታሪክ እንዳነበብነው (ትግራይም በመለስ የተመራው ፋሺዝም) የጀርመን ደም የሌለውመነወር መጥፋትና መገለልእንዳለበት ከሁሉም በላይእኛበሚለው የአርያን የዘር የበላይነት በሚያንፀባርቅ አስተሳሰብ ተመርዞ የተከተለው የጀርመን ሕዝብ የአርያን የዘር የበላይነት በሚያንፀባርቅ አስተሳሰብ በጎውና መጥፎውን የሚለይበትን ህሊናውን አሽቀንጥሮ በመጣል የራሱን ማንነት አሳልፎ ለናዚ መሪዎች በገፀ-በረከትነት ሰጥቷል። ብዙዎቹ ውጭ አገር የሚኖሩ የአማራ ምሁራንም ልክ እንደ ሂትለር “Nordic! Nordic! “አማራ! አማራ!” እያለ በግለት ለሚያስፈክራቸው ወጣቱ ፋሺስት የራሳቸውን ማንነት አሳልፈው በመስጠትባንድ ቤት አንድ መሪበሚል ፋሺሰታዊናሰንትራሊሰትለመመራት በመኮልኮል ላይ ናቸው።

በግሌ አሁን የገባሁት የፖለቲካ ሁኔታ የትግሬዎችና የኦሮሞ ብሔረተኞች ስታገላቸው እንደነበረው ሁሉ፤ አማራዎችምወደ ብሔረተኛነትበመግባታቸው  ተመሣሣይ ሁኔታ በማየቴ በዛው ባለፍኩት አድካሚ ጉዞ እንደገና መግባቴን ሳይ አዘንኩ።

ቀለም ቆጠረ የሚባለው አማራው ክፍል በዛው በክፉ ዘመን ወቅት የመርዘኛው የትግራይ ብሄርተኝነት ሰለባ በመሆን ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነ የወያኔ አገዛዝ ደጋፊና አቃፊ ሆኖ ሲያስቸግረን መኖሩን ብዙዎቻችሁ ታውቃላችሁ ብየ እገምታለሁ። አሁን ደግሞ አንጃ" አላውቅ ምን አላውቅበማለትከሱ የተለዩትን እያነቀየሚገድልና የሚያግት፤ የሚጠልፍ፤ ሽማግሌዎችን በእምብርክክ የሚያስኬድ እብሪተኛየፋኖ መሪ አፈ ቀላጤ ሆነው ለሚደርሰው ሰብአዊ ጥሰት ከመቃወም ይልቅ አጉራ ዘለል የመንደር ጎረምሳ  አቃፊና ደጋፊ  (በተለይ ዲያስፖራ) ሆነው ተከስተዋል። መጨረሻው ምን ይሆን? የነ ተሎ ተሎ ቤት ግድግዳው ሰምበሌጥ!!

ጌታቸው ረዳ

 

 

 

No comments: