Friday, June 30, 2023

አፈንጋጮች የፈጠሩት ባለ አዲሱ “ዲ ኤን ኤው” ትውልድ መልስ ለፊልም ሰሪና መምህር ለፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ በኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ ዕይታ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 6/30/2023Haile

                             አፈንጋጮች የፈጠሩት ባለ አዲሱዲ ኤን ኤው” ትውልድ

መልስ ለፊልም ሰሪና መምህር ለፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ

በኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ ዕይታ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

6/30/2023Haile

 

Haile Gerima film imperfect journey 

ትናንት እስታሊን የተባለ “ኢትዮጵያ ፈርሳ ሳልሞት በህይወቴ ማየቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ” በማለት የታወቀው ጸረ ኢትዮጵያው ድዋዊው የወያኔ ሚዲያ ቱልቱላ ለፕሮፓጋንዳው እንዲመቸው የአንዳንድ እውቅ ኢትዮጵያዉያን ምሁራን ቃለ መጠይቅ እየዳሰሰ ይጠቀምባቸዋል። ትናት ድንገት ፌስቡክ ቪዲዮ ላይ የዚህ ልጅ ሚዲያ “በቲክ ቶክ ቨርዢን” ያየሁት የፊልም መምህርና ፊልም ሰሪ የሆኑት ታዋቂው  የሃርቨርድ መምህር ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ እያሞካሸ ንግግራቸው ሲያደንቅ ድንገት አደመጥኩና የሰጡትን አስተያየት ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የማይገናኝ  ስሜተኛ ወቃሽ (unrelated blame) ሆነው ስላገኘሁዋቸው አልተመቹኝም።

 ቪዲዮው የቆየ ቢሆንም ንግግራቸው ግን አሁንም ስራ ላይ ነው (አክቲቭ ነው)። ምሁር ናቸው፤ የፖለቲካ ምጥቀታቸው ግን ጠንካራ አይደለም። ስለ ኢትዮጵያ ያላቸው ፍቅር ግን ሞልቶ የፈሰሰ ፍቅር እንዳለቸው አጠራጣሪ አይደለም። ችግሩ የሚከተለው አባባላቸውን እንምለክት፡

ባንድ በዛው በቀረበው ቃለ መጠይቃቸው እንዲህ ይላሉ፡             

<<ከኢትዮጵያ ማፈንገጥ የተጀመረው ማፈንገጥ ፈልጎ ሳይሆንና ፈረንጆች ቆርቁረውት ሳይሆን፤ “ኢትዮጵያ” የሚለው ነው “እንድታፈነግጥ” የሚያደርግህ። የኢትዮጵያን ትርጉም ሳይገባው፤ታሪኩን ሳያውቅ “ሴንትራሊቲውን ይዞ” ቪዛህን ይጠይቅሃል፡ ያኔ አፈንግጠህ ትሄዳለህ፤ ይሰለችሃል።  ኢትዮጵያዊም ሆነ ኤርትራዊ አንድ ላይ ለመሆን የሰለቸው “ለወደፊቱም ብዙ ሊሰለቻቸው ይመጣሉ)፤ ይህችን መሃሉን ይዞ እኔ እኮ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያሰቃይህ ነው ችግሩ”>>፡ ይላሉ

መሃሉን ይዞ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ባይገባኝም (እንደ ወያኔዎች አባባል ወይንም እንደ ተኮላ ሓጎስ አባባል “ሸዋ” (መሃለኛው አገር?) ማለት ይሆን? ወይስ ሌላ ትርጉም?

ይሁን እና ፕሮፌሰሩ በደፋና ከመናገር ይልቅ በስም ቢገልጹልን ይቀለን ነበር ፤ ሆኖም በደፈና ለገለጹት ትንታኔአቸው መልስ ያሸዋል።

ይህ አባባለቸው የወያኔና ኦሮሙማ ሚዲያዎች በደምብ ወድደውት “ለማፈንገጣችሁ” ምክንያት “ኢትዮጵያ” የሚለው ሃይል ነው ብለው ጥሩ “የመሸሸጊያ ሽፋን” ስለሆኑላቸው በየሚዲያቸው እንደ ምሳሌ እየጠቀሱ ቪዲዮውን እየደጋገሙ ሲጠቅስዋቸው እያደምጥን ነው። የፕሮፌሰሩ አባባል በስነልቦና እሳቤ (ትምህርት) ከውስጣቸው የሚከነክናቸው ባንድ ቡድን የተገፉበት በግሃድ ሊነግሩን ያልፈለጉ የተዳፈነ ቁጣ እየገፋቸው እንደሆነ እገምታለሁ። ያም ሆነ ይህ ምክንያታቸው ከፖለቲካ ዐውቀት ደካማነት የተነሳ ነው ብየ እገምታለሁ።

ባጭሩ ያም ሆነ ይህ፤ አባባላቸው ለቃላቴ አጠቃቀም ይቅርታ እየጠየቅኩ ይህንን ታላቅ አትዮጵያ ሰው መዳፈር እንደሆነ ሳይወሰድብኝ “የፖለቲካ ድንቁርና” ይመስለኛል። አንድ ቡድን/በራሳቸው ቃላት “ትውልድ” አፈጋጭ የሆነበት ምክንያት አንድ ሰው “እኔ ብቻ ነኝ ኢትዮጵያዊ” ስላለው እንዲህ ለምን ትለኛለህ ብሎ “ያፈነገጠ አፈንጋጭ” ከ1960 ጀምሮ እስካሁን ድረስ አልሰማሁም። እሳቸው እንሚነግሩን ኤርትራኖችና አንዳንድ ኢትዮጵያዉያን (ኦነግ ፤ወያኔ ወዘተ…) ተገንጣይ ክፍሎች ለፍንገጣቸው ምክንያት እሳቸው ከሚሉት ጭራሽ አይገናኝም።

የዛሬ ትውልድ ከ60ዎቹ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያለው ማለቴ ነው አዲስ DNA (መለ-ዘር) በጭንቅላቱ ተተክሎበታል። አፈንጋጭም ሆኗል፤ ሌባም አጭበርባሪም ገዳይ የሰው ስጋ የሚበላ (ካኒባሊሰት) ዕርጉዝ የሚያርድ የሰው ደም ጨው ጭምሮበት የሚጠጣ ትውልድ ቢያነስ ወደ ላ ትተን በዚህ 5 አመት ውስጥ እንኳ በተጎጂ እማኞች ምስክርነት ሰምተናል በምስልም አይተናል። ለዚህ አፈንጋጭነትም ሆነ አጭበርባሪ ባሕል የመለውጥ ምክንያት እውን ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት ነው? አይደለም።

ይህንን በተመለከተ አንድ  የኔን የብዙ አመታት የትግል ልፋት ኣይቶ ሁሉንም በየመልኩ እየታገልኩና እየተበሳጨሁ መምጣቴን ኣይቶ አንድ ወዳጄ በኢመይል የጻፈልኝን የቆየ መልዕከቱ ላጋራችሁ ፡

እንዲህ ይላል፡-

 ይህ ትውልድ የወላጆቹና የድሮ ቅድመ ኣያቶቹ DNA ከውስጡ አለ ለማስተማር ከጣርክ ድካምህ ከንቱ ነው፡ ጤንነትህም ላይ ቀውስ ያመጣብሃል። አገሪቱ ትኖራለች; ትውልዱ ግን የተለወጠእርኩስ ፤ ለብቻየ የሚል ግለኛ፤ ስሜተኛ፤ዘራፊ፤ መሃይም፤ ወላጆቹን የሚዳፈር ብሎም የሚገድል፤ ሃይትን የግንዘብና የዝሙት መጠቀሚያ የሚያፈደርግ አጭበርባሪ፤ ደፍሮ በማይገባበት ትግል ጨፋሪና ባሕል አልባ የሆነ ባለ አዲስ DNA በምድሪቱ ላይ መኖሩ ላንዳች ደቂቃም ቢሆን አትጠራጠር

ሲል ጽፎልኝ ነበር።

ይህ ባለ አዲስ DNA ትውልድ ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት “ኢትዮጵያ” የሚለው ሃይል ነው እንዲለወጥ ያደረገው ወይስ በአገራችን አዲስ የባህል ወረራ ስለተፈጸመ ነው? መልሱ ለገንጣዩ (ላፈንጋጩ) ምክንያት “አዲስ የባሕል ወረራ” በመከናወኑ ምክንያት ነው።

ይህ እንዲፈጸም የብዙ መቶ አመታት በውስጥ ቅጥረኞቻቻው እና በውጭ ሃይላት የተከናወነ አዝጋሚ ሂደት ተከናውኗል። በኢትዮጵያ ታሪክ ሁለት ክስተቶች ተከስተዋል። ገንጣይና እና የግንጠላ ቀስቃሽ (አስፈንጋጭ እና አፈንጋጭ)።

ኢትዮጵያ ከዘመነ አክሱም ጀምሮ የሃይማኖት፤የመልክአ-ምድር እና የባህል ወረራ ተፈጽሞባታል። አጥቂዎቹ ከዘመነ አክሱም ጀምረው ያው እነሱ ናቸው አልተለወጡም (ትንሽ አዳዲሶች ተጨመሩባቸው እንጂ የጥነቶቹ ናቸው፡)  አንዴ ይሳካላቸዋል፤ አንዴ አልተሳካለቸውም። ለዘመናት ሲሸምኑት የነበረው ሴራ በ1983 ዓ.ም በትግሬዎች በኩል በመጨረሻ  ተሳካለቸው። ከላይ ወዳጄ የጠቀሰውን የባህልና የፖለቲካ እንዲሁም የመልክአ-መሬት *ግንጣላ/ማፈንገጥ” ለውጥ በኢትዮጵያ ተከናውኗል። ኤርትራም ተገንጥላለች ትግሬዎችም ግንጠላው እውን ሊያደርጉት ሞክረዋል፤ አልተሳካም ፤ አሁንም ቢሆን አልተኙም።

 ኦሮሞዎችም የመልክአ-ምድር፤ የባህል የጽሑፍ ቋንቋ ለውጥ አድርገው የመሬትም የባህልም ወረራ ፈጽመዋል፤ ብዙ ጉዳት አድርሰዋል፤ እያደረሱም ነው። ይህ ሁሉ የተከሰተው ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት አፈንጋጮቹ “ኢትዮጵያ” የሚለው ሃይል ስላስገደዳቸው ሳይሆን በደምብ የተጠና ሴራ በአገራችን ለዘመናት በሂደት ስለተከናወነ ነው። እነዚህ ሴራዎች ምንድናቸው?፡ፕሮፌሰሩ አያውቁዋቸውም ሳይሆን አንባቢን ለማስገንዘብ ነው፡

ከራሴ መጽሐፍ የተገኘው “የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው?” ከሚለው  ‘የብከላ ሂደት በኢትዮጵያ *ሳብቨርዥን” ከሚለው ንኡስ ርዕስ ልጥቀ

 (ለ) አራቱ የግዝገዛ ደረጃዎ……..91

   1-የሞራል ዝቅጠት Demoralization ………………ገጽ91           

   2-አገርን ማናጋት   Destabilization………………ገጽ93

   3-በቀውስ ቀለበት ውሰጥ መግባት  Crisis…….  ገጽ104

   4-የውሸት እርጋታ    Normalization………….  ገጽ104

ብታነቡት አፈንጋጮችም ሆኑ አሁን ላላው ባለ DNA አዲሱ ትውልድ ልናይ የበቃንበት ምክንያት ከላይ የተጠቀሱ በውጭ ጠላቶች ቁርቆራ (ሽፍን ወረራ) አራቱ ዋና ዋና ርዕሶች ተግባራዊ ስለሆኑ ምክንያት እንጂ ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት “ኢትዮጵያ” የሚለው ተናጋሪ ወይንም ቪዛ ሰጪና ከልካይ ምክንያት የተጫወተው ጨዋታ ከኖረ “ኢሚንት” ነው። ከኖረም ጉዳቱ (ኢፌክቱ) ፈረንጆቹ “ኢነሲግኒፊካት” የሚሉት “ኢምንት” ነው።

ጋዜጠኛና ደራሲ መስፍን ማሞ ስለ ሟቹ ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሹፋ አንስቶ ባንድ ጽሑፉ ኢብራሒም የከተበውን አንዲህይ ጠቅሳል፤ (ባጭሩ አሳጥሬ እጠቅሳለሁ)፤

“ታሪክ ያለቀ ነው፤ የተፈፀመ። ስለዚህም ስህተት ከነበር ለይተን ልናርመው፤ በጎውን አውጥተን የበለጠ ልናጎለብተው እንጂ። ‘ቴዎድሮስ ካሳሁን አፄዎቹን ያወድሳል። አፄዎቹ ደግሞ ሙስሊሙን ጨቁነዋል…ሙስሊም እንደ መሆንህ መጠን ልትቃወመው ይገባል’ የሚል ‘ምሁር መካሪን’ ራሴው ዓቃቤ ህግ ሆኜ፣ ክስ መስርቼ፣ ጥፋተኛ አስብዬ፤ ራሴው ደግሞ ዳኛ ሆኜ እስር ቤት ብወረውረው ደስ ይለኛል…ምኞቴ ነው። ይሄንን ‘ምክር’ እንኳን ለዕድሜ አቻዎቼ ለመጠቆም አደባባይ ልወጣ አይደለም አብረውኝ ላደጉት በጣም ለምወዳቸው በዕድሜ እጅግ ታናናሾቼ ለእህቶቼ ልጆች ዘኪዬ እና ኢብሮዬ አይመጥንም። ሳት ብሎኝ ይኽን ስል ቢሰሙ እንኳን (ፍፁም አልልም እንጂ) በእነርሱ የግንዛቤ አቅም እንኳን እየነሆለልኩኝ መሆኔን ልብ ብለው የሚስቁብኝ ይመስለኛል…አጎቴ ምን ነካው?

ይልና

…..ኢትዮጵያ የብዙ ሺህ ዓመታት ውጤት ነች። በጣም በርካታ መጽሐፍትም ስለ ኢትዮጵያ ተጽፏል። ከተለያዩ አቅጣጫዎች እና ፍላጎት ጋር’ ሲሉን ነበር። አዎን ኢትዮጵያ ብዙ ነች። ያለፍንበት ዘመንም ረጅም ነው። ያለፍንበት ዘመንን የሚገልፁልን ብዙ መጽሐፍትም አሉን። እነዚያን መጽሐፍት የምናነበው፣ የምንመረምረው እና የምናጠናው አሁን እኔ ቂም ወርሼ፣ ጥላቻን በልቤ አርግዤ፣ በቀልን በመሻት ከወንድሜ ጋር ልጋደልባቸው አይደለም…ዘኪዬ እና ኢብሮዬም ጊዜያቸው ሲደርስ ከወንድሞቻቸው ጋር እንዲፋጁ አይደልም… አንድ የሚያደርጉንን ነጥቦች ነቅሼ፣ የሚያስማማንን አበጥሬ እና በጋራ የሚያኮሩንን ለይቼ ብላቴናው የሚመኛትን በፍቅር የተሞላች ምርጥ ሀገር ለማየት እንጂ…!!! ለማንኛውም ወደ ፍቅር ጉዞ እያላችሁ ደግሞ ዛሬ………..!!!” >>  (ኢብራሂም ሺፋ)

ብሎ ጽፎ ወደ እማይቀረው ዓለም ተሰናብቶናል ሲል ብዕረኛው አውትራሊያ የሚኖር ጋዜጠኛና ደራሲ መሰፍን ማሞ ጠቅሶታል።

ከሟቹ ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሹፋ የምንይዘው ነጥብ ፡

<ያለፍንበት ዘመንም ረጅም ነው። ያለፍንበት ዘመንን የሚገልፁልን ብዙ መጽሐፍትም አሉን። እነዚያን መጽሐፍት የምናነበው፣ የምንመረምረው እና የምናጠናው አሁን እኔ ቂም ወርሼ፣ ጥላቻን በልቤ አርግዤ፣ በቀልን በመሻት ከወንድሜ ጋር ልጋደልባቸው አይደለም…ዘኪዬ እና ኢብሮዬም ጊዜያቸው ሲደርስ ከወንድሞቻቸው ጋር እንዲፋጁ አይደልም…>>

 የሚለው ምክር የሚያሳየን ፕሮፌሰሩ የሚለትን ሳይሆን ለቂምና ለአፈንጋጭነቱ መነሻ ያለፈውን እየነቀሱበቀልን በመሻት አርስ በርሳችን እንድንጋደል በውጭ ሃይላት የተጻፉት መጻሕፍቶች  እንደ እነ 1) Marxism and Leninism; Stalin 2) Abyssinia The Powder Barrel  A Book the most burning question of the day;(Author- Baron Roman Prochazka 1935) በጣሊያን ጊዜ ሙሶሊኒ አስተዳዳር ኢትዮጵያነ ሲያስተዳድር የተከለው አስተዳዳር ምን እንደሚመስልና (ትግሬዎችና ኦሮሞዎች እንዲሁም ኤርትራኖች) የተከተሉት አሁን ላላው የርስ በርስ መገዳደልና ማፈንገጥ መነሻ እንደሆነ በግሩም አቀራረብ ሰነዱን አስደግፎ የጻፈ ጣሊያናዊው ፕሮፌሰር አልቤርቶ ሳባኪን መጽሐፍ ማንበብ ነው፡ (3) Ethiopia: The Last Two Frontiers (Eastern Africa Series, 10) Paperback – August 15, 2013 by John Markakis (Author) (4) Ethiopia: Anatomy of a Traditional Polity - by John Markakis 1974) እና የመሳሰሉ መጽሐፍቶችን ማንበብና  እና አሜሪካኖችነ አንግሊዞች በኢትዮጵያ ምሁራን ታዋቂ ሰዎችና ወታደራዊ ክፍሎች “ሲ አይ ኤ” እና “ኤም አይ” እንዲሁም እስላሙ ክፍልም አረቦች የመለመልዋቸው “ዋሃቢዎች” የተለያዩ የጴንጤ፤ የ666፤ ወዘተ….ሃይመኖት የውስጥ ተቀጣሪዎች ለፍንገጣው ዋና ተዋናዮች ናቸው።

ፕሮፌሰሩን ላስታውስ የምፈልገው “ጯሂ ያጣ ጩኸት” የሚለው የፕሮፌሰር የመጨረሻ መጽሐፍ ላይ በምርጫ 97 (በወያኔ ጊዜ) አንዲት የአሜሪካ ዲፕሎማት “የታሰሩ የፖለቲካ መሪዎች” እስርና መፈታት ጣሊቃ በመግባት (ድብቅ ስራዋን ለመስራት) ለማስፈታትና ለማስታረቅ ላይ ታች ስትል የነበረች አሜሪካዊት ባንድ ስብሰባ ላይ “ኢትዮጵያ ለአራት ትከፈላለች፤ ይህ የማይቀር ነው” ስትል ጩሆታችሁ ፋይዳ አያመጣም ማለትዋን ጽፈውታል። ይህ እንግዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ አፈንጋጭ የበዛበት ምክንያት ከውጭ ሃይላት የተጠናቀረ የባህልና የፖለቲካ ሴራ ሥራው በደምብ ሰርቶ እሸት ሆኖ አፍርቶ ሴራው ስለተሳካ እንጂ “ኢትዮጵያ” የሚለው ምክንያት ሰውን እየገፈተረ ስላስፈነገጣቸው አይደለም (በምርጫ 97 አሜሪካን ኤምባሲ የተጨወተው የጣልቃ ገብነት ሚና ከትዝታችን ውስጥ አሁንም አለ፤ ዛሬም እየተጨወቱ ነው) ።

 ወያኔዎችና ኦነጎች የፕሮፌሰሩን ንግግር እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ማታም ጥዋትም በየሚዲያቸው ሲሰብኩበት ማየታችን የሚያስገርም ባይሆንም ፕሮፌሰሩ ግን አገሪቱ በውጭ ሴራና በአገር ቅጥረኞች ሴራ “በአፓርታይድ ፋሺዝም” እየተነዳች መሆንዋን ማየት ተስኗወቸው “አፈንጋጩ” *እኔ የምተረጉመው (አፓርታይዱ) “ኢትዮጵያ” የሚለው ሃይል ነው  የፈጠረው  የሚለው ክርክራቸው ካንድ የታወቀ ከፍተኛ ምሁር የሚጠበቅ ንግግር እይደለም። አፈነገጠ ማለት “ሄደ ወጣ፤ከመስመር ውጭ ከማዕከል ተሰናበተ፤ተገነጠለ……ወዘተ ያለው ትርጉም ነው። ተገንጣዩ ለአፈንጋጭነቱ እሳቸው የሚሉት ምክንያት ቢሰጥም ሃቅነት የለውም።

“ከኢትዮጵያ ማፈንገጥ የተጀመረው ማፈንገጥ ፈልጎ ሳይሆንና ፈረንጆች ቆርቁረውት ሳይሆን” የሚለው ክርክራቸው ስንፈትሽ፤  የመከነ ትውልድ ይልቅኑ ለምን ተፈጠረ የሚለው ብከላ ቢያጤኑት እየመከርኩ፤ ለምሳሌ የወላጆቹና የድሮ ቅድመ ኣያቶቹ DNA ከውስጡ ተለየው ‘የ27” አመት አዲሱ ትውልድ በትንሹ እንፈትሽ ብንል በፈረንጅ ባሕል ቁርቆራና በውስጥ አርበኞች የባሕል ወረራ አጥማቂ ቡድኖች መሆኑን ባንድ ገጣሚ የተገጠመውን ግጥም እንስማማና በዚሁ ግጥም አንባቢዎቼን ልሰናበት፦

ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ!

ሲታሰር ለሽ ብለሽ ሲፈታ ሆይ ሆይ!

የሚለው ስለ ሕዝብ የታሰሩትን ለማስፈታት ከመታገል ይልቅ ተሰቃይተው ከእስር ሲፈቱ በሆይ ሆይ እና  ዕልልታ የሚጨፍርና የሚቀበል፤ እንደ አህያ ሜዳ አደራሽ ወለል ላይ እየተንከባለ አጭበርባሪ የሃይማኖት ሰባኪዎች የሚጫወቱበት የሃይማኖት ተሰባኪ የተፈጠረባት ኢትዮጵያዊ አዲስ ትውልድ የተረጨበት አዚም ስንፈትሽ “ኢትዮጵያ” የሚለው ሃይል ሳይሆን “አዚም” ሰሪዎቹ ለ35 አመት በወጣቱ ሕሊና ያጠነጠኑት ድብቅ የውስጥና የውጭ አገር የአስፈንጋጮችና የአፈንጋጮች አዚም መሆኑን ይህችን ትንሽዋን ምሳሌ ማየት በቂ ነው።

እርስዎ “ቁርቆራ” (ውትወታ) የሚሉት እኔ “የውስጥ ቅኝ ግዛት” ብየ የምተረጉመው “ቁርቆራ” ለ35 አመት ኢትዮጵያን እያሰቃያት ያለው ሃይል “ኢትዮጵያ” የሚለው ቡድን ሳይሆን ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ በውጭ ሃይላት የተሰበኩና የተቀጠሩ አፈንጋጭ ሃይሎች ናቸው።

ሰላም እንሰንብት!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

 

No comments: