የኢሳያስ አፈወርቂ የወያኔን ጸረ ኢትዮጵያነት የገለጸበትን ንግግሩን በመቁረጥና በማዛባት የወያኔን ባሕሪ ለመሸፈን የተከሄደበት የኤርሚያስ ለገሰ ኮምፓስ ሚዲያ
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
July 3, 2023
ትናንት በድንገት ፌስቡክ ቪዲዮ ላይ አንድ ነገር ተመለከትኩኝ እና ቀልቤን ሳበው። ያልተናገረውን ንግግር ቆርጠው ኢሳያስ ኢትዮጵያን ቆራርጠን እንበትናታለን ብሏል ብላ የዋሸችን አዲሲትዋ የወያኔ “ፓስተር” ማርያማዊት በኤርሚያስ ለገሰ ሚዲያ ተላልፎ ተገረምኩኝ።
ለዘመናት አታድረጉት እያልናቸው ከጽንፈኞች እና አፈንጋጭ ቡድኖች ጋር የከሰረ የመሞዳመድ ፖለቲካ ከስሮ ያየንበት ወቅት ሳይበቃን” ዛሬ ይግረማችሁ ብሎ ኤርሚያስ ለገሰ
ተመልሶ እንደ አዲስ ወደ አክራሪ ሃይላትን በመጠጋት ፖለቲካ እየሰራ እየመሰለው ያለው ኤርሚያስ ለገሰ ጋር ይህች “ፓስተር” አብራው በሚዲያው ውስጥ ትስራ አትስራ ባለውቅም (ምክንያቱም ሚዲያው ብዙም አልተከታተልኩትምና)
ሆኖም
በ2018 ዓ.ም (በፈረንጅ ዘመን ) ኢሳየስ አፈወርቂ ያደረገውን ቃለ መጠይቅ ማርያማዊት የተባለች ይህች ሴት የተለያዩ ዕንግዶች በተጋበዙበት የውይይት መድረክ
ላይ ኢሳያስ በ2018 (በፈረንጅ) ዓ.ም ቃለ መጠይቁ ውስጥ ወያኔ ስለ ኢትዮጵያ የነበረው የ27 አመት ጸረ ኢትዮጵያ
ባሕሪና ፖሊሲ ባስገራሚ አገላለጽ የገለጸበትን ቪዲዮ “ጠምዝዛ ቆርጣ” ኢሳያስ ኢትዮጵያን በታትነህ ማጥፋት’ ነው ብሎ የተነጋረበትን ይኼው ቪዲዮውን አድምጡ ብላ ከአንድ ኤርትራዊ እና
ሁለት ትግሬ፤ አንዱ ያልተገራው እስታሊን ገብረስላሴ ነው ሌላው Eri 360 (Ethio 360ን ላማጣጣልና ለመስደብ የተዘጋጀ) በኤርትራ ሚዲያ “ስም” ሽፋን ፕሮፓጋንዳ የሚሰራ የታወቀ የፌስ ቡክ የወያኔ ቱልትላ ካድሬ
እና ሦስተኛዋ እርስዋ አዘጋጅዋ። ከነዚህ በስተቀር ሌለው አንድ ኦሮሞ
የኩሽ ሚዲያ አዘጋጅ (ሸኔ ኦነግ) ፤ እና ሌላው መሞዳሞድ መለሳለስ የሚታይባቸው አማራ የመስሉኛል (ካልተሳሳትኩ) ኢንጂነር ሙሉጌታ ይባላሉ። ሌለው ኤርሚያስ ለገሰ ነው።
በተቀረ
ትግረኛ የማያደምጡተን 3 እንግዶችን ለማሳመን
ኢሳያስ የተናገረውን እውነተኛ የወያኔን አጀንዳ ወደ ኢሳያስ በማዞር ወያኔነትዋን ለመከላከል የሄደችበት ርቀት ሳደምጥ “ይህች ልጅ ሁሌም ትገርመኛለች” (ካሁን በፊት በዚች ልጅ የሰራሁትን አቃቂር (ኮመንታሪ አሁንም ፈልጉት ተለጥፏል)።
ኢሳያስ ወያኔን ለምን በሚገባ በጥሩ የትግርኛ አገላለጽ ወያኔን አጋለጠልን በሚል እሳቤ ነው? ወይስ ምንድ ነው?
ኢሳያስ ለወያኔ የገለጸውን እውነተኛ የወያኔ ገጽታ ደብቀው ኢሳያስ ለኢትዮጵያ እንደተናገረና እንደተመኘ አስመስለው ከሙሉ ንግግሩ ቆርጠው ለምን ውሸት አቀነባብረው ትግርኛ ለማያደምጡና ኢሳያስ ቃለ መጠይቅ ያላደመጡ ትግረኛ
አድማጮችን የማይገባ ፕሮፓጋንዳ ሊሰሩ ሞከሩ?
አዛብተው ያቀረቡትን የኢሳያስ ንግግር እንዲህ ይላል፤
መጀመሪያ ትግርኛ ከዚያ አማርኛ እተረጉምላችኋለሁ፤
አርእሰቱ ደግሞ አስቂኝ ነው ፤ መሳቅ ካለባችሁ ከዚህ አርእስቱ ጀምሩ!
እንዲህ ይላል
“ብልፅግና ፓርቲ ደብቆት የነበረው ቪዲዮ አፈትልኮ ወጣ!!” ይላል፤
አሁን እስኪ በፈጣሪ! ብልፅግና በዚህ ቪዲዮ የምን ሞኖፖሊ አለውና ደበቀው?
እውነት ይሄ ያልበሰሉ መሃይሞች በየ ቲክቶኩ የሚያቀርቡትን ቪዲዮ አምጥታ
እንደ እውነት ማስተጋባትዋ የሚገርምም የሚያስቅም ነው። አየ ኤርሚያስ ለገሰ “ታጥቦ ጭቃ?” የወያኔዎች ፕሮፐጋንዳ መሳሪያ ሚዲያ ሆነህ አረፍከው?
የተዛባውና ተቆራርጦ የቀረበው የኢሳያስ የትግርኛ ንግግር እንዲህ ይላል፤
“ኢትዮጵያ ፋሕ ፋሕ ከነብላ ኣለና ፤ ኢትዮጵያ በታቲንካ በታቲንካ ክትቋጻጸራ ፤ ብፖለቲካ ፋሕፋሕ ከተብላ አለካ ንኢትዮጵያ። ምስ አምሓራስ ይትረፍ ብሓባር ክንነበር ብሓባር ክንልምን ኣይንኽእልን። ኢትዮጵያ ክንገዝኣ ወይ ከነማሓድራ እንድሕር ኮይንና ኢትዮጵያ ፋሕ ፋሕ ከነብላ ኣለና”
ተቆርጦ ተጣምሞ የቀረበው የላይናው አማርኛ ትርጉም ትርጉም እንዲህ ይላል
አማርኛ፡
“< ኢትዮጵያ በታትነን አንድትበተን እናደርጋታለን። ኢትዮጵን ለመቆጣጠር በፖለቲካ በመበታተን ነው። ከአምሐራ ጋር እንኳን አብረን መኖር አብረን መለምንም አይቻልም። ኢትዮጵያን ለመግዛትና ማስተዳዳር ከፈለግን ኢትዮጵያን እንድትበታተን ማድረግ አለበን።”>>
ይላል ማርያማዊት የኢያሳያስን ንግግር በማጣመም ቆርጣ ቆራርጣ
ያሰራጨቺውን የውሸት ፕሮፓጋንዳ።
እውነታው ግን ያ አልነበረም፤ ይህች ልጅ ለምን እንደምትዋሽ ባይገባኝም (ኢሳያስን ስለጠላች ያልሆነ የውሸት ፕሮፓጋንዳ አጣምማ ማቅረበዋ ወያኔ ለምን ተጋለጠ ነው?)።
የኢሳያስ ትክክልኛ ንግግር ግን ያልተቆረጠው ንግግሩ ይኼው እንዲህ ነበር ያለው።
“25 አመት አልፏል በግምገማ ስንመለከተው እኔ “ሙክታታት” ነው የምለው “ጆክስ” ቀልዶች ማለት ነው። ወያኔዎች የኢትዮጵያ ፌደራል መተዳደሪያ የሚሉት ወረቀታቸው ተመልከቱት፤ እኔ አይቸዋለሁ እንደ እዚያ ያለ የዘመኑ መሳቂያ (ጆክ) ማግኘት አትችሉም። የሚገርመው ደግሞ በአገሪቱ የተለያዩ ቡድኖች ግጭት መፍቻ ተብሎ አንድ አካል የጻፈው
ሕገ መንግሥት ተመሰረ።
እንደዚህ ያለ የሚገርም “ጆክ” ፈልገህ የትም ዓለም ማግኘት አትችልም።
,,… ያ አጀንዳ ኢትዮጵያ ብሔሮች መታዳደርያ ብለው ይጠሩታል። ግን የወያኔ መተዳደርያ ነው።
…… አንቀጽ 39 የሚባለውን በፌደራላዊት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ስም የተደነገገው አንቀጽ የወያኔ ቁጥር አንድ አጀንዳ ነው። እባካችሁ አንብቡትና ምን እንደሚል ትረዱታላችሁ። ይህ አንቀጽ ሰትመለከቱት
አንቀጹ እራሱ የሚወስደን ኢትዮጵያ በብሔር፤ በኤትኒክ ተከፋፍላ መበታተን አለባት ነው።
,,….. በነዚያ ያለፉት 25 አመት ፖለቲካውን ስንፈትሽም እንዴት ወደ እንደዚያ ያለ አገር በታኝ ፖለቲካ ሊከሰት ቻለ ብትሉኝ እኔ የምለው “የወያኔ በሽተኛ ሕሊና” ያመጣው ክስተት ነው። ይህ ደግሞ የወያኔ ቁጥር አንድ የወያኔ አጀንዳ ነው።
…… ካሁን በፊት ሁለቱ አገሮቻችን እንዴት በሰላም ማስኖር አንችላለን ብለን ግንኙነት ፈጥረን ነበር፤ እነሱ ግን “አይሆንም ከኢትዮጵያ ጋር አብረን መኖር አንችልም አንኳን አብረን መኖር አብረን መለመንም አንችልም” ሲሉን ነበር። እኛም እስኪ ይበርዱ ይሆናል ብለን ሁኔታውን ተከታተልነው።
……. እኛ ከመቶ 6 ነን በሕዝብ ብዛት። ስሆነም ኢትዮጵያን ለመግዛት ከፈለግን ፡ኢትዮጵያን በታትነን መግዛት ነው (እርስበርሱ ሕዝቡ እንደማይደማመጥ ማድረግ ነው)። ተራማጅ ሕገመንግሥት ዲሞክራሲያዊ ፌደራለዊ ሪቡብሊክ ኢትዮጵያ ተብሎ በስም እያሞካሸ ከኋላ ሆኖ የሃገሪቷን መበታተን ሲገፋ የነበረው ሃይል/ ኣእምሮ/ ወያኔ ነው። ያ ደግሞ ወደ ኋላ ተመልሰን ስንመለከተው “ኢትዮጵያን እንዴት በታትነህ፤ በታትነህ በታትነህ መግዛት እንዳለበት ሲተገብር የነበረው ከኋላ ሲገፋ የነበረው የወያኔ በሽተኛ ሕሊና እና ቁጥር አንድ የወያኔ አጀንዳ ነው።”
ከመሰረቱ ስትመለከቱት ለውጭ ተመልካች ለማሞኘት የብዙሃን ፓርቲ ነው እንዲባል “ኢሕአዴግ” ብሎ ራሱን ጠራ ፤ 100 በመቶ ግን ተቆጣጣሪው ያው ወያኔ ነው። ምክንያቱም ኣጀንዳቸው ኢትዮጵያን ለመግዛት ስለሆነ ዜጎች በብሔር፤ በቡድን በቋንቋ በታትነህ ፤ በታትነህ ፤ በታትነህ አንድነቱን ለያይተን
መግዛት ነው የሚል ነው፤፡ ይህ አሁን ዛሬ እያየነው ያለው ውጤት የዛው አጀንዳ ውጤት ነው። የመበታተን አጀንዳ።
………. እባካችሁ ተው እየተከተላችሁት ያለውን አስተዳዳር ለሃገር አይጠቅምም፤ ይበልጥ የሚበትን ነው ብለን ሃሳብ ሰጥናቸው ነበር። እኛ ገስጋሽ ፓርቲ ነን
.እያሉ መጨረሻ እኛ የፈራነው ነገር ተከሰተና አሁን እየሆነ ያለው ነገር የዛው የመበታታን አጀንዳቸው ኢትዮጵያን አንበትናለን የሚለው ውጤት ነው።
……. ያንድ ንኡስ ቡድን የመላይቱ አገር የምጣኔ ሃብት መቆጣጠር ማለት እጅግ አደገኛ ነው። የምጣኔ ሃብት ቅራኔ ውስጥ አስገብተህ በብሔር ቅራኔ አዋቅረህ ሰፊውን ሕዝብ (ሌሎችን ብሔሮች) አግልሎ ተመልካች እንዲሆን አድርጎ አንድ ቡድን ‘ብቻውን’ የምጣቤ ሓብቱ ተጠቃሚ ማድረግ ከዚህ የበለጠ አደገኛ ጨዋታ አልነበረም። አሁን እያየነው ያለው የዚያ ውጤት ነው።
…..አገር “ዳብል ድጅት” ዕድገት አደረገች እየተባለ አውሮጳውያን እየተነዛላቸው መጨረሻ “አገር በዕዳ ተጥለቅልቃ እየጎተተች” መላው አገሪቱ ተሽጣ ወደ ድሕነት እንድትሄድ የሃገሪቱ ንብረትን ምጣኔ ሃብት ባንድ “ጠባብ ቡድን” ቁጥጥር እጅ እንዲገባ ስለተደረገ አሁን ዞሮ ዞሮ ዛሬ እያየነው ወዳለነው ሁኔታ ተሸጋግሯል። አሁን ያለው ሁኔታ የዚያ ውጤት ነው። “>>
ሲል ኢሳየስ በሰፊው በሚገርም ግሩም አገላለጽ የታዛባውንና የሚያውቀውን የወያኔ ባሕሪ፤ወንጀል፤ፍላጎት እና አጀንዳ ነበር የገለጸው። እውነታው ይህ እያለ የኤርሚያስ ማርያማዊት ሚዲያ ኢሳያስ ያልተናገረውን ገልብጠው በማቅረብ ትግርኛ ለማያደምጡ ሰዎች አሳስተዋቸዋል።
ጨረስኩ - ቪዺዮውን ከሥር አድምጡት እነሆ! Ethiopian Semay
ጌታቸው ረዳ::
ERi-TV: Local Media
Interview With President Isaias Afwerki, January 14, 2018
https://www.youtube.com/live/iHSuYgzEW48?feature=share
No comments:
Post a Comment