የለንደን ጉብኝቴ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian
Semay)
June 4.2023
የመልዕክት ሳጥኔን ስመለከት ከብዶት ሞልቶ አገኘሁት። “ምን ነካህ ጠፋህ’ሳ?
ታምመህ ነው ወይስ የጤና፤ ክፉ አይንካህ” ብላችሁ ለተጨነቃችሁልኝ የዘወተር ተከታታዮቼና ወዳጆቼ እያመሰገንኩ በሌላ በኩልም የኔን
ጽሑፍ በመውድድ ስትከታተሉኝ የነበራችሁ ተከታዮቼም የኔን ጤንነትና
ደህንነት ግድ ያልነበራችሁም ጭምር አብሬ ሁላችሁም አመሰግናለሁ።
ብሞትም፤ብታመምም ስንት አስታዋሽና ረሺ እንዳለኝ አጋጣሚ ያየሁበት ወቅት
በመሆኑ ደስ እያለኝ፤ አንግሊዝ አገር እና ሆላንድ/ዳች/ ስጎበኝ ፖለቲካና ዜና ፍጹም ባለማየቴ አሁን ላለው ፖለቲካ አዲስ ሆኜ
ስለተሰማኝ ተከታዮቼ ሰፊ ጊዜ ስጡኝና ሁኔታውን እስካጤን ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁኝ እጠይቃለሁ።
ሁኔታው የፓለስታይን “የኢንቲፋዳ الانتفاضة” አብዮት በማስነሳት የነጮች ቅጥረኛ
የሆነው የኦሮሙማው ጴንጤው የኦነጎቹ መንግስት ከሃዲው አብይ አሕመድ ያስጨንቁታል ብየ ስጠብቅ አሁን እንዳየሑት ከሆነ ግን ወጣቱ
“በለብለብ” ሁኔታ እንጂ ስጠብቀው የነበረው “ፋታ ነሺ አስጨናቂው የአማራ ወጣቶች ኢንቲፋዳ” ማየት አልቻልኩም።ለማንኛውም ድካምም
ስላለኝ ትንሽ አረፍ ብየ ፖለቲካው እስካጤነው ድረስ ለሁላችሁም አመሰግናለሁ።
እንግሊዝ አገርና ሆላንድ ያለችሁ ዘመዶቼና ወዳጆቼ ላደረጋችሁልኝ ቤተሰባዊ መስተንግዶ ከልብ አመሰግናለሁ።
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment