የቀዳማይ ወያኔ መስራች የብላታ ሃይለማርያም ረዳ ልጅ የሆነው ካሳ ሃይለማርያም አባቱ ያስተማሩት
የሸዋ አማራ ጥላቻው ከትግርኛ ወደ አማርኛ ልተርጉምላችሁ እነሆ!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
June 17/2020
ጉዳዩ
ሽምግልና ተልዕኮ ይዘው ወደ ትግራይ/መቀሌ ሄደዋል ስለተባለው ጉዳይ በፌስ-ቡክ የጻፈው ነውረኛ ጽሑፉን ይመለከታል።
ወደ ትርጉም ከመሄዴ በፊት ስለ
አባት እና ልጅ ትንሽ ልበል። ብላታ ሃይለማርያም ማናቸው ለምትሉ ባጭሩ ከርዕሱ እንደምትመለከቱት የቀዳማይ ወያኔ መሪ የነበሩ ናቸው።
የብላታነት ማዕረግ ከጣሊያን የተሰጡት ሃይለማርያም ረዳ ብዙ ተመራማሪዎች እንደጻፉት በዘመነ አፄ ሃይለስላሴ ከሽፍታነት እስከ የጉልተኛው
ሥርዓት ተሿሚና አስፈጻሚ ሆነው ገበሬውን እንዳላስከፉት ሁሉ በሗላ ትግራይ ውስጥ የተነሳው የገበሬዎች አቤቱታን “ውሻ በቀደደው
ጀብ ይገባበታል” በሚለው በሚገርም ብልጣብልጥ ስልት ተጠቅመው “እነዚህ ሽዌዎች ምን አድርጉ ነው የሚሉን?!” በሚል ብሔረተኛነት
ባጀበው ስሜት በመነሳሳት “ሥልጣን ከትግራይ እጅ ለምን ወጣች” በሚል ማንኛውም አክራሪ የሆነ ብሄረተኛ እንደሚከተለው ሁሉ እሳቸውም
“ወደ አጼ ምኒሊክ ዘመን ወደ ኋላ ተመልሰው ስልጣን ከትግራይ እጅ ለምን ወጣች፤ በሚል ቀደም ብሎ በነበራቸው የአማራ (ሽዋ) ጥላቻቸውን
በማጠናከር ብጤዎቻቸውን በማስተባባር የድሃውን እውነተኛ ብሶት ‘ጠልፈው’ ወደ “አማራ እና ትግሬ” ቅራኔ በማሳደግ የቀዳማይ ወያኔን
አመፅ በመምራት ቀዳሚ ስፍራ የያዙ ናቸው።
ብላታ ሃይለማርያም ቀዳማይ ወያኔን
በመሩበት ወቅት የተከተሉት ማኒፌስቶ (አዋጅ) እጅግ ከከረረ አምባገነናዊነት አልፈው ከአንድ ‘የተዋህዶ ክርስትያን አማኝ’ የማይጠበቅ
ማኒፌሰቶ አውጥው እውን ያደረጉ ናቸው። ምናልባትም ለማታውቁት አዋጁ እዚህ ልጥቀስላችሁ እና ወደ ልጃቸው እንሻገራለን፡
ያወጁትን የጊዜያዊ መንግሥት መተዳደሪያቸውን
ስንመረምር ከ6 አመት በፊት ያቀረብኩላችሁ ዛሬም ደግሜ ላቅርብላችሁ። እንዲህ ይላል፤
የምንከተለው ሃይማኖት (የቀዳማይ
ወያኔ ጊዜአዊ መንግስት) ሃይማኖታችን (የአፄ ዮሐንስ)፤ገዢያችን (እየሱስ ክርስቶስ) ፤ ጠባቂያችን (ሃይለማርያም ረዳ)፤ባንዴራችን
(የኢትዮጵያ) ነበር ያሉት። እንዲህ ይላል። (ገረብ ማለት ጅረት/አካባቢ ማለት ነው) (ከ12 ፈለግ/ጀረቶች ከሚዋሰነው ሕዝብ የተውጣጣ
የጊዜያዊ መንግሥት ተወካዮች ማለት ነው።)፤
(አዋጅ ስማ! አዋጅ ስማ!
በትግርኛ፤ ከታች በአማርኛ ትርጉም
ይከተላል።
“…ስምዑ፤ስምዑ!
አዋጅ ሃይለማርያም አዋጅ ገረብ
እዩ
ገዛኢና _ እየሱስ ክርስቶስ፤
ሓላዊና _ ሃይለማርያም፤
ዳኝነትና _ ናይ ዓሰርተ ክልተ
ገረብ፤
ባንዴራና _ ባንዴራ ኢትዮጵያ፤
ሃይማኖትና _ ናይ ሃፀይ ዮውሃንስ
ህዝቢ ትግራይ ወያነ ተኸተል!
ገረብ መንግሥቲ ተቐበል!”
አዋጅ! አዋጅ!
ይህ አዋጅ የሃይለማርያም እና የገረብ
አዋጅ ነው።
ገዢያችን_ እየሱስ ክርስቶስ፤
ጠባቂያችን_ ሃይለማርያም፤
ዳኝነታችንም_ ከ12 ገረብ ተወጣጥተው
የወሰኑት የፍትሕ ዳጅነት ይሆናል።
ባንዴራችን_ የኢትዮጵያ ባንዴራ
ነው።
ሃይማኖታችንም _ የአፄ ዮሐንስ
ነው።
የትግራይ ሕዝብ ሆይ! ወያኔን ተከተል!
የትግራይ ሕዝብ ብቸኛ የሆነው የገረብን
መንግሥት ተከተል!
በማለት ‘በአንድ እየሱስ፤ አንድ
ሕዝብ፤ አንድ ድርጅት፤ አንድ ሃይማኖት፤ አንድ መሪ፤” የሚከተል “የገረብ መንግሥት” ተከተል ሲል አውጇል።
የዛሬ የወያኔ ትግሬዎች “ሸዌዎች
አንድ መንግሥት፤አንድ ቋንቋ፤ አንድ ድርጅት፤አንድ ሕዝብ፤አንድ ሃይማኖት” ይላሉ ሲል “በፀረ ሸዋነት ሕሊና የተቀረጸው” የብላታ
ልጅ ደግሞ ሸዌዎች ሊገዙን ፈልገው አፈር አስበላናቸው፤አሸንፈውን ነበር ዛሬ አሸንፍናቸው፤ ዲሞክራሲ ከትግራይ ሕዝብ አልፎ ለሌሎቹ
ተርፎ መብታቸው ተከብሮ በልማት ጎዳና እየተጓዘ ይገኛል” ይላል ልጃቸው። እሱ አጥብቆ በሚጠላት በሸዋ አገር ገበሬዎች ታርሶና ተፈጭቶ
የበቀለ የሸዋ ምግብ እየተመገበ “ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ አካውንታንት” የተማረው ልጃቸው። እኔ ይህንን ስታዘብ ‘ኢትዮጵያ
አገሬ ሆይ ይህንን እየሰማሽ ምን ብታደርጊ ይሻልሽ ይሆን?” እላለሁ።
በብላታ መሪነት የጸደቀው አዋጅ
ከላይ ያለው አልበቃ ብሎ’ የሚለተለውን አዋጅ ተግባሪ እንዲሆን ምክር ቤቱ (ገረብ ዓረና) ተጨማሪ አዋጅ አከለበት፤ -
ድሮ በሃይለስለሴ ዘመን አንድ ሞገደኛም
ሆነ አንድ ሰው ወደ ሕግ ለማቅረብ አንሂድ ስትለው “በሃይለስላሴ በሕግ አምላክ” ሲባል ነበር። የመሳፍንቶች እና የነገሥታት ዘሮች
የሚበዙበት እና የሚወለዱበት አካባቢ እንደርታ አውራጃ በቀዳማይ ወያኔ ለንጉሥ ሃይለስላሴ አንገዛም በማለት “12 ገረብ” (አስራ
ሁለት ጅረት) በሚል ስም ጊዜያዊ የአማጽያን መንግሥት ሕዝባዊ ባይቶ/ጉባኤ/አሰምብሊ) መስርቶ በነበረበት ወቅት “ዝባን ገረብ”
(በገረብ ሕግ አምላክ) በማለት አንድ ሰው እንድትቆም ተማጽኖህ ካልቆምክ፤ ወይንም “በገረብ ሕግ ዳጅነት ላለመዳኘት አምቢ ካለ”
የገረብ ሕግ ረግጦ እንደሄደ ተቆጥሮ የሚከተሉት በሕግ የጸደቀ የገረብ አዋጅ ይፈረድበታል።
እንዲህ ይላል፤-
የቀዳማይ ወያኔ የእርምጃዎች መግለጫ፤
(1ኛ)-የገረብ ሕግ ያላከበረ ታምሞ
የአልጋ ቁራኛ በሆነበት ወቅት አግዚአብሔር ይማርህ ተብሎ በማንኛውም ጐብኚ እንዳይጎበኝ፤
(2ኛ)- በሐዘን ጊዜ ጥናቱን ይስጥህ
ተብሎ እንዳይጠየቅ/ለልቅሶ እንዳትደርሱት
(3ኛ)-ከሕዝብ እና ማሕበራዊ ግንኙነት
እንዲገለል። የሚሉ ነበሩ።
በዚህ አጋጣሚ
አፄ ዮሃንስም አንድ ሃይሞኖት ለማድረግ
ሞክረዋል። ፕሮተስታንት ወይንም እስላም የተባለ ወደ ኦርቶዶክስ ካልተጠመቀ ከትግራይ ግዛቴ ለቃችሁ ወደ ሌላ አገር ሂዱ ብለው አውጀዋል።
መረጃየን ላቅርብ፡
“Internal Rivalries
and Foreign Threats (1869-1879) Edited by Sven Rubenson page 6 ስንመለከት አሰገኸይ የተባሉ
የቤተክሕነት ምሁር የሆኑ ትግሬ ሰው “የአንቶይን ዲ አባዲ” የተባለ አውሮጳዊ ወዳጅ/አስተርጓሚ/ዜና ነጋሪ/አገር አስተዋዋቂ የነበሩ
በAssegehen to Antoine d’ Abadie, 12,Feb, 1869 በሚል ርዕስ አሰገኸኝ ለ ‘ዲ አባዲ’ በግዕዝ ርዕስ የጻፉትን
ደብዳቤ እንዲህ ይላል።
“ትብጻሕ ሃበ አቶ አንደጦንዮስ
ዘአባዲያ ሙሑረ ጥበባት…….” እያሉ ሰፋ ያለ በግዕዝ ሰላምታቸውን ካቀረቡ በኋላ፤ ወደ አማርኛ በመግባት፤
“ታሪክ ዘደጃዝማች ካሳ አባ በዝብዝ
የትግሬ ንጉሥ እንዲህ ነው። አባ ተክለ አልፋ የሚባሉ መነኩሴ ዘደብረ በርበሬ ነበሩ፡ ቅባት ናቸው፡ ያባ በዝብዝ የንስሐ አባት
ወደ ተዋህዶ ሃይማኖት ግቡ ብሎ ተማጠናቸው። አባ ተክለ አልፋም፤ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ትርጓሜው እንዴት
ነው፡ ብለው ጠየቁት። አላውቅም አለ። ደጃዝማች ካሳም ደንቆሮ ነህ፡ብለው .. የነብስ አባታቸውን ገረፉት።
፪ኛ ታሪክ፤
ደጃዝማች ካሳ አባ በዝብዝ በትግሬ
ያለ ቅባት ሁሉ ወደ ሃይማኖቱ ይግባ። እምቢ የሚል ሁሉ በምገዛው አገር አይኑር አሉ። በትግሬ ያሉ ቅባቶች ሁሉ ወደ አባ በዝብዝ
ሃይማኖት ገቡ፡ አባ ተክለ አልፋ ግን ገዝተው ወደ ታላቅ ገደል ወጡ፡ ያባ በዝብዝ አጎት ደጃዝማች አርአያ ከብዙ ጦር ጋር ተከተለው፡ከገደል
አወረዱዋቸው፤በነፍጥም እንደመቱዋቸው፤ፈርተው ከገደል ወረዱ፡ ግዝታቸውንም ፈቱ፡ ወደ ሌላ አገርም አባ ተክለ አልፋ ተሰደዱ።”
(( Internal Rivalries and Foreign Threats (1869-1879) Edited by Sven Rubenson
page 6 ምንጭ ከላይ የጠቀስኩት መጽሐፍ ገጽ 6 )
የብላታ ሃይለማርያም ኮቴ የተከተሉ
ወያኔዎችና ልጃቸው የሸዋ ነገሥታት ጸረ ትግሬ ስለሆኑ ፤ኢትዮጵያን በአሃዳዊ ስርዓት ገዝተዋታል፤ እያሉ አማራ የሚሏቸውን ነገሥታት
ሚዛን ባልጠበቀ ዘለፋ እና ውንጀላ ሲወነጅሏቸው፤የራሳቸው የትግራይ መሳፍንት እና ነገሥታት እና ቀዳማይ እና ዳግማይ ወያኔ ግን
ከላይ በማስረጃ እንዳቀረብኩላችሁ ታሪካቸውን እየሸሸጉ በየሚዲያቸው ሲያብዱ ሌላውን ሲወነጅሉ እያዳመጧችኋቸው ነው። እነሆ አሁን
የትግራይ መሳፍንቶች እና ነገሥታት ሥርዓት እውነታው በመረጃ ይዛችሁታል። ሌላም ስትፈልጉ “ደቂቀ ተወልደ መድህን” የሚለው በ2005
ዓ.ም ያሳተምኩትን የአማርኛ መጽሐፌን አንብቡ እና ትግሬዎች የተለየ ሃይማኖት ለያዘ የትግራይ ሰው ምን ዓይነት ፍዳ ያደርሱበት
እንደነበረ ዓድዋ ላይ የታየው ፍዳ አንብቡ።
እንቀጥል።
ካሳ ሃይለማርያም የብላታ ሃይለማርያም
ልጅ ነው። አማርኛ ከትግርኛ በበለጠ አሳምሮ ይናገራል (አማርኛ የመጀመሪያ ቋንቋው ነው በሚያሰብል ሁኔታ ይናገራል)። የተኮላተፈ
ትግርኛ ተናጋሪ ሲሆን፤ አማርኛ በሚነገርበት አገር ተሞላቅቆ ያደገ ፤ ወላጆቹ ከእንደርታ አካባቢ ቢሆኑም እንደ ብዙዎቹ የእንደርታ
ተወላጆች ልሳናቸውን እየተው አንዳንድ ትግሬዎች “አስማሪኖ/አስመርኛ/ ብለው በሚጠሩት ኤርትርኛ እና የትግሬ “አሽዓ” ኛ በሚመስል
የትግርኛ ልሳን ለመናገር የሚሞክር፤ ከዚያም አልፎ የወላጅ አባቱን መጽሐፍ በዚህ ልሳነ ቅኝት እንዲጻፍ የፈቀደ ነው”።
ስለ ልጁ ከንቱ የሸዋ ጥላቻው ለወደፊቱ
በግምገማ ስለማቀርበው ለጊዜው እናቆየውና አባትየው ብላታ ሃይለማርያም ረዳ ከሞቱ በኋላ ብላታ የጻፉት ሰነድ እና አደረጉት የተባለው
ቃለመጠይቅ አሜሪካ አገር በዋሺንግተን ዲሲ ኗሪ በሆነው በኩር ልጃቸው (በመጀመሪያ ልጃቸው) በሆነው በካሳ ሃይለማርያም ረዳ የበላይ
ሃላፊነት አገር ውስጥ የታተመ “ገረብ ዓረና ወያነ ትግራይ 1933-1939 ዓ.ም” የሚል ባለ 502 ገጽ የያዘ የትግርኛ መጽሐፍ
ከሁለት አመት በፊት (በ2010 ዓ.ም) መቀሌ ከተማ ተመርቆ ለትግራይ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የታሪክ ጥናት መማርያ (ካሪከለም)
እንዲሆን እራሱ መቀሌ ድረስ በመሄድ በስጦታ ተሰጥቶ የትግራይ ታዳጊ ወጣት ተማሪዎች በሸዋ ጥላቻ ታንጸው እንዲቅፁበት የተበረከተ
መጽሐፍ ነው።
ይህ መጽሐፍ በግዥ መልክ እንዲልክልኝ
ካሳን አነጋግሬው “እሺ ብሎ የኔን አስፈላጊውን አድራሻ ከወሰደ በኋላ” ብደውል ብደውል መልእክትም ብልክለት “ውሃ ውስጥ እንደገባች
ዓይጥ ድምፅ ሊሰጠኝ አልፈለገም” ከዚያም ዘመዶቼ ከትግራይ እንዲልኩልኝ አድርጌ መጽሐፉ ያገኘሁት በቅርብ ሲሆን በመጽሐፉ ዙርያ
የምሰጠው ግምገማ እስክሰጥበት ድረስ እስከዛው ድረስ ለዛሬ መነሻ የሆነኝን ይህ የብላታ ልጅ በፌስቡኩ የለጠፈው አንድ ወዳጄ እንድመለከተው
የላከልኝን ከአባት ወደ ልጅ ተላልፎ አላባራ ያለው በሸዋ ያጠነጠነ ጥላቻውን “ድሮ አሸንፈውን ነበር ዛሬ እኛ አሸንፈናቸዋል እነሆ
አንድ ባንድ ሆነናል!” የሚለውን የካሳ ሃይለማርያም ቂም ቋጣሪነት ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጎምኩላችሁን እንድታነቡት እነሆ።
መጀመሪያ አማርኛው ከዚያም ለሰነዱ ተያያዢነት እንዲመች ወደ መጨረሻ የካሳ ሃይለማርያም የትግርኛውን ጽሑፍ አያይዤዋለሁ።
ይህ ጽሑፍ የጻፈበት መነሻው፤ ሰሞኑ
ወደ መቀሌ ተጉዘዋል የተባሉት “ሽማግሌዎችን” አስመልክቶ ከሸዋ ጋር እያያዘ እየተቸበት ጽሑፉ የእንደርታዎቹ የወላጆቹ የትግርኛ
አጻጻፍ ዘይቤ ሳይሆን ኤትርኛም፤ ዓረብኛ ቃልም የተቀላቀለበት “የዓድዋ ፤ አክሱም ፤ ሽረ” ኗሪዎች የሚናገሩትና የሚጽፉት “መለስ
ዜናዊና ጓዶቹ ያስተማሯቸው” ወያኔዎች ከበረሃ ጀምረው በበላይነት የተጠቀሙበት የትግርኛ አጻጻፍ ዘይቤ ነው የተጻፈው ፡ ስለዚህ
ለአማርኛ አንባቢ እነሆ ተርጉሜዋለሁ።
እርቅና ሽምግልናን አስመልክቶ እኛ
እና ሸዋ ባለፉት 130 ዓመታት እኩል አንድ ባንድ ነበርን ፤የዛሬው ሽምግልናስ ምን ይሆን?
የሸዋ ነገሥታት መፈናፈኛ ሲያጡ
እኛን (ትግሬዎችን) ለማጥፋት ተንኮል ሲጠነጥኑ ሁሌም የሚሮጡት “ወደ ሽምግልና ነው”። ሁሉም የሽምግልና ጥያቄዎች የሚቀርቡት መነሻቸው
ከሸዋ ነው። በ1881 ዓ.ም ንጉሠነገሥት አፄ ዮሐንስ የማህዲን ወረራን ለመመከት ሲዘጋጁ ፤ ምኒልክና አምሳያዎቹ በአፄ ዮሐንስ
ላይ ተንኮል እየሰሩባቸው መሆኑን ሲያውቁ ምኒልክን ሊቀጡት ወደ ሸዋ ለመሄድ ተዘጋጅተው ነበር። ምኒልክ ይህንን ሲያውቅ ተሎ ተሯሩጦ
“ጌታዮ ሆይ ይማሩኝ” ብሎ በጥር 10/ 1881 ዓ.ም ከእንጦጦ የጻፈው ደብዳቤ አጎቱን ደጃዝማች ዳርጌ ሽምግልና አስልኮ (እንዳይቀጡት)
አጃጃላቸው።በዚህ ተጃጅለው ምኒልክን ከመቅጣት ይልቅ ፊታቸውን ወደ መተማ ዘመቻ አዞሩ።
ተንኮለኛው ምኒልክ ግን ሴራው እያጠነጠነ
መነኮሳት ያልሆኑ ግን “መነኮሳት” አስመስሎ ዕርቅ እያለ አስሰርጎ በማስገባት በሁለተኛው ወር ንጉሳችንን አስገደለብን። “በሽምግልና
ስም አሸነፉን!”
ከ100 አመት በኋላ በ1983 ዓ.ም
የደርግ ስርዓት ወደ መቃብሩ ሊወርድ ሲቃረብ በሁለት መንገዶች ወደ ዕርቅ ተሯሯጠ። ባንድ በኩል መንግሥቱ ሃይለማርያም እራሱ አሜሪካኖችን
“አስታርቁኝ” ብሎ ጠየቀ። ከዚየም መስፍን ወልደማርያም የሚመራው “የሽማግሌዎች” ቡድን ጊዮን ሆቴል ውስጥ “የሰላም አማራጭ” የሚል
ሰነድ አዘጋጅተው ታችና ላይ ይሯሯጡ ነበር።
ሽምግልናውን በሚመለከት እስከ ጣሊያን ድረስ በመሄድ የዳግማይ ወያኔ መሪዎች ተወያይተውበታል። ሲወያዩም ላንድ አፍታም
ቢሆን ዘመቻችን (ትግላችንን) ሳናቆም ቀጠልን። ከዚያም ለመቶ አመታት በጫንቃችን ላይ ዝጎ (ሻግቶ) የነበረው ሰርዓት ከስሩ ነቅለን
ጣልነው። እኛ አሸነፍናቸው! አንድ በአንድ ሆንን!
በ1881 እነሱ በተንኮል በለጡንና ንጉሣችንን ነጠቁን። በ1983 ዓ.ም ግን ከገራገርነታችን ተምረን ልባም ሆን እና
እኛ አሸነፍናቸው።መሪያቸውም እንደ “አያቶቹ” አገር ጥሎ ፈረጠጠ። የዛሬዋ ሽምግልናስ ማን ይሆን ዘዴኛ/ በመሆን በጥበብ እንዳለፈው
ሕዝባችንን የሚያሻግር!?
የሆኖ ሆኖ ሽማግሌዎቹ 14 ቀን በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ ሳይደረግ ወደ ቤታችን (ወደ አገራችን) እንዳይገቡ ፡ ሲገቡም
የሚከተሉት ሁኔታዎችን ማጣራት አለባቸው፦
• እነዚህ ሽማግከሌዎች እነማን ናቸው? ማን ነውስ ያሰማራቸው? የሚሉ የመመካከሪያ ሃሳቦችን ማንሳትና ይፋ እንዲሆን
መደረግ አለበት!
• የራስን በራስ የመወሰን መብት
ወደ ድረድር የሚቀርብ አይደለም። የዚህ ሽምግልና መነሾ ሰላም ከሆነ ግን ባለቤቶቹ የትግራይ ሕዝብ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ማለት
ነው። ስለሆነም ግልጽነት፤ተጠያቂነት እንዲኖሮው ለማድረግ በሽምግልናው ወቅት የተደረጉ ሁሉም ክንዋኔዎች በስዕለ-ድምፅ (በቪዲዮ)
ተቀርፆ ለሕዝባችን እና ለመላው ዓለምም እንዲያየው መደረግ አለበት። (ካሳ) "
በማለት የብላታ ሃይለማርያም ልጅ
ካሳ ሃይለማርያም በጥላቻ ሕሊና የቀጨጨው ጩጬ ሕሊናው፤ ዛሬም ዘመን ሰለጠነ በተባለበት ዘመን ንጉሳችን ተነጠቅን እያለ ባለፉት
የነገሥታት የሥልጣን መነጣጠቅ ዘመን የተደረገውን እንደሕልም ሆኖበት አክራሪ ፋሲሰቶች በመቃዠት የሚሰቃዩበት ወደ ኋላ ዞሮ የማስተንተን
ቀውስ ነው ዛሬ በዚህ ጽሑፍ ካሳ ወደ 130 አመት ዞሮ እየጋለበ ያለው።
የኢትዮ ሰማይ ተከታታዮች እንደምታውቁት
በ28 አመት ትግራይ ምን ዓነት ማፈሪያ አዲስ ትውልድ እንዳፈራችና በቂም በቀል የተበከለ ትውልድ እንደተከሰተ እንድታውቁትና እንድትወያዩበት
የተቸሁበትን ትችትና ትርጉም እዚህ አበቃሁ። "ሼር" አድርጉት፡ ሃሳብ ስጡበት!
ትግርኛውም ከታች አያይዤዋለሁ።
አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ) June 16, 2020
ኣብ ታሪኽ ሽምግልና ኣብ ዝሓለፈ
130 ዓመታት ትግራይን ሸዋን ሓደ ብሓደ ኢና! እዛ ናይ ሎሚኸ?
መንግስትታት ሸዋ ዓቕሎም እንትፀቦምን
ከጥፍኡና እንትሽርሑን ኩልግዘ ናብ ሽምግልና እዮም ዝጓየዩ፡፡ ኣብ ታሪኽ እውን ኩሎም ሽምግልናታት ዝነቐሉ ካብ ሸዋ እዩ፡፡ ብ1881
ዓ.ም ንጉሰ ነገስት ሃፀይ ዮሃንስ ንመኸተ ወራር ማህዲስት እናተዳለው እንተለው፤ ምኒልክ ኣንፃሮም ምስ ጥልያንን ካልኦትን ብድሕሪት
ውሽጣውሽጡ እናሸርሐ ምዃኑ ምስፈለጡ፤ ክቐፅዑዎ ናብ ሸዋ ነቒሎም ነይሮም፡፡ ሽዑ ምኒልክ ተጓይዩ 10 ጥሪ 1881 ካብ እንጦጦ
ደብዳበ ፅሒፉ፤ ጎይታይ መሓሩኒ ኢሉ ንኣኩኡ ደገዝማች ዳርጌ ሽምግልና ልኢኹ ንንጉሰ ነገስትና ኣዘናግኦም፡፡ ገፆም ካብ ምኒልክ
መሊሶም እውን ናብ መተማ ወፈሩ፡፡ ምኒልክ ግና ሰሩ ዘይሓደገ ፈለስቲ ኣምሲሉ እናለኣኸ፤ ዕርቂ ምስ በለ ኣብ ካልኣይ ወርሑ ንንጉሰ
ነገስትና ኣቕተሎም፡፡ ብስም ሽምግልና ስዒሮምና!
ድሕሪ 100 ዓመት ብ1983 ዓ.ም
ስርዓተ ደርጊ ናብ ኣፈዕርበቱ ምስተቓረበ፤ ብክልተ ኣንፈት ናብ ዕርቂ እዩ ዝተጓየየ፡፡ ብሓደ ወገን መንግስቱ ሃይለማርያም ባዕሉ
ንኣሜሪካ ሸምግሉኒ ኢሉ ብዕሊ ሓተተ፡፡ መስፍን ወልደማርያም ዝመርሖ ጉጅለ “ሽማግለታት” ድማ ኣብ ግዮን ሆቴል ናይ ሰላም መማረፂ
ዝብል ሰነድ ኣዳልዮም ላዕልን ታሕትን ይጓየዩ ነይሮም፡፡ ንቱ ሽምግልና ተቐቢልና መራሕቲ ዳግማይ ወያነ ክሳብ ጥልያን ከይዶም ዘትዮም
ግን ወፍርና ንፃት እውን እንተየሞንገና ቀፀልና፡፡ ብምዃኑ እውን ንሚኢቲ ዓመት ኣብ ልዕሌና መሪቱ ዝነበረ ስርዓት ካብ ሱሩ መሃውናዮ፡፡
ንሕና ሰዓርናዮም፤ ሓደ ብሓደ ኮንና፡፡
ብ1881 ንሳቶም ጎሪሖም ንንጉስና
መንጠሉና፤ ብ1983 ግና ንሕና ለቢምና ተዓወትናሎም፤ መራሒኦም ከም ኣያታቱ ዓዲ ሓዲጉ ሃደመ፡፡ እዛ ናይ ሎሚ ሽምግልናኸ? መን
እዩ ለባምን ንህዝቡ ዘሻግርን!?
ብዝኾነ እዛ ሽምግልና ዘይትተርፍ
እንተኾይና 14 ማዕልቲ እንተይተወሸቡ ናብ ገዛና ከይኣትዉና! ምስ ኣተዉ እውን፤
• እዞም ሸምገልቲ እንመን እዮም? መን እዩ ኣዋፊሩዎም? መበገሲኦምን
ሽቶ እዙ ሽምግልናን? ወዘተ… ዝብሉ ዝርዝር መመያየጢ ነጥብታቱ (terms) ክንፅርን ዕላዊ ክኸውንን ኣለዎ!
• መሰል ዓርሰ ውሳነ ናብ ዘተ እውን ክቐርብ የብሉን!! መንቀሊ እዙ
ሽምግልና ሰላም እንተኾይኑ ግና፤ ብዓልዋና እዙ ሽምግልና ህዝቢ ትግራይን ህዝቢ ኢትዮጵያን እዩ ማለት እዩ፡፡ ብምዃኑ እውን ግልፅነትን
ተሓታትነትን ምእንታን ክህልዎ፤ ኩሉ ከይዱ ብቪድዮ ተቐሪፁ ብዕሊ ብሚዲያታት ንህዝብናን ንዓለምን ክመሓላለፍ ኣለዎ! #ካሳ )
ከትግርኛ ወደ አማርኛ ትርጉም ጌታቸው
ረዳ (ኢትዮጵን ሰማይ)
No comments:
Post a Comment