Tuesday, June 30, 2020

ሓጫሉ እጅግ ሲበዛ ሞገደኛ እና በባለተራነት ስሜት ተሰፍጦ የጥጋበኛነት ግሳት ሲያገሳ የነበረ፤ ምላሱ በልኩ የማይቆጣጠር “ግዙፋን ዋርካዎቻችንን” ሲያረክስ የነበረ ወጣት ነበር፡ ነብስ ይማር! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay) June 30/2020


ሓጫሉ እጅግ ሲበዛ ሞገደኛ እና በባለተራነት ስሜት ተሰፍጦ የጥጋበኛነት ግሳት ሲያገሳ የነበረ፤ ምላሱ በልኩ የማይቆጣጠር “ግዙፋን ዋርካዎቻችንን” ሲያረክስ የነበረ ወጣት ነበር፡ ነብስ ይማር!
ጌታቸው   ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)
June 30/2020
 ሓጫሉ ለምን ሞተ? ማንስ ገደለው? እንዴት ሞተ? ብዙ ሰዎች መላምታቸው ሲነታረኩበት አንብቤ ገርሞኛል። ልጁ ከሰማይ በታዘዘለት ቀነ ቀጠሮ በተጠራበት ወቅት ሄዷል (ሁላችንም የየራሳችነን መጥሪያ ቀኖች አሉን)። ኦነጎች እና በወያኔዎች በነፍጠኛነት እየተወገዙ፤ በሓሰት ተወንጅለው ባጭር የተቀጩ ብዙ ኢትዮጵያውያን እናስታውሳለን። አንደኛውና ቀዳሚው ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ፤ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ እና ሚሊዮኖች ተቀጥቅጠው ተረሽነው፤ተሰቅለው፤አንገታቸው ታርደው፤ብልታቸው የተኮላሹ፤ በመርዝ የተገደሉ ሚሊዮኖች ናቸው።ዛሬ ሓጫሉ በጥይት ተገደለ የሚል ዜና ሰምተናል።

ኢትዮጵያውያንና የኮርያ ሕዝቦች ልዩ አልቃሾች ናቸው። ይንሰቀሰቃሉ። ሰው በግፈኞች ሲገረፍና ብልቱ ሲኮላሽ፤ እናቶችና ባለትዳሮች ሲደፈሩ፤ ወጣት ሴቶች ሲያለቅሱ፤ተጠልፈው ደብዛቸው ሲጠፋ፤ ግን ምንም የማይሰማቸው፤ ዛሬም ለግፈኛ መሪዎች የሚያጎበድዱ ኢትዮጵያውን ሁሉ ዛሬም ለመከራችን ዋናው ተጠያቂዎች ናቸው። ለመከራችን ዋናው ተጠያቂ የነበረው ‘መለስ ዜናዊ’ ሲሞት “ከላይ እንደገለጥኩት “መሬት ትዋጠን” ብለው ስቅስቅ ብለው ያለቀሱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን እናስታውሳለን።

“አንተም ክፉ ነበርክ ክፉ ሰደደልህ..” ሲሉ የነበሩ ጥንታዊ አያቶቻችን ዛሬ የነሱ ልጆች የሆንን የሐበሻ ልጆች በተቃራኒ ቆመን “ሰው ሲያፈናቅሉ የነበሩ፤ በተሰጣቸው መድረክ ተጠቅመው አገር የሚያፈርስ ቅስቀሳ ሲያደርጉና ከተማው ገጠሩ ሲያውኩ ሰላም ሲያደፈርሱ የነበሩ “ጋኔሎች በሞት ሲሰናበቱ ” ወደ እርግብነት ለውጠው “የሚያለቃቅሱ” ኢትዮጵያውያን የመለያ ባሕሪቸው ሆኖ ዛሬም አለ። ቤተክርስትያኖቻቸው እና መስጊዶቻቸውን ሲያቀጥሉላቸው ፤ሰንደቃላማቸው እና ማተባቸው በመንግሥት ወኪሎችና ታጣቂዎች እንዲያወልቁ ሲደረግ “እነሱን የሚቆጣጠረው” መንግሥት ማሞካሸትና ማሽቃበጥ የኢትዮጵያውን ባሕሪ ሆኖ ቀጥሏል።

ዛሬም በሕይወት ቆመው በሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ደም እጃቸው በደም የጨቀየው እነ ኢሳያስ አፈወርቂ የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ወንጀለኞችን “በወኪሎቻቸው ጋባዥነት” ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ተደርጎ “በገደልዋቸው ሰዎች አገር ተንፈላስፈው ባንዴራቸው እየተውለበለበላቸው “ወላጆቻችን ወንድሞቻችን እህቶቻችን ጥርሳቸውን እየነቀልክ ስላባረርክልን፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች የሳህል ተራራ በውሃ ጥም እያቃጠልክ ምሽግና አስፋልት ቆፋሪዎች አድርገህ በባርነት ስለገደልካቸው ፤ ወደብ አልባ እንድንሆን የዓረቦች ሙርከኞች ስላደረግኸን “እንወድሃለን” የሚሉ የሙታን ልጆች በገፍ ተፈጥሯል። ወንጀለኞች የሚንቀባረሩበት አገር ብቸኛው የአበሾች አገር “ኢትዮጵያ” ነች። “ጋኔሎች” ሲሞቱም አይጠየቁም፤ አይወቀሱም፤ ሲኖሩም አይጠየቁም አይወቀሱም፡በቃ!

ተጠቂ ሙታኖች የሚጮሁባት ኢትዮጵያ!

በሚገርም ክስተት አንዳንድ ሰዎች ፈስ-ቡክ ላይ ሲጽፉ ያነበብኩት “ሓጫሉ ስለሞተ አማራዎች እንዳይገደሉ፤ ሕዝብ እንዳይገዳደል እርስ በርስ ጦርነት አንዳይነሳ ዝም በሉ ይላሉ” ፤ ሓጫሉ ስለተገደለ ሳይሆን አገር የሚደፈርሰው ፤ወንጀለኛው ስርዓት በሕዝባዊ ስርዓት ተለውጦ ወንጀለኞች ከሥልጣን ካልተወገዱ ስርዓቱ እስካለ ድረስ የሞገደኞች መገዳደል ቀጣይ ነው። ባሕሪው ነው፡ (28 አመት ያየነው ይህ ነበር) አሁን ብሶበታል ።ለዚህ ነው ይህ ሥርዓት ተሎ መወገድ አለበት ብለን የምንቀሰቅሰው።

አንድ ሰው “በሕይወት እያለ ሲያሳየው የነበረው የተረኛነት ግሳት ከሞተ በሗላ በምንዘግብ ሰዎች ውርጅብኝ ሲያወርዱብን የሕሊናቸው ጩጬነት ነው ብለን ብናልፈውም” ይሕ ባሕሪ እስከ መቸ ይቀጥላል? የሚለው ግን መልስ አልተገኘለትም። “ሓጫሉ” እጅግ ሲበዛ የተወጣጠረ ባለጊዜነትን ሽቅብ ያወጣው፤ መኪና ሲነዳ ሕዝብ በተሰበሰበበትና በመተላለፊያ ጎዳና ላይ “ሽጉጥ” መሳርያ ከኪሱ እያወጣ ሰላማዊን ሰው ሲቃጣ እና ሲያስፈራራ የነበረ ጥጋቡን መቆጣጠር ያልቻለ ፤ የተረኛነትን ስሜት በአፍንጫው የወጣ እጅግ ሞገደኛ ሰው ነበር።

መለስ ሲሞት ብዙ ሰዎች ፡እንደሰው ሰውነኝና ማዘን አለብኝ” እያሉ ሲያለቅሱ ልባቸው የተሰበረ አንጋፋ ሰዎች አይቻለሁ (እንደ እነ ታማኝ በየነ አይነቶቹ ልባቸው ወለል ብሎኣቸው አይሮፕላን ሲወርዱ “በቴክስት መልእክት” መርዶውን ሰምተው መራመድ እስኪያቅታቸው የተሰናከሉ አዛኝ ፍጡራን አይተናል) በእነ በቀለ ገርባ ፤በነ ጃዋር፤ በእነ ዳውድ ኢብሳ፤ በእነ ተስፋየ ግበረአብ ፖለቲካ ሕሊናው በአክራሪ ፖቲካ ተወጥሮ አማራውን ሲያወግዝ፤ ምኒሊክን እርኩስ አድርጎ ሲኮንን የነበረ፤ የትላልቅ ዋርካዎቻችን መልካም ዝናን ያቈሸሸ፤ ልጓም የበጠሰ ሞገደኛ “ፀብ የሚዘራ” አዝማሪ ነበር።

ሓጫሉ እንደተመኘውም “ተረኛ ኦሮሞዎች ፈረሳችሁን እየጋለባችሁ ምኒሊክ ቤተመንግሥት ተቆጣጠሩት “ ብሎ እንደዘፈነላቸው ሁሉ ፤ ያለው አልቀረም “ተረኞቹ ኦነግንና ኢሳያስ አፈወርቂን በውስጥ አርበኛነት ሲያገለግሉ የነበሩ እነ “ኮለኔል “አብይ አሕመድ” የመላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተቃውሞ እና “ደም” ምርኩዝ አደርገው ምንሊክ በተመንግሥት ቁጢጥ ብለው በሁለት አመት ውስጥ ለመስማት፤ለማየት የሚሰቀጥጥ ዘግናኝ ወንጀል ሲደርግ “አልሰማንም አላየንም” እያሉ “ንጸሐን አስረው ፤መግረፍ፤ማሰቃየት፤ነብሰጡሮችን በግፍ አስረው ያስወርዱ ካለፉት ያልተሻሉ “የባሱ ጋኔሎች” ሆነው በንጹሓን ደም ቀለዱ። =

ሓጫሉ ምላሱ በልኩ የማይቆጣጠር “አማራን በጡት ቆራጭነት እያወገዘ በአኖሌ ሃውልት ቆሞ በኩራት ተኮፍሶ ፎቶ መነሳትን የሚወድ” እጅግ ሲበዛ “አግረሲቭ” የነበረ እሱን በሚመስሉ መጎደኞች ተገደለ፡ በቃ! ።ከሥርዓተ አልባ መሪ እና “አናርኮ ፋሺስት” የሆነ ሥርዓት የሚከሰተው ክስተት “ሞገደኞች” እርስ በርሳቸው የሚገዳደሉበት ክስተት ውጤት ነው።

ባለ ተረኞቹ ከሥልጣን ካልወረዱና መሰርያቸውን ለሕዝባዊ ስርዓት ካለስረከቡት መገዳደሉና ግድያው የስርዓቱ ባሕሪ ነውና አገሪቱ በመገዳደል ማዕበል ውስጥ እየተናጠች ትቀጥላለች። ወንጀለኞችን በየቦታው እየሾመ አገሪቱ የሚያምሳት እራሱ አብይ አሕመድም አብይ እራሱ እንደተናገረው መገዳደሉ ይቀጥላል ብሏል። አይደለም እንዴ? ስለሆነም ነብስ የመጠፋፋቱ አሳዛኝ ክስተት ሓጨሉን “በድንገት በላው”፤ ታሪኩ ይኼው ነው፤ በቃ! ማን ገደለው?ተገደለ? የሚለው መላምት ውስጥ መግባቱ “ድካም ነው”። ጥያቄው ከዚህ በኋላስ ባለተራው ማን ይሆን? ሁ ኢዝ ኔክሰት?
ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)

No comments: