Saturday, February 21, 2026

እነሆ ዛሬ የ ህ.ወ.ሓ.ት ፋሺዝም ያስከተለው የሲኦል ህይወት ተጀምሯል!!! ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) 2/21/2021 ዳግም የተለጠፈ 2/21/26

 

እነሆ ዛሬ ... ፋሺዝም ያስከተለው የሲኦል ህይወት ተጀምሯል!!!

ጌታቸው ረዳ

(Ethio Semay) 2/21/2021 ዳግም የተለጠፈ

2/21/26

ወደ ዋናው ርዕሰ ከመግባቴ በፊት መጀመሪያ የሐዘን መግለጫየን ላስቀምጥ። ሰሞኑን በወያኔ ፋሺሰት ነብሰገዳዮች ህይወቱን ባጭር ለተቀጨው የፈንቅል እንቅስቃሴ መሪ ለነበረው መምህርየማነ ንጉሰነብስ ይማር በማለት የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ ሐዘኑን ይገልጻል።የማነ በአማራ ላይ ሲሰነዝረው የነበረውናስቲ የሆነያለተገረዘ ምላሱ የኣእምሮ በሽተኛ ሳይሆን አልቀረም ነበር የሚል ጥርጣሬ አለኝ። ያም ሆኖ ወያኔ ሲፈጠርፈሪስለሆነ ባስተሳሰብ የሞገተውን በጥይት በመቅጨት የለመደበት ባህሪው ስለሆነ ብዙ ሺዎቹን የትግራ ተወላጆችና ኢትዮጵያዊያን ተቀናቃኞቹን ቀጭቷል። መስዋዕቱ የማነ ሲሰጣቸው በነበረው አንዳንድ ሃሳቦች ባይጥሙኝም፤ በመራራው ረዢም የትግል ጉዞ ካፈራናቸው የትግራይ ወጣቶች አንዱ የሆነ ይህ የትግራይ ወጣት ኮቴአችንን በመከተልወያኔበፍርሃት እንዲርበደበድ ያደረገው ጉልህ ሚና የማይረሳ የትግራይ ወጣት ታጋይ ስለነበር አድናቆቴን ልቸሮው አፈልጋለሁ። ነብስ ይማር! አምላክ ለቤተሰቡ መጽናናትን ይስጥ! ትግሉ ይቀጥላል!

አሁን ወደ ርዕሳችን ልግባ።

እንደምታውቁት ልክ እንደ ኦሮሞ ማሕበረሰብ 95% በሚያስብል ግምት ኦነግን እንደተከተለ ሁሉ በተመሳሳይነት ቁጥር ትግሬዎችም እንዲሁ 1928 . ጣሊያኖች ለኢትዮጵያዊያን ትተውልን የሄዱት የቀየሱትን የፋሺዝም ርዕዮትየአንጎል አጠባተጠቂዎች ተቀባዮች ናቸው። የትግራይን ሕዝብ ከኢትጵያዊነት ስነ ልቦና ለማላቀቅ ረዢም ጊዜ ተወስዶ በርካታ የአእምሮ ማጠቢያ ቴክኒኮችን (ዘፈኖችን፤ተውኔቶችን፤መጽሐፍቶችን፤ንግግሮችን…. ወዘተ) ተካሂደዋል። ለዚህ ሁሉ ተጠያቂቆቹ የተማሩት ከፍሎች ናቸው።

በሚገርመኝ ሁኔታ የፋሺሰት ተቃዋሚ ነን የሚሉ ሳይቀር ደደቢት በረሃ ውስጥ ወያኔ የመሰረተው የየካቲቱ 11/1967 . የኢትዮጵያን የባሕር ወደቦችን ለጠላት ለመስጠት እና ፋሺዝም ለማንገስ የተመሰረተው የትግል ቀንና ወር መከበር አለበት ለዚያ መስዋዕት የሆኑትን እና ለነመለስ ዜናዊ ጭምር የቆመው የመቀሌው ሃውልትም በክብር መያዝ አለበት እያሉየወያኔ ፖለቲካ ተቃዋሚ ነንእያሉ ነገር ግን የወያኔን “አርቲፋክት” (ቅርስ/አሻራ) የሚያከብሩ የፋሺዝም አሽቃባጮች ሳያፍሩ ዛሬም ችግሩ እንዲያብብ ድጋፍ እየሰጡ ነው።

በዚያ ወር እና አመተምህረት የትግራይ ብሔረተኞች የቀየሱትን ጸረ ኢትዮጵያ የሆነውየትግሬዎች የፋሺዝም ፖለቲካትግራይ በረሃ ውስጥ ለዚህ ርዕዮትመወለድና ማደግለሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ስቃይ መነሾ የሆኑት ህይወታቸውን የሰው የወያኔ ታጋዮች ከተሰውትም መሃል የሰው ልጅ በእሳትና በፈላ ውሃ እየለበለቡ ሲመረምሩ የነበሩ ሰው መሳይ አራዊቶችም እንደ ቅዱሳን መላዕክት እንዲታዩ በክብር እንዲነሱ እያደረጉ ነው። በዚህ አሳዛኝ ታሪክ በላንበት ወቅትየትግራይ ፋሺዝምበሰፊው ሕዝብ ሕሊና ተቀባይነት እንዲኖሮው የሙታን ድርሳኖችን፤ ግጥሞችን እና ማስታወሻዎችን በየትምህርት ቤቶች እና በዓላት በማሰራጨት ሰፊ የሕሊና አጠባ በመደረጉ ወያኔ እና የትግራይ ሕዝብ ባስተሳሰብ አንድ ናቸው ስል የነበረውን በምክንያት እንደነበር ለበርካታ አመታት ጽሁፎቼን የተከታተላችሁ አንባቢዎቼ የምታውቁት ታሪክ ነው።

እነሆ ዛሬ ምንም በማያውቁ የትግራይ ህጻናት እና ሌላ ቀርቶ አስነዋሪ በሚባል ስነምግባር በውሾችና በፈረሶችወገብላይሽጉጥእያስታጠቁ በኬሚካል የተቀመመ ቀለም የወያኔ ባንዴራ በእንሰሰታቹ ቆዳ ላይ በመቀባት በወታደራዊ የሙዚቃ ማርሽ እያጀቡ ፋሺስታዊ አይበገሬነታቸውን (Invincibility) በሕዝቡ ጭንቅላት እንዲቀረጽ በማድረግ የትግራይ ማሕበረሰብ በማይወጣው ስቃይ ውስጥ እንዲገባ አድርገውታል።

ቀደም ብየ በበርካታ ጽሁፎቼ እንደገለጽኩት ኤርትራኖች በተከተሉት የተሳሳተ የትግላቸው በመጨረሻ ያገኙት ትርፍ ቢኖርየረገሙዋትን ኢትዮጵያን ተመልሳ እንድታኖራቸው በስደት መልክ መለመንን፤ ውርደትን ስቃይን አካለ ስንኩልነት...” ነው። ለዚህ ሁሉ ውርደት ኢሳያስ አፈወርቂ ነው ቢሉም መጀመሪያ ተጠያቂዎቹ ማንም ሳይሆን ኤርትራኖች በራሳቸው ያመጡት ስቃይ ተጠያቂዎቹ እራሳቸው እንደሆኑት ሁሉበትግራይ ሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ስቃይም ተጠያቂው ወያኔና እንዲሁም 99% የትግራይ ምሁራኖች እና እራሱ የትግራይ ሕዝብ እንዲሁም የወያኔ ዲቃላውአብይ አሕመድእንደሆኑ ከሦስት ሳምንት በፊት በጻፍኩት ላይ መመልከት ይቻላል።

ኤርትራኖች 29 አመት በፊት ዘምባባ እና ከበሮ ይዘው እየዘለሉ ሲጨፍሩ የነበረውን የስካርና የትዕቢት መንፈስ ዛሬ እንዴት እንደበረደላቸውና ለስቃይ እንዴት እንደታደረጉ የታዘብነውን ያህል ትግሬዎችም የፋሺዝምን ምስረታ ያበሰረው የካቲት 11 በመጣ ቁጥር፤ ሕሊና ቢስ የኪነት ሰዎችን እየሰበሰቡ ሕዝቡን እያማለሉ ሲያስጨፍሩትትግራይ አሁን ላለቺው የሲኦል ህይወትእንደሚዳርጓት ስንናገር ነበር። እንዴት እንደሆነ እንመልከት።

 ኤርትራኖችበስካራቸው ዘመንጆሮአቸው መስማት እንዳቃታቸው ሁሉ እኔ እንደ ትግሬነቴ አሁን ያለው እየመጣ የነበረው አደጋ ስለታየኝ እየተጓዛችሁበት ያለውን አደገኛ ጉዞ ተሎ ካልገታችሁት በትግራይ ሕዝብ (በራሴ ዘመዶችም ጭምር) ላይ መራራ ህይወትን ያስከትላል ብየ ሳስጠነቅቅ ማንም ሰሚ አልነበረም። በሚገርም ሁኔታ አሁን ወያኔዎችተከበብንእያሉ ያሉትን ሁኔታ 4 መዓዝን ተከብብው መውጫ በር እንደሚያጡ በቃለ መጠይቄ ገልጬ ነበር። ወቅቱምሕገምንግሥታችን ከተነካ በየመንደራችን እንከፋፈላለን ወይንም ወደ ሌላ ሁለተኛ የጦርንት አዙሪት እንገባለንሲልስብሓት ነጋበተናገረበት ወቅት” (1997 ምርጫ ይመስለኛል አመተምህረቱን በትክክል ባላስተውሰውም) አበበ ሃይሉ በሚያዘጋጀው ሳንሆዘ ዩኒቨርሲቲ ራዲዮ ጣቢያ ላይ ስብሓት ነጋ በሰነዘረው የግንጠላ አማራጭ እንዳብራራ ቃለመጠይቅ አድርጎልኝ አሁን እየታየ ያለውበተለያዩ የጠላት ድምበሮች ተከብበናልእያሉት ያለውን ኡኡታ እንደሚከሰት ተንበየ ነበር። እነሆ ዛሬ ... ፋሺዝም ያስከተለው የሲኦል ህይወት ተጀምሯል።

በተደጋጋሚ እንደምታውቁት የትግራይ ምሁራን ራሳቸውን ለፋሺዝም አምልኮ ሸጠዋል። የወያኔ መሪዎች የትግራይ ምሁራንን በመያዝ ሕዝቡን በማሕበራት አደራጅቶ የሕዝቡን ሥነ-ልቦና ለራሱ በሚመች በመበዝበዝ በቁጥጥራቸው ሥር አድረገውታል። በቁጥጥር ስር ለማድረግ ዘገምተኛና ረቂቅ የትግራዋይነትኔትወርክበመዘርጋት ያከናወኑት ስልት የአእምሮ አጠባ የተከናወነበት የትግራይ ሕዝብ በፋሺዝም ትምህርት እንደታጠበ እንኳን ሕዝቡ እራሱ የተሸረበለት ሴራ አይገነዘበውም። ሌላ ቀርቶ በጣም ብሩህ በጣም ራሳቸውን የሚገነዘቡ ሰዎች የሚባሉት እንኳን በዚህ መሰሪ ወጥመድ ተይዘው ሊወድቁ ችለዋል፡፡ የወያኔ ፋሺቶች ያከናወኑት ተመሳሳይነቱለብ/ሞቅ ባለው/ ድሰት የተጣደቺዋን የእንቁራሪቷ ታሪክ የተሰማት ደስታ እና መጨረሻ ውሃው ቀስ እያለ እየፈላ እንዴት ጠብሶ እንዳቃጠላት ሁሉ፤ የትግራይ ሕዝብም በጭፈራ ጦዞ የትዕቢት ሐረጎችን ያዘሉ ዘፈኖችን እያመነዠከ ቀስ እያለ በቀበኞቹ ተንኮል እራሱን ለማቃጠል በቅቷል።

እኔ እንደምረዳው ለመፍትሄ አስቸጋሪ የሚያደርገው ነገር፡ ዛሬም እንደዚያ ችግር ውስጥ ገብቶ ለዕርዳታ የመጣለትን እህልአዳኞቼየሚላቸውን ወያኔዎች መንገድ ላይ ጠብቀው እህልና መድሃኒት የጫኑ መኪኖችን ሲያጋዩዋቸው እያየ ተቃውሞ ያለማሰማቱ የሚያስገነዝበን ነገር ቢኖር የትግራይ ሕዝብ የአንጎል አጣባው የተኮናወነው በወያኔ መሪዎች ምስል ስለተገነባ ወያኔን አስወግዶ በራሱ አስተሳሰብ መቆም እንደማይችል ስላሳመኑት በአሳዛኝ ሁኔታ ግማሽ ጎኑ ጭለማ ውስጥ እየገባ ነው። ከወያኔ አስተሳሰብ ተላቅቆ በእራሱ ምስል እንደገና ለመቆም የታጠበበትን ዘመን ያህል እንደገና ያን ያህል ብዙ አመታትን ይጠይቃል። እንደገባኝ ከሆነሕዝቡ እራሱን ትንሽ አድርጎወያኔንትልቅ አድርጎ እንዲያምን ተደርጓል።

ዛሬ በየሚዲያው የምናደምጣቸው የወያኔ ጀሌዎች የበለጠ ሰብዓዊነት የጎደለው ነገሮችን ሲያደርጉና እየዋሹ መሆናቸውን እያወቁም ቢሆን ለነገ የሚባል ጭንቅላት አልተፈጠረባቸውም፡፡ በሚገርም ሁኔታ የወያኔ አጃቢዎች ያልነበሩ አዳዲስ ጀሌዎች እየተከናወነ ባለው ጦርነት የወያኔ መሪዎች በሚያሳፍርና በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተማረኩ አይተው ምክንያቱ በማናውቀው ሁኔታየቡድኑ አካልሆነው የወያኔ ቱልቱላ አዳማቂዎች ሆነው የተቀላቀሉ ብዙ ሰዎችን ታዝበናል።

ወያኔ በደረሰበት ሽንፈት ምክንያት የወያኔ ሚዲያዎችአልሞትንምለማለት ፋሺዝም ማራኪ ለማድረግ የሚያሰራጩዋቸውን ምስሎችን ተመልከቱ። መሳጭና የብሔረተኞችን ልብ የሚያማልሉ ሙዚቃዎችን በማስደመጥ የተከታዮቻውን የልብ ምት ለማረጋጋት ሌት ተቀን እየጣሩ ነው። የዚህ ቀቢሰ ተስፋ ዓላማዓይነ ስውር ታዛዥነትንቀጣይነቱ እንዲኖሮው መግፋት ነው። ሆኖም የወያኔ ትግራይ ፋሺዝምየትግራይ ሕዝብ ዛሬም የሙጥኝ ካለወደ ማይወጣው የገሃነብ ህይወት በራሱ ፈቃድ እየገባ መሆኑን ግንዛቤ እንዲይዝና ውጭ አገር በምቾት እየኖሩ ያሉትየወያኔ ትግራይጀሌዎች አሁን እየነደደ ከሚታየው ከሚንቀለቀለው እሳት የራቁ ስለሆኑ ጦርነት ለነሱእንደ ኳስ ጨዋታአድርገው ጦርነቱ እያበረታቱት ስለሆነ፤ እራሳቸው ወደ ጦርነቱ መክተት ያልፈቀዱ ከነዚህየሃሰት ቡድኖችራሳችሁን እንድታርቁ ምክሬን እለግሳለሁ።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

No comments: