ከፊት ሆኖ ይምራን እኛ እንከተለው ሻለቃ ዳዊት እና ብርሃነመስቀል ነጋ የሰለሞን ተካልኝ ቅጂዎች
ጌታቸው ረዳ
2/18/26
Ethiopian Semay
በፎቶግራፍ ላይ የምታይዋቸው ሁለት ሰዎች ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ እና አምባሳደር ብርሃነመስቀል ነጋ ናቸው። ብርሃነመስቀልን አላውቃቸውም
(ማወቁን እንኳን ቀረብኝ!!!) ፤ ሻለቃ ዳዊት ግን በርካታ ሃገራዊ ስሕተቶች አንዳንዱም በባንዳነት ለሻዕቢያ ፐሮፓጋንዳ ድጋፍ
በሆነ መልኩ የተከራከሩ እና የጻፉ፤ ሲነሽጣቸውም በታሪክ የሚመዘገቡ መልካም ሰነዶችንና መጻሕፍቶችን ጽፈው ያበረከቱ ፤በዚህም ምክንያት በድጋፍም በተቃውሞም ብዙ መጣጥፎች የጻፍኩላቸው ታዋቂ
ምሁር ናቸው።
ሰላም እንደምን ሰነበታቸሁ!
በአጣዳፊ ሥራ ተወጥሬ ስለነበርና በወቀቱ አልመጣሁም። ዛሬ ስለ እነዚህ ሰዎች እና ሰለ የፋኖ
ዘረኛነትን እንመለከታለን።
በቅርቡ እነዚህ ሁለት ሰዎች እና ጀርመን ሃገር የሚኖሩት ልዑል አስፋወሰን አስራተ ካሳ ጋር
ሆነው፤ የጫካ ዱርየነት ባሕሪ በመከተል ወደ አስራ ምናምን ተበታተኖ እርስበርስ ሲታኮስ የነበረ የአማራ ፋኖ ታጣቂዎችን አንድ አድረገን
መጣንላችሁ ብለው በሚዲያ ሲጎረኑ ሰምተናቸዋል።
አሰገራሚ የሆነኝ ነገር «ንጹሃንን በመረሸንና በመግረፍ የታወቁ እነዚህ ግባ የማይባል
የፖለቲካ እና የሽምቅ ተዋጊነት ስልቶችና የፖሊሲ አወቃቀሮች የሚከተሉ ፥ በአብዛኛው በጎጃም ፋኖ መሪዎች የሚቦወዝ «የአማራ ፋኖ
ብሔራዊ ንቅናቄ/አፋብን/AFNM) የተባለው ታጣቂ ድርጅት ወርቅ ቀባበተው ፥ ሰማይ ሰቅለው ተፋላሚዎችን ለማስታረቅ በሰለጠኑበት
ሙያቸው ተመድበው በየዓለማቱ በተላኩበት የአስታራቂነት ሙያቸው እንዲህ
ያሉ ተፋላሚዎች ፈጽሞ ያላዩ እና በኢትዮጵያ ታሪክም እንዲህ ያሉ ምጡቃን ነፃ አውጪ መሪዎች ያላጋጠማቸው መሆናቸውን ከሰማየ ሰማያት
የተላኩ ሙሴዎች አስመስለው ሲያደንቋቸው ሰምቸ፤ “እንዲህ ያሉ የተማሩ
ሰዎች ወደ ትንሽነት የጎተታቸው ግፊት ምን ይሆን?” የሚል ጥያቄ ጭሮብኛል።
በነዚህ ሰዎች የተደነቁት በተለይ
«ያ ደም የጠማው አስርሰ ማረ የተባለ በብዙ ወንጀሎችና ንግግሮቹ በጥቁር መዝገብ የመዘገብኩት የሕሊና ቀውስ ያለው የሚያስመስለው
“አስረስ ማረ” የተባለው የዚህ ንቅናቄ የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ”
በሻለቃ ዳዊትና በአምባሳደር ብርሃነመስቀል ተደጋግሞ ሲሞገስ የሚነግረን ነገር ሁለቱም የዚህ የጎጃም ፋኖ አባሎች መሆናቸውን
ነጋሪ ነው። ለዚህ ማሳያም “ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ እራሳቸው «እነዚህ መሪዎቻችን» እያሉ ሲናገሩ ሰመተናቸዋል። ስለዚህም ሁለቱም አባሎች እንጂ ገለለተኛ ታዛቢዎች አለመሆናቸውን ነው እየነገሩን
ያሉት።
አስገራሚው ደግሞ ‘የፋኖ የመድረኩ ዋና አወያይ የጎጃሙ አስረስ ማረ መሆኑን ስንሰማ ስቀን ማለፉ የሚመረጥ ነው።
ታስታውሱ እንደሆነ የመጀመሪያው የፋኖ አንድነት ሙከራ ስንት ተንኮል ጎንጉነው ቢመጡም በመጨረሻ
ታላቁ እስክንድር ነጋ በድምጽ ሲበልጣቸው ፤ ዘመነ ካልመራ አንቀበልም ብለው ስብሰባው ሲበትኑት ታስታውሳላችሁ?
ከዚያ የተከተለው ግድያና ሰዶ -ማሳደድ ያሳዩን የጫካው እውነታዊ ቲያትራቸው የምታውቁት የትናንት ማታ ትዝታ ነው። አሁንስ
የአንድነት ተብየው ጉባኤ ማን ነበር መድረኩን ሲመራው የነበረው? አሁንም ያው ጎጃም ነበር (ደም የጠማው የዳዊትና የብረሃነ መስቀል
አርበኛ ‘’አስረስ ማረ’’)!!!
ለምን የመድረክ መሪነቱን ለመያዝ ፈለጉ? ያቺን የሚጋደሉላት የመሪነት ቦታ ለመያዝ ማለት ነዋ!! አሁን ፣በፖለቲካ ፥ በሕዝብ አደረጃጀት ፥ በጽናትና ሁሉንም በመታገስ ፥ በፖሊሲ አቀራረጽና ለሕዝብ መስዋዕት በመሆን ዓለም የመዘገበለትን ባለ ታላቅ ማሕደሩ ‘’ታላቁ እስክንድር ነጋ’’ ፈቅዶ ቦታውን ሲለቅላቸው እንደ ጅብ ተንግገተው መሪነቱን ያዙ። ከዚህስ በኋላስ?
ከዚህስ በኋላ የሚከሰተው ከደቡብ አፍሪካው ስምምነት ማግስት (ልክ በማገስቱ!!!) በወያነ
ካምፕና አመራር ውስጥ ምን እንደሚከሰት እንደተነበይኩትና እውነታ እንደሆነው ሁሉ ፤ በነዚህ ፋኖዎችም የመገዳደልና የመከፋፈል የመክዳትም
(የመሰለምም) ክስተት ጭምር የሚሆነውን በማስረጃ ለወደፊቱ አስነብባችኋለሁ።
ይህ ታጣቂ ቡደን ከመሪዎቹ ጀመሮ
እሰከ ተራ ተዋጊዎቹ በርካታ አከራሪ ብሔረተኞች «ሃይማኖት እና ነገድ ነክ አክራሪዎች» የተሰገሰጉበት ነው።
ሻለቃ ዳዊትም ይሁን ብርሃነመስቀል ነጋ መሪዎቻቸን ሲሉ የሚጠሯቸው ፋኖዎች ላንድ ዓላማ የወጡ ናቸው> ሲሉ
ሰምተናቸዋል። እንዲህ ከሆነ አመራሮች እርስ
በርስ ለምን ይገዳደሉ ነበር? ብለን ብንጠቃቸው መልስ አይኖራቸውም። ለዚህ መልስ የሰጠ አንድ ምስኪን ሰው ግና
አለ። እሱም ፤ ዳዊት እና በረሃነመስቀልን በማወያየት ጎጃሞቹ ከመረጡዋቸው የጎጃሞቹ (የፋኖዎቹ) ሚዲያ ቡድን “አማረ አሰፋ” የተባለ የጣና ቲ ቪ አባል ነው። እንዲህ ይላል፡
« የአማራ
ሕዝብ (ፋኖ) አንድ እንዳይሆን የተሰራበት መንገድ ስላለ ነው»
። የላል። ሰነፍ ሰው ጥፋት አለኝ አይልም፤ጣቱን የሚቀስረው ለስንፍናውና ለመውደቁ ምክንያት ሌላ አካል ነው ብሎ ያመካኛል።የፋኖ
ታጣቂ እርስ በርሱ የመገዳደሉ መስጢር አንድ እንዳንሆን ሰለተሰራብን
ነው፡ ይላሉ።
አንድ እንዳይሆኑም ይሁን ወንጀል ለመፈጸም የተሰራባቸው ክታብ እና የተሰራባቸው ድግምት ለማወቅና ለመፍታት ከጎጃሞቹ ባለይ የተሰወረ
ዕውቀት ይኖር ይሆን? ሕጻናትን መረሸን፤ መምሕራንን መረሽን ፥ የተያዘ ምርኮኛን ቅንድብ መላጨት ፥ ድሆች እናቶች ሲጋራ እና አረቄ እየሸጡ
ልጆቻቸው እንዳያስተምሩ ማገድ ፥ የተማረከውን ማዋከብና ማሸማቀቅ... ለምን እንዲያ ያለ ነውር እድትሰሩ የተሰራባችሁ
መንገድ ካወቃችሁት፤ በማን እንደተሰራባችሁ ለምን አትነገሩንም?
ይህ ሁሉ ግደል ተገዳደል ፤ይህ ሁሉ ዘረኛ ስድብ መሰዳደብ እስክንድር አማራ አይደለም ኢትዮጵያዊ ነው” ፥ «ግምባሩንና ቅንድቡን በለው»፤ የሚለው «የአስረስ ማረ» እና የመሰሎቹ ትዕዛዝ በመጨረሻው ለፍርድ ቀን ስትጠየቁ «ወንጀል እንድትሰሩ የተሰራባችህ ድግምት» ማስረዳት ትችላላችሁ?
መሪዎቻችን አንድ አድርገናቸዋል ብለው እነ ሻለቃ
ዳዊት ለሕዝብ ሲያውጁ ፤ በሚገርም ነገር እርስ-በርሳቸው ይገዳደሉ እንደነበር ቢያውቁም ያንን የመሪዎቻቸውን ወጀንጀል ለመደበቅ
ሲሉ በማደባበስ እንዲህ ፤ ለምሳሌ ሻለቃ ዳዊት እንዲህ ይላሉ፦
«አለ መነጋገርና አለመደማመጥ ነበር፡ መደማመጣና መነጋገር ሲያደርጉ “መፈትሔ አገኙለት” ፡
በማለት «መገዳደሉንና ዘረኛነትን እንደ ቀላል አይተውታል»፡
ሻለቃ ዳዊት ከታወቀ የአሜሪካ
ዩኒቨርሲቲ በከፈተኛ የሕግ ዲግሪ የተመረቁ የሕግ ምሁር ናቸው። “ሲገዳደሉት የነበረው የመገዳደል ወንጀልን” አለመደማመጥና አለመነጋገር ነበር”
ወደ ማለት የዳዳቸው እኝህ ምሁር ተራ የዕቁብ (የዕድር) ሰዎች ንትርክ አደርገው ሲያቀርቡት፤ የኛን የመታዘብ ብቃታችንን በንቀት መዝነውታል።
የሽምግልና እና የሰብአዊ መብት ነክ ልምድ ያለን አመባሳደሮች ነን እያሉ ሲጎረኑበት የነበረው
ልምዳቸው ፋኖ ላይ ሲደርሱ ተፈትነው ወደቀዋል። አስገራሚው ደግሞ ገለልተኞች ነን ይሉና ሰከንድ ሳይርቁ “እነዚህ መሪዎቻቸን” እያሉ በጫካ
አጉራ ዘለልነታቸው እና በአክራሪነታቸው የምናውቃቸው የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ምጥቀት የጎደላቸው የፋኖ መሪዎችን መሪዎቻችን ሲሉ ይደመጣሉ።
ያንን ሲያጠናክሩትም «እነዚህ መሪዎቻችን ታላቅዋን ኢትዮጵያ ወደ ከፍታ የወስዷታል፤ አዲሰ አበባም ያስገቡናል” እያሉ ሳይሸማቀቁ
ይነግሩናል።
እገሌ አማራ እገሌ ደግሞ ኢትዮጵያዊ የሚሉ ኢትዮጵያዊን የሚያጥላሉ የፋኖ ኢንተርሃሙዌ ታጣቂ መሪዎችን ‘መሪዎቻችን’ እያሉ በማሞካሸት የወደቁበት
የፍቅር ጥልቀት “በብሔረተኝነት መለከፋቸው ማሳያ ነው”።
ብሔረተኝነት ከፉ ፍቅር ነው። አንዴም ይሁን ተደጋጋሚ ፍቅር ያልያዘው ሰው መቸም የለም (መናልባት
ጠቂቶች)፤ ፍቅር ስሜትን ከቁጥጥር ውጭ አድርጎ የሕሊና እና የነርቭ የሕዋሳት መቀያየርን የሚያስከትል ነው። ፍቅር ብዙ ገጽታ አለው።
የሰው ፍቅር፤ የንብረት ፍቅር ፥ ለራስ ፍቅር የሃይማኖት እና የፖለቲካ ፍቅር ወዘተ... ፍቅሮች አሉ።
ሰዎች በፖለቲካ ፍቅር በፖለቲካ ታዛዥነት (ለመሪዎች ያላቸው ፍቅር) Politics
Obedience” ሲወድቁ ራሳቸውን እስከመሰዋት እና ማስገመት ይደርሳሉ።
ራሳቸውን ያስገመቱ በቅርቡ “በአናርኮ ፋሺቱ ፋኖ” ፍቅር የወደቁ ሰዎችን አይተናል። ብዙዎቹ
ውጭ አገር የሚኖሩ “በጣም ጥቂት የአማራ ” ምሁራን ናቸው።
ፋኖ የተባለው “አክራሪ በሔረተኛ” የሚመሩት ሰዎች ደም በጠማቸው ብዙዎቹ ኤርትራ ውስጥ የአንዳርጋቸው እና የብርሃኑ ነጋ ጭፍራ የነበሩ ታጣቂዎች ናቸው።
ይህንን ታጣቂ የሚመሩት ዓድዋዎች ወያነን ሲመሩት እንደነበሩት ሁሉ ፋኖንን የሚመሩትም በዙዎቹ ጎጃሜዎች ናቸው። ይህንን ድርጅት በቀዳሚነት
የሚያንቀሳቅሱትና ግምባር የሚታዩት ጎጃሜ ግለሰቦችን እንጥቀስ ቢባል አንደኛው፤ አስረስ ማረ” የተባለው የሰው ነፃነትን
የሚጋፋ ፥ የያስረሸናቸው ደም የሚያክለፈልፈው ፥ ዘረኛ ፥ በጣም ናርሲትና ትዕቢተኛው አስረስ ማረ ሲሆን፤ አብሮት የበላዩ
የሆነው «የነጋሽ እና የአንጋሽ ዘር የሆንኩኝ ፥ ከእናቴ ማሕጸን ሆኜ ያገኝሁትን የታላላቅ ሕለመኞች ልጅ የሆንኩኝ ፥ በታሪክና
በዲኤንኤ የተላለፈልኝን ሕልሜን «እስክንድር ነጋ ሕልሜን ነጠቀው»
እያለ በሚዲያ በግልጽ ለሥልጣን ሲቃዥ የነበረበትን ሕልሙን ተሳከቶለት የበላይ ሆኖ የወጣው ዘመነ ካሴ የተባለው የሥልጣን ቅዠታም
የፋኖ ታጣቂዎችን በመሪነት የሚመራ እና የመሳሰሉ ታዛዦቹ የሚመሩት ድርጅት ነው።
እነዚህ ደግሞ ለፍትሕ የቆሙ
ሳይሆኑ ጸረ ፍትሕ የሆኑ፤ ትችት የማይፈቅዱ የጫካ አጉራ ዘለል የሆኑ፤
ተራ ዝርፍያ ውስጥ የገቡ ድብደባ (ቶርቸር) ፤የባንክ ዝርፍያ የሚያካሂዱ፥ ሕጻናትን ተመራዎችን እና የመምህራንን ግድያ ትዕዛዝ
የሰጡ አክራሪ ብሄሔረተኝነት እና ወንጀል መስራትን የሚደፍሩ ናቸው።
በሚገርም ነገር ከላይ ከተጠቀሱት የሻለቃ ዳዊት እና የብርሃነመስቀል ነጋ “መሪዎች” ከሆኑት “እስክንድር ኢትዮጵያዊ እንጂ አማራ አይደለም” ከሚሉት በተጨማሪ የፋኖ መሪዎች አንዱ ድሮ የወያኔ ባሕላዊ ጄነራል የነበረ «ተፈራ ማሞ» የተባለው በቅርቡ በዙዎቻችንን ያስደነገጠ ዘረኛ አዋጅ አውጇል።
ተፈራ አስገራሚ ሰው ነው። በቅጽል
ስሟ “መነን ሃይለ” እያለች ራሰዋን የምትጠራ ወሎየዋ ሚስቱ ወደ ኤርትራ እየተመላለሰች ከሻዕቢያ መሪዎች ጋር ፎቶ እየተነሳች
እኛን
ትግሬዎችን “ቅማላም፤አጋሜ” እያለች የሻዕቢያ ተልዕኮ ለማስፈጸም <<የትግራይ ሕዝብ በሙሉ ከወሎ ተጠራርገው ወደ አገራቸው ወደ ትግራይ ይባረሩ>> እያለች “ኢንተርሃሙዌዊ የዘር
ቅስቀሳ” ማድረግዋን እየገረመን አሁን ደግሞ ተፈራ ማሞ እራሱ የአማራ ስም በያዝን ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊቶች ላይ የሚያስደነግጥ
ዘረኛ አዋጅ አውጆብናል።
«የአማራ
ሥም የያዙ አማራ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን የአማራ
ስም መጠቀም ማቆም አለባቸው»
ሲል አውጇል።
የነ ሻለቃ ዳዊት እና የነ በርሃነመስቀል ነጋ መሪዎች አንዱ የሆነው ተፈራ ማሞ
እየነገረን ያለው ‘’የፋኖ ዋና ተልዕኮ አማራ ያልሆኑ
የአማራ ስም የወሰዱ ሁሉ ክእንግዲህ ወዲህ እንዳይጠሩበትና በልዋጭ በየነገዳቸው ስም እንዲጠሩ ለማስገደድ “ፋኖ” በትጋት እንደሚሰራ
ነው ከወዲሁ እየነገረን ያለው”።
እነዚህ የእነ ዳዊት መሪዎች ናቸው።ይህንን ዘረኛ ቅስቀሳም ለታጣቂ ሰልጣኞችና እሱ ለሚያዋጋቸው
ታጣቂዎቹ እንዲሁም ለአማራ ሕዝብ ይህንን ዘረኛ ፖሊሲው እያስተማረ ነው።
ይህንን አዋጅ በተፈራ
ማሞ በኩል እንዲነገር የተደረገው ዘረኛ ቅስቀሳ በፋኖ አማራር እውቅና
የተደረገ ነው።
እውቅና ባይኖሮው
ኖሮ ድርጅቱ ተሎ ብሎ በማውገዝና ተፈራን ከሥልጣኑ በማውረድ ድርጀቱ “የኢትዮጰያን ሕዝብ ይቅርታ መጠይቅ ነበረበት»
፤ ሆኖም
በድርጅቱ ፖሊሲ እውቅና ስለተነገረ ፤ እሰካሁን ድረስ ምንም ያሉት የለም።
የፋኖ ደጋፊዎች ያልሆኑ
የአማራ ምሁራንም ዝምታን መርጠዋል።
ይህ ዘረኝነት ወያኔዎችም ትግራይ ውስጥ የአማራ ስም የያዙ የትግራይ ተወላጆች እና በአማርኛ
ስም ያላቸው ንግድ ቤቶች ወደ ትግርኛ እንዲለወጥ በድምጺ ወያነ ራዲዮ እና በትግርኛ ቋንቋ ምሁራን (ሁለት የዩኒቨርሲቲ መምህራን)
በኩል ሲነጋገሩበት እንደነበር እና ለሕዝቡ የስልክ ጥሪ መነጋገሪያ መድረክ ክፍት ተደረጎ ውይይት ሲደረግ መቀሌ ከተማ የትግራይ ከተማ ሳትሆን የአማራዎች ከተማ ሰለመሰለች የአማራ ስም ያላቸው እና ኗሪዎችዋ የሚንነጋገሩበት ትግርኛም አማርኛ
የተቀላቀለበት «ዲቃላ-ትግርኛ» በመሆኑ ትኩረት እንዲደረግበት ሲያሳስቡ እንደነበር ካሁን በፊት አንድ
መጣጥፍ አቅርቤ በድረገጾች ተለጥፎ እንደነበር አስታውሳለሁ።
ተፈራ ማሞም ዕድሜውን ሙሉ ወያነ ያስተማረቺውን የጥላቻ ትምሕርት
ፋኖ ውስጥ ይዞት ስለገባ «አማራ ያልሆነ ሰው የአማራ
ስም መጠቀም የለበትም» ማለቱ በናዚ ጀርመን ዘመንም በደም
የአርያን/ኖርዲክ/ ጀርመን ደም ያልሆኑ ሰዎች የቤተሰብ እና የግል
ስሞችን የመቀየር ሕግ 1939-1938 ውስጥ ወጥቶ ነበር።
የቤተሰብ እና የግል ስሞች መቀየር ሕግ ላይ ያለው አስፈፃሚ ትዕዛዝ የሚያሳየው "አይሁድ ያልሆኑ" የጀርመን ስም ያላቸው አይሁዶች ከእውነተኞቹ የደም ጥራት ካላቸው ጀርመኖች ለመለየት ሲባል ተጨማሪ ስም እንዲይዙ በማስገደድ "እስራኤል" ለወንዶች እና "ሳራ" የሚለው ስም ለሴቶች እንዲሰጥ ሆኗል።
ሁሉም የአይሁድ ፓስፖርቶች "J" በሚለው ቀይ
ፊደል ታትሞባቸዋል።
በዚህ መልክ የፋኖዎቹ የነ ተፋራ
ስማችን ተጠቀማችሁ የሚለው ስሞታና ሰበብ ከናዚዎች ፖሊሲ ጋር ሰናስተያየው የናዚ መሪዎች የጦርነት ዝግጅታቸውን ሲያፋጥኑ፣
በጀርመን እና በኦስትሪያ ፀረ-ሴማዊ ሕግ በአይሁዶች ላይ የበለጠ ሥር ነቀል ስደት እንዲፈጠር መንገድ ጠርጓል።
የሕጉ ዓላማ የጀርመን አይሁዶች በግልጽ እንዲታወቁ ማድረግ እና ከጀርመን ኮሚኒቲ (ሕዝባዊ
ማሕበር) መለየት ነበር።
በተመሳሳይ
መልኩ በፋኖ መሪዎች ናዚያዊ ንግግር መሰረት «እስክንድር ኢትዮጵያዊ እንጂ አማራ አይደለም» «አማራ
ያልሆኑ በአማርኛ ስም የሚጠሩ ሰዎች ስማቸው ይለውጡ” ሐጎስ፤ ፣ ነመራ፤ ኦባንግ ኔቶ፤ ታዲዮስ፤ ታንቱ ......ወዘተ (የሴቶች ስምም ሓዳስ..... ወዘተ በየነገዳችሁ ጨምሩበት)የሚል በመታወቂያ ስማችን ላይ ይጠቀስ ብሎ «ፋኖ አዲሰ አበባ ገብቶ 4 ኪሎ ሲቆጣጠር፤ በሚደነግገው ሕገ-መንግሥት ላይ ናዚዎች “ጀይ/J/” የሚል ፊደል በአይሁዶቹ መለያ ካርድ እንዳተሙበት ሁሉ
“አ” የሚለው ፊደል እንዲሁ ለጠሩ ለነጠሩ አማራዎች ሲሆን “ኢ” የሚል ፊደል ደግሞ አማራ ላልሆኑ ወይም “ዘርን ላደፈረሱ”
(ለተዳቀሉ) ኢትዮጵያዊያን በመታወቂያ ካርዳችን እንደሚያሰፍሩበት
ከወዲሁ መገመት ይቻላል።
ምክንያቱም
ይህንን የተፈራ አዋጅ በይፋ ድረጅቱ አላዋገዘውምና ይህንን አዋጅ እውን ያደርገዋል ብየ በድፍረት እከራከራለሁ።
በዲያስፖራ የሚኖሩ የዚህ ድርጅት (ሃርድ ኮር ደጋፊ) የሆኑ በጣት የሚቆጠሩ ሄደውም መጥተውም የማይጠቅሙ የአማራ መሁራን ተብየዎቹ እና በዘረኝነት እየጨቀዩ ያሉት መሪዎቻቸው (ፋኖዎች) እና የነሱ ቱልቱላ ሚዲያዎቻቸው ከነዚህም አብረው በየቲክታክ መስኮቶች ተቸከለው ይህንን ዘረኝነት ወደ አየር የሚያስተጋቡ መንጋዎቻቸው ከወያነ ውድቀት ማግስት የተከሰቱ አዳዲስ ዘረኞች ናቸው።
የአማራ ስም የኔ እንጂ የማንም ኢትዮጵያዊም ይሁን ኢትዮጵያ
ያደገ ፈረንጅ ሊጠቀምበት አይፈቀድም <<አምሐራ ስም ለአማራ ብቻ>> የሚል አደገኛ ቅስቀሳ በምሁራን ዘንድ ትኩረት ሳይደረግበት ማየት ወያነና ኦነጎች በአማራዎች ላይ ያደረሱት ግፍ የአማርኛ ስም በያዝን በኢትዮጵያዊያትና ኢትዮጱያዊያን ላይ እየተዘመተብን ያለው ይህ የፋኖዎች
ዘመቻ በቀላሉ እየታለፈ ቢሆንም ለወደፊቱ እግር እየተከለ ስለሚሄድ ስጋት የሚጭር ንግግር ነው።
እነኚህ የፋኖ መሪዎችና ተከታዮቻቸው ካንደበታቸው የሚያሰራጩት መልዕክት እውቁ ኢትዮጵያዊው “የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን” ንግግር አስታወሰኝ።
እንዲህ ይላል፡
<<ሐይቅ ዳር ተሰብስበው እንቁራሪቶቹ አብዝተው ስለጮሁ ሐይቁ የእንቁራሪቶች ነው ማለት አይደለም። ለክብራቸው ሲሉ ዝም ያሉ ብዙ ዓሳዎች ሐይቁ ውስጥ አሉ>>
ይላሉ።
የነ ሻለቃ ዳዊት መሪዎች እገሌ ኢትዮጵያዊ እንጂ አማራ አየደለም ፥ የአማራ ስም የያዙ አማራ
ያልሆኑ ሰዎች ስማችንን አስረክበው በራሳቸው ስምና አገር ይጠቀሙ ወደ እሚል ጭራሽ ወደ ዕብደት የደረሱ የፋኖ መሪዎችን ስንመለከት ነብሱን ይማረው የዶ/ር ደረጀ
አባባል ነው ዓይኔ ላይ ድቅን ያለው። እንዲህ ብሎ ነበር፦
<<የአማራ ብሔረተኛነት ድግሞ ጭራሽ ወደ ዕብደት የደረሰ ነው -Almost ወደ
near madness የደረሰ ነው» አሁን የአማራ ናሺናሊዝም የሚባል የለም ነው የምለው >> << ከኖረ ግን
እግዚአብሔር አይቅናው ቀንቶት ሥልጣን ከያዘ የአማራ ናሺናሊዝም የሂትለርን የሚመስለው ፋሺዝም ነው እዚች ሃገር የሚያሰፍነው!>>
ብሎ ነበር፡ ነብስ ይማር ኢትዮጰያዊው ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ። አሁን ያንን የተነበየውን ትንቢት እውን ሆነ።
የነ ሻለቃ ዳዊት እና የነብርሃነመስቀል መሪዎች ዕበደትና ዘረኛነት በተጠቀሱት መሪዎች ብቻም
አልተወሰነም። እሰላምና አማራ አበረው ቁርስ መካፈልም ይሁን ሥልጣን ላይ እስላም
መውጣት የለበትም የሚሉ እንደ እነ መሳፍንት ተስፉ የመሳሰሉ በጎንደር የፋኖ መሪዎችም ለድርጅቱ ዘረኛነት ማዳበሪያዎች ናቸው።
ሻለቃ ዳዊትና አምባሳደር በርሃነመስቀል
ነጋ እነዚህን የፋኖ መሪዎችን “መሪዎቻችን” እያሉ በአድናቆት ሲፈነድቁና በእንዲህ ያለ መሃይምነት ሲቸነከሩ ማየት ይገርማል።
ሻለቃ ዳዊት ከደስታቸው ብዛት
«ታላቋን ኢትዮጵያ ማስወለድ የሚችሉ በይዘት የተለዩ፥ እንደዚህ ያለ የተለየ ውይይት ተሳትፌ እና መስክሬ አላውቅም አልሰማሁም ። መጨረሻም ዕምባ ነው የተናነቀኝ፡....» ሲሉ በረሃነመስቀል ነጋም እንዲሁ ያለ ማፈር እነዚህን አዳዲስ ናዚዎች ሲያቆለጳጵሱ መስማት እኛን ኢትዮጵያዊያኖችንም ይሁን እግዚአብሔርን አልፈሩም። እዚህ ላይ ያስታወሰኝ ነገር አሁንም የጦቢያው ጸሐፊ ሙሉጌ ሉሌን ነው።
ጸሐፊው እንዲህ ይላሉ፤
‘አቤቱ የሚፈሩት ስጣቸው!’ « እግዚአብሔር ኢትዮጵያ አይደለም። እኛም ብንሆን ኢትዮጵያን አይደለንም። ወደ ትግሬነት፣ ወደ አማራነት፥ ከምባታነት፥ ሐዲያነት፥ ኦሮሞነት፥ ወዘተ፤ ተሸሽነናል። 80 ቤቶች ስርተናል። ኢትዮጵያዊነት የሚባል ነገር የሌለና ያልነበረ መሆኑ በሚነገርበት አገር ፤ እግዚአብሔር ብቻውን ኢትዮጵያዊ ሊሆን ነው? ወይስ ከክፍፍሉ (ከጎሳዎቹ) የትኛውን ይምረጥ?» ብለው ነበር።
ታዲያ «ከፊት ሆኖ ይምራን እኛ እንከተለው» እያሉን ያሉት “የሰለሞን ተካልኝ ቅጂዎቹ እነ ሻለቃ ዳዊት እና አምባሳደር ብርሃነመስቀል ነጋ ሁሉም እየወጣ የፈለገውን ዘረኛ ንግግር እንዲናገር የሚፈቅድ በሥርዓት የማይመራ ከዚህ ታጣቂ ቡድን ጋር የሚያቁነጠንጥ “እፍ ፥ እፍ ፍቅር!” የያዛቸው እነዚህ ሰዎች
«እልፍ አእላፍ ኢትዮጰያዊ ይህችን አገር ተመልሶ ላለማየትና እየተፈጠመ -ቃል እየገባ- ሲወጣ እግዚአብሔር ኢትዮጰያዊ የሚሆንበት ምን ምክንያት፤ ምንስ ግዴታ አለበት? ታላቁን ጌታ ክእነ መለስና ከነ ነጋሶ ጋር በአንድ አገር የኖር ዘንድ እንፍረድበት?» እንዳሉት ታላቁ ጸሐፊ፥
ታላቁን ጌታና ታላቁ የአማራ ሕዝብ ከነዚህ መንፈሳዊ ባዶነትና የሕሊና እራቁትነት ከተጠናወታቸው
ከአዳዲሶቹ የፋኖ ዘረኞች ክእነ አስረስ ማረ እና ከነ ተፈራ ማሞ ባንድ አገር ይኖሩ ዘንድ እንፍረድበት?እንዴትስ በዚህ የዘረኛነታቸው
ባሕሪ ሕዝቡን እንዲመሩት እንፈቅዳለን?
ሰላም እንስንብት
ጌታቸው ረዳ

No comments:
Post a Comment